ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ሀገር በውር ድንብር በጭፍን ሲመራ
መንገዱ እንዲታዬን እስኪ አብሩ ደመራ ፡፡

#ሜሮን_ጌትነት

@getem
@getem
Forwarded from Mykey (Mikiyas Liyew (Mykey))
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መልካም በዓል
@Mykeyonthestreet
#የአንቂ በላተኞች!

(ሚካኤል አስጨናቂ)

።።።።።።።።።።።።።።

ዘጠኝ ሰዓት ሲሆን፤

ዶሮዬ ቀስቅሶ በለገሰኝ ንቃት

እሱን እያረድሁኝ ...

ፅልመቴን ገፍፌ እደርሳለሁ ንጋት።

።።።

ድሮውንስ ቀስቃሽ በማን ይወደዳል?

ህዝብ ንቃ ሲሉት.. .

ምሁር አልይ ብሎ ዲን ድንጋይ ያዘንባል

ነብይ አስጠፍንጎ ወንበዴን ያስፈታል።

።።።።

ንጉስም በተራው...

ማሸለቡ ይብቃህ ንቃ ያሉት 'ለት

ነብዩን ሳይሰቅል አያገኝም እረፍት።

@getem
@getem
@getem
አንድነት በሀገሬ
"""""""""""""""""""

ሰይጣን ተሳቀቀ
ከጦቢያ ሀገሬ
ታስሮ ተጠፍንጎ ወደ ሩቅ ተመራ፤
በአንድ ቢውሉበት
ጁምአ ስግደትና የመስቀል ደመራ፤
በአንድነት ስንፀልይ
ሰማይ የታከክን ሆነናል ተራራ፤
አቤት ስናስፈርራ
አቤት ስናኮራ!!!

አብርሃም
@Run_Viva_Run

@getem
@getem
@getem
ገጣሚው ዝም ይላል!
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።።።።።።።
#ኸረ ነይማሽን!
ታዘቢው ምድርሽን
ቃላት ፈንጂ ሆነው ፥ ባንዳ ተጨነቀ
ቅኔያት አብረው ...
ያበጃጁት ገመድ ፥ ጠላትን አነቀ።
እስቲ ታዘቢልኝ.. .
ሀገሬው በሙላ ፥ ጠፍቶት ስንኝ ውሉ
መንጋ ናቸው ሲባል ...
ስማቸው ሳይጠራ ፥ እኛ ነን ይላሉ ።
እንኪያስ ምን እንበል.. .
ከአዳምነት ጎራ ፥ ማንነቱን ሽሮ
ሰው ውሻ ነኝ ካለ ፥ በቃል ተደናብሮ
ሳልሰይመው ደርሶ ፥ ሳልጠራው ከመጣ ፥ አቤት ብሎ ካለ
ገጣሚው ምን ግዴ?
አንተ አይደለህ አልለው!
በመንጋነት ግብር ፥ በውሻነት ስሌት ፈቅዶ እየዋለ :)

@getem
@getem
@getem
ለምሽታችን
💚


ኢትዮጲያችን ጥላሁን ገሰሰ
በስንታየሁ አለማየሁ

መደመም ውሰጤን ሲሞላው
ግርምት አፌን ሲያሲዘኝ
እንዲህ ባዲስ አመት በር
በመስከረም የአበባ ወር
አንድምታዬን መግለፅ ሲያመረኝ
ጥላሁን ነው ትዝ የሚለኝ፡፡
ጋሼ ዛሬ መስከረም 17 ዕለት በሕይወት ቢኖር ኖሮ 79ኛ ዓመቱን ይይዝ ነበር፡፡ ክቡር ዶከተር አርቲስት ጥላሁን ገሰሰ ዛሬ ልደቱ ነው፡፡ እንደ ጥላሁን አይነቱን ምርጥ ኢትዮጲያዊ ስብዕና ዓመቱን ሙሉ ዘክሮ ፣ ዓመቱን ሙሉ ሲያከብሩት ቢዘልቁ ከፍ ያለ ደስታና ክብር የሚያስገኝ ነው የሚመስለኝ፡፡
ንጉሱን ዛሬ በልደቱ ቀን እናስታውሰው ብለን እንጂ መቼስ ስለሱ ያልተባለ ፣ ያልተፃፈ እና ያልተነገረ ነገር ሳይኖር ቀርቶ አይደለም፡፡ ጥላሁን ከኢትዮጲያ ሰንደቅነቱ ባለፈ በመስከረም ወር ተፈጥሮ በድምፁም ወርሃ መስከረምን ያነገሰ ፣ የአዲስ ዓመት መባቻን አድምቆ በአድባርነት የቆመ እውነተኛ አርቲስት ነው፡፡
ከልጅነት እስከ እውቀት አዲስ ዓመት ሲመጣ ፣ በዓሉን በዓል ከሚያስመስሉልን ጣዕመ ዜማዎች ውስጥ እንደ ዘሪቱ ጌታሁን እንቁጣጣሽ ፣ እንደ አስቴር አወቀ እዮሃ አበባዬ ሁሉ የጥላሁን ገሰሰም ወርቃማ ስራዎች ይገኙበታል፡፡ ጥሌ እንቁጣጣሽ ሲል ፣ የ 13 ወር ፀጋ ሲል እንዲሁም ክረምት አልቆ በጋ ሲል እንደተለመደው ትንፋሹ ከስጋ አልፎ ከነፍስ የሚሰካበት ዘዬ አለው፡፡
በያመቱ ለኛ እንቁጣጣሽ
ደስ ይበለን እንኳን ደህና መጣሽ
እያለ አደይ አበባዋን ልክ እንደ ሰው በመልካም ምኞት ይቀበላታል፡፡ ሰለኛ ስትል መውጣቷንም ከገጣሚው ተቀብሎ በውብ ዜማው ከሽኗታል፡፡ አበባን የአይን ቀለብ ፣ ልምላሜን የመንፈስ እርካታ አድርጎ የማድረግ ስነ-ልቦናዊም ፣ ሰዋዊም ሳይንስ አለ፡፡ ይህንኑ እውነታ ነው ጥላሁን ያውመ ከአዲስ አመት መንፈስ ጋር አገናኝቶ በውብ ድምፁ ያቀነቀነው፡፡ በአበቦች መዓዛ መርካታችንንም እንዲህ አስረግጦ ገልጧል….
ክረምት አልቆ በጋ
መስከረም ሲጠባ
አውዳመት አልፎ
አዲሱ ሲገባ
በአበቦች መዓዛ ረከቷል ልባችሁ
ረክቷል ልባችሁ
ሕዝቦች ሁሉ በጣም እንኳን ደስ አላችሁ
እንኳን ደስ አላችሁ፡፡
የአዲስ ዓመት መባቻን በዚህ አይነት የደስታ መንፈስ ያውድና ….የማይሰለቸው ጥላሁን የ13 ወር ፀጋ ሲል ከጰጉሜ እስከ ጰጉሜ ዓመቱን ሙሉ ስላሉን ክብረ በዓላት ፣ ጭፈራና ፈንጠዚያዎች ፣ ሰርጉና ፋሲካው ፣ ውብ ኢትዮጲያዊ ቀለሞችን በዜማው ሲያሳምር እናስተውላለን፡፡
በፀሀይ ብርሃን ደምቃ ክረምትና በጋ
የትውልድ ሃገር ያላት የ አስራ ሶስት ወር ፀጋ
ወግና ልማዳችን የወረስነው ካበው
አውዳመቱ ትዝታው አይጠፋም ያው ነው
.
እንኳን ደረስክ ሲባባል
ወዳጅ ከጎረቤቱ
ትዝታው መች ይጠፋል
አቤት ማስደሰቱ፡፡
.
አቤት ባዲሱ አመት
ዘመኑ ሲለወጥ
ያበቦቹ ሽታ መአዛው ሲመስጥ
ኮበሌው ሲጨፍር
ሲል መስከረም ጠባይ
ኮረዳዋም ባታሞ
ስዞር በራሷ ቀዬ
አሲዮ መስቀል ሲመጣ
አሲዮ ደምቆ ደመራ
ሁሉም በደጁ ችቦ ሲያበራ
በልጅ ባዋቂው ደምቆ ጭፈራ
በልልታ ሎጋ ደምቆ ሲደራ
ከብረው ይቆዩን በሚል ጨዋታ
የልጅ ምርቃት ያባት ስጦታ
እያለ ይቀጥልና ስለ ገና ጨዋታው ፣ ስለ ጥምቀቱ ፣ ስለ ፋሲካው ያነሳሳና ወዲያ ተሸግሮ ስለ ሐምሌና ነሐሴ ዳመናና ሰብል ብሎም ስለ ቀጣዩ ቡሄ ዳግመኛም ስለ መስከረም እንዳሻው በሰጠው ድምፅ እንዳሻው ዓመቱን ያስሳል…..ኑሯችንን ይቃኛል፡፡

ዛሬ ጥላሁንን ማውጋት ፣ ጥላሁንን መፃፍ ፣ ጥላሁንን መተረክ የፈለኩት ልደቱ ስለሆነ ነው፡፡ ነገር ግን ጥላሁንን ለማንሳት ደግሞ ምን ምክንያት ያስፈልጋል…..እሱን ለማንሳት ምክንያት ፈለግን ማለት ስለ ኢትዮጲያ ለማውራት ሰበብ ፈለግን እንደማለት ነው……በኔ እምነት ሀገርን ለመተረክና ስለሃገር ለመወያየት ሰበብ አያስፈልገንም…ጥላሁንም እንዲያ ነው ለኔ፡፡
እንደሱ ያሉትን ምልክትና አድባር የሆኑ ሰዎች አብዝተን ብናስታውስና ብንዘክር ዘወትር እንደሚባለው መሰል ዜጎችን ለማፍራትም ሁነኛ መላ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ በአንድ ወቅት በዚሁ በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ስለ ጥላሁን በተፃፈው ፅሁፍ ውስጥ እንዲህ የምትል አረፍተ ነገር አንብቢያለሁ…..” ዘፈን ለጥላሁን የእንጀራ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሕይወት ቁስል ማከሚያ መድኃኒት መሆኑንም በታሪኩ ውስጥ እናያለን፡፡ ምናልባትም ከብዙ አድናቂዎቹ በላይ በዘፈኖቹ ስሜቱ የሚነካው ጥላሁን ራሱ መሆኑን ስናነብ ፣ ጥላሁንን እንደ አዲስ የማወቅ ስሜት ይሰማናል” ትላለች፡፡
ጥላሁን ኢትዮጲያዊ ስሜቱን ለማከም ተፈጥሮ በሰጠችው ተሰጥኦ በትንፋሹ ሲታገስና ሲያባብል የኖረ ይመስለኛል፡፡ ህማሙንና ቁስሉን ፣ ማዘንና መደሰቱን ሁሉ በሀገሩ ስር ሆኖ በሃገሩ ቃል ሀገርን እየጠራ አንጎራጉሮላታል፡፡ የሚዘፍናትን ኢትዮጲያ ለማለት ብቻ የሚላት ሳይሆን ሆኖ የሚተውናት ናት፡፡ ጥላሁንን ማስታወስ የክፍለ ዘመናችንን ሙዚቃ መዳሰስ ነው…..ብንጠቅሰው ብንዘረዝረው አያልቅም ፣ ትንፋሹ ያረፈባቻውና የሱ ድምፅ በኪነት ያባበላቸው ሃሳቦች የትየለሌ ናቸው…ሁሉም እንደየመረዳቱ መጠን የተለየ አተያይ የሚመዝባቸው ስራዎቹም በርካታ ናቸው፡፡ ጥላሁንን ለመግለፅ ሻለቃ ክፍሌ የደረሱለትን ዜማውን እራሱ ጥላሁን ያሰናዳውን አንድ ምርጥ ስራ ልጥቀስ …..
“በአካል ሳይፈተን በአካል ሳይነካ
የማን ምንነቱ ግብሩ ሳይለካ
እርግጥ በተፈጥሮ በወል ስም ይጠራል
በቁም ነገር መድረክ ሰው ከሰው ይለያል”
ይህ ስራው መልሶ እራሱን ጥላሁንን የሚገልፅልኝ ድንቅ ስራው ነው…….ጥሌ ጥሩ ሃሳብ ሲያገኝ ዜማውን በሚፈልገው መንገድ እራሱ የመስራት ልምድም እንዳለው ባለሙያዎች ሲናገሩ ሰምቻለሁ….በቁም ነገር መድረክ ሰው ከሰው እንደሚለይ ጥላሁን እራሱን ማየት በቂ ነው፡፡ ሀገራችን ውስጥ እንደነ ኤፍሬም ታምሩ ፣ ቴዲ ታደሰ ፣ ሂሩት ፣ ሙሉቀን መለሰ ፣ ነዋይ ደበበ ፣ አለማየሁ እሸቴ ፣ ሚኒሊክ ወስናቸው ፣ አስቴር አወቀ ፣ ብዙነሽ በቀለ ፣ እጅጋየሁ ሺባባው ፣ ቴድሮስ ካሳሁን ፣ እዮብ መኮነን ፣ ዘሪቱ ከበደና የመሳሉት ብዙ የሙዚቃ ሰዎች አሉን ይሁንና ከሁሉ በላይ ከፍ ባለ ስሜትና ጥልቀት….በመሰጠት ሙዚቃን መስሎ ሳይሆን ሆኖ በመኖር ፣ አያሌ ቁምነገሮችና ሀገራዊ አተካራዎችን አሳምሮ በማንጎራጎር ፣ ሲሻው እንደ አርበኛ በል ሲለው እንደ ተዋናይ ባስቀመጡት መድረክ ልክክ ብሎ አምሮ በከፍታ በመስራት ጥላሁንን በቁምነገር መድረክ ሰው ከሰው ይለያል ብንለው….ጎልቶ መለየቱን ብንነግረውና ዛሬም በምናብ ብናወጋው ስህተት እንደማንሰራ አውቃለሁ፡፡
ጥላሁን በተጠየቀበት መድረክ ሁሉ እንጉርጓሮ ህይወቱ መሆኑን ያለ እንጉርጓሮ መኖርም ማሰብም እንደማይሻ ሲናገር ብዙ ጊዜ አድምጠናል፡፡ የሱ እንጉርጓሮዎች ሁሉ ጌጦቻችን ፣ ትንፋሾቹ ሁሉ እስትንፋሳችን ሆነው ስሜታችንን በመኮርኮራቸው ምህኛት ይህ ሰው ትክክለኛው የሙዚቃ ወዳጅ ብቻ ሳይሆን ጥላሁን ማለት ሌላው የሙዚቃ ስሟ ነው ብለን ቁጭ ብድግ ብለንለታል….ለዘመናት በስሜት ትውልድ ተቁነጥንጦለታል፡፡
ጥላሁን ኢትዮጲያ በምትፈልገው ቦታ ሁሉ አቤት ብሎ ያልተሰለፈበት ቦታ ቢገኝ ከህይወት ካለፈ በኋላ ነው፡፡ እንጂ ኢትዮጲያ ስትራብ….
ዋይ ዋይ ዋይ ሲሉ
የርሃብን ጉንፋን ሲስሉ
እያዘንኩኝ ባይኔ አይቼ
ምንላድርግ አለፍኳቸው ትቼ
ሲል በእንባ ታጅቦ ወቅቱን በሚገባ በሚችለው ተሰጥኦው ከትቧል…ስሜቷን ስሜቱ አድርጎ ለአለም በድምጡ አውግቷል፡፡ በጦር ሜዳ ውሎ እነ ዘማች ነኝን ፣ እነ አጥንቴም ይከስከስ ፣ እነ ወደፊት በሉለት
ስንታየሁ:
ይለይለትን ፣ ለውዲቷ ሀገሬን የመሳሰሉትን በመጫወት ከወታደሩ ጎን መሆኑን ፣ ሀገር የሁላችን አድባር የሁላችን አለኝታና መከታ
👍1
መሆኗን ሲያንጎራጉር ኖሯል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ጥላሁን በሴት መስሎ በፍቅር አምሳል የተጫወታቸውንም ስራዎቹን ብናይ ትንፋሹ ሊገልፅና ሊወክል የፈለገው ሀገርን እንጂ አንዲትን ኢትዮጲያዊ ሴት ላለመሆኑ ግልፅ ነው…..ለምሳሌ የጠላሽ ይጠላ ሲል ፣ እኔ ልሁን እንጂ የማልጠቅም ርካሽ ሲል ፣ እዩአት ስትናፍቀኝ ሲል በዚያ ገፀ ባህሪው ኢትዮጲያ ናት….ቁስሉና ርሃቡ ሀገር ናት፡፡ ከመጀመሪያ ስራው ጥላ ከለላዬ ጀምሮ እስከ መጨረሻ ስራው ቆሜ ልመርቅሽ ድረስ ሀገር በትንፋሹ ስትነግስ ፣ በድምፁ ስትከብር ኖራለች፡፡
በቀጣይነት ጥላሁንን እንደ አርበኛ ፣ እንደ ሙዚቀኛ ፣ እንደ ተዋናይ ምን ሰርቶ እንዳለፈ ፣ ምናችን እንደነበረ እንቃኘዋለን፡፡ ብሎም ብዙ ሊተነተኑ የሚችሉ ሙዚቃዎቹን እያስተነተንን በምናብ ከርሱ ጋር እናወጋለን …በመልክት ለቀጣይ ተተኪ የቤት ስራ እናኖራለን….በግርምት በስራዎቹ እንደሰታለን ብዬ አስባለሁ፡፡
‹‹ትንፋሼ ተቀርጾ ይቀመጥ ማልቀሻ
ይህ ነው የሞትሁ’ ለት የኔ ማስታወሻ››
ብሎ ነበር ንጉሳችን፡፡ በእርግጥ እሱ እንዳለው ትንፋሹ ነው ማስታወሻችን ብለን ከሃሳቡ መስማማት እንችላለን…በትንፋሹ ውስጥ የገለፃት ኢትዮጲያ ነችና…..በውስጣችን ለዝንታለም ትንፋሹ ትንፋሻችን ኆኖ ዘልቋል ይዘልቃልም፡፡


መልካም ዕለተ መስቀል ይሁንላችሁ

# ከታቢው ስንታየሁ አለማየሁ


#እኛም ጋሽ ጥላሁንን ለመዘከር በድምፅ አንጎራጉረናል

ሸጋ ምሽት!💚
@getem
@getem
@balmbaras
(በረከት በላይነህ)
.
.
*የማጋራት ጣዕም*
ብልህ!
ስንጥቅ ምጣድ ጣደ ፣
ሽንቁር ድስቱን ጣደ ፤
ቅጠሉን ፣
እንጨቱን ፣
ኩበት ...ምናምኑን በእርጥቡ ማገደ ።
.
እንክርዳዱን ፈጨ ፣ ያለእርሾ አቦካ ፤
የነቀዘ ጓያ በሽሮ ስም ከካ ።
.
ዲቃላውን ድንች ፣
ከደረቀው ሽንኩርት ፣
ከወየበው ጎመን ፣
ከሸክላው በርበሬ - ያለጨው ቀየጠው ፤
ከዚያ !
"እንብላ !" ይለናል 'በሰው' ሊያጣፍጠው
............ ገፅ 66 ............
የመንፈስ ከፍታ

@getem
@getem
@getem
////አስፈራኸኝ///


ቀድመህ ወደድከኝ ....እሺ ወደድከኝ
እንደወደድከኝ .... ባይንህ ነገርከኝ
እየወደድከኝ..... እየፈለከኝ
ቀርበህ ለመንገር .... ምነው ፈራኸኝ?
እጆቼን መያዝ ..... እየተመኘህ
በፍርሀት ሲርድ ..... መለ አካልህ
አይኖቼን ደፍረህ ...... ማየት ካቃተህ
ወይ አልቀረብከኝ ..... ወይ እኔ አልራኩህ
ከሩቅ ስታየኝ ..... ከሩቁ ሳይህ
ላታስጨርሰኝ .... እያሰጀመርከኝ
እውነት አንተ ልጅ .... ፈርተህ አስፈራኸኝ

///***ሀና ሰዋለ***///

@getem
@getem
@getem
ያልወደደ አበደ
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
በሰው የደረሰ...
በኔ ላይ እንዳይደርስ ፣ ስፈራና ስቸር
ወድጄሽ እንዳላብድ ፣ ስጠነቀቅ ነበር፡፡
ታድያ ምን ያደርጋል
በከንቱ ፍርሃት ፣ ባክኖ መጠንቀቄ
ዋናው እብደት ነበር ፣ ከመውደድ መራቄ፡፡

@getem
@getem
ለምሽታችን
💚


ዛሬ ከግጥም ውጪ በሆነ ጉዳይ ነው ሀሳብ እንድትሰጡበት ስለፈለኩኝ ነው #በተለይ ሴቶች


ለውብ ቀን!
💚

# እቃወማለሁ !!!
# ሴትን_ከእውቀቷ_ይልቅ_በቁንጅናዋ_መመዘን_ለምትፈልጉ
( በዓለም ለ40ኛ ፣ በሀገራችን ለ32ኛ ጊዜ የሚከበረውን " የዓለም የቱሪዝም ቀን "
ምክንያት በማድረግ የአዲስ አበባ ባህል ፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ከመርሀ ግብሮቹ
መሀል የቁንጅና ውድድር ማካሄድ መሆኑ እጅግ የሚያሳፍር ነው ። ለሴቶች የተሻለ ስፍራን
እሰጣለሁ በሚል መንግሥት ስር ፣ ቢሮው ኪነጥበብን ያህል የለውጥ መሳሪያ በእጁ እያለ
የሴቶችን ቁንጅና ( አካል ) ለቱሪዝም ቁስ አድርጎ ማቅረቡ እጅግ አሳዛኝ ነው ። ዓለም
ሴቶችን በቁንጅና የሚያወዳድርበትና እንደ ሸቀጥ የሚሸጥበት የራሱ ዓላማ ይኖረዋል ።
50% ሚኒስትሮቿንና የርዕሰ ብሔርነት ወንበሯን ለሴቶች እኩልነት የሰጠችው ኢትዮጵያ
የሴት ልጆቿን ገላ አራቁታ ለገበያ ማቅረቧ ግን ጊዜውን የማይዋጅ ክብረ ነክ ድርጊት ነው
። # ከፍልስምና ፬ አሳቢዎች አንዱ # ቡርሐን_አዲስ ስለ ቁንጅና ውድድር ይህን ብሏል ።


# ቴዎድሮስ፦ “የቁንጅና ውድድር” የሚባለው ነገር ከዚህ ጋር ተዛምዶ ነው የሚታየኝ፡፡
ዓለም ሴት ልጅን አሳንሶ ካየባቸው መንገዶች አንዱ የቁንጅና ውድድር ነው፡፡ ሴትን
ከሃሳቧና ከእውቀቷ በላይ በማይወዳደር ቁንጅናዋን መለካት ቀጣይ እርምጃው የወሲብ
ባርነት መስሎ ነው የሚታየኝ፡፡ እነዚህ የቁንጅና ውድድር አዘጋጆች ለሽንፈታቸው
“ውስጣዊና ውጫዊ የሚል ስያሜ ቢሰጡትም በሐሳብ መወዳደርን ከቁንጅና ውስጥ
አውጥቶ መመዘኛ ማድረግ ሲቻል አንድ ላይ የጠቀለሉት “ውስጣዊ ቁንጅና” የሚባለው
የውጫዊው መሸፈኛ ስለሆነ ነው፡፡ የውጪውን ትተህ የአማራን፡ የጋምቤላን፣ የኦሮሞን፣
የትግራይን፣ የደቡብን ሴቶች በአንድ መስፈርት መዳኘት ሴትን ከሰውነት አውርዶ ሸቀጥ
መደርደሪያ ላይ ማስቀመጥ መስሎ ይሰማኛል፡፡ አሁን ስትናገረው ደግሞ አንተ
ከገለፅካቸው ህብረተሰብን ማደንዘዣ መንገዶች አንዱ መደረጉን አስባለሁ፡፡ “የዘር ካርድ”
ላይ ያነሳኸውን በሽፋን የማጥመድ ስልት አያይዘህ ብታይልኝ፡፡

# ቡርሐን ፦ ሁኔታዎቹ በጣም የተያያዙና በጥናት የመጡ ናቸው፡፡ ፍሩይድ “ወሲብ
ባህሪያችንን ይቃኛል” አለ፡፡ ከዚያ በፊት ለነበሩት በሃይማኖትም ሆነ በሞራል ለሚመሩት
ህዝቦች ግን የወሲብ ስሜትህን መቋቋም መቻልህ ነው አንተን ትልቅ የሚያሰኝህ፡፡
በስሜት ላይ የበላይ መሆን ነው ሃያልነት፡፡ ግን “ስሜት ነው የሚገዛን” ብሎ ስነ ልቦናውን
ሲያመጣው፣ ማህበረሰቡ ቁስ ሸማች መሆንና ገንዘብ ዋና ገዥ መሆን አለበት የሚል
አስተሳሰብ ሲዳብር “ሰዎች የእኛ አስተሳሰብ ደጋፊና ተከታይ ብቻ እንዲሆኑ ለማስቻል ምን
ማድረግ አለብን?” ብለው ነው እንደገና ተቀምጠው የመከሩበት፡፡ በቃላትም በሐሳብም
ጨዋታ ነው የተያዘው፡፡

"ዘመናዊነት" (modrnism ) የሚለውን ቃል ራሱ የስልጣኔ ሳይሆን የኢኮኖሚ ቃል ነው።ስልክ እንቀያየር ብለን ሁለታችን ስናወጣ የአንተ ሳምሰንግ በመሆኑና የኔ ጣና ሞባይል
በመሆኑ ብቻ እኮ የኔን ሸሸግ አደርገዋለሁ፤ የኔ የተሻለ ቢሠራም እንኳ:: ከዚያ ውጭ
ለአዕምሮህ፣ ለተፈጥሮህ፣ ለሞራልህ ሳይሆን ለስሜትህ የሚሆኑ እንደነ ቁንጅና ውድድር፣
ሞዴሊንግ፣ ፋሽን የመሳሰሉት የተከሰቱት በዚያ ነው፡፡ ሰዎች በስሜት እንዲመሳሰሉ
ካደረግህ ተመሳሳይ ምርት ብታመርትም ተመሳሳይ ገዥ ታገኛለህ፡፡ ውበት የሚባለው ነገር
እኮ በተፈጥሮ ወይም በእውነት ሳይሆን በፋሽኑ ኢንዱስትሪ እንዲዳኝ ነው የተደረገው፡፡
ነጮቹ “ቅጥነት ነው ቁንጅና” ካሉ ቀጭኗ የተሻለ ዋጋ ታወጣለች፡፡ እሷ የምትለብሰው
የዘመናዊ ፋሽን ምልክት ተደርጐ ስለሚቆጠር ዋጋው ከፍ ያለ ይሆናል፡፡ ግን በእርግጠኝነት
ውበት ማለት ቅጥነት ነው እንዴ? ለማን? “ድንቡሽቡሽነት” ከውበት መለኪያነት ተሰረዘ
ማለት ነው? ማን ነው የኢትዮጵያዊቷ ሴት ውበት ለኪ? በትክክል ካሰብን ግን እያንዳንዱ
ማህበረሰብ የራሱ የሆነ የቁንጅና መለኪያ አለው፡፡ የአንዱ ለሌላው አይሰራም፡፡ እንዴት
አድርገህ ነው በባህል፣ በሐሳብ፣ በአኗኗር ከማይገናኝ ዓለም ላይ ሰብስበህ አንድ የዓለም
ቆንጆ የምትመርጠው?

የሞዴሊንግ ትልቁ ሥራው ሸቀጥ ማሻሻጥ ነው፡፡ እውቀት አይደለም፡፡ ሐሳብ አይደለም፡፡
የሞዴሊንግ ዓለም እየሰፋ ከሄደ ራሳቸው ሴቶቹ ቆንጆ ለመሆን የውበት መጠበቂያ
ምርቶችን በብዛት ይጠቀማሉ፡፡ ቆንጆ የምትላት ሴት መጀመሪያ በተፈጥሮ ማንነቷ
እንዳልተወዳደረች በሂደት ግን የቁንጅና መጠበቂያ ምርቶችና የሜክአፕ ግዞተኛ ትሆናለች፡፡
ያለ ሜክአፕ በፍፁም ከቤት የማትወጣ ትሆናለች፡፡ ሴቶቹ ላይ የማይሠራ ሙከራ
(Experiment) የለም፡፡ የከንፈር ቀለም እኮ ብዙ መቶኛው ቫዝሊን ነው፡፡ ሰባት ብር
የሚሸጠውን ቫዝሊን የሆኑ ኬሚካሎችን ጨማምረህ የከንፈር ቀለም ማድረግ ዋጋውን
ውድ ያደርግልሃል፡፡ የከንፈር ቀለም ዋና ምንጩ ወሲባዊ ስሜት መፍጠር ነው፤ ከንፈርን
ከብልት ጋር ማመሳሰል ነው፡፡ ሰውነትን ይበልጥ እርቃን ማድረግ ነው፡፡

አንዳንድ ማስታወቂያዎችም እንደ ከንፈር ቀለሙ ናቸው፡፡ የምታስተዋውቀው የለስላሳ
መጠጥ ሆኖ የምታሳየው ግን ለወሲብ የቀረበች ሴትን ስሜት ነው፡፡ “ለምን?” ስትል
በትክክል ፋሽን በራሱ ሐሳቡ የሸቀጥ ገበያ ስለሆነ ነው፡፡ ፋሽን አዕምሮን፣ ስነልቦናን
የማውረድ መንፈስም አለው፡፡
ትራክተር ወይም መኪናን በሴት ማስተዋወቅ ትርጉሙ ምን ነው? ሴቷን አይተህ መኪናውን
ታያለህ ለማለት ነው:: እኔ እንደው ሴቶቻችን በጣም ቢያስቡበት የምለው ፆታዊነትን ነው፡፡
በጣም ቢያስቡበት መልካም ነው፡፡ “የፆታ እኩልነት” የሚለውን ትርክት በጣም በጣም
በአፅንኦት ረጋ ብለው ቢያዩት በጐ ነው፡፡ ሴቷ “ወንዱ የሚሠራውን መሥራት አያቅተኝም”
ከሚለው ወጥታ በጨዋ መንገድ “ወንድነት ምንድነው?”፣ “ሴትነት ምንድነው?” የሚለውን
መመርመር በጣም ያስፈልጋል፡፡



የፆታዊነትና የፆታ እኩልነት ትርጓሜ በራሱ ችግር ያለው ነው፡፡ ራሱ ላይ ነው ትልቅ ችግር
የፈጠረው፡፡ ዛሬ ሴትን የምትለካት በእውቀቷ አይደለም፤ በጥበቧ አይደለም፤ በምርምሯ
አይደለም፡፡ የምትለካው በቁንጅናዋ ነው፡፡ አንጀሊና ጁሊና አንጌላ አሜሪካን ቢቀርቡ ለማን
ነው ትኩረት የምትሰጠውና ማንን ነው የምታከብረው? ጥቅል አሳቢነት ላይ አይደለም
ሴቶቹን የምትፈልጋቸው፡፡ እንደውም አሁን አሁንማ የሴት ቦታ የሚመስለን ሸቀጡአካባቢ
ነው፡፡ ስለዚህ ሴትን የምንለካበት መነፀር ራሱ ከስጋነቷ ውጭ ክብር የሰጠ አይደለም፡፡
ግን እውነት ሴት ቦታዋ ይህ ሆኖ ነው እንዴ? ማሰብና መመራመር ሳትችል ቀርታ ነው
እንዴ? ሸቀጥ እንደሆነች ተደጋግሞ ፕሮፓጋንዳ መሠራቱ ያመጣው ውጤት ነው፡፡ ባል
እንዴት አድርጐ ከሚስቱ ሐሳብ ይጠብቃል? ሚስቱ ተውባና ተቀባብታ የወሲብ ማሽን
ሆናለት እንድትኖር ነው የሚፈልገው፡፡ ይህም አስተሳሰብ የGlobal consumer Culture
Society ውስጥ ነው፡፡ አራት ነጥብ፡፡

------------------------------------------------


#በዚህ ሀሳብ ላይ አስተያየት ብትሰጡበት #በተለይ ሴቶች

@getem
@getem
@balmbaras
👍3
Senedu 👇👇👇

እኔ ስልጣን ቢኖረኝ መጀመሪያ እምከለክለው ማስታወቂያ መስራትን ነው ።
ለነገሩ ከእግዜሩ ጀምሮ ወንድ ሆኖ በምንመራበት አለም ብዙ ማለትም አይቻልም ።
በወተት ውሰጥ ቅቤ መደበቁን ያወቁ ሴቶችን ፣ ጥጥን ሸማ አርገው ያለበሱ ሴቶችን
ጥበብ ከካደና ከቀማ ዓለም ብዙ ተስፋ አልጠብቅም ።
ከሸቀጥነት ወርደን ፈጣሪ የለገሰንን ሰውነት በኘላስቲክ ሰርጀሪ እስከመቀየር ደርሰናል ኮ ።
ካፒታሊዝም ዘመኑን ጨርሶ እስክንገላገል መላው የራቀ ነው ።

ቡርሐንዬ ምርጤ ።💚


Black ሴት:👇👇👇


እኔ ሙሉ በሙሉ በዚህ ፅሁፍ እስማማለሁ
ከልጅነትህም እኮ ቤተ ዘመዱ ሲመርቅህ ጥሩ ባል...እያለ ነው😁እንጂ ተምረህ ተመርቀህ አይልህም በውበታቸወደ መለካትም ሚፈልጉ ይኖራሉ
ቆንንጆ ወይም ሴት ስለሆነች ብቻ ሁሉ ነገር እንደምፈፅም ምታስብ አጠፍም በራሷ እጅ ሴትነቷን ምታወርድ ሰርታ ማሳየት ሳይሆን በፆታዋ ምታምን
አንደኛዋን ባየንበት ሌላዋን ማየትም አግባብ አይደለም ሁሉሏን ሴት በአንድ ሚፈርጁ አሉ
አንዳንዴ ሴቶች አራሳችን እራሳችንን ማስከበር ይኖርብና
ለምሳሌ ሞዴል ልትሆን ውድድር ሄዳ ሙሉ ራቆትሽን ቁሚ ማለት ምን ይሉታል?
በገዛ ፈቃድም እርቃን ሚሄድም አለ
በተለይ ሀገሬ ላይስንመጣ ደሞ ድንቅ ሚለኝ ክሊፕ ሊሰራወይ ፊልም እራቆት ልብስ ለብሳ ወይ እንብርት ታሳይና ምነው ስትላት ዘመናዊ... እኔ ምለው ግን ልክ እንደ ማንነቷ መገመት እንጂ ድብልቅልቅ አርጎ ሴት ሆሆሆሆ ማለት ቢታሰብበት

Essias Belachew👇👇👇


ተፈጥሯዊቷን እና ሀገር በቀሏን የሀበሻ ቆንጆ ባላየ አልፈን በሜካፕ
ያብረቀረቀች እና አርቴፊሻል ውበት ያጠለቀች ሴት እየመረጥን ለሴቶቻች መረን መውጣት
መንገዱን ጨርቅ ያደረግንላቸው እኛ አይደለንም እንዴ?
እስቲ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሙስሊም እህቶቻችን የሚያደርጉትን ቀሚስ ተመልከት፡፡
የወገብን ቅጥነትና የዳሌን ስፋት ከራቁት በላይ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ አይደለም እንዴ?
ይህ ለምን ሆነ? ወንዶችዬ ሴቶችን የምንፈልጋቸው ለዛ ስለሆነ ነው፡፡
የትኛው ባል ነው ሚስቱን አማክሮ ቢዝነስ የሚሰራ? ለነገሩ የዘመኑ ቢዝነስ እንኳን ከሰው
ከራስም አያማክር፡፡ ግን ሴት የወንድ ደጋፊ እንደመሆኗ መጠን የጎደለህን ነው
የምትሞላልህ፡፡ የጠየቀካትን ነው የምትመልስልህ፡፡ ያደረካትን ነው የምትሆንልህ፡፡ ልቧ
እየደማም ቢሆን፡፡


Hana Getachew:👇👇👇


Awe gn setochn betam aweredachuhachew malete kesetochu ylk sraw ymeslegmal yastelachhu bergt enem bzum aldegfewm belela ager yetegezan yakl new yemisemagn gn agelalethachu betam setochn aweredebgn

Mknyatum mekom sayhon hidetun mastekakel tlk neger new bye asbalehu maletm egnam yerasachnn yebahlachnn yemiyakorann yehager lbsachnn saygelalet yemiyaswbu bzu negeroch alun slezih endemannetachn bnseletnbet bay negn


2 demo sra blo yeyazew bzu sew ale makomu tekebaynet bzum aynorewm aymeslhm gade ?

3 demo yeset liji wbet medebeka endehone ye ahun zemen sew bzum ayamnm wbet bemegelalet slemimeslen tnsh lemekeyer ykebdal



Sûmëyã:👇👇👇

mejemeriya dereja ene bebekule yetefetro lyunetachnn ena ekulnetn bnley des ylegnal.ekul edme lay Yalu wend ena set akrbek blhnetachewun bfetsh yesetua liyamezn ychlal gulbet demo yewendu....leza ekulnetachnn be tefetro banlekaw elalew .......fation betkklm kastesasebua ylk wuchawi melkua ledaggnet mikerbbet new.enesu tefetrowan madnek new ylalu gn ewunetaw gn aemrowan kechawetaw awutto be wuchiyawi akalua endtasb mareg new


NH^2:👇👇👇


Allah lemn endefeteregn awkalew.....betam bzu menged kefite ale esun slemak etegalew....wend slehone bcha endemibeltegn endiyasb alfekdletm....."yekunjna wuddr" kalu rasu lk aydelem....enen mimesl wub yelem ko enesu gn endesua kalhonsh wub adeleshm lillugn yfelgalu beallah sra talka ligebu asbew yhon?....alfelglachewm yenesun fashion kotetam ybelugn...fara nech ybelu.....and haq awkalew and ken mekebel maychlut kefta lay endemgegn!!

Yemr amesegnalew slegna egna banakm wendneth yayehewun ewuneta endatnager slaladeregeh amesegnalew.....


Ego Ego:👇👇👇

ለኔ እዚ የምናየው ዓለም ላይ ያለ ነገር በሙሉ ልምድና የልምድ ውጤት ነው
መውለድና መወለድንም ጨምሮ የልምድ ፈጣሪዎች ደግሞ እኛው ነን አብዛኞቻችን መንገዳችንን የመረጥነው ያለፈውን ትውልድ በመከተል ነው የጨመርነው አልያም ያሻሻልነው ነገር ይኖራል እንጂ የፈጠርነው አዲስ ነገር የለም ግን ራሳችንን ከመሆን በመነሳት የምንለውጠው ነገር ይኖራል

ሴቶች ላይም እንደዛው ነው
ለኔ የወንድና የሴት ልዩነት ከተፈጥሮ ያለፈ ነገር የለውም
ልዩነት ብለን የምናስቀምጣቸው አይምሮአችን ውስጥ ቀድመን ያለማመድናቸውን ሃሳቦች ነው የፆታ እኩልነት ውልደት በራሱ ነገሮችን በውስንነት ከማየት በሚመጣ ሃሳብ የተገነባ ነው ይህን ሃሳብ ለመፍጠር አልያም ሴቶች ዝቅ ባለ መንገድ ለመታየታቸው ራሳቸው ሴቶች ትልቁን ድርሻ ይወስዳሉ ባይ ነኝ

ሰዎች እኛ ላይ የሚኖራቸውን አስተሳሰብ የምንፈጥረው ራሳችን ስለሆን!

የሌሎቹ አስተያየት በቀጣይነት የሚመጣ ነው በዋናነት ሴቷ ራሷ የምትፈልገውን ነገር ለማግኘት ሴትነቷን አልያም ውበቷን መጠቀምን ትመርጣለች ይሳካላታል ትገፋበታለች ስለዚህ ጊዜዋንም የምታጠፋው የምትፈልገውን የሰጣት ውበቷ ላይ ስለሚሆን እውቀቷንና ሃሳቧን ከመጠቀም ትቆጠባለች ምንም ነገር መፍጠር የሚችለው አይምሮዋ መታየት አይችልም አካላዊ ገፅታዋ ብቻ ይጎላል

እንግዲ አስቡት ራሷን የምታስብበት መንገድ ከራሷ አልፎ ለሌሎች ይታያል
ስለዚህ ሌሎች ስለሷ የሚያስቡት ነገር አያስገርምም
ሁሉም የምርጫችን ውጤት ነው ራቁትሽን ሾው አርጊ ስትባል ያስገደዳት የለም ትልቁ የስኬት መንገዷ አድርጋ ስላሰበችው እንጂ

ሁላችንም ኃላፊነትን መውሰድ እንለማመድ ባይ ነኝ
ራሳችንን መሆን መርሃችን ይሁን!
------------------------------------------


#በጣም እናመሰግናለን አሁንም ሴቶች ሀሳባቹን ብትሰጡበት ደስ ይለኛል




# ሸጋ ምሽት!!💚


@getem
@getem
@balmbaras
👍1
Betty Tesfaye:👇👇👇

takaleh 1 1giza bemtayew bemtsemaw neger wede rash ye hiwot flsfna tgebaleh enam yrashn mnged tketelaleh gn ya menged yet yadershal bergt bzu erkata ltagegnbet tchilaleh lemsalia enia ye 2008 temeraki negn enam fetari ymesgen tru bemibal wtiat new yetemerekut bihonm gn yenia ye alebabes style ke sraw ga slemayhiad srawn mesrat alfelekum le 1 amet yahl berasia menged hiadku malet new kezam zendro ke samnt befit ቤተሰቦቸን masdest sleneberebgn ena erasianm mekeyer slalebgn wede bank industry tekelakelku bachiru be hiwotia matat yemalfelgachewn negeroch atahu malet new (bachiru achir lbsm hone suri lebshe alakm neber) gn yebankun formality lemamualat sibal achir lbs melbes gd new kezam lebesku gn hlinaye likebelew alchalem kerasia ga megachet jemerku( ayto yetemegnat endamenezerebat kutr new) so manew tfategnaw yemil tyakia selam alsetegn ale kezam gelayen kemasay suri yshalal alkun sefi suri lebesk (siat ye wendn wend ye siatn ylebs zend altefekedem) bachiru bzu selam yeminesu negeroch endalu hulu yemiyasgeddh negerm ynoral. enantes yhn endiat tayutalachihu?


ZION:👇👇👇


ላነሳኸው ሀሳብ.......

ምን አልባት ሁሉን ሰው አሁን ስላለው የሴቶቻችን ነገር ብትጠይቅ ዘመኑ ነው ሊልህ ይችላል።ዘመን እኔ እና አንተ ነን ለምናረጋቸው እያንዳንዱ ነገር ሁላችንም ሀላፊነት ያለብን።እውነት ነው ከትላንት ዛሬ ሁሉም ሴት ለውጥ አለው ።በምን ብትል ግን . ...ስለ ልብሷ፣ስለ ውበቷ ...ብቻ ነው አልልህም።ከምታውቃቸው ሴቶች መሀል ስንቶቹ በ አእምሮአቸው ፣በአስተሳሰባቸው፣በመልካምነታቸው ትጠቅሳቸዋለህ????ያን የምልህ እናንተም ወንዶች ስለኛ ያላችሁ ግምት ምን ያህል እንደሆነ እንድታስብ ነው።አንድ ጓደኛህ ፍቅረኛ መያዙን ቢነግርህ የመጀመሪያ ....ከሁሉም ጥያቄህ በፊት ምንድነው ምጠይቀው??????? ሁላችንም እናውቃለን "ቆንጆ ናት ???እስኪ አሳየኝ"ነው ምትለው አደል ወንድሜ??.....ግን ለምን ???ለምን ስለ መልካምነቷ ፣ ከፍቅረኝነት አልፋ መልካም እናትነቷ፣ባጠቃላይ ስለ ስብእናዋ መጠየቅ ከበደ????
እህታችንን በዙሪያ ያሉ ሴቶችን ስለ ስብእናቸው ውበት ስለ ሀይማኖታቸው ህግጋት አንነግርም እናም እንወቃቀሳለን ።

Amsal Fentie:👇👇👇


Menesat yalebet gudey nw mkniyatum bzu giza kekrbachin yalen neger tkuret ansetewm malet setochi bzu giza golto mtayetn nw mnfelgew beka andanda enkuan kom blen masebn anfelgm beka endezemenu mehon ye wuchun fashin meketel berasachin behal mekurat eresan ewnet lemenager ahun yalenbat zemen enkuan betam nw miyasazn ahun wede fashinu snmeta enkuan betam nw miyasafrew setup lji bezi melku mttay khone ewnetm lesetochi yewrede kbr mtaybet mdrek nw yhin fashin eko wede bahlawi lbsochi dizine biyadergut yteshale neger mftar ychalal bye asbalew


#በጣም እመሰግናለው ሁላችሁንም 🙏🙏


ሰላም እደሩልኝ!💚

@getem
@getem
@balmbaras
#ኧረ_አምሳለ!
(ምልዕቲ ኪሮስ ኃይሌሥላሴ)


ሰዉ በዘመን ጅረት...................
ዘመን በሠዉ ጀርባ እንደገሠገሠ
ይኸዉልሽ እንግዲ ክፉ ቀን ደረሰ...
ይኸዉ እንዲ ሆነ:
አንች ስትሄጅ;-
ፀሀይ ጠዋት ቀረች
ጨረቃ አኮረፈች
ሰማይ አለቀሰ
መሬት ተቆረሰ
ጨዋታ ፈረሰ....
አንች ሳትኖሪ:-
አኩኩሉ አይነጋም...
በሰኞ ማክሰኞ ዉብ ቤት አይገዛም ...
በሌባና ፖሊስ ባባሮሽ ጨዋታም...
እንደሮጠ ቀርቷል ማንም ሰዉ አልመጣም....
ህፃናቱ ከቦ አሁንም ቁጭ ብሏል...
መሐረቤን ብሎ አንድ ልጅ ይዞራል...
ህፃናቱ ከቦ ቁጭ ብሏል አሁንም...
መሃረቡን ያየም አየሁኝ አይልም ...
ብጫቂ መሐረብ መች ሆነና ቁቡ...
ነገረ ጨዋታዉ አንች ነሽ አሳቡ....
ኧረ አምሣለ.... ኧረ ሆይ...
ጨዋታ ለዛ አጣ አንዴ ብቅ በይ....
የህፃናት ተረት ከግማሹ አለቀ...
ትመጣለች ብሎ አንቺን የጠበቀ....
ቤትና ሃገር ቤት የሚል ሃሳብ መክኖ...
የሀገሪቱ ጉብል ቀረ ተበትኖ...
እንካ ስላንትያ እንቆቅልሻቸዉ...
ሳይፈታ ቀረ እርቀሽባቸዉ....
'ቢበስል ባይበስል ትመጭ ይመስል'
ብለን ያሟረት ነዉ....
ለካስ አንች ላይ ነዉ....
ኧረ አምሣለ ኧረ ምነዉ...
ደጅሽ የተከልሽዉ ምን አይነት እንኮይ ነዉ....
ያዉም በአኩኩሉ በዉሸት ጨዋታ...
እንደተደበቀች እሷ ብቻ ቀርታ....
ምድር በትካዜ ሰማይ በመከራ...
አለ እስካሁን ድረስ እምባዉን ሲያዘራ.....
የምሥኪኑ ደሀ አገዳዉ አሽቶ...
ይሄዉ ባንች ምክንያት ዝናቡ በርትቶ....
የቀየዉ ገበሬ እህል ተበላሸ....
ኧረ አምሳለ እያለ በነጋ በመሸ.,.
ያገር ሽማግሌ ያገሪቱን ዳኛ...
ስልጣኑን ወሠደዉ ነጠቀዉ ቀማኛ.,.
ፍርድ ተጏደለ...
ድሃ ተበደለ...
መነኩሴም ያለቅሳል ኧረ አምሣለ እያለ .....
ኧረ አምሣለ ኧረ ሆይ....
ያሳደገሽ መንደር አይናፍቅም ወይ....?
የእናቶች እህታ የህፃናት እምባ....
ወዴት አደረሰሽ ወዴት ይዞሽ ገባ....
የእረኛ እሮሮ...
ያዝማሪ ከበሮ...
የገጣሚ ዋይታ...
ያጋፋሪ እምቢልታ....
የዋሽንቱ ቅኝት ዜማና ምታቸዉ...
ኧረ አምሣለ ሆነ አፍ መፍቻ ቋንቋቸዉ....
አለመምጣት አለ...
አለመምጣት አለ አለመተያየት...
ባንድ አምሣለ ናፍቆት ግጥም ብሎ መቅረት....
ስለእማምላክ ቢሉት አንጀቱ ሚራራ...
በራብሽ ከች የሚል ከጭንቅሽ 'ሚጋራ....
ሀገር-እግር የለዉም ወጥቶ አይፈልግሽም...
እርግማኑም ክፋ ላንችም አይቀናሽም...
ወንዝና ተራራም ወገን አይሆንሽም....
....... እናም...
ሠዉና ቀየዉን እያሠናሠነ...
የጉብሉን መዝሙር አጣፍጦ የከየነ....
ሰዉ ማለት... ሰዉ ማለት ...
ሰዉ ማለት ሃገር ነዉ ባይልም በቃሉ....
ይግባሽ አንድ ሚሥጥር - ሰዉን ከሠዉ ብቻ የመቀላቀሉ::

@getem
@getem
@getem
1👍1
የመክፈቻውን መልክ!!!!!!


ለተዘጋው ህይወት፤
ወርጅናሌ አድርጎ፤
አይተኬ አድርጎ፤
ልዩ መክፈቻ አርጎ፤ የሰራህን ጌታ፤
ህልሙን አትንጠቀው ፤
ቁልፍህን አትሸቅጥ፤
ያልተሰጠህን በር፤
ግር ብለህ አትግፋ፤
በእንዝመት መፈክር በመንጋ ጫጫታ፤
ይኸው ዛሬ ድረስ፤
ቁልፉ ጩኸት በልቶት፤
ተከርችሞባታል፤
የተፃፈችልህ ያንተ በር ተዘግታ።


ሁሉም የራሱን ቁልፍ፤
የመክፈቻውን መልክ ማየት ተዘናግቶ፤
በሩ ዳዋ ዋጠው፤
የየሰው በራፍ ፤
በጅምላ እንክፈት ባይ በጩኸት ተዘግቶ።
ያልተሰጣቸውን በር እየደፈሩ፤
የቁልፋቸውን ልክ፤
የበራቸውን ልክ ምስጢር ሳያጠሩ፤
ኑ እንክፈት ሲሏቸው፤ ደቦ እየሰገሩ፤
እነ ያለቦታው፤
ሞኝ ቁልፍ ይዘው በየሜዳው ቀሩ።


የሰሪህን ምኞት፤
የጥሪህን ማጀት ፤
ከተዘጋው ህይወት ፤
ከጨለማው ጎታ፤
ነጥቀህ እንድትዘርፍ ፤
ዘርፈህም እንድትሰጥ፤
የተሰጠህን ዘር ዝረፍና ውሰድ እንደ ዳልጋ አንበሳ፤
በራስ መሆን ቁልፍህ፤
ያንተን በር ክፈት ያንተን መክሊት አንሳ።

(( ጃ ኖ ))💚💛❤️

ሸጋ ምሽት!💚

@getem
@getem
@balmbaras
1
Tinsu:👇👇👇

Ya I guess he is right now a days bzu astesasboch sele site lej yalewn vision eyekeyerew new ye sensation mastawkiyaw ke HIV mekelakelun kemenager yeleke ke site gar adero miyagegnbetn erkata yastrwawkal (bamarch shapam site codomun yastrwawkal) ye pasta wastawkiyawm pastaw be 3 dekika endemibesel lemasetewawk sitetuwa kesera meta baluwa bite erbot tekofuso ke lejochu gar erabene eko sile misteyew ke sera wed kushena asgebto pastaw endebeselelt yastrwawkal bzu gizi site lej goal achieve setaderge advertisement ayseram gen sele fashion show bzu telkete selilelegn menager aldeferen from what I know gen zir r a lot of things to do to improve our level of advertising

Thank you


Emebet T:👇👇👇

በነገራችን ላይ ለዚህ እንደ ተጨባጭ ማስረጃ በፂ ያነሳችው ሀሳብ በቂ ነው እኛነታችንን የረሳን እየመሰለኝ ነው ሰው እያወቀ እንዴት ደደብ ይሆናል እየተማረ እንዴት ይነፍዛል እንዴት በገዛ ገንዘቡ ሞትንስ ይገዛል በገዛ ሚሞሪው የሚፈልገውን ሳይሆን የሚፈልጉትን ለምን ይጭኑበታል እኛ የህዳር አህያ ነን እንዴ መጠየቅ ያረጋል ሊቅ ብሎል ያ ሞኙ ገበሬ። እኔ አሁን የማወራላችሁን ምን አልባት የሚገባቹ የሆነ አንድ ከውጭ የመጣ ፈረስ አጣቢ ሲነግራቹ ነው አልያም የቆዳ ቀለሙ የበጨጨ ዝንጀሮ ነው እኔ መናገሬን አላቆምም እየሄድንበት ያለው መንገድ የሚያጠፋን ነው። በተለይ ስጡን የሆንን ሰወች የምንጠቀመው ምን እና ምን እንደሆነ ብንለይ ባይ ነኝ

ለሴቶች የፌሚኒስት አይዲያ ይዘው የሚሞገቱ ተከራካሪወች እንዳላቹ ባቅም አንዳቸው ግን የሴትን መስፈርት አያሟሉም እላላው እኔ ለምን ከሆነ ጥያቂያቹ መጀመሪያ የኛ ሀገሮቹን ማለቴ ነው ስለ ባህላቸው አያውቁም እርግጥ ባህል ሁሉ ትክክል ነው ሳይሆን ጠቃሚውን ማስቀጠል አንድ ጥያቄ ልጠይቃቹ ስንማር የሴትን ብልት መገረዝ በዘመነው ሰው አስተሳሰብ በሽታ አለው ይላላሉ ዘመናዊነት የመጣው እንደኔ ለኛ ከ አፄ ቴድሮስ ዘመን በኃላ ነው ይህም ማለት ከ 1800 ጀምሮ ማለት ነው ኢትዮጵያ ከዛ በፌት ቢያንስ በትንሹ ለመቶ አመታታት ሴቷቿን ትገርዝ ነበረ ግን በዘመኑ ጥፋት እንደነበረው ያጠና ሰው አለ ወይስ ነጭ መጥቶ ስለነገረን ትክክል ነው ብለን ተቀበልን ሴቶቹስ ፌስቱላ የሚሉት ህመም እንዳጠቃቸው ታውቋል ይገረዙ ግን ማለቴ አይደለም !!!!!


ሲቀጥል እምነት የላቸውም ለምሳሌ የፌሚኒስቶች ትልቁ ግብ ሴት ከወንድ የበላይ ማረግ ነው ያርጉዎት እኔ ምን ጨነቀኝ ነገር ግን ፍፃሜው ይከፋል እኔ እሷ ከሌለች ብቻዬን ነኝ እሷ እኔ ከሌሌለው ባዶ ነች ፍፃሜው የበላ ሆነች ማለት ስሜት የሚባለው ነገር ይጠፋል እሷ በፈለገችው መንገድ መኖር ትጀምራለች ከዛ ተመሳሳይ የፆታ ግንኙነት የሚል ደሞ ይነሳል ልቀጥል. .....


በመጨረሻም የሴይጣን ጮሌ መጫወቻ ሆነን ቁጭ

ፌሚኒስቶችን አንድ ጥያቄ ብጠይቃቸው ደስ ይለኛል ለሴት ነው ለወንድ ነው ጥብቅናቸው
???

ኢቲቪ ዘሞተች በሚል አንድ ፅሁፍ ላይ ድሮ ታላቅ ፌልም ስናይ መሳሳም ቢራ ምናምን በጥቁር ነገር ይሸፈናል አሁን አንድ ወንድ ዘፋኝ ስለ ሴት እየዘፈነ አጠገቡ 15 ትልልቅ ቂጥ ያላቸው ሴቶች መተው እየተሻሻሹት ይዘፍናሉ ይህ ወንድ ከአስራምስቱ የኔ ቸው አስራ ስድስተኛ ሁኜ እንደ ማለት ልቀጥል. ....

በዛ ላይ ለሴቶች ጥብቅና ከቆሙ እኩልስ ከሆኑ አፈርማቲቪ አክሽን ነው የሚሉት እሱ ነገር ሴቶቹ የበላይ እንዲሆኑ ሳይሆን የበታች እያረጋቸው ነው። ይችን እንኮን? ??


በፌልሞቻችን ላይ የሚነገረን እኮ ሴት ከሆንሽ እንደቧንቧ ውሀ ማንም ይከፍትሻል ብሎ እስከመቀልድ በሚያሳይ መልኩ ነው ተውና አታሳምሙን ጣይቱ ብትሰማ ምን ትላላለች ፣ፉራ ብትሰማ ምን ትላላለች ፣ የቃቄ ውርዶት ብትሰማ ምን ትላላለች እንኳን እነሱ ሞተው ስማቸው ብቻ ቀረ ለእብድ ህዝብ መዳኒቱ አልዛይመር ነው እሱን ደሞ ከወጉን ቆዩ ጠላና ጠጅ አረቄ የምታወጣ ሴት ተጨቆነች አሉ አሺ አልናቸው አረቄውም ጠጁም ቀረ እነሱ ቢራ የተባለ በጠርሙስ የታሸገ መጠጥ አመጡልን አሜን አልን ተቀበልናቸው ስንጠጣ የራስ ትተን የሰው አምላኪ ሆነን ቀረን ዘመኑ የንጉስ ነው የአንበሳ ነው የሜታ ነው የዳሽን ነው ፋብሪዎቹ የነማን ናቸው ጠይቅ? ???


ሴቷ እቤቷ ተቀምጣ ሰፌዷን ሰርታ ጥጥ ፈትላ ሸምና ቋጭታ ጥልፉን ጠልፋ ስታበቃ እረ ይቺ ሴት ተሰቃየች አሉ እነሱ እሷ አላላለችም መማር አለባት እሺ ትማር ተማረች ጨረሰች ፈትላ የሰራችውን ቀሚስ አስጥለው ሚኒ እስከርት አለበሷት ልብስ ከዛስ ቢሮ ገባች ሽቶውን ኩሉን ምኑኑን ሰጧት ተቀባባች ይቺ ሴት ዘመነች ከጊዜ በኃላ ፌት ሲገረጣ ቆዳ ገፈፋ እሱ አልሆን ሲል ደሞ ሌላ በመጨረሻ ተስፋ ቆርጣ እቤት ስትቀመጥ ውበት ማለት ውስጣዊ ነው የሚል ሳይኮሎጂ መፅሀፍ ይሸጡላት እንዴት የሚያዎጣ ቢዝነስ ነው ባካቹ ልጀምረው አይደል? ??


በነገራችን ላይ እኔ ባወኩት ልክ አይደለም ማወራው ባየሁት ነው በነገራችን ላይ ከሚኒ እስከርት ዎጋ የሚኒ ሚኒ ሚኒ እስከርት ዎጋ ውድ ነው ለምን መሰላቹ ሀበሻ ውድ ነገር ይወዳል

አቦ ይመቻቹ ሀሳብ ስጡ በሰለጠነ መንገድ እ
Am nationalist


Meg@tg:👇👇👇

ዛሬ በልቤ ያለውን ሃሳብ ነው ያመጣቹት እና በጣም አመሰግናለው:: ልክ ነው እኛ ሴቶችም ብንሆን የተባረክንበትን አላወቅነም፡፡ ሁሌም ቢሆን ከውስጣዊ እውቀታችን ይልቅ ለውጫዊ ደምቀታችን ነው የምንጨነቀው ምክንያቱም የትኛው ወንድ ነው እስኪ ከሴት ልጅ ቁንጅና ይልቅ ውበትዋን ለማድነቅ የተዘጋጀ እሚፈልጋትሰ ለዚ ምስክር እሚሆኑን ደግሞ ሀገርን በማስተዋወቅ ትልቅ ሚና ያላቸው ሙዚቃዎቻን ተጠቃሽ ይምስሉኛል ሁሉም እኮ ስለ ከነፈረዋ ዳሌዋ ቂ..ዋ ነው እነጂ ስለ ሃገር አዋቂነተዋ ሰለ መካሪነተዋ ሰለ እውቀትዋ እኮ የተዘፈኑት በጣም ጥቂት ናቸው በጣት የሚቆጠሩ በጣም ጥቂት ማለት ምናልባት መፈለግ መደነቅስ ምን ዋጋ አለው ይህ ነው ወይ መኖር ትሉ ይሆናል ግን አንዳንዴ እሱም ዋጋ አለው በተለይ ሴት ላይ ይህን ለማወ ደግሞ ራስሽ አጠብቂም ጣኦት መስለሽ አተጠብቂኝም ተብላ ከነልጆችዋ የተተወችን እናት ማየት በቂ ነው ሴትነት ለገባት እና ማንነትዋን ላወቀች ሴት ግን ቦታ የለም የትም ቢሆን ምክንያቱም ጊዜው የማወቅ ሳይሆን የመታወቅ ነው ጨረስኩ አመሰግናለው ፡፡

---------------------------------------------------

#በጣም እናመሰግናለን 🙏


" ናካይታ"💚 ሰላም እደሩ!💚



@getem
@getem
@balmbaras
መስከረም 26 በዉቧ ባህር ዳር ከተማ በግራንድ ሪዞርት እና ስፓ ሽ ዝንቦች አንድ ሆነው ማእድን እንደማይከፍቱ ሁሉ ሽ መጥፎ አመለካከቶችም ኢትዬጵያን እያፈርሱም በሚልመሪቃል የንጉስ ማእድ የተሰኘ ታላቅ የስነ ፅሁፍ ምሽት ተዘጋጅቷል።በፕሮግራሙ
ግጥም
መነባንብ
ወግ
ድስኩር
ፉከራ
ቀረርቶ እና ሌሎችም እዝናኝ ዝግጅቶች በታዋቂ እና አንጋፋ ደራሲያን እና ገጣሚያን ይቀርባል መስከረም 26 ከ 11:ሰአት ጅምር በግራንድ ሪዞርት እና ስፓ እንዳይቀሩ መግቢያ ትኬቱን በ አቢሲኒያ እና በአባይ ባንኮዝ ሁሉም ቅርንጫፎች እና በተለያዩ 20 የሚሆኑ ኤጀንቶች ያገኙታል።

አዘጋጅ ቢራቢሮ ኢቨንት ኦርጋናይዘር
@getem