ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#የአንድ_አፈር_አፈሮች

ፍቅራችንን
ድንበር ወሰን ላይገድበው
ሁለት ክልል ላይመጥነው
መገዳደል ፍት' ላይሆነው
በሽንፈትህ እሠይ ላልል
በሽንፈቴ እፎይ ላትል
ከቂም በቀል ፍቅር ላይበቅል
ልጅህ በእጄ ለምን ይሙት
ልጄስ በእጅህ ለምን ትሙት
እኔና አንተ እኮ
የአንድ እናት ልጆች
ወንድማማቾች
ያንድ አፈር አፈሮች
ርስት አፈሩማ
ይቅርም ከወደዚህ ይሂድም ወደዚያ
ያው ነው የኢትዮጵያ ያንድ አፈር መጠሪያ
ወዲያ ካለው የቀድሞዋ ወዲህ ካለው የእስካሁኗ
ግዳይ ጥዬ በልጅህ ደም በጀግንነት ላልጠራ
ግዳይ ጥለህ በልጄ ደም ላትፎክር ላታቅራራ
ወንድም ገድለው ላይፎክሩ
ጀብዱ ሰርተው ላይኩራሩ
ያዘን ሙሾ ሊዘምሩ
እንደ ማተብ የእምነት ክር ፍቅር ድሩ ላይበጠስ
ባዘናችን ላትዘፍኑ በሞታችሁ ላንደንስ
ስሙር አይሁን ነጭ ሴራው ደስ አይበለው የጠላት ነፍስ
ልጅህ አይሙት በልጄ ጣት
ልጄም አይሙት በልጄ ቀስት
እኔና አንተ እኮ
ከዘመናት በፊት
በታሪክ በሃይማኖት
በባህል በትውፊት
በደስታ በችግር
ስም የለሽ ስመ-ጥር
በጋሻና በጦር ጀብደኛ ባላገር
ያንድ አያቶች ዘር የሁለት አፈር ሠፈር
ስም የለሽ በጥጋብ
ስመ-ጥር በረሃብ
እያሉ ሲተቹህ እያሉ ሲተቹን
በሙጫ ስድብ አጣብቀውን
ሲተቹን መተቸት ሲተቹን መተቸት
እንዳለ ስናውቀው እንዳለ ስታውቁት
ካንድ እናት ተወልደን በሁለት አባት አድገን
አንድ ውሃ ተራጭተን አንድ አፈር አቡክተን
ቃታ ስንሳሳብ
እሺ ላይለው ልብህ ደስ ላይለው ልቤን
እኮ እንዴት እኔና አንተ ዛሬ እንዲህ እንጫከን
እኔና አንተ እኮ
ያንድ እናት ልጆች
ወንድምና እህቶች
ያንድ አፈር አፈሮች
እናም ወንድም ስማኝ ልስማህ
ደስ አይበለው ነገር ሰሪ አንተን ከኔ ጸብ ሲያቃባ
እንዘምር ባንድ እንዝለል ወሰን አይኑር የደም ካባ
በመሞትህ ደስ ላይለኝ ውስጥ ልቤ እዥ ሊያነባ
የናቱ ልጅ ልጅህ ገድሎ ላያሰማ ጉሮ ወሸባ
ፍቅር እንጂ ግድባችን ወሰን አይኑር የደም ካባ
ይልቅስ ልንገርህ
ኩራቴ ኩራትህ
ታሪኬ ታሪክህ
የሚያመጻድቀኝ የሚያመጻድቅህ
የኔም ያባቴ ነው ያንተም የአባትህ
ከቢዘን ባስቀድስ ከግሸን ብትሰልስ
በአክሱም ብትኮራ
ብሸልል በአስመራ
ያንተ አባት አባቴ አባቴ አባትህ
የሚያመያጻድቀኝ የሚያጻድቀኝ ታሪኬ ታሪክህ
መሆኑን ስናውቀው መሆኑን ስታውቁት
በደምና ባጥንት በስጋ በጅማት በታሪክ በትውፊት
መንታ ናቸው ሲሉን
እኮ እንዴት እኔና አንተ ዛሬ እንዲህ እንጫከን
በብቀላ ጸጸት በቀር ወንድም ጥሎ ላይፎክር
ጀግና ተብሎ ሜዳይ ላይኖር
በናቴ ልጅ በመጨከን እሺ ላይለኝ የልቤ በር
ወንድ ልጄን ግዳይ ጥለህ ላይፈታ የደምህ ስር
ካንድ ደብር አድገን በአንድ አስቀድሰን አንድ ዳዊት ደግመን
ካንድ መስጊድ ኖረን ባንድ ሰላት አድገን አንድ ቁርዓን ቀርተን
እኮ እንዴት እኔና አንተ ዛሬ እንዲህ እንጫከን
ለጉዳትህ ተሰዉቼ
ላንተ ክብር ብዙ ሞቼ
ስላንተ ነጻነት ካገርህ ደሜ አለ
በናቕፋ ተራሮች እቅፍ የታዘለ
መጎዳቴን እምቢ ብለህ
ስለ ክብሬ ተሰውተህ
የሰጠኸኝ ክቡር ደምህ
ያንተም አጽም ዓድዋ አለ
ለጦቢያ ነጻነት ስለኔ የዋለ
መንታ ናቸው ሲሉን
ፍቅር ናቸው ሲሉን
እያወቁት ልቦናችን
ሁለት ክልል ላይመጥነን
ድንበር ወሰን ላይገድበን
መገዳደል ፍት' ላይሆነን
በሽንፈትህ ስንዘምር "በለው" ያሉን ሊታዘቡን
ነጭ ሴራ ወጣው ሊሉን
ስጋ ክንድህ ሲደማብህ ልቦናችን ሊያዝብን
ባለም ዜና ድላችንን ደም ጥማት ነው ብለው ሊሉን
ልጅህ በጄ ለምን ይሙት
ልጄስ በእጅህ ለምን ይሙት
ስማኝ ወገን
ደስ አይበለው ነገር ሰሪ አንተን ከኔ ጸብ ሲያቃባ
እንዘምር ባንድ እንዝለል ወሰን አይኑር የደም ካባ
ርስት አፈሩማ
ይቅርም ከወደዚህ ይሂድም ወደዚያ
ያው ነው የኢትዮጵያ ያንድ አፈር መጠሪያ
ወዲያ ካለው የቀድሞዋ ወዲህ ካለው የእስካሁኗ
እናም በሞቱት ሞት
እኔና አንተ አንሙት
እኔና አንተማ
የአንድ እናት ልጆች
ወንድምና እህቶች
ያንድ አፈር አፈሮች
#ኤፍሬም_ስዩም

@getem
@getem
@getem
👍1
#የአንድ_አፈር_አፈሮች
#ኤፍሬም_ስዩም



ፍቅራችንን
ድንበር ወሰን ላይገድበው
ሁለት ክልል ላይመጥነው
መገዳደል ፍት' ላይሆነው
በሽንፈትህ እሠይ ላልል
በሽንፈቴ እፎይ ላትል
ከቂም በቀል ፍቅር ላይበቅል
ልጅህ በእጄ ለምን ይሙት
ልጄስ በእጅህ ለምን ትሙት
እኔና አንተ እኮ
የአንድ እናት ልጆች
ወንድማማቾች
ያንድ አፈር አፈሮች
ርስት አፈሩማ
ይቅርም ከወደዚህ ይሂድም ወደዚያ
ያው ነው የኢትዮጵያ ያንድ አፈር መጠሪያ
ወዲያ ካለው የቀድሞዋ ወዲህ ካለው የእስካሁኗ
ግዳይ ጥዬ በልጅህ ደም በጀግንነት ላልጠራ
ግዳይ ጥለህ በልጄ ደም ላትፎክር ላታቅራራ
ወንድም ገድለው ላይፎክሩ
ጀብዱ ሰርተው ላይኩራሩ
ያዘን ሙሾ ሊዘምሩ
እንደ ማተብ የእምነት ክር ፍቅር ድሩ ላይበጠስ
ባዘናችን ላትዘፍኑ በሞታችሁ ላንደንስ
ስሙር አይሁን ነጭ ሴራው ደስ አይበለው የጠላት ነፍስ
ልጅህ አይሙት በልጄ ጣት
ልጄም አይሙት በልጄ ቀስት
እኔና አንተ እኮ
ከዘመናት በፊት
በታሪክ በሃይማኖት
በባህል በትውፊት
በደስታ በችግር
ስም የለሽ ስመ-ጥር
በጋሻና በጦር ጀብደኛ ባላገር
ያንድ አያቶች ዘር የሁለት አፈር ሠፈር
ስም የለሽ በጥጋብ
ስመ-ጥር በረሃብ
እያሉ ሲተቹህ እያሉ ሲተቹን
በሙጫ ስድብ አጣብቀውን
ሲተቹን መተቸት ሲተቹን መተቸት
እንዳለ ስናውቀው እንዳለ ስታውቁት
ካንድ እናት ተወልደን በሁለት አባት አድገን
አንድ ውሃ ተራጭተን አንድ አፈር አቡክተን
ቃታ ስንሳሳብ
እሺ ላይለው ልብህ ደስ ላይለው ልቤን
እኮ እንዴት እኔና አንተ ዛሬ እንዲህ እንጫከን
እኔና አንተ እኮ
ያንድ እናት ልጆች
ወንድምና እህቶች
ያንድ አፈር አፈሮች
እናም ወንድም ስማኝ ልስማህ
ደስ አይበለው ነገር ሰሪ አንተን ከኔ ጸብ ሲያቃባ
እንዘምር ባንድ እንዝለል ወሰን አይኑር የደም ካባ
በመሞትህ ደስ ላይለኝ ውስጥ ልቤ እዥ ሊያነባ
የናቱ ልጅ ልጅህ ገድሎ ላያሰማ ጉሮ ወሸባ
ፍቅር እንጂ ግድባችን ወሰን አይኑር የደም ካባ
ይልቅስ ልንገርህ
ኩራቴ ኩራትህ
ታሪኬ ታሪክህ
የሚያመጻድቀኝ የሚያመጻድቅህ
የኔም ያባቴ ነው ያንተም የአባትህ
ከቢዘን ባስቀድስ ከግሸን ብትሰልስ
በአክሱም ብትኮራ
ብሸልል በአስመራ
ያንተ አባት አባቴ አባቴ አባትህ
የሚያመያጻድቀኝ የሚያጻድቀኝ ታሪኬ ታሪክህ
መሆኑን ስናውቀው መሆኑን ስታውቁት
በደምና ባጥንት በስጋ በጅማት በታሪክ በትውፊት
መንታ ናቸው ሲሉን
እኮ እንዴት እኔና አንተ ዛሬ እንዲህ እንጫከን
በብቀላ ጸጸት በቀር ወንድም ጥሎ ላይፎክር
ጀግና ተብሎ ሜዳይ ላይኖር
በናቴ ልጅ በመጨከን እሺ ላይለኝ የልቤ በር
ወንድ ልጄን ግዳይ ጥለህ ላይፈታ የደምህ ስር
ካንድ ደብር አድገን በአንድ አስቀድሰን አንድ ዳዊት ደግመን
ካንድ መስጊድ ኖረን ባንድ ሰላት አድገን አንድ ቁርዓን ቀርተን
እኮ እንዴት እኔና አንተ ዛሬ እንዲህ እንጫከን
ለጉዳትህ ተሰዉቼ
ላንተ ክብር ብዙ ሞቼ
ስላንተ ነጻነት ካገርህ ደሜ አለ
በናቕፋ ተራሮች እቅፍ የታዘለ
መጎዳቴን እምቢ ብለህ
ስለ ክብሬ ተሰውተህ
የሰጠኸኝ ክቡር ደምህ
ያንተም አጽም ዓድዋ አለ
ለጦቢያ ነጻነት ስለኔ የዋለ
መንታ ናቸው ሲሉን
ፍቅር ናቸው ሲሉን
እያወቁት ልቦናችን
ሁለት ክልል ላይመጥነን
ድንበር ወሰን ላይገድበን
መገዳደል ፍት' ላይሆነን
በሽንፈትህ ስንዘምር "በለው" ያሉን ሊታዘቡን
ነጭ ሴራ ወጣው ሊሉን
ስጋ ክንድህ ሲደማብህ ልቦናችን ሊያዝብን
ባለም ዜና ድላችንን ደም ጥማት ነው ብለው ሊሉን
ልጅህ በጄ ለምን ይሙት
ልጄስ በእጅህ ለምን ይሙት
ስማኝ ወገን
ደስ አይበለው ነገር ሰሪ አንተን ከኔ ጸብ ሲያቃባ
እንዘምር ባንድ እንዝለል ወሰን አይኑር የደም ካባ
ርስት አፈሩማ
ይቅርም ከወደዚህ ይሂድም ወደዚያ
ያው ነው የኢትዮጵያ ያንድ አፈር መጠሪያ
ወዲያ ካለው የቀድሞዋ ወዲህ ካለው የእስካሁኗ
እናም በሞቱት ሞት
እኔና አንተ አንሙት
እኔና አንተማ
የአንድ እናት ልጆች
ወንድምና እህቶች
ያንድ አፈር አፈሮች

©ገጣሚ #ኤፍሬም_ስዩም

@getem
@getem
#የአንድ_አፈር_አፈሮች
(ኤፍሬም ስዩም)
ፍቅራችንን
ድንበር ወሰን ላይገድበው
ሁለት ክልል ላይመጥነው
መገዳደል ፍት' ላይሆነው
በሽንፈትህ እሠይ ላልል
በሽንፈቴ እፎይ ላትል
ከቂም በቀል ፍቅር ላይበቅል
ልጅህ በእጄ ለምን ይሙት
ልጄስ በእጅህ ለምን ትሙት
እኔና አንተ እኮ
የአንድ እናት ልጆች
ወንድማማቾች
ያንድ አፈር አፈሮች
ርስት አፈሩማ
ይቅርም ከወደዚህ ይሂድም ወደዚያ
ያው ነው የኢትዮጵያ ያንድ አፈር መጠሪያ
ወዲያ ካለው የቀድሞዋ ወዲህ ካለው የእስካሁኗ
ግዳይ ጥዬ በልጅህ ደም በጀግንነት ላልጠራ
ግዳይ ጥለህ በልጄ ደም ላትፎክር ላታቅራራ
ወንድም ገድለው ላይፎክሩ
ጀብዱ ሰርተው ላይኩራሩ
ያዘን ሙሾ ሊዘምሩ
እንደ ማተብ የእምነት ክር ፍቅር ድሩ ላይበጠስ
ባዘናችን ላትዘፍኑ በሞታችሁ ላንደንስ
ስሙር አይሁን ነጭ ሴራው ደስ አይበለው የጠላት ነፍስ
ልጅህ አይሙት በልጄ ጣት
ልጄም አይሙት በልጄ ቀስት
እኔና አንተ እኮ
ከዘመናት በፊት
በታሪክ በሃይማኖት
በባህል በትውፊት
በደስታ በችግር
ስም የለሽ ስመ-ጥር
በጋሻና በጦር ጀብደኛ ባላገር
ያንድ አያቶች ዘር የሁለት አፈር ሠፈር
ስም የለሽ በጥጋብ
ስመ-ጥር በረሃብ
እያሉ ሲተቹህ እያሉ ሲተቹን
በሙጫ ስድብ አጣብቀውን
ሲተቹን መተቸት ሲተቹን መተቸት
እንዳለ ስናውቀው እንዳለ ስታውቁት
ካንድ እናት ተወልደን በሁለት አባት አድገን
አንድ ውሃ ተራጭተን አንድ አፈር አቡክተን
ቃታ ስንሳሳብ
እሺ ላይለው ልብህ ደስ ላይለው ልቤን
እኮ እንዴት እኔና አንተ ዛሬ እንዲህ እንጫከን
እኔና አንተ እኮ
ያንድ እናት ልጆች
ወንድምና እህቶች
ያንድ አፈር አፈሮች
እናም ወንድም ስማኝ ልስማህ
ደስ አይበለው ነገር ሰሪ አንተን ከኔ ጸብ ሲያቃባ
እንዘምር ባንድ እንዝለል ወሰን አይኑር የደም ካባ
በመሞትህ ደስ ላይለኝ ውስጥ ልቤ እዥ ሊያነባ
የናቱ ልጅ ልጅህ ገድሎ ላያሰማ ጉሮ ወሸባ
ፍቅር እንጂ ግድባችን ወሰን አይኑር የደም ካባ
ይልቅስ ልንገርህ
ኩራቴ ኩራትህ
ታሪኬ ታሪክህ
የሚያመጻድቀኝ የሚያመጻድቅህ
የኔም ያባቴ ነው ያንተም የአባትህ
ከቢዘን ባስቀድስ ከግሸን ብትሰልስ
በአክሱም ብትኮራ
ብሸልል በአስመራ
ያንተ አባት አባቴ አባቴ አባትህ
የሚያመያጻድቀኝ የሚያጻድቀኝ ታሪኬ ታሪክህ
መሆኑን ስናውቀው መሆኑን ስታውቁት
በደምና ባጥንት በስጋ በጅማት በታሪክ በትውፊት
መንታ ናቸው ሲሉን
እኮ እንዴት እኔና አንተ ዛሬ እንዲህ እንጫከን
በብቀላ ጸጸት በቀር ወንድም ጥሎ ላይፎክር
ጀግና ተብሎ ሜዳይ ላይኖር
በናቴ ልጅ በመጨከን እሺ ላይለኝ የልቤ በር
ወንድ ልጄን ግዳይ ጥለህ ላይፈታ የደምህ ስር
ካንድ ደብር አድገን በአንድ አስቀድሰን አንድ ዳዊት ደግመን
ካንድ መስጊድ ኖረን ባንድ ሰላት አድገን አንድ ቁርዓን ቀርተን
እኮ እንዴት እኔና አንተ ዛሬ እንዲህ እንጫከን
ለጉዳትህ ተሰዉቼ
ላንተ ክብር ብዙ ሞቼ
ስላንተ ነጻነት ካገርህ ደሜ አለ
በናቕፋ ተራሮች እቅፍ የታዘለ
መጎዳቴን እምቢ ብለህ
ስለ ክብሬ ተሰውተህ
የሰጠኸኝ ክቡር ደምህ
ያንተም አጽም ዓድዋ አለ
ለጦቢያ ነጻነት ስለኔ የዋለ
መንታ ናቸው ሲሉን
ፍቅር ናቸው ሲሉን
እያወቁት ልቦናችን
ሁለት ክልል ላይመጥነን
ድንበር ወሰን ላይገድበን
መገዳደል ፍት' ላይሆነን
በሽንፈትህ ስንዘምር "በለው" ያሉን ሊታዘቡን
ነጭ ሴራ ወጣው ሊሉን
ስጋ ክንድህ ሲደማብህ ልቦናችን ሊያዝብን
ባለም ዜና ድላችንን ደም ጥማት ነው ብለው ሊሉን
ልጅህ በጄ ለምን ይሙት
ልጄስ በእጅህ ለምን ይሙት
ስማኝ ወገን
ደስ አይበለው ነገር ሰሪ አንተን ከኔ ጸብ ሲያቃባ
እንዘምር ባንድ እንዝለል ወሰን አይኑር የደም ካባ
ርስት አፈሩማ
ይቅርም ከወደዚህ ይሂድም ወደዚያ
ያው ነው የኢትዮጵያ ያንድ አፈር መጠሪያ
ወዲያ ካለው የቀድሞዋ ወዲህ ካለው የእስካሁኗ
እናም በሞቱት ሞት
እኔና አንተ አንሙት
እኔና አንተማ
የአንድ እናት ልጆች
ወንድምና እህቶች
ያንድ አፈር አፈሮች
------ * * * ------

@getem
@getem
@getem
1👍1