ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ራስን መሆን
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
እኔ "እኔ"ን ብሆን፤
ራሴን ጠንስሼ፤ከራሴ አብራክ፤
ራሴን ወልጄ፣
ራሴን ፈቅጄ፤
ራሴን ወድጄ፤
ከዕውቀት በለስ ዛፍ ራሴን አግጄ፤
ራስን ለመፍጠር፤
ራስን ለማንጠር፤
በሕይወት ሚስጥራት "እኔ"ን ብወጥር፤
ሁሉ ትርጉም አልባ፤
በራሪ ገለባ፤
የትም 'ሚገባ!
እና?
እኔ "እኔ"ን ብሆን
አልችልም ሰው መሆን!!!
.

@getem
@getem
@lula_al_greeko
የስንብት ዑደት
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
ቅር እያለው፤
የመለየት ሲቃ፤
የስንብት ዑደት፣ደልቆ እያመሰው፤
ደህና ሰንብች ብዬ ልሳኔን ስወቅሰው፤
"እንኳን ደህና መጣህ!" 'ምትል
አገኘሁ ሌላ ሰው!
የስንብት ዑደት፤
መለያያ መንገድ በርክቶ ባለበት፤
አዲስ ሆኖ አያውቅም
"ደህና ሰንብች" ማለት!
ስንብት ወንዝ ሆኖ. . .
የኋሊት እየናጠ ኑሮዬን ቢከልሰው፤
እንደ ገሃ አፈር ለሁለት ቢገምሰው፤
ጥያቄዬ ሌላ ነው. .
"ተክታሽ የመጣች፤
በምስራቄ የወጣች፤
የትዝታሽን አልቦ ከኔ የሰበረች
እሷ ግን ማን ነች?
የትስ ነበረች?"
መጥታ እስክትሄድ፤እስክትሰናበተኝ
የትዝታዎች አልቦ እያንከራተተኝ
ካንዷ ምህዋር ነቅሎ፣ሌላ ላይ ከተተኝ!
ቀድሞም. . .
ፍቅር በነፍሴ አድራ፤ትንቢቴን ስናገር
ሕይወት ይቀጥላል፤
ፍቅር ይቀጥላል፤ብዬሽም አልነበር?
.


@getem
@getem
@huluezih
ብዥታ ሕይወት
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
ያልደረቀ እንባ
ያልደረቀ ቁስል
የፈጣሪን ቁጣ
ፍርዱን የሚመስል!
.
የባጀ ሕሊና
እረፍት አልባ ብክነት
የሟጠጠ ተስፋ
የማይነሱት ውድቀት!
.
የተረሳ ሕልም
የታቀፈ ረመጥ
እያሉ መገለል
በሰው ተስፋ መቁረጥ
.
የማስመሰል እውነት
የድመት ምናኔ
የተዛባ ሐሳብ
"ይኽ ዓለም ለምኔ?"

የመላዕከ ሞት ጥሪ
የገሃነም ጫፍ ጨዋታ
የገነት ማፈግፈግ
የኑሮ መተታ!
.
የመነጎልኩት ሁሉ፤የተጻፉት ሁሉ . . .
በሕይወቴ ውስጥ አሉ!
ውድቀቴም. . .
የቁም ሞቴም. . .
ድካሜና ብክነቴም. . .
ያንቺው መሄድ ነው. . .
የሄደ እግርሽን ዳና ተከትሎ
ካስለመድሺው አድባር አንቺ የለሽ ብሎ
መዓት ሰፈረብኝ መዓቱን ጠቅልሎ!
.
@huluezih
@getem
@getem
👍1
የስቲከር ግጥም
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
አንቺ ዘመናይ ነሽ ሥልጡን 'ምትወጂ፤
ደስታ እና ኅዘንሽን በስቲከር ምታውጂ
እኔ ሆደ-ባሻ፤
ካልነኩኝ ማልገኝ እንደ ጠላት ፈንጂ!
ቃላትን ትቼ. . .
ስንኞችን ትቼ. . .
ባንቺ የነፍስ ቋንቋ ቋንቋዬ እንዲገባሽ፣
በስቲከር ላስረዳሽ!
እና እንደዚህ ነው. . .
.
😳😍🤔💋
😱😏🤭😘💋
🤷‍♂🤝👋👂👥
🗣👥👨‍🔧👥!!!!
.
❤️👭💑😡😞
🙅‍♀👰🤵🤰🤱
💔🏳
😕🏳
🙈🙉🙊⚠️
😭😖⚠️⚠️⚠️!!!
.
(ገባሽ?😡)

@AM_HERE -COMMENT




.
@huluezih
@getem
@getem
የነበረኝ የለም፣ያለኝ አልነበረም!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
ወደ ውስ ጤ ገባሁ. . .
የውስጤ ውስጥ ላይ ዘልቄ ተገኘሁ!
ያገኘሁት ገረመኝ. . .
ያጣሁት አመመኝ!
ድር የዋጠው ትዝታ፤
ያልበላሁት ገበታ፤
የተረሱ ሰዎች፣
የአደራ ልቦች፣
ዳር-አልባ ናፍቆት፤
ያልታቀደ ስርቆት፣
ያልተፈታ እንቆቅልሽ፣
'ሚያስፈራ አባርሮሽ፣
ያላለቀ መንገድ፤
የፈረሰ መውደድ፣
ቆራሌው ማንነት፣
ውሸት ብቻ እውነት!
የነበረኝ የለም
ያለኝ አልነበረም፣
ሊኖረኝ የቃጣው መኖር አልጀመረም!
በዚህ ሁሉ መሐል. . .
ያጣሁት ምን ቢያመኝ
የቀረው ቢገርመኝ፣
ቁም-ነገር ፍለጋ፣
የውስጠኛዬን ባሕር፣ቀዝፌ ስዋኘው፣
እንደ ክራር ክሮች፣ድርድሩን ስቃኘው፣
የሚረባኝ ነገር ራሴን ብቻ አገኘሁ!
.
@huluezih

@getem
@getem
@getem
👍1
እንቅልፌን ፈራሁት!
.
(#ፈይሠል_አሚን)

ዓይኖቼን ሊዘጋ እንቅልፌ ሲታገል፤
‹‹ባልነቃስ›› የሚል ስጋት ለልቤ ሲታደል፤
እንቅልፌን ፈራሁት. . .
ዓይኔን አቆየሁት።
ሰው ግን ይደንቃል. . .
ዕጣውን እንዳወቀ ከገሚስ ሞት ተጋጥሞ
‹‹ነገ እንገናኝ›› ይላል
ከመተኛቱ ቀድሞ!
አሁን ሸለብ አርጎኝ ደግሜ ባልነቃስ?
ከሰጠምኩበት ዓለም ዳግመኛ ባልወጣስ?
ዛሬን ከሔድኩበት ለነገ ባልመጣስ?
እንቅልፍ ፍርሃቴን እውን ካደረገ
የምጠብቀው ቀን ይቀር ይሆን ነገ?
እንጃ!
እንቅልፌን ፈራሁት ደግሜ ባልነቃስ?
የተስፋዬ መንገድ ተኝቼ ቢያበቃስ?
ዘወትር ያሸልባል፤አይ ሰው መከረኛው
እንቅልፍን አምኖ እንዴት ነው ‘ሚተኛው?
.
@getem
@getem
@huluezih
ከሔድኩ አልመጣም!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
"አትግፋኝ!"ብዬህ ነበር መዘዙን ፈርቼ፤
"አትንኪው!" ብያለሁ ቁስሌን አሳይቼ፤
"ጠግበው እንደናቁት እንደጣሉት እህል
እስከ ጥግ አይችሉም ሰዎች የኔን ያህል!"
ታግሼ. . .
አብሼ. . .
ስከፋ. .
በይሆናል ተስፋ. . .
ባልፍም በጥሞና ቃላት ባላወጣም፣
ሳይገፉኝ አልሔድም
ከሔድኩም አልመጣም!
ተንቄ. . .
ወድቄ. . .
ደቅቄ. . .
ሳልጀምር አልቄ. . .
ፈርጄ እሔዳለሁ፣ኅዘን ሳጠራቅም፤
በመሸሼ ብቻ፣ብሶቴ ባያልቅም. . .
ከጀመርኩት መንገድ፣ተመልሼ አላውቅም!
.
@huluezih

@getem
@getem
እምነት ወይስ እውነት?
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
በድንገት ቅጽበታት፣
በጦዘ ምትሐት፣
ጆሮ ያቃጭላል. . .
ባልዋልሽበት ሥፍራ፣ድምጽሽን ይሰማል
ሞገድሽን ፍለጋ ንፋስን ይቀድማል!
.
ዓይኔ ይዳክራል. . .
የተረሳ መልክሽ፣"ሽው!" ይላል ከፊቴ፣
እምነት ወይስ እውነት
የሌለን ማየቴ?
መንጠፍሽን አምኖ፣እንደምን ያይሻል?
እኔ አብጃለሁ ወይ አንቺ መጥተሻል!
.
@huluezih

@getem
@getem
@getem
"አንድ ቀን" በሚል ተስፋ. . .
.
ጥርስ ነክሰን መጣን፣በእሳት በረመጡ፣
ይክሰናል ብለን የቀን አመጣጡ!
.
"ዛሬ"ን አታቅልለው፤
"ዛሬ"ን አታባክነው፤
"አንድ ቀን!" ብለህ
የናፈቅከው ቀን ነው!
.
#ፈይሠል_አሚን
.
@huluezih
@getem
@getem