ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ንፋስ ጎርፍ ማእበል
.
.
.
ቀዝቃዛዉን ክብድ አየር
ጠሊቅና ሰፊዉን ባህር
ተቋቁመሽ ነፋስ ጎርፉን
ካሻገርሺኝ ማእበሉን
ፅናት ካለሽ ለንፋሱ
ለሚነፍሰዉ ከባህሩ
ወደብ ደርሰሽ ካሳረፍሺኝ
ከእትብቴ ከአፈሩ
ያዢዉ መልህቁን ቅዘፊዉ ባህሩን
እኔም ልሁን መርከቢቱን
በዘመንሽ በዘመኔ የበቀለዉን የመከራ ችግኝ
በቀዝቃዛዉ ክቡድ አየር የሚያልፈዉን የእሳት ብናኝ
ሰዉ በመሆን ጉጉት ባለመሆን ስጋት
በሰዉነት ህሊናዬ ያደረዉን ታላቅ ፍራት
ተቋቁመሽ ንፋስ የጎርፉን ካሻገርሺኝ ማእበሉን
ያዢዉ መልህቁን ቅዘፊዉ ባህሩን
እኔም ልሁን መርከቢቱን
ከጥልቁ ያሉትን አስፈሪ እንስሳት
ንፋስ ያመጣዉን የማእበል ጩኸት
በዘመንሽ በዘመኔ ሳይደምን
እርግጠኛ ሆነሽ ካሳየሺኝ ነገን
ይሄዉ ልቤ መርከብሽ ነዉ
ይዘሺዉ ሂጂ በፈቀድሺዉ
ግና ዉዴ እቴ ፍቅሬ
አደራሽን አደራሽን አደራሽን
ንፋስ ጎርፍ ማእበሉን
ተቋቁሞ ማሻገሩን
ንፋሱ ሀያል ነዉ
ጎርፉ በጣም ፈጣን
ባህሩ ጥልቅ ነዉ
ጥግ የሌለዉ ወሰን
አየሩ ክቡድ ነዉ ገፅን የሚያደምን
አደራሽን ..... አደራሽን ....... አደራሽን

@paappii
@getem

#ephrem seyoum