እፉ - ዬ - ገላ
©ሲራክ ወንድሙ
.
ከጊዜ የዛፍ ጥላ
ከቀን ቤልጅግ ቀላ'
ቃታ ሳይታከል
ሳይጠለል አካል
ያቺ እፉ - ዬ - ገላ ፥ ያቺ እኔ የምወዳት
መውደድ ነፋስ ገፍቶ ፥ ከእኔው ዳር አቆማት
ወደ እኔው አመጣት።
ግና ...
ነፋስ ያደቆናት ምታቃጥል ገላ ፣
ደብር የለሽ ቀዳሽ ፥ የልቦራ ጥላ ፤
የመምጣቷ ሸማ ፥ ሞቆ ሳያሞቀኝ ፣
የመሄዷ ጨንገር ፥ ሸንቁጦ ሳይገርፈኝ ፤
መምጣቷ ሳይደላ ፥ መሄዷም ሳይከፋ ፣
ወረት 'ሚባል ነፋስ ፥ ድንገት ይዟት ጠፋ።
.............. © ሲራክ ወንድሙ
@getem
@getem
@getem
``````````````
©ሲራክ ወንድሙ
.
ከጊዜ የዛፍ ጥላ
ከቀን ቤልጅግ ቀላ'
ቃታ ሳይታከል
ሳይጠለል አካል
ያቺ እፉ - ዬ - ገላ ፥ ያቺ እኔ የምወዳት
መውደድ ነፋስ ገፍቶ ፥ ከእኔው ዳር አቆማት
ወደ እኔው አመጣት።
ግና ...
ነፋስ ያደቆናት ምታቃጥል ገላ ፣
ደብር የለሽ ቀዳሽ ፥ የልቦራ ጥላ ፤
የመምጣቷ ሸማ ፥ ሞቆ ሳያሞቀኝ ፣
የመሄዷ ጨንገር ፥ ሸንቁጦ ሳይገርፈኝ ፤
መምጣቷ ሳይደላ ፥ መሄዷም ሳይከፋ ፣
ወረት 'ሚባል ነፋስ ፥ ድንገት ይዟት ጠፋ።
.............. © ሲራክ ወንድሙ
@getem
@getem
@getem
❤1
#የግርጣት_ሰላምታ
© ሲራክ ወንድሙ @siraaq
.
ለደባ እሩቅ ናት - ዝምታ ነው ቤቷ - ሰቀላው ሰገነት ፣
ጅራፏ ውሽንፍር - ቁጣዋ ሞት ጠሪ - የዘላለም ግርጣት ።
የአድማስ ማዶው - ቅላት ምስሏን ዘዋሪ ፣
ግዛቷ ገመገም - የመብረቅ ስባሪ ።
ግልምጫዋ እቶን - የጉድ ቁና ሰፈፍ ፣
ሰማይ ከዋክብቱን - አጥምዶ ሚያረግፍ ።
የሸማዋ ጥለት - ቢሸመን በእግዜር እጅ ፣
ቢደወር ቢታጠብ - ቢሰጣ አርያም ደጅ ።
እሷ እንደው እሷ ናት - አይሞቃት አይደንቃት ፣
ዝም ነው አመሏ - አይዳዳትም ቅብጠት ፣
ጥለቷ ነውና -
ያ ቀስተ ደመና - የሰማይ መቀነት ።
"""""""""""""".........///////...... """"""""""""""""" #________ሲራክ_ወንድሙ
___
@getem
@getem
@getem
© ሲራክ ወንድሙ @siraaq
.
ለደባ እሩቅ ናት - ዝምታ ነው ቤቷ - ሰቀላው ሰገነት ፣
ጅራፏ ውሽንፍር - ቁጣዋ ሞት ጠሪ - የዘላለም ግርጣት ።
የአድማስ ማዶው - ቅላት ምስሏን ዘዋሪ ፣
ግዛቷ ገመገም - የመብረቅ ስባሪ ።
ግልምጫዋ እቶን - የጉድ ቁና ሰፈፍ ፣
ሰማይ ከዋክብቱን - አጥምዶ ሚያረግፍ ።
የሸማዋ ጥለት - ቢሸመን በእግዜር እጅ ፣
ቢደወር ቢታጠብ - ቢሰጣ አርያም ደጅ ።
እሷ እንደው እሷ ናት - አይሞቃት አይደንቃት ፣
ዝም ነው አመሏ - አይዳዳትም ቅብጠት ፣
ጥለቷ ነውና -
ያ ቀስተ ደመና - የሰማይ መቀነት ።
"""""""""""""".........///////...... """"""""""""""""" #________ሲራክ_ወንድሙ
___
```````````_________
@getem
@getem
@getem
👍2
#ስጋት_የገባው_ልብ
...................©ሲራክ ወንድሙ
እቱ የኔ ገላ ፥ የመንገዴ ማሾ ፣
የፍቅሬ ጥንስሱ ፥ ብቅልና ጌሾ ፤
እቱ የኔ ሰፈፍ ፥ የነብስ ወንዜ ቅጂ ፣
ናፍቆትሽ አስዳኸኝ ...
ፍቅርሽ አስለቀሰኝ ፥ እንደመንፈቅ ልጂ ።
.
ሚሻልም ቢመጣ ፥ አንድ አይስቴው ተኳሽ ፣
ፈሪ አይናቅም ፥ ውጭ ውጩን 'ማያመሽ ።
ተይማ ፥ ተይማ ፣
ተይማ ፥ ተይማ ፣
ጣል ጣል አታርጊኝ ፥ እንዳደፈ ሸማ።
................. // ................
@getem
@getem
@getem
...................©ሲራክ ወንድሙ
እቱ የኔ ገላ ፥ የመንገዴ ማሾ ፣
የፍቅሬ ጥንስሱ ፥ ብቅልና ጌሾ ፤
እቱ የኔ ሰፈፍ ፥ የነብስ ወንዜ ቅጂ ፣
ናፍቆትሽ አስዳኸኝ ...
ፍቅርሽ አስለቀሰኝ ፥ እንደመንፈቅ ልጂ ።
.
ሚሻልም ቢመጣ ፥ አንድ አይስቴው ተኳሽ ፣
ፈሪ አይናቅም ፥ ውጭ ውጩን 'ማያመሽ ።
ተይማ ፥ ተይማ ፣
ተይማ ፥ ተይማ ፣
ጣል ጣል አታርጊኝ ፥ እንዳደፈ ሸማ።
................. // ................
@getem
@getem
@getem
👍2
#ወዲያ_ሽሽ_ይለኛል!
© ሲራክ ወንድሙ @siraaq
.
ኑረት ሲረክስብኝ ፥ ሲሆን እንደ እቃ 'ቃ ፣
አዎን ያስፈራኛል ፥ የዘመን አታሞ
.................... ፥ የዘመን ድለቃ ፤
የድግግሞሽ ሰልፍ ፥ የእሽ ፡ ክርክሪት ምልዓት ፣
ሰው ሆኖ ተኝቶ ፥ ትል ሆኖ እንደመንቃት ።
ንጋት አድባር ሆኖ ፥ የሀገር ጌጥ የሀገር ዳስ ፣
ጀምበር በሰረቀ በአመሻሹ ፈለግ ፥ እንደካህን መርከስ ፤
እንደምኩራብ ከብሮ ፥ እንደ እንትን መንኳሰስ ።
አዎን ያስፈራኛል...
ወዲያ ሽሽ ይለኛል...
ወዲህ ግድም እሩጥ ፣
ወዲህ ግድም አምልጥ ፤
ወዲያ ጥግህን ያዝ ፥ ይለኛል ይለኛል ፤
የዘመኑ ቅኔ የዘመኑ መንፈስ ፥ መንን ያሰኘኛል ፤
ወዲያ ሽሽ ይለኛል ።
.............. | ። | ...............
ነሐሴ ፳፻፲፫ ዓ.ም
@getem
@Getem
@getem
© ሲራክ ወንድሙ @siraaq
.
ኑረት ሲረክስብኝ ፥ ሲሆን እንደ እቃ 'ቃ ፣
አዎን ያስፈራኛል ፥ የዘመን አታሞ
.................... ፥ የዘመን ድለቃ ፤
የድግግሞሽ ሰልፍ ፥ የእሽ ፡ ክርክሪት ምልዓት ፣
ሰው ሆኖ ተኝቶ ፥ ትል ሆኖ እንደመንቃት ።
ንጋት አድባር ሆኖ ፥ የሀገር ጌጥ የሀገር ዳስ ፣
ጀምበር በሰረቀ በአመሻሹ ፈለግ ፥ እንደካህን መርከስ ፤
እንደምኩራብ ከብሮ ፥ እንደ እንትን መንኳሰስ ።
አዎን ያስፈራኛል...
ወዲያ ሽሽ ይለኛል...
ወዲህ ግድም እሩጥ ፣
ወዲህ ግድም አምልጥ ፤
ወዲያ ጥግህን ያዝ ፥ ይለኛል ይለኛል ፤
የዘመኑ ቅኔ የዘመኑ መንፈስ ፥ መንን ያሰኘኛል ፤
ወዲያ ሽሽ ይለኛል ።
.............. | ። | ...............
ነሐሴ ፳፻፲፫ ዓ.ም
@getem
@Getem
@getem
👍3
እናቷን ጨረቃ
.
©ሲራክ ወንድሙ
Each day provides its own gifts.
( የአሜሪካውያን አባባል )
አንዳንድ ንጋቶች ነብሴን በሀሴት ይሞላሉ። ግድቡን እንደጣሰ ውሃ መላው ሰውነቴ በተስፋ ሲጠመቅ እንባ ያንቀኛል።
ለካ የእሷ መኖር በነፍሴ ሰማይ የወጣችው ደማቅ ፀሀይ ነች። ብዙ ሰው ስለ እሷ ሳወራ እህትህ ናት አይለኝም። ፍቅረኛህ ነች ይለኛል።
ናፍቆቷ ከአቅሜ በላይ ሲሆን ስቅስቅ ብዬ አልቅሼ አውቃለሁ። ለምን ተዋወቅን ብዬ እግዜርን ያማረርኩበት ቀን ብዙ ነው። ንጋት ላይ ድምጿን ሰምቼ ቀኔ ደምቆ ሲውል እንደእኔ የምትወደው ልጅ የለም ብዬ አመስግኜው አውቃለሁ።
እሷ ረቂቅ ናት ነብሷ ብዙ ቅኔ አለው።
.
መኖርሽ ኩራቴ
ልደትሽ ልደቴ
ሰርክ ሰርኩን እንድታደም
እንደ ዳዊት የቃል ድጋም
ውብ ነብስሽ ገዳሜ
እንደ ሳቅሽ አስገምግሜ
ካለመኖር ያሳር እጣ
ቀን ጎድሎብኝ እኔን ሳጣ
አንቺ መጣሽ
አገኘሁሽ
ቀን ሞላልኝ - ነጋ ዘመን
መኖር ሆነ የኔ - ውጥን
፪
ለድል የተራበ
ሽንፈት የጠገበ
በዘመን ተገፍቶ - ሀሴት የታዘለ
የኔ ገላ አካል - አንቺ ጋ ነፍስ አለ
የልቤ ውብ ቅንድብ
አንች የነፍሴ ምኩራብ
ሽፍንፍን አድርጌ - ሰስቼ ልውደድሽ
ስቃይሽን ልውረስ - አንቺን ክፉ አይንካሽ
መራብሽን ልራብ
ህመምሽን ልጥገብ
አንቺ የመውደድ ጥግ - የሰው መጀመሪያ
የህይወቴ ሰንደቅ - ሰውነት ማሰሪያ
አምላኬ አምላክሽ
አምላክሽ አምላኬ
በዘመን ስጦታው አንቺን ሰጠኝና
ይኸው ሙሉ አረገኝ መኖሬ እንዲቀና
.................. / / ..................
ሩሐማዬ የኔ ደግ እህት እንኳን ተወለድሽልኝ!
ዛሬ የአንቺ ልደት ብቻ አይደለም የኔም ልደት ነው አንቺ ባትኖሪ ምን ያህል ጎደሎ እንደምሆን ልነግርሽ የምችልበት ቃል ቢኖር ምንኛ በታደልኩ ግን አጣሁ።
የኔ ደማቅ ኮከብ ጥንካሬዬ አንቺ ነሽ
ብዙሃን እህት ልክ እንደእናት ናት ይላሉ። እኔ ግን በእሱ አልስማማም እህት ትንሿ እናት ናት። ነብስሽ ፣ ለፍቅር ፣ ለመውደድ ለደስታ የተሰጠች ስጦታ ነች።
ባለፈው " ወንድምዬ በልደቴ ቀን እኮ ፈተና አለብኝ አያስጠላም? " ስትይኝ ቅር አለኝ።
ለምንድነው ልደታችን ያላለችው ብዬ አሰብኩ። ሩ አንቺ ባትኖሪ እኮ ባዶ ነኝ።
የኔ አንገታም 😂 የኔ ዶለዝ 😂 አብዝቼ እወድሻለው
በህይወቴ ቦታ ካላቸው ሰዎች መድቤሻለሁ።
የኔ ልዩ ሴት አለኝ የምለውን ሁሉ አጥቼ አንቺን ከጎኔ ባገኝ የምከፋ አይነት ሰው አይደለሁም።
በቃ አጋነንክ ይሉኛል እንጂ አንቺ ለእኔ ሀገር ነሽ ፣ አለም ነሽ ፣ የደስታ ምንጩ ኩሬ ነሽ። ከዚህ በላይ ምን አለ የኔ ትንሿ እናት?
ዘመንሽ ይባረክልኝ ! ሺህ አመት ኑሪልኝ
የአንቺ መኖር የእኔ መቆም ተስፋ ነውና አቆያት ልውደዳት ብዬ ስፀልይ ሲራክም ይኖር ዘንድ ምክኒያት ይሁን ማለቴን እግዜሩ ሳይረዳ ይቀራል? ( አይቀርም )
እህት አትመሰገንም እንጂ መስቀሌን ስለተሸከምሽ ብዙ ምስጋና ነበረኝ ግን ተዝቆ የማያልቅ ውዴታዬን እንቺ እወድሻለሁ።
ዛሬ ልደታችን ነው። ጨረቃዋ ሳትቀር ይላታል። ካላላትም እንደ ገጣሚው እናቷን እንላታለን።
እናቷን ጨረቃ😂
መልካም ልደት ለእንቁዋ እህቴ ለሩሐማ ማሾ ሀይሌ❤
ቅዳሜ መስከረም 8 2014 ዓ.ም
Each day provides its own gifts.
.
©ሲራክ ወንድሙ
Each day provides its own gifts.
( የአሜሪካውያን አባባል )
አንዳንድ ንጋቶች ነብሴን በሀሴት ይሞላሉ። ግድቡን እንደጣሰ ውሃ መላው ሰውነቴ በተስፋ ሲጠመቅ እንባ ያንቀኛል።
ለካ የእሷ መኖር በነፍሴ ሰማይ የወጣችው ደማቅ ፀሀይ ነች። ብዙ ሰው ስለ እሷ ሳወራ እህትህ ናት አይለኝም። ፍቅረኛህ ነች ይለኛል።
ናፍቆቷ ከአቅሜ በላይ ሲሆን ስቅስቅ ብዬ አልቅሼ አውቃለሁ። ለምን ተዋወቅን ብዬ እግዜርን ያማረርኩበት ቀን ብዙ ነው። ንጋት ላይ ድምጿን ሰምቼ ቀኔ ደምቆ ሲውል እንደእኔ የምትወደው ልጅ የለም ብዬ አመስግኜው አውቃለሁ።
እሷ ረቂቅ ናት ነብሷ ብዙ ቅኔ አለው።
.
መኖርሽ ኩራቴ
ልደትሽ ልደቴ
ሰርክ ሰርኩን እንድታደም
እንደ ዳዊት የቃል ድጋም
ውብ ነብስሽ ገዳሜ
እንደ ሳቅሽ አስገምግሜ
ካለመኖር ያሳር እጣ
ቀን ጎድሎብኝ እኔን ሳጣ
አንቺ መጣሽ
አገኘሁሽ
ቀን ሞላልኝ - ነጋ ዘመን
መኖር ሆነ የኔ - ውጥን
፪
ለድል የተራበ
ሽንፈት የጠገበ
በዘመን ተገፍቶ - ሀሴት የታዘለ
የኔ ገላ አካል - አንቺ ጋ ነፍስ አለ
የልቤ ውብ ቅንድብ
አንች የነፍሴ ምኩራብ
ሽፍንፍን አድርጌ - ሰስቼ ልውደድሽ
ስቃይሽን ልውረስ - አንቺን ክፉ አይንካሽ
መራብሽን ልራብ
ህመምሽን ልጥገብ
አንቺ የመውደድ ጥግ - የሰው መጀመሪያ
የህይወቴ ሰንደቅ - ሰውነት ማሰሪያ
አምላኬ አምላክሽ
አምላክሽ አምላኬ
በዘመን ስጦታው አንቺን ሰጠኝና
ይኸው ሙሉ አረገኝ መኖሬ እንዲቀና
.................. / / ..................
ሩሐማዬ የኔ ደግ እህት እንኳን ተወለድሽልኝ!
ዛሬ የአንቺ ልደት ብቻ አይደለም የኔም ልደት ነው አንቺ ባትኖሪ ምን ያህል ጎደሎ እንደምሆን ልነግርሽ የምችልበት ቃል ቢኖር ምንኛ በታደልኩ ግን አጣሁ።
የኔ ደማቅ ኮከብ ጥንካሬዬ አንቺ ነሽ
ብዙሃን እህት ልክ እንደእናት ናት ይላሉ። እኔ ግን በእሱ አልስማማም እህት ትንሿ እናት ናት። ነብስሽ ፣ ለፍቅር ፣ ለመውደድ ለደስታ የተሰጠች ስጦታ ነች።
ባለፈው " ወንድምዬ በልደቴ ቀን እኮ ፈተና አለብኝ አያስጠላም? " ስትይኝ ቅር አለኝ።
ለምንድነው ልደታችን ያላለችው ብዬ አሰብኩ። ሩ አንቺ ባትኖሪ እኮ ባዶ ነኝ።
የኔ አንገታም 😂 የኔ ዶለዝ 😂 አብዝቼ እወድሻለው
በህይወቴ ቦታ ካላቸው ሰዎች መድቤሻለሁ።
የኔ ልዩ ሴት አለኝ የምለውን ሁሉ አጥቼ አንቺን ከጎኔ ባገኝ የምከፋ አይነት ሰው አይደለሁም።
በቃ አጋነንክ ይሉኛል እንጂ አንቺ ለእኔ ሀገር ነሽ ፣ አለም ነሽ ፣ የደስታ ምንጩ ኩሬ ነሽ። ከዚህ በላይ ምን አለ የኔ ትንሿ እናት?
ዘመንሽ ይባረክልኝ ! ሺህ አመት ኑሪልኝ
የአንቺ መኖር የእኔ መቆም ተስፋ ነውና አቆያት ልውደዳት ብዬ ስፀልይ ሲራክም ይኖር ዘንድ ምክኒያት ይሁን ማለቴን እግዜሩ ሳይረዳ ይቀራል? ( አይቀርም )
እህት አትመሰገንም እንጂ መስቀሌን ስለተሸከምሽ ብዙ ምስጋና ነበረኝ ግን ተዝቆ የማያልቅ ውዴታዬን እንቺ እወድሻለሁ።
ዛሬ ልደታችን ነው። ጨረቃዋ ሳትቀር ይላታል። ካላላትም እንደ ገጣሚው እናቷን እንላታለን።
እናቷን ጨረቃ😂
መልካም ልደት ለእንቁዋ እህቴ ለሩሐማ ማሾ ሀይሌ❤
ቅዳሜ መስከረም 8 2014 ዓ.ም
Each day provides its own gifts.
👍12❤2
ምን ነካሽ ?!
©ሲራክ ወንድሙ @siraaq
.
' ጥፋቱ የማን ነው? ' ፥ ብዬ እንዳልጠይቅሽ ፣
ቃልሽን ሳልሰማ ፥ እንባ ነው ሚቀድምሽ !
ምንድነው ገላዬ? ፥ ውስጥሽን በርዞ ፣
የልብሽን ደጀን ፥ መሻከር ወዝውዞ ፤
ቂም አይሉት እልህ ፥ በነፍስሽ ተረግዞ ፣
ዜማሽ ቅኝት አጥቶ ፥ በሀዘን እንጉርጉሮ ፣
' ተወኝ ! ' የሚያስብልሽ ፥ ለአይን እንኳን አቅሮ ?
ለምን ነው አካሌ ??....
ሰውነት እርስቱን ፥ ቀን ሲገፋው ማልዶ ፣
በእምነት የካቡት ቃል ይወድቃል ተንዶ ፤
ፍቅርን ባነፁበት ፥ በቀየዱት ቀዬ ፣
እንዴት መልስ ይሆናል ፥ ለየምን እዬዬ?
ድክምክም አድርጎ ፥ ፍዝዝ ትክዝ ትክዝ ፣
አዚም ተከናንቦሽ ፥ ቀንሽን ሲበርዝ ፣
በጣት ያልጠለቀ ፥ የልባችን ኪዳን ፣
' ምን ነካት? ' ይለኛል ፥ ገፅሽ ሲደማምን።
እውነትም ምን ነካሽ ? ፥ ምን አየሽ እርግቤ
የሀሴቴ ደንገል ፥ የነብስ ረሀቤ
ምን ነካሽ? ፥ የኔ ወርቅ
የህይወት ውቧ ሰንደቅ
የናፍቆት ዶሰኛ
የቀን አመለኛ
የአይኔ ስር መሀረብ
የትዝታ ቀለብ
የሳቅሽ መስክ ላይ ፥ መከፋት ሳር ግጦ ፣
አዛኝ አንጀትሽን ያ ጭካኔሽ በልጦ ፤
በአይንሽ ስትገርፊኝ ፣
በኩርፊያሽ ስታስሪኝ ፣
በእምባሽ ልቤ ወልቆ ፥ ዝምታሽ ሲያደቀኝ ፣
' ያቺ ሴት ናት! ' ብሎ ማመኑ ጨነቀኝ።
እናልሽ ገላዬ ፥ አንቺ የነፍሴ ኩሬ
ድክምክም አድርጎ ፥ ፍዝዝ ትክዝ ትክዝ ፣
አዚም በገባሩ ፥ ቀንሽን ሲበርዝ ፤
በጣት ያልጠለቀ ፥ የልባችን ኪዳን ፣
'ምን ነካት? 'ይለኛል ፥ ገፅሽ ሲደማምን ።
ምን ነካሽ በእኔ ሞት??
.
.................... //// ....................
መስከረም ፳፻፲፬ ዓ.ም
@getem
@getem
@getem
©ሲራክ ወንድሙ @siraaq
.
' ጥፋቱ የማን ነው? ' ፥ ብዬ እንዳልጠይቅሽ ፣
ቃልሽን ሳልሰማ ፥ እንባ ነው ሚቀድምሽ !
ምንድነው ገላዬ? ፥ ውስጥሽን በርዞ ፣
የልብሽን ደጀን ፥ መሻከር ወዝውዞ ፤
ቂም አይሉት እልህ ፥ በነፍስሽ ተረግዞ ፣
ዜማሽ ቅኝት አጥቶ ፥ በሀዘን እንጉርጉሮ ፣
' ተወኝ ! ' የሚያስብልሽ ፥ ለአይን እንኳን አቅሮ ?
ለምን ነው አካሌ ??....
ሰውነት እርስቱን ፥ ቀን ሲገፋው ማልዶ ፣
በእምነት የካቡት ቃል ይወድቃል ተንዶ ፤
ፍቅርን ባነፁበት ፥ በቀየዱት ቀዬ ፣
እንዴት መልስ ይሆናል ፥ ለየምን እዬዬ?
ድክምክም አድርጎ ፥ ፍዝዝ ትክዝ ትክዝ ፣
አዚም ተከናንቦሽ ፥ ቀንሽን ሲበርዝ ፣
በጣት ያልጠለቀ ፥ የልባችን ኪዳን ፣
' ምን ነካት? ' ይለኛል ፥ ገፅሽ ሲደማምን።
እውነትም ምን ነካሽ ? ፥ ምን አየሽ እርግቤ
የሀሴቴ ደንገል ፥ የነብስ ረሀቤ
ምን ነካሽ? ፥ የኔ ወርቅ
የህይወት ውቧ ሰንደቅ
የናፍቆት ዶሰኛ
የቀን አመለኛ
የአይኔ ስር መሀረብ
የትዝታ ቀለብ
የሳቅሽ መስክ ላይ ፥ መከፋት ሳር ግጦ ፣
አዛኝ አንጀትሽን ያ ጭካኔሽ በልጦ ፤
በአይንሽ ስትገርፊኝ ፣
በኩርፊያሽ ስታስሪኝ ፣
በእምባሽ ልቤ ወልቆ ፥ ዝምታሽ ሲያደቀኝ ፣
' ያቺ ሴት ናት! ' ብሎ ማመኑ ጨነቀኝ።
እናልሽ ገላዬ ፥ አንቺ የነፍሴ ኩሬ
ድክምክም አድርጎ ፥ ፍዝዝ ትክዝ ትክዝ ፣
አዚም በገባሩ ፥ ቀንሽን ሲበርዝ ፤
በጣት ያልጠለቀ ፥ የልባችን ኪዳን ፣
'ምን ነካት? 'ይለኛል ፥ ገፅሽ ሲደማምን ።
ምን ነካሽ በእኔ ሞት??
.
.................... //// ....................
መስከረም ፳፻፲፬ ዓ.ም
@getem
@getem
@getem
👍5
የደጋ በረከት
.
©ሲራክ ወንድሙ @siraaq
.
የተስፋ ሀገር ወዲያ ፥ የሀሳብ ሀገር ወዲህ ፣
ፋኖሱ ተሰዷል ፥ ሊመሽ ነው እንግዲህ ፤
ዶሮ ከቆጥ ሰፍሮ ፥ ሊኮኩል ሲቀጥር ፣
ይሄንን እያየ ፥ ልቤ ሲለኝ ጠርጥር ፣
በምናልባት መናጥ ፥ የቀን ድግግሞሽ ፣
እንዳሞራው ፍጥነት ፥ አክናፍ እሽክርክሮሽ ፤
ከቀየዋ ሳልሄድ ፥ በሯም ሳይዘጋ ፣
አድማስ ሲደማምን ፥ ምሽት ሲዘረጋ ፣
ባዶ እጄን ወጣለሁ ፥ ውብ አይኗን ፍለጋ።
__°°° _
የደጋ በረከት
መስከረም ፳፻፲፬ ዓ.ም
@getem
@getem
@getem
.
©ሲራክ ወንድሙ @siraaq
.
የተስፋ ሀገር ወዲያ ፥ የሀሳብ ሀገር ወዲህ ፣
ፋኖሱ ተሰዷል ፥ ሊመሽ ነው እንግዲህ ፤
ዶሮ ከቆጥ ሰፍሮ ፥ ሊኮኩል ሲቀጥር ፣
ይሄንን እያየ ፥ ልቤ ሲለኝ ጠርጥር ፣
በምናልባት መናጥ ፥ የቀን ድግግሞሽ ፣
እንዳሞራው ፍጥነት ፥ አክናፍ እሽክርክሮሽ ፤
ከቀየዋ ሳልሄድ ፥ በሯም ሳይዘጋ ፣
አድማስ ሲደማምን ፥ ምሽት ሲዘረጋ ፣
ባዶ እጄን ወጣለሁ ፥ ውብ አይኗን ፍለጋ።
__°°° _
የደጋ በረከት
መስከረም ፳፻፲፬ ዓ.ም
@getem
@getem
@getem
❤1
ገላዬ....
ከመስኩ ላይ ቆሜ ፥ እምባን ባረገዘ
በናፍቆት ወይቦ ፥ በተድበዘበዘ
በዚያ መንታ አይኔ...
የመራቤን ጅራፍ ፥ የምኞቴን ጩኸት
ላንቀላፋው ጤዛ ፥ ለወፍ ጎጆው ምልዓት
ዘምሬ
ዘምሬ
ደስኩሬ
ደስኩሬ
ህቅ ባለው መንፈስ ፥ ምሬት ባየው ልሳን
ብናገር ለእነሱ ፥ የኔን እንዲህ መሆን
የአንቺ ወዲያ መቅረት ፥ የንጋት ሰቀቀን
በጉድ ወጣ እያሉ ፥ ለሰማይ ለምድሩ
ለሰው ላራዊቱ ፥ ለቀየው መንደሩ
መስቀሉ ናት ብለው ፥ ናፍቆት ወለፈንዴ
ተሸነፈ ብለው ፥ ያሙኝ ይሆን እንዴ?
.................. / / .....................
© ሲራክ ወንድሙ
@getem
@getem
@getem
ከመስኩ ላይ ቆሜ ፥ እምባን ባረገዘ
በናፍቆት ወይቦ ፥ በተድበዘበዘ
በዚያ መንታ አይኔ...
የመራቤን ጅራፍ ፥ የምኞቴን ጩኸት
ላንቀላፋው ጤዛ ፥ ለወፍ ጎጆው ምልዓት
ዘምሬ
ዘምሬ
ደስኩሬ
ደስኩሬ
ህቅ ባለው መንፈስ ፥ ምሬት ባየው ልሳን
ብናገር ለእነሱ ፥ የኔን እንዲህ መሆን
የአንቺ ወዲያ መቅረት ፥ የንጋት ሰቀቀን
በጉድ ወጣ እያሉ ፥ ለሰማይ ለምድሩ
ለሰው ላራዊቱ ፥ ለቀየው መንደሩ
መስቀሉ ናት ብለው ፥ ናፍቆት ወለፈንዴ
ተሸነፈ ብለው ፥ ያሙኝ ይሆን እንዴ?
.................. / / .....................
© ሲራክ ወንድሙ
@getem
@getem
@getem
👍4❤1
ፀሎቴን ባሰማ ፥ እንደሰው ዝም አለኝ
እሱንም ዘመቻ ፥ ወሰዱት መሰለኝ
.......
የእቴሜቴ ጀምበር
©ሲራክ ወንድሙ
.
እረኛ አይዘምርም ፥ ዝም ነው አድባሩ
ፋኖስ ክሩን አጥቷል ፥ መሸ ደህና እደሩ
ቡሬ መንደር ራቃት ፥ የለችም ከቤቷ
በሌት አልዘመረች ፥ ከፍቷታል ወፊቷ
ማልዶ ሌት ሚያነቃኝ ፥ ዶሮ በጉድ ወጣ
የሌት ድምፁን ሸጦ ፥ መውዜር ይዞ መጣ
ወዲያም ወደ ሰማይ
ከጎጆዬ በላይ
ፀሎቴን ባሰማ እንደሰው ዝም አለኝ
እሱንም ዘመቻ ወሰዱት መሰለኝ
.
የዛች የእዝነት አርማ ፥ የህዋ ላይ ሰንደቅ
እንዴት ቀን ከፍቶባት ፥ ውብ ጀምበሯ ትጥለቅ
ከዛች ከገራገር ፥ ከደጊቱ ዳሴ
እንደምን ብርቅ ይሁን ፥ ሰላም ለእለት ጉርሴ
ኧረ እንደምን በምን
ኧረ እንደምን በምን
አምነን ያነገስነው ብራ ቀን ይዳምን
እኔን አፈር ይብላኝ ፥ ለእኔ ቀኑ ይክፋ
አንቺን ያሳጣችሽ ፥ ያች አለም ትደፋ
እስከ መች አስከ መች ፥ የአረር ሙዳይ ቋጥረን
እንደጃኖ ኩታ ፥ ዝናር ጥለት አርገን
ሀገር እያጠፋን ፥ ያልፋል እንላለን ?
እንዴት ነው መሰንበት ?
መውዜር እንደነዶ በሚመዘዝበት?
ኧረ እንደምን በምን
ኧረ እንደምን በምን
አምነን ያነገስነው ብራ ቀን ይዳምን?
.
ከጩኸትሽ ማዶ ፥ ካኮረፈው ሰማይ
ቄራ ከመሰለው ፥ ከአድማስሽ ሸራ ላይ
እብሪት ያጠላበት ፥ ምስል ድንገት ካየው
ለቸር አንመስለኝም ፥ ያን ጊዜ ፈራለሁ
አርብ አርቡን አመሻሽ
የሰማዩ ገላ ሲመስል የደም ሻሽ
ንትብ የለበሰ
ከወደ አንገቱ ዘሞ የተዘለሰ
ይሁዳሽን ባላይ ፥ ወድቆ ሲያንሰራራ
መስቀል ሆኗል ለሻጭ ፥ ገዢ ራሱን ያኩራ
ከክርስቶስ ይልቅ ፥ ይሁዳ ነውና ሚረከብ መከራ
ምክኒያቱም ......
ዘመን እያሰፉ
ትውልድ ለሚነቅፉ
ነገር ጠንቷል ዛሬ ፥ አውቀውት ይረፉ
ለሻጭ መስቀል ሊሆን ፥ ምሏልና ዛፉ
.
በኑረት ቀራንዮ ፥ በህይወት ጎለጎታ
ከገዳይሽ ቀዬ ፥ አንቺ ሆነሽ ጌታ
በሰማያ አኮርባጅ ፥ ወዲያ ስትላጊ
የመከራን መስቀል በሌት ተሸክመሽ ፥ መንገድ ስትፈልጊ
ጨረቃዋ ገባች ፥ ከደመና ጉያ
ከዋክቶች ሸሽተው ፥ እንደሰደድ ቋያ
ጠረንሽን ገፍተው ፥ ከገላሽ ሲርቁ
በንቄት ሸምቀው ፥ ሊጥሉሽ ዘለቁ
.
ዞር ብንል ወዲያ ፥ አራራይ መረዋ
ቀና ብንል ኦና ፥ የጠቆረ ህዋ
የፀሎትሽ ጩኸት ፥ ካልደረሰው ያ ' ቃል
እሱም እንደሰዉ ዘምቶልሽ ይሆናል።
..................... //// ..............
©ሲራክ ወንድሙ @siraaq
የእቴሜቴ ጀምበር
ህዳር ፳፻፲፬ ዓ.ም
https://tttttt.me/getem
https://tttttt.me/getem
እሱንም ዘመቻ ፥ ወሰዱት መሰለኝ
.......
የእቴሜቴ ጀምበር
©ሲራክ ወንድሙ
.
እረኛ አይዘምርም ፥ ዝም ነው አድባሩ
ፋኖስ ክሩን አጥቷል ፥ መሸ ደህና እደሩ
ቡሬ መንደር ራቃት ፥ የለችም ከቤቷ
በሌት አልዘመረች ፥ ከፍቷታል ወፊቷ
ማልዶ ሌት ሚያነቃኝ ፥ ዶሮ በጉድ ወጣ
የሌት ድምፁን ሸጦ ፥ መውዜር ይዞ መጣ
ወዲያም ወደ ሰማይ
ከጎጆዬ በላይ
ፀሎቴን ባሰማ እንደሰው ዝም አለኝ
እሱንም ዘመቻ ወሰዱት መሰለኝ
.
የዛች የእዝነት አርማ ፥ የህዋ ላይ ሰንደቅ
እንዴት ቀን ከፍቶባት ፥ ውብ ጀምበሯ ትጥለቅ
ከዛች ከገራገር ፥ ከደጊቱ ዳሴ
እንደምን ብርቅ ይሁን ፥ ሰላም ለእለት ጉርሴ
ኧረ እንደምን በምን
ኧረ እንደምን በምን
አምነን ያነገስነው ብራ ቀን ይዳምን
እኔን አፈር ይብላኝ ፥ ለእኔ ቀኑ ይክፋ
አንቺን ያሳጣችሽ ፥ ያች አለም ትደፋ
እስከ መች አስከ መች ፥ የአረር ሙዳይ ቋጥረን
እንደጃኖ ኩታ ፥ ዝናር ጥለት አርገን
ሀገር እያጠፋን ፥ ያልፋል እንላለን ?
እንዴት ነው መሰንበት ?
መውዜር እንደነዶ በሚመዘዝበት?
ኧረ እንደምን በምን
ኧረ እንደምን በምን
አምነን ያነገስነው ብራ ቀን ይዳምን?
.
ከጩኸትሽ ማዶ ፥ ካኮረፈው ሰማይ
ቄራ ከመሰለው ፥ ከአድማስሽ ሸራ ላይ
እብሪት ያጠላበት ፥ ምስል ድንገት ካየው
ለቸር አንመስለኝም ፥ ያን ጊዜ ፈራለሁ
አርብ አርቡን አመሻሽ
የሰማዩ ገላ ሲመስል የደም ሻሽ
ንትብ የለበሰ
ከወደ አንገቱ ዘሞ የተዘለሰ
ይሁዳሽን ባላይ ፥ ወድቆ ሲያንሰራራ
መስቀል ሆኗል ለሻጭ ፥ ገዢ ራሱን ያኩራ
ከክርስቶስ ይልቅ ፥ ይሁዳ ነውና ሚረከብ መከራ
ምክኒያቱም ......
ዘመን እያሰፉ
ትውልድ ለሚነቅፉ
ነገር ጠንቷል ዛሬ ፥ አውቀውት ይረፉ
ለሻጭ መስቀል ሊሆን ፥ ምሏልና ዛፉ
.
በኑረት ቀራንዮ ፥ በህይወት ጎለጎታ
ከገዳይሽ ቀዬ ፥ አንቺ ሆነሽ ጌታ
በሰማያ አኮርባጅ ፥ ወዲያ ስትላጊ
የመከራን መስቀል በሌት ተሸክመሽ ፥ መንገድ ስትፈልጊ
ጨረቃዋ ገባች ፥ ከደመና ጉያ
ከዋክቶች ሸሽተው ፥ እንደሰደድ ቋያ
ጠረንሽን ገፍተው ፥ ከገላሽ ሲርቁ
በንቄት ሸምቀው ፥ ሊጥሉሽ ዘለቁ
.
ዞር ብንል ወዲያ ፥ አራራይ መረዋ
ቀና ብንል ኦና ፥ የጠቆረ ህዋ
የፀሎትሽ ጩኸት ፥ ካልደረሰው ያ ' ቃል
እሱም እንደሰዉ ዘምቶልሽ ይሆናል።
..................... //// ..............
©ሲራክ ወንድሙ @siraaq
የእቴሜቴ ጀምበር
ህዳር ፳፻፲፬ ዓ.ም
https://tttttt.me/getem
https://tttttt.me/getem
Telegram
ግጥም ብቻ 📘
✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።
✔ @getem @serenity13
✔ @wegoch @Words19
✔ @seiloch @shiyach_bicha
✔ @zefenbicha
@leul_mekonnen1
✔ @getem @serenity13
✔ @wegoch @Words19
✔ @seiloch @shiyach_bicha
✔ @zefenbicha
@leul_mekonnen1
👍4
Forwarded from ግጥም ብቻ 📘 (C-ራክ)
🍋የዋርካ ስር ጤዛ 🍋🍋
🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋
........... ©ሲራክ ......
በእለተ ከተራ ፥ በበዓል ዋዜማ፣
አደባባይ ሳይሽ ፥ ደምቀሽ በሃገር ሸማ ፣
ወርውር ወርውር አለኝ ፥ ሎሚውን ግዛና፣
ሎሚ ሻጭ ፈለግኩኝ......
ጎዳናውን ሙሉ ፥ ስዞር አመሸሁኝ።
በጥምቀተ ባህር ፥ ህዝብ ሁሉ በሆታ ፣
እያጨበጨበ ፥ ታቦቱን አጅቦ ሲገባ በእልልታ፣
ማጨብጨብ ተስኖኝ ...
እልልታ ጠፍቶብኝ...
ሎሚ ፈልጋለሁ ፥ ከአይኔ ሳትጠፊብኝ።
ይኸውልሽ ውዴ ....
አትታደል ሲለኝ ፥ ቢጠፋ ነው እንጂ ..
እድሌ ባይቀና ፥ ብኩን ብሆን እንጂ..
ከአስራ አምስት ቀን በፊት ፥ ለጨዋታ ብዬ ፣
ለገና ጨዋታ ፥ ለአሲና ገናዬ ፣
ዱላ እየፈለግኩኝ ፥ ከጫካ ገብቼ ፥
ሎሚ ጨፍጭፌያለሁ ፥ ዛፉን ተመኝቼ ።
እድል እንደዚህ ናት ፥ የዋርካ ስር ጤዛ ፣
ይኸው እኔ ዛሬ ፥ በዋዛ ፈዛዛ፣
እልፍ የሎሚ ዛፍ ፥ ጨፍጭፌ ሳበቃ፣
አንድ ሎሚ አጣው ፥ ለአንቺ የሚበቃ ።
አዬ እድል እያልኩኝ ፥ ከወደ አመሻሽ ፥ ከቤቴ ገብቼ ፣
ሎሚ ዛፍ ተከልኩኝ ፥ ለዓመቱ አስልቼ ።
እስከዛ ግን አንቺ .....
ሎሚ ወርዋሪዎች ፥ በሌሉበት መንገድ
ሂጂልኝ ግድ የለም፣
ዘንድሮን ያለፍኩት ፥ ሎሚ ቢጠፋ እንጂ...
ፈርቼስ አይደለም።
ወርውር ያለኝ ልቤ .....
ተግቶ ተሰናድቶ ፥ ዓመቱን ጠብቆ፥ በእለተ ከተራ ፣
እመጣለሁ ብሏል ፥ ከአስር ሎሚ ጋራ።
🍋🍋🍋🍋የዋርካ ስር ጤዛ 🍋🍋🍋🍋
--------- ሲራክ ወንድሙ @siraaq
@getem
@getem
@getem
🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋
........... ©ሲራክ ......
በእለተ ከተራ ፥ በበዓል ዋዜማ፣
አደባባይ ሳይሽ ፥ ደምቀሽ በሃገር ሸማ ፣
ወርውር ወርውር አለኝ ፥ ሎሚውን ግዛና፣
ሎሚ ሻጭ ፈለግኩኝ......
ጎዳናውን ሙሉ ፥ ስዞር አመሸሁኝ።
በጥምቀተ ባህር ፥ ህዝብ ሁሉ በሆታ ፣
እያጨበጨበ ፥ ታቦቱን አጅቦ ሲገባ በእልልታ፣
ማጨብጨብ ተስኖኝ ...
እልልታ ጠፍቶብኝ...
ሎሚ ፈልጋለሁ ፥ ከአይኔ ሳትጠፊብኝ።
ይኸውልሽ ውዴ ....
አትታደል ሲለኝ ፥ ቢጠፋ ነው እንጂ ..
እድሌ ባይቀና ፥ ብኩን ብሆን እንጂ..
ከአስራ አምስት ቀን በፊት ፥ ለጨዋታ ብዬ ፣
ለገና ጨዋታ ፥ ለአሲና ገናዬ ፣
ዱላ እየፈለግኩኝ ፥ ከጫካ ገብቼ ፥
ሎሚ ጨፍጭፌያለሁ ፥ ዛፉን ተመኝቼ ።
እድል እንደዚህ ናት ፥ የዋርካ ስር ጤዛ ፣
ይኸው እኔ ዛሬ ፥ በዋዛ ፈዛዛ፣
እልፍ የሎሚ ዛፍ ፥ ጨፍጭፌ ሳበቃ፣
አንድ ሎሚ አጣው ፥ ለአንቺ የሚበቃ ።
አዬ እድል እያልኩኝ ፥ ከወደ አመሻሽ ፥ ከቤቴ ገብቼ ፣
ሎሚ ዛፍ ተከልኩኝ ፥ ለዓመቱ አስልቼ ።
እስከዛ ግን አንቺ .....
ሎሚ ወርዋሪዎች ፥ በሌሉበት መንገድ
ሂጂልኝ ግድ የለም፣
ዘንድሮን ያለፍኩት ፥ ሎሚ ቢጠፋ እንጂ...
ፈርቼስ አይደለም።
ወርውር ያለኝ ልቤ .....
ተግቶ ተሰናድቶ ፥ ዓመቱን ጠብቆ፥ በእለተ ከተራ ፣
እመጣለሁ ብሏል ፥ ከአስር ሎሚ ጋራ።
🍋🍋🍋🍋የዋርካ ስር ጤዛ 🍋🍋🍋🍋
--------- ሲራክ ወንድሙ @siraaq
@getem
@getem
@getem
👍32❤23🔥4👎1
#ቅድመ_ጥንቃቄ
.
©ሲራክ ወንድሙ
.
አዳም እንዳይቀና - በሄዋን ገላ ማሳ ፣
ደረቱ ላይ ጠፈው - ጡት መሳይ ጠባሳ ።
............. °°°°°^^^ ....×××××××.........
https://tttttt.me/getem
.
©ሲራክ ወንድሙ
.
አዳም እንዳይቀና - በሄዋን ገላ ማሳ ፣
ደረቱ ላይ ጠፈው - ጡት መሳይ ጠባሳ ።
............. °°°°°^^^ ....×××××××.........
https://tttttt.me/getem
Telegram
ግጥም ብቻ 📘
✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።
✔ @getem @serenity13
✔ @wegoch @Words19
✔ @seiloch @shiyach_bicha
✔ @zefenbicha
@leul_mekonnen1
✔ @getem @serenity13
✔ @wegoch @Words19
✔ @seiloch @shiyach_bicha
✔ @zefenbicha
@leul_mekonnen1
❤14👍11👎3😱3
የተስፋ ቃል እርሾ ፩
© ሲራክ ወንድሙ
አንቺ ስትመጪ ...
የጎበጠው ቀና ፣
መንገዱም ጨርቅ ሆነ ፥ ያልገራው ጎዳና ።
ዝጉ ተከፈተ ፥ ወለል አለ በሩ ፣
የተጣላ ሁሉ ፥ ታረቀ ከእግዜሩ ።
አንቺ ስትመጪ ....
የመሸው ቀን ነጋ ፥ ፀዳል ሞላ ቀዬው ፣
ያስጨነቀው ሁሉ ፥ ሄደ እየለቀቀው ።
ችሎት ሞቴ ያለ ፥ ጓሮ ተሰማራ ፣
በቀን ጦስ የጎሸው ፥ ድፍርስርሱ ጠራ ።
አንቺ ስትመጪ ....
ቀናት አዲስ ሆኑ ፥ ተዋቡ በልኩ ፣
መልከ ጥፉ ኮራ ፥ ናኘበት በመልኩ ።
ሁሉም ፥ ላይሆን ሆነ ፤
አለሙን የተኛ ፥ ቀጣፊ ታመነ ።
.......................
የካቲት ፳፻፲፬ ዓ.ም
https://tttttt.me/getem
© ሲራክ ወንድሙ
አንቺ ስትመጪ ...
የጎበጠው ቀና ፣
መንገዱም ጨርቅ ሆነ ፥ ያልገራው ጎዳና ።
ዝጉ ተከፈተ ፥ ወለል አለ በሩ ፣
የተጣላ ሁሉ ፥ ታረቀ ከእግዜሩ ።
አንቺ ስትመጪ ....
የመሸው ቀን ነጋ ፥ ፀዳል ሞላ ቀዬው ፣
ያስጨነቀው ሁሉ ፥ ሄደ እየለቀቀው ።
ችሎት ሞቴ ያለ ፥ ጓሮ ተሰማራ ፣
በቀን ጦስ የጎሸው ፥ ድፍርስርሱ ጠራ ።
አንቺ ስትመጪ ....
ቀናት አዲስ ሆኑ ፥ ተዋቡ በልኩ ፣
መልከ ጥፉ ኮራ ፥ ናኘበት በመልኩ ።
ሁሉም ፥ ላይሆን ሆነ ፤
አለሙን የተኛ ፥ ቀጣፊ ታመነ ።
.......................
የካቲት ፳፻፲፬ ዓ.ም
https://tttttt.me/getem
Telegram
ግጥም ብቻ 📘
✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።
✔ @getem @serenity13
✔ @wegoch @Words19
✔ @seiloch @shiyach_bicha
✔ @zefenbicha
@leul_mekonnen1
✔ @getem @serenity13
✔ @wegoch @Words19
✔ @seiloch @shiyach_bicha
✔ @zefenbicha
@leul_mekonnen1
👍21❤15🔥7
#አበባ_አየሁ
©ሲራክ ወንድሙ
እሩቅ ለሩቅ ሆነን
ይጠባል መስከረም ፥ ይታጠናል ህዳር
ፀደይ እየዳኸ
ክረምት ይጋልባል ፥ ተስፋዬን ሳሳምር
አምና በዚህ ሰዓት ፥ ጠበቅኩሽ በውርጩ
እስኪያልፍብኝ ሀሩር ፥ ወፎች እስኪንጫጩ
ጠበቅኩሽ ፥ ጠበቅኩሽ
የሌት ውብ እንቅልፌን ፥ በናፍቆት መጅ ድጬ
በመምጣትሽ እርሾ ፥ ልቤን አሳብጬ።
የአንቺ ሀገር ወዴት ነው የአድማስሽ አቀበት ?
እግሬን ላወላዳ ፥
ይቆምልኝ እንደው የልቤ ትኩሳት
ተይ ንገሪኝ ባክሽ ፥ ወዴት ነው ባዕቱ
ካቻምና ላይ ቆሜ ፥ መነነ ዘመኑ ከነፈ ጊዜያቱ
የተራራው ደረት በአደይ ፂም ጎልምሶ
የሀምሌ ጨለማ
ባባረረው ብርሃን ፥ ሲሄድ ተለሳልሶ
እንደው ለአዲስ ዓመት ፥ ትጋቴን አስታውሰሽ
ናፍቆት ፣ ተስፋ ፣ ፍቅርን - አንድ ላይ ታቅፈሽ
በሬን ከፍተሽ ግቢ ፥ አበባ - አየሁ ብለሽ
....
©ሲራክ @siraaq
https://tttttt.me/getem
©ሲራክ ወንድሙ
እሩቅ ለሩቅ ሆነን
ይጠባል መስከረም ፥ ይታጠናል ህዳር
ፀደይ እየዳኸ
ክረምት ይጋልባል ፥ ተስፋዬን ሳሳምር
አምና በዚህ ሰዓት ፥ ጠበቅኩሽ በውርጩ
እስኪያልፍብኝ ሀሩር ፥ ወፎች እስኪንጫጩ
ጠበቅኩሽ ፥ ጠበቅኩሽ
የሌት ውብ እንቅልፌን ፥ በናፍቆት መጅ ድጬ
በመምጣትሽ እርሾ ፥ ልቤን አሳብጬ።
የአንቺ ሀገር ወዴት ነው የአድማስሽ አቀበት ?
እግሬን ላወላዳ ፥
ይቆምልኝ እንደው የልቤ ትኩሳት
ተይ ንገሪኝ ባክሽ ፥ ወዴት ነው ባዕቱ
ካቻምና ላይ ቆሜ ፥ መነነ ዘመኑ ከነፈ ጊዜያቱ
የተራራው ደረት በአደይ ፂም ጎልምሶ
የሀምሌ ጨለማ
ባባረረው ብርሃን ፥ ሲሄድ ተለሳልሶ
እንደው ለአዲስ ዓመት ፥ ትጋቴን አስታውሰሽ
ናፍቆት ፣ ተስፋ ፣ ፍቅርን - አንድ ላይ ታቅፈሽ
በሬን ከፍተሽ ግቢ ፥ አበባ - አየሁ ብለሽ
....
©ሲራክ @siraaq
https://tttttt.me/getem
Telegram
ግጥም ብቻ 📘
✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።
✔ @getem @serenity13
✔ @wegoch @Words19
✔ @seiloch @shiyach_bicha
✔ @zefenbicha
@leul_mekonnen1
✔ @getem @serenity13
✔ @wegoch @Words19
✔ @seiloch @shiyach_bicha
✔ @zefenbicha
@leul_mekonnen1
👍34❤29👎2🔥2
ይመስላል ፍለጋ
@siraaq
.
ለበራድ ፡ ጎጆዬ ፡ እንዲሆናት ፡ ብዬ ፥ ፍሙን ፡ ብልክላት፣
ያቺ ፡ የአደራ ፡ ፍሜ ፥ በመንገድ ፡ አግኝታ ፡ ቦታ ፡ ብትጠይቃት ፣
አላውቃትም ፡ ብላ ፥ ዘማ ፡ አሳለፈቻት።
ፍም ፡ አላት ፡ ይሉኛል ፥ አይሞቃትም ፡ ዳሴን፣
ነብስ ፡ አለህ ፡ ይሉኛል ፥ አልሞላም ፡ በድኔን።
ፈልጌ ፡ አስሼ ፡ አገኛት ፡ እንደሆን ፥ ውብ ፡ ቀኔን ፡ ብሰዋ፣
አልተገናኘችም ፡ ከጥንት ፡ እስከዛሬ ፥ ነብሴ ፡ ከስጋዋ።
....****......*****.....
መስከረም ፳፻፲፭ ዓ.ም
''''''''''''''''' ' " ''''''''''''''''''''''''''
©ሲራክ ወንድሙ
@getem
@getem
@getem
@siraaq
.
ለበራድ ፡ ጎጆዬ ፡ እንዲሆናት ፡ ብዬ ፥ ፍሙን ፡ ብልክላት፣
ያቺ ፡ የአደራ ፡ ፍሜ ፥ በመንገድ ፡ አግኝታ ፡ ቦታ ፡ ብትጠይቃት ፣
አላውቃትም ፡ ብላ ፥ ዘማ ፡ አሳለፈቻት።
ፍም ፡ አላት ፡ ይሉኛል ፥ አይሞቃትም ፡ ዳሴን፣
ነብስ ፡ አለህ ፡ ይሉኛል ፥ አልሞላም ፡ በድኔን።
ፈልጌ ፡ አስሼ ፡ አገኛት ፡ እንደሆን ፥ ውብ ፡ ቀኔን ፡ ብሰዋ፣
አልተገናኘችም ፡ ከጥንት ፡ እስከዛሬ ፥ ነብሴ ፡ ከስጋዋ።
....****......*****.....
መስከረም ፳፻፲፭ ዓ.ም
''''''''''''''''' ' " ''''''''''''''''''''''''''
©ሲራክ ወንድሙ
@getem
@getem
@getem
👍37🔥5❤3