["እቺን ዓመት አትተወኝ"]
ጊዜ የሰቀለውን እንቅብ
ሞት ከብብት ሲስብ
ጉብዝናን
ውብ ዝናን ወራት ሲንቀው
ምን ብዬ ጌታን ላስበው ..?
ምን ብዬ ?
ዝም ብዬ..?
* * * * *** * *
ለየቀን ትካዜ :ለየቀኑ መሃት
እድሜ እየሰጡ አሟሟትን መሳት
አቋቋሜን መርሳት .
ከሆነ እጣዬ
በል እንጂ አንድዬ
ላግራሞት አዱለኝ
ንጋት ማምሻን አዝሎ ቀኔን አይከልለኝ
ያጎበጠኝ
የደገፈኝ -ሸክም
እሹሩሩ: አልችል ባለ አቅም
እንዲማ...
ከመንገድ አልዘልቅም ..!
* * * **
መገፋፋቱ እዳ
ቆሜም አልሆነልኝ [ሁኜ] ለራስ ሰው እንግዳ
እንግዲያ..
ቋሚ ከተጎዳ [ሟች ]ሞትን በምን የሚ ጎዳ..?
** * **
ተስፋ: መኖሬን ሲስተው
"አለሁ"ማለትን :ስሰስተው
ዘመን: ያፈራው እሸት አለፈኝ
በል...
አንተም "እቺን አመት አትተወኝ"
አትተውኝ
ቀናም: አይል: የጎበጠው
ዐይለመልም :የደረቀው
አትተወኝ
ሰው :ማሰሮ አካሉ
ጠጠር :ለማከሉ
አይጠፋውም :እና
አተወኝ :እንደ :አምና
እሸቱ ገላዬ : ተስፋህን: አባብላል
ቅራሪ: ከታቹ : ዘቅጦ :አስተውላል
" እቺን አመት አትተወኝ"
ስርህ ልፅና ከስሬ ንቀለኝ ..
ታዲያ እቺን ብቻ አደራ
"በነቀልከኝ ቅጽበት በመንግስትህ አስበኝ"
አልያ .................መኖር ያጓጓኛል
ደሞ ደሞ _ ተስፋ ይበልጠኛል...!
ኪሩቤል ዘርፉ 🥀
@getem
@getem
ጊዜ የሰቀለውን እንቅብ
ሞት ከብብት ሲስብ
ጉብዝናን
ውብ ዝናን ወራት ሲንቀው
ምን ብዬ ጌታን ላስበው ..?
ምን ብዬ ?
ዝም ብዬ..?
* * * * *** * *
ለየቀን ትካዜ :ለየቀኑ መሃት
እድሜ እየሰጡ አሟሟትን መሳት
አቋቋሜን መርሳት .
ከሆነ እጣዬ
በል እንጂ አንድዬ
ላግራሞት አዱለኝ
ንጋት ማምሻን አዝሎ ቀኔን አይከልለኝ
ያጎበጠኝ
የደገፈኝ -ሸክም
እሹሩሩ: አልችል ባለ አቅም
እንዲማ...
ከመንገድ አልዘልቅም ..!
* * * **
መገፋፋቱ እዳ
ቆሜም አልሆነልኝ [ሁኜ] ለራስ ሰው እንግዳ
እንግዲያ..
ቋሚ ከተጎዳ [ሟች ]ሞትን በምን የሚ ጎዳ..?
** * **
ተስፋ: መኖሬን ሲስተው
"አለሁ"ማለትን :ስሰስተው
ዘመን: ያፈራው እሸት አለፈኝ
በል...
አንተም "እቺን አመት አትተወኝ"
አትተውኝ
ቀናም: አይል: የጎበጠው
ዐይለመልም :የደረቀው
አትተወኝ
ሰው :ማሰሮ አካሉ
ጠጠር :ለማከሉ
አይጠፋውም :እና
አተወኝ :እንደ :አምና
እሸቱ ገላዬ : ተስፋህን: አባብላል
ቅራሪ: ከታቹ : ዘቅጦ :አስተውላል
" እቺን አመት አትተወኝ"
ስርህ ልፅና ከስሬ ንቀለኝ ..
ታዲያ እቺን ብቻ አደራ
"በነቀልከኝ ቅጽበት በመንግስትህ አስበኝ"
አልያ .................መኖር ያጓጓኛል
ደሞ ደሞ _ ተስፋ ይበልጠኛል...!
ኪሩቤል ዘርፉ 🥀
@getem
@getem
👍30❤15
#
ያንከራተተሽ ቀሚስ
ሳህራ ተገኝቷል
ቤት አለ ያልሽው ልጅ
ከአሹሃው ተኝቷል
ሚጫወቱት ልጆች
ጠፍተዋል አታውቂም
እግዜርን ነው እጂ
ዜጋሽን አትንቂም
ጫማ ተጠይቀሽ
እግር ተለምነሽ
መንገድ እንድትሰጭ
የሚያደርግሽ ጋኔል
ወይ አግብተሽ ኑሪ
ወይ አብረሽው ውጭ
ዱካሽ ዶፍ ሲያጠፋው
መገኘትሽ ሲደበዝዝ
ሽማግሌው ሲረጣጥብ
ያ ህፃን ሲገረዝዝ
ቀሚሱ ግማሽ ግማሽ
እሾህ ይሆን የቀደደው
ልጅሽ ሞኝ እንቅልፋሙን
ማንስ ይሆን የወለደው
ትንሽ ቃዳ መሬት
ሰጠሽኝ በበርሃ
በሬው አቃጠለው
ግሏል ያንቺ አሹሃ
ዝናብ ቢያጣ እንኳ
ዕንባ አያጣም ድሃ
[ ብለሽ አፅናናሽኝ
ችግኝ እጂ ሽሮ መች ሰጠሽኝ
አልኩሽ ]
ትንሿ ክር ተጠንጥና
ቀሚስ ነበር ለአርባ አመት
አንቺም ቅንጭር ወይ አታድጊ
ልክሽ አይሆን በአርብ ሰንበት
[ እባቡ ውሃ ጠምቶት ገበሬሽን ሲለምን
እስኪጠግብ ጠቶ ገበሬሽን ሲያመሰግን?
...............አየሁት..........ቆይ እንዴትግን ? ]
አምስት ጣቱን የሚታየው
በርሃው ላይ የተኛው ሰው
ዝም ብሎ ቆፍሮታል
ፍቅረኛሽን ለቀመሰው
ተጠማዞ እንደ እባብ
አይናገር አይታመን
ምላሱ ላይ መርዝ የለው
ገበሬው ግ..ን ?..እንዴት ይመን
ምሳር ይዞ ለሚኖር
ለካንቻ ላይ ለቁጥቋጦ
እባብ ቢያገኝ መምታት እጂ
አያዝንለት የዕንባ ድጦ
እባክሽን እናት አለም
ገበሬዋ እመት ባክሽ
አለ ያልሽው ልጅሽ የለም
ደርቆ አድሯል ከችግኝሽ
ያስፈለግሽኝ ቀሚስ ደሞ
ሳህራ ላይ ቢፈለግም
እኛ ጌጥ ጌጡን እጂ
ሟች ልጅ አንፈልግም
'
'
'
ግዕዝ ሙላት
@geez_mulat
@getem
@getem
@paappii
ያንከራተተሽ ቀሚስ
ሳህራ ተገኝቷል
ቤት አለ ያልሽው ልጅ
ከአሹሃው ተኝቷል
ሚጫወቱት ልጆች
ጠፍተዋል አታውቂም
እግዜርን ነው እጂ
ዜጋሽን አትንቂም
ጫማ ተጠይቀሽ
እግር ተለምነሽ
መንገድ እንድትሰጭ
የሚያደርግሽ ጋኔል
ወይ አግብተሽ ኑሪ
ወይ አብረሽው ውጭ
ዱካሽ ዶፍ ሲያጠፋው
መገኘትሽ ሲደበዝዝ
ሽማግሌው ሲረጣጥብ
ያ ህፃን ሲገረዝዝ
ቀሚሱ ግማሽ ግማሽ
እሾህ ይሆን የቀደደው
ልጅሽ ሞኝ እንቅልፋሙን
ማንስ ይሆን የወለደው
ትንሽ ቃዳ መሬት
ሰጠሽኝ በበርሃ
በሬው አቃጠለው
ግሏል ያንቺ አሹሃ
ዝናብ ቢያጣ እንኳ
ዕንባ አያጣም ድሃ
[ ብለሽ አፅናናሽኝ
ችግኝ እጂ ሽሮ መች ሰጠሽኝ
አልኩሽ ]
ትንሿ ክር ተጠንጥና
ቀሚስ ነበር ለአርባ አመት
አንቺም ቅንጭር ወይ አታድጊ
ልክሽ አይሆን በአርብ ሰንበት
[ እባቡ ውሃ ጠምቶት ገበሬሽን ሲለምን
እስኪጠግብ ጠቶ ገበሬሽን ሲያመሰግን?
...............አየሁት..........ቆይ እንዴትግን ? ]
አምስት ጣቱን የሚታየው
በርሃው ላይ የተኛው ሰው
ዝም ብሎ ቆፍሮታል
ፍቅረኛሽን ለቀመሰው
ተጠማዞ እንደ እባብ
አይናገር አይታመን
ምላሱ ላይ መርዝ የለው
ገበሬው ግ..ን ?..እንዴት ይመን
ምሳር ይዞ ለሚኖር
ለካንቻ ላይ ለቁጥቋጦ
እባብ ቢያገኝ መምታት እጂ
አያዝንለት የዕንባ ድጦ
እባክሽን እናት አለም
ገበሬዋ እመት ባክሽ
አለ ያልሽው ልጅሽ የለም
ደርቆ አድሯል ከችግኝሽ
ያስፈለግሽኝ ቀሚስ ደሞ
ሳህራ ላይ ቢፈለግም
እኛ ጌጥ ጌጡን እጂ
ሟች ልጅ አንፈልግም
'
'
'
ግዕዝ ሙላት
@geez_mulat
@getem
@getem
@paappii
👍18❤10🔥2
የፈጣሪ_ልሳን
እጆቼን ዘርግቼ........
ልጸልይ ልማልድ ከደጅኽ ተገኘኹ
አንጋጥጬ ሽቅብ በሐሳቤ ዋኘኹ
ተንበርክኬ ለምሕላ በግንባሬ ተደፍቼ
ቀና ማለት ተዘነጋኝ የቃል ጸሎት ረስቼ
ያ'ንደበትኸ ልሳን ከየት ተሠወረ?
ቃል ከምላሴ ላይ እንደምን ታወረ?
ዝም....
ዝም ዝም....... !
እንደው ዝም! ዝምታዬ ቀረ
ሰምተኸኛል አንተ
በዝምታ ልሳን ጸሎቴ ሰመረ።
ገጣሚ #ተስፋሁን_ከበደ
@getem
@getem
@paappii
እጆቼን ዘርግቼ........
ልጸልይ ልማልድ ከደጅኽ ተገኘኹ
አንጋጥጬ ሽቅብ በሐሳቤ ዋኘኹ
ተንበርክኬ ለምሕላ በግንባሬ ተደፍቼ
ቀና ማለት ተዘነጋኝ የቃል ጸሎት ረስቼ
ያ'ንደበትኸ ልሳን ከየት ተሠወረ?
ቃል ከምላሴ ላይ እንደምን ታወረ?
ዝም....
ዝም ዝም....... !
እንደው ዝም! ዝምታዬ ቀረ
ሰምተኸኛል አንተ
በዝምታ ልሳን ጸሎቴ ሰመረ።
ገጣሚ #ተስፋሁን_ከበደ
@getem
@getem
@paappii
❤63👍11🔥3🤩1
ከላኩት ላይመለስ ከአፍ የወጣ ቃል
መውደዴን ነግሬያት መጥላቷን ማን ያውቃል
ትጥላኝ..... እንጃ......
ትውደደኝ...... አላውቅም
ላፌ ለከት የለኝ...የማወጣውን ቃል አልጠነቀቅም
ምን ይሉታል አሁን "እወድሻለሁኝ" ብሎ መቀባጠር
ቆይቶ ለሚጠፋ ለዛን ጊዜ ስሜት ብቻ ለሚፈጠር
"እኔም" አለች ከዘገየ ስሜት ውጥን ያለቀ 'ለት
"እወድሻለሁኝ" ባልል ምን አለበት
የነበረን ስሜት ላልመልሰው ዳግም
"እኔም" ያልሽኝ ሰዓት ከምኔ ላገግም?
ይፀፅታል የችኩል ቃል
ያሰቃያል ያለፈ 'ለት
"እወድሻለሁኝ" ባልል ምን አለበት
ዮኒ
ኣታን @yonatoz
@getem
@getem
@getem
መውደዴን ነግሬያት መጥላቷን ማን ያውቃል
ትጥላኝ..... እንጃ......
ትውደደኝ...... አላውቅም
ላፌ ለከት የለኝ...የማወጣውን ቃል አልጠነቀቅም
ምን ይሉታል አሁን "እወድሻለሁኝ" ብሎ መቀባጠር
ቆይቶ ለሚጠፋ ለዛን ጊዜ ስሜት ብቻ ለሚፈጠር
"እኔም" አለች ከዘገየ ስሜት ውጥን ያለቀ 'ለት
"እወድሻለሁኝ" ባልል ምን አለበት
የነበረን ስሜት ላልመልሰው ዳግም
"እኔም" ያልሽኝ ሰዓት ከምኔ ላገግም?
ይፀፅታል የችኩል ቃል
ያሰቃያል ያለፈ 'ለት
"እወድሻለሁኝ" ባልል ምን አለበት
ዮኒ
ኣታን @yonatoz
@getem
@getem
@getem
👍57🔥11😱4❤3👎3😁3🎉2
-
አንደኛውን ባሏን
ቀይባህር ስትሰደው፤
አንደኛውን ደግሞ
ዝምባብዌ ስትሰደው፤
እኛ ልጆቿ ነን በመጣ በሄደው
ምንወናበደው!።
ኸረ ስንቱን ቻልነው፡
ኸረ ስንቱን ቻልነው፧
.
ያሁኑን አናውቅም
ያሁኑን አናውቅም
ቅዱስ ይሁን እርኩስ፤
እሳት የማያበርድ
እሳት የማይለኩስ።
ያሁኑን አናውቅም
መልአክ ይሁን ሰይጣን፥
አለም እያሳየ
ሰፈር እያሳጣን፤
ማማርን ከደም ጋር፡
ደስታሽን ከሀዘን እያጨማለቀው፤
እርሱን ብትፈቺ
ምን እንደሚመጣ
ፈጣሪ ነው ሚያውቀው።
አሁን ልመርቅሽ
.
አሜን በይ ... አሜን
አሜን በይ ... አሜን
እንባሽን በሳቅ ይተካው
ገላሽን እሳት አይንካው
ችግርሽ ይምከን በሩቁ
ባሎችሽ ይጨማለቁ።
ድንበር ላይ
እባብ ይጠምጠም
ያለፈሽ እግሩ ይቀልጠም
ቅሌትሽ ገሀድ አይውጣ
ጎዳናሽ አላፊ አይጣ
፨
ባሎችሽ ሜዳ ቢነሱኝ
እንደ ልጅ ምቦርቅበት፥
ከደጅሽ ገሸሽ አታርጊኝ
ስምሽን ልመርቅበት።
እምዬ የኔ አጎብዳጅ
እምዬ የኔ አሳቢ፡
ደህና ባል እስከምናገኝ
ሌላ ባል እንዳታገቢ!።
፨
ስምሽን በአለም ስለጥፍ
መልክሽን በእጄ ሳቀልም፥
ወደድኩሽ ባልኩበት ቤቴ
ባይተዋር መጤ ብመስልም፤
ዝምታሽ የእርታሽ ወሰን
ልጅ ልቤን እያስደነቀው፥
ከልቤ ስለምወድሽ
አይጠፋም የምጠይቀው...
ባልሽ ግን ፀባዩ እንዴት ነው
ቀን በቀን ይለዋወጣል፥
አስመራ ሄደ ስትዪው
መቀሌ ደርሶ ይመጣል?
እንዴት ነው ሰሞኑን ውሎው
ህመሙ ሳሉ በዛበት
ከእንቅርቱ ድኖ ሳይገግም
ማንቁርቱ ተጨመረበት?
ሳስበው አንቺም መሮሻል
የምስኪን የደሃ ሮሮ፤
ሰቆቃው ይቀንስ ይሆን
ባልሽን ብትፈቺ ኖሮ?
፨
ምከሰው ዳኛው ሆኖብኝ
እምባዬ የኔ ጠበቃ፤
ፍትህን ሽተው ለማግኘት
መበደል ብቻ ላይበቃ፤
ቁጭቴን እንዳልመሰክር
ሾተሏን እያቀመሱኝ፡
እንደ ልጅ መብቴን ሳልጠይቅ
ባሎችሽ ምላሴን ነሱኝ።
፡
ባሎችሽ ሜዳ ቢነሱኝ
ባሎችሽ ሰፈር ቢነሱኝ
እንደ ልጅ ምቦርቅበት
ከደጅሽ ገሽሽ አታርጊኝ
ስምሽን ልመርቅበት ...
አሜን በይ ..አሜን
አሜን በይ ..አሜን!
የጠላሽ እቃው ይንጠልጠል
የከዳሽ በሳት ይቃጠል
ሚሰብክሽ ጥይት አይጠጣ
ሞቶልሽ ቀባሪ አይጣ
ጀግኖችሽ ህያው ይሁኑ
ህልምሽም ይስመር በውኑ
ያልጠራሽ ይገፈፍ ልብሱ
ትል ይሁን አልጋው ትራሱ
ተስፋሽን በሩን የዘጋ
ባለበት ጎኑ ይወጋ
፨
ሰቆቃ ጩኸት ሲበዛ
መቸገር ቤትሽን ሲያምሰው፥
እምባሽንን ስላባባሰ
ባል ብለን የመረጥነው ሰው፤
እምዬ የኔ ገራገር
እምዬ የኔ አሳቢ፡
ደህና ባል እስኪላክልሽ
ሌላ ባል እንዳታገቢ!።
፨
ያልደላሽ የምስኪን ቁንጮ
ልጆችሽ በልተው የረሱሽ
ከትቢያ ወስደው ለመጣል
ከዙፋን ስበው ያነሱሽ
ቢረግጡሽ የማትከፊ
ቢገፉሽ ክንድሽ የማይዝል
ባል ብለሽ ያገባሽው ሰው
ስጋሽን እስኪዘለዝል
ዝም ያልሽው ሆደ ሰፊዋ
እምዬ የኔ አሳቢ
ደህና ባል እስከምናገኝ
ሌላ ባል እንዳታገቢ!።
፨
ባይከፋም እንዳምናው ባልሽ
ባይሰክር እፍኝ ባይጠጣም
በሰላም አፍሮ እንደገባ
በተአምር ሰላም አይወጣም
አንሻም ቃሉ ቢደልል
አንፈልግ ግርማው ቢበዛም፤
የርሱ አፍ ቅቤ ማቅለጡ
ለኛ ሆድ ቁራሽ አይገዛም።
እምዬ የኔ ገራገር
እምዬ የኔ አሳቢ
ደህና ባል እስከምናገኝ
ሌላ ባል እንዳታገቢ!።
by @mikiyas_feyisa
@getem
@getem
@getem
አንደኛውን ባሏን
ቀይባህር ስትሰደው፤
አንደኛውን ደግሞ
ዝምባብዌ ስትሰደው፤
እኛ ልጆቿ ነን በመጣ በሄደው
ምንወናበደው!።
ኸረ ስንቱን ቻልነው፡
ኸረ ስንቱን ቻልነው፧
.
ያሁኑን አናውቅም
ያሁኑን አናውቅም
ቅዱስ ይሁን እርኩስ፤
እሳት የማያበርድ
እሳት የማይለኩስ።
ያሁኑን አናውቅም
መልአክ ይሁን ሰይጣን፥
አለም እያሳየ
ሰፈር እያሳጣን፤
ማማርን ከደም ጋር፡
ደስታሽን ከሀዘን እያጨማለቀው፤
እርሱን ብትፈቺ
ምን እንደሚመጣ
ፈጣሪ ነው ሚያውቀው።
አሁን ልመርቅሽ
.
አሜን በይ ... አሜን
አሜን በይ ... አሜን
እንባሽን በሳቅ ይተካው
ገላሽን እሳት አይንካው
ችግርሽ ይምከን በሩቁ
ባሎችሽ ይጨማለቁ።
ድንበር ላይ
እባብ ይጠምጠም
ያለፈሽ እግሩ ይቀልጠም
ቅሌትሽ ገሀድ አይውጣ
ጎዳናሽ አላፊ አይጣ
፨
ባሎችሽ ሜዳ ቢነሱኝ
እንደ ልጅ ምቦርቅበት፥
ከደጅሽ ገሸሽ አታርጊኝ
ስምሽን ልመርቅበት።
እምዬ የኔ አጎብዳጅ
እምዬ የኔ አሳቢ፡
ደህና ባል እስከምናገኝ
ሌላ ባል እንዳታገቢ!።
፨
ስምሽን በአለም ስለጥፍ
መልክሽን በእጄ ሳቀልም፥
ወደድኩሽ ባልኩበት ቤቴ
ባይተዋር መጤ ብመስልም፤
ዝምታሽ የእርታሽ ወሰን
ልጅ ልቤን እያስደነቀው፥
ከልቤ ስለምወድሽ
አይጠፋም የምጠይቀው...
ባልሽ ግን ፀባዩ እንዴት ነው
ቀን በቀን ይለዋወጣል፥
አስመራ ሄደ ስትዪው
መቀሌ ደርሶ ይመጣል?
እንዴት ነው ሰሞኑን ውሎው
ህመሙ ሳሉ በዛበት
ከእንቅርቱ ድኖ ሳይገግም
ማንቁርቱ ተጨመረበት?
ሳስበው አንቺም መሮሻል
የምስኪን የደሃ ሮሮ፤
ሰቆቃው ይቀንስ ይሆን
ባልሽን ብትፈቺ ኖሮ?
፨
ምከሰው ዳኛው ሆኖብኝ
እምባዬ የኔ ጠበቃ፤
ፍትህን ሽተው ለማግኘት
መበደል ብቻ ላይበቃ፤
ቁጭቴን እንዳልመሰክር
ሾተሏን እያቀመሱኝ፡
እንደ ልጅ መብቴን ሳልጠይቅ
ባሎችሽ ምላሴን ነሱኝ።
፡
ባሎችሽ ሜዳ ቢነሱኝ
ባሎችሽ ሰፈር ቢነሱኝ
እንደ ልጅ ምቦርቅበት
ከደጅሽ ገሽሽ አታርጊኝ
ስምሽን ልመርቅበት ...
አሜን በይ ..አሜን
አሜን በይ ..አሜን!
የጠላሽ እቃው ይንጠልጠል
የከዳሽ በሳት ይቃጠል
ሚሰብክሽ ጥይት አይጠጣ
ሞቶልሽ ቀባሪ አይጣ
ጀግኖችሽ ህያው ይሁኑ
ህልምሽም ይስመር በውኑ
ያልጠራሽ ይገፈፍ ልብሱ
ትል ይሁን አልጋው ትራሱ
ተስፋሽን በሩን የዘጋ
ባለበት ጎኑ ይወጋ
፨
ሰቆቃ ጩኸት ሲበዛ
መቸገር ቤትሽን ሲያምሰው፥
እምባሽንን ስላባባሰ
ባል ብለን የመረጥነው ሰው፤
እምዬ የኔ ገራገር
እምዬ የኔ አሳቢ፡
ደህና ባል እስኪላክልሽ
ሌላ ባል እንዳታገቢ!።
፨
ያልደላሽ የምስኪን ቁንጮ
ልጆችሽ በልተው የረሱሽ
ከትቢያ ወስደው ለመጣል
ከዙፋን ስበው ያነሱሽ
ቢረግጡሽ የማትከፊ
ቢገፉሽ ክንድሽ የማይዝል
ባል ብለሽ ያገባሽው ሰው
ስጋሽን እስኪዘለዝል
ዝም ያልሽው ሆደ ሰፊዋ
እምዬ የኔ አሳቢ
ደህና ባል እስከምናገኝ
ሌላ ባል እንዳታገቢ!።
፨
ባይከፋም እንዳምናው ባልሽ
ባይሰክር እፍኝ ባይጠጣም
በሰላም አፍሮ እንደገባ
በተአምር ሰላም አይወጣም
አንሻም ቃሉ ቢደልል
አንፈልግ ግርማው ቢበዛም፤
የርሱ አፍ ቅቤ ማቅለጡ
ለኛ ሆድ ቁራሽ አይገዛም።
እምዬ የኔ ገራገር
እምዬ የኔ አሳቢ
ደህና ባል እስከምናገኝ
ሌላ ባል እንዳታገቢ!።
by @mikiyas_feyisa
@getem
@getem
@getem
❤66👍55😢10🔥3😱2
Discover more about this topic by visiting https://tttttt.me/dogshouse_bot/join?startapp=2H-hloxORHKMqDS8Gwvfbw today."
የምርቃና ግፉ
የሙዚቃ ሊቁ፣
ሙዚቃ ቀማሚው ዜማ እየቀመረ
ጠባቧ "ስቲዲዮ " ጫት ሞልቷት ነበረ።
ሳተናው ነጋዴ ትርፉን እያሰላ
ሊቅም ቁርሱን በላ።
ሹማምንቶቻችን ፣
ገንቢ አፍራሾቻችን ፣
ዕቅዱን ሲጽፉ ፣
በትዕዛዝ ያደገ አወደይ ቀጠፉ።
ጎረምሳው አፍቃሪሽ ጫት በዱቤ ቅሞ፣
ደብዳቤ ጻፈልሽ ከገረባ መሃል
ምርቅን ቃላት ለቅሞ።
እናስ!
መሪ ከተከታይ፣
ፍትህ ከተበዳይ፣
ጥበብ ከአድናቂው፣
መላሽ ከጠያቂው
የነቃ ከእውኑ
የተኛ ከሕመሙ
ውበት ከቀለሙ
እኮ በምን ስሌት? እንደምን ይስማማ?
ሰጪና ተቀባይ እኩል አልቃሙማ።
(በረከት በላይነህ)
@getem
@getem
የሙዚቃ ሊቁ፣
ሙዚቃ ቀማሚው ዜማ እየቀመረ
ጠባቧ "ስቲዲዮ " ጫት ሞልቷት ነበረ።
ሳተናው ነጋዴ ትርፉን እያሰላ
ሊቅም ቁርሱን በላ።
ሹማምንቶቻችን ፣
ገንቢ አፍራሾቻችን ፣
ዕቅዱን ሲጽፉ ፣
በትዕዛዝ ያደገ አወደይ ቀጠፉ።
ጎረምሳው አፍቃሪሽ ጫት በዱቤ ቅሞ፣
ደብዳቤ ጻፈልሽ ከገረባ መሃል
ምርቅን ቃላት ለቅሞ።
እናስ!
መሪ ከተከታይ፣
ፍትህ ከተበዳይ፣
ጥበብ ከአድናቂው፣
መላሽ ከጠያቂው
የነቃ ከእውኑ
የተኛ ከሕመሙ
ውበት ከቀለሙ
እኮ በምን ስሌት? እንደምን ይስማማ?
ሰጪና ተቀባይ እኩል አልቃሙማ።
(በረከት በላይነህ)
@getem
@getem
👍57❤15😁8🔥2
ስልጣን አርጋኝ ፡ ክህነት ኮት
ሀይል አርጋኝ ፡ የመለኮት
ህይወት አርጋኝ፡ የእስትንፋስ
ግዑዝ አርጋኝ ፡ እንደ ንፋስ
ጣዕም አርጋኝ ፡ ዘለላ ማር
ውበት አርጋኝ ፡ እጥፍ ማማር
ጋሻ አርጋኝ ፡ ብረት ግግር
ዝናብ አርጋኝ ፡ ለባዶ እግር
እርቅ አድርጋኝ ፡ ለጠበኞች
ቅናት አርጋኝ ፡ ለምቀኞች
ስጦታ አርጋኝ ፡ ቀይ አበባ
እቅፍ አርጋኝ ፡ እንደ አንቀልባ
ሽፍን አርጋኝ ፡ እንደ አይን
ጣፋጭ አርጋኝ ፡ እንደ ወይን
ስዕል አርጋኝ ፡ ስውር ቀለም
ቋሚ አርጋኝ ፡ የዘላለም
ጉርሻ አርጋኝ ፡ የደስታ እድር
ቀልዴን ለሰው.. ስታበድር
ሳቄን ለሰው .. ስታበድር፤
ግትር አርጋኝ ፡ የቆመ ፖል
ብርሃን አርጋኝ ፡ እንደ አምፖል
ገመድ አርጋኝ ፡ ዳገት መውጫ
ዘመን አርጋኝ ፡ መለወጫ
ሜካፕ አርጋኝ ፡ የውበት ኩል
ጓደኞቿን .. ስትኮለኩል
ዘመዶቿን ..ስትኮለኩል
መኖሪያ አርጋኝ ፡ አዲስ ተስፋ
ቅድሚያ አድርጋኝ ፡ የወረፋ
እረፍት አርጋኝ ፡ ሰላም ማደር
ምርጫ አርጋኝ ፡ ያለ ወደር
ዲምፕል አርጋኝ ፡ ስርጉድ ስጋ
ውስኪ አርጋኝ ፡ ያልተወጋ
ምክንያት አርጋኝ ፡ የሞቅታ
እስር ልቧን .. ስትፈታ
ሸሚዝ ቁልፏን.. ስትፈታ
የፈራችው ነገር ሆነ
ያሰበችው ተፈጠረም፥
ያልሆንኩላት አልነበረም።
ድብቅ አርጋኝ ~ መስታውቷ
ህመም አርጋኝ~ መድሃኒቷ
ሀሩር አርጋኝ ~ በረዶ ቁር
ብርሃን አርጋኝ~ ድፍን ጥቁር
ስትደበዝዝ ~ ስትቀልም
ስትበራ ~ ስትጨልም
ስትደሰት ~ ስታዝንብኝ
ስትሞትብኝ ~ ስትድንብኝ፤
ሁሉን መሆን፡
ለመደብኝ!።
© @mikiyas_feyisa
@getem
@getem
@paappii
ሀይል አርጋኝ ፡ የመለኮት
ህይወት አርጋኝ፡ የእስትንፋስ
ግዑዝ አርጋኝ ፡ እንደ ንፋስ
ጣዕም አርጋኝ ፡ ዘለላ ማር
ውበት አርጋኝ ፡ እጥፍ ማማር
ጋሻ አርጋኝ ፡ ብረት ግግር
ዝናብ አርጋኝ ፡ ለባዶ እግር
እርቅ አድርጋኝ ፡ ለጠበኞች
ቅናት አርጋኝ ፡ ለምቀኞች
ስጦታ አርጋኝ ፡ ቀይ አበባ
እቅፍ አርጋኝ ፡ እንደ አንቀልባ
ሽፍን አርጋኝ ፡ እንደ አይን
ጣፋጭ አርጋኝ ፡ እንደ ወይን
ስዕል አርጋኝ ፡ ስውር ቀለም
ቋሚ አርጋኝ ፡ የዘላለም
ጉርሻ አርጋኝ ፡ የደስታ እድር
ቀልዴን ለሰው.. ስታበድር
ሳቄን ለሰው .. ስታበድር፤
ግትር አርጋኝ ፡ የቆመ ፖል
ብርሃን አርጋኝ ፡ እንደ አምፖል
ገመድ አርጋኝ ፡ ዳገት መውጫ
ዘመን አርጋኝ ፡ መለወጫ
ሜካፕ አርጋኝ ፡ የውበት ኩል
ጓደኞቿን .. ስትኮለኩል
ዘመዶቿን ..ስትኮለኩል
መኖሪያ አርጋኝ ፡ አዲስ ተስፋ
ቅድሚያ አድርጋኝ ፡ የወረፋ
እረፍት አርጋኝ ፡ ሰላም ማደር
ምርጫ አርጋኝ ፡ ያለ ወደር
ዲምፕል አርጋኝ ፡ ስርጉድ ስጋ
ውስኪ አርጋኝ ፡ ያልተወጋ
ምክንያት አርጋኝ ፡ የሞቅታ
እስር ልቧን .. ስትፈታ
ሸሚዝ ቁልፏን.. ስትፈታ
የፈራችው ነገር ሆነ
ያሰበችው ተፈጠረም፥
ያልሆንኩላት አልነበረም።
ድብቅ አርጋኝ ~ መስታውቷ
ህመም አርጋኝ~ መድሃኒቷ
ሀሩር አርጋኝ ~ በረዶ ቁር
ብርሃን አርጋኝ~ ድፍን ጥቁር
ስትደበዝዝ ~ ስትቀልም
ስትበራ ~ ስትጨልም
ስትደሰት ~ ስታዝንብኝ
ስትሞትብኝ ~ ስትድንብኝ፤
ሁሉን መሆን፡
ለመደብኝ!።
© @mikiyas_feyisa
@getem
@getem
@paappii
❤46👍46🔥3
፩
የመኖር ጥበብ — ልታቀብሉኝ ....
“እስኪ በርጋታ — ስማው ” ስትሉኝ
(ተቀብያችሁ....)
ውል ያለው ነገር ይናገር መስሎኝ
(እንደምክራችሁ ) ጆሮ ሰጥቼው ፤
ግራ ገብቶኛል ልቤን ሰምቼው ።
፪
የመኖር ጥበብ — ልታቀብሉኝ .....
“በልብህ መንገድ — ተጓዝ” ስትሉኝ
ብዙ ስትነግሩኝ — እንድከተለው ፤
ተደናገርኩኝ — እግሬ ግር አለው ።
(ተጋባሁ ግራ በልቤ መላ....)
ተነስቶ አይራመድ መንገድ አያሰላ ፤
ወይ ፊት አይል ኋላ (አንድ ቦታ ቆሞ)
ደረት ስር ተጋድሞ....
(በደስታ በፌሽታ )
እስክስታ ይወርዳል ፤
(ወይ ባዘን በሙሾ)
በለቅሶ ያረግዳል ፤
(እንጂ ጓዙን ይዞ ...)
ልብ ወዴት ይሄዳል!?
ሁሉ ተራምዶ ሲያልፍ — ዓለም ሲግተለተል
“ቆሞ ቀር” ይሆናል— ልቡን የሚከተል ።
፫
እቀናለሁ በእሷ.....
ከስሜቷ በላይ ይበልጣል ሃሳቧ ፤
(ልቧን አትሰማውም)
እሷ ስትናገር ይሰማታል ልቧ ።
አልተሾመባትም — ተሹማበታለች ፤
አትከተለውም — ታስከትለዋለች ።
ጌታ ናት ለነፍሷ ፤
(ራስ ናት ለራሷ ....!)
አልሆንኩም እንደ እሷ ።
፬
የመኖር ጥበብ — ልታቀብሉኝ .....
“በልብህ መንገድ — ተጓዝ” ስትሉኝ
(ተቀብያችሁ)
“እሺ” ብያችሁ....
ካረፈበት ግርጌ ከቆመበት ኋላ
(እንደተገተርኩኝ ሆኜ የእሱ ጥላ ....)
ስናፍቅ ስጠብቅ ይሄድ እንደሁ ብዬ.....፤
(እሷ ተራመደች ልቧን አስከትላ)
እኔ ቆሜ ቀረሁ — ልቤን ተከትዬ ።
------
ሚያዚያ ፳፮— ፼፪፲፮ ዓ.ም
@Bekalushumye
@getem
@getem
@getem
የመኖር ጥበብ — ልታቀብሉኝ ....
“እስኪ በርጋታ — ስማው ” ስትሉኝ
(ተቀብያችሁ....)
ውል ያለው ነገር ይናገር መስሎኝ
(እንደምክራችሁ ) ጆሮ ሰጥቼው ፤
ግራ ገብቶኛል ልቤን ሰምቼው ።
፪
የመኖር ጥበብ — ልታቀብሉኝ .....
“በልብህ መንገድ — ተጓዝ” ስትሉኝ
ብዙ ስትነግሩኝ — እንድከተለው ፤
ተደናገርኩኝ — እግሬ ግር አለው ።
(ተጋባሁ ግራ በልቤ መላ....)
ተነስቶ አይራመድ መንገድ አያሰላ ፤
ወይ ፊት አይል ኋላ (አንድ ቦታ ቆሞ)
ደረት ስር ተጋድሞ....
(በደስታ በፌሽታ )
እስክስታ ይወርዳል ፤
(ወይ ባዘን በሙሾ)
በለቅሶ ያረግዳል ፤
(እንጂ ጓዙን ይዞ ...)
ልብ ወዴት ይሄዳል!?
ሁሉ ተራምዶ ሲያልፍ — ዓለም ሲግተለተል
“ቆሞ ቀር” ይሆናል— ልቡን የሚከተል ።
፫
እቀናለሁ በእሷ.....
ከስሜቷ በላይ ይበልጣል ሃሳቧ ፤
(ልቧን አትሰማውም)
እሷ ስትናገር ይሰማታል ልቧ ።
አልተሾመባትም — ተሹማበታለች ፤
አትከተለውም — ታስከትለዋለች ።
ጌታ ናት ለነፍሷ ፤
(ራስ ናት ለራሷ ....!)
አልሆንኩም እንደ እሷ ።
፬
የመኖር ጥበብ — ልታቀብሉኝ .....
“በልብህ መንገድ — ተጓዝ” ስትሉኝ
(ተቀብያችሁ)
“እሺ” ብያችሁ....
ካረፈበት ግርጌ ከቆመበት ኋላ
(እንደተገተርኩኝ ሆኜ የእሱ ጥላ ....)
ስናፍቅ ስጠብቅ ይሄድ እንደሁ ብዬ.....፤
(እሷ ተራመደች ልቧን አስከትላ)
እኔ ቆሜ ቀረሁ — ልቤን ተከትዬ ።
------
ሚያዚያ ፳፮— ፼፪፲፮ ዓ.ም
@Bekalushumye
@getem
@getem
@getem
❤28👍22
"ሳይፀልዩ ማደር"
የተራበ ነብር ከሩቅ ተመልክታ
ሚዳቋ ፀለየች....
"አውጣኝ አውጣኝ" አለች ለፈጠራት ጌታ
ነብሩም ተርቦ
ወደ አምላኩ ቀርቦ
ሚዳቆዋን አይቶ - አንጀቱ ከሆዱ እንደተጣበቀ
ፈቅዶ እንዲሰጠው - አምላኩን ጠየቀ
.
የሁላችን ሰሪ ፀሎታቸውንም - ሰማቸው ፈጣሪ
አምላክም በድምፁ - ሚዳቆዋን አላት
"እሩጠሽ አምልጪ - ከበረታው ጠላት"
.
ነብሩንም አለው - "እሩጥ ተከተላት
ምግብ አድርገህም ብላት"
ሚዳቆዋ ስትሮጥ
ከነብር ለማምለጥ
ነብሩም ሲከተላት
ሆዱን ሊሞላባት
.
ቋጥኙን ስትዘል እግሯ ተስፈንጥሮ
ሆዱን ብትረግጠው የተኛው ከርከሮ
ከእንቅልፉ ሲነቃ ልክ ሲደነብር
ጉሮሮውን ያዘው የፀለየው ነብር
.
አውጣኝ ያለው ወቶ - አብላኝ ያለው በላ
ሳይፀልይ ያደረው - ከርከሮ ተበላ።
.
.
.
ገጣሚ:-በረከት በላይነህ
@getem
@getem
@paappii
የተራበ ነብር ከሩቅ ተመልክታ
ሚዳቋ ፀለየች....
"አውጣኝ አውጣኝ" አለች ለፈጠራት ጌታ
ነብሩም ተርቦ
ወደ አምላኩ ቀርቦ
ሚዳቆዋን አይቶ - አንጀቱ ከሆዱ እንደተጣበቀ
ፈቅዶ እንዲሰጠው - አምላኩን ጠየቀ
.
የሁላችን ሰሪ ፀሎታቸውንም - ሰማቸው ፈጣሪ
አምላክም በድምፁ - ሚዳቆዋን አላት
"እሩጠሽ አምልጪ - ከበረታው ጠላት"
.
ነብሩንም አለው - "እሩጥ ተከተላት
ምግብ አድርገህም ብላት"
ሚዳቆዋ ስትሮጥ
ከነብር ለማምለጥ
ነብሩም ሲከተላት
ሆዱን ሊሞላባት
.
ቋጥኙን ስትዘል እግሯ ተስፈንጥሮ
ሆዱን ብትረግጠው የተኛው ከርከሮ
ከእንቅልፉ ሲነቃ ልክ ሲደነብር
ጉሮሮውን ያዘው የፀለየው ነብር
.
አውጣኝ ያለው ወቶ - አብላኝ ያለው በላ
ሳይፀልይ ያደረው - ከርከሮ ተበላ።
.
.
.
ገጣሚ:-በረከት በላይነህ
@getem
@getem
@paappii
❤98👍59👎3
የእኔን ማኅሌት በዚ ባገኛት....😂😂
[ማኅሌት ]
ንዑድ ክቡር ብዬ፣
እንደ ወንጌል ተቀብዬ፣
ሰግጄለት ያንቺን ምስል፣
(ያፀድቀኝ ይመስል... )
የስምሽን ማእተም አስሬ፣
እንደ አምላክ አክብሬ፣
ስሠግድልሽ ባለኝ አቅም፣
(እግርሽ መምታት ምን ባያውቅም...)
ምስጋና መስዋእቴ ላንቺ ስም አያልቅም።
[ሳልሞት…]
እንድትደርሺ በነፍሴ፣
(ሳልፈርድበት በራሴ... )
ወደሰማይ አንጋጥጬ፣
ውብ ቃላትን መራርጬ፣
አምጣት አምጣት እለዋለሁ፣
ወደ ሰማይ እጮሀለሁ፣
እንደያሬድ ዜማ ባልፈጥር፣
ከፀጋውም ባልቆነጥር፣
(በናፈቅሽኝ ቁጥር....)
(በተክሌ ዝማሜ.... )
ማኅሌቱን ቆሜ፣
ኪዳኑን አድርሼ፣
ቅዳሴ ቀድሼ፣
የማነጋበት ህልም፣
በቁም ቅዠት ሳልም፣
ማኅሌት ብቻ ነው የሚደጋገመው፣
ጅል አፌ 'ሚጥመው፣
እሱ ነው ማእተሜ
(የመናፈቅ ስሜ… )
ጠርቼ ማልጠግበው፣
ሁሌም እለት እለት
የሚወጋኝ ስለት
የማነበንበው፤
ፅድቅን የመሰለ
(ስምሽ ከውስጤ አለ… )
ሰር በሰረከ
ጠዋቱም በነጋ፣
እያደር ታካቅ ነው
ለኔ ያንቺ ዋጋ።
ከመግዘፍ ይገዝፋል
ከልቀት ይልቃል፣
ከመርዘም ይረዝማል
ከጥልቀት ይጠልቃል፣
ከስፋት ይሰፋል
ከርቀት ይርቃል።
የተሰጠሽ ፀጋ
እግዜር የተመነው፣
መጠን አይገልፀውም
ከልኬት በላይ ነው።
ዜማ ነሽ አራራይ
ግእዝና ዕዝል፣
ልቤ አንቺነትሽን ነው
በጀርባው የሚያዝል፣
እያንጎራጎረ
የእሹሩር ዜማ፣
በጣም በለሆሳስ
ላንቺም ሳይሰማ፣
ማ ማን ይስማኝ እያለ
ለሚጮኸው ጩኸት፣
ኅ ኅሊናው ሸፍቶ
ባይታመንለት፣
ሌ ሌት ሲያዜምሽ
ያድራል፣
ት ትምጣልኝ እያለ
ጮሆ ይዘምራል።
ርክራክ አርዝሞ
ዜማን እየቃኘ፣
ቃላት አፈራርቆ
ውስጥሽን ተመኘ።
ተራራ ወጥቼ
የምለፈልፈው፣
(በልቤ ምፅፈው)
ታላቁ መልክሽ ነው
ውስጤ የገዘፈው።
ልቤም ፈሪነቱን
ባንቺ ይደብቃል፣
የግጥሙ ቤት መድፊያ
በማኅሌት ያልቃል።
የመኖር ሰዋስው
የመናፈቅ ስሌት
የዜማዬ ቅኝት
ድንቅ ነሽ ማኅሌት።
✍ ይቴ (@gtmwustie)
አርብ 12/12/2016
@getem
@getem
@gitimtm
[ማኅሌት ]
ንዑድ ክቡር ብዬ፣
እንደ ወንጌል ተቀብዬ፣
ሰግጄለት ያንቺን ምስል፣
(ያፀድቀኝ ይመስል... )
የስምሽን ማእተም አስሬ፣
እንደ አምላክ አክብሬ፣
ስሠግድልሽ ባለኝ አቅም፣
(እግርሽ መምታት ምን ባያውቅም...)
ምስጋና መስዋእቴ ላንቺ ስም አያልቅም።
[ሳልሞት…]
እንድትደርሺ በነፍሴ፣
(ሳልፈርድበት በራሴ... )
ወደሰማይ አንጋጥጬ፣
ውብ ቃላትን መራርጬ፣
አምጣት አምጣት እለዋለሁ፣
ወደ ሰማይ እጮሀለሁ፣
እንደያሬድ ዜማ ባልፈጥር፣
ከፀጋውም ባልቆነጥር፣
(በናፈቅሽኝ ቁጥር....)
(በተክሌ ዝማሜ.... )
ማኅሌቱን ቆሜ፣
ኪዳኑን አድርሼ፣
ቅዳሴ ቀድሼ፣
የማነጋበት ህልም፣
በቁም ቅዠት ሳልም፣
ማኅሌት ብቻ ነው የሚደጋገመው፣
ጅል አፌ 'ሚጥመው፣
እሱ ነው ማእተሜ
(የመናፈቅ ስሜ… )
ጠርቼ ማልጠግበው፣
ሁሌም እለት እለት
የሚወጋኝ ስለት
የማነበንበው፤
ፅድቅን የመሰለ
(ስምሽ ከውስጤ አለ… )
ሰር በሰረከ
ጠዋቱም በነጋ፣
እያደር ታካቅ ነው
ለኔ ያንቺ ዋጋ።
ከመግዘፍ ይገዝፋል
ከልቀት ይልቃል፣
ከመርዘም ይረዝማል
ከጥልቀት ይጠልቃል፣
ከስፋት ይሰፋል
ከርቀት ይርቃል።
የተሰጠሽ ፀጋ
እግዜር የተመነው፣
መጠን አይገልፀውም
ከልኬት በላይ ነው።
ዜማ ነሽ አራራይ
ግእዝና ዕዝል፣
ልቤ አንቺነትሽን ነው
በጀርባው የሚያዝል፣
እያንጎራጎረ
የእሹሩር ዜማ፣
በጣም በለሆሳስ
ላንቺም ሳይሰማ፣
ማ ማን ይስማኝ እያለ
ለሚጮኸው ጩኸት፣
ኅ ኅሊናው ሸፍቶ
ባይታመንለት፣
ሌ ሌት ሲያዜምሽ
ያድራል፣
ት ትምጣልኝ እያለ
ጮሆ ይዘምራል።
ርክራክ አርዝሞ
ዜማን እየቃኘ፣
ቃላት አፈራርቆ
ውስጥሽን ተመኘ።
ተራራ ወጥቼ
የምለፈልፈው፣
(በልቤ ምፅፈው)
ታላቁ መልክሽ ነው
ውስጤ የገዘፈው።
ልቤም ፈሪነቱን
ባንቺ ይደብቃል፣
የግጥሙ ቤት መድፊያ
በማኅሌት ያልቃል።
የመኖር ሰዋስው
የመናፈቅ ስሌት
የዜማዬ ቅኝት
ድንቅ ነሽ ማኅሌት።
✍ ይቴ (@gtmwustie)
አርብ 12/12/2016
@getem
@getem
@gitimtm
👍34❤16🔥1🎉1
ስት---ሄጂ ንገሪኝ-፪
(ሳሙኤል አለሙ)
°
°
ኩኩሉ...
ሻርቡን ተከናንበሽ
ኩኩሉ...
ሂጃማውን ለብሰሽ
ኩኩሉ...
ዘንቢሉን ሸከፍሽው
ነግቷልን ስጠብቅ
ናፍቆቱን ወሰድሽው።
°
°
የት አለሽ ከጓሮው
የት አለሽ ከጓዳው
እያየሽ ማድጋው
እያየሽ ዝም አለ
ከዘንቢሉ ሆድ ላይ ዓይኑን እንዳልጣለ
ዓይኑን በጨው አጥቦ
እንዴት ይጨክናል
እራሱም ተርቦ
°
°
ይኸው አደራ ያልሻቸው
እናቱ የሞተበት
ገበያ የሄደበት
ይለያሉ ከቶ...ከቶውን ይለያሉ
አንዴ በቁጣ አንዴ ባለንጋ
መምጣትሽን ሲያቀሉ
እንባዬም ተደበቀ ፥ ያለ ዓመሉ
°
°
ኩኩሉ...
መሄዱ---እንደ ያኔው ግዜ መስሎኝ
ኩኩሉ...
መምጣቱ ---እንደ ልጅነቴ መስሎኝ
መስሎኝ...መስሎኝ...መስሎኝ ብቻ!
የ'ናቴን መሳይ
የ'ናቴን አቻ
ካሁን አሁን ስጠብቃት
አሁን ካሁን ጋራ ተደባለቀብኝ
እንዴት ልለየው ነው...
መምጣት ከመቅረት ጋ ፤ ሲመሳሰለብኝ
ነግቶልኝ እስካገኝሽ...
ካሁን አሁን ፤ እያሉ የሚሸነግሉትን
ድንገት እየሄዱ ፤ ወጥተው የሚቀሩትን
ለምዶብኛል'ና ፤ እጠብቃለው ያደኩበትን።
ሳሙኤል_አለሙ
@Samuelalemuu
@getem
@getem
(ሳሙኤል አለሙ)
°
°
ኩኩሉ...
ሻርቡን ተከናንበሽ
ኩኩሉ...
ሂጃማውን ለብሰሽ
ኩኩሉ...
ዘንቢሉን ሸከፍሽው
ነግቷልን ስጠብቅ
ናፍቆቱን ወሰድሽው።
°
°
የት አለሽ ከጓሮው
የት አለሽ ከጓዳው
እያየሽ ማድጋው
እያየሽ ዝም አለ
ከዘንቢሉ ሆድ ላይ ዓይኑን እንዳልጣለ
ዓይኑን በጨው አጥቦ
እንዴት ይጨክናል
እራሱም ተርቦ
°
°
ይኸው አደራ ያልሻቸው
እናቱ የሞተበት
ገበያ የሄደበት
ይለያሉ ከቶ...ከቶውን ይለያሉ
አንዴ በቁጣ አንዴ ባለንጋ
መምጣትሽን ሲያቀሉ
እንባዬም ተደበቀ ፥ ያለ ዓመሉ
°
°
ኩኩሉ...
መሄዱ---እንደ ያኔው ግዜ መስሎኝ
ኩኩሉ...
መምጣቱ ---እንደ ልጅነቴ መስሎኝ
መስሎኝ...መስሎኝ...መስሎኝ ብቻ!
የ'ናቴን መሳይ
የ'ናቴን አቻ
ካሁን አሁን ስጠብቃት
አሁን ካሁን ጋራ ተደባለቀብኝ
እንዴት ልለየው ነው...
መምጣት ከመቅረት ጋ ፤ ሲመሳሰለብኝ
ነግቶልኝ እስካገኝሽ...
ካሁን አሁን ፤ እያሉ የሚሸነግሉትን
ድንገት እየሄዱ ፤ ወጥተው የሚቀሩትን
ለምዶብኛል'ና ፤ እጠብቃለው ያደኩበትን።
ሳሙኤል_አለሙ
@Samuelalemuu
@getem
@getem
👍48❤8😱1
ሥዕል ለወዳጅ ዘመዶ ስጦታ ማበርከት የምትፈልጉ በ+251984740577 ይደውሉ።
ወይም @gebriel_19 ላይ ፎቶ በመላክ በ ተመጣጣኝ ዋጋ ማዘዝ ይችላሉ!
@seiloch
@seiloch
ወይም @gebriel_19 ላይ ፎቶ በመላክ በ ተመጣጣኝ ዋጋ ማዘዝ ይችላሉ!
@seiloch
@seiloch
❤10👍7
#እግዜሩ ነህ የምትገርመኝ
ምኞትን ያህል ነገር ፣ ተፈጥሮ ስትቸረኝ
በእጅህ አበጃጅተህ የኳልካትን እንስት ደጄ እያሳየኝ
አታመንዝር አልከኝ!
.
እግዜሩ ነህ የምትገርመኝ
ምድሪቷ ታጥራብን ፣ በእሾህ አሜኬላ
ወዙን ሲያዘንብ ነው ፣ አዳም የሚበላ።
እህስ እንዴት ይሁን?
ተመልከት መንገዱን…
በዚ’ም በዛ’ም ያለው ፣ አለበት ደንቃራ
በቃ ልስረቅ ልንጠቅ
ቀን መሽቶ ቢያልፍልኝ...
እንዲህ አልል ነገር ፣ እሳት ዲን አለብኝ።
.
እውነት!
እውነት!
እውነት!
እግዜሀር ነህ የምትገርመኝ
ድመት አርገህ ፈጥረህ “ወተት አትንጠቀኝ”
ነብር አርገህ ፈጥረህ “ፍየል አትስረቀኝ”
እያልከኝ ፣
እንደዚህ አትበለኝ...
ብዬም አልበሳጭ ፣ አላሸሙር ነገር
ፈጣሪህን አክብር ይላል የሕግህ በር ።
(ሚካኤል.አ)
@getem
@getem
@getem
ምኞትን ያህል ነገር ፣ ተፈጥሮ ስትቸረኝ
በእጅህ አበጃጅተህ የኳልካትን እንስት ደጄ እያሳየኝ
አታመንዝር አልከኝ!
.
እግዜሩ ነህ የምትገርመኝ
ምድሪቷ ታጥራብን ፣ በእሾህ አሜኬላ
ወዙን ሲያዘንብ ነው ፣ አዳም የሚበላ።
እህስ እንዴት ይሁን?
ተመልከት መንገዱን…
በዚ’ም በዛ’ም ያለው ፣ አለበት ደንቃራ
በቃ ልስረቅ ልንጠቅ
ቀን መሽቶ ቢያልፍልኝ...
እንዲህ አልል ነገር ፣ እሳት ዲን አለብኝ።
.
እውነት!
እውነት!
እውነት!
እግዜሀር ነህ የምትገርመኝ
ድመት አርገህ ፈጥረህ “ወተት አትንጠቀኝ”
ነብር አርገህ ፈጥረህ “ፍየል አትስረቀኝ”
እያልከኝ ፣
እንደዚህ አትበለኝ...
ብዬም አልበሳጭ ፣ አላሸሙር ነገር
ፈጣሪህን አክብር ይላል የሕግህ በር ።
(ሚካኤል.አ)
@getem
@getem
@getem
❤35👍25😁10😱3👎2
ማንም አይሰብረኝም
ከእንግዲህ ብረት ነኝ ፤
ማንም አይገፋኝም
ከእንግዲህ ዓለት ነኝ ፤
ማንም አያውቀኝም
ከእንግዲህ ባህር ነኝ ፤
አታታልለኝም
ከእንግዲህ ይቺ ዓለም ፣
በተስረቅራቂ ድምፅ
በዥንጉርጉር ቀለም ፤
ማንም የማያውቀው
ማንም ያልቀመሰው
ወፍራም ጨለማ ነው ስጠጣ የኖርኩት ፤
ብቻዬን ሁኜ ነው
ከሰው 'ርቄ ነው ፤ ስለሰው ያወቅኹት ።
ከእንግዲህ በኋላ
ምንም አይገርመኝም ፤
ደግ ቀን ቢመጣ
ህልም ስጋ ቢለብስ
ዕድሜ አበባ ቢኾን
ብዬ _ ም አልመኝም ።
ከእንግዲህ በኋላ
ምንም አያስቀኝ
አያስለቅሰኝም ፤
ጣዕም'ም አይጥመኝ
አምሮት አያምረኝም ።
ከእንግዲህ በኋላ
ምድር ጨርቋን ጥላ
'' ወይኔ ! '' ስትል ባያት
< ጉዳይሽ ! > ነው 'ምላት ።
የስሜቴን ቀፎ አቃጥዬዋለሁ
አዛኝ ...
የዋህ ልቤን
'ሩቅ ጥዬዋለሁ ፤
አደንድኘዋለኹ '' እኔን'' እንደ ብረት
እንኳንስ ሊሰበር
ንቅንቅ እንኳ አይልም ማንም ቢሄድበት ።
ረዣዥም ሌቶች
ትንንሽ ምኞቶች
ስብርባሪ ህልሞች
ጠፊ በሪ ፍቅሮች
የዕድሜ መሰንጠቆች
የዕድሜ ስብራቶች
ያጠጡኝን ሃሞት ምንግዜም አልረሳም
ሳስቶ ለሚመጣ ከእንግዲህ አልሳሳም
ጡንቻዬ ፈርጥሟል
ብቻ በኾንኩበት ፤
ትንሽ ፈገግታ እና ብዙ ዝምታ ነው
ጥሩ ኑሮ ማለት ።
ቴዎድሮስ ካሳ
@getem
@getem
ከእንግዲህ ብረት ነኝ ፤
ማንም አይገፋኝም
ከእንግዲህ ዓለት ነኝ ፤
ማንም አያውቀኝም
ከእንግዲህ ባህር ነኝ ፤
አታታልለኝም
ከእንግዲህ ይቺ ዓለም ፣
በተስረቅራቂ ድምፅ
በዥንጉርጉር ቀለም ፤
ማንም የማያውቀው
ማንም ያልቀመሰው
ወፍራም ጨለማ ነው ስጠጣ የኖርኩት ፤
ብቻዬን ሁኜ ነው
ከሰው 'ርቄ ነው ፤ ስለሰው ያወቅኹት ።
ከእንግዲህ በኋላ
ምንም አይገርመኝም ፤
ደግ ቀን ቢመጣ
ህልም ስጋ ቢለብስ
ዕድሜ አበባ ቢኾን
ብዬ _ ም አልመኝም ።
ከእንግዲህ በኋላ
ምንም አያስቀኝ
አያስለቅሰኝም ፤
ጣዕም'ም አይጥመኝ
አምሮት አያምረኝም ።
ከእንግዲህ በኋላ
ምድር ጨርቋን ጥላ
'' ወይኔ ! '' ስትል ባያት
< ጉዳይሽ ! > ነው 'ምላት ።
የስሜቴን ቀፎ አቃጥዬዋለሁ
አዛኝ ...
የዋህ ልቤን
'ሩቅ ጥዬዋለሁ ፤
አደንድኘዋለኹ '' እኔን'' እንደ ብረት
እንኳንስ ሊሰበር
ንቅንቅ እንኳ አይልም ማንም ቢሄድበት ።
ረዣዥም ሌቶች
ትንንሽ ምኞቶች
ስብርባሪ ህልሞች
ጠፊ በሪ ፍቅሮች
የዕድሜ መሰንጠቆች
የዕድሜ ስብራቶች
ያጠጡኝን ሃሞት ምንግዜም አልረሳም
ሳስቶ ለሚመጣ ከእንግዲህ አልሳሳም
ጡንቻዬ ፈርጥሟል
ብቻ በኾንኩበት ፤
ትንሽ ፈገግታ እና ብዙ ዝምታ ነው
ጥሩ ኑሮ ማለት ።
ቴዎድሮስ ካሳ
@getem
@getem
❤71👍48🔥7🎉1