ግጥም ብቻ 📘
67.4K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ያል-ሻረ ፍቅር
          °
              °
                 °  
                መውደዴ ጋ'ራ፤
                                      ማፍቀሬ ተራራ፤
ብውልም ካንቺ ጋ።
                        ባመሽም ካንቺ ጋ።
                                     ለመድረስ እራቀኝ
                      ኩይሳው ልብሽ ጋ።
                    °
                 °
             °
የካቻምናው ንፋስ
ወደ እፉዬ ገላሽ፤
                   ወደ አንቺዬ ጥላሽ፤
                                  ገፍቶት...ገፍቶት፤
              ገለባው ባልሽን
አመጣው ጎትቶት።
                   °
                       °
                          °
                        ብናኙ ዛሬም ድረስ
                       ጠረኑ አሁንም  ድረስ
አ  ስ   ነ  ጠ   ሰ  ሽ
                           ከልብሽ ተሰንቅሮ፤
                       እኔን ብልሽ፤
         አልምር አለሽ፤
እንደ ድሮ።

       #ሳሙኤል_አለሙ
@Samuelalemu5
ሀዋሳ , ሰኔ 30-2015 ዓ.ም


@getem
@getem
@getem
👍223🔥2👎1
የተረሳው እንባ
°
°
ዝናቡ ዶፍ ጥሎ ፥ አባርቶ እንዳበቃ፣
ደጅ-ደጁ ናፈቀሽ ፥ እንጃ ለቀጠሮ
እንጃ ለጥየቃ።
ተጣጠብሽ።
ተኳኳልሽ።
ተጫማሽ።
°
°
አየሽ አይደል! ደጁን
መረገጫም የለው፣
ቻው...ቻው...ተባብለን
እስከ----ምን'ለያየው፣
በጎርፍ ተ...ጥ...ለ...ቅ...ል...ቋ...ል።
-----የዘነጋሽውን ፥ እንባዬን አክሏል።
°
°
አየሽ አይደል! ደጁን
አልፎ ሂያጅ ሲዘሉት፤
ለቀናት...ለቀናት...
ከብቶቹ ሲረገጡት፤
ለቀናት...ለቀናት...
ጋሪዎች ሲያምሱት፤
ለቀናት...ለቀናት...
ወጣ ገባ ስትይ ፥ አቁሮ የቀረው፤
እንባዬ ነበረ ፥ ደጅሽ የነበረው።
°
°
#ሳሙኤል_አለሙ
@Samuelalemuu


@Getem
@Getem
@Getem
👍21😢116
አትፍረጂብኝ...!
°
መኖር አደባባይ ሆነና
እግረ-መንገዴን ፥ እግረ-መንገዷን
መላተም ሆነ
ከኔ ጋ ግዷን።
(ተረፈች'ና...)
°
ቤት ለንቦሳ ማለቷ ቀርቶ
ካይኔ ከጎጆው ፥ ገባች በድንገት
እንባዬን ስታይ ፥ ተደበላልቋል
ሲኦል ከገነት።
(አዘነች'ና...)
°
አጠለለችው የደስታ እንባዬን
ደሞ ዝቃጩን ፥ ቅራሪ ሐዘኔን
ሳትግትልኝ ፥ አሸውት ዓይኔን
ትንኝ ነሽ ብየ
ንክሻሽን ብየ
°
(አትፍረጂብኝ...)
°
የዝግባውን አጥር ፥ ምስጥ እንደበላው
"አለህ ግን..." አትበይኝ ፥ ቆሜ ስላለው
እኔ ለራሴ...
እንደ ጠጅ-ቤት ንብ ፥ ሐዘን ከቦኛል
በዌይራ ባጥነው
እንባ ያመልጠኛል።
°
(አትታዘቢኝ...)
°
በኩለ ቀን ጅብ እንደ ወለደ ዓይነት
ብርሃን ቀላቅሎ ዝናም የጣለ 'ለት
ብሶት አጭቆ ፥ ጥርሴን ካሳቅሽው
እንባ ያወርዳል ፥ ጉንጬን ባየሽው
°
(አትፍረጂብኝ...)
°
እንባ ከ ጤዛው
እስስት ከቦታው ፥ ታይቶ አይለይም
ወጣልኝ ቢባል ፥ አገኘው ቢባል
እድሌ ሆኖ ፥ ልቤ ሚደረሰው
እኔን የሚለኝ ፥ የአንድ ቀን ሰው።
°
(አትፍረጂብኝ...)
°
#ሳሙኤል_አለሙ
@Samuelalemuu

@Getem
@Getem
@Getem
👍4916🔥1
#እሺ!
°
ምግቡ ጨው አይብዛው
እሺ!
ቡናም አትጠጣ አትደጋግም
እሺ!
አትንቀሳቀስ እስክታገግም
እሺ!
°
°
እሺ በ'ሽታዎች ታጥሮ
ማን-ቀጥ-ቀጥ - ማላቡ - ማቃር
                                 - ማቃሰቱ
ስስቅ ሆዴን አመመኝ
ባሌለበት ምልክቱ።
°
°
አወጣ መላ-ምት
አወረደ ግምት
ለመኖር ስትል
ለራስህ ብትል
አትሳቅ ብሎኝ ፥ አስጠነቀቀኝ
እሺ እንዳልኩት ፥ ሳቄ ሲርቀኝ
እምቢ ምልበት ፥ አፌ ናፈቀኝ
    
    #ሳሙኤል_አለሙ
@Samuelalemuu

@getem
@getem
@getem
👍5115
ቂም ያዘ መሰል...
አፈሩ ከዳኝ 'ረፍት ባልሰጠው
ባገኘሁ ቁጥር ስለምረግጠው

#ሳሙኤል_አለሙ
@Samuelalemuu

@Getem
@Getem
29😢22👍9🔥1
የት ልንደርስ?
(ሳሙኤል አለሙ)

[እ--ወ--ድ--ሃ--ለ--ው
እ--ወ--ድ--ሻ--ለ--ው]
ባንዲት መኺና ፥ ሞልተው ሊሳፈሩ
መልዕክት መጣና
ተቀጣጠሩ።

እንደ ደረሱ...
ከአፍ መናኸሪያ ፥ ወደ ልብ ሊጓዙ
ለጉዞኣቸው መዳረሻ
ቆሎውን ኩኪሱን ገዙ።

ሊሞላ...ሊሞላ...ሊሞላ
ሊሞላ ሲል
አንተ ነ-ሃ
አንቺ ነ-ሻ
በመሃል ስንባባል
ለካስ ቃል ይደነግጣል።

ይኸው እያቸው...
የሞላውን ትተው ፥ በኔና ባንቺ ኩርፊያ
ይኸው እያቸው...
ወደ መጡበት ፥ ሊመለሱ በጥድፊያ
ይኸው እያቸው...
የጋራ ቃላችንን
ነጥለን ስናሳፍራቸው።

[እ]--[ወ]--[ድ]--ሻ--[ለ]--[ው]
--- --- --- --- --- --- ---
[እ]--[ወ]--[ድ]--ሃ--[ለ]---[ው]

#ሳሙኤል_አለሙ
@Samuelalemuu


@getem
@getem
👍3510🔥3