#ተረጅልኝ ግጥሜን
………………………………
…………ልክ እኮ ነው ያልሽው፡
ግጥሜ ሀዘንን እንጅ…
ደስታን አይነግርሽም፡
አይኔ አለቀሰ እንጅ…
ጥርሴ ሳቀ አይልሽም፡
መጎዳቴን እንጅ…
ባንች መደሰቴን አያሳውቅሽም፡
፩ነቴን እንጅ…
ሠው እንዳለኝ ጭራሽ…እንድታምኝ አይሻም፡
ግን……አትናደጅብኝ ተረጅልኝ ግጥሜን፡
ቢከብደኝ ጊዜ እንጅ…
ብዕር አስነብቸ…ለመንገር ደስታየን፡
ብፈልግማ ኮ……
የሳቅሁትን ሳይሆን ልስቅ ያሠብኩትን፡
ውስጤ ጭንቁን ትቶ የልቤ ሀሴቱን፡
ቅሬታውን ረስቶ ባንች መደሰቱን፡
ይነግርሽ ነበረ…………
ግን……እባክሽን ውዴ ተረጅልኝ ግጥሜን፡
ከዘመኑ ሠው ጋ…እንባ ከሚያስቀው፡
መሀረብን ነፍጎ…ከንፈር ከሚመጠው፡
ያንተ መውደቅ ለኔ ከሚል መነሻ ነው፡
ሊመደብ አይሻም ሊያጣ ህሊናውን፡
በብእሩ ዕንባ…ሊነግርሽ ደስታውን።
✍#ተፃፈ_በዳዊት_ሠለሞን
@getem
@getem
@gebriel_19
………………………………
…………ልክ እኮ ነው ያልሽው፡
ግጥሜ ሀዘንን እንጅ…
ደስታን አይነግርሽም፡
አይኔ አለቀሰ እንጅ…
ጥርሴ ሳቀ አይልሽም፡
መጎዳቴን እንጅ…
ባንች መደሰቴን አያሳውቅሽም፡
፩ነቴን እንጅ…
ሠው እንዳለኝ ጭራሽ…እንድታምኝ አይሻም፡
ግን……አትናደጅብኝ ተረጅልኝ ግጥሜን፡
ቢከብደኝ ጊዜ እንጅ…
ብዕር አስነብቸ…ለመንገር ደስታየን፡
ብፈልግማ ኮ……
የሳቅሁትን ሳይሆን ልስቅ ያሠብኩትን፡
ውስጤ ጭንቁን ትቶ የልቤ ሀሴቱን፡
ቅሬታውን ረስቶ ባንች መደሰቱን፡
ይነግርሽ ነበረ…………
ግን……እባክሽን ውዴ ተረጅልኝ ግጥሜን፡
ከዘመኑ ሠው ጋ…እንባ ከሚያስቀው፡
መሀረብን ነፍጎ…ከንፈር ከሚመጠው፡
ያንተ መውደቅ ለኔ ከሚል መነሻ ነው፡
ሊመደብ አይሻም ሊያጣ ህሊናውን፡
በብእሩ ዕንባ…ሊነግርሽ ደስታውን።
✍#ተፃፈ_በዳዊት_ሠለሞን
@getem
@getem
@gebriel_19
👍1