ግጥም ብቻ 📘
67.5K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
የአንድ ቀን ዘላለም



ከሰው ህላዌ ላይ
ልክ እንደቆጣሪ ትር ትር እያለች
በ'ሽክርክሮሽ ጡዘት
በክብዮሽ ሂደት ዞራ እየገጠመች
የ'ስትንፋስን ኑረት
አስልታ በጊዜ እድሜ እየቀመረች
የእፍታን ጥድፈት
ዘላለም በሚያህል ተረት እያቀፈች
በሽራፊ ሰከንድ
በደቂቃ ክምር
በሰአታት ድምር ሕይወት እያሰላች
የእያንዳንዱ ኗሪ
ታሪክ መከተቢያ
ወጥንቅጥ ሰሌዳ ብዙ አንድ ቀን አለች፡፡
እዚች አንድ ቀን ላይ....
እዚያ ጋር ይሳቃል እዚህ ይለቀሳል፡፡
ልደት ጥሪም አለ ሙት ዓመት ይኬዳል፡፡
ባ'ላዋቂ ሳሚ እምነት ይሰበካል፡፡
ባ'ስብቶ አራጅ ልሳን ክ'ደት ይወደሳል፡፡
በጨቅላው ሳይበቃው
ጉድጓዱ ተምሶም
ሽቅብ ተጎንብሶ ቁልቁል ተንጠራርቶ
በእናት የሚጦር ልጅ
ደልቶት ይታዘላል
በእርጅና አንቀልባው ልጅነቱን ጠርቶ።
የማታ እንጀራውን
ያላ'ሳብ ይውጣል
በቃኝ በማታውቀው በእናቱ አስነጉቶ፡፡
በዚ'ች አንድ ቀን ላይ ይህ በ'ንዲህ እንዳለ
እግዜር ሆይ ያሳይህ ደሞ ይሄም አለ፡፡
" ከብካይ እኔነት
ካ'ለም መንገላታት ከስቃይ ተዛምዶ
ባ'ብሮ መሳይ ኑረት
ሐሴቱ ለራቀው ከዋይታው ተጋምዶ
" < አይመጣም > ያለውን
ደግ ቀኑን ጠርቶ
<እፎይ> ማለት ላሻ ከሽኩቻ ተርፎ
በማ'ረግ አጊጦ
በክብር ተንቆጥቁጦ
የማንነቱ ጥግ የቅድስና ጫፍ ሆኖ ተሰልፎ
" መኖር ለፈለገ
ከምክረ ከይሲ ሐሳብ ነፍሱን ለታደገ
" ፍቅር
ፍቅር
ፍቅር
የስንቆች ሁሉ ስንቅ
የትጥቆች ሁሉ ትጥቅ የፍጡራን ስምረት
ከልቡ ላኖረው
ሳይሰስት የሚያድል የዘላለም ሕይወት..."
ተብሎ ይሰበካል።
ተሰባኪም ያምናል፡፡
በዚች አንድ ቀን ላይ እኔም ይኸው አለሁ...
በታዘብኩት ሁሉ
በስብከት ታጥሬ ይሄንን እላለሁ...
በሰማሁት ሁሉ
በእምነት ተቀፍድጄ እንዲህ አደርጋለሁ፡፡
" ለዘዋሪ ኑሮ ለማይጎበኘው ፅድቅ
ለምኞታም ሕይወት ጥሪት ለሆነው ብርቅ
" ያሰበውን ሁሉ
ያለመውን ሁሉ
ሲያባርረው የሚያልፍ ሳይዝ እጅ ከፍንጅ
ቡትቷም ገላውን
ሲወለድ አጥልቆ
ሲሞት ለሚያወልቀው ለታካች የሰው ልጅ
" ከሕይወት መዝገብ ላይ ጠቅሰናል እያሉ
እያሽቀረቀሩ
ዕውን እየሰረዙ ቅዠት እየሳሉ
< ፍቅር ጥገብ - - ፍቅር ብላ >
< ፍቅር አትርፍ - - ፍቅር ሙላ >...."
የሚሉ ጠቢባን በበዙባት መሬት
አስፈሪ ደንደሳም የጋጋኖ ጩኸት
የሐሳዊ መሲሕ የምኩራብ ላይ ስብከት
የሚመስለኝ ቃሉ ሲያሰግረኝ በምኞት
በክረምት ውድቅት ውስጥ
ወቅትን ተገን አ'ርገው ለድሪያ እንደወጡ
እንደመንደር ውሾች
ስሜት ሲያሽካካብኝ ጠፍቶኝ መላ ቅጡ
የወንድነት ልኬ
የትምክህ'ቴ ጥግ
የሚታይባትን ከወርቅ አብረቅርቆ
ስንቱ ሚመኛትን
ሳያገኝ ያጣትን
< እህቴ > ሚላትን በሀፍረቱ ታንቆ
በአንድ ቀን ተስፋው
የሚኖርላትን
ስውር ፍላጎቱን እንኳንስ ከሌላው ከራሱ ደብቆ
ፍቅር በታ'ምሩ
ከእግሬ ስር አስጥቶ በጭንቅ ሸምቅቆ
< ጥለኸኝ አቲ'ድ >ን
የሚያስለምናትን በእጦት ፍ'ራት ደፍቆ
ኮረዳዋ ሴቴን ላገኝ ወጥቻለሁ፡፡
ለኔ ምቶ'ነውን
ሀገር እንዲያውቅልኝ እጅግ ጓጉቻለሁ፡፡
የዛሬው አንድ ቀን መታያ ቀኗ ነው፡፡
የዛሬው ልዩ ቀን መድመቂያ ቀኗ ነው፡፡
ዕፁብ ድንቅ ሴቴ
ሀያ - ከሁለቷን ዛሬ ትደፍናለች
ለውልደቷ ሐሴት
በሚቃዧት መሐል ዛሬ ትነግሳለች፡፡
በልደቷ ቀን ላይ
ከሚመጡት መሐል 'እገሌም' አይቀርም
ስራው ቢያስጠላኝም
በደንብ አውቀዋለሁ ስሙም አልጠፋኝም
አድጦኝ ብጠራው
ጠብ አይልልኝም ላፌ አይሞላልኝም፡፡
ድልድዩን ተሻግሮ
የታች ሰፈር ልጅ ነው ሲፈጠር የጀለ
እንዲህ መሆኑን ሊያይ
ጉድ አያውቄ ሕዝብም
የሱን መጨረሻ ያኔ ነው የሳለ
የት ይደርሳል ብሎ
በሱ ሽቅብ መውጣት
እንዳ'ዋቂ ሰርቶት በተስፋ የማለለ፡፡
ቅብጠት ሲያለዝበው ተስመነመነና
ላ'ቅመ ማፍቀር ሳይደርስ አፈቀርኩ አለና
" በሙሉ እኔነት ላይ
ፍቅር ያጀገነሽ
ቀጭን ሽንፈቴ ነሽ ከድር የሰለለ
ላግኝሽ አልልም
በልቤ እንደያዝኩሽ
ወዳ'ፈሬ ልግባ" በማለት የማለ፡፡
የኑሮ መስመሩን
ግዙፍ ዐላማውን ቀብጦ ያቀለለ
ለማያገኛት ሲል
ያለአንዳች ስስት አሽቀንጥሮ የጣለ፡፡
እናቱን አውቃለሁ
የእናትነት ማ'ረግ ናቸው ጉልላቱ
ማንም ባይገኝም
ማ'ረግ ሊሰጣቸው የገባው እውነቱ፡፡
ነፍስ ሳውቅ ጀምሮ
እንኳንስ መከታ ድጋፍ ሊሆን ተርፎ
አባቱን አላውቅም
ከስሙ ቀጥሎ ከመሰደር አልፎ፡፡
መከረኛ እናቱ
ላይግል የቆረረ
ቀዝቃዛ ሕይወትን ይዘው በወሳንሳ
የሶስት ሰው ሸክምን
የተተኪ አጋዡን
ፈረቃውን ሁሉ ችለው በአበሳ
በብቻ ትግላቸው
አጋዥ አልባ ሆነው
እዚህ አድርሰዋል የቆመን ሬሳ፡፡
ጠላ ይጠምቃሉ፡፡
አረቄ ያወጣሉ፡፡
እዚያው ጉሮኖ ውስጥ ለንግድ ይወጣሉ፡፡
ከሰካራም ጥጋብ
ከሰካራም ትፋት
በ< ይኼም ያልፋል > ቀንበር እየተናነቁ
ወዛቸው ገርጥቶ
ገላቸው ተፍቆ
የቀይ ጥቁር ሆነው ሆዱን ይሞላሉ፡፡
ላንድያ ልጃቸው
አምሳለ እየሱስ
ከማንም እንዳያንስ ልብሱን ይገዛሉ፡፡
ማንም ሳያያቸው
ከሁሉ ሸሽገው
ለውሎው የሚሆን ኪሱ ይሸጉጣሉ፡፡
በዚ'ች አንድ ቀን ላይ ይህ በ'ንዲህ እንዳለ
እግዜር ሆይ ያሳይህ ደሞ ይሄም አለ፡፡
ያመንኩትን ሁሉ
ያወኩትን ሁሉ
አንዴ እየታዘብኩ አንዴ እየፈከርኩ
በቆንጆ መፈቀር
በልደቷ መድመቅ
ባ'ገር ይወቅ እብሪት ላልነቃ እንደሰከርኩ
................እኔም ይኸው አለሁ..................
በዚ'ች አንድ ቀን ላይ ይህ በ'ንዲህ እንዳለ
እግዜር ሆይ ያሳይህ ደሞ ይሄም አለ፡፡
እውነት አለን ብለው
ከሕይወት መፅሐፍ
ጠቅሰን ነው እያሉ ፍቅር የሚሰብኩ
ባርነት ለማውረስ
ነፍስያን ለመግዛት
የደከመን መንፈስ የሚያንበረክኩ
በሚናፈቅ ተስፋ
መቼም በማይመጣ
ሌላውን አክስመው እነሱ እሚፈኩ
..................ሰዎችን አያለሁ.................
በዚ'ች አንድ ቀን ላይ ይህ በ'ንዲህ እንዳለ
እግዜር ሆይ ያሳይህ ደሞ ይሄም አለ፡፡
ያንዲትን ሴት ፅናት
ለልጇ የምትኖር ራሷን አሙታ
በማያገኛት ሴት
የውበት ፍላጻ ነፍሱን የተመታ
ያንድ ልጇ ኑረት
ተመልካችን ቀርቶ ፈጣሪን ሲያምታታ
.................ቆሜ እገረማለሁ..................
እዚ'ች ቀን ላይ ቆሜ....
ግራ ቀኝ ሲገባኝ
እግዜር ሆይ የምሬን
ሁሉ ሲሆንብኝ ለመልስ የቸገረ
ስላንተ አምላክነት
ሁሉንም ቻይነት
በደካማው ልቤ ጥርጣሬ አደረ፡፡
በዚ'ች ቀን ላይ ቆሜ...
ይሄን ሁሉ ክስተት
ይሄን ሁሉ ኑረት ባ'ንድነት ያሰረ
ውጥንቅጥ ድርሳኑን
እንካችሁ ለታሪክ መዝገብ የሰደረ
የሰዉ ዘርን ሁሉ
ባይበጠስ እትብት
ቁራኛ ልክፍቱ ላይቀደድ ሰፍቶ
አንዱን ላ'ንዱ ሰ'ቶ
ባይቻል አስችሎ
ሁሉን የሚያስታግስ በዕጣ ፈንታ ቋጭቶ
< ይህም ሆነ > እያለ
የሕይወትን ብቅል
የኑረትን ድፍድፍ ፀንቶ የሚያብላላ
በአንዲት ቀን እድሜ
ዐልፋና ኦሜጋ
ዘላለም የሚያህል ታሪክ የሚያሰላ
የዚህ ሕይወት ቀማሪ
ሁሉን የሚነዳ የዚህ ሕይወት ዘዋሪ
ሌላኛው ፈጣሪ
< እኮ ወዴ'ት አለ!? > ብዬ እጠይቃለሁ
በጥድፊያዬ መሐል
መልሱን ሳላገኘው
ወደሌላ ግምት እሸጋገራለሁ፡፡
እንዲህ እየገመትኩ
ልደት ጥሪ ልሄድ ተዘጋጅቻለሁ፡፡



( አልቋል እንዴ!? አላለቀም )😊

((ጆኒ ሃብቴ)))💚💛

@getem
@getem
@balmbaras
👍1
ተኳሹ ደረሳ!!!!!


የጀሊሉ ባሪያ ፤ የነቢ ደረሳ ፤
ሶላቴን ሰግጄ ፤
ረቢል አለሚን ፤ በዚክር የማወሳ ፤
እኔ ነኝ ሸህ ኢብሬ ፤
አገሬን ሲነኳት፤
እምቧ ዘራፍ ብየ ጠበንጃ ማነሳ ።
በአንድ እጄ ሙስብሃ ፤
በአንደኛው ጠበንጃ፤ ይዤ ምዋጋላት ፤
አትንኳት እያሉ ፤ ነቢ በአሻጋሪ የተናገሩላት ፤
እምየ ኢትዮጲያ ፤
ዛሬም ዛውያው ስር ፤ ተኳሽ ደረሳ አላት! !!!!

((( ጃ ኖ ))💚💛

@balmbaras
@getem
@getem
ጠባብ
(ደሱ ፍቅርኤል)
አገር አገር አትበይ አንች አገረ ብርቁ
የኔም አገር አለኝ የሚታይ በሩቁ
ብየ ብዘፍንላት - ባ'ሽሙር እያየችኝ
የታለች አገርህ? - ብላ ጠየቀችኝ
በኩራት ላሳያት
ፈጥኜ ብጠቁም እጆቼን ወዳ'ገር
ቁመቴ አጠረና አላሳየኝ አለ የቆምኩበት መንደር
ከተራራው አናት ከከፍታው ሆኖ እጁን ካልጠቆመ
አገር አትታይም መንደር ላይ ለቆመ።
@getem
@getem
@kaleab_1888
🔥3
ኢቅራእ!!!


የሰማውን ይዞ ፤
ያየውን ጠምዝዞ ፤
ሁሉም በየጎራው ፤
ፊደል እየሻረ ፉከራ እያበዛ ፤
ጃሂል ልታይ አለ ፣
ተሸከሙኝ አለ ፤
ልክ እንደ ወሳንሳ ፤ ልክ እንደጂናዛ ።


ጃሂል ከምሸከም ፤
ድንጋይ ከምሸከም ፤ ትክሻየ አውጥቼ ፤
ኪታቤ ጋር ልዋል ፥
ዛሬም በስተርጅና፤ አንገቴን ደፍቼ ፤
የከተበ ሲሽር ፤
ይኸው ስንት ዘመን ፤ አይተዋል አይኖቼ ።


በዚህች በኛ ቀየ ፤
ጃሂል በየሜዳው ፤
ልርገጣችሁ ብሎ ፤ ስለሚደነፋ ፤
ይማረን እያለ ፤
ቀለሜው በሙሉ ፤ ቀለም ላይ ተደፋ! !!!!

((( ጃ ኖ )))💚💛

የኔዋ❤️ሸጋዋ ፍልቅልቅ ያለች ቅዳሜ ትሁንላቹ!!!

@balmbaras
@getem
@getem
👍1
መነሻ ስዕል !

( ገ/ክርስቶስ ደስታ )

አያልቅም ይህ ጉዞ ማስመሠል መተርጎም ፤

በቀለም መዋኘት፥

በመስመር መዋኘት፥

ከብርሃን መጋጨት፤

ለማወቅ ለመፍጠር ባዶ ቦታ መግባት፤

መፈለግ ..መፈለግ ፥

አዲስ ነገር መፍጠር ፤

ከማይታየው ጋር ሄዶ መነጋገር ፤

ሕይወትን መጠየቅ ፥

ሐሳብን መጠየቅ ፥

መሄድ..መሄድ..መሄድ...

ከጨረቃ በላይ ፥

ከኮኮቦች በላይ፥

ከሰማዩ በላይ፥

መጓዝ ወደሌላ ባዶ ቦታ መግባት፤

በሃሣብ መደበቅ መፈለግ ማስገኘት ፤

አያልቅም ይህ ጉዞ...!!!

..


( ሚያዝያ 3 1955 )

@getem
@getem
@poemempire
አደረገሽ አሉ


ነገ ይሉት ቀንን ለብቻ እንደ ማለም
ከልብሽ ከተማ ድንግዝግዝ ጭልምልም
መሄጃ እንደ መጥፋት እንደ መደናገር
ከአእመሮሽ ጓዳ እንደ መርሳት ነገር
አደረገሽ አሉ


በሌት በጨረቃ ከእንቅልፍ እንደ መንቃት
በቅዥት ድግምግም እንቅልፍ እንደ መፍራት
በእንባ ብዛት አይንሽ አብጦ እንደ መፍረጥ
ፎቶዬን እያየሽ ተስፋ እንደመቁረጥ
አደረገሽ አሉ


ሰርክ እንደ መጠጣት ብርሌ እንደመያዝ ውስኪ እንደመጨበጥ
ስሜን እየጠሩ በዛቻ በስድብ ሰው እንደ መበጥበጥ
ሰክሮ እንደ መውደቅ
ከሰውነት ወጥቶ በሃሳብ መንምኖ ከስቶ እንደማለቅ




አደረገሽ አሉ


በእኔ እንደ መማል ሌላ ገላ ታቅፈሽ አዲስ ሰው ለመልመድ
በፍቅራችሁ መሃል ስሜን እንደመጥራት ደግሞ እንደመናደድ
ስሜን ሲያነሱ በክፉ ሲጠሩኝ ተዉ እንደማለት
በሃጢያትማሳበብናፍቆኝ ላለማለት
አደረገሽ አሉ


አንገትሽን ደፍተሽ ዘወትር እንደማንባታ
ከተለመድሽበት ከከተማው መጥፋት
ፎቶዬን እያዩ አንዴ እንደመሳቅ በትዝታ ፈረስ
እንደገና ማዘን በሃይል እየጮሁ እንባ እንደማፍሰስ
አደረገሽ አሉ


አደረገሽ አሉ


ነብዪ ኃ/ገብርኤል
ማክሠኞ የካቲት 12 , 2010ዓ.ም

@getem
@getem
@gebriel_19
#ድንቄም_ፃድቅ

ክብሩን ጥብያ ጥሎ ፤ በጎሳ ቀረርቶ
ከዘር ይማግጣል ፤ፍፁም ፍቅር ፈርቶ
ማ-መንዘር ሀገር ላይ ፤ ያ ሁሉ ተረስቶ
መ-መንዘር ፅድቅ ሆነ ፤በዝርዝር ተኮርቶ!

ውድነህ ተሾመ
16/06/2011

@getem
@getem

""
ዋ.....አድዋ ብሎ
አርበኛው ሲነሳ
ነጭን ብቻ አይደለም፤
ሰውን ብቻ አይደለም፤
ከኩራት ጫፍ ቆሞ
ሞትን ድል ነው የነሳ፨

(አብርሃም)

@getem
@getem
# ግኝት


በሔዱበት መንገድ
መራመድ ጀምሬ ፣ መቀጠል አቃተኝ፤
ተመልሼ መጣሁ ፣
ልፋቴ እየቆጨኝ ፣ እያንቀጫቀጨኝ።
ግና በመንገዱ........
የሄዱበት ሁሉ፣ ስላልተመለሱ፣
አዲስ ነው ተባለ፣ መመለሴ ራሱ።

# መዘክር -ግርማ

@getem
@getem
@getem
።።።።።የፍቅርሽ ሃያልነትሽ።።።።።

~~~~~~~~~~~~~~~~~

ያኔ ስንገናኝ በጓደኝነታችን፤
ድንገት ሳናስበው በፍቅር መጥለቃችን፣
ወደታች እንደሚሠምጥ የባህር ድምፅ እንጉርጉሮ፤
የፍቅርሽ ሃያል በደሜ ውስጥ ገብቶ ልቤን ጎርጉሮ፤
መተንፈስ እስኪያቅተኝ መናገር ተቸግሬ፤
ለመናገር የፈራሁት አንቺን አፍቅሬ፤

-------ሁሌም እልሻለው-------
--------እወድሻለው------

እና እምልሽ አንቺን ካገኘው ከወደድኩሽ በኅላ፤
ያለኝን ሁሉ አየው ተመልሼ ወደኅላ፤
አለም አንቺን ሰጠችኝ፤
ደስተኛ እንድሆን አደረገችኝ፤

ጥይት እንኳን ቢተኮስ የማይበሳውን ልቤ፤
በአንቺ ፍቅር ብቻ በአንቺ ፍቅር ተከፈተ ልቤ፤

--------ሁሌም እልሻለው----------
--------አፈቅርሻለው------

# አብዲሳ ዳመና #
2011

@getem
@getem
ይድረስ ለኢትዮጵያ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

ⓜⓡ◦ ⓣⓡⓤⓜⓟ

በየወንዛ-ወንዝሽ በተራራው ቤትሽ÷
በነፋስ በዱሩ አንቺ ባለሽበት፤
ክፉን ባሳደገ ያገር ልቦናሽ ውስጥ÷ የሰላምታ ቃሌን አምላክ ያኑርበት።

እንዴት ነሽ ኢትዮጵያ እጅ ያለሽ ሐገሬ፤
ዛሬስ እደዊሀ ትያለሽ አስሬ?።
ገነቷ ምድራችን በሰማያት ላለው ለአዶናይ እግዜሩ፤
የምተዘረጊያቸው እጆችሽ ይክበሩ፦
ብለን ያልንላቸው፤
ሙሰኛን ያቀፉ የዘንድሮ እጆችሽ እቴ እንደምን ናቸው።
ቁመትሽ ከምድር እስከሰማይ ደርሶ፤
የሻሽሽ ጥለቱ አረንጓዴ ቢጫ ደመናን ገርስሶ፤
ዝርፍፋት ቀሚስሽ ምድርን እንዳልሞላ፤
አካልሽ ምስኪኑ በጉንዳን ተበላ።
ይበልሽ ሐገሬ...ይብላኝ ለምስኪኑ ለኔ ቢጤ ደሐ፤
ሐብታምስ ቤቱ ነው ወለላ ገላሽን ባዋዜ እየበላ።
ይበልሽ እምዬ....አውሬ ላሳደግሽው፤
ካካልሽ ስር ወቶ ቅድስት አካልሽን ለሚሸነሽነው፤
ይበልሽ ካልኩማ የሚልሽ ብዙ ነው።
ቢሆንም ሐገሬ..!
ካፈረሽ አፍርሶ አፈር ስላረገን፤
ብንበታተንም ፈራርሰን ያንቺ ነን።

ቢሆንም ሀገሬ..!
የበላሽ ቢበላ ሆዱ እስከሚወጠር፤
ሲቀደድ ያንቺ ነው ላካልሽ ግብአት ለመሬትሽ አፈር።
ቢሆንም ባበዛ የሚሆን ብዙ ነው፤
ጉንጬን ከማለፋ ይህንም ትቻለው።
ግን እንደው ሐገሬ..!
ድፍረት ባይሆንብኝ እናትን ማንጓጠጥ፤
በንቅርት ላይ አይነት አካሌን ማሽሟጠጥ፤
ጥያቄ ነበረኝ ላካል ለሰንደቅሽ፤
ላገር ማህፀንሽ ለቃል ኪዳን ስምሽ፤
እንደሚከተለው እኔ ስጠይቅሽ፤
መልስሽን ላኪልኝ ባየርሽ ሸፍነሽ።

ሐገሬ!?!
እንደሚታወቀው... የገዘፈ አቋም የቀጠነ ወገብ ደርባባ ሰውነት፤
ጠይም የቆዳ መልክ ብሩህ ያይን ውበት፤
ሰልካካ ባይሆንም የሚያምር አፍንጫ፤
ማህፀን እንዳለሽ የሚችል እርግጫ፥
እናውቃለን እኛ።

(ጥያቄዬ ግን እጅሽን ይመለከታል።)

ይህን ሁሉ ሰቶሽ ፈጣሪ እግዜሩ፤
ልጆንም ወልደሽ ሲሰፍሩ በምድሩ፤
መንጋሽ እንዳሸዋ እንደ ሰማይ ኮከብ፤
ሲበዛ ሲባዛ ያለከልካይ ገደብ፤
በሰሜን በደቡብ በምስራቅ በምራብ፤
ላገዛዝ ነው በሚል ተራ ከንቱ ሰበብ፤
ክልሉን ሲሰራ ድንበሩን ሲያሰምር፤
ተራራን ለማቆም ምክንያቱን ሲከምር፤
ልምጭ ያልቀጠፈው ጭኑ ስር ያልገባ፥ ያልቀጣው መዳፍሽ፤
ያካልሽ አንድ አካል እንደምነው እጅሽ?።

ዳዊት በመጣፉ መኳንንት ሲመጡ፤
ወደሰማይ ጌታ ሽቅብ የሚሰጡ፤
እጅ አላት ኢቶጵያ ያለለት መዳፍሽ፤
ያካልሽ አንድ አካል አንደምነው እጅሽ።

ፍጥረቱ ልጆችሽ፥ከኢቶጵያነትሽ ላይ ኢቶጵያነት ወስደው፤
መጠያየማቸው አንቺን መምሰላቸው፤
ይህ ሁሉ እውነት ነው።
(ግን እንደው ሃገሬ ድፈረት ካሎነብኝ)፦
የልጆሽ ሁሉ አባታቸው ማነው?
እነሱ እንደሚሉት ዘር ባባት ከሆነ የሚተላለፈው፤
ዘራቸውን ይስሙ አባታቸው ማነው።
(ከፈቅድሽልኝስ እኔ ልንገራቸው)
ሐገራት በሙሉ እንኳንስ ኢቶጵያ፤
ወልደው ቢያሳድጉ በእቅፋቸው ጉያ፤
እናት መሆናቸው በደንብ ይታወቃል፤
ያባታቸው ነገር ጥያቄን ይፈጥራል።
እኔ ግን ሐገሬ ካንቺ እንደሰማሁት፤
ካየርሽ ካፈርሽ እንደ ተረዳሁት፤
የልጆችሽ አባት የሰማይ ፈጣሪ፤
የልጆችሽም ዘር አይደለም አማራ፥ አይደለም ኦሮሞ፥አይደለም ምድራዊ።
ዘርሽ የተዘራው ከላይ ስለሆነ ከፈጣሪ መዳፍ፤
ቢበቅልም የሱ ነው ቢሆንም አእላፍ።
እናማ ካፈርሽ ዘር ሆኖ መብቀሉ እናቱ ሲያረግሽ፤
ዘራችን ይሆናል ዘሩን የዘራብሽ።
እንኳን ብሔር ቀርቶ የተቀላቀለው፤
እምነት ቢለየንም ዘራችን አንድ ነው፤
እናት ኢቶጵያ አባት ፈጣሪ ነው።
ይኸው ነው።
============¤===========

@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
የላስቴዋ !!!!!!


አገሯ ላስታ ነው ከሜዳው ሽምሽሃ ፤
ጥርሷ ሲናገረኝ ፤
ቀጥ ብየ ቀረሁ እንደ ኩሬ ውሃ ።
ንጉስና ቅዱስ ነበሩ አባትሽ፤
አንችም ላስቴ ሆነሽ፤
አላፊ አግዳሚውን ፤ ታሰግጃለሽ ።
ላስታ ላሊበላ ፤
የአባቶችሽ ሃገር ፤ አንች ያለሽበት ፤
አፈሩ ክምሩ፤ ታአምር የሞላበት፤
እኒያ ዘመዶችሽ ፤
በድንጋይ ቤት መስራት ፤ እንዴት አወቁበት??
የጥርሷ ውቅራት ፤ የተዥጎረጎረው ፤
ብርቱካን ከንፈሯ ፤ የተገማሸረው ፤
በሳቅ መረታቴን ደግሞ ማን ነገረው????
ይማም መሸሻ ሃገር ላስታ ተወልደሽ፥
ልውሰድ ልውሰድ፤ ባዩ ተጋደለብሽ ፤
ምናለብሽ አንች ፤
የሞተ እየሸኘሽ፤ ቋሚ እያመጣሽ።
የላስታ ጉልላት፤ ይታያል በየጁ ፣
አንችን አንችን ብለው ፤ ወንዶቹ ተፋጁ ።
የላስታ ደመና ፤
የራያ ደመና ፤
ወፍራም ዝናብ ሆኖ ፤ፈሰሰ አሉ ደሴ ፤
መቼም ድንበር የለው ፤
የኔ አይሉት ነገር ፤ ወሎና መነኩሴ።
ላስታ መናገሻው ፤ መሪ ነው ጠበሉ ፤
እስኪ ጥርሷ ያውጋኝ፤ እናንተ ዝምበሉ ።
ጥርሷ መጋልማ ፤ አይኗ ላምባዲና ፤
ተነስ ትለኛለች፤
ከነ አጅሬ መንደር ፤ አይና ቡግና ሆና!!!!!
ቡግና ነው አገሬ፤ አይና ነው እያለች ፤
ያች የላስታ ልጅ ፤
በእርጎ ዳማይ ጥርሷ፤አያል ሰው ገደለች ።
ይኸ ድፍን ልቤ ፤ ዱር የተላመደው ፤
አልቤን እያኖጋ ፤ ተከዜ ሚወርደው ፤
እንደተነካ ሰው ፤
አንች ላይ ሲሆን ነው፤ የሚወላገደው።
ላስታ ካኮረፈ ፤ ግዳን ከተቆጣ ፤
እንኳን አባወራ ፤
ተከዜም ከእየላ ፤ ከደብሩም አይወጣ ።
እንደ አቦሃይ ጋራ ፤
ወኔዋ ወደላይ፤ ወዲያንዲያ ተሰቅሎ ፥
አልቻልኩም ተረታሁ ፤
ጀባ በለኝ ላስታ ፤ ነጃ በለኝ ወሎ ።

((( ጃ ኖ ))💚💛

@balmbaras
@getem
@getem
ዝክረ አደዋ!!💚💛

ዛሬ የካቲት 19 ቀን ከቀኑ 11:00 ሰዓት ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር ይቀርባል

የምትችሉ..ጊዜው እና ሁኔታው የፈቀደላቹ ብትታደሙ....ለማለት ነው

#መግቢያ በነፃ ነው

@getem
@getem
@balmbaras
አራዳ ጊዮርጊስ ከፍ ካለው ቦታ፤
ለእምዬ ምኒሊክ፤
እነሆውዳሴ ፤፤ እነሆ ሰላምታ

💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️
@getem
@getem
@balmbaras
…ጥበብን ልምከርህ…
(ለራሴ ነው የፃፍኩት😉)
:
'ላለው ይጨመራል'፤ ያለህን አትጣ
ጨርቅ ለመለመን፤ እርቃንህን አትውጣ
ጥበብን ልንገርህ…
ክብርህን አትጣ፤ ክብር ያለው ስታይ
ክብር የጣልክለት፤ ክብርህን ነው የሚያይ
አጉል በዝቷልና
ምድርህን እረግጦ፤ ሰማይ ሰማይ የሚያይ።😡
:
ብዙም አታስረዳው…
አውቆ ያላወቀ፤ ካልፈለገ አያውቅም
ጥርስ ያላመው ዱቄት፤ ለጉሮሮ አይርቅም
ሆዱ ያልጠገበ፤ ውሃ አይራመድም
:
ሳይረፍድ እወቅበት…
ብቻህን ተወገዝ፤ ተነጠል ከመንጋ
ለመረገጥ ሂወት፤ ለታይታ አትፍጋ
ጨለማውን እረፍ፤ በብርሃን ትጋ
:
በውላጅ ጥበብህ፤ በውራጅ አትኩራ
ጥበብን ውለዳት፤ የራስህን ስራ
ከኋላ አትቅር፤ ፊቶቹን አትፍራ።
መሆንን ሂድበት፤ እርምጃህን ጀምር
አንድ ጠርቅመህ ነው፤ የሚኖርህ ክምር
ክብርህን ሳታጣ፤ አክባሪህን አክብር
:
ጥበብን ልምከርህ
እውነት ደምስርህ ናት፤ የሀበሻ ደምህ
ሰርቀህ ከሚያምርብህ፤ ሙተህ ይለፍብህ
መኖርህ ቢረሳም፤ ህያው ነው እውነትህ
:
ጥበብን ልምከርህ
አዋቂ ነኝ አትበል፤ ባልታወቀ አለም
ተኮፋሽ ያረገህ
አለማወቅ እንጂ፤ ማወቅህ አይደለም።
:
ልንገርህ… ልምከርህ …
ስጋን ለማደለብ፤ ነፍስህን አታክሳ
ከጥበቦች ሁሉ፤ የፊቱን አትርሳ
<ላለው ይጨመራል፤ ያለህን አትጣ
ጨርቅ ለመለመን፤ እርቃንህን አትውጣ>
:

አብርሃም (የሙሉ ልጅ)
፲፱-፮-፳፻፲፩

@getem
@getem
@yemulu_lij