፨፨፨፨የይቅርታ መሐልይ፨፨፨
ማነዉ የፈለገኝ?
በማይነጋ ሌሊት
በማይመሽ ቀን መሀል
ተዘርሬ ስገኝ።
ከተዉሽኝ በኀላ 'ርቃን ቀርታ ነፍሴ
እንኳን ከሰው ዐዉድ ተነጠልኩ ከራሴ፡፡
፨ ፨ ፨
ተመልሼ ልምጣ ተመልሰሽ ነዪ
ልጣል ምሰሶዬን ማገርሽን ጣዪ
አዲስ ቤት መገንባት ዛሬ መች ይደላል
ለምደዉ ወደተዉት መመለስ ይቀላል፡፡
፨ ፨ ፨
ካሳ ባልክልሽ ቁና ጤፍ ሰፍሬ
ባዶ እጄን አልቆምም ከደጅሽ ደፍሬ
ጵንፍ የለሽ ይቅርታን ውሰጅ ከከንፈሬ፡፡
★★★በእውቀቱ ስዩም★★★
@getem
@getem
@lula_al_greeko
ማነዉ የፈለገኝ?
በማይነጋ ሌሊት
በማይመሽ ቀን መሀል
ተዘርሬ ስገኝ።
ከተዉሽኝ በኀላ 'ርቃን ቀርታ ነፍሴ
እንኳን ከሰው ዐዉድ ተነጠልኩ ከራሴ፡፡
፨ ፨ ፨
ተመልሼ ልምጣ ተመልሰሽ ነዪ
ልጣል ምሰሶዬን ማገርሽን ጣዪ
አዲስ ቤት መገንባት ዛሬ መች ይደላል
ለምደዉ ወደተዉት መመለስ ይቀላል፡፡
፨ ፨ ፨
ካሳ ባልክልሽ ቁና ጤፍ ሰፍሬ
ባዶ እጄን አልቆምም ከደጅሽ ደፍሬ
ጵንፍ የለሽ ይቅርታን ውሰጅ ከከንፈሬ፡፡
★★★በእውቀቱ ስዩም★★★
@getem
@getem
@lula_al_greeko
👍1
ለጥበብ አፍቃርያን
--------------------------
ተናፋቂው የፋና ብዕር የጥበብ ምሽት በገና ዋዜማ ቅዳሜ27/2011 አ.ም ምሽት12:00ሰአት በዝዋይ ቱሪስት ሆቴል አዳራሽ
*ስነ-ግጥም
*መነባነብ
*ወግ
*ተውኔት እና ሌሎችም
ዳግም ልደት ለኢትዮጵያዊነት!
የመግቢያ ዋጋ 15 ብር ብቻ
አዘጋጅ ፋና ብዕር
@Tebeb_mereja
@tebeb_mereja
--------------------------
ተናፋቂው የፋና ብዕር የጥበብ ምሽት በገና ዋዜማ ቅዳሜ27/2011 አ.ም ምሽት12:00ሰአት በዝዋይ ቱሪስት ሆቴል አዳራሽ
*ስነ-ግጥም
*መነባነብ
*ወግ
*ተውኔት እና ሌሎችም
ዳግም ልደት ለኢትዮጵያዊነት!
የመግቢያ ዋጋ 15 ብር ብቻ
አዘጋጅ ፋና ብዕር
@Tebeb_mereja
@tebeb_mereja
?
“ጊዜ ብሎ ነገር
ጅማሬ የሌለው ፥ የማናየው አልቆ
ነባራዊ አይደለም
የፈበረከው ነው ፥ የሰው ልጅ ተጨንቆ
አለ የሚባለው
ይህ ቅፅበት ብቻ ነው ፥ እድሜ ለዘንድሮ
ነቅቼ ነው እንጂ
ጊዜ እውነት መስሎኝ ፥ አምን ነበር ድሮ፡፡”
ቢለኝ አዳመጥኩት
ሃሳቡን ግን ጣልኩት፥ ሳያሻኝ ማስረጃ
እስከዛሬ ድረስ
አልነቃሁም ካለ ፥ የከርሞንም እንጃ፡፡
ድሮና ዘንድሮን
ለማንፀሪያው ጠቅሶ ፥ ወድቆ ከጊዜ እቅፍ
ከአሁን ቅፅበት ሌላ
ጊዜ የለም ማለት ፥ መንቃት ወይስ እንቅልፍ?
@getem
@paappii
#Haileleul Aph
“ጊዜ ብሎ ነገር
ጅማሬ የሌለው ፥ የማናየው አልቆ
ነባራዊ አይደለም
የፈበረከው ነው ፥ የሰው ልጅ ተጨንቆ
አለ የሚባለው
ይህ ቅፅበት ብቻ ነው ፥ እድሜ ለዘንድሮ
ነቅቼ ነው እንጂ
ጊዜ እውነት መስሎኝ ፥ አምን ነበር ድሮ፡፡”
ቢለኝ አዳመጥኩት
ሃሳቡን ግን ጣልኩት፥ ሳያሻኝ ማስረጃ
እስከዛሬ ድረስ
አልነቃሁም ካለ ፥ የከርሞንም እንጃ፡፡
ድሮና ዘንድሮን
ለማንፀሪያው ጠቅሶ ፥ ወድቆ ከጊዜ እቅፍ
ከአሁን ቅፅበት ሌላ
ጊዜ የለም ማለት ፥ መንቃት ወይስ እንቅልፍ?
@getem
@paappii
#Haileleul Aph
<ቀራፂሽ>
ቅኔ ድጓ ቢደረደር
ጠፍቶ እኩያሽ ባንቺ መስከር
ደሞ ከጭስ መወዳጀት
ከብርጭቆ ጋር መጃጀት
ከትዝታሽ ጋር መባዘት
ከበደልሽ ጋር መፋጨት
ከምስልሽ ጋር ግብግብ
አንችን ለመስራት አፈር ስክብ
ከፈጣሬ ጋር ፍጥጫ
በድንሽን እንጂ እስትንፋስሽን ኬት ላምጣ
ቅኔ ድጓ ቢደረደር
ጠፍቶ አቻሽ ባንቺ መስከር
ከሸራ ጋር መከራከር
ከቀለም ጋር መፎካከር
ቆይ ላፍርሠው ሳቅሽ ጠፋ
ከሀውልቱ አልደምቅ አለ ወዙን አጣ
ውብ ገላሽን አጠቆርኩት
ጠረንሽንም አጣውት
ቆይ ላፍርስሽ እንደገና
ውበትሽን ልመልሠው ዳግም ዳግም ልገንባና፡፡
✍......አብርሀም(ልጅ ኤቢ)
@getem
@getem
@komeb
ቅኔ ድጓ ቢደረደር
ጠፍቶ እኩያሽ ባንቺ መስከር
ደሞ ከጭስ መወዳጀት
ከብርጭቆ ጋር መጃጀት
ከትዝታሽ ጋር መባዘት
ከበደልሽ ጋር መፋጨት
ከምስልሽ ጋር ግብግብ
አንችን ለመስራት አፈር ስክብ
ከፈጣሬ ጋር ፍጥጫ
በድንሽን እንጂ እስትንፋስሽን ኬት ላምጣ
ቅኔ ድጓ ቢደረደር
ጠፍቶ አቻሽ ባንቺ መስከር
ከሸራ ጋር መከራከር
ከቀለም ጋር መፎካከር
ቆይ ላፍርሠው ሳቅሽ ጠፋ
ከሀውልቱ አልደምቅ አለ ወዙን አጣ
ውብ ገላሽን አጠቆርኩት
ጠረንሽንም አጣውት
ቆይ ላፍርስሽ እንደገና
ውበትሽን ልመልሠው ዳግም ዳግም ልገንባና፡፡
✍......አብርሀም(ልጅ ኤቢ)
@getem
@getem
@komeb
ክረምት አግቢዎች
( ናትናኤል ጌቱ )
.
አንዲት አምፖል ከበው ፣ ‘ሚዞሩ 'ሚከንፉ
ወድቀው የሚረግፉ
ክንፋቸው ሲረግፍ ፣ ደግሞ ‘ሚሰለፉ
የክረምት ገቢዎች ፣ ክረምት ሳያስገቡ
ወይ ባማራጭ ሀሳብ ፣ ወንዝ ሳይገድቡ
መንኪት ሳይገነቡ ፣ ውሀ ሳይኖራቸው
ክረምት አግቢ ብሎ ፣ ማን ስም ለገሳቸው?
…
አልገባም ክረምቱ ፣ ሰልፋቸውን አይቶ
አልመጣም ዝናቡ ፣ በእነሱ ተጠርቶ
ወቅቴ አለፈ ብሎ ፣ ሲሰወር ሐሩሩ
ጥንድ ጥንድ ሰርተው ፣ መሰለፍ ጀመሩ
….
ተፋላሚ አጥተን ፣ ድሮ ስንንቃቃ
ማዋጣት ያልቻሉ ፣ የመጠለያ እቃ
አየሩ ቀዝቅዞ ፣ የበጋው አሻጥር
ጊዜ ራሱ ፈቶት ፣ የሙቀቱን አጥር
ፍልሚያው እንዳበቃ
እናዝምት ይሉናል ፣ ሺ የጦር አለቃ
…
ጸሀይ መቶን ያኔ … ስንደነጋገር
“ኸረ ከልሉልን ፣ ይሄን መብራት ነገር"
ብለን ስንነግራቸው
ተደብቀው ኑረው ፣ እነሱ ራሳቸው
ጸሀዩ ሲሸፈን ፣ በጥቁር ደመና
ዘግይተው መጡና
የሚበራ ነገር ፣ መፈለግ ጀመሩ
ሊያጨልሙብን ነው
እኛ ያበራነውን ፣ አምፖል እየዞሩ
.
@getem
@getem
@gebriel_19
( ናትናኤል ጌቱ )
.
አንዲት አምፖል ከበው ፣ ‘ሚዞሩ 'ሚከንፉ
ወድቀው የሚረግፉ
ክንፋቸው ሲረግፍ ፣ ደግሞ ‘ሚሰለፉ
የክረምት ገቢዎች ፣ ክረምት ሳያስገቡ
ወይ ባማራጭ ሀሳብ ፣ ወንዝ ሳይገድቡ
መንኪት ሳይገነቡ ፣ ውሀ ሳይኖራቸው
ክረምት አግቢ ብሎ ፣ ማን ስም ለገሳቸው?
…
አልገባም ክረምቱ ፣ ሰልፋቸውን አይቶ
አልመጣም ዝናቡ ፣ በእነሱ ተጠርቶ
ወቅቴ አለፈ ብሎ ፣ ሲሰወር ሐሩሩ
ጥንድ ጥንድ ሰርተው ፣ መሰለፍ ጀመሩ
….
ተፋላሚ አጥተን ፣ ድሮ ስንንቃቃ
ማዋጣት ያልቻሉ ፣ የመጠለያ እቃ
አየሩ ቀዝቅዞ ፣ የበጋው አሻጥር
ጊዜ ራሱ ፈቶት ፣ የሙቀቱን አጥር
ፍልሚያው እንዳበቃ
እናዝምት ይሉናል ፣ ሺ የጦር አለቃ
…
ጸሀይ መቶን ያኔ … ስንደነጋገር
“ኸረ ከልሉልን ፣ ይሄን መብራት ነገር"
ብለን ስንነግራቸው
ተደብቀው ኑረው ፣ እነሱ ራሳቸው
ጸሀዩ ሲሸፈን ፣ በጥቁር ደመና
ዘግይተው መጡና
የሚበራ ነገር ፣ መፈለግ ጀመሩ
ሊያጨልሙብን ነው
እኛ ያበራነውን ፣ አምፖል እየዞሩ
.
@getem
@getem
@gebriel_19
ንፋስ ጎርፍ ማእበል
.
.
.
ቀዝቃዛዉን ክብድ አየር
ጠሊቅና ሰፊዉን ባህር
ተቋቁመሽ ነፋስ ጎርፉን
ካሻገርሺኝ ማእበሉን
ፅናት ካለሽ ለንፋሱ
ለሚነፍሰዉ ከባህሩ
ወደብ ደርሰሽ ካሳረፍሺኝ
ከእትብቴ ከአፈሩ
ያዢዉ መልህቁን ቅዘፊዉ ባህሩን
እኔም ልሁን መርከቢቱን
በዘመንሽ በዘመኔ የበቀለዉን የመከራ ችግኝ
በቀዝቃዛዉ ክቡድ አየር የሚያልፈዉን የእሳት ብናኝ
ሰዉ በመሆን ጉጉት ባለመሆን ስጋት
በሰዉነት ህሊናዬ ያደረዉን ታላቅ ፍራት
ተቋቁመሽ ንፋስ የጎርፉን ካሻገርሺኝ ማእበሉን
ያዢዉ መልህቁን ቅዘፊዉ ባህሩን
እኔም ልሁን መርከቢቱን
ከጥልቁ ያሉትን አስፈሪ እንስሳት
ንፋስ ያመጣዉን የማእበል ጩኸት
በዘመንሽ በዘመኔ ሳይደምን
እርግጠኛ ሆነሽ ካሳየሺኝ ነገን
ይሄዉ ልቤ መርከብሽ ነዉ
ይዘሺዉ ሂጂ በፈቀድሺዉ
ግና ዉዴ እቴ ፍቅሬ
አደራሽን አደራሽን አደራሽን
ንፋስ ጎርፍ ማእበሉን
ተቋቁሞ ማሻገሩን
ንፋሱ ሀያል ነዉ
ጎርፉ በጣም ፈጣን
ባህሩ ጥልቅ ነዉ
ጥግ የሌለዉ ወሰን
አየሩ ክቡድ ነዉ ገፅን የሚያደምን
አደራሽን ..... አደራሽን ....... አደራሽን
@paappii
@getem
#ephrem seyoum
.
.
.
ቀዝቃዛዉን ክብድ አየር
ጠሊቅና ሰፊዉን ባህር
ተቋቁመሽ ነፋስ ጎርፉን
ካሻገርሺኝ ማእበሉን
ፅናት ካለሽ ለንፋሱ
ለሚነፍሰዉ ከባህሩ
ወደብ ደርሰሽ ካሳረፍሺኝ
ከእትብቴ ከአፈሩ
ያዢዉ መልህቁን ቅዘፊዉ ባህሩን
እኔም ልሁን መርከቢቱን
በዘመንሽ በዘመኔ የበቀለዉን የመከራ ችግኝ
በቀዝቃዛዉ ክቡድ አየር የሚያልፈዉን የእሳት ብናኝ
ሰዉ በመሆን ጉጉት ባለመሆን ስጋት
በሰዉነት ህሊናዬ ያደረዉን ታላቅ ፍራት
ተቋቁመሽ ንፋስ የጎርፉን ካሻገርሺኝ ማእበሉን
ያዢዉ መልህቁን ቅዘፊዉ ባህሩን
እኔም ልሁን መርከቢቱን
ከጥልቁ ያሉትን አስፈሪ እንስሳት
ንፋስ ያመጣዉን የማእበል ጩኸት
በዘመንሽ በዘመኔ ሳይደምን
እርግጠኛ ሆነሽ ካሳየሺኝ ነገን
ይሄዉ ልቤ መርከብሽ ነዉ
ይዘሺዉ ሂጂ በፈቀድሺዉ
ግና ዉዴ እቴ ፍቅሬ
አደራሽን አደራሽን አደራሽን
ንፋስ ጎርፍ ማእበሉን
ተቋቁሞ ማሻገሩን
ንፋሱ ሀያል ነዉ
ጎርፉ በጣም ፈጣን
ባህሩ ጥልቅ ነዉ
ጥግ የሌለዉ ወሰን
አየሩ ክቡድ ነዉ ገፅን የሚያደምን
አደራሽን ..... አደራሽን ....... አደራሽን
@paappii
@getem
#ephrem seyoum
#ለፍቅር_ከሆነ
።።።።።።።።።።።።።።።።
ለፍቅር ከሆነ ሺ ጊዜ ልገፋ
ቀጥረሽኝ አትምጪ ልተክዝ ልከፋ
መውደዴን ስነግርሽ እንዳሻሽ ሳቂብኝ
ሺ ጊዜ ስደውል ሺ ጊዜ ዝጊብኝ
ልሙት
የሚወድሽ ልቤን ላንቺ እንዳስገዛሁት
ልብ አ'ርጊልኝ ታዲያ ለ_ፍ_ቅ_ር ነው ያልኩት
አንቺማ አንቺ ነሽ ፍቅር የማይገባሽ መውደድ የማታውቂ
ባፈቀረሽ ሰው ላይ ያላንዳች ምክንያት ምታፌዥ ምትስቂ
አንቺማ አንቺ ነሽ ቀጥረሽ የምትቀሪ የሚወድሽን ሰው
ድንጋይ ልብ የተቸርሽ ፍቅር የማይገባ ፍቅር የማይሰርፀው
እንዳ'ንቺማ ቢሆን
እንዳ'ንቺማ ቢሆን ድሮ ከበፊቱ
ይለይልኝ ነበር ይቆርጥልኝ ነበር ገና በጠዋቱ
ግን ፍቅር ነውና ካንቺ ጋር ያሰረኝ
ስወድሽ እንደኖርኩ ስወድሽ ይቅበረኝ
✍ #መኖር ደጉ
@getem
@getem
@gebriel_19
።።።።።።።።።።።።።።።።
ለፍቅር ከሆነ ሺ ጊዜ ልገፋ
ቀጥረሽኝ አትምጪ ልተክዝ ልከፋ
መውደዴን ስነግርሽ እንዳሻሽ ሳቂብኝ
ሺ ጊዜ ስደውል ሺ ጊዜ ዝጊብኝ
ልሙት
የሚወድሽ ልቤን ላንቺ እንዳስገዛሁት
ልብ አ'ርጊልኝ ታዲያ ለ_ፍ_ቅ_ር ነው ያልኩት
አንቺማ አንቺ ነሽ ፍቅር የማይገባሽ መውደድ የማታውቂ
ባፈቀረሽ ሰው ላይ ያላንዳች ምክንያት ምታፌዥ ምትስቂ
አንቺማ አንቺ ነሽ ቀጥረሽ የምትቀሪ የሚወድሽን ሰው
ድንጋይ ልብ የተቸርሽ ፍቅር የማይገባ ፍቅር የማይሰርፀው
እንዳ'ንቺማ ቢሆን
እንዳ'ንቺማ ቢሆን ድሮ ከበፊቱ
ይለይልኝ ነበር ይቆርጥልኝ ነበር ገና በጠዋቱ
ግን ፍቅር ነውና ካንቺ ጋር ያሰረኝ
ስወድሽ እንደኖርኩ ስወድሽ ይቅበረኝ
✍ #መኖር ደጉ
@getem
@getem
@gebriel_19
የስጁዱ ሜዳ! !!!!!!
ይህ የሜዳ ጎበዝ ፤
ገምባሌውን ታጥቆ ፤
ማልያውን ለብሶ፤
እርም እርም ሲል፤
ለኳሱ ለጡንቻው ሲያረገርግ ውሎ፤
ደግሞ በርከክ ይላል ፤
ከስጁዱ ሜዳ አሏህ አክበር ብሎ ።
ከሜዳው መሃከል ፤
አዛን የወጣ እለት ፤
ስጁድ የወረደ ብሎ መርሃባ ፤
አይተናል ሰምተናል ፤
እንኳን በዱንያ ቤት ፤
በአኬራውም ሜዳ ብዙ ጎል ሲያስገባ ።
((( ጃ ኖ )))💚💛❤️
ሸጊቱ ጁምኣ!💚💛❤️
@balmbaras
@getem
@getem
ይህ የሜዳ ጎበዝ ፤
ገምባሌውን ታጥቆ ፤
ማልያውን ለብሶ፤
እርም እርም ሲል፤
ለኳሱ ለጡንቻው ሲያረገርግ ውሎ፤
ደግሞ በርከክ ይላል ፤
ከስጁዱ ሜዳ አሏህ አክበር ብሎ ።
ከሜዳው መሃከል ፤
አዛን የወጣ እለት ፤
ስጁድ የወረደ ብሎ መርሃባ ፤
አይተናል ሰምተናል ፤
እንኳን በዱንያ ቤት ፤
በአኬራውም ሜዳ ብዙ ጎል ሲያስገባ ።
((( ጃ ኖ )))💚💛❤️
ሸጊቱ ጁምኣ!💚💛❤️
@balmbaras
@getem
@getem
~~☞ #የተገዘተ_ሠማይ ☜~~
ቀንን በፀሀይ ማታን በጨረቃ
ሠማይ እንደዛ ነች ሲያይዋት ምታነቃ
የቸኮለ መሪጌታ ገዝቶ ሳይተዋት
ነካክቶ አደፍርሶ ውበቷን ሳይነጥቃት
.
ሠማያዊ ዐይኗን በጉም የተኳለች
የንጋት ፈገግታዋን በፀሀይ ያደመቀች
የለሊት ኩርፊያዋን በጨረቃ የደበቀች
ማንም ወጥቶ ወርዶ ብሎም አስሮ ፈቶ
በቀኗም ሰርቶባት በለሊቷም ተኝቶ
ባልፈታው ቅኔዋ አፅናፏን ቃኝቶ
ከወዲያ ወዲህ ባዝቶ ዋትቶ
ከሷ በላይ ላሰበው ቀና ብሎ ተሰውቶ
መገዘቷንም ሳያውቅ መፈታትዋን የሚያጋንን
የኔ ቢጤ የተከፋ አንጋጦ የሚለምን
.
ወና ጎጆ ውስጥ ሰፊ ልቡን ያከተመ
በማይገባው ተስፋ ነገውን ያስታመመ
ድሃ የሚባልን ተረት አፏን በዳቦ ሊያብስ
ከተገዘተች ሠማይ ስር ቢቅለሰለስ
ሃብታም ይሉት በራሪ ክንዷ ላይ ቢንተራስ
.
የተፈታ አካሏን አስገዝቶ ቢያቆላልፍ
የታችኛው ድሃ የመሬቱ ሠፈፍ
የተገዘተ ሠማይ ይዞ ለማስፈታት የሚሠለፍ
------------ $ --------
፡-#ተክለ_ዮሀንስ(ከሰባተኛ)
@getem
@getem
ቀንን በፀሀይ ማታን በጨረቃ
ሠማይ እንደዛ ነች ሲያይዋት ምታነቃ
የቸኮለ መሪጌታ ገዝቶ ሳይተዋት
ነካክቶ አደፍርሶ ውበቷን ሳይነጥቃት
.
ሠማያዊ ዐይኗን በጉም የተኳለች
የንጋት ፈገግታዋን በፀሀይ ያደመቀች
የለሊት ኩርፊያዋን በጨረቃ የደበቀች
ማንም ወጥቶ ወርዶ ብሎም አስሮ ፈቶ
በቀኗም ሰርቶባት በለሊቷም ተኝቶ
ባልፈታው ቅኔዋ አፅናፏን ቃኝቶ
ከወዲያ ወዲህ ባዝቶ ዋትቶ
ከሷ በላይ ላሰበው ቀና ብሎ ተሰውቶ
መገዘቷንም ሳያውቅ መፈታትዋን የሚያጋንን
የኔ ቢጤ የተከፋ አንጋጦ የሚለምን
.
ወና ጎጆ ውስጥ ሰፊ ልቡን ያከተመ
በማይገባው ተስፋ ነገውን ያስታመመ
ድሃ የሚባልን ተረት አፏን በዳቦ ሊያብስ
ከተገዘተች ሠማይ ስር ቢቅለሰለስ
ሃብታም ይሉት በራሪ ክንዷ ላይ ቢንተራስ
.
የተፈታ አካሏን አስገዝቶ ቢያቆላልፍ
የታችኛው ድሃ የመሬቱ ሠፈፍ
የተገዘተ ሠማይ ይዞ ለማስፈታት የሚሠለፍ
------------ $ --------
፡-#ተክለ_ዮሀንስ(ከሰባተኛ)
@getem
@getem
ሃውልቱ!!!!!!!!!
እምየ ምኒሊክ ፤
እንጀራው ምኒሊክ ፤
አንተ ባትወለድ ፤
በጦር በጎራዴ ፤
ጠላት ባይመተር ፤ ባንዳ ባይደፈር ፤
ጦቢያ ሚሏት ሃገር ፤
ከባንዲራዋ ጋር ፤
በአድዋ ሰማይ ስር ፤ቆማ ባትታፈር ፤
ማርያምን ልበልህ ፥
አራዳ ጊወርጊስ ፤
የሚቆመው ሃውልት፤ እንዲህ ይሆን ነበር ።
((( ጃ ኖ ))💚💛❤️
@balmbaras
@getem
@getem
እምየ ምኒሊክ ፤
እንጀራው ምኒሊክ ፤
አንተ ባትወለድ ፤
በጦር በጎራዴ ፤
ጠላት ባይመተር ፤ ባንዳ ባይደፈር ፤
ጦቢያ ሚሏት ሃገር ፤
ከባንዲራዋ ጋር ፤
በአድዋ ሰማይ ስር ፤ቆማ ባትታፈር ፤
ማርያምን ልበልህ ፥
አራዳ ጊወርጊስ ፤
የሚቆመው ሃውልት፤ እንዲህ ይሆን ነበር ።
((( ጃ ኖ ))💚💛❤️
@balmbaras
@getem
@getem
🔥1
🖤ናፍቆት💓
ይህን ያክል ብየ መግለጽ ቢቸግረኝ
ናፍቆት ነፋስ ሆኖ መጨበጥ ሲያቅተኝ
ትዝታ ፈረሱ ከዳመናው በላይ
ውብ አይንሽን እንዳይ
ሽምጥ ሲያስጋልበኝ
ናፍቆት ሞት ነው አልኩኝ
እኔ አንችን እስካገኝ!!
።ጆሽ።
@getem
@getem
@gebriel_19
ይህን ያክል ብየ መግለጽ ቢቸግረኝ
ናፍቆት ነፋስ ሆኖ መጨበጥ ሲያቅተኝ
ትዝታ ፈረሱ ከዳመናው በላይ
ውብ አይንሽን እንዳይ
ሽምጥ ሲያስጋልበኝ
ናፍቆት ሞት ነው አልኩኝ
እኔ አንችን እስካገኝ!!
።ጆሽ።
@getem
@getem
@gebriel_19
ሙሌ አባ መንገዴ
አስያ አስያ፣
ንኡድ ቃል አምሳያ፣
እንኪ ስላንትያ፣
እሸትሽ ቅኔ ነዉ፣ ገላሽ ቦለቅያ፣
አቦ በየጁ ሞት፣ አቦ በወልዲያ፣
አቀብይኝ ዛሬ፣
ቅኔ እምኩልበት ፤ ቅኔ መሞሸሪያ፤
ትመጫለሽ አሉ፣
በ “ሙልየ..” ሲሉሽ ፣
የጁ ኪቢ ቃሉ፤ ማክሰኞ ገበያ፡፡
አስያ ጨብራሪት፣
የሃራ ወበሎ ፤ የታች ቆላይቱ፣
ጨብረር ጨብረር በይ፣
ተንጎማለይበት ፤ ነይማ ሸጊቱ፣
ወፈፍ ወፈፍ በይ፣
በጎጆየ ታዛ፣ አልፈሽ በምርጊቱ፡፡
ሀድራዉ ከሞቀበት፣
ቱፍታው ከሞላበት ፤ ከእነ ኩሌ ማጀት፣
ሀቂቃ አይደለም ወይ?
ካ'ስያ ጋር ኑሮ ፤ ካ'ስያ ጋር ማርጀት።
አውገረድ አስያ ፤
በበልጅግሽ ባሩድ፣ ባልቤንሽ ማንገቻ፣
እንደ ንጉስ አሽከር ፤
አሻቅቦ ያያል ፤ ቀልቤ አንችኑ ብቻ፤
ምን ያድርግ ብለሽ ነው፤
ወትሮም ከላይ ቤት ነዉ፣ ቅኔና ኮርቻ፡፡
ተገማሸሪበት ፤
ቀብረር ቀብረር በይ፣ አስያ በሞቴ፣
አህሪቡ ስትይኝ ፤
ጅስሜ ይበረታል ፤ ይጠናል ጉልበቴ ።
ከሙሉጌታ ጋር፣
ከሙሉ ሸጋ ጋር፣
ጉባርጃ ማርያም ላይ ፤ ያሰርሽዉ ቃል ኪዳን፣
እኔንም ዘንድሮ ፤
ጠራኝ ግጠም አለኝ፣ አወደኝ እንደእጣን፡፡
እኔም እንደ ሙሌ፣ እንደሙሉጌታ፣
ቀየዉ እንዳስከፋዉ፣ እንደቆላ ሽፍታ፣
ግጠም ግጠም አለኝ፣ የያዘኝ በሽታ፡፡
እገጥማለሁ እንጅ፣
በየበራበሩ ቅኔ ዛር አለብኝ፣
ላዩን በውድመን ፤
ታቹን በሶደማ ፤
አስያ ጨብራሪት፣ ወስዳ ሸሽጋብኝ፡፡
ልለማመን እስቲ፣
በእነነየ ጉፍታ ፤ በየጁ ቀለበት፣
ልመጀነዉ እስቲ፣
በአውገረድ ሹምባሽ ቤት ፤የላስቴን አቀበት፣
እንደግሽር ገላ፣ እንደወዳጅ እብለት፣
ምርኩዝ የሚሆነዉ፣ ለታፈረ ጉልበት፣
ጠብቆ ሲሰፋ ነው ፤ ቅኔና ዘለበት፡፡
ሀየ በል ገለሌ፣ እምቢ በል ጃዉሳ፣
ልቤ “..ቸ..” በል አለኝ “..ቸ..” በል ደንገላሳ፣
ብረር ብረር አለኝ፣ ቅኔ ቀለም አንሳ፣
ወትሮም ወደ ላይ ነዉ፣ ቅኔና ግሪሳ፣
ግጠም ግጠም አለኝ ፣ በልጅግህን አንሳ፣
አውቃለሁ አምናለሁ፤
የሞት ባልንጀር ነዉ፣ ቅኔና ወሳንሳ፡፡
አስያ ከገባች፣ ከማጀቷ ወጥታ፣
ጎዝጉዙልኝ ካለች፣ ወዳጃ ተጠርታ፣
ጀማዉ ከደመቀ፣ ቅጥሩ ከተፈታ፣
ግጠም ግጠም አለኝ፣ እንደሙሉጌታ፡፡
አያ ሙሌ ሆዴ፣
ቅኔ እሳት አመዴ፣
ከርታታዉ ዘመዴ፣
እኔ አለሁህ ልበል? አንተ አለሀኝ እንዴ?
ሰገነት ባትወጣ፣ ግብርህ ባይታወቅ፣
በሺህ ጋዜጠኛ፣ ስምህ ባይዳመቅ፣
በቲፎዞ ባሩድ፣ ባይሞቅ ያንተ ሽታ፣
በጭብጨባ ባይድን፣ ያንተ ሆድ በሽታ፣
ቃል አልተሸነፈም፣ ቅኔህ አልተረታ፣
“ታላቁ ሰዉ መጣ”፣
“ባለቅኔዉ መጣ”፣
“ያ ደራሲዉ መጣ”፣
ብለዉ ባይሰግዱልህ፣
ብለዉ ባይጮሁልህ፣ ምን ግድህ ምን ግዴ፣
አትንሰፈሰፍም ፣ለሹመት ለጓንዴ
ስሙልኝ አያምርህ፣ እንደቆላ ገዴ፣
አቦ ሆድ ይመርቅ፣ ሙሌ አባ መንገዴ፡፡
((( ጃ ኖ )))💚💛❤️
(( ማስታወሻነቱ ለባለቅኔው
ሙሉጌታ ተስፋየ ❤️❤️❤️) )
ፍልቅልቅ ቅዳሜ!💚!💛!❤!!
@balmbaras
@getem
@getem
አስያ አስያ፣
ንኡድ ቃል አምሳያ፣
እንኪ ስላንትያ፣
እሸትሽ ቅኔ ነዉ፣ ገላሽ ቦለቅያ፣
አቦ በየጁ ሞት፣ አቦ በወልዲያ፣
አቀብይኝ ዛሬ፣
ቅኔ እምኩልበት ፤ ቅኔ መሞሸሪያ፤
ትመጫለሽ አሉ፣
በ “ሙልየ..” ሲሉሽ ፣
የጁ ኪቢ ቃሉ፤ ማክሰኞ ገበያ፡፡
አስያ ጨብራሪት፣
የሃራ ወበሎ ፤ የታች ቆላይቱ፣
ጨብረር ጨብረር በይ፣
ተንጎማለይበት ፤ ነይማ ሸጊቱ፣
ወፈፍ ወፈፍ በይ፣
በጎጆየ ታዛ፣ አልፈሽ በምርጊቱ፡፡
ሀድራዉ ከሞቀበት፣
ቱፍታው ከሞላበት ፤ ከእነ ኩሌ ማጀት፣
ሀቂቃ አይደለም ወይ?
ካ'ስያ ጋር ኑሮ ፤ ካ'ስያ ጋር ማርጀት።
አውገረድ አስያ ፤
በበልጅግሽ ባሩድ፣ ባልቤንሽ ማንገቻ፣
እንደ ንጉስ አሽከር ፤
አሻቅቦ ያያል ፤ ቀልቤ አንችኑ ብቻ፤
ምን ያድርግ ብለሽ ነው፤
ወትሮም ከላይ ቤት ነዉ፣ ቅኔና ኮርቻ፡፡
ተገማሸሪበት ፤
ቀብረር ቀብረር በይ፣ አስያ በሞቴ፣
አህሪቡ ስትይኝ ፤
ጅስሜ ይበረታል ፤ ይጠናል ጉልበቴ ።
ከሙሉጌታ ጋር፣
ከሙሉ ሸጋ ጋር፣
ጉባርጃ ማርያም ላይ ፤ ያሰርሽዉ ቃል ኪዳን፣
እኔንም ዘንድሮ ፤
ጠራኝ ግጠም አለኝ፣ አወደኝ እንደእጣን፡፡
እኔም እንደ ሙሌ፣ እንደሙሉጌታ፣
ቀየዉ እንዳስከፋዉ፣ እንደቆላ ሽፍታ፣
ግጠም ግጠም አለኝ፣ የያዘኝ በሽታ፡፡
እገጥማለሁ እንጅ፣
በየበራበሩ ቅኔ ዛር አለብኝ፣
ላዩን በውድመን ፤
ታቹን በሶደማ ፤
አስያ ጨብራሪት፣ ወስዳ ሸሽጋብኝ፡፡
ልለማመን እስቲ፣
በእነነየ ጉፍታ ፤ በየጁ ቀለበት፣
ልመጀነዉ እስቲ፣
በአውገረድ ሹምባሽ ቤት ፤የላስቴን አቀበት፣
እንደግሽር ገላ፣ እንደወዳጅ እብለት፣
ምርኩዝ የሚሆነዉ፣ ለታፈረ ጉልበት፣
ጠብቆ ሲሰፋ ነው ፤ ቅኔና ዘለበት፡፡
ሀየ በል ገለሌ፣ እምቢ በል ጃዉሳ፣
ልቤ “..ቸ..” በል አለኝ “..ቸ..” በል ደንገላሳ፣
ብረር ብረር አለኝ፣ ቅኔ ቀለም አንሳ፣
ወትሮም ወደ ላይ ነዉ፣ ቅኔና ግሪሳ፣
ግጠም ግጠም አለኝ ፣ በልጅግህን አንሳ፣
አውቃለሁ አምናለሁ፤
የሞት ባልንጀር ነዉ፣ ቅኔና ወሳንሳ፡፡
አስያ ከገባች፣ ከማጀቷ ወጥታ፣
ጎዝጉዙልኝ ካለች፣ ወዳጃ ተጠርታ፣
ጀማዉ ከደመቀ፣ ቅጥሩ ከተፈታ፣
ግጠም ግጠም አለኝ፣ እንደሙሉጌታ፡፡
አያ ሙሌ ሆዴ፣
ቅኔ እሳት አመዴ፣
ከርታታዉ ዘመዴ፣
እኔ አለሁህ ልበል? አንተ አለሀኝ እንዴ?
ሰገነት ባትወጣ፣ ግብርህ ባይታወቅ፣
በሺህ ጋዜጠኛ፣ ስምህ ባይዳመቅ፣
በቲፎዞ ባሩድ፣ ባይሞቅ ያንተ ሽታ፣
በጭብጨባ ባይድን፣ ያንተ ሆድ በሽታ፣
ቃል አልተሸነፈም፣ ቅኔህ አልተረታ፣
“ታላቁ ሰዉ መጣ”፣
“ባለቅኔዉ መጣ”፣
“ያ ደራሲዉ መጣ”፣
ብለዉ ባይሰግዱልህ፣
ብለዉ ባይጮሁልህ፣ ምን ግድህ ምን ግዴ፣
አትንሰፈሰፍም ፣ለሹመት ለጓንዴ
ስሙልኝ አያምርህ፣ እንደቆላ ገዴ፣
አቦ ሆድ ይመርቅ፣ ሙሌ አባ መንገዴ፡፡
((( ጃ ኖ )))💚💛❤️
(( ማስታወሻነቱ ለባለቅኔው
ሙሉጌታ ተስፋየ ❤️❤️❤️) )
ፍልቅልቅ ቅዳሜ!💚!💛!❤!!
@balmbaras
@getem
@getem