#ሰኞ
#መርገመ_በለስ እና #አንጾሖተ_ቤተ መቅደስ
‹‹ያቺ በለስ ጌታ ወደርሷ ከመምጣቱ በፊት ለምልማ ቅጠል አውጥታ ነበር››
#ቅ/ዮሐንስ_አፈወርቅ
#በማለዳ(ሲነጋ) ወደ ከተማ(ሀገር) መጣ ሲል:- ጌታችን አዳም ወደ ወደቀበት ስፍራ ወደዚያ ሀገር መጣ፤ያን ጊዜም ተራበ መራቡም እንጀራና ሕብስትን ሳይሆን ስለ ሰው ድኅነት ተራበ ራሱ በወንጌልም ሲናገር ‹‹የእኔስ መብል የላከኝን የአባቴን ፈቃድ አደርግ ዘንድ ነው እናንተም በላከኝ በአባቴ ታምኑ ዘንድ ነው ››ዮሐ4፤34 ፤ክርስቶስ ወደ ዓለም ሲመጣ እንደ ማለዳ ጸሐይ ነው (የቀትርም የአመሻሽም ያይደለ) የማለዳ ጸሐይ ጨለማውን ገፎ ነው የሚመጣው ክርስቶስም ጨለማ የተባለ ክፉ ከይሲ ዲያብሎስን በጽንሰቱ ድል እየነሳው ተገለጠ፤የማለዳ ጸሐይ እንደ ቀትር ፀሐይ አይፋጅም አይለበልብም ክርስቶስም ለዓለሙ ተመጥኖ የሕይወት ብርሃን ሆኖ ከመዓቱ ምሕረቱ የቀረበ ሆኖ የተገለጠ ነው፡፡ጌታችን በወንጌሉም “የዓለም ብርሃን እኔ ነኝ የሚከተሉኝ የሕይወት ብርሃንን ያገኛል እንጂ በጨለማ ውስጥ አይመላለስም “ዮሐ8፤12 ሲል በቃሉትምህርት በተአምራቱ በደሙ ፈሳሽነት በብዙ ወገን ድኅነተ-ብርሃኑን ሊሰጠን በመምጣቱ ነው፡፡ ፀሐይ ለሁለቱም እኩል ታበራለች ስለርሷ ብርሃንነት ራሷም ትመሰክራለች ሆኖም ግን ጸሐይን ማየት የተሳነው ሕልውናዋን አይረዳም እንዲሁ ክርስቶስም ጸሐይ ሆኖ ለእስራኤል ቢመጣ ፀሐይነቱን ተረድተው ለሞቁት ለሰውነታቸው ኃይልን ለልብ ዓይናቸው ማየትን የሰጠ ነው፡፡
#የበለስ_ፍሬ ፡- የተባሉ ጉባኤ አይሁድ (ቤተ አይሁድ) ናቸው፤ጌታችንም የሃይማኖት ፍሬ ፈልጎባቸው ቢመጣ ከመጽሐፍተ ኦሪት ከነቢያት በቀር አላገኘም ፤የተጻፈውን በተግባር ፍሬ አልተመለከተባቸውም፡፡ ያንጊዜም ረገማት ቤተ አይሁድም ክርስቶስን ባለማመናቸው በኋላም እንደ ወንበዴ በመስቀላቸው ርግማንን አትርፈዋል፡፡ነገር ግን አይሁዳውያን ቢረገሙም እነርሱን ያልመሰሉትን ቀትቷቸዋል ማለት አይደለም፡፡ምክንያቱም ከቤተ አይሁድ እስጢፋኖስን የመሰለ ሰማዕት ተገኝቷል፤እነ ቅዱስ ጳውሎስን የመሰለ ሐዋርያም ተገኝቷል ‹‹ በስምንተኛው ቀን የተገረዝሁ ከእስራኤል ትውልድ ከብንያም ወገን ከዕብራውያን ዕብራዊ ኝ ስለ ሕግ ብትጠይቁ ፈሪሳዊ ነበርሁ›› #ፊል3፤5
#የበለስ_ፍሬ :- ጌታችን የረገማት በለስ አዳምና ሔዋንን የጣለች ዕጸ በለስ ናት፤ጌታም ለዘላለም ፍሬ አይገኝብሽ ማለት በሰው ላይ አትሰልጥኚ ብሎ ፍዳ መርገምን እንዳጠፋት አስረዳን፡፡ በርግጥ ፍዳ መርገሙን የፈጸመው በጽንሰት ጀምሮ በስቅለት ነው፡፡ በለስ ፍሬ የተባለ በሰው ላይ ሰልጥኖ የነበረ ምልዓተ ኃጢአት ነው መጽሐፍት ኃጢአትን በለስ ይሏታል፤ምክንያቱም የበለስ ቅጠል ሰፊ ደስ የምታሰኝ ናት እንዲሁም የኃጢአት መንገድ ወደ ጥፋት የምትወስድ ሰፊ በር ናት፤የበለስ ፍሬ በመብላትና በማላመጥ ጊዜ ጣፋጭ ናት እንዲሁ ኃጢአት ሲሠርዋት ደስ ታሰኛለች ከሠርዋት በኋላ ግን መከራ ታመጣለች በሚሠርዋት ጊዜ ጣፋጭ ከሠርዋት በኋላ ግን መራራ ናት፡፡ አዳምና ሔዋንም ለጊዜው በለሷ ጣፋጭና ውብ ሆና ታየቻቸው በውሃላ ግን መራራ ሞት አመጣችባቸው፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞን ‹‹ከአመንዝራ ሴት ከንፈር ማር ይንጠባጠባልና አፍዋም ከቅ የለሰለሰ ነውና ፍጻሜዋ ግን እንደ እሬት የመረረ ነው ሁለት አፍ እንዳው ሰይም የተሳለ ነው እግሮችዋ ወደ ሞት ይወርዳሉ አረማመድዋም ወደ ሲዖል ነው›› #ምሳ5፤3-5 ማርን በቀመስናት ጊጊ ለአፍና ለጉሮሮ ጣፋጭ ናት ከዚያ በውሃላ ግን የሚጎዳ መራራ ሆኖ እናገኘዋለን፤አመንዝራም ሴት አንደበተ ለስላሳ ናት ከማር ከስኳር የሚጣፍጥ ነገርን ትናገርሃለች ወዲያውኑ መራራ ሞትም ከእርሷ ያገኝሃል ሲል ነው፡፡ አርዌ ምድር እባብም(ሰይጣን ተዋሕዷት) ሔዋንን ስትናገራት አንደበቷ የጣፈጠ ነበር፤በሽንገላዋ ግን መራራ ነበረች፡፡
#የበለስ ፍሬ:- የተባለ አዳም የበለስ ፍሬ ከበላ በውሃላ ፈርቶ የተሸሸገባት የበለስ ቅጠል ናት፡፡ ‹‹የሁለቱም ዓይኖች ተከፈቱ እነርሱም ዕራቁታቸውን እንደሆኑ አወቁ የበለስንም ቅጠሎች ሰፍተው ለእነርሱ ለራሳቸው ግልድ አደረጉ›› ዘፍ3፤7 አዳምና ሔዋን ፈርተው የተሸሸጉበት በለስ አስቀድሞ ዕጸ በለስን የቀጠፉባስ ዛፍ ቅጠል ነው፡፡
ነገር ግን በዚህ ቅጠል ይሸፈን ዘንድ የቁርበት ልብስ አለበሳቸው ፡፡ ጌታችን ያደረቃት በለስ ይህቺ አዳምና ሔዋን ተሸሽገውባት የነበረችውን ምክንያተ ፍዳ ወመርገም የሆነችውን ነው፡፡ ሊቁ አፈወርቅ ዕደ ወርቅ ዮሐንስ ‹‹አዳም በገነት ዕርቃኑን ሆኖ ሳለ በየትኛው ቅጠል ነበር መሸፈኛ ሰፍቶ ዕርቃኑን የሸፈነ ይህች ቅጠል እንዴት እንደደረቀች አየህን አዳም የለበሳት ዕርቃኑን የሸፈነባት አይደለችምን ጌታ ኢየሱስ ወደ ለመለመችው ዛፍ መጥቶ አዳም ዕርቃን የሸፈነባትን ቅጠል በቃ አደረቃት አዳምን ድኃ ሁኖ ስለዘገኘው ንጹሕ የሆነ የብርሃንንም
ልብስ ሰጠው ይኸውም ብርሃን ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ የተሰራ ነው ፤የበለስን ቅጠል አድርቆ የነፍስን ድኅነት ሰጠው ተድላ ደስታ ባለባት ገነት ፍጹም የሆነ የተድላ ደስታ ልብስ ተጎናጽፎ እንደ መላእክት ሕያው ሁኖ ሲኖር ከይሲ ያሳተችው አዳምን እንዴት እንደዳነ አስባለሁ›› #ግብረ_ሕማማት ገጽ 163/164 ቁ.ጀ50-54
#ፍሬ_ግን_አላገኘባትም
________________
ወንጌሉ እንዳስቀመጠው ጊዜው የፍሬ ወር አልነበረም;ለምስጢሩ ግን ወዲያውኑም ደረቀች ሲል ደግሞ ለዘመናት የሰለጠነ ፍዳ መርገም ሞት ዲያብሎስ ጠፋ ተሸረ ሲል ነው፡፡ #ኛ_ቆሮ 15÷55 ‹‹ሞት ሆይ መውጊያህ የት አለ፤ሲዖል ሆይ ድል መንሳትህ የት አለ››የሚለው ተፈጸመ፤ምክንያቱም አስቀድሞ በትንቢት ተነግሮ ነበርና ‹‹ከሲዖል እጅ እታደጋቸዋለሁ ከሞትም እቤዣቸዋለሁ ሞት ሆይ ቸነፈርህ ወዴት አለ ሲዖል ሆይ ማጥፋትህ ወዴት አለ ርኅራኄ ከዓይኔ ተሰወረች›› #ት.ሆሴዕ 13፤14 ክርስቶስ በሰው ላይ የሰለጠኑ ክፉ በለሶችን አድርቆ አጥፍቶልናል ይህንንም ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅ ‹‹መጥቶም ፍትወታት እያትን ኃጣውዕ ርኩሳንን አጠፋ ሁከቱን ጸጥ አደረገ ዕጸ በለስንም አድርቆ
ብሩህ በሆነ ሕይወት በሃይማኖት የበቀለውን ዕጸ መስቀል ተከለልን ›› #ግብረ_ሕማማት ገጽ 167 ቁ.104 በበለስ የመጣውንም ርግማን በዕጸ መስቀሉ ድል ነሳው ፤በለሷን ሲረግም በአንጻሩ በለስ ዕጸ መስቀልን ተከለልን፡፡
#ይህ_የከበረ የተዘረጋ መስቀል ሥሩ በምድር ጫፉ በሰማይ ያለ ቅጠሉ የማይረግፍ አበባው ለጥፋት ፍሬው ለሞት ያልሆነ ነው፡፡ባለ በገናው ነቢዩ ዳዊትም ‹‹ወይከውን ከመዕጽ እንተ ትክልት ኅበ ሙሐዘ ማይ እንተ ትሁብ ፍሬሃ በበጊዜሃ ወቁጽላኒ ኢይትነገፍ -በውኃ ዳር የተተከለ በየጊዜው ፍሬውን የሚሰጥ ቅጠሉም የማይረግፍ ›› #መዝ1÷3 ክርስቶስ በዕጸ መስቀሉ ክፉ በለስ የተባሉ ዲያብሎስና ሠራዊቱን የቀጣበት ፤ዛሬም ለሚያምኑበት ወደ ሰማይ የሚያወጣ መሰላል ነው፡፡ይቺ ዕለትም መርገመ በለስ ተብላለች
#ከዚህ ቀጥሎ ወደ ቤተ መቅደስ ሔደ፤ ቤተ መቅደስ ቤተ ጸሎት፣ ቤተ መሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተ ምሥያጥ /የንግድ ቤት/ ሆኖ ቢያገኘው፤ «ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች… እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት» ማቴ. 21፤13 ብሎ የሚሸጡበትን ሁሉ ገለበጠባቸዉ፣ ገርፎም አስወጣቸዉ፣ ይህም የሚያሳየዉ ማደሪያው ቤቱ የነበርን እኛ የአዳም ልጆች ኃጢአት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢአታ ችንን ሁሉ እንዳራቀልን
............ #ይቆየን ..........
ግብሐት :- ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሰ/ት ቤት ሰሌዳ መጽሔት

ዐውደ ምሕረት
Photo
ከወደቁ አይቀር .....#ለጽዮን
____________________
አንዳንድ ውድቀቶች ካለ አስፍላጊ አቋቋሞች በእጅጉ የተሻሉ ናቸው ። ለምሳሌ ከሐውልቱ እንደምናየው ለጽዮን መውደቅ በእውነቱ ዋጋ ያለውና የተሻለ አወዳደቅ ነው::
#ይህ በመጠኑና በውበቱ ከፍ ያለው ሃውልት አሁን ሳይወድቅ ቆሞ ካለውና በቅርቡ ከሮም ከመጣው ዕድሜ ይሁን በሰው ሀገር ያለ ቦታው መቆሙ የሞራል መላሸቅ ያስከተለበት የሚመስለሁ እንደ አዛውንት ጎብጦ በመደገፊያ በግድ ከቆመው ሐውልት በተለየ መልኩ በፊት ለፊቱ ወድቆ ይታያል::
ይህ የአክሱም ሐውልት ከመሐመድ ግራኝ ወራራ በኋላ የተነሳችው ሴቷ ግራኝ ዮዲት ጉዲት ካስከተለችው ጥፋቶች መካከል የጥፉቷን ግንባር ቀደም ገፈት ቀማሽ የሆነ ታሪካዊ የሀገር ቅርስ ነው :: ዮዲት በክርስቲያንኖችና በቤተክርስቲያን ላይ ባደረባት የተሳሳት ጥላቻ ኃያሌ የጭካኔ ተግባራትን በክርስቲያኖችና በቤተክርስቲያን ላይ ያስከተለች የታሪክ ጠባሳ ነች ::
#ከበዙ ጥፉቶች በኃላ ወደ እዚህ ወደ አክሱም ሐውልት መቆሚያ አካባቢ ስትደርስም ጭፍሮቿ እንደለመዱት የእክሱምን ሐውልቶች ይጥሏቸውና ይሰባብሯቸው ዘንድ ተራኮቱ ዮዲትም ሁሉንም ሐውልቶች አትጣሏቸው አንዱንና ትልቁን ለዐይንም የሚማርከውን ሐውልት ብቻ ጣሉት ሌሎቹን ግን እንዳትነኩ ስትል ትዕዛዝ አስተላለፈች ጭፍሮቿም ለምን? ሲሉ ጠየቁ
በሌሎች ቦታዎች እዳደረግን ሁሉንም ብንሰባብርና ብናወድማቸው መጪው ትውልድ ሲያቸው አንድ ጊዜ ተበሳጭቶ ብስጭቱን ይተወዋል የሚያምረውን ና ተለቅ የሚለውን ሃውልት ብቻ ብንጥለውና ሌላው ብንተውለት ግን ባየውና በሰማው ቁጥር ይህ ትልቁኮ ባይወድቅ ከነዚኞቹ በላይ ውብ የሀገር ቅርስ ሆኖ ይታይ ነበር እያለ ዘላለም ዓለሙን እየተቃጠለ ሲብሰለሰል ይኖራል ገባችሁ ስትልም አምቧረቀችባቸው::
#ሐውልቱ ግን ለትውልዱ ቁጭት ሳይሆን ትምህር ይሆን ዘንድ ወደ ጽዮን ወደቀ ተንበርከኮም ሰገደላት ። የጌታዬ እናት በፊትሽ እቆም ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል? እያለም ተሳለማት ሉቃ1÷43። ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ ልብ ያለውም ልብ ያድርግ "በፈሊጥ ካልገባው በፍልጥ " እንዲሉ ። ሰው ሁለት ጊዜ ይማራል ይላሉ ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድህን አንድ በሣር " ሀ " ብሎ ካልሆነም በአሳር " ዋ "ብሎ ። ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ብራና ዳምጠው ቀለም በጥብጠው በሣር ስግደት እንደሚገባት ሲያስተምሩን ካልገባን በአሳር ጎንበስ ማለታችን አይቀርምና ከአሳሩ በፊት በሳሩ ተማሩ እንላለን።
“ #የአስጨናቂዎችሽም_ልጆች_አንገታቸውን_ደፍተው_ወደ_አንቺ_ይመጣሉ ፥ የናቁሽም ሁሉ #ወደ_እግርሽ_ጫማ ይሰግዳሉ፤ #የእግዚአብሔርም ከተማ፥ የእስራኤል #ቅዱስ_የሆንሽ_ጽዮን ይሉሻል።”
#ኢሳ 60፥14
አ.አ ኢትዮጵያ
ተርቢኖስ ዘተክለ ኤል
ኅዳር 21/2013ዓ.ም የተከተበ

#ይህ_ጎልያድን የገደለ #ሐዲስ_ዳዊት ነው!
________________________________
#ገድለ_ጊዮርጊስ
#በተኵላና_በእባብ ላይ ትጫማለህ፤ #አንበሳውንና_ዘንዶውን ትረግጣለህ። #በእኔ_ተማምኖአልና አስጥለዋለሁ፤ ስሜንም አውቆአልና እጋርደዋለሁ። #ይጠራኛል እመልስለትማለሁ፥ በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋራ እሆናለሁ፤አድነዋለሁ አከብረውማለሁ። " #መዝ 90(91)÷13-15
ይህ #የእግዚአብሔር_ቃል ነው ፤ እንግዲህ #እግዚአብሔር_ያከበረውን ማን ያቃልለዋል? #ማንም!

#የእግዜር እጅ /The hand of God/
እግር ኳስ ከዓለማችን ስፖርቶች ሁሉ እጅግ ተወዳጅ የሆነ ስፖርት ነው። የስፖርት ዓይነቶች ብዙና አያሌ ቢሆኑም እንደ እግር ኳስ ስፖርት ግን የገነነ የለም ።
#የስፖርት ዜና እንይ ስንል እንኳ የእግር ኳስ ዘገባዎችን እንከታተል ማለታችን እንደሆነ ተደርጎ ብቻ ይታሰባል ። ይህም እግር ኳስ ሌሎች ስፖርቶች እንዳልተፈጠሩ አድርጎ በማስረሳት በብዝዎቻችን ልቡናና አእምሮ ላይ እንደነገሰ ያመላክታል።
እግር ኳስ ተወዳጅ ከመሆኑ አልፎ ተወዳጂና ታዋቂ ያደረጋቸው ሰዎችም አያሌ ናቸው። ከነዚህ ሰዎች መካከል አርጄንቲናዊው ማራዶና አንዱ ነው።
#እንደ_ግሪጎሪያን የዘመን ቀመር ጥቅምት 30 ቀን 1960 ዓ.ም ከዛሬ 60ዓመት በፊት ላኑስ ፣ ቦነስ አይረስ ፣ አርጀንቲና ከተማ ውስጥ የተወለደው ማራዶና ወይም በሙሉ ስሙ (Diego Armando Maradona) /ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና/ ዓለም የምታውቀው በእግር ኳስ ነው።
ይልቁኑ የእግዚአብሔር እጅ /Hand of God/ በመባል በምትታወቀው ግቡ በስፖርቱ ወዳጆች ልብ ውስጥ አይረሴ አድርጋ አትማዋለች ።
#ዲያጎ አርማዶ ማራዶና በ1986 በሜክሲኮ የተካሄደውን ውድድርን በበላይነት መቆጣጠር ችሎ ነበር፡፡ እንግሊዝን በተሸነፈበት የ1-1 የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ በዓለም ዋንጫው ውስጥ በጣም የማይረሱ ሁለት ግቦችን አስቆጠረ።
ከነዚህም አንዷ በጭንቅላቱ መግጨት እንደማይሆንለት ሲረዳ እስከሚችለው ከዘለለ በኋላ በቴክኒክ እጁን በመጠቀም ኳሷን ወደ ግብነት ቀየራት ዳኛው በጭንቅላቱን ገጭቶ እንዳገባው አስበው አጸደቁለት። በኃላ ግን በጭንቅላት ሳይሆን በእጅ እንደተቆጠረች የዓለም ሕዝብ ዐወቀ ግቧም “የእግዚአብሔር እጅ ግብ” በመባል የምትታወስ ግብ ሆነችለች፡፡ ዛሬ ድረስ ማራዶና ሲነሳ ይህች ግብ አብራው ትነሳለች።
#በሁላችንም የሕይወት እግር ኳስ ውስጥ አናስተውላትም እንጂ የእግዚአብሔር እጅ አለች ከጅምሩ አጥንት ሰክቶ ጅማት ወጥሮ ደም አሰራጭቶ ያበጃጀን ይህው የእግዚአብሔር እጅ ነው በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ የእግዚአብሔር እጅ የሌለችበት ጊዜና ቦታ የለም "ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ ነህ፤ ወደ ሲኦልም ብወርድ፥ በዚያ አለህ። እንደ ንስር የንጋትን ክንፍ ብወስድ፥ እስከ ባሕር መጨረሻም ብበርር፥ በዚያ #እጅህ_ትመራኛለች_ቀኝህም_ትይዘኛለች " እንዲል ነቢዩ መዝ138(139)÷8-10
እነ_ቫር እና ጎል ላይን ቴክኖሎጂ ሳይመጡ በፊት እግር ኳስ ከነ ወዙ መቆየት ችሎ ነበር አሁን አሁን ግን ጨዋታ ሁሉ ቆሞ በቴክኖሎጂ እገዛ ፍርድ የሚቀለበስበት ሁኔታ ተፈጥሯል ይህም የተወዳጁን የእግር ኳስ እስፖርት አዝናኝ ኩነቶች በእጅጉ አደብዝዘውታል ።
#በእግር ኳስ ጨዋታ ውስጥ ከበረኛና የእጅ ከሚወረውር ተጫዋች በቀር ኳስን ሆን ብሎ በእጅ መንካት አይፈቀድም ወይም እጅን ወደ ኳስ ማምጣትና መንኳት ክልክል ነው። ካልሆነ ግን "ማኖ" ብሎም የቅጣት ምቶችን ያስከትላል ከፍ ሲልም በቢጫና በቀይ ካርዶች ከጨዋታው ሊያስወጣ ይችላል። ታዲያ ይህች የማራዶና ግብ እንዴት ከግብ ተቆጠረች? ብለክ ታስብ ይሆናል መልሱ ቀላል ነው "የእግዚአብሔር እጅ" ስለሆነች ነው። የእግዚአብሔር እጅ ማኖ የላትም
ምድራዊ ሕግ በእጅህ እዳትነካ ቢያስጠነቅቅህም የእግዚአብሔር እጅ ካንተ ጋር ካለች እግር ኳሱን ቅርጫት ኳስ ብታደርገው እንኳ ዓላማህ ግብን ይመታል ። ባርም ጎል ላይን ቴክኖሎጂም አይቃወሙህም።
#ይህ_ሲባል ግን ወዳጄ የእግዚአብሔር እጅ አጭበርባሪውንና አታላዮን ትወዳለች ከእርሱ ጋርም ታብራለች ማለት አይደለም። የቤቱ ሁለተኛ ልጅ ብትሆንና ብኩርናን አጥብቀህ ብትሻት መሻትህን አውቆ እንደ ያዕቆብ ፊተኛ ያለው ቀዳማዊ ፣ተከታይ የሆነ መሪ ፣ታላቅ ያለው በኩር ያደርግሃል ማለቴ ነው። እንደ ዔሳው ካቃለልካት፣ በኩርናህን ካልጠበካት ፣ በምስር ወጥም ከሸጥካት ግን የመጀመሪያው መጨረሻ አንተ ትሆናለህ በእግር ብታገባው እንኳን ግብ የተሻረ ይሆናል ፊተኞች ዋለኞች ዋለኞችም ፊተኞች ይሆናሉ የሚለው ቃል የሚከወነው በሰው መሻትና በእግዚአብሔር እጅ እንደሆነ ዕወቅ። #ዘፍ25÷34
#የእግዚአብሔር እጅ ተንጠራርተው ከግባቸው ላልደረሱ ብቻ ትቀጠላለች እንጂ ባሉበት ቆመው ያለ ጥረት ተአምር ለሚጠብቁት አትቀጠልም ሞክረህ ባቃተ ጊዜ ብቻ እርዳታ ጠይቅ አቤቱ ከአርያም ክድህን ስደድልኝ በለው።
በባለጋራዬ በሥጋ ፍቃድ፣በሰይጣን ፈተና ፣ በዓለም መውጊ ተውግቼ መሸነፍ አልፈልግም አድነኝ ብለ ጥራው እነሆ፥ የእግዚአብሔር እጅ ፈጥና ታድንለች በጠላቶችህ ላይም ድልን ታቀዳጅሃለች። “ #እነሆ_የእግዚአብሔር_እጅ ከማዳን አላጠረችም ፤ ጆሮውም ከመስማት አልደነቈረችም "
#ኢሳ 59፥1
#እኔም_እንደ_ፔሌ አንድ ቀን በሰማይ ኳስ እንገፋለን ባልለውም ይህን የዓለማችን የእግር ኳስ ፈርጥ ግን ነብስህን ይማራት ሳልል ማለፍ አልፈልግም 🙏!
#Thank_you Armando
ኃ/ማርያም
አ.አ ኢትዮጵያ
ጥር 3/2013 ዓ.ም

Forwarded from የዘማሪ ዳዊት ክብሩ Zemari Dawit Kibru Official Telegram Channel
#ይህ_ጥምቀት_ለኔ_አይደለም !
(አንብባችሁ ስትጨርሱ ሼር በማድረግ ተባበሩን !)
አክሱም ዩኒቨርስቲ ካስተዋወቁኝ መልካም ሰዎች መካከል በስመ ክርስትናዋ ወለተ ጻድቅ አንዷ ናት ! እንደ አጋጣሚ ሆኖ በተደራራቢ ምክንያት ትምህርቷን መቀጠል ባትችልም ግቢ እያለን ግን ፍጹም መንፈሳዊ ትጋትን ከ መንፈሳዊ ኑሮ ጋር አስተባብራ ትኖር ነበር።
"ዩኒቨርስቲ ላወቀበት ገዳም ፤ ላላወቀበት ሲዖል ነው!" የዘወትር መርህ እና መሪ ቃልዋ ነበር ።
ታድያ ከረጅም ጊዜ በኋላ በፌስ ቡክ ውስጥ መስመር (#Inbox) ላይ እርሷነቷን የሚገልጥ መልዕክት አስቀምጣልኝ በጣም ደስ እንዳላት እና ከቻልኩ ስልኬን እንዳስቀምጥላት እርሷም ስትችል እንደምትደውልልኝ ገልጻ ስለነበር ስልኬን አስቀመጥኩላት። ወትሮም ወዳጅ ደስ ብሎት አይደል ተችግሬም ቢሆን መፈላለግ ይገባልና።
በዛው ሰሞን አንድ የውጭ ስልክ ጥሪ በስልኬ ላይ ጠራ። እርሷ ልትሆን እንደምትችል ገምቼ ስለነበር ከአንድ ጥሪ በኃላ ስልኩን አነሳሁት ። ግምቴ ትክክል ነበር ። ወለተ ጻድቅ ነበረች ። ጊዜ ካለወጠው ትዕትናዋ እና የንግግር ቃናዋ ጋር ብዙ ሰላምታ ከተለዋወጥን በኃላ ደስ ስላሰኛት ታሪክ አጫወተችኝ ።
ታሪኩ እንዲህ ነው !
ትምህርት ካቋረጠች በኃላ ብዙ የህይወት ውጣ ወረድ ስለተደራረበባት እና የቤተሰቧን ህይወት ለማሻሻል ወደ አረብ ሀገር ለስደት በቤት ሰራተኛነት እንደሄደች ነገረችኝ። እዚያ በማይመች ቦታ ላይ ቢሆንም እንኳ ከእንቅልፍ ሰዓትዋ ቀንሳ የእመቤታችንን ውዳሴዋን ከመጸለይ አቋርጣ አታውቅም ።
ታድያ እዚህው አ.አ እያለች የጀመራት የእግር ጥዝጣዜ በስራ ቦታዋ መልኩን እየቀየረ ወደ እብጠት ማደግ ጀመረ ። ተደጋጋሚ ጊዜ ወደ ህክምና ብትሄድም መፍትሄ ሊሰጧት አልቻሉም። አንድ ምሽት ግን እጅግ እብጠቱ ስለጨመረ እና ቆማ ለመስራት ስላስቸገራት ወደ ከፍተኛ ህክምና ትገባለች። ከብዙ ምርመራ በኃላ ዶክተሮቹ በሽታው ወደ መላ ሰውነቷ በመሰራጨቱ እና ከቀጥጥር በላይ ስለሆነ ምንም ማድረግ የማይቻልበት ደረጃ ስለደረሰ የሞትዋን ቀን ብቻ ትቁጠር የሚል መርዶ አረዷት !
ይህ ግን ለወለተ ጻድቅ የሚያስደነግጣት ዜና አልነበረም። እንደ ቅደስ ጳውሎስ ❝በሕይወት ሆነን ብንኖር ለጌታ እንኖራለንና፥ ብንሞትም ለጌታ እንሞታለን። እንግዲህ በሕይወት ሆነን ብንኖር ወይም ብንሞት የጌታ ነን።❞ ብላ ራስዋን ካረጋጋች በኋላ አ.አ ለምትገኝ እናትዋ ጋር ቀጥታ ደውላ እንዲህ አለቻት !
" እናቴ ከአንቺ ተወልጃለው እና ያንቺ ስጋ ማለት የኔ ስጋ ነው :: ስለዚህ እባክሽ እናቴ ትንሽ እያመመኝ ስለሆነ ልደታ ቤተክርስቲያን ሄደሽ 3 ጊዜ ተጠመቂልኝ " ይህንን የሰሙት እና የታዘዙትን ለመፈጸም ወደ ማኅደረ ስብሃት ቅድስት ልደታ ቤተክርስቲያን ሄዱ ወደ ጥምቀት ቦታም ሲገቡ ሦስቴ እያማተቡ " #ይህ_ጥምቀት_ለኔ_አይደለም ይልቁንም የልጄ የወለተ ጻድቅ ነው " እያሉ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ተጠመቁላት ።
የሦስት ቀን ጥምቀት እንደ ጨረሱ የወለተ ጻድቅ እግር ላይ የነበረው እብጠት እንደ ቅርፊት እየተቀረፈ ወደቀ። እጅግ ድንጋጤ ውስጥ የነበሩት አሰሪዎችዋ በሚያዩት ነገር በመደናገጣቸው ወደ ህክምና ስፍራ ሲወስዷት ምንም አይነት በሽታ እንደሌለባት ገለጹላት ።
የሞትዋን ቀን እንድትቆጥር የነገራት ዶክተር ተደጋጋሚ ምርምራ ቢያደርግላትም ምንም ሊያገኝባት አልቻለም ።
" ወጥመድ ተስበረ እኔን አመለጥኩኝ ...! "
ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል ሲል ጠየቃት ? እርሷም እንዲህ አለች አምላኬን የወለደች ልደታ ማርያም ታሪኬን ቀየረችው ።
የሚገርመው ጀርመን ለመዝናናት ከአሰሪዎችዋ ጋር በሄደች ጊዜ ተመርምራ ነጻ ነሽ ተብላለች።
ለእኔ የደረሰች የቃናዋ እመቤት ላንተም ትድረስልህ ! ብላ መረቀችኝ ። አሜን ! አንቺ ሴት እምነትሽ ታላቅ ነው !
እግዚአብሔር እንዳልተውን ሲነግረን እንዲህ ያለ ተዓምራት እያደረገልን ያጽናናል !
እኔም እላለው ለእህታችን የደረሰች የቃናዋ እመቤት ለእናንተም ትድረስላችሁ። ምልጃዋ አይለየን :: የህይወት ቋጠሯችንን ትፍታልን ።
(ባለታሪክዋን አስፈቅጄ ለሁሉ ትምህርት ይሆን ዘንድ ጻፍኩት ።)
ዲ.እስጢፋኖስ ደ
ጥር 12 / 2015
አ.አ/ ኢትዮጲያ

________

(ባለታሪክዋንኘ አስፈቅጄ ለሁሉ ትምህርት ይሆን ዘንድ ጻፍኩት ።)