ግጥም ብቻ 📘
67.4K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
#የአንቂ በላተኞች!

(ሚካኤል አስጨናቂ)

።።።።።።።።።።።።።።

ዘጠኝ ሰዓት ሲሆን፤

ዶሮዬ ቀስቅሶ በለገሰኝ ንቃት

እሱን እያረድሁኝ ...

ፅልመቴን ገፍፌ እደርሳለሁ ንጋት።

።።።

ድሮውንስ ቀስቃሽ በማን ይወደዳል?

ህዝብ ንቃ ሲሉት.. .

ምሁር አልይ ብሎ ዲን ድንጋይ ያዘንባል

ነብይ አስጠፍንጎ ወንበዴን ያስፈታል።

።።።።

ንጉስም በተራው...

ማሸለቡ ይብቃህ ንቃ ያሉት 'ለት

ነብዩን ሳይሰቅል አያገኝም እረፍት።

@getem
@getem
@getem