የክረምት አፍቃሪ
.
አንዳንዴ በብላሽ፥
አንዳንዴ በቅናሽ፥
የምጠጣው ቡናሽ…
ይነሽጠኝና - ደጃፍሽ ላይ ቆሜ
ያቦል ቡና ድፍረት - ላዬ አገልድሜ
“ለምን ባንድ ጎጆ - ቤቱን አጫጭሰን
በረከቦት ዙሪያ - አንድ ጋቢ ለብሰን
ክፍቱን ላለ ቤቴ - እንደድስት ግጣም
ባዶዬን ሞልተሽው - ክረምቱን አንወጣም?”
ልልሽ እየዳዳኝ
በጋን ሳስብ ጎዳኝ!
በጋ ላይ ምን አለ?
ፀሐይ እየዋለ፥
አየር እየጋለ፥
ሲያልበው ያመሻል
ማን መታቀፍ ይሻል?
አንቺን ለማሳመን - ምን ሰበብ ይመጣል?
እንደክረምት ቡና - በጋስ ቤት ይጠጣል?
በምን አሞግሼ፥
ምን ብዬ ደግሼ፥
የዘውትር ደንበኛሽ - የቡና ቀበኛሽ
እንዴት ቤት ላስገባሽ - አንቺን ከነቡናሽ?
እኔ የለመድኩት - የዝናብ ቀን ቡና
አንቺን ደሞ ሳውቅሽ - ከጎንሽ ጀበና
ማታ ስትነሺ - አብሮሽ ስኒ ይነሳል
አንቺን ያለስኒ - ይከብደኛል መሣል::
ቡናም የለመድኩት - አንቺን ላይ ስመጣ
ካንቺም የተጠለልኩ - ደመናው ሲቆጣ
ዝናብ ነው ዕጣዬ
ደጃፍሽ ላይ ጣዬ።
ያጣምረን ወይ ያስጋን
አላውቀውም በጋን።
ይኾናል ወይ ላንቺ - ይሆናል ወይ ለኛ?
ኾኜ ልቀር ነው ወይ - የቡናሽ ደንበኛ?
ለስኒ፥ ጀበናሽ፥
ነፃ ሳልል ቅናሽ፥
ብቻ ከነቡናሽ፥
ከሙሉ ገመናሽ፥
ይህንን ኦና ቤት - አሟሙቂውና
እየበላን ቆሎ - እየጠጣን ቡና
ዝናብን እያየን - ተቃቅፈን ነው መክረም
ቡናሽ ካልተመቸው - ቢቀርስ መስከረም!
የዝናብን ፍቅር - ካደረቀው በጋ
አንቺ ቤቴ ገብተሽ - ክረምትስ ባይነጋ?
By abere
@getem
@getem
@paappii
.
አንዳንዴ በብላሽ፥
አንዳንዴ በቅናሽ፥
የምጠጣው ቡናሽ…
ይነሽጠኝና - ደጃፍሽ ላይ ቆሜ
ያቦል ቡና ድፍረት - ላዬ አገልድሜ
“ለምን ባንድ ጎጆ - ቤቱን አጫጭሰን
በረከቦት ዙሪያ - አንድ ጋቢ ለብሰን
ክፍቱን ላለ ቤቴ - እንደድስት ግጣም
ባዶዬን ሞልተሽው - ክረምቱን አንወጣም?”
ልልሽ እየዳዳኝ
በጋን ሳስብ ጎዳኝ!
በጋ ላይ ምን አለ?
ፀሐይ እየዋለ፥
አየር እየጋለ፥
ሲያልበው ያመሻል
ማን መታቀፍ ይሻል?
አንቺን ለማሳመን - ምን ሰበብ ይመጣል?
እንደክረምት ቡና - በጋስ ቤት ይጠጣል?
በምን አሞግሼ፥
ምን ብዬ ደግሼ፥
የዘውትር ደንበኛሽ - የቡና ቀበኛሽ
እንዴት ቤት ላስገባሽ - አንቺን ከነቡናሽ?
እኔ የለመድኩት - የዝናብ ቀን ቡና
አንቺን ደሞ ሳውቅሽ - ከጎንሽ ጀበና
ማታ ስትነሺ - አብሮሽ ስኒ ይነሳል
አንቺን ያለስኒ - ይከብደኛል መሣል::
ቡናም የለመድኩት - አንቺን ላይ ስመጣ
ካንቺም የተጠለልኩ - ደመናው ሲቆጣ
ዝናብ ነው ዕጣዬ
ደጃፍሽ ላይ ጣዬ።
ያጣምረን ወይ ያስጋን
አላውቀውም በጋን።
ይኾናል ወይ ላንቺ - ይሆናል ወይ ለኛ?
ኾኜ ልቀር ነው ወይ - የቡናሽ ደንበኛ?
ለስኒ፥ ጀበናሽ፥
ነፃ ሳልል ቅናሽ፥
ብቻ ከነቡናሽ፥
ከሙሉ ገመናሽ፥
ይህንን ኦና ቤት - አሟሙቂውና
እየበላን ቆሎ - እየጠጣን ቡና
ዝናብን እያየን - ተቃቅፈን ነው መክረም
ቡናሽ ካልተመቸው - ቢቀርስ መስከረም!
የዝናብን ፍቅር - ካደረቀው በጋ
አንቺ ቤቴ ገብተሽ - ክረምትስ ባይነጋ?
By abere
@getem
@getem
@paappii
👍57❤21🔥6
ስሚኝማ...
@ወዬ...
"እወድሻለሁ"❤️
@እኔም ውድድ ነው ማደርግህ😍
እንጃ ብቻ.....ፍቅር ነው መሰለኝ
ካንቺ ጋር ሳወራ የሚያንተባትበኝ😔
@አፈቀርከኝ እንዴ😜??
አላውቅም!...
ትንሽ ጭንቅ ይላል
አንደበት መልስ ካጣ ፍቅር ነው ይባላል😒?
@እእእእእ....😳
አዋ...
አላውቀውም ይሄን ስሜት ምን ይሁን ምን አዲስ ነገር
ብዙ ቆንጆ ቢኖር ላንዷም እንኳን አልበገር
ያንቺን ግን እኔንጃ....ጠለቅ ይላል ጭንቀት ፍጥሩ
የነገው ሚካኤል ይኸው አንድ ወሩ
@የምርህን ነው...😳😳
ባል እንዳለኝ አያወከው
ለዛ ነው የከበደኝ 😑
ለዛ ነው ያሳበደኝ😑
ዮኒ
ኣታን @yonatoz
@getem
@getem
@getem
@ወዬ...
"እወድሻለሁ"❤️
@እኔም ውድድ ነው ማደርግህ😍
እንጃ ብቻ.....ፍቅር ነው መሰለኝ
ካንቺ ጋር ሳወራ የሚያንተባትበኝ😔
@አፈቀርከኝ እንዴ😜??
አላውቅም!...
ትንሽ ጭንቅ ይላል
አንደበት መልስ ካጣ ፍቅር ነው ይባላል😒?
@እእእእእ....😳
አዋ...
አላውቀውም ይሄን ስሜት ምን ይሁን ምን አዲስ ነገር
ብዙ ቆንጆ ቢኖር ላንዷም እንኳን አልበገር
ያንቺን ግን እኔንጃ....ጠለቅ ይላል ጭንቀት ፍጥሩ
የነገው ሚካኤል ይኸው አንድ ወሩ
@የምርህን ነው...😳😳
ባል እንዳለኝ አያወከው
ለዛ ነው የከበደኝ 😑
ለዛ ነው ያሳበደኝ😑
ዮኒ
ኣታን @yonatoz
@getem
@getem
@getem
👍70😁23❤14😢10👎6🔥5
ባፈቀርኩት ሰው ስለተጎዳሁ
ባፈቀረኝ ሰው ስለተከዳሁ
ፍቅር ሚባል ቃል በሰማሁ ቁጥር
ሳጥናኤል ነው በአእምሮዬ ቋት ቀድሞ ሚሰፍር
አትፍረጅ ብስቅም
አይግረምሽ ባፌዝም
አፈቅርኃለው መባል
የልቤን ቅንጣት ስጋ ቆንጥጦ አይዝም
ትወጂኛለሽ!
እና ምን አገባኝ?
መልስ ሲፈልግ ነው
ፍቅር መስቀል አጥቶ መቀመቅ ያስገባኝ
ትጠብቂኛለሽ!
አቦ ተንቀሳቀሽ!
መከተል አይሻም
የተፈቃሪ ልብ አፍቃሪ ሳይሸሽ
ትጸልይኛለሽ!
አትሞኝ አንች ሴት
የተመኙት ዕለት
እንደዋዛ አይገኝ ሞት እና ሀሴት
ይደቁስሻል
ያበራይሻል
በፍቅር ተገን ሰይጣን ለምድ ለብሶ
ጠልተሽኝ ኑሪ
ልብሽ ይቸንከር ደም እንባ አልቅሶ
ባልጠበቀው ነው ጋኔል ሚረታ
ወደድኩህ ሳትይ
ፍቅርሽን ግለጭ ልክ እንደ ጌታ
#ኤልዳን
@eldan29
@getem
@getem
@getem
ባፈቀረኝ ሰው ስለተከዳሁ
ፍቅር ሚባል ቃል በሰማሁ ቁጥር
ሳጥናኤል ነው በአእምሮዬ ቋት ቀድሞ ሚሰፍር
አትፍረጅ ብስቅም
አይግረምሽ ባፌዝም
አፈቅርኃለው መባል
የልቤን ቅንጣት ስጋ ቆንጥጦ አይዝም
ትወጂኛለሽ!
እና ምን አገባኝ?
መልስ ሲፈልግ ነው
ፍቅር መስቀል አጥቶ መቀመቅ ያስገባኝ
ትጠብቂኛለሽ!
አቦ ተንቀሳቀሽ!
መከተል አይሻም
የተፈቃሪ ልብ አፍቃሪ ሳይሸሽ
ትጸልይኛለሽ!
አትሞኝ አንች ሴት
የተመኙት ዕለት
እንደዋዛ አይገኝ ሞት እና ሀሴት
ይደቁስሻል
ያበራይሻል
በፍቅር ተገን ሰይጣን ለምድ ለብሶ
ጠልተሽኝ ኑሪ
ልብሽ ይቸንከር ደም እንባ አልቅሶ
ባልጠበቀው ነው ጋኔል ሚረታ
ወደድኩህ ሳትይ
ፍቅርሽን ግለጭ ልክ እንደ ጌታ
#ኤልዳን
@eldan29
@getem
@getem
@getem
👍43❤12😢12😱6🔥3👎1
አፍሽ ውሸት ሲሸት
ንግግርሽ መቼ ገባኝ ፣
ጆሮሽ መጥፎ፥የቻይና ቃል
ምታደምጭው አይሰማኝ ፣
ከንፈርሽ የድርቅ ምች
ተቀብቶም ሚያስደነግጥ
ሰው እኮ ሞኝ ነው
ላንቺ ፀጉር እንጨት ሲልጥ
ስኬት አለሽ እንደሚሉት
ሱፍ ለብሳ ምታገሳ
ከራባትሽ ከአባትሽ ሞት
ትታያለች ተከልሳ
እንዳንቺ ተልከስክሳ...
አይንሽ ጥቁር፥ ፀጉር የለው
ብሌን የለው፥ ነጭም የለው
ለተመልካች
አይቶ አይመርጥም
ግራ አጋቢ ሸንጋራ ነው፣
ዳሌሽ ወጥ ሲርገበገብ
ህፃን ነበርሽ ገና ገና፣
ለንቋጣ ነው ላጣጥ ግርፊያ
ውበትሽን ለሚያጠና፣
ባንባ ፍሬ እዬወደቀ
ምግብ ሆኖ ቡፌ ሲቀርብ
እንጨት ፈላጭ ይሳሳታል
ምግብሽን ቀምሶ ሲጠርብ
ሆኖም ሆኖም ይወዱሻል
ቆንጆ ወንዶች በየተራ
ጡትሽን ለመታሸት
ማሳጅ ነው ያንቺ ጣራ
ይወዱሻል እነ እግዜሩ
ይወዱሻል እነ አምላኩ
የፈጠረ ሲኮራብሽ
ያልፈጠሩሽ ተሳቀቁ
@geez_mulat
ግዕዝ ሙላት
@getem
@getem
@paappii
ንግግርሽ መቼ ገባኝ ፣
ጆሮሽ መጥፎ፥የቻይና ቃል
ምታደምጭው አይሰማኝ ፣
ከንፈርሽ የድርቅ ምች
ተቀብቶም ሚያስደነግጥ
ሰው እኮ ሞኝ ነው
ላንቺ ፀጉር እንጨት ሲልጥ
ስኬት አለሽ እንደሚሉት
ሱፍ ለብሳ ምታገሳ
ከራባትሽ ከአባትሽ ሞት
ትታያለች ተከልሳ
እንዳንቺ ተልከስክሳ...
አይንሽ ጥቁር፥ ፀጉር የለው
ብሌን የለው፥ ነጭም የለው
ለተመልካች
አይቶ አይመርጥም
ግራ አጋቢ ሸንጋራ ነው፣
ዳሌሽ ወጥ ሲርገበገብ
ህፃን ነበርሽ ገና ገና፣
ለንቋጣ ነው ላጣጥ ግርፊያ
ውበትሽን ለሚያጠና፣
ባንባ ፍሬ እዬወደቀ
ምግብ ሆኖ ቡፌ ሲቀርብ
እንጨት ፈላጭ ይሳሳታል
ምግብሽን ቀምሶ ሲጠርብ
ሆኖም ሆኖም ይወዱሻል
ቆንጆ ወንዶች በየተራ
ጡትሽን ለመታሸት
ማሳጅ ነው ያንቺ ጣራ
ይወዱሻል እነ እግዜሩ
ይወዱሻል እነ አምላኩ
የፈጠረ ሲኮራብሽ
ያልፈጠሩሽ ተሳቀቁ
@geez_mulat
ግዕዝ ሙላት
@getem
@getem
@paappii
❤31👍26👎14😱2🤩2
ነበር
ነበር ምትል ቃል ዉስጥ ስንት ህመም አለ?
በልብ ቁስል ቋጥሮ ስቃይን ያዘለ
እፍኝ ተድላን አስጨብጦ ክምር ሀዘን ያስታቀፈ
ኩራዝ ትዝታን አሳይቶ ፀሐይ ተስፋን የዘረፈ
በፍቅራችን ጓዳ ከደስታችን ገዝፎ ተራራ ያከለ
ነበር ምትል ቃል ዉስጥ ስንት ህመም አለ ?
ዘረ-ሠናይ
@Prince_Zeresenay
@getem
@getem
@getem
ነበር ምትል ቃል ዉስጥ ስንት ህመም አለ?
በልብ ቁስል ቋጥሮ ስቃይን ያዘለ
እፍኝ ተድላን አስጨብጦ ክምር ሀዘን ያስታቀፈ
ኩራዝ ትዝታን አሳይቶ ፀሐይ ተስፋን የዘረፈ
በፍቅራችን ጓዳ ከደስታችን ገዝፎ ተራራ ያከለ
ነበር ምትል ቃል ዉስጥ ስንት ህመም አለ ?
ዘረ-ሠናይ
@Prince_Zeresenay
@getem
@getem
@getem
👍52❤21😢11🔥2
ከዘመን እስራት
ከህይወት ማደሪያ ከቀን ተቃቅሬ
ወደ ጥልቅ ሩቁ ወደታች ማትሬ
ጊዜ ከማይደፍረው
ሰው ከማይደርስበት
ሁሉም ራሱን ጥሎ
ወድቆ ከቀረበት
ርቄ ተከልዬ
በሀሳብ አንቀልባ
እርቃኔን እንዳለሁ
ልብሽ ውስጥ ልገባ
ከጅስሜ ርጋፊ
ከህልቆ ቢስ ነብሴ
ነኝ ካልኩት ወዲያ
ዳር ይዤ ከራሴ
የልጅነቴን ብሩህ ሙዚቃ
በሳቅሽ ዜማ በገላሽ ኖታ
ፍም እሳት ሆኜ
እንድጫወተው
ሌቱን በዜማ ስወተውተው
ትኩስ እንባዬ ወርዶ አቃጠለኝ
ነጋ መሰለኝ
By አዲብ
@getem
@getem
@paappii
ከህይወት ማደሪያ ከቀን ተቃቅሬ
ወደ ጥልቅ ሩቁ ወደታች ማትሬ
ጊዜ ከማይደፍረው
ሰው ከማይደርስበት
ሁሉም ራሱን ጥሎ
ወድቆ ከቀረበት
ርቄ ተከልዬ
በሀሳብ አንቀልባ
እርቃኔን እንዳለሁ
ልብሽ ውስጥ ልገባ
ከጅስሜ ርጋፊ
ከህልቆ ቢስ ነብሴ
ነኝ ካልኩት ወዲያ
ዳር ይዤ ከራሴ
የልጅነቴን ብሩህ ሙዚቃ
በሳቅሽ ዜማ በገላሽ ኖታ
ፍም እሳት ሆኜ
እንድጫወተው
ሌቱን በዜማ ስወተውተው
ትኩስ እንባዬ ወርዶ አቃጠለኝ
ነጋ መሰለኝ
By አዲብ
@getem
@getem
@paappii
👍31❤19👎2🤩1
አንዲት ሴት ነበረች
ቤትና ትዳሩን
ህይወቱን የረሳ
ዘወትር በስካር
ዱላ የሚያነሳ
ቀን የጣለው ባሏን
ተቋቁማ የኖረች
ወዟ የነጠፈ
አንዲት ሴት ነበረች።
የእናትነቷን
ቤቷን ላለመፍታት
መበደሏን ችላ
መኖር ያታከታት
ግፍ ስለበዛባት
ጉንተላ ግርፋት
የደም እንባን
ማፍሰስ ሁሌም ያለጥፋት
የአብራኳን ክፋዮች
እንቁ ልጆች ጥላ
አንድ ጨቅላ ህጻን
በጀርባዋ አዝላ
ልብስ ሳትል ለአካል
ጫማ ሳትል ለእግሯ
ሀገር ጥላ ጠፋች
እናት ገራገሯ
ገደሉን ወረደች
ተራራውን ወጣች
እንባ እያወረደች
ክብሯንም ስላጣች
የአንገቷ ማስገቢያ
አንድ ወዳጅ ስታጣ
ከጎዳና አደረች
ለስቃይ ተጋልጣ
እድለ ቢስ እናት
በድካም ስሜቷ
ረሀብ ደቁሷት
ባልቀመሰ አንጀቷ
ልጇን ለመመገብ
ፍፁም ስላልቻለች
የእሷን ጥም ረስታ
ስለ ልጇ አዝናለች
እንባ ጉንጯን ሞልቷል
ጎስቋላ አይኗ ቀልቷል
ምንም እንደማትችል
የአቅሟን ማለቅ አምና
እጇን ዘረጋችው
ቆመች ለልመና
ይቺ ምስኪን እናት
ደስታ የማይቀናት
By ይቴ(@gtmwustie)
@getem
@getem
@getem
ቤትና ትዳሩን
ህይወቱን የረሳ
ዘወትር በስካር
ዱላ የሚያነሳ
ቀን የጣለው ባሏን
ተቋቁማ የኖረች
ወዟ የነጠፈ
አንዲት ሴት ነበረች።
የእናትነቷን
ቤቷን ላለመፍታት
መበደሏን ችላ
መኖር ያታከታት
ግፍ ስለበዛባት
ጉንተላ ግርፋት
የደም እንባን
ማፍሰስ ሁሌም ያለጥፋት
የአብራኳን ክፋዮች
እንቁ ልጆች ጥላ
አንድ ጨቅላ ህጻን
በጀርባዋ አዝላ
ልብስ ሳትል ለአካል
ጫማ ሳትል ለእግሯ
ሀገር ጥላ ጠፋች
እናት ገራገሯ
ገደሉን ወረደች
ተራራውን ወጣች
እንባ እያወረደች
ክብሯንም ስላጣች
የአንገቷ ማስገቢያ
አንድ ወዳጅ ስታጣ
ከጎዳና አደረች
ለስቃይ ተጋልጣ
እድለ ቢስ እናት
በድካም ስሜቷ
ረሀብ ደቁሷት
ባልቀመሰ አንጀቷ
ልጇን ለመመገብ
ፍፁም ስላልቻለች
የእሷን ጥም ረስታ
ስለ ልጇ አዝናለች
እንባ ጉንጯን ሞልቷል
ጎስቋላ አይኗ ቀልቷል
ምንም እንደማትችል
የአቅሟን ማለቅ አምና
እጇን ዘረጋችው
ቆመች ለልመና
ይቺ ምስኪን እናት
ደስታ የማይቀናት
By ይቴ(@gtmwustie)
@getem
@getem
@getem
👍86😢63❤26🎉2😱1
ለአባቴ
✍️©እስራኤል
በድቅድቅ ጨለማ መሐል ፣
የምትፈነጥቅ መብራቴ
በጥም በረሃብ ስቀጣ፣
የምታጠግበኝ ራቴ።
አባቴ።
ምእት ቦታ ተከፋፍለህ፣
በእኔ ሐሣብ ጭንቀት ግዞት
ነገዬን ልቦናህ አስልቶ ፣
መንፈስህ ኒሻኔን ይዞት
መቀመቅ ወርደህ በእሳት ፥
ሩህን ጠባሳ ወርሶት
አሁንም እንባህ ለእኔ ነው ፥
ችግሬ ሆድህን አብሶት
ጋሬጣ አሜኬላዬ ፥
በእግሮችህ ተሰንቅረዋል
ጫንቃና ብርቱ ክንዶችህ ፥
በሸክሜ ተዘልሰዋል
ዋጋህን በስሌት ተመን ፥
ደርሼ አልደርስበትም
አንድ ነብስ በቂው አይደለም፥
ሦስት አራት አያንስበትም።
አባቴ
ለካስ አባት በእናት አንጀት ፥
ኮስታራ ገፅ አሣይቶ
የጋተውን መራራ ሐሞት ፥
በሳቅ ግርዶሹ አቆይቶ
የብቻውን የዕንባ ጠበል ፥
በብቻ መቅደሱ ረጭቶ
መከራን በክንዱ ትግል ፥
ስቃይን ያለ ግልግል
ብቻውን የገጠመ ሰብ ፥
ምን ካሣ ይመጥነዋል
ምን ይበቃዋል ቢታሰብ።
አውላላ በረሃ መሐል፥
ለምለም መስክ የምታሳየኝ
ጭንጫ ካልኩት ህይወቴ ላይ፥
ወዛም ምንጭ የምታቆየኝ።
የእዳ መዝገቤ ሽረት፥
ድካምን ማዘናጋብህ
የህይወት ዘመኔ ተረት፤
አይኖችህ ሳይከደኑ፥
ትንፋሽህ በርዶ ሳይጠፋ፥
ጉልበትህ ሳይካዳህ በፊት
በአስታጠቀከኝ ወኔ ዝናር
ሽንፈትን ላድርገው ወንፊት
መልካም ያልሁትን መባ
ላቅርበው አባቴ አንተ ፊት።
@AdamuReta
@getem
@getem
@getem
👍45❤25
"ባጭር ቀረን" ስንል - እድሜ ላበደሩን
ቀርፀው ላሳመሩን
ለኩሰው ላበሩን
ቺርስ!!
።።።።
ፊታችንን ዐይተው
እንደተቸገርን - ካይናችን ላወቁ
ስለማርያም ብለን
እስክንለምናቸው - ቆመው ላልጠበቁ
ቺርስ!!!
።።።።
ወድቀው ለማይጥሉ -ነግሰው ለሚያነግሱ
ነውራችንን ዐይተው
ልክ እንደ ድመት ኩስ ፣ ለሚያለባብሱ
ብድር አበድረው ፣ ፈጥነው ለሚረሱ😉
ቺርስ!!!!
።።።።።።
ላባ ላረጉልን ፣ የመከራ ሸክሙን
ቀልደው ላሳቁን ፣ ተጫውተው ላከሙን
በቸከ ዘመን ላይ...
ስጋ ለበስ ትንግርት -ሆነው ላስደመሙን
ቺርስ!!!!!
።።።።።።።።።።።
(✍️ Bewketu Seyoum )
መልካም ልደት በውቄ!!!
@getem
@getem
@paappii
ቀርፀው ላሳመሩን
ለኩሰው ላበሩን
ቺርስ!!
።።።።
ፊታችንን ዐይተው
እንደተቸገርን - ካይናችን ላወቁ
ስለማርያም ብለን
እስክንለምናቸው - ቆመው ላልጠበቁ
ቺርስ!!!
።።።።
ወድቀው ለማይጥሉ -ነግሰው ለሚያነግሱ
ነውራችንን ዐይተው
ልክ እንደ ድመት ኩስ ፣ ለሚያለባብሱ
ብድር አበድረው ፣ ፈጥነው ለሚረሱ😉
ቺርስ!!!!
።።።።።።
ላባ ላረጉልን ፣ የመከራ ሸክሙን
ቀልደው ላሳቁን ፣ ተጫውተው ላከሙን
በቸከ ዘመን ላይ...
ስጋ ለበስ ትንግርት -ሆነው ላስደመሙን
ቺርስ!!!!!
።።።።።።።።።።።
(✍️ Bewketu Seyoum )
መልካም ልደት በውቄ!!!
@getem
@getem
@paappii
❤50👍34🔥2
ይናገራል ፎቶ-፪
...
ከኮሞዲኖው ላይ
ከግድግዳውም ላይ
አንቺኑ አንቺኑ ሳይ
ከኔ ዘንድ የቀረ ፥ ፎቶሽን ታቅፌ
ምላሽ ጠብቃለው
ይናገራል ፎቶ ፥ የሚል ግጥም ፅፌ
...
[
ይናገራል ፎቶ
ብጠብቃት ቀ.....ና.....ት
ብጠብቃት ሳ...ም...ን...ታ...ት
ብጠብቃት ወ..........ራ............ት
ብጠብቃት አ........መ.......ታ.........ት
እኔን ከማናገር ፥ ዝምታ በልጦባት
ከፎቶው ላይ ቀረች፤
ሳሎን እየዋለች ፥ ሳሎን እያደረች።
]
ወረቀቱን ቀደድኩ ፥ ግጥሙን ሰርዤው
ፎቶውን መለስኩ ፥ ከአልበሙ ሸጉጬው
...
እንግዲህ ምን ትሆኚ!
አልፎ አልፎ እየመጣ
እንግዳ ያይሻል ፥ እስረኛ ስትሆኚ።
ሲናፍቅሽ ኮሞዲኖው
ሲናፍቅሽ መደርደሪያው
ሲናፍቅሽ የትላንቱ
ታወሪኝ ይሆናል ፥ ልክ እንደ በፊቱ
ሳሙኤል አለሙ
@samuelalemuu
@getem
@getem
...
ከኮሞዲኖው ላይ
ከግድግዳውም ላይ
አንቺኑ አንቺኑ ሳይ
ከኔ ዘንድ የቀረ ፥ ፎቶሽን ታቅፌ
ምላሽ ጠብቃለው
ይናገራል ፎቶ ፥ የሚል ግጥም ፅፌ
...
[
ይናገራል ፎቶ
ብጠብቃት ቀ.....ና.....ት
ብጠብቃት ሳ...ም...ን...ታ...ት
ብጠብቃት ወ..........ራ............ት
ብጠብቃት አ........መ.......ታ.........ት
እኔን ከማናገር ፥ ዝምታ በልጦባት
ከፎቶው ላይ ቀረች፤
ሳሎን እየዋለች ፥ ሳሎን እያደረች።
]
ወረቀቱን ቀደድኩ ፥ ግጥሙን ሰርዤው
ፎቶውን መለስኩ ፥ ከአልበሙ ሸጉጬው
...
እንግዲህ ምን ትሆኚ!
አልፎ አልፎ እየመጣ
እንግዳ ያይሻል ፥ እስረኛ ስትሆኚ።
ሲናፍቅሽ ኮሞዲኖው
ሲናፍቅሽ መደርደሪያው
ሲናፍቅሽ የትላንቱ
ታወሪኝ ይሆናል ፥ ልክ እንደ በፊቱ
ሳሙኤል አለሙ
@samuelalemuu
@getem
@getem
👍52❤26😢9😁3👎2
ሲጋራ
በአንድ የሲጋራ ቁራጭ ብዙ የታፀፈ
ብዙ ታሪክ አለ በጣም የገዘፈ
አንባቢ የሌለው
ጭሱ የከለለው
ብዙ ታሪክ አለው
ብዙ ህመም አለው
ብዙ ቁስል አለው
ረግጠን ያለፍነው
ፍፁም ልብ ያላንነው
እሳት ወዳጅ አርጎ ከሰው ዘር እርቆ
ህመም የታቀፈ በጭስ ተደብቆ
መንገድ በተጣለች የሲጋራ ቁሮ
ትልቅ ሰው አያለው ከዳር ተሰንቅሮ
ህይወቱን የሰጠ ደሰታውን የሰጠ
እችን ሻማ ህይወት በሳት ያቀለጠ
በሲጋራ ፍቅር
ለምን
ሲጋራ ስለማትጎዳው
እንደ ሰው ስለማትከዳው
by kerim
@getem
@getem
@getem
በአንድ የሲጋራ ቁራጭ ብዙ የታፀፈ
ብዙ ታሪክ አለ በጣም የገዘፈ
አንባቢ የሌለው
ጭሱ የከለለው
ብዙ ታሪክ አለው
ብዙ ህመም አለው
ብዙ ቁስል አለው
ረግጠን ያለፍነው
ፍፁም ልብ ያላንነው
እሳት ወዳጅ አርጎ ከሰው ዘር እርቆ
ህመም የታቀፈ በጭስ ተደብቆ
መንገድ በተጣለች የሲጋራ ቁሮ
ትልቅ ሰው አያለው ከዳር ተሰንቅሮ
ህይወቱን የሰጠ ደሰታውን የሰጠ
እችን ሻማ ህይወት በሳት ያቀለጠ
በሲጋራ ፍቅር
ለምን
ሲጋራ ስለማትጎዳው
እንደ ሰው ስለማትከዳው
by kerim
@getem
@getem
@getem
👍34❤10😢6🔥4👎3
[የቢራቢሮዋ እንጉርጉሮ]
___
ከፅጌዎች ማሳ መሀል...
(አንዲት ቆንጆ የተዋበች...)
ህብረ ቀለም ቢራቢሮ ፤
በሸረሪት ፈትለ-ድር ውስጥ...
ተጠምጥማ ክንፏ ታስሮ ፥
የራስ ሙሾ የመሰለ
ታፈልቃለች እንጉርጉሮ ።
(እንጉርጉሮ ታሰማለች...)
እንዲህ እንዲህ ታዜማለች....
🦋
«ያለፍኩትን ልናገረው...
ልናዘዝ ለጣ
ከአንዱ አበባ ወዳንዱ ጋ ....
ብርር ..ብርር — “ ቢራቢሮ ”
ክንፍ ተክላልኝ ተፈጥሮ...
አድርጋኝ ነፃ በራሪ ፥
(ተውቦ ተኩሎ ኗሪ)
ወዲያ ወዲህ...
ወዲያ ወዲህ...
ብክን ብክን – ስብር ስብር
እጥፍ ዘርጋ — ብር ብር...
ደሞ ቀና ደሞ ደፋ
ብዙ ብዙ ስለፋ
ይሄን ቀምሼ ያም እንዳያልፈኝ
ሽቅብ ምኞቴ ሲያክለፈልፈኝ
አሮጌ ሆዳም ሸረሪት...
ባሮጌ ድሩ — ጠለፈኝ ።
ገላ አካሌ ተተብትቦ
ስሱ ክንፌ ታሰረ ፤
እንኳን “መብረር”
“መኖር” — ቀረ ።
(ጠበቀብኝ ሰንሰለቱ)
ጠግቦ አደረ ሸረሪቱ ...
ቀለማም ክንፌ — ሆዱን ሞላለት
(ጨለመችብኝ ህይወቴ)
እራት ሆነለት (ውበቴ) ።
🦋
“ነፃ ነኝ” ብለው
“ክንፍ አለኝ” ብለው....
'ማረፍ' የሌለው — መብረር ቢያበዙ
ወጥመድ አያጣም — የመንገድ ጓዙ ።
(ያልቀመሱትን መቅመስ ቢያጓጓም ...)
የእግር ማረፊያ...የምኞት ልጓም ...
(የመብትም ማብቂያ...)
“ልክ” ያስፈልጋል፤
ሙሉ ነፃነት — “ባሪያ” ያደርጋል ። »
🦋
_
By @Bekalushumye
@getem
@getem
@getem
___
ከፅጌዎች ማሳ መሀል...
(አንዲት ቆንጆ የተዋበች...)
ህብረ ቀለም ቢራቢሮ ፤
በሸረሪት ፈትለ-ድር ውስጥ...
ተጠምጥማ ክንፏ ታስሮ ፥
የራስ ሙሾ የመሰለ
ታፈልቃለች እንጉርጉሮ ።
(እንጉርጉሮ ታሰማለች...)
እንዲህ እንዲህ ታዜማለች....
🦋
«ያለፍኩትን ልናገረው...
ልናዘዝ ለጣ
ረ ሞቴ ፤
ባንድ ቦታ የማትጸና...
ብኩን ነበረች ህይወቴ ።
ባካኝ ነበርኩ ከንቱ ፍጥረት....
የማልሰክን የማልረጋ ፤
ከዚም ከዚያም ጣ
ም ፍለጋ...ከአንዱ አበባ ወዳንዱ ጋ ....
ብርር ..ብርር — “ ቢራቢሮ ”
ክንፍ ተክላልኝ ተፈጥሮ...
አድርጋኝ ነፃ በራሪ ፥
(ተውቦ ተኩሎ ኗሪ)
ወዲያ ወዲህ...
ወዲያ ወዲህ...
ብክን ብክን – ስብር ስብር
እጥፍ ዘርጋ — ብር ብር...
ደሞ ቀና ደሞ ደፋ
ብዙ ብዙ ስለፋ
ይሄን ቀምሼ ያም እንዳያልፈኝ
ሽቅብ ምኞቴ ሲያክለፈልፈኝ
አሮጌ ሆዳም ሸረሪት...
ባሮጌ ድሩ — ጠለፈኝ ።
ገላ አካሌ ተተብትቦ
ስሱ ክንፌ ታሰረ ፤
እንኳን “መብረር”
“መኖር” — ቀረ ።
(ጠበቀብኝ ሰንሰለቱ)
ጠግቦ አደረ ሸረሪቱ ...
ቀለማም ክንፌ — ሆዱን ሞላለት
(ጨለመችብኝ ህይወቴ)
እራት ሆነለት (ውበቴ) ።
🦋
“ነፃ ነኝ” ብለው
“ክንፍ አለኝ” ብለው....
'ማረፍ' የሌለው — መብረር ቢያበዙ
ወጥመድ አያጣም — የመንገድ ጓዙ ።
(ያልቀመሱትን መቅመስ ቢያጓጓም ...)
የእግር ማረፊያ...የምኞት ልጓም ...
(የመብትም ማብቂያ...)
“ልክ” ያስፈልጋል፤
ሙሉ ነፃነት — “ባሪያ” ያደርጋል ። »
🦋
_
By @Bekalushumye
@getem
@getem
@getem
👍51❤26🔥6
እኖራለሁ ብለው
ኑረው ላኗኗሩን
ዝም አልን እያሉ
ጩኸው ለሚያስጠሩን
እገላለው ብለው
ከጫካ ደን ላሳደገን
እገላለሁ ብለው
ከሞት በሩ ላሳጠረን
አኖራለሁ ብለው
ሞቱን ደሙን አስተማረን
የራሳቸው ጉዳይ
አቦ ፍታ ላሉን
ከእርግብ ላባ አይደለም
መብራት የከለሉን
ሲባልግ ተስፋችን
ሲባልግ ኑሯችን
በዘመነ ሻንቡቅ
ምንኛ ቢሳቀቅ
የሰው ተስፋ ይሻላል
ጌታን ከመጠበቅ
የሰው ተስፋ ሞትን ይዟል
የሰው ተስፋ ይናደፋል
የጌታም ዝምታ ነው
መምጫ ቀኑ የሚረብሽ
ከእኛ እልፈት እስኪጠለሽ
ጠጋ ብሎ እየራቀ
ሳይታሰብ ባለም ሚያመሽ
'
'
@geez_mulat
ግዕዝ ሙላት
@getem
@getem
@getem
ኑረው ላኗኗሩን
ዝም አልን እያሉ
ጩኸው ለሚያስጠሩን
እገላለው ብለው
ከጫካ ደን ላሳደገን
እገላለሁ ብለው
ከሞት በሩ ላሳጠረን
አኖራለሁ ብለው
ሞቱን ደሙን አስተማረን
የራሳቸው ጉዳይ
አቦ ፍታ ላሉን
ከእርግብ ላባ አይደለም
መብራት የከለሉን
ሲባልግ ተስፋችን
ሲባልግ ኑሯችን
በዘመነ ሻንቡቅ
ምንኛ ቢሳቀቅ
የሰው ተስፋ ይሻላል
ጌታን ከመጠበቅ
የሰው ተስፋ ሞትን ይዟል
የሰው ተስፋ ይናደፋል
የጌታም ዝምታ ነው
መምጫ ቀኑ የሚረብሽ
ከእኛ እልፈት እስኪጠለሽ
ጠጋ ብሎ እየራቀ
ሳይታሰብ ባለም ሚያመሽ
'
'
@geez_mulat
ግዕዝ ሙላት
@getem
@getem
@getem
👍23❤16😁2👎1
ባንድ ሀገር እየኖርን
ባንድ መንደር ሳለን ፣
ወዲያ ሲስቁ
ወዲህ እናለቅሳለን ፣
ባንድ ግቢ ሀገር
ባንድ አጥር እያለን፣
ወዲያ ድግስ ሲሆን
ተስካር እንውላለን ፣
ወዲህ ማዶ ሰባራ እንባ፣
ወዲያ ሰፈር ደስታ መባ፣
ዓለም ገፋን እንደ ዕንባ፣
ተንቀናል ተከፍተናል
እንዳብሽ አበባ ፣
ወዲያ ማዶ ሰባራ ሳቅ
ወዲህ ማዶ ሙሉ ማቅ
ንጉስ መላ ጠፍቶት
ኳስ ይጫወታል፣
ሞት ሬሳ ወገን
በስታዲየም ተኝቷል፣
ወዲህ ሲሆን፥የእግዜር ሰንበት
ሞት ይገኛል ባለንበት
ዜጎች ሁሉ ዝም አሉ
አለም ሁሉ ሸሼን፣
በውስጥ ተባይ አለ
ሁሉም አጠለሼን፣
ምንድነው ጥፋታችን
በሞትስ የታሼን
ባንድ ቤት እያለን
ማዘን ካሳቀቀን
እንግዲህ ዝም ነው
ጊዜ ያፈራርደን
@geez_mulat
ግዕዝ ሙላት
መታሰቢያነቱ
ለኢትዮጵያውያን
@getem
@getem
@getem
ባንድ መንደር ሳለን ፣
ወዲያ ሲስቁ
ወዲህ እናለቅሳለን ፣
ባንድ ግቢ ሀገር
ባንድ አጥር እያለን፣
ወዲያ ድግስ ሲሆን
ተስካር እንውላለን ፣
ወዲህ ማዶ ሰባራ እንባ፣
ወዲያ ሰፈር ደስታ መባ፣
ዓለም ገፋን እንደ ዕንባ፣
ተንቀናል ተከፍተናል
እንዳብሽ አበባ ፣
ወዲያ ማዶ ሰባራ ሳቅ
ወዲህ ማዶ ሙሉ ማቅ
ንጉስ መላ ጠፍቶት
ኳስ ይጫወታል፣
ሞት ሬሳ ወገን
በስታዲየም ተኝቷል፣
ወዲህ ሲሆን፥የእግዜር ሰንበት
ሞት ይገኛል ባለንበት
ዜጎች ሁሉ ዝም አሉ
አለም ሁሉ ሸሼን፣
በውስጥ ተባይ አለ
ሁሉም አጠለሼን፣
ምንድነው ጥፋታችን
በሞትስ የታሼን
ባንድ ቤት እያለን
ማዘን ካሳቀቀን
እንግዲህ ዝም ነው
ጊዜ ያፈራርደን
@geez_mulat
ግዕዝ ሙላት
መታሰቢያነቱ
@getem
@getem
@getem
👍51😢25❤11😱1
⨳
ብታረፍጅ...
ሀሳቤን ሰብስቤ ቃላት ሳውጠነጥን፣
ላንደበቴ ውበት ለክብርሽ ሚመጥን፣
ያው ሳቅሽ ሽልማት
ትልቅ ስጦታ አይደል?
ምን ባደርግ ይበጃል በገፍ ለመታደል?
(እያሰላሰልኩኝ..!)
...
ብታረፍጅ...
ለማንሰርከክ ፡ ስርክክ ልቤን፣
ልትንጅው ፡ ቀልብ ካቤን፣
ተውበሽ ፡ ልታፈዥኝ፣
አፌን በእጅ ፡ ልታስይዥኝ፣
ፀጉርሽን ስትነካኪ
የልብስ አይነት ስትለኪ..
(እያወቅሽ)
ሙሉ እንደሆንሽ..
በዝተሽ በዝተሽ የምትተርፊ፣
ላለመጉደል ስትለፊ፣
ያንን አርገሽ ይንን ስትረሽ፣
መስታወት ፊት ተገትረሽ፣
(እያሰብኩኝ..!)
...
ብታረፍጅ
አይነስውር እየመራሽ
ዝናብ ጥሎ እያበራሽ
ጫማሽ ድንገት ተበጥሶ
ሊስትሮ ገይ ገና አድሶ
እያሰብኩኝ..)
(እየተቁነጠነጥኩ...)
..
...ብታረፍጅ
የመምጣትሽ እምነት
የተቆጣጠረኝ ፣
ተሸራረፈና ፡ ፍርሃት ዘየረኝ።
ብትቀሪ..
የሚጨልም ፊቴ ድምቀት ፣
የጉጉቴን ከባድ ውድቀት ፣
የቀኔን መበላሸት ፣
ሳይነጋልኝ ወዲያው መምሸት፣
የደስታዬን አደራረቅ፣
ስቅል ልቤን አፈራረጥ፣
(እያሰብኩኝ)
ብትቀሪ..
ምን እንደሚውጠኝ
ስታረፍጂ ተረዳሁኝ።
እና ይልመድብሽ..
ግዴለም ሁሌ አርፍጂ
አደራሽን ( አትቅሪ እንጂ )
⨳
*ብንያም እጅጉ
@getem
@getem
@getem
ብታረፍጅ...
ሀሳቤን ሰብስቤ ቃላት ሳውጠነጥን፣
ላንደበቴ ውበት ለክብርሽ ሚመጥን፣
ያው ሳቅሽ ሽልማት
ትልቅ ስጦታ አይደል?
ምን ባደርግ ይበጃል በገፍ ለመታደል?
(እያሰላሰልኩኝ..!)
...
ብታረፍጅ...
ለማንሰርከክ ፡ ስርክክ ልቤን፣
ልትንጅው ፡ ቀልብ ካቤን፣
ተውበሽ ፡ ልታፈዥኝ፣
አፌን በእጅ ፡ ልታስይዥኝ፣
ፀጉርሽን ስትነካኪ
የልብስ አይነት ስትለኪ..
(እያወቅሽ)
ሙሉ እንደሆንሽ..
በዝተሽ በዝተሽ የምትተርፊ፣
ላለመጉደል ስትለፊ፣
ያንን አርገሽ ይንን ስትረሽ፣
መስታወት ፊት ተገትረሽ፣
(እያሰብኩኝ..!)
...
ብታረፍጅ
አይነስውር እየመራሽ
ዝናብ ጥሎ እያበራሽ
ጫማሽ ድንገት ተበጥሶ
ሊስትሮ ገይ ገና አድሶ
እያሰብኩኝ..)
(እየተቁነጠነጥኩ...)
..
...ብታረፍጅ
የመምጣትሽ እምነት
የተቆጣጠረኝ ፣
ተሸራረፈና ፡ ፍርሃት ዘየረኝ።
ብትቀሪ..
የሚጨልም ፊቴ ድምቀት ፣
የጉጉቴን ከባድ ውድቀት ፣
የቀኔን መበላሸት ፣
ሳይነጋልኝ ወዲያው መምሸት፣
የደስታዬን አደራረቅ፣
ስቅል ልቤን አፈራረጥ፣
(እያሰብኩኝ)
ብትቀሪ..
ምን እንደሚውጠኝ
ስታረፍጂ ተረዳሁኝ።
እና ይልመድብሽ..
ግዴለም ሁሌ አርፍጂ
አደራሽን ( አትቅሪ እንጂ )
⨳
*ብንያም እጅጉ
@getem
@getem
@getem
❤33👍30🔥12