ግጥም ብቻ 📘
67.4K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ሐሙስ መስከረም 29 ሰም እና ወርቅ 22 ኛው የኪነ ጥበብ ምሽት በ ኢትዮጹያ ሆቴል

@getem
የአፍቃሪ ስንብት
(መዘክር ግርማ)

እሄዳለሁ ብለሽ፣ ሻንጣሽን ካነሳሽ
ትናንትናችንን፣ በዛሬ ከረሳሽ
አላስገድድሽም፣ መሄድ ካ'ሻሽ ሂጂ
ባይሆን ተከትየሽ፣ እመጣለሁ እንጂ።

@getem
@getem
@getem
#ቀለም_ቀቢ_ትውልድ
.
.
አንዲት ግርግዳ ነበረች ፥ ስሟን "ሀገር" የሚሏት
ከድሮ በፊት የኖሩ፣ የጥንት ሰዎች የሰሯት
-
የሆነ ትውልድ እጆች ፣ ሊያጌጧት ቢያስቡ
እርቃን ሰውነቷን ፣ አንዳች ቀለም ቀቡ!
-
በሌላ ዘመን ደ’ሞ ፣ ሌሎች ልጆቿ መጡ
"ይህ ነው የሚሻል" ብለው ፣ ሌላ ቀለም ለወጡ!
.
እንዲህ እንዲያ እያለ…..
አዲሶች ሲመጡ፣ ነባሮች ሲሄዱ
አመታት ነጎዱ!!
.
ባለ ብሩሽ ሁሉ --
ምስኪን ገላዋ ላይ ፣ መልኩን እየሳለ
ለጌጥ ያሉት ቀለም --
ያለቅጥ ወፍሮ ፣ ግርግዳ አከለ!
.
እናም ይህች "ሀገር"…
በእረፍት አልባ ብሩሽ ፣ በሁለት በኩል ታንቃ
በቀለም ግግር ውስጥ ፣ አለች ተደብቃ!
-
ወጪና ወራጁ
መዋቅሩን ትቶ ፣ ሲጨነቅ ለውበት
(ያስተዋለ የለም... )
የግርግዳው ስሪት --
ድንጋይ ይሁን ጭቃ
ብረት ይሁን እንጨት።
--------------//-----------
( በርናባስ ከበደ )
[ከ"ፊደልና ቅኔ" የግጥም መድብል]

@getem
@getem
@getem
👍1😁1
ጥቁር ነጭ ግራጫ
(ነብይ መኮንን)

...ሰው እያለ አጠገባችን
ቅንነቱን ማየት ሲያመን
ከኛ አብሮ በሕይወት ቆሞ ፤ መልካሙን ስምን
መጥራት ሲያንቀን
"ሰው ካልሞተ ወይ ካልሄደ አይነሳም" እንላለን
እንዲህ እያልን፤
ስንቱን ጠቢብ እየሸኘን፤
አበባውን ቀጥፈን ጥለን፤ አበባ (እ)ናስቀምጣለን።

@getem
@getem
@getem
1👍1
ሰውዬው!!!!!!!!
በእንቶ ፈንቶ ወሬ፣
በአርቲ ቡርቲ፣ ጩኸት፣
በድሪቶ ድልቂያ፣
ይወድቃል መስሏቸው፣ሲገፉ ሲገፉ፣
ጭራሽ!!!!
ጎራውን የሚንድ፣
ገፍትሮ የሚጥል፣
ጥሶ የሚገባ፣ የቆላ ጅግሳ፣
ሰባብሮ የሚጥል፣ አርማጃው ጃውሳ።
ልቡ ሙልት ያለ፣
ውስጡ የታተመ፣
በድልና ስኬት፣ ካፍ እስከ ገደፉ፣
ይህንን ጃውሳ፣
የብረት ግድግዳ፣
የብረት ምሰሶ፣አርገውት አረፉ!!!!!!!
((( ጃ ኖ ))

ደስ ብሎናል
# ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ!
ሸጋ ጁምኣ!

@getem
@getem
@getem
👍1
ዕ-ም-ነ-ት(ልዑል ኃይሌ)

በጎባጣነቴ ተመርኩዘው ሲያልፉ፤
ምሩኝ እንድላቸው ዓይኖቼን አጠፉ፤
ዓይኖቼም ቢጠፉ መንገድ መች ይጠፋል፤
ያመረኮዘ ሠው አቀርቅሮ ኖሮ
መንገድ ስላጠና እንቅፋቱን ያልፋል፤
ተይ ምሪኝ አልልም
ልምራም ካልሽ እንዳሻሽ፤
ጎብጬም ታውሬም አየዋለሁና የአንቺን መጨረሻሽ፤
አልሰጋም መንገዱን አልፈራም መመራት፤
ዓይኔን ብታጠፊም
ከውስጥ አኑሪያለሁ የማይጠፋ መብራት፤
አልፈራም መመራት!!
...
አለሁ ካለሽበት
ሄዳለሁ በገደል ሄዳለሁ በሐይቁ፤
ዋጋ ያጣልና
እስከጥግ ቢያፈቅሩ እምነት እያራቁ፤
ምሪኝ ባንቺ መንገድ
እኖራለሁ ባሻሽ፤
ታውሬም ጎብጬም
በዕምነቴ አየዋለሁ ያንቺን መጨረሻሽ
27-01-2012 ዓ.ም.

@getem
@getem
@getem
ለተለያየ የእድገት ውስንነት ላለባቸው ልጆች እንዲሁም ለመደበነኛ ተማሪዎች!
ምዝገባ ጀምረናል!
አድራሻ- ተጦርሀይሎች ከሸዋ ሱፐርማርኬት ጀርባ
0925266565
0913255921
@Medi5255
የማላፈርሰውን፤
ተራራ ጉብታ፤
ልክ እንደዥንጀሮ፤
እስኪ ልጫር ብየ መታገል አልወድም፤
መታከት ነው እንጅ፤
ሰማይ ያስቀመጠው፤
በምድር ጫጫታ ከወንበሩ አይወርድም።


#የኛ ሰፈር መንዙማ


ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሜ!! እምወድሽዋ💚💛

@getem
@getem
@balmbaras
ነገሮች ከባድ ሊመስሉ ይችላሉ። የኢትዮጵያዊነት ወርቅ ዋጋ ያልገባቸው ብዙ ወገኖቻችን ሊስቱ ይችላሉ። ኢትዮጵያ ግን አትፈርስም። በብሔራዊ ቲያትር የሰጠሁትን ዲስኩር ተጋበዙልኝ። ይህን መልእክት ሼር ማድረግና ዩ ትዩብ ቻናሌ ላይ ሰብስክራይብ ማድረግም እንዳትረሱ።
https://youtu.be/fLv5K2RfuPQ
ለኢትዮጵያ!
(በላይ በቀለ ወያ)
,
ይብላኝለት እንጂ...
በዘር ተከፋፍሎ ፣ ለሚታመስ ቤቷ
ይብላኝለት እንጂ...
ተሸርፎ ተሸርፎ ፣ ላለቀ መሬቷ
ይብላኝለት እንጂ...
ደረቷን ስትደቃ ፣ ለወረደው ጡቷ
ይብላኝለት እንጂ...
ባዘን ፀጉሯን ስትነጭ ፣ ለገጠበ አናቷ
ይብላኝለት እንጂ..
ቁንጅናውን ላጣ ፣ ማድያታም ፊቷ...
፡፡፡፡፡፡፡
ከዚ ሁሉ ኋላም
የዘመን ጥላሸት ፣ መልኳን ተለቅልቃ
ቁንጅናዋ ርቋት ፣ ፉንጋነትን ታጥቃ
ልንጠላት አንችልም ፣ ውብ ሀገር ነች በቃ!!!

@getem
@getem
@getem
# የሃጥያት_እርከን ?
ስለ ገንዘብ ብሎ
ሐሰት ከሚናገር፣
በገንዘብ ተገዝቶ
አፋን ከሚዘጋ፣
ሁሉም እንደ ስራው ፡ ኩነኔ ሲደርሰው
ከነኚህ ከሁለቱ ፡ የማን ነው ሚብሰው?

|| በርናባስ ከበደ ||

@getem
@getem
@getem
Audio
መቼ ነው?

ፀሃፊ: ሮማን ተወልደ
አንባቢ: ኃይማኖት ግርማ

@getem
@getem
የማምነውን ፍቅር

የነፍሴን ሰው መሻት ካወቅኩኝ ጀምሮ
የሴትን ጸጋነት ካመንኩኝ ጀምሮ
ይሄው አስሳለሁ
ሰው እፈልጋለሁ።
የስሜቴን ንግሥት የውስጥያዬን ልክ
አላገኘኋትም ብፈልግ፣ ብፈልግ።

ይሰምራል እያልኩኝ፣ ይዣለሁ ፍለጋ
ዘመናት አለፉ፣ ብቻዬን አምሽቼ ብቻዬን ሳነጋ።

ባየኋት እንስት ውስጥ ሳሰላው ምኞቴን
ምኞቴ ተንዶ፣ በቆሰለ ልቤ የምቀር ሌጣዬን
በታየኋት ሴት ውስጥ የወጠንኩት ፍቅር
አቁስላኝ ወይ ቆስላ ትርፉ ያው መቃቃር።

ላየችኝ አልሆናት፣ ያየኋት አትሆነኝ
መፈቃቀር ማለት ይቻል አመስል አለኝ።
የማምነውን ፍቅር ልኖረው ተሳነኝ
የፍቅር አምላክ ሆይ ባክህ ተለመነኝ።

©ዘርዓሰብ ሣጌጥ
፪\፪\፪፳፩፪ ዓ.ም

@getem
@getem
@getem
👆👆 ለምሽታችን
💚

እናም በዚሁ አጋጣሚ የቴዲ አፍሮ "ተያት ይቺ አለም ለሀቅ የላትም ዳኛ " የሚለው የሙዚቃው ግጥሙ ወይም ሙዚቃው ያለው ካለ ቢልክልኝ አመስጋኝ ነኝ🙏🙏

ሸጋ ምሽት!💚

@getem
@balmbaras
#ስሜ_ተላወሰ

ሞገደኛው ሽፍታ !!
ሀገር ያሸበረ
ስንቱን ያኮላሸ
ስንቱን ያነፈረ
ሀገር ተይዞለት ፥ እግሬ ሳይሄድ ከርሱ
ሚሽትክን ጠብቆ ፥ ጭኗት በፈረሱ
ባዘዘው ሰው ጤፉ !!
ያለ መኮነኑ
ያለ መጠየፉ
ደርሶ ሰው እንዳጣች ፥ አጋደማት ቢሉ
ባንቺ እጁን ማንሳት ፥ በኔ መታበሉ
እሺም
እንቢም ጠፍቶኝ ፥ አጡዞኝ ነገሩ
ገፍቶኝ ...እንዳልገፋው !!
አንቺ ከበስሩ
ይድላሽ ብዬ እንዳልሰድ ፥ አልጋና ጠፍሩ
ሽሙጦ በኔው ነው ፥ አድባርና አውጋሩ
ሲበደል ለኖረ ፥ አልፎም ገፈት ቀማሽ
ብሩክ ማንነቱ ፥ እሬት ግንባር ሲታሽ
ምንም አለ ምንም
ደግም ሰራ ክፉ ፥ እሱው ነው ተወቃሽ !
በልክ የለሽ ትግስት
ወንድነት ሲፈተን ፥ በፍቅር ፣ በክብሩ
ስንቱ ስሙ ጠፋ
በተጓደለ ፍርድ ፥ የእውነቱ ጅማት ፥ ተበጥሶ ክሩ።

#አብርሀም_ተክሉ

@getem
@getem
@getem