" #እምዬ_ምኒልክ የታሪክ #ፈርጥ "
______________________
አፄ ምኒልክ ከአፄ ልብነድንግል ልጅ ከአቤቶ ያዕቆብ ትውልድ ሲያያዝ የመጣ የስመ ጥሩ ንጉሥ የሣህለ ሥላሴ የልጅ ልጅ የንጉሥ ኃይለ መለኮት ልጅ ናቸው።
#ትውልዱም_ከአቤቶ ያዕቆብ ዠምሮ ቢቆጠር አፄ ምኒልክ ፲ ፫ ተኛ ይሆናሉ፤ ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ከአባታችው ከሸዋው ንጉሥ ኃይለ መለኮት ሣህለ ሥላሴ ና ከእናታቸው ወይዘሮ እጅጋየሁ ለማ አድያም ቅዳሜ ነሐሴ ፲ ፪ ቀን ፲ ፰ ፻ ፴ ፮ ዓ.ም. ደብረ ብርሃን አካባቢ አንጎለላ ከሚባል ሥፍራ ተወልደዋል፤ ከዚያም በ አንጎለላ መቅደላ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ክርስትና ተነሱ።
አያታቸው ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ የልጁን መወለድ ሲሰሙ “ምን ይልህ ሸዋ” በሉት ብለው ስም አወጡ። እሳቸው “…ምኒልክ በሚል ስም የሚነግሥ ንጉሥ ኢትዮጵያ ን ታላቅ ያደርጋታል” የሚል ትንቢት ስለነበር ‘ምኒልክ’ የኔ ስም ነው ብለው ነበር። ሆኖም፣ በህልማቸው ከልጁ ጋር አብረው ቆመው ከሳቸው ጥላ የልጁ ጥላ በልጦ፤ በእግር የረገጡትን መሬት ሲያለካኩ እሳቸው ከረገጡት ልጁ የረገጠው ረዝሞ አዩ።
#ከዚህ በኋላ “ምኒልክ የኔ ስም አይደለም። የሱ ነው። ስሙን ምኒልክ በሉት” ብለው አዘዙ ። ይላል ( ጳውሎስ ኞኞ “አጤ ምኒልክ” በተባለው መጽሐፉ /ገጽ ፲፪)
አፄ ምኒልክ በተወለዱ በ፲ ፩ ዓመት በ፫ ወር በሺ ፰ ፻ ፵ ፰ ዓ.ም አፄ ቴዎድሮስ ወደ ሸዋ በመጡ ጊዜ ይዘዋቸው ወደ ጎንደር ሄዱ ፤ በዚያም አፄ ቴዎድሮስ ብልዕነታቸውንና አስተዋይነታቸውን ተመልክተው አብረው በማዕረግ ይዘዋቸው ሲኖሩ ቆዮ በመጨረሻም ሴት ልጃቸውን ወይዘው አልጣሽ ቴዎድሮስን ዳሩላቸው።
#በዓመት_በዓል የፈረስ ጉግስ ከምኒልክ በቀር ሌላ ሰው አይታይም ነበር ይባላል። በመጨረሻ ግን አፄ ቴዎድሮስ ኢትዮጵያን አንድ አደርጋለሁ በማለት ያቀዱትን ዕቅድ ፣ በያሉበት መኳንቱና ሕዝቡ እየሸፈቱ ስላበላሹባቸው ከብስጭት የተነሳ ሰውን ሁሉ ያለ ሕግ በገደሉና ባሰሩ ጊዜ እንደዚሁ አቤቶ ምኒልክን አስረው ወደ መቅደላ ላኩዋቸው ፤ በዚያም ከታመኑ አሽከሮቻቸውና ከእናታቸው ከወይዘሮ እጅጋየሁ ጋር ሆነው ከሸዋ ባለ አባቶች ጋር ውስጥ ውስጡን እየተላላኩ ምቹ የማምለጫ ጊዜ ሲፈልጉ ወዲያው አፄ ቴዎድርስ የትግሬና የጎንደር፣ የበጌምድርም ሕዝብ ሸፍቶባቸው ወደ ላይና ወደ ታች ሲሮጡ አቤቶ ምኒልክ ከወሎዎች ጋር ውስጥ ውስጡን ተስማምተው ከመቅደላ ፲ ፰ ፻ ፶ ፯ ዓ.ም ሰኔ ፳ ፬ ቀን ሌሊት አምልጠው ወሎ ገብተው አደሩ ።
በዚህ ጊዜ አቶ በዛብህ እንደ ንጉሥ ሆነው ሸዋን ሲገዙ ይህንኑ ሰምተው ነበርና እሰሪልኝ ብለው ለወሎ ገዢ ለወዘሮ ወርቂት ገጸ በረከት ጨምረው ላኩላቸው ወይዘሮ ወርቂትም ስለ አቶ በዛብህ ሳይሆን መቅደላ ለታሰረው ልጃቸው ለውጥ አድርገው ለአፄ ቴዎድርስ ለመመለስ ምኒልክ የቁም እስረኛ አድርገው ወደ አፄ ቴዎድሮስ መልክተኛ ላኩ ።
#መልክተኞቹም ወደ መቅደላ በደረሱ ጊዜ አፄ ምኒልክ አምልጠው ስለነበር አፄ ቴዎድሮስ ተበሳጭተው እስረኛውን ሁሉ እጅና እግሩን እየቆረጡ ገደል ሲጥሉ እንዲ ተብሎ ተገጠመላቸው።
" #አፄ_ቴዎድሮስ_እጅግ_ተዋረዱ
#የሸዋን_ሰው_ሁሉ_እጅ_ነስተው_ሄዱ "
#የወይዘሮ ወርቂትም ልጅ አብሮ መጣሉን ሰሙ ስለዚህ መልክተኞቹ ተመልሰው ይህንኑ ለወዘሮ ወርቂት ነገሩ ወይዘሮ ወርቂትም በእግዚአብሔር ሥራ ተደንቀው ቦሩ ሜዳ ላይ ምኒልክን ተቀብለው፣ “ #የሸዋ_ሰው_አውራህ_መጥቷልና_ደስ_ይበልህ_ተቀበል ” ብለው አዋጅ አስነግረው፣ አጃቢ አድርገው በመለከትና እምቢልታ አሳጅበው ከሸዋ ድንበር ድረስ ላኳቸው። ሸዋን ‘ንጉሥ ነኝ’ እያሉ ይገዙ የነበሩት አቶ በዛብህ የምኒልክን ወደመሀል ሸዋ መግፋት ሲሰሙ ለመውጋት ጋዲሎ ከተባለ ሥፍራ ተሠልፈው ሲጠባበቁ፣ አንዲት ሴት እንዲህ ስትል ገጠመች።
«ማነው ብላችሁ ነው ጋሻው መወልወሉ፣
ማነው ብላችሁ ነው ጦራችሁ መሾሉ
ማነው ብላችሁ ነው ካራችሁ መሳሉ፣
የጌታችሁ ልጅ ነው ኧረ በስመ አብ በሉ»
በኃላ ግን አቶ በዛብህ ስለተሸነፈ ከዛ ሸሽተው አፍቀራ ገቡ ከዚህ በኃላ አቤቶ ምኒልክ ከሸዋ በመጡ በ፲ ዓመት ንጉሥ ተብለው ሲገዙ አቶ በዛብህ አፍቀራ ሆነው ታርቀው ለመግባት ወደ ንጉሥ አማላጅ ላኩ።
በዚህ ጊዜ ንጉሡ ሊታረቋቸው ሲያስቡ የአቶ በዛብህን ሀሳብ አውቃለው ባይ ቀርቦ " አቶ በዛብህ አሁን ታርቄ ልግባ የሚለው ከገባ በኃላ መኳንንቶን እየሰበከ ለማስከዳት ነው እንጂ በእውነት እርቅ ፈልጎ አይደለም በእውነት እርቅ ፈልጎ ከሆነ የአፈቀራን ምሽግ አስረክበኝ ይበሉትና እስቲ ያስረክብሆ?! " ብሎ ተናገረ። ንጉሥ ምኒልክም አቶ በዛብህን የአፍቀራን ምሽግ እንዲያስረክብ ጠየቁት አቶ በዛብህም እኔስ ፈቅጄ ነበር አሽከሮቼ ግን ተው አታስረክብ ይሉኛል ስላሉ ይህም በቂ ምክንያት ሆኖ ስላልተቀበሏቸው ወዲያው ተያዙና ፍርድ ተጀመረ ።
#በፍርዱም_መጀመሪያ ጋዲሎ ላይ አላስገባም ብለው መዋጋታቸውንና ሁለተኛም የአፍቀራን ምሽግ አላስረክብም ማለታቸው እየተጠቀሰ ይሙት በቃ ተብሎ ተፈርዶባቸው በጥይት ተደበደቡ በጥይትም ሲመቱ ባሩዱ ከልብሳቸው ላይ ተያይዞ ገላቸው ስለነደደ አንዲት ሴት ከዚህ ቀጥሎ ያለውን ገጠመች፤
" #አንተም_ጨካኝ_ነበርክ_ጨካኝ_አዘዘብህ
#እንደ_ገና_ዳቦ_ከላይም_ከታችም_እሳት_ነደደብህ "
አፄ ምኒልክ በአባታቸው ዙፋን ተቀምጠው ንጉሥ ምኒልክ እየተባሉ ይገዙ ዠመር። እንዲህም አድርገው እስከ ፲ ፰ ፻ ፸ ዓ.ም ድረስ ለ፲ ፪ ዓመት በሙሉ የበላይነት ሸዋን ሲገዙ ኖሩ።
የጽሁፉ ግብቶች፦
- ተክለ ጻድቅ መኩሪያ " የኢትዮጵያ ታሪክ"
- ጳውሎስ ኞኞ “አጤ ምኒልክ”
አ.አ ኢትዮጵያ
ተክለ ኤል ኃ/ማርያም
የካቲት ፲ ፰ /፳ ፻ ፲ ፫ ዓ.ም

#ብርሃን_ዘኢትዮጵያ እቴጌ ጣይቱ ብጡል
_____________________________
« #ብርሃን_ዘ_ኢትዮጵያ » በሚል ቅፅል ስም የታወቁት እቴጌ ጣይቱ ከአባታቸው ደጃዝማች ብጡል ኃይለ ማርያም እና ከእናታቸው ወይዘሮ የውብ ዳር ነሐሴ ፲ ፪ ቀን ፲ ፰ ፻ ፴ ፪ ዓ/ም በጌምድር ውስጥ ደብረ ታቦር ከተማ ተወለዱ።
በ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት በተወለዱ በ ፹ ቀናቸው ጥቅምት ፳ ፯ ቀን ፲ ፰ ፻ ፴ ፫ ዓ/ም በደብረ ታቦር ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ክርስትና ተነሡ።
#በልጅነት ዘመናቸው በዚሁ ደብር ውስጥ ዳዊትን ሲከታተሉ ከቆዩ በኋላ በጊዜው ይሰጡ የነበሩትን ሌሎች የሃይማኖት ትምህርቶች በየታላላቁ አድባራት በመዘዋወር ያጠናቀቁ ስለመሆናቸው ታሪክ አዋቂዎች ይናገራሉ። የተማሩባቸውም መፃሕፍት ተጽፈው ይገኙ የነበረበትን የግዕዝ
ቋንቋ አጣርተው ያውቁ ነበር። እናታቸው ወይዘሮ የውብዳር ከባለቤታቸው ደጃዝማች ብጡል ኃይለ ማርያም ከሞቱ በኋላ በጅሮንድ መዩ የተባሉትን የ ዓፄ ቴዎድሮስን ባለሟል አግብተው ነበር። እሳቸውም ጣይቱ ብጡል ትምህርት እንዲቀስሙ ለማድረግ ልዩ መምህር ቀጥረውላቸው እንደነበር ይታወቃል።
#እቴጌ_ጣይቱ በማኅደረ ማርያም ሆነው ሲማሩና መፃሕፍትን ይቀጽሉ በነበሩበት ጊዜ ለቤተክርስቲያን መጋረጃ መሥሪያ በትርፍ ጊዜያቸው ፈትል እየፈተሉ ያቀርቡ ነበር። በ በገና ቅኝትና ድርደራም በኩል የታወቁ ባለሙያ እንደነበሩ ይተረክላቸዋል።
ከ ንጉሥ ምኒልክ ጋር ጋብቻ እንደመሠረቱ
________________________
#የሸዋው ንጉሥ ምኒልክ በሸዋ የዓፄ ቴዎድሮስ እንደራሴ ከነበሩት አቶ በዛብህ ጋር ነሐሴ ፲፯ ቀን ፲፰፻፶፯ ዓ/ም በጋዲሎ አካባቢ በተደረገው ጦርነት ድል አድርገው ወደ አንኮበር ገብተው በ ነሐሴ ፳፬ ቀን ነገሡ። በነገሡም በአሥራ ሁለት ዓመታቸው የፋሲካ ን በዓል በ ባሕር ዳር አቅራቢያ ሱሉልታ ላይ ዋሉና ደብረ መይ በጣይቱ ብጡል እናት በወይዘሮ የውብዳር ቤት ከጣይቱ ብጡል ጋር ተጫጭተው ስለጋብቻቸው ተነጋገሩ። ከዚያም ዋና ከተማቸው ወደነበረችው ደብረ ብርሃን ተመልሰው መጡ።
ከተጫጩ ከሁለት ዓመት በኋላ ወይዘሮ ጣይቱን ለማስመጣት በቤተ መንግሥቱ በተደረገው ምክር መሠረት አለቃ ተክለማርያም ወልደ ሚካኤል ደብዳቤ ተሰጥቷቸው ተላኩ። በዚያም አስፈላጊው ሁሉ በተፋጠነ ሁኔታ ተሟልቶ በ ጐጃም በኩል ደንገጡሮችና አሽከሮች አስከትለው ጉዞውን ጀመሩ።
#ደብረ_ብርሃንም በገቡ ጊዜ ንጉሡ /ምኒልክ/ ታላቅ አቀባበል አደረጉላቸው። ከዚያም ጣይቱ ወንድማቸው ራስ ወሌ ብጡል ዘንድ ለጥቂት ዓመታት ተቀምጠው ከቆዩ በኋላ የጋብቻቸው ስነ-ሥርዓት የ ፋሲካ ዕለት ሚያዝያ ፳፭ ቀን ፲፰፻፸፭ ዓ/ም በ አንኮበር መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ቁርባን ተቀብለው ተጋቡ።
አፈወርቅ ገብረ ጊዮርጊስ “ዳግማዊ አጤ ምኒልክ” በተባለው መጽሐፋቸው ገጽ ፴ ፱-- ፵ ፩ ላይ “ከልዢነት ጀምረው ሲመኟት እንደ ህልም ሲአልሟት ትኖር የነብረችው ጣይቱ ብጡል በ ፲፰፻፸፭ ዓ/ም ደብረ ብርሃን ገባች ንግሥተ ሸዋ ሆነች ወዲያው የፋሲካ ለት አንኮበር መድኃኔ ዓለም ቆርበው ሁለቱ ተጋቡ። … ፀሐይቱ ለማለት ጣይቱ ተባለች ነገር ግን ከጣይቱ እጣይቱ ለመባል ይገባታል።” [2] ይላሉ
« #ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ» ተብለው ዘውድ ስለ መጫናቸው
_________________________
ንጉሡ «አፄ ምኒልክ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ» የሚለውን ስም በተቀዳጁ በማግሥቱ ጥቅምት ፳ ፯ ቀን ፲ ፰ ፻ ፹ ፪ አ/ም ወይዘሮ ጣይቱ ብጡል እቴጌ ተብለው ተሰየሙ።
#የሥርዓተ ዘውዱ አፈፃፀም በከፍተኛ መሰናዶ የተጠናቀቀ በመሆኑ እጅግ ደማቅ እንደነበር ከተፃፉ ፅሁፎች ለማወቅ ይቻላል። እቴጌ ጣይቱም ጳጳሱ አቡነ ማቴዎስ ከንጉሠ ነገሥቱ እጅ የተቀበሉትን ዘውድ ደፉላቸው።
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በታወቁበት «እቴጌ ጣይቱ ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ» በሚል የክብር ስም ማኅተም ተቀረፀላቸው። እነዚሁ ታሪካዊ ሂደቶች እቴጌይቱን በኢትዮጵያ ዱኛዊ፣ ወታደራዊና ማኅበራዊ ኑሮ ውስጥ ከፍተኛና ብሩህ ሚና ለመጫወት የቻሉ አድረገዋቸዋል።

#ቅድስት_ቤተ_ክርስቲያን በዐድዋ
_____________________________
ጦርነት አስከፊ ነው የጦርነት ደግ የለውም ሆኖም በዓለማችን ላይ ቅዱስ ጦርነት ፤የመስቀል ጦርነት ተብለው የተጠሩ የጦርነት ዐይነቶች ነበሩ።
በአለፉት ሺህ ዓመታት በጥንታዊ ሀገራችን ኢትዮጲያ ከተፈጸሙ ታሪካዊ ነገሮች አንዱ በሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊ ተራዳኢነት ጀግኖች አባቶቻችን በፋሽሽት ኢጣልያ ላይ የካቲት ፳ ፫ ቀን ፲ ፰ ፻ ፹ ፰ ዓ.ም የተቀዳጁት የዐድዋ ድል ነው ይህ ድል የመላው አፍሪካ ጥቁር ሕዝቦች ድልና የነፃነት ብርሃን በመባል ይታወቃል።
#ጀግኖች_አባቶቻችንን በአድዋው ጦርነት የረዳቸው የሰማዕታት አለቃ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሕገ ወንጌልን በማስተማርና አምልኮተ ጣኦትን በመንቀፍ ስለ ፈጣሪያችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕሪ አምላክነት እየመሠከረ ከግፈኖች አረማውያን ብዙ መከራ ተቀብሎ በአደባባይ መራራ ሞትን ፊት ለፊት በመጋፈጥ ሰባት ዓመታትን ከተጋደለ በኃላ ሚያዝያ ፳ ፫ ቀን የሰማዕትነትን አክሊል ተቀብሏል።
ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሚያዝያ ፳ ፫ ቀን ሰማዕትነትን ጊዮርጊስ በተቀበለበት ዕለት ከፈጣሪው ከኢየሱስ ክርስቶስ ልዮ ልዮ የምሕረት ቃል ኪዳን ተቀብሏል።ከተቀበለው ቃል ኪዳን መካከል በስምህ ተማጽኖ መታሰቢያህን የሚደርገውን እኔ በመከራው ቀን እረዳዋለሁ የሚል ይገኝበታል።
#ሊቀ_ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ የሰማዕትነትን አክሊለ ክብር ከተቀበለ በኃላ በአካለ ነፍስ ሆኖ ወደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተማኅጽኖ አቀረበ ይኸውም " ምስለ ፍልሠትኪ ደምርኒ እሙ" የፈጣሪየ የኢየሱስ ክርስቶስ እናት እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ ሰማዕትነትን ከተቀበልኩባት ከፋርስ ምድር የአጽሜ ፍልሠት ቀን ከአንቺ የፍልሰትሽ በዓል ቀን ጋር ነሐሴ ፲ ፮ ቀን ተባብሮ እንዲከበርልኝ ፈቃድሽ ይሆን በማለት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ለመነ።
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም እንዳልከው ይሆንልሃል ስለሆነም አንተም ከእግዚአብሔር አስራት ሁና የተሰጠችኝን ኢትዮጵያን ገበዝ (ጠባቂዋ) ሆነህ ጠብቃት አለችሁ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስም አንቺ እንዳልሽ ይሁን እመቤቴ አለ ስለዚህም ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ገበዝ ወይም ጠባቂ ሁኖ ከእግዚአብሔር ተሹሟል።
#የቅዱስ_ጊዮርጊስ ፍልሰተ አጽም ከፋርስ ወደ ልዳ በነሐሴ ፲ ፮ ቀን ማለትም የእመቤታችን ቅዱስ ሥጋ ከጌቴ ሰማኒ ወደ መንግሥት ሰማያት በፈለሰበት (በዕርገቷ) ዕለት ተፈጽሞለታል። ይህን የቅዱስ ጊዮርጊስና የእመቤታችን ስምምነት በሚገባ የምታውቀው ሀገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከወራሪ ጠላት እና ከክፉ ነገር ሁሉ እንደሚጠብቃት ዘወትር ታምናለች።
በመሆኑም በጥንት ኢትዮጵያ የሚታወቅና ይደረግ የተበረ አንድ ነገር አለ ከቅድመ አያቶቻችን ጀምሮ የሚደረገውም ወጣት ኢትዮጵያዊን የሰማዕቱን የቅዱስ ጊዮርጊስ ማኅበርተኞች በመሆን በአንድነት ይሰበሰባሉ፤ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም በየጊዜው እየተሰበሰቡም ሰለ ፈረስ ግልቢያ ፣ስለ ጦር ጉግስ፣ የጦር ስልትና ወታደራዊ የጀግንነት ትምህርት እየተማሩ እንዲያድጉ ያደርጉ ነበር።
#አባቶቻችን በዚህ ዕድገታቸው የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስና የለገራቸው ኢትዮጵያ ፍቅር አብሮ ያድጋል የጀግንነት ወኔአቸውና ሥነ ምግባራቸውም የላቀ ይሆናል እንዲህ ሁነው የሚድጉት ኢትዮጵያዊያን በማናቸውም ነገር በቀላሉ የማይበገሩ ስለሆኑና የሰማዕቱን የቅዱስ ጊዮርጊስ ረድኤት ስለማይለያቸው በየትኛውም የጦርነት ታሪክ የተሸነፉበት ጊዜ የለም።
እንደሚታወቀው በኢትዮጵያ ታሪክ አፄ አምደ ጽዮን የጦር ሰው ነበሩ።በቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ያላቸው እምነትና ተማጽኖ በእጅጉ የላቀ እንደነበርም ይነገርላቸዋል። በኢትዮጵያ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም ቤተ ክርስቲያን መሥራት የተስፋፋውም በእርሳቸው ዘመን ነው።
#በኢትዮጵያ የሥልጣኔ ታሪክ ዘመናዊ አስተዳደር እንዲስፋፋ ከፍተኛ ጥረት ያደረጉት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ እንደ ቀድሞዎ አባቶቻችን ከኢትዮጵያ ገበዝ(ጠባቂ) ከሰማዕት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የነበራቸው ፍቅር እጅግ የላቀ ነበር ። ዳግማዊ አፄ ምኒልክ የነገሱበት ዘመን በጊዜው የነበሩ የኢጣልያ ባለ ሥልጣኖች ቃላቸውን እየለወጡና እያታለሉ ሀገራችን ኢትዮጵያ በቀኝ ግዛት ለመያዝ ቆርጠው የተነሱበት ዘመን ነበር።
የኢጣልያን ጦር መረብን ተሻግሮ ወደ ትግራይ እየገሰገሰ መምጣቱ ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በሰሙ ጊዜ በ ፲ ፰ ፻ ፹ ፰ ዓ.ም የክተት አዋጅ አድርገው በጥቅምት ወር ወደ ትግራይ ሄዱ ጣሊያንን ለመፋለም ወደ ትግራይ ሲሄዱ ሁል ጊዜ ኢትዮጵያን በመርዳት የሚታወቀውን የሰማዕቱን የቅዱስ ጊዮርጊስንእና የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማርያምን ታቦት ይዘው ነበር የሄዱት ወቅቱም የዐቢይ ጾም መጀመሪ ስለነበር አብሯቸው የዘመተው አብዛኛው አርሶ አደር ገበሬ ጾሙን ሳይታ እየጾመ ነበር የተከተላቸው። እርሳቸውም ቢሆኑ ምንም እንኳ ዕለቱ እሁድ ቢሆንም ቅዳሴ ገብተው እስከ ረፋዱ ሦስት ሰዓት አስቀድሰው ነው ወደ ጦርነቱ የገቡት ።
..............ቀጣዮን የመጨረሻ ክፍል ይመልከቱ........
#ዐውደ_ምሕረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.facebook.com/112544300256976/posts/277932900384781/?app=fbl

____________________________
...የመጨረሻውና አስደማሚው ኩነት...
#ዳግማዊ_አፄ ምኒልክ ታቦተ ጊዮርጊስ በድንኳን ይዘው አድዋ ላይ ሰፍረው በነበረ ጊዜ ባንዳ የነበረ ሰው በኢትዮጵያ የጦር ሰፈር መሰላቸት እንዳለና ስንቅ እያለቀ መሆኑን ለኢጣሊያኖት እየሄደ ያወራ ነበር። ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ይህን ወሬ በሰሙ ጊዜ በድንኳኑ ውስጥ የቅዱስ የጊዮርጊስ ታቦት የሚገለግለውን ካህን ጠርተው እንደ አባቶቼ ተዋግቼ እንድሞት እባክህን ጦርነቱን አስጀምረው ብለህ ንገርልኝ ሲሉ ይልኩታል።እርሱም እንደታዘዘው ያደርጋል።
ጦርነቱ ሲጀመር የኢትዮጲያ ወታደሮች በኢጣልያን ጦር ይጠቁ ጀመር ለዚህም ትልቁ ምክንያት ጀግንነታቸው ነበር ጣሊያኖች ምሽግ ይዘው ሲተኩሱ ጀግኖች አባቶቻችን ግን ምሽግ ውስጥ ተደብቆ መተኮስን እና ማጥቃትን እንደ ነውር በመቁጠር ደረታቸውን እየገለበጡ ፊት ለፊት ይዋጉ ስለነበር ነው ።በእውነቱ ይህ.ግሩም ድንቅ የሆነ ጀግንነት ነው!...
#እቴጌ_ጣይቱም ኢጣሊያ ይጠጣው የነበረውን የውኃ ጉድጓድ አስያዙት በዚህም ጣልያን ትንሽ ተዳከመ ሆኖም ሐበሻ መጠቃቱን አልቀረም ነበር ። ይህን የሐበሻን መጠቃት የተመለከተው የልዳው ሰማዕት ከእመቤታችን ጋር የገባውን ቃል ይፈጽም ዘንድ በነጭ አባ ላይ ፈረሱ ተቀምጦ መጥቶ ኢጣልያኖችን ፈጃቸው ድሉም የኢትዮጵያ ሆነ። ይህንንም በምርኮ የተያዙ የኢጣሊያ ጭፍሮች በአድናቆት ሆነው መስክረዋል።
በዚህም የድል ወቅት በጎጃም ዲማ በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በፍሬም የተሰቀለ ትልቅ የቅዱስ ጊዮርጊስ ሥዕል ነበር:: ጠዋት የገዳሙ እማሆይ አቃቢ ግብረ ማህረዕ ለመፈጸም ይህን ሥዕል ሊሳለሙ ሲገቡ ሥዕሉን ከቦታው ያጡታል በኃላ ወደ ማታ ይህው ሥዕል እየበረረ መጥቶ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ሲገባ ያዩታል እማሆይም አቃቢም አባቴ ጊዮርጊስ የት ውለህ መምጣትህ ነው ? ቢሉት ጌታሽን " ምኒልክን ስረዳው ውዬ መምጣቴ ነው" ብሎ በስብአዊ ልሣን አናገራቸው።
#እማ_ሆይም ከሥዕሉ በጦርነቱ የኢትዮያን አሸናፊነት ተረድተው በዕልልታ አቀለጡት:: አፄ ምኒልክም ከድሉ ሲመለሱ ከደስታቸው የተነሳ በአዲስ አበባ ለሰማዕቱ ውለታ ይሆን ዘንድ ፒያሳ የሚገኘውን የገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያንን ሰሩለት::
ዋቢ:- ልሳነ ተዋህዶ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ጥር ፪ ሺህ ፫ ዓ.ም ያሳተመው መጽሔት
................ይቆየን ...........
#የእግዚአብሔር_ቸርነት_የድንግል_ማርያም_አማላጅነት_የሰማዕቱ_የቅዱስ_ጊዮርጊስ_ጥበቃና_ረድኤት አይለየን!
" ዐውደ ምሕረት የእናንተ "

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
‹‹ገዳመ ቆሮንቶስ እና ፈተናዎቹ››
______________________
በቆሮንቶስ ተራራ ላይ የተመሠረተ ሲሆን በኢያሪኮ ይገኛል፡፡ ከኤልሳዕ ምንጭ ዋናውን
መንገድ ወደ ቀኝ በመተው በግራ በኩል ባለው ጎዳና በመጓዝ ቆሮንቶስ ተራራ ሥር
ይደረሳል፡፡ ወደ ገዳመ ቆሮንቶስ ለመሄድ ተራራውን በእግር መጓዝ ግድ ይላል፡፡ ዳገቱን
ጨርሶ ከተራራው መካከል የሚገኘው ጌታ 40 መዓልትና 40 ሌሊት ጌታ የጾመበት ሥፍራ
ተለይቶ ይታያል (ቅድስት ሀገር ገጽ 111-112)
እንግዲህ ጌታችን በዚህ ቅዱስ ሥፍራ አብነት ይሆነን ዘንድ በትሕትና እንደ ጾመ እንደ
ጸለየ ሁሉ(ማቴ 11፥29/ ዮሐ 13፥13/ ማቴ 4፥1) ክርስቲያኖችም አሠረ ፍኖቱን
በመከተል በግብር በመምሰል ይሄንኑ ጾም በታላቅ መንፈሳዊ ትጋት እንዲጾሙ ቅድስት
ቤተክርስቲያናችን ታዛለች ታስተምራለች፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገዳመ ቆሮንቶስ ከዘረጋ ሳያጥፍ ከቆመ
ሳይቀመጥ ከጾመና ከጸለየ በኃላ በእነዚህ ሦስት ርዕሰ አጣው በተባሉ ፈተናዎች ተፈትኗል
እነርሱም
*ስስት:- ይህም ድንጋይዮን ዳቦ እንዲሆን እዘዝና ብላ እንብላ ማለቱ ነው እርሱ ሰው
በእንጀራ ብቻ አይኖርም ከእግዚአብሔር አፍ ከሚወጣ ቃል ጭምር እንጂ በማለት ድል
ነስቶታል:: ዲያቢሎስ ይህን ያለው አስቀድሞ ለዮሴፍ ድንጋዮን ዳቦ አድርጎ እንደመገበው
ስላወቀ ነው ይህ የፈተና ዓይነት በይበልጥ መነኮሳትት ይገዳደራቸዋል ይፈትናቸዋል::
* ትዕቢት:- ይህ ደግሞ የተራራ ጫፍ ላይ ወስዶ (በፍቃዱ ሄዶለት ነው እንጂ አስገድዱት
አይደለም) እግርህም በድንጋይ ከቶ እንዳትሰናከል መላእክቱን ስላንተ ያዝልሃል ተብሎ
ተጽፎል ስለዚህ እራስህን ከዚህ ዘርውር በማለቱ ታውቆል ማቴ 4÷6 ጌታችንም ጌታ
እግዚአብሔር አትፈታተነው ተብሎ ደግሞ ተጽፎል ብሎ ድል ነስቶታል እስራኤል ዘሥጋ
እግዚአብሔር ያድነናል እያሉ እራሳቸውን ከእረጃጅም ተራራ ላይ እራሳቸውን እየፈጠፈጡ
ይሞቱ ነበር እግዚአብሔርም አያድናቸውም ነበር ተፈታትነውታልና :: ይህ የፈተና ዓይነት
በይበልጥ በካህናትና በቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ላይ ይበረታል እውቀቴ የነጠቀ
አይምሮዬ የረቀቀ ነው ሲሉ ይታበያሉ ይህም ትዕቢት ነው ጌታችን መድኃኔታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ ግን ማድረግ እየቻለ ሁሉ የእርሱ ሆኖ ሳለ ያለውን አላደረገለትም ምን አቅቶኝ
ብሎም አልታበየም::
ሌላውና ሦስተኛው ፈተና ፍቅረ ነዋይ ነው (ገንዘብን መውደድ)
ፍቅረ ነዋይ :-ይህ ደግሞ የዓለምን ሀብት አሳይቶ ወድቀህ ብትሰግድልኝ ይህን
እሰጥሀለው በማለቱ በፍቅረ ነዋይ እንደፈተነው ታውቆል ጌታችንም ወግድ አንተ ከይሲ
ለጌታ ለአምላክህ ብቻ ስገድ ተብሎ ተጽፎል ብሎ ድል ነሳው ዘጸ 20÷1 ይህ ዓይነቱ ፈተና
ቨአረጋዊያን ላይ ጎልቶ ይታያል::ብር ከሌለኝ ማን ይጦረኛል በሚል ወደ ጠንቆይ ወደ
ቃልቻው ስለ ገንዘብ ብለው ይሆዳሉ ጠንቆይ ግን የገንዘብ ምንጭ ሌሆን አይችልም ከነ
ስሙም ጠንቋይ ማለት ጠንቀ ነዋይ የሀብት ጠንቅ ማለት ነው::ከጅምሩ ክርስቲያን ገንዘብ
መውደድ አይገባቸውም ገንዘብ የሚወድ የክርቶስ ጠላቶች ናቸውና ወልደ ይሁዳ ናቸው
እኛስ እንዴት እንጹም?
† በሙሉ አቅማችን እስኪርበን እንጹም:: አንዳንድ ጊዜ የተወሰኑ ሰዓታትን ለመሙላት
የምናደርገው ትግል ከመንፈሳዊነት ዉጭ ያደርገናል:: / ማቴ.4፥2 ፤ ሐዋ. 10፥1/
† በደስታ እንጹም:: የጾም ወቅት የንስሐና የሐዘን ይሁን እንጂ መንፈሳዊ ደስታንም
ያጎናጽፈናል:: ስለዚህ ደስ እየተሰኘን የምንፈጽመው እንጂ እንደ ቅጣት ማሰብ
አይገባንም:: /ዕብ.13፥9/:: ካለንበት ሁኔታ ጋር በማነጻጸር እንዳንደክምም
የእግዚአብሔርን ውለታ ማሰብና ስላደረገልንም ነገር ሁሉ በደስታ በማመስገን እንጹም::
‹‹የማይበላም ለጌታ ብሎ አይበላም እግዚአብሔርንም ያመሰግናል።›› (ሮሜ 14፥6)
† ጾማችንን ከበጎ ምግባር ጋር ማስተሳሰር ያስፈልገናል:: ምጽዋትና ጾም የማይነጣጠሉ
የአንድ ርግብ ሁለት ክንፎች ናቸውና ድሆችን ከማሰብ የተቸገሩትን ከመርዳት ጋር ያለች
ጾም ቶሎ ወደ ብፅዕና ታደርሳለች:: ስግደትና እንባን እንዳቅማችን መጠን እንደተሰጠን ጸጋ
ልንፈልጋቸው ይገባል::
†ወገኖቻችንን ማኅበራችንንና ሃገራችንን በማሳሰብ እንጹም::
† ጾማችንን የመላው ሕዋስ ማድረግ:: ጾም የተወሰነ የአካል ክፍላችን ተግባር ሳይሆን
የመላ ሕዋሳችን ነው:: ፈቃዳችንን ለፈቃደ አምላክ ለማስገዛት የላቀ ልምምድ
የምናደርግበት ወቅት ካለ የጾም ወራት ቀዳሚዎቹ ናቸው:: በመሆኑም በመላ ሕዋሳቶቻችን
እንጹም:: / ዘዳ.6፥5፤ ማር.12፥30/::
† ያለ ግብዝነት ልንጾም ያስፈልጋል
† ከእንስሳት ተዋጽኦዎች ና ከአስካሪ መጠጦች መከልከል ያስፈልገናል:: /
መዝ.108፥24፤ ዳን.10፥3/:: ያለዚያ ጾማችን ከመረቁ አውጡልኝ ከሥጋው ጾመኛ ነኝ
ይሆንብና::
@AwediMeherit
@AwediMeherit
ተርቢኖስ ሰብስቤ
ኃ/ማርያም
የካቲት 18/20112ዓ

ዐውደ ምሕረት
Photo
/Link/ በአረንጓዴ የተቀመጠውን ሊንክ በመጫን የብራና መጽሐፍ ታዳሚ ይሁኑ!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://tttttt.me/brana_Book
https://tttttt.me/brana_Book
📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://tttttt.me/brana_Book
https://tttttt.me/brana_Book
📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖
ዐውደ ምሕረት
Photo
ዐውደ ምሕረት: