ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
# አለመታደል

እምዬ ኢትዮጵያ
ቡቃያሽን ለማየት
እርሻሽ ላይ ብትዘሪ፣
ልክ እንደ ዶሮ
ዘርሽን የሚለቅም
አያጣሽም....ጫሪ !!!

# ሀብታሙ_ወዳጅ
@getem
@getem
@yeyhudaanbesa
****ፍፃሜዉ****(ሳሙኤል አዳነ)

የሚሽከረከሩ አለምን በገንዘብ
አድምቀው ያበዙ ተፈጥሮን በጥበብ ፣
-
ያገር ተወካዮች የአለማት መሪ ፣
ጎዳና የሚኖር በልቶ ፍርፋሪ ፣
-
ኑሮ ያቆሰለው ያገር ወንደላጤ፣
የተጎሳቆለ ምስኪን የኔ ቢጤ ፣
-
ጠቢብ ስአሊያን ድንቅ ሙዚቀኛ ፣
ሽጋ መልከ መልካም ታዋቂ ዝነኛ ፣
-
የኔ አይነት አመዳም ባሪያ መልከ ጥፉ ፣
እውቅ ባለሀብቶች
ሚሊዮን ተርቦ ቢሊዮን ያቀፉ ፣
አንቱ የተባሉ በስም የገዘፉ ፣
ይኖራሉ በአለም እንዲህ ተለያይተው ፣
ምድርና ሰማይ ቤታቸውን ሰርተው ።
-
ይሄ ሁሉ አዳም አንድ ሆኖ ደሙ ፣
ስጋው አፈር ሲለብስ
ሲለይ ከአለሙ ፣
መአረጉ ቀርቶ
ሁሉም በአንድ ላይ ሬሳ ነው ስሙ ።

11/10/08
6፡00 am
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ

@getem
@getem
@Gebriel_19
የጨለማ ጥግ
(ልዑል ሀይሌ)

ተስፋ አትስጪኝ ንጋቴ
መጨለም መምሸቱ ካልቀረ
ውሰጂው የነገ ጥጋቴን
በልብሽ መደብ ያደረ
ዘመናት ባደረ ተስፋ
እንድቋደስሽም አልሻ
አንቅሬ ተፋሁሽ ንጋቴ
ዳግም ሄድኩኝ በጨለማ
ዳግመኛ ታመምኩ በግርሻ
..
ይመስገነው!
ካንቺ አርቆ ከጨለማ ላዛመደኝ
ይመስገነው!
ካንቺ ሽሽት ወደ ወህኒ ላወረደኝ
ላመስግነው ተንበርክኬ
ለዚህ ላበቃኝ ፈጣሪ
ጨለማውን ባይፈጥርልኝ
ምን ይሆን ነበር እጣዬ
ንጋቴ ክደሺኝ ስትቀሪ

፲፯-፪-፳፻፲፩

@getem
@getem
@lula_al_greeko
👍1
ሀገሬ2

የሀዘን ከረጢት የእንባ ስልቻ
ታስሮባት የኖረች በእድሜ መቀነቻ

ያላረገ ፀሎት
ያልተሰማ ምልጃ
ስትኖር ተሸክማ
የእርግማን ፍርጃ


ከጊዜ በኋላ
ቀድማ የጠበቀችው ውለታ ቢስ አለም
ምን ክብሯን ቢጋፋ
ሁሉም ይቀየራል ብላ ብታስብም
ቢኖራትም ተስፋ
በዘመናት እንባ አይኗ ብቻ ጠፋ

ምን ያህል ጥላሁን

@getem
@getem
@gebriel_19
[ሰውነቷ]
.
.
ሽፋሽፍቷ
በነግህ ጮራ ተገርፎ
ፀዳሉ ከዓይኖቿ ተርፎ
ፊቴን ሲዳስስ ነቃሁ
የታጨደ ደምግባቷን
በንጋት በ'ሮቼ ወቃሁ።
ገለባዋ
እየረገፈ ከጀርባዋ
ገሚሱ ሽቅብ ያርጋል
ገሚሱ ወለል ይረጋል።
ከነቃች
ብትቆይም ጥቂት ደቂቃ
ጀንበር ሽፋሽፍቶቿን፥ መግረፉን እስኪያበቃ
የደረሰ ክምር ሰብሏ፥ በበ'ሮቼ እስኪወቃ
ዘረጋች እንጂ እጆቿን
አልገለጠችም ዓይኖቿን።
ያ'ፏን ማድመጥ አልሻም
አውቃለሁ ያ'ካሏን ቋንቋ
ሃዘኗ አይን አይፈልግም
ጥርስ አይናፍቅም ሳቋ።
ዘር ማየት ነው ያ'ይን ጥቅሙ
ደም ይቆጥራል አፍም ባቅሙ
ትተኛልኝ አፏ ይረፍ፥
ትተኛልኝ አፏን ትዝጋ፥
ትተኛልኝ ደስ ይለኛል
ሳይገለጥ የዳሰሰኝ፥
ሳትነቃ የማዋራው፥
[ሰውነቷ] ይሻለኛል።

@paappii
@getem

#rediet aseffa
👍1
< ሲገባኝ.....>

ቀንይታገሳታል
ፍቅሬ ያሳሳታል
በዚም ጋር ከፍቷታል
ፍቅሬ ተጨንቃለች
የሀሳብ ዳር አታለች


እኔም አስባለው
መኖርአብሮ መሆን
መኖር መለያየት
እዳልሆነ አውቃለው

መሳሳብ ነው እንጂ በደም መወዳጀት
መጣጣም ነው እንጂ በፍቅር መጃጀት

መራራብ ነው እንጂ በሰሀት ልዮነት
እንጂ መኖር ማለት
አይደል አብሮመሆን
አይደልመለያየት፡፡


ፀሀፈ..ልጅ ኤቢ(አብርሀም)

getem
getem

@artbekiyechalal
1
~ነግ በኔ...~
===//===

ጊዜ ምፀተኛው~ይመሻል ይነጋል
ጊዜ ጉልበታሙ~ይመጣል ይሄዳል
ቀን አየሰፈረ~ቀን እየቆጠረ~ያነሳል ይጥላል

@getem
@paappii
# ብርሀኔ
ማለዳ ሰግጄ
ወገግታ ከፀሀይ ፣ ፈፅሞ አለመንኩም
ከጨረቃም ጉያ
የብድር ጨረሯን ፣ አልተለማመጥኩም።
ግና..
ጨረቃ እና ፀሀይ
ዝምታዬን አይተው ፣ በቀኔ ሊያሾፉ
የጨለማ ባሪያ
የሚል ስም ሰጥተውኝ ፣ ባጠገብሽ ሲያልፉ
የንጋቴን ንጋት
አይንሽ አዮና ፣ ተሸማቀው ጠፉ።
<<ሚኪያስ ሚሊዮን ሽፈራው>>
@getem
@yeyhudaanbesa
​​ዛሬም ሼ መንደፈር!!!!!

በነ ያሬድ ቅኔ፣ በነ ቢላል ቀለም፣
በጦቢያ ምድር ላይ፣ በደጋጎቹ አለም፣
አንድ ነው ሃበሻ፣ አንድ ነው ዘላለም፣
አትጠራጠሩ፣
እስከመጨረሻው የሚለየው የለም።



ሌላ ሼ መንደፈር!!!!


በስመአብ ቢስሚላሂ፤ ቢለያይ ቋንቋቸው፤
ፈጣሪ በሰማይ፤ አንድ ላይ ሰማቸው።


(( የዛሬ 70 አመት ግድም ሸገር አዲስ አበባ ፤ አራዳ
ጊዮርጊስ፤ ሙስሊምና ክርስቲያን ወገኖች ስለ ሰላም
ባንድ ላይ እየፀለዩ ሳለ))

እንግዲህ ዛሬም ከመቼውም ጊዜ በላይ ሀገራችን ፀሎት የሚያስፈልግባት ጊዜ ነው......ክርስቲያኖችም ሙስሊሞችም ለሀገራችን ፀሎት እናድርግ !!
ዛሬ ኢትዮጵያ ክርስቲያኑም ሙስሊሙም በነጭ ልብሱ ተውቦ ሚገማሸርበት ቀን ነው....ተመስገን እንኳን ኢትዮጵያዊ ሆንኩኝ...

((( ጃ ኖ ))💚💛❤️


ሸጋ ጁምኣ!!!!💚💛❤️

መልካም የጥምቀት በዓል ይሁንላቹ! !!!!💚💛❤️

@balmbaras
@getem
@getem
…ይሉኛል…
:
ይሉኛል አበደ
በ'ራሱ ቀለደ
:
ይሉኛል ፈላስፋ
ከ'ራሱ የጠፋ
:
ይሉኛል ዝርክርክ
ማማር የማይፈልግ
:
ይሉኛል ይሉኛል
እኔ'ን ሰው መሮኛል
ሰው እኔ'ን ናፍቆኛል።
:
(እኔን እኔን አትበሉኝ!!)
፱-፬-፳፻፲፩
@getem
@getem
@gebreil_19
👍1
ንጋት....
"ንጋት" ማለት ምንድን ነው? የአዋፉቱ እልልታ?
የመኪና ትርምስ የሰልፈኛ ህዝብ ጋጋታ?
የእረኞቹ ፉጨት ፣ የኮረዳ ሴት እስክስታ?
ነጋ ማለት ይሄ ነው ...?
አይደለም !
ነጋ ማለት ፣ ንጋት ይሉት ቋንቋው ይህ አይደለም
ያንተ እውነት ያንቺ መተት በእኔ ልብ ውስጥ እንዲጨልም
ነጋ ሲባል ይህ አይደለም!

ቅቤ አያልም ጮራ እረፋድ 'ሚያደርቃት
ጠብታ ሚያፈካት ንጋት ማለት ቅጠል ናት
ወይ ደግሞ ....
እርጅናን አጨልመን ወጣትነትን ካበራነው
ምሽቱን የምናብ እረፍት ንጋቱን ከበጠበጥነው
ነጋ ስንል እየመሸ መሽም ማለቱ ሲነጋ ነው፡፡
እርግጥ ነው ፣ እኔም ድኩማን አፍቃሪሽ
አንቺን ከማሰብ ስገታ ሲነጋ ነው ቀኔ ሚመሽ
አይኖቼን ጨፍኜ መንፈሴን አብርቼ
በፍቅርሽ ሰክሬ መፈጠሬን ስቼ
ፍዝዝዝ
ድንግዝዝ
ቡዝዝ
ብዬ ሳስብሽ
ለኔ ነግቷል ቀኑ ላንቺ መሸ ሲሉሽ፡፡

ንጋት ማባነኗ ነው ከማምሻ የሚለያት፡፡
የነፍሳቱ ፣ የፏፏቴው ድምድምታ
በ "ታ" ቤት ያለቀ ታይቶ ጠፊ ሀሳብ
ተጀምሮ ሚቀር የማይቋጩት ምናብ

ንጋት እሱ ነው ካልሺኝ
ንጋትሽ የኔ አመሻሽ ነው
በአዋፋቱ ድንፋታ በሰማይ መብረቅ እሩምታ
ከምናቤ እየባነንኩ ፣
የትራስ መብራቴ ሲጠፋ ካንቺ በምናብ ስለይ ሲነጋ መሼ እላለሁ፡፡

(Gere tizazu)

@getem
@getem
@gebriel_19
ነጭ ጥበብ ልበሽ፣ነጭ ቀሚስ ልልበስ፣

ከእግዜርሽአልቅሺ፣ከአላህ ቤት ላልቅስ፣

ሁለት እምነት አለን ያለማንገራገር፣

ይህች ነች ኢትዮጵያለአለም እንናገር።


#ጁሙኣ እና #ጥምቀት
በፀሎት የቆመች ሀገር!!!!
Nur El Habesha

@getem
@getem
@gebriel_19
ሳት ሆኘ ስነድ: አንቺ ቆፈን ወርሶሽ
ሎሚ ብወረውር: እንቧይ ሆኖ ደርሶሽ
ዝምድና ሳያንሰን: እየቆየሽ ባዳ
መላመድ ሳይጎድለን: እያደር እንግዳ
እንግዲህ ደና ሁኝ!
ምኞቴም በረደ: ቁጣየም አለፈ
ከእድሉ ጋር ታግሎ: ማነው ያሸነፈ?

@getem
@paappii

በእውቀቱ ስዩም
(የማለዳ ድባብ)
ጥበብኛ:
፨፨፨፨፨፨፨የኔ አበባ፨፨፨፨፨፨፨
P
ስርሽ የጸደቀ፥ በሚረጨው፤ ውሀ በሚረጨው
ጸበል

ልብሽ´ቄስ እንደረገጠው እንደ ጥምቀት ሜዳ
ታቦት የሚቀበል
ፍቅር የሚቀበል

ድምጽሽ<ጦሙን>እንዳደረ እንደ ካህን ትንፋሽ
እንደ ካህን ዜማ
ጆሮን እየረሳ ለልብ የሚሰማ.
(ስትዘምሪ)

× ×. እኔ~ሽ .× ×
ወዳጅሽ ለመሆን ማየት ማይታክተኝ
ላዘቦት ቀጠሮ~~ፍቅርሽ ያነከተኝ

°°°°ታቦት እያነገስኩ አንቺን የምከተል°°°°°
አ . አ
••••አንቺን እያነገስኩ ታቦት የምከተል••••

× ×. እኔ~ሽ .× ×

ለልደት ያልሆነ --)(--ለጥምቀት ያልሆነ
ልብም ልብስም የለበስኩት
ከጴጥሮስ የባስ°°ስቅለቱ ላይ ሳይደርስ
፥ገ,ና፥ በጥምቀቱ ጌታዬን የካድኩት

× ×. አንቺው .× ×
አንዴ ስሚኝ ባመት አንዴ መጥቶ በታቦታቱ ስም
ጠበሳ ቢነግስም
ጌታውን የረሳ ያውም በጌታው ቀን ለትዳር
አይደርስም
እያልኩ ባደባባይ ህጸጽ ላወጣ ስል ፍቅርሽ
ይይዘኟል
ያንቺ..ና ኔ ትዳር እንዴት እንደጠና በጣም
ይገርመኛል
-'-'-ካዲያ እንዲ ሲሆን ስብከት ቀይራለው-'-'-
አይዞ.አ.ችሁ
ይቅናችሁ

የደስታ ቀን ይሁን አምላክን አንግሱ
..ድንገት ከተገኘ ጥሩ ሴት ጥበሱ..

ልክ እንደ እኔ

// መልካም ጥምቀት ለሁሉም \\


ተጻፈ
@semuuuuuu
ጥር 10 ~11 / 2011
ስንከትር~ስንጠመቅ

@getem
@getem
@gebriel_19
👍3
የእነ እቴጌን ቀሚስ! !!!!!

ይች መንጃራ ልጅ ፤
"""ለጥምቀት ያልሆነ ፤
ምናባቱ ቀሚስ ፤
በጣጥሱት """"" እያለች፤
በመኪናው መንገድ ፤
ሰበር ሰካ እያለች ፤ ተረገረገችው ፤
የነ እቴጌን ቀሚስ ፤
የጣይቱን ማእረግ ፤
ተልትላ ዘልዝላ ፤ቀዳ ለበሰችው ፤
አቦ አትፍረዱባት፤
ወትሮም ራቁቷን ፤ ነበር ያደገችው ።

((( ጃ ኖ ))💚💛❤️

ሸጋ የጥምቀት በዓል!!!

የኔዋ ሸጊቱ ቅዳሜ💚💛❤️!!

@balmbaras
@getem
@getem
1