ገጣሚው ዝም ይላል!
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።።።።።።።
#ኸረ ነይማሽን!
ታዘቢው ምድርሽን
ቃላት ፈንጂ ሆነው ፥ ባንዳ ተጨነቀ
ቅኔያት አብረው ...
ያበጃጁት ገመድ ፥ ጠላትን አነቀ።
እስቲ ታዘቢልኝ.. .
ሀገሬው በሙላ ፥ ጠፍቶት ስንኝ ውሉ
መንጋ ናቸው ሲባል ...
ስማቸው ሳይጠራ ፥ እኛ ነን ይላሉ ።
እንኪያስ ምን እንበል.. .
ከአዳምነት ጎራ ፥ ማንነቱን ሽሮ
ሰው ውሻ ነኝ ካለ ፥ በቃል ተደናብሮ
ሳልሰይመው ደርሶ ፥ ሳልጠራው ከመጣ ፥ አቤት ብሎ ካለ
ገጣሚው ምን ግዴ?
አንተ አይደለህ አልለው!
በመንጋነት ግብር ፥ በውሻነት ስሌት ፈቅዶ እየዋለ :)
@getem
@getem
@getem
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።።።።።።።
#ኸረ ነይማሽን!
ታዘቢው ምድርሽን
ቃላት ፈንጂ ሆነው ፥ ባንዳ ተጨነቀ
ቅኔያት አብረው ...
ያበጃጁት ገመድ ፥ ጠላትን አነቀ።
እስቲ ታዘቢልኝ.. .
ሀገሬው በሙላ ፥ ጠፍቶት ስንኝ ውሉ
መንጋ ናቸው ሲባል ...
ስማቸው ሳይጠራ ፥ እኛ ነን ይላሉ ።
እንኪያስ ምን እንበል.. .
ከአዳምነት ጎራ ፥ ማንነቱን ሽሮ
ሰው ውሻ ነኝ ካለ ፥ በቃል ተደናብሮ
ሳልሰይመው ደርሶ ፥ ሳልጠራው ከመጣ ፥ አቤት ብሎ ካለ
ገጣሚው ምን ግዴ?
አንተ አይደለህ አልለው!
በመንጋነት ግብር ፥ በውሻነት ስሌት ፈቅዶ እየዋለ :)
@getem
@getem
@getem