የዝምታ ጩኸት
.
.
.
ተሳዳቢ አንደበት ሰሚ አልባ ጆሮ፤
ፅልመት የወረሰው ትርጉም አልባ ኑሮ፤
ከተስፋ ጉልላት አሽቀንጥሮ 'ሚጥል፤
ትንፋሽ አሳጥቶ በቁም የሚገድል፤
ወላፈኑ ሚፋጅ የስሜት አቀበት፤
ሌላው የማይሰማው የዝምታ ጩኸት።
✍በኤደን ታደሰ እንደተፃፈ
@topazionnn
@getem
@getem
.
.
.
ተሳዳቢ አንደበት ሰሚ አልባ ጆሮ፤
ፅልመት የወረሰው ትርጉም አልባ ኑሮ፤
ከተስፋ ጉልላት አሽቀንጥሮ 'ሚጥል፤
ትንፋሽ አሳጥቶ በቁም የሚገድል፤
ወላፈኑ ሚፋጅ የስሜት አቀበት፤
ሌላው የማይሰማው የዝምታ ጩኸት።
✍በኤደን ታደሰ እንደተፃፈ
@topazionnn
@getem
@getem
❤63👍30🎉1
ቢፍለቀለቅ ንፍር ውኃ
... ... ... ቢግለበለብ እቶን እሳት
ልጣል ብያዝ በአጥፊ እጆች
... ... ... ብወረወር ተብሎ ቅጣት
ይከፈታል ለምስጋና
... ... ... ቢሸበብም አፍ መዳፌ
መቀዝቀዙ ከቶም አይቀር
... ... ... ነዶ ቢታይ መጥፊያ ሰይፌ
አይወረኝም አንዳች ፍርሃት
... ... ... አይችልም ውስጤን ሊንድ
አቅፌ የለ ገብርኤልን
... ... ... ለዘላለም በልቤ ክንድ
የተራቡ አናብስቶች
... ... ... እንዲበሉኝ ብጣል ጉድጓድ
ግፍ እንድጋት ቢፈርዱብኝ
... ... ... አምላክህን እያሉኝ ካድ
ስቄ አልፋለሁ በፊታቸው
... ... ... ሺ ቢያዛጋም ሞት ሊውጠኝ
መዘጋቱ ከቶም አይቀር
... ... ... እንድቆይ አምላክ ካጨኝ
አልናወጽም ብቦጫጨቅ
... ... ... አልሰጋም ላፍታ ቅንጣት
ይዤ የለ መልአኩን
... ... ... ለዘላለም በልቤ ጣት
#ኤልዳን
@eldan29
@getem
@getem
@getem
... ... ... ቢግለበለብ እቶን እሳት
ልጣል ብያዝ በአጥፊ እጆች
... ... ... ብወረወር ተብሎ ቅጣት
ይከፈታል ለምስጋና
... ... ... ቢሸበብም አፍ መዳፌ
መቀዝቀዙ ከቶም አይቀር
... ... ... ነዶ ቢታይ መጥፊያ ሰይፌ
አይወረኝም አንዳች ፍርሃት
... ... ... አይችልም ውስጤን ሊንድ
አቅፌ የለ ገብርኤልን
... ... ... ለዘላለም በልቤ ክንድ
የተራቡ አናብስቶች
... ... ... እንዲበሉኝ ብጣል ጉድጓድ
ግፍ እንድጋት ቢፈርዱብኝ
... ... ... አምላክህን እያሉኝ ካድ
ስቄ አልፋለሁ በፊታቸው
... ... ... ሺ ቢያዛጋም ሞት ሊውጠኝ
መዘጋቱ ከቶም አይቀር
... ... ... እንድቆይ አምላክ ካጨኝ
አልናወጽም ብቦጫጨቅ
... ... ... አልሰጋም ላፍታ ቅንጣት
ይዤ የለ መልአኩን
... ... ... ለዘላለም በልቤ ጣት
#ኤልዳን
@eldan29
@getem
@getem
@getem
❤71👍31👎2🔥2🎉1
☀️ፀሃይ ልጠይቅሽ☀️
ሰማሽኝ ወይ ፀሃይ
ያለሽ ከሰው በላይ
ከዛ ከከፍታ ከዛ ከሩቅ ስፍራ
ሆነሽ ከሰማይ ስር
ሚታይሽ ከሆነ ከጥግ እስከጥጓ
የኛ ሰዎች ምድር
ስሚኝ እባክሽን አንዴ ተባበሪኝ
እኔ ከርታታውን
ውሃ አጣጬን እንደው አይተሻት ከሆነ
አገናኚኝ አሁን።
📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝
✍️ @BEGITIMENAWGA
@getem
@getem
@getem
ሰማሽኝ ወይ ፀሃይ
ያለሽ ከሰው በላይ
ከዛ ከከፍታ ከዛ ከሩቅ ስፍራ
ሆነሽ ከሰማይ ስር
ሚታይሽ ከሆነ ከጥግ እስከጥጓ
የኛ ሰዎች ምድር
ስሚኝ እባክሽን አንዴ ተባበሪኝ
እኔ ከርታታውን
ውሃ አጣጬን እንደው አይተሻት ከሆነ
አገናኚኝ አሁን።
📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝
✍️ @BEGITIMENAWGA
@getem
@getem
@getem
👍44❤15🤩6
አፍ አውጥቶ ሐኪም ሚጠራው
... ... ... እልፍ ገንዘብ የአሸን ብር
ከታማሚው ስቃይ በላይ
... ... ... አስታማሚን የሚያሸብር፤
አስታማሚን ሚያስደነግጥ
ብርታት ወኔን ሚሰለቅጥ
የሰናፍጭ ቅንጣት ተስፋን
... ... ... አሽቀንጥሮ ወዲያ ሚጥል
ምሬት ብሶት አስዘንቦ
... ... ... በእንባ ገመድ ሚያንጠለጥል።
፧
እንደ ስምኦን ቄሬናዊው
... ... ... ተጋራኹ የልጄን መስቀል
እስኪላጥ ስስ ጫንቃዬ
... ... ... ተሸከምኩም ስጋት ቀንበር።
ትድን ይሆን?
ትሞት ይሆን?
ተፍረከረኩ
ተንኮታኮትኩ፤
ተስፋ አዝዬ
በጭንቀት ዝዬ
እኔን ገበርኩ
ያለኝን ሸጥኩ።
ጨረስኩ!
አየሁት ቤቴን
ዳበስኩት ኪሴን
ካንቺ ምስል በቀር ምንም የለም በእጄ፤
ሁሉን ሽጨዋለሁ ትድን ብዬ ልጄ።
እመቤቴ ማርያም አልሸጥሽ እንደ እቃ፤
ነይ አብረን እናልቅስ ነይ እንዘን በቃ።
ምናለኝ ካንቺ ውጭ
... ... ... ማን አለኝ ካንቺ በቀር
ነይ መድኃኒት ሁኛት
... ... ... የልጄ ልብ ሳይሰበር
ነይ ዳብሻት በመዳፍሽ
... ... ... ነይ እቀፊያት እንደጌታ
አንቺ ነሽ ማር ሐኪሟ
... ... ... አንቺ ነሽ የነፍሷ አለኝታ
፧
እኔማ አቅም የለኝ
እኔማ እጅ አጠረኝ
እንባ እንጂ ምን ቀረኝ!
#ኤልዳን
@eldan29
@getem
@getem
@getem
... ... ... እልፍ ገንዘብ የአሸን ብር
ከታማሚው ስቃይ በላይ
... ... ... አስታማሚን የሚያሸብር፤
አስታማሚን ሚያስደነግጥ
ብርታት ወኔን ሚሰለቅጥ
የሰናፍጭ ቅንጣት ተስፋን
... ... ... አሽቀንጥሮ ወዲያ ሚጥል
ምሬት ብሶት አስዘንቦ
... ... ... በእንባ ገመድ ሚያንጠለጥል።
፧
እንደ ስምኦን ቄሬናዊው
... ... ... ተጋራኹ የልጄን መስቀል
እስኪላጥ ስስ ጫንቃዬ
... ... ... ተሸከምኩም ስጋት ቀንበር።
ትድን ይሆን?
ትሞት ይሆን?
ተፍረከረኩ
ተንኮታኮትኩ፤
ተስፋ አዝዬ
በጭንቀት ዝዬ
እኔን ገበርኩ
ያለኝን ሸጥኩ።
ጨረስኩ!
አየሁት ቤቴን
ዳበስኩት ኪሴን
ካንቺ ምስል በቀር ምንም የለም በእጄ፤
ሁሉን ሽጨዋለሁ ትድን ብዬ ልጄ።
እመቤቴ ማርያም አልሸጥሽ እንደ እቃ፤
ነይ አብረን እናልቅስ ነይ እንዘን በቃ።
ምናለኝ ካንቺ ውጭ
... ... ... ማን አለኝ ካንቺ በቀር
ነይ መድኃኒት ሁኛት
... ... ... የልጄ ልብ ሳይሰበር
ነይ ዳብሻት በመዳፍሽ
... ... ... ነይ እቀፊያት እንደጌታ
አንቺ ነሽ ማር ሐኪሟ
... ... ... አንቺ ነሽ የነፍሷ አለኝታ
፧
እኔማ አቅም የለኝ
እኔማ እጅ አጠረኝ
እንባ እንጂ ምን ቀረኝ!
#ኤልዳን
@eldan29
@getem
@getem
@getem
👍49❤19😢2🤩1
የዘመን ኑሮ
ድንጉጥ ህይወት መሀል
መጥፎ ብቻ አይደለም
የተለቀ ደስታም አቅልን የሚያስት ነው
በፈራ ተባ ውስጥ እችላለው ማለት
ዘበት!
በዝች አለም ጊዜ ጊዜ እንጂ ሚፈርድህ
ጊዜ እንጂ ሚያስኬድህ
በአንተነትህ ጠፍቷል አንተን መፈለግህ
እንቁ ብትሆን በዘመንህ
ጊዜ ግን ሲጎሽምህ
እንዲ ትባላለህ
"አንተን ማን አረገህ የብርሌ ጠጂ
ጊዜ ማሳለፊያ ቅራሪ ነህ እንጂ"
በእንዲ ባለ ህይወት
ህይወትን ልትፈልግ ብትቃርም እንኳን
ጊዜህ ካላሟሸህ
ከቶ ሳትሰማ እንጀራህም አያምር
ጊዜህ ስላረገህ ዘመንህን ጥላሸት
ለመደሰት እንኳን ሆኗል በፍርሀት
ስለሆነም.......
በል እንግዲ ታጠቅ መኖር ሆኗል ውጊያ
ምርኮ እንኳን አይሰራም ቢያሻህ መጠለያ
የዚ ዘመን ውጊያ ህግ አለው አትበል
እንደ እንስሳት ልፊያ ነፃ ትግል ሆኗል
በዚው ከቀጠለ.......
ወዶ መኖርህን ይቅር በቃ እርሳው
እንኳንስ ለመኖር....
ለማበድ ብትፈልግ ፍቃድ ልጠይቅ ነው።
ቴዲ ጌትነት።
@getem
@getem
@getem
ድንጉጥ ህይወት መሀል
መጥፎ ብቻ አይደለም
የተለቀ ደስታም አቅልን የሚያስት ነው
በፈራ ተባ ውስጥ እችላለው ማለት
ዘበት!
በዝች አለም ጊዜ ጊዜ እንጂ ሚፈርድህ
ጊዜ እንጂ ሚያስኬድህ
በአንተነትህ ጠፍቷል አንተን መፈለግህ
እንቁ ብትሆን በዘመንህ
ጊዜ ግን ሲጎሽምህ
እንዲ ትባላለህ
"አንተን ማን አረገህ የብርሌ ጠጂ
ጊዜ ማሳለፊያ ቅራሪ ነህ እንጂ"
በእንዲ ባለ ህይወት
ህይወትን ልትፈልግ ብትቃርም እንኳን
ጊዜህ ካላሟሸህ
ከቶ ሳትሰማ እንጀራህም አያምር
ጊዜህ ስላረገህ ዘመንህን ጥላሸት
ለመደሰት እንኳን ሆኗል በፍርሀት
ስለሆነም.......
በል እንግዲ ታጠቅ መኖር ሆኗል ውጊያ
ምርኮ እንኳን አይሰራም ቢያሻህ መጠለያ
የዚ ዘመን ውጊያ ህግ አለው አትበል
እንደ እንስሳት ልፊያ ነፃ ትግል ሆኗል
በዚው ከቀጠለ.......
ወዶ መኖርህን ይቅር በቃ እርሳው
እንኳንስ ለመኖር....
ለማበድ ብትፈልግ ፍቃድ ልጠይቅ ነው።
ቴዲ ጌትነት።
@getem
@getem
@getem
👍40❤18👎2😢2
ሥዕል ለወዳጅ ዘመዶ ስጦታ ማበርከት የምትፈልጉ በ+251984740577 ይደውሉ።
ወይም @gebriel_19 ላይ ፎቶ በመላክ በ ተመጣጣኝ ዋጋ ማዘዝ ይችላሉ!
@seiloch
@seiloch
ወይም @gebriel_19 ላይ ፎቶ በመላክ በ ተመጣጣኝ ዋጋ ማዘዝ ይችላሉ!
@seiloch
@seiloch
❤6👍6😱5
Forwarded from ሥዕል ብቻ © (Leul M.)
ተጋብዛችኋል !
ሠዓሊና ገጣሚ ከበደች ተክለአብ በቤቷ በአዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ በ አለ የሥነጥበብና ዲዛይንት/ቤት ኦገስት 7 ከረጅሙና ከማይታመነው የህይወት ልምዷ ልታካፍለን አስባለች።
ትታደሙ ዘንድ እንጋብዛለን።
#አገኘሁ_አዳነ_ድልነሣሁ
@seiloch
@seiloch
ሠዓሊና ገጣሚ ከበደች ተክለአብ በቤቷ በአዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ በ አለ የሥነጥበብና ዲዛይንት/ቤት ኦገስት 7 ከረጅሙና ከማይታመነው የህይወት ልምዷ ልታካፍለን አስባለች።
ትታደሙ ዘንድ እንጋብዛለን።
#አገኘሁ_አዳነ_ድልነሣሁ
@seiloch
@seiloch
👍20❤3
ቁመትሽ ይታያል ፥ ታጥሪያለሽ ከቦታው
ስንጫወት ነበር ፥ ፍሬሙ የወደቀው
አይነ እውር አባትሽ፥ ሰምቶ እንደወደቀ ፣
ፈርተን ተለያየን፥
እስኪጠገን ድረስ ጨዋታ አለቀ ፣
በየፍሬሙ ጠርዝ ፥ተደብቀን ሳለን ፣
ያ ሰአይ አባትሽ ፥ሰራሁ ብሎ ወገን፣
ከሁለት ስንጥቅ ፍሬም እኛን ሲፈልገን፣
ከታች ከላይ አርጎ
እንዳንገናኝ በፍሬም አጠረን ፣
ግዕዝ ሙላት
@geez_mulat
@getem
@getem
@paappii
based idea : instagram Photo 👋
ስንጫወት ነበር ፥ ፍሬሙ የወደቀው
አይነ እውር አባትሽ፥ ሰምቶ እንደወደቀ ፣
ፈርተን ተለያየን፥
እስኪጠገን ድረስ ጨዋታ አለቀ ፣
በየፍሬሙ ጠርዝ ፥ተደብቀን ሳለን ፣
ያ ሰአይ አባትሽ ፥ሰራሁ ብሎ ወገን፣
ከሁለት ስንጥቅ ፍሬም እኛን ሲፈልገን፣
ከታች ከላይ አርጎ
እንዳንገናኝ በፍሬም አጠረን ፣
ግዕዝ ሙላት
@geez_mulat
@getem
@getem
@paappii
based idea : instagram Photo 👋
❤34👍24😢3👎2
መናፈቅ ማለት …
ከወትሮው በድንገት
ከከተማ ግፊያ
ከሰፊው ገበያ
ከሰው ትርምስ
ከህይወት ግብስብስ
አረፍ ብለው ባልጋ
ከራስ ጋር ሲወጋ
የአስቴር እና ኤፍሬም
አባባይ ሙዚቃ ...
አንጀትንን ሲገርፍ
ትዝታን ሲያነቃ
እንዲህ ይመስለኛል !
..
መናፈቅ ማለት..
በቡሄ አመሻሽ
እርግት ባለ ሰማይ
ልጅነት ሲወያይ
ሲሸት የኩበት ጭስ
የአሪቲ ቃና መንደርን ሲዳብስ
ውብ አደይ አበባ ምድሪቷን ሲያነግስ
እንዲህ ይመስለኛል !
..
መናፈቅ ማለት ..
እኔና አንቺ አፍረን
ከዓይን ተሸሽገን
ከመስቀል ዳመራ
ሸሽተን ከጓደኞች
ፈልገን ሰዋራ ...
ተቃቅፈን እየሄድን
ውሎን ስንጋራ
ስትሰጪኝ ፖፖቲን
‘’ፖስት ካርዴስ ?’’ ብለሽ
ኪሴን ስትዳብሽኝ
እንዲህ ይመስለኛል ።
..
መናፈቅ ማለት …
ትምህርት ሊዘጋ ወቅት
ድራማ ተውነን
በሰኔ ሰላሳ ለመታየት ደምቀን
በድራማው መኃል
ፈልገን ስህተት
ከልብ የሳቅን ዕለት
ከሳቅን በኋላ
ኩሪፊያ ሲከተለን ...
ድፍን ሶስት ወራትን
ያለመገናኘት ፍርሀት ሲውጠን
ስትሰናበችኝ በጥልቁ ዝምታ
ዓይንሽን እያየሁ
ዓይኖቼን እያየሽ
የቆዘምን ለታ …..
እንዲህ ይመስለኛል ።
..
መናፈቅ ማለት …
(ሚካኤል አ )
@getem
@getem
@getem
ከወትሮው በድንገት
ከከተማ ግፊያ
ከሰፊው ገበያ
ከሰው ትርምስ
ከህይወት ግብስብስ
አረፍ ብለው ባልጋ
ከራስ ጋር ሲወጋ
የአስቴር እና ኤፍሬም
አባባይ ሙዚቃ ...
አንጀትንን ሲገርፍ
ትዝታን ሲያነቃ
እንዲህ ይመስለኛል !
..
መናፈቅ ማለት..
በቡሄ አመሻሽ
እርግት ባለ ሰማይ
ልጅነት ሲወያይ
ሲሸት የኩበት ጭስ
የአሪቲ ቃና መንደርን ሲዳብስ
ውብ አደይ አበባ ምድሪቷን ሲያነግስ
እንዲህ ይመስለኛል !
..
መናፈቅ ማለት ..
እኔና አንቺ አፍረን
ከዓይን ተሸሽገን
ከመስቀል ዳመራ
ሸሽተን ከጓደኞች
ፈልገን ሰዋራ ...
ተቃቅፈን እየሄድን
ውሎን ስንጋራ
ስትሰጪኝ ፖፖቲን
‘’ፖስት ካርዴስ ?’’ ብለሽ
ኪሴን ስትዳብሽኝ
እንዲህ ይመስለኛል ።
..
መናፈቅ ማለት …
ትምህርት ሊዘጋ ወቅት
ድራማ ተውነን
በሰኔ ሰላሳ ለመታየት ደምቀን
በድራማው መኃል
ፈልገን ስህተት
ከልብ የሳቅን ዕለት
ከሳቅን በኋላ
ኩሪፊያ ሲከተለን ...
ድፍን ሶስት ወራትን
ያለመገናኘት ፍርሀት ሲውጠን
ስትሰናበችኝ በጥልቁ ዝምታ
ዓይንሽን እያየሁ
ዓይኖቼን እያየሽ
የቆዘምን ለታ …..
እንዲህ ይመስለኛል ።
..
መናፈቅ ማለት …
(ሚካኤል አ )
@getem
@getem
@getem
❤73👍41😢5🔥4
የቀለም ቀንድ ሆኖ አንደበቱ ከሚረታ
ነፃነቱን ሽቶ ፥ በየጥሻው ስርጥ ውስጥ ቃታ ከሚፈታ
ሀገር ከሚመራ …
ቅኔ ፣ ፆመ ድጓ ፣ ቁርአንም ከሚቀራ
በአዲስ ግኝት ሳይንስ ፥ ከሆነልን ካስማ
አጃኢብ ካሰኘን ፥ በግጥም በዜማ
ከሚሰዋው ከሚደማው
ከዛ የአብዮት ዘብ …
ህዋዋ ላይ መጥቆ ፥ ካስገኝልን ረብ
ጥላም ከሚሆነን ፥ በንዋይ በገንዘብ
ዝናው ህያው ሆኖ ዛሬም ድረስ ከሚዘገብ
ከዚህ ሁሉ በላይ ጀግና ነው የምለው
ጽድቁን አደላድሎ ፥ ሞትን የናቀን ነው ።
(ሚካኤል አ)
@getem
@getem
@getem
ነፃነቱን ሽቶ ፥ በየጥሻው ስርጥ ውስጥ ቃታ ከሚፈታ
ሀገር ከሚመራ …
ቅኔ ፣ ፆመ ድጓ ፣ ቁርአንም ከሚቀራ
በአዲስ ግኝት ሳይንስ ፥ ከሆነልን ካስማ
አጃኢብ ካሰኘን ፥ በግጥም በዜማ
ከሚሰዋው ከሚደማው
ከዛ የአብዮት ዘብ …
ህዋዋ ላይ መጥቆ ፥ ካስገኝልን ረብ
ጥላም ከሚሆነን ፥ በንዋይ በገንዘብ
ዝናው ህያው ሆኖ ዛሬም ድረስ ከሚዘገብ
ከዚህ ሁሉ በላይ ጀግና ነው የምለው
ጽድቁን አደላድሎ ፥ ሞትን የናቀን ነው ።
(ሚካኤል አ)
@getem
@getem
@getem
❤21👍11🔥2
አንቺ...
እንዴት ነሽ ግን?
ደህና ነሽ?
አትዋሺኝ
አትዋሺኝ:
ሀዘንሽን በጥርስሽ ጫፍ
ለምንድነው ምትደብቂው፥
እንዳልከፋሽ እንዳምንሽ ነው
የሞት ሞትን ምትስቂው?
አላምንሽም;
አላምንሽም!
ኑሮ ህይወት እንደደላሽ;
ብትነግሪኝም የውሸት ቃል፤
አንዱም እውነት እንዳልሆነ፡
ካይኖችሽ ላይ ያስታውቃል።
ማሳመኛ ሀተታዎች
አንደበትሽ ሲለቃቅም፥
ፊት የግዱን ፈገግ ቢል
አይን እውነቱን አይደብቅም!።
ደካክሞሻል
ህይወት ፍዳው፤
ፈትኖሻል
እምነት እዳው!።
ጠፍቶብሻል
መኖር ውሉ፤
ሰልችቶሻል
ማስመሰሉ!።
ማረፍን ነው የምትጓጊው፥
ህይወት ሆኗል የቁም እስር
ምኞትሽ ነው ለአንዴም እንኳን፡
ብትተኚ እናትሽ ስር ።
አትደቢቂኝ
አይጠፋኝም፦
የሀዘንሽ መቀስ ስንኩል፤
አትሳቂ እያመመሽ፥
ነይ አልቅሺ በ'ኔ በኩል!።
by @mikiyas_feyisa
@getem
@getem
@paappii
እንዴት ነሽ ግን?
ደህና ነሽ?
አትዋሺኝ
አትዋሺኝ:
ሀዘንሽን በጥርስሽ ጫፍ
ለምንድነው ምትደብቂው፥
እንዳልከፋሽ እንዳምንሽ ነው
የሞት ሞትን ምትስቂው?
አላምንሽም;
አላምንሽም!
ኑሮ ህይወት እንደደላሽ;
ብትነግሪኝም የውሸት ቃል፤
አንዱም እውነት እንዳልሆነ፡
ካይኖችሽ ላይ ያስታውቃል።
ማሳመኛ ሀተታዎች
አንደበትሽ ሲለቃቅም፥
ፊት የግዱን ፈገግ ቢል
አይን እውነቱን አይደብቅም!።
ደካክሞሻል
ህይወት ፍዳው፤
ፈትኖሻል
እምነት እዳው!።
ጠፍቶብሻል
መኖር ውሉ፤
ሰልችቶሻል
ማስመሰሉ!።
ማረፍን ነው የምትጓጊው፥
ህይወት ሆኗል የቁም እስር
ምኞትሽ ነው ለአንዴም እንኳን፡
ብትተኚ እናትሽ ስር ።
አትደቢቂኝ
አይጠፋኝም፦
የሀዘንሽ መቀስ ስንኩል፤
አትሳቂ እያመመሽ፥
ነይ አልቅሺ በ'ኔ በኩል!።
by @mikiyas_feyisa
@getem
@getem
@paappii
❤101👍37😢9😱1
ከ'ሳተ ገሞራ
እንደማር ወለላ
በጣት
ዝቆ ማውጣት
አውጥቶ ጣት መጥባት፣
መላስ ሲንጠባጠብ
በዲን ምላስ ማርጠብ
ቀላጭ ፍሙን ማኘክ
ማኘክና ማድቀቅ
ማድቀቅና ማላም
እንደዚያች ወላድ ላም
ላስ አርጎ እሳቱን
ቻል አርጎ ፍጅቱን
መዋጥ በዝምታ
እንዲያ ነው ይቅርታ።
በእግሮቻችን ዳና
ባተምነው ጎዳና
ስንጓዝ የቀና
እንቅፋት ሲቀስፈን
ጥጉን ተደግፈን
ቁስላችንን ማፈን፤
እግራችን ምስኪኑን
ዝምታ ክኒኑን
ዋጥ አርጎ የግዱን
ተወግቶ እንዳይደማ
አቁሳዩ ሳይሰማ
ግሽልጡን ደምድሞ
ቁስል ላይ ጠምጥሞ
ካህን መሆን መፍታት
ጸሎት ለእንቅፋት
ማድረስ በዝምታ፣
እንዲያ እንጂ... መች ዋዛ?
መች ቀላል ይቅርታ?
ይቅርታ መች ቀላል?
ለሰጪ ይከብዳል
ለሰጭ ካልከበደ፡ ተቀባይ ያለምዳል
ለማዳ ተቀባይ ፡ ከርሞ ያቃልላል
ከርሞ የቀለለ፡ ይነሳል ይወድቃል
ከዚያ በኋላማ ፡ምኑ ይጠየቃል?
እንቅፋት ይረክሳል፡ እግር ይደነዝዛል
የተጠመጠመው፡ ቁስል ያመረቅዛል
ድንጋይ የበዛበት፡ ድንጋይ ልብ ያፈራል
ከዛ በኋላማ ፡ ምኑ ይነገራል?
ማን ማንን ይፈራል? ማን ለማን ይራራል?
ጠጠር ያናቀፈው፡ ዓለት ሆኖ ያድራል።
ወድቀው ሳይነሱ
ሳይዘሩ ሳያርሱ
እንደ ኦሪት መና
ይቅር ከደመና
አይውረድ ከሰማይ፤
ሲያቀሉት ይከብዳል
ይቅርታና ሲሳይ።
የሬት የኮሶና
የግራዋ ድቃይ
ሲቀምሱት በስቃይ
«ሁለተኛ!» ብለው
እንደምጥ ላይደግሙት
በወለዱት ምለው
ፍም እሳት ተረግጠው
በጥፍር አፈሩን፡ሳር ቅጠሉን ቧጥጠው
ከፍሙ ማር ቆርጠው
ጎመራ እሳት ውጠው
አምጠው አምጠው
ማቅቀው ተንሰቅስቀው፡ በጊዜ ይሁንታ
እስኪነሱ ድረስ፡ መሞት ነው ይቅርታ።
(Red-8)
ይቅርታ መች ቀላል?
@getem
@getem
@paappii
እንደማር ወለላ
በጣት
ዝቆ ማውጣት
አውጥቶ ጣት መጥባት፣
መላስ ሲንጠባጠብ
በዲን ምላስ ማርጠብ
ቀላጭ ፍሙን ማኘክ
ማኘክና ማድቀቅ
ማድቀቅና ማላም
እንደዚያች ወላድ ላም
ላስ አርጎ እሳቱን
ቻል አርጎ ፍጅቱን
መዋጥ በዝምታ
እንዲያ ነው ይቅርታ።
በእግሮቻችን ዳና
ባተምነው ጎዳና
ስንጓዝ የቀና
እንቅፋት ሲቀስፈን
ጥጉን ተደግፈን
ቁስላችንን ማፈን፤
እግራችን ምስኪኑን
ዝምታ ክኒኑን
ዋጥ አርጎ የግዱን
ተወግቶ እንዳይደማ
አቁሳዩ ሳይሰማ
ግሽልጡን ደምድሞ
ቁስል ላይ ጠምጥሞ
ካህን መሆን መፍታት
ጸሎት ለእንቅፋት
ማድረስ በዝምታ፣
እንዲያ እንጂ... መች ዋዛ?
መች ቀላል ይቅርታ?
ይቅርታ መች ቀላል?
ለሰጪ ይከብዳል
ለሰጭ ካልከበደ፡ ተቀባይ ያለምዳል
ለማዳ ተቀባይ ፡ ከርሞ ያቃልላል
ከርሞ የቀለለ፡ ይነሳል ይወድቃል
ከዚያ በኋላማ ፡ምኑ ይጠየቃል?
እንቅፋት ይረክሳል፡ እግር ይደነዝዛል
የተጠመጠመው፡ ቁስል ያመረቅዛል
ድንጋይ የበዛበት፡ ድንጋይ ልብ ያፈራል
ከዛ በኋላማ ፡ ምኑ ይነገራል?
ማን ማንን ይፈራል? ማን ለማን ይራራል?
ጠጠር ያናቀፈው፡ ዓለት ሆኖ ያድራል።
ወድቀው ሳይነሱ
ሳይዘሩ ሳያርሱ
እንደ ኦሪት መና
ይቅር ከደመና
አይውረድ ከሰማይ፤
ሲያቀሉት ይከብዳል
ይቅርታና ሲሳይ።
የሬት የኮሶና
የግራዋ ድቃይ
ሲቀምሱት በስቃይ
«ሁለተኛ!» ብለው
እንደምጥ ላይደግሙት
በወለዱት ምለው
ፍም እሳት ተረግጠው
በጥፍር አፈሩን፡ሳር ቅጠሉን ቧጥጠው
ከፍሙ ማር ቆርጠው
ጎመራ እሳት ውጠው
አምጠው አምጠው
ማቅቀው ተንሰቅስቀው፡ በጊዜ ይሁንታ
እስኪነሱ ድረስ፡ መሞት ነው ይቅርታ።
(Red-8)
ይቅርታ መች ቀላል?
@getem
@getem
@paappii
❤54👍39🔥16
--------
ዓሳ አጥማጅ
ነፋስ በሚያስደንሰው ውሀ መሀል
ባየው የፀሀይ ግባት....
መረቡን ፈታ
አሳው'ን ጣለ
ከእጅ'ም ከሆዱ በፆሙ ዋለ።
ግን...
ባህሩ'ን ወደደው
ዳንሱ ገረመው!
:
ሲራራ
ሀጋይ በሚበላው አሸዋ መሀል
ላገኘው የሀረግ ጥላ
ሰግዶ እንቅልፉን ተኛ!
ወደነጠፈው ገበያ....
ነቅቶ ተነሳ
እሱም ሁሉን ረሳ!
:
አታክልተኛው
ወደሚያውቀው አፀድ ገባ
ወጣ...ገባ...
ለምለምለሙን አጣው
ጠፋበት ሽታው
ፍርሀት ገባው ለባለሱቁ!
አለቀሰ... ውበት ስለመድረቁ
ልቡ ውሀ አፈሰሰ...
ረሰረሰ።
:
አስበው ሳይሆን ደንግጠውለት
ሸሽተውት ሳይሆን ተገኝተውለት
ንቀውት ሳይሆን ተነክተውለት
አንዳንዴ ለህይወት
ሁሉንም ትቶ....
ወድቆ እፎይ ማለት!
Yishak abriham
@getem
@getem
ዓሳ አጥማጅ
ነፋስ በሚያስደንሰው ውሀ መሀል
ባየው የፀሀይ ግባት....
መረቡን ፈታ
አሳው'ን ጣለ
ከእጅ'ም ከሆዱ በፆሙ ዋለ።
ግን...
ባህሩ'ን ወደደው
ዳንሱ ገረመው!
:
ሲራራ
ሀጋይ በሚበላው አሸዋ መሀል
ላገኘው የሀረግ ጥላ
ሰግዶ እንቅልፉን ተኛ!
ወደነጠፈው ገበያ....
ነቅቶ ተነሳ
እሱም ሁሉን ረሳ!
:
አታክልተኛው
ወደሚያውቀው አፀድ ገባ
ወጣ...ገባ...
ለምለምለሙን አጣው
ጠፋበት ሽታው
ፍርሀት ገባው ለባለሱቁ!
አለቀሰ... ውበት ስለመድረቁ
ልቡ ውሀ አፈሰሰ...
ረሰረሰ።
:
አስበው ሳይሆን ደንግጠውለት
ሸሽተውት ሳይሆን ተገኝተውለት
ንቀውት ሳይሆን ተነክተውለት
አንዳንዴ ለህይወት
ሁሉንም ትቶ....
ወድቆ እፎይ ማለት!
Yishak abriham
@getem
@getem
👍41❤14👎7