ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
!!ሰረደ !!ደረሰ !!ሰረደ
"የብርሃን ዕለታችን" ሰረደ እነሆ በጣት የሚቀሩ ቀናት ቀርተውታል።
የመግቢያ ትኬቶች በስፋት እየተቸበቸቡ ይገኛል። በዚህ ለየት ባለ የእንድቅትዮን ምሽት ላይ ቢገኙ ያተርፋሉ።

የመግቢያ ትኬቶቹን:-
፩.ጃፋር መፅሐፍት...ለገሃር
፪.ዮናስ መፅሐፍት...ብሔራዊ
፫.ዩኒቨርሳል መፅሐፍትና የፅሕፈት መሣሪያ መሸጫ መደብር ...፬ ኪሎ ፬.አብርሽ ስቱዲዮ.....ሰሜን ማዘጋጃ
ያገኛሉ።

እንዲሁም በስልክ ቁጥር:- ፱-፲-፺፱-፵፰-፶፫(0910994853)
እንዲሁም ፱-፴፰-፸-፵-፳(0938704020) ይደውሉ። ታኅሳስ ፲፰
ዋቢ ሸበሌ ሆቴል አይቀርም።

@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
"አንቺ ኢትዮጵያ እውነት በድየሽ ተሆነ ነፍሴን አይቀበላት። አልበደልሁሽ ተሆነ ወንድ አይብቀልብሽ!" አባ ኮስትር በላይ ዘለቀ ሊሰዋ ሲል የተናገረው።
።።
የበላይ መጨረሻ
(ጌትነት እንየው)
.
.
የእስትንፋሴ መቁረጫ ገመድ ነው
እዚህ ተንጠልጥሎ የማየው?!
የበላይ የሞት መወጣጫ እርከን ነው
ይህ መሰላል እዚህ የቆመው?!
ገማባው የጠላት መርዶ የእርሳስ ልሳኔ ይናገር
" በላይ የወንዶች ቁና!"
እንኳን ለነጭ ገመድ፣ ለሺ ጠብመንጃም
አይደነብር።
አዎ፣ እኔ እንደሁ ጥንትም አውቃለሁ
አባቴ በንጉስ ጭራ ቆይ፣ በባሩድ ማረር መክሰሉን
በእርሳስ መለብለብ መንደዱን
በድኑ ለገመድ መዳረጉን።
እናም አሁን " የዘለቀ ልጅ" ለነጭ ገመድ
አይፈራም በለው
ለአደገዳጊ ቧልተኛ፣ ለእንከፍ አሳባቂ ይብላኝ
እንጂ:_
ሞት እንደሁ አብሮኝ የኖረ፣ ስቅላቴም ያባቴ ነው።
ግን አንች ጥቁር አገር ጥቁር አፈር:_
መፀነሻ ከርስ የጥቁር ዘር
አያልፉሽ ጋራሽ ይናገር
አባይ ጅረትሽ ይመስክር
ላንቺ የኖረ ማን ሆኖ?
ላንቺ የሞተ ማን ሆኖ? ባንቺስ የኖረ ማን ነበር?
ልጆችሽ በመስክሽ ቧርቀው
ከሸጥሽ ውሃ ጠጥተው
ጥቁር ሰማይሽን ተማጥነው
ጥቁር አፈርሽን አርሰው በልተው
በዱርሽ " አሆ በል" ብለው
የሰላም አየርሽን ስበው
መች ገሸሽ አሉ በክፉ ቀን
አንቺን ለመከራ ዳርገው?!
ከደብር ደብር ተሰባስበው
ተገን አድርገው ዱርሽን
ከወንዝ ወንዝ ተጠራርተው
ምሽግ መሽገው ፊላሽን
ከአገር አገር ተፈላልገው
ከለላ አርገው ጨለማሽን
ተፋለሙ እንጂ ልጆችሽ
መች ሸሹ አንቺን የትም ጥለው?
መች ጥለውሽ ጠፉ እንደሌሎች
ነጭ አሞራ ይብላት ብለው!?
ታዲያ መች ለኔ ነበር ይህ ገመድ እዚህ መታበቱ
ለነሱ ነበር እንጂ
ከነፃነትሽ ደስታ ምገው
ከሰላምሽ ፍሬሽ ቀጥፈው በልተው
በክፉ ቀን ለሸለቱ
ነጭ አሞራ ይብላት ላሉቱ
" የእናት ሆድ ዥንጉርጉር " አሉ አበው አይተው
ሲተርቱ
እውነትም ነጭና ጥቁር ዥንጉርጉር እንጂ ከጥንቱ!
እውነትም ባንዳና አርበኛ ዥንጉርጉር እንጂ
በብርቱ!
ነፍስሽ እንኳን…
ነፍስሽ እንኳን ከጫካሽ ጋር ከሾህ ከሳርሽ አብሮ
ጠላትሽ በእሳት ሲአቃጥል ከእሳት ልጆችሽ እሳት
ጭሮ…
እኔ ሸክሚቱን ስሰጥሽ
እሷ ህይወት ስትዳረግሽ
የሻሽ ወርቅ ልጄን እንኪ ስልሽ
በዚያች እለት
በዚያች ሰአት
አፋዳሽ ባንዳ ሁሉ የት ጠፍቶ ነበር ከጎንሽ!?
ነጭ አመድ ቦቅቧቃ ባንዳ
ለአጥቂ ጠላትሽ ሲል "አለሁ"
እኔ ለክብርሽ በተጋደልሁ
ለእንባሽ ቆሜ በተፋለምሁ
የታጠፈ አንጀቴን አጥፌ
ለታጠፈ አንጀትሽ ባለምሁ
ለአርነትሽ ዘብ ሆኜ
ለሰላምሽ ምላጭ በሳብሁ፣…
እንዴት እጄን ለካቴና
አንገቴ ለገመድ ይዳረግ ኢትዮጲያ!?
ይህ ነው እንዴ
የጀግንነቴ ወሮታ የአርብኝነቴ ክፍያ?!
ሰው ያልወለደው ሰው ይመስል፣ የዘር ሃረግ
እየሳቡ
ራሳቸውን ራስ ብለው ራስ ለልጃቸው ለሚያደልቡ
ከሰው እርከን ተፈናጥረው
" የመላእክ የአጥንት ፍላጭ ነን!"
የሚያሰኝ የደም ህንፃ ለሚክቡ
እንዴት ለነሱ ይሁን ደስታሽ
የነፃነት እምቡጥ ፍሬሽ?
እንዴት ባንዳ ለባንዳ ይሸላለም
ይሿሿም አዙባሽ ለሹምባሽ!?
ከጀግና ማህፀንሽ የፈለቁ ጀግና ልጆችሽ
ባፀደቁሽ
በእንከፍ አሳባቂዎች መታለብሽ
በደም በአጥንት አነፍናፊ
በዘር ቆጣሪ መቦጨቅሽ
በአራሙቻ አረም ውሃ አጠጪ፣ በስግብግብሽ
መመጠጥሽ
የሚቀርበት ጊዜ ነው የናፈቀኝ…
እንጂ እኔንስ ዛሬን ንሺኝ
ብቻ ለጥቁር አፈርሽ እንደሞትሁ
ጥቁር አፈርሽን አትንፈጊኝ!…
ፊትስ ነፃ ስትሆኚ
ጥቁር አፈርሽን ልግፋ አልሁ እንጂ
መች ልሾም ልሸለም አልሁኝ?
ወደፊትስ ለስሜ እንጂ
መች ለሹመታቸው ቁብ አለኝ!…
እና ልመናዬ አንቺ እማማ!…
ከሹመታቸው ይልቅ ስሜን በላይ አኑሪልኝ
"ሀ" ሲባል " በላይ" ብለሽኛልና " በላይ" ብለሽ
አስታውሺኝ!
ሹመታቸውን ገፈሽ ከስጋዬ አርቀሽ ቅበሪልኝ!
ስሜን ከስራዬ አቆራኝተሽ ከስጋዬ በላይ አኑሪልኝ!
ይኸው ነው የዛሬ ልመናዬ በቀር ሲነጋ ፍረጂኝ!!
በተረፈ አንቺ አገር!
የኔን ጀርባ ለጅራፍ
የነሱን ደሞ ለካባ ሊአደርግ ከሆነ ነፃነትሽ
የጀግና አንገት ለገመድ
የባንዳን ለወርቅ ሀብል ሊዳርግ ከሆነ አርነትሽ
አንቺ ኢትዮጲያ!…
አንቺ ምድር!…
ከርሞ አሳባቂ ቢያመክን ርግማን ማህፀንሽ
ተወልዶ ላይባረክ ነገር ወንድ ልጅ አይውጣብሽ!!

@getem
@getem
@lula_al_greeko
1
ከምኒሊክ ቤት!!!!!!!


በደሞዝ ሞት እንዳትጨርሰው !!!
ከምኒሊክ ቤት ፤
ፋሲል ደመወዝ ፤
ግባ ተብሎ ፣ ወጉ ደረሰው ።
ከደመቀ ጋር ከተዳመቀው ፤
ፋሲል ሲገባ ፤
እንኳን መተማን ቋራን ደነቀው ።
አረሱት ብየ መሬት ድንበሩን ፤
ሰጥተውኝ ነበር መደናገሩን ፥
በደሞዝ ሞት ፤
ፋሲል አይከዳም ፤ እናት ሃገሩን!!!!!
ባገሩ ጃኖ እንደሸለለ ፤
ደሞዝ ይሙት ብሎ እንደማለ ፤
ፋሲል አረሱት ፤
አንጎራጓሪው ፤ የክፉ ቀኑ ፤ እኔ ነኝ አለ ።
አሁን ምን ሊሆን ፤
እንደነ እንትና ፤
በድሉ አጥቢያ ላይ ፤
ፉከራ አብዝቶ ፤ አጉል መወዝወዝ ፤
ያኔ ነው እንጅ ፤
ጀግና ሲጠፋ ፤
አረሱት ብሎ ደሜን ያሞቀው ፤ ፋሲል ደመወዝ ።
እንግዲህ ጎንደር ፤
እስኪ እርገጥ እርገጥ ውረድ አጀባ፤
ከምኒሊክ ቤት ፤
አቦይ ሲባረር ፤ፋሲል ሲገባ ።
በደሞዝ ሞት.....በልልኝ እስኪ.....

(( ጃ ኖ ))💚💛❤️

@balmbaras
@getem
@getem
የሱፍ አበባ ነሽ
( ናትናኤል ጌቱ )
አልተመለከትሽም ?
ሳቅሽ ዘቢብ ሁኖ ፣ ምድሩን ሲያጣፍጠው
የፈገግታሽ ዘሀ ፣ ሁሉን ሲቀይጠው
ሰሌን የነበረው ፣ ለሐፍ ሁኖ ሲያበራ
የበዛ ውበትሽ ፣ ላንቺም እስኪያስፈራ
አይኖችሽ ሲፈኩ፣ ኮኮበ ዝሑራ
መስለው እንደሚያድሩ አልተገነዘብሽም ?
የሱፍ አበባ ነሽ ፣ የበረሀ ኮሽም
...
ንቦቹ ያልቡሻል ፣ አኮሌ ገድበው
ፀሀያቱ ሁሉ ፣ ይሞቁሻል ከበው
የሽቱ አበባዎች ፣ ይምጉሻል ቀርበው
እንዚራሽን ይዘሽ ፣ ለአንባው ሳትዘይሚ
የገረጀ መንፈስ ሳታለመልሚ
ከወዘናሽ በታች ፣ ድንጉል ስትስሚ
ጀንበር ሁነሽ ሳለ ፣ ኩራዝ ተከትለሽ
እንደ ስናር በቅሎ ፣ በዳገቱ ሰግረሽ
እድሜሽን አባክነሽ ፣ እንባ ለብሰሽ ቀረሽ ?
የሱፍ አበባ ነሽ !
...
አየሩን በእጆችሽ ፣ ስትችይ ልትቀዝፊ
አየሁሽ ስትለፊ
ከእርከንሽ ዝቅ ያለ ፣ ለማበጀት አጋር
አጵሎን ሁነሽ ሳለ ፣ ከደርባባዎች ጋር
አኮፋዳ ከፍተሽ ትለማመኛለሽ
ከጠዋት እስከማታ ፀሀይ ተከትለሽ
ማለዳ በምስራቅ ፣ በምዕራብ ምሽቱን
አንገት መቀልበሱን
ተለማምደሽዋል
ሊቅ ሁኖ ተፈጥሮ ፣ ዘሊብ ሁኖ መዋል
ለፀፀት ያልዳረሽ ፣ የሱፍ አበባ ነሽ
ሐር ሁነሽ ሳለ ፣ መደዴ ሸመነሽ !
...
ባንቺ አልተፈወሰም ?
ዝማ ያስጨነቀው ፣ ፈዋሽ ዳማከሴ ?
ዘማዊ ሆንሽና ፣ ልብስሽ የመነኩሴ !
ቢጫ እየለበሱ ፣ ከአንድ ፀሀይ ጋራ
ዝም ብሎ ዳንኪራ … ?
ከቡኒ ክብሽ ላይ ፣ ነጭ ሁኖ ተሰቅሎ
ኮኮብ መሆን ሲችል ፣ ዘርሽ ሆነ ቆሎ !!
የሱፍ አበባ ነሽ ! አንሰሽ አትተከይ
ስለራቀሽ ብቻ ፣ ጀንበር አትከተይ
አይንሽን ብታይ ፣ የብርሀን ምንጭ አለው
ፀሀዮች ይዙሩ ፣ አንቺን ተከትለው
አልተመለከትሽም ? የሱፍ አበባ ነሽ
ሰርፍ ሁነሽ ሳለ ፣ መደዴ ሸመነሽ
ባንገትሽ ሳትዞሪ ፣ የነጋው አይመሽም
አበባ ነሽ የሱፍ ፣ ከረባት የለሽም !
ከስቃይ ተዋደሽ ፣ መንፈስሽ ዋለለ
ዘባተሎ ተባልሽ ፣ ቬሎ ሁነሽ ሳለ
ማር እየከነበልሽ ተጣባሽ ጡት አስጥል
ጨለማ አታፈቅሪም ስለማያቃጥል !
የሱፍ አበባ ነሽ …የሱፍ አበባ ነሽ

@getem
@getem
@lula_al_greeko
"ይድረስ ለሄዋኔ "

ኑሮ እንዴት ይዞሻል እንዴት ነሽ ሄዋኔ
ይመስገን ደህና ነኝ አታስቢ ለእኔ
..................ይልቅስ ሄዋኔ
ወጣትነት አልፎ እርጅና ሳይመጣ
ከቻልሽ ነይልኝ ፡ካልሆነ እኔ ልምጣ
ግን ልትመጪ ከሆነ ፡መንገድ
ሳትጀምሪ
ማንነቴን ሰምተሽ ፡ከቀረሽም ቅሪ
ወደ እኔ ለመምጣት ሀሳብ ስትሰንቂ
የሞላ ቪላ ቤት ፎቅ እንዳትጠብቂ
ጥሪትም የለኝም ወርሼ የማወርስሽ
ቤት ማጀቴ ፡ባዶ ጮማ እንዳላጎርስሽ
ልብሴም ድሪቶ ነው ፡ፊቴም ውበት
የለው
ልቤም የእንባ ናዳ ክህደት ፡ያቆሰለው
ግን ይህን ሁሉ አይተሽ መፀየፍ
ሳይረታሽ
ንፁህ ፍቅሬ ገዝቶሽ ፡ወደ እኔ
ከመጣሽ
እ.ጠ.ብ.ቅ.ሻ.ለ.ሁ........በደስታ
ፈንጥዤ
በሰባራው ልቤ ንፁህ ፍቅርን ይዤ፡፡

@getem
@getem
@gebriel_19
Audio
ቅድስት ሆይ

ገጣሚና አቅራቢ :በሱፍቃድ ዲባባ
ሙዚቃ : ተመስገን እርቁ

@getem
@getem
@lula_al_greeko
~አዋዋል~

እንደ እናቴ ውለሽ + እንደ አባትሽ ሳስብ
ጎጆ ሚቀለሰው ትዳር የሚያ'ብብ

........አሊያ........

ቃና ባየሽ ቁጥር
ከጣደፈሽ ፍቅር
፡ካጣደፈሽ ወኔ፡
፥አልገባኝም ቀንሽ አልገባሽም ቀኔ

''..አ.መ-ሻ.ሽ ወሳኝ ነው..''
ለትዳራችን ጣ'ም ለቤት ቅድስና
~~በነፍሰ-ጡር ኑሮ~~~
ችግር እያነሰ እንዳያምርሽ ዝና
×እስቲ እዪ ዜና×
በየለቱ ...ቀንሽ በየለቱ...ማታ
ቢያንስ.....
እንዳገኛት የልጄ ገላ ላይ የ'-ሀገሬን-' ሽታ፤



@ሰሙ
ተጫረ
ጁምአ..ታህሳስ 19..(2011)
የገብርኤልን ጽዋ....ጠላ እየሞላሁ።

@getem
@getem
@gebriel_19
።እቴ።
(በውቀቱ ስዩም)

ይስጥሽ ከቁመቴ ከላዬ ቀንሶ
ያስረዝምሽ አንቺን እኔን አሳንሶ
ከሰጎን እረዝመሽ ስትቆሚ ከጎኔ
ቁመቴን መጽውቼሽ ጫጩት ላክል እኔ፤
ይስጥሽ ከጸጉሮቼ ከአናቴ ላይ ዘግኖ
ይገጠብ ራሴ ያንቺ ተጎንጉኖ
አወይ ጸጉሯ ብለው ኮረዶች ሲያወሩ
ድጥ ራስ ነህ ብሎ ይዝለፈኝ ሰፈሩ፤
... እቴ
ይስጥሽ ከወዜ ላይ ጨልፎ ከፊቴ
ይቅዳልሽ ከደሜ ጠልቆ ከጅማቴ
ከአይን ያውጣሽ እያለ ሲመርቅ አድናቂ
እስቲ እግዜር ይማርህ ይበለኝ ጠያቂ።

እቴ
እጄን ብትፈልጊ
እግሬን ብትፈልጊ
አንገቴን ደረቴን
ተሰጥኦ ሀሳቤን
ያደምቀኛል ብለሽ ያሰብሺውን ሁላ
እግዜር ከኔ ወስዶ ከሰጠሽ በኋላ
ያስቀርልኝ አይኔን
ያስቀርልኝ አይኔን
አንቺን ማየት ብቻ ያኖረኛል እኔን

@getem
@getem
@gebriel_19
######ምስል####
ስመጣ የሚሄድ ስሄድ የሚመጣ
ቁልቁል አስመልክቶኝ ሽቅብ የሚወጣ
ረጭጭጭ ካለው ውድቅት ምስስጥ ብዬ ሳለሁ
ቀልብ የመግፈፍ አመል ክፋ አባዜ ያለው
ሰርክ የሚመላለስ አሚወደድ እሚጠላ
አሚየሳምም..ደስስ..የሚል እሚሚሚሚመር አሚበላ
............በነጋ በጠባ !!!!
ከች እልም እያለ ልቤን የሚያሸብር
አይ ተናፋቂው ጉድ *ያንቺ -ጥላ* ነገር፡፡
አሸር ሙዜ

@getem
@getem
@gebriel_19
#የወ.ዘ.ተ ግጥም (የዜድ)2011

ኤር or አዲስ
ለምን ይሆን?

የጥላቻ መንገድ፣
የክፋት ግሳንግስ፣
መልህቁን ጥሎብን፣
እንዲ ምንታመስ።
ያንቺ ምቀኝነት ፣
ያንተ መሰሪነት፣
በምን ቢታነፅ ነው?
የማይበገረው የማይፈራርሰው።
መሰረቱ ክፋት ወ.ዘ.ተ መጣላት፣
ሴሰኝነት ጥማት ወ.ዘ.ተ መዳራት፣
ፍትህ በመበደል ወ.ዘ.ተ ማስገደል፣
መሰረቱ ውሸት ወ.ዘ.ተ መፋታት፣
መሰረቱ ገንዘብ ወ.ዘ.ተ መስገብገብ፣
ስሌቱ ጥላቻ ወ.ዘ.ተ እኔ ብቻ፣
መሰረቱ ሰይጣን እንዲ ያስተጣጣን
መሰረቱ ብሔር የኔም ያንቺም መንደር፣
ወዘተ ብልሽት ወ.ዘ.ተ እርግማን፣
ሰርክ የሚያናውዝ እፎይታ ያስጠማን።


ለሰውነት ልኩ ለ ህይወቱ ማገር ፣
አስማምቶ ሚያኖረው ፣
ቅን ወ.ዘ.ተ እምነት ነው።
ሌት ተቀን ቢደከም ሰው ባካል ቢለፋ፣
ነገን የሚያኖረው ፣
ያ ወ.ዘ.ተ ተስፋ።
በምድር ስንኖር፣
እውነትን ከምህረት ተስፋና እምነትን
መሰረት አደርጎ ውስጣችን ካበተ ፣
ነገን እናያለን በእፎይታ የሚያኖር
የፍቅር ወ.ዘ.ተ።✌️❤️


@getem
@getem
ሰባራ_እድል
.
እኔስ ስዬው ነበር ፥ ቀኔን በአምሳሌ
ግን አልገጥም አለኝ፥ ሰባራው እድሌ።
.
እጄን ባወናጭፍ ፥ ተራራው ፈለሰ
እፊቱ ባነጥስ ፥ አለት ተገመሰ።
ኮቴዬን ሲሰማ ፥ ሐረግ በግሩ ቆመ
ሰላምታ ሊሰጠኝ ፥ ዘንባባ ዘመመ።
.
ለእንጀራ ስኳትን ፥ ወረደልኝ መና
ለፈረስ ታጥቄ ፥ ሄድኩኝ በደመና።
የታመንኩት በትር ፥ ከጄ 'ማልነጥለው
አምልጦኝ ቢወድቅ ፥ ባህሩን ከፈለው።
.
ኧረ ኤድያ! ....
.... ኧረ የለም! ...
የለም! ... የለም! የለም!
የቱም ሥር አልያዘም
ኣንዱስ እንኳ አልሆነም
የወጠንኩት ሁሉ
አ-ል-ተ-ከ-ና-ወ-ነ-ም።
.
የሰመረ ቢኖር
የያዘልኝ ነገር ፥ ከንጋት ምኞቴ
በሰላም አውለኝ ፥ የሚለው ጸሎቴ።
-------------------//---------------------
( በርናባስ ከበደ )

@getem
@getem
@gebriel_19
ሞኝ ፍቅር
..
ለሱ!
ሰው ብቻ አይደለችም..
ጠፈር ናት ባካሏ፥መሬት ናት በነፍሷ፤
ዕድሜልኩን ቢሮጥ አያመልጥም ከሷ።
..
© በዕውቀቱ ስዩም
የግጥም አምባ
@getem
@getem
@gebriel_19
💚💛❤️💚💛❤️💚💛💖

እንቺ ሰላንቲያ
( በላይ በቀለ ወያ)
.
.
እንቺ ሰላንቲያ
በምንቲያ
በቋራ
ምን አለ በቋራ
ቆራጡ ገብርዬ ፣
የአፄ ቴዎድሮስን ፣ ሹሩባ እየሰራ
ያገር ፍቅርን እና
የህዝቧን አንድነት ፣ ባንድ እያዋኀደ
ቴዎድሮ አናት ላይ ፣ አንድ አርጎ ገመደ
ጎንጉኖ ሳይጨርስ
ከቋራ ተነስቶ ፣ ወደ ጋፋት ሔደ፡፡
፡፡፡፡
እንካ ሰላንትያ
በምንቲያ
በጋፋት
ምን አለ በጋፋት
ሀገር ያላወቀው ፣ የገብርዬ ጥፋት
ጉንጉኑን ረስቶ ፣ ለመድፍ መጋፋት፡፡
ገብርዬ ጨርሶ ፣
የቴዎድሮስን ፀጉር ፣ ስላልጎነጎነ
አንድ የቀረ ጉንጉን ፣ የተበታተነ
ለእንግሊዞች ጦር....
መቅደላ ማድረሻ ፣ ፅኑ መርከብ ሆነ፡፡
"
እንኪ ሰላንትያ
በምንትያ
በመቅደላ
ምናለ በመቅደላ
ያኔ ማንም የለም ፣
ከእንግሊዝ ጦርና ፣ ከቴዎድሮስ ሌላ
የሚወደው ቀኙ ፣ ገብርዬ እጁ ዝላ
የሚወዳት ሰንደቅ ፣
በወንበዴ መሐል ፣ እያየ ተሰቅላ
ግራው ሲኮንናት ፣ ቀኙ ሲያወድሳት
አንድ ጀግና ሞተ ፣ አንድ ሀገር ለማንሳት፡፡
፡፡፡፡፡፡
እንካ ሰላንትያ
በምንትያ
በአንድ ሀገር
ምን አለ በአንድ ሀገር
ዛሬ ላይ ከፋፍሎ ፣ የሚያፋጀን በዘር
አለ ብዙ ነገር
በደም የሚያጣባን ፣ አለ ብዙ መዥገር
ተጣብቆ ሚመጠን
ፀሐይ እየሸጠ ፣ ኩራዝ የሚሰጠን
አለ ብዙ ብዙ
ባለፈ ጠባሳ ፣ አዲስ ቁስል ሰጪ
ነፃነት ሳያውቅ
ነፃ አውጪ ነኝ የሚል ፣ መሀይም ነፃ አውጪ
ጥበብ ማይታየው ፣ ከጠብመንጃ ውጪ
አለ ብዙ ብዙ
ክብር ምን እንደሆን ፣ የማያቅ ደንቆሮ
ሲነኩን ዝም ብሎ
ሳይነኩት የሚጮህ ፣ አምሳለ ቆርቆሮ
የድል አጥቢያ አርበኛ
አፉ ክፍት የሆነ ፣ ባለ ድፍን ጆሮ
አለ ብዙ ቡዙ
💚💛❤️

@getem
@getem
@gebriel_19
የዕንባ ስንኞች 2...
_____
(እዮብ ዘ ማርያም)
.
ስኬቴን ባገኘው፣
ከሰማይ ጠቀስ ዛፍ ወደ ምድር ወርዶ
አንቺ የሌለሽበት ሁሉም ነገር ባዶ

የሀብት ተራራ፣
ጉጆዬን በጥጋብ ቢያረሰርሰው
እንዴት አድርጌ ነው፣?
ምላስ በሌለበት ስኳርን ምቀምሰው፡፡

ያለምንም እረፍት፣
ልቤ በየቀኑ በዲን እሳት ያራል
አይኔ ዕንባ አዝሎ ሀዘኔ ይከራል
ራሴን ልጠይቅ፣
ደሜ አንቺ ከሌለሽ ደም ስር ምን ይሰራል

ዳግም እንዳገኝሽ የናፍቆት ሀገሬን
ደሜ አንቺ ከራቅሽኝ አንግበሽው ፍቅሬን
በቃኝ መኖር በቃኝ፣
ወዳንቺ እንድመጣ ልቁረጠው ደም ስሬን


@getem
@getem
@gebriel_19
የፊታችን ሐሙስ

ሰም እና ወርቅ
ድንቅ ምሽት እንዲያሳልፉ ተጋብዘዋል።
መግቢያ 100 ብር
መገናኛ ቫምዳስ ሲኒማ

@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
»»» ቅኝት_ትዝታዬ ««

ገላሽ ሙዚቃ ነው ሰውነትሽ ኖታ
ሲነካኩት ዘፈን ሲለዩት ትዝታ።

#ezana

@getem
@paappii
ሀገር ሲናፍቀን የምንዘፍነው ዘፈን
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ስለመግባባት አውርተን ፣ አለመግባባት ሲተርፈን
ላንድነታችን ተሟግተን ፣ ልዩነታችን ሲጠልፈን
ህዝቦቿ ሆነን ሳንሆን ፣ የሀገር ናፍቆት ሲገርፈን
‹‹እህህ›› እያልን
‹‹ዋሆዬ›› እያልን
‹‹አሄሄ›› እያልን ፣ እንዘፍናለን ዘፈን፡፡
……………………………….
ለ‹‹ፍቅር›› ባልነው መሰረት ፣ ‹‹ጥላቻ›› ተክለን ስናንፅ
‹‹እኔ›› የሚለው ቅፅ ይዞ ፣ ‹‹እኛ›› የሚለው ሲያጣ ቅርፅ
በምድረ በዳ ጆሮ ላይ ፣ አዳማጭ ባጣ ብኩን ድምፅ
ዘፈን እንዘፍናለን
‹‹ እህህ ፣ዋሆዬ ፣ አሄሄ›› እንላለን፡፡
…………………………………………
/አዝማች/ ‹‹እህህ ፣ ዋሆዬ ፣ አሄሄ/
……………………………………….
‹‹ጠጥተን ሳለ ሚጠማን ፣ እየተመገብን ሚርበን
እየለበስን ሚበርደን ፣ እሳት ዳር እሳት ደርበን
በተቀባነው ሳንወዛ ፣ ብናጌጥ የማያምርብን
ምን ጉድ ነው ምን ፈረደብን?››
እያልን እንዘፍናለን…..
ያልጎደለንን ስንሞላ ፣ ፀጋና ፍቅር ገድሎብን፡፡


@getem
@getem
@gebriel_19
#ምን_ላርግልሽ

ምን ላርግልህ ብለሽ
                 ዘፈን የዘፈንሽው፡
ምታደርጊለትን አንችስ
                 መች አጣሽው፡፡
"ምን ላርግልህ" ብለሽ
               ሰው ከማደናበር፡
"ምን ላርግህ" ብትይው፡
               እናደንቅሽ ነበር፡፡

አብዱ ራህማን

@getem
@getem
@gebriel_19
😁1
አስረሽ ፍችው
.
#Dave
/
አፍቅረሽ ስትተይኝ~አፍቅሬሽ ተቀጣሁ
እሱን ስትፈልጊ
እኔም በተራዬ ~ልፈልግሽ ወጣሁ
ክብር ይሁንና
አንችን ከሱ ጋራ~ላገናኘ ፍቅር
በመፈለጌ ውስጥ
ማንነቴን ጥዬ ~ሳላገኝሽ ብቀር
ለካስ ባንች ሰበብ
ራሴን ፈልጌ~እያገኘሁ ነበር

@getem
@getem
@gebriel_19