ገብርሔር02
<unknown>
ውይይት
#በእንተ_ገብርሔር
ክፍል ሁለት
በወንድሞቻችን
#ዮሴፍ_ዘለቀ
#ኢዮብ_ክንፈ
#ተርቢኖስ_ሰብስቤ
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
#በእንተ_ገብርሔር
ክፍል ሁለት
በወንድሞቻችን
#ዮሴፍ_ዘለቀ
#ኢዮብ_ክንፈ
#ተርቢኖስ_ሰብስቤ
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
Audio
ውይይት
#በእንተ_ገብርሔር
ክፍል ሦስት
በወንድሞቻችን
#ዮሴፍ_ዘለቀ
#ኢዮብ_ክንፈ
#ተርቢኖስ_ሰብስቤ
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
#በእንተ_ገብርሔር
ክፍል ሦስት
በወንድሞቻችን
#ዮሴፍ_ዘለቀ
#ኢዮብ_ክንፈ
#ተርቢኖስ_ሰብስቤ
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
Forwarded from ዐውደ ምሕረት (1ኛ ሳሙ 7:12 αβεпεζεя)
መኑ ውእቱ ገብርሔር ???
ታማኝ አገልጋይ ማነው?
ለእያንዳንዱ እንደ ዓቅሙ፥ ለአንዱ አምስት መክሊት ለአንዱ ሁለት ለአንዱም አንድ ሰጠና ወደ ሌላ አገር ወዲያው ሄደ።
አምስት መክሊትም የተቀበለው ሄዶ ነገደበት ሌላም አምስት አተረፈ፤
እንዲሁም ሁለት የተቀበለው ሌላ ሁለት አተረፈ።
አንድ የተቀበለው ግን ሄዶ ምድርን ቈፈረና የጌታውን ገንዘብ ቀበረ።
ከብዙ ዘመንም በኋላ የእነዚያ ባሮች ጌታ መጣና ተቆጣጠራቸው።
አምስት መክሊት የተቀበለውም ቀረበና ሌላ አምስት መክሊት አስረክቦ። ጌታ ሆይ፥ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ፥ ሌላ አምስት መክሊት አተረፍሁበት አለ።
ጌታውም። መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው።
ሁለት መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ። ጌታ ሆይ፥ ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ፥ ሌላ ሁለት መክሊት አተረፍሁበት አለ።
ጌታውም። መልካም፥ አንተ በጎ፥ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፥ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው።
አንድ መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ። ጌታ ሆይ፥ ካልዘራህባት የምታጭድ ካልበተንህባትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤
ፈራሁም ሄጄም መክሊትህን በምድር ቀበርሁት፤ እነሆ፥ መክሊትህ አለህ አለ።
ጌታውም መልሶ እንዲህ አለው። አንተ ክፉና ሃኬተኛ ባሪያ፥ ካልዘራሁባት እንዳጭድ ካልበተንሁባትም እንድሰበስብ ታውቃለህን?
ስለዚህ ገንዘቤን ለለዋጮች አደራ ልትሰጠው በተገባህ ነበር፥ እኔም መጥቼ ያለኝን ከትርፉ ጋር እወስደው ነበር።
ስለዚህ መክሊቱን ውሰዱበት አሥር መክሊትም ላለው ስጡት፤
ላለው ሁሉ ይሰጠዋልና ይበዛለትማል፤ ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል።
የማይጠቅመውንም ባሪያ በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጡት፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።
ለመሆኑ ታማኝ አገልጋይ ማነው?
ኑሮዬ ይበቃኛል የሚል በተሰጠው ወቶ ወርዶ ነግዶ ያተረፈ በተሰጠው ነገረ ፈጣሪውን ያላማረረ ገብረ ሐካይ ያልሆነ ታማኝ ቸር ገብርሔር ማን ይሆን?

#መዝሙር
#ለንስሐ_ሞት_አብቃኝ
በዘማሪት #ሰብለ_ስፍር
ለንስሓ ሞት አብቃኝ /2/
በሂሶጵ እርጨኝ እጠበኝ
እንደ በረዶ አንጻኝ /2/
አመፃዬ በዛ ኃጢአትን ጨመርኩኝ
ልቤ ደነደነ ክፋትን ፈጸምኩኝ
እንደ ፈርዖን ልቤ እንዳይጸናብኝ
አድነኝ እንደ ኖኅ አምላክ ራራልኝ
አድነኝ /3/ ስለ ድንግል ብለህ አድነኝ
አድነኝ /2/ ስለ ጻድቃን ብለህ አድነኝ
ኃጢአቴም በረታ ሰለጠነብኝ
ከቃልህ አስወጣኝ ሕግህን ጣስኩኝ
እንደ ነነዌ ሕዝብ ንስሓን ስጠኝ
ምሕረትህን ልከህ ልቤን ስበርልኝ
አድነኝ /3/ እንደ ቸርነትህ አድነኝ
አድነኝ /2/ እንደ ምሕረትህ አድነኝ
ያደፈዉ ገላዬን አንተ አጥራልኝ
ከሰዶም ገሞራ እንዳይብስብኝ
መንገድና ሕይወት አንተ ነህ ምራኝ
የቅዱስ ጴጥሮስን ንስሓ ስጠኝ
አድነኝ /3/ እንደ ቸርነትህ አድነኝ
አድነኝ /3/ ስለ እናትህ ብለህ አድነኝ
አድነኝ /2/ ስለ ጻድቃን ብለህ አድነኝ
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
#ለንስሐ_ሞት_አብቃኝ
በዘማሪት #ሰብለ_ስፍር
ለንስሓ ሞት አብቃኝ /2/
በሂሶጵ እርጨኝ እጠበኝ
እንደ በረዶ አንጻኝ /2/
አመፃዬ በዛ ኃጢአትን ጨመርኩኝ
ልቤ ደነደነ ክፋትን ፈጸምኩኝ
እንደ ፈርዖን ልቤ እንዳይጸናብኝ
አድነኝ እንደ ኖኅ አምላክ ራራልኝ
አድነኝ /3/ ስለ ድንግል ብለህ አድነኝ
አድነኝ /2/ ስለ ጻድቃን ብለህ አድነኝ
ኃጢአቴም በረታ ሰለጠነብኝ
ከቃልህ አስወጣኝ ሕግህን ጣስኩኝ
እንደ ነነዌ ሕዝብ ንስሓን ስጠኝ
ምሕረትህን ልከህ ልቤን ስበርልኝ
አድነኝ /3/ እንደ ቸርነትህ አድነኝ
አድነኝ /2/ እንደ ምሕረትህ አድነኝ
ያደፈዉ ገላዬን አንተ አጥራልኝ
ከሰዶም ገሞራ እንዳይብስብኝ
መንገድና ሕይወት አንተ ነህ ምራኝ
የቅዱስ ጴጥሮስን ንስሓ ስጠኝ
አድነኝ /3/ እንደ ቸርነትህ አድነኝ
አድነኝ /3/ ስለ እናትህ ብለህ አድነኝ
አድነኝ /2/ ስለ ጻድቃን ብለህ አድነኝ
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
ቅድስ ጳውሎስ ስለምን ሞኝ ነኝ አለ
1) ስለ ትህትና :- ክርስቲያኖች በኑሯቸው ሁሉ መዐዛ ክርስቶስን የሚሸቱ ክርስቶሳዊ ናቸውና መሪያቸውን ክርስቶስን በኑሮ ሁሉ ይመስሉታል :: እንዲመስሉትም ካሳሰባቸው ነገሮች አንዱ የዋህነት ወይም በፍቃድ ሞኝ መሆን አንዱና ዋናው ነው " ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ " እንዲል ማቴ 11÷ 29 ይህ የክርስቶስ ሞኝነት ካለማወቅ ከቂልነት የመጣ አይደለም ከየዋህነት የመነጨ ነው እንጂ በዚህም በበግ ተመስሏል:: " ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ እንዲሁ አፉን አልከፈተም " ኢሳ53÷1-12
ታዲያ ቅዱስ ጳውሎስም ክርስቶስን በኑሮ ሁሉ መስሎታል ከዛም አልፎ ለታናናሾቹ "፤ እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እናንተም እኔን ምሰሉ። ሲል መክሮናል " 1ኛቆሮ 11÷1 ስለዚህ ከፍጽም ትህትናው የተነሳ እራሱን ሞኝ አለ::ቅዱስ ጳውሎስ እራሱን ሞኝ ብቻ ብሎም አላበቃም ከሁሉ በኃላ ብሎ እራሱን የሁሉ መጨረሻ እንደሆነ ከተናገረ በኃላ ጭንጋፍ ነኝ ብሎ እራሱን ጠርቷል "፤ ከሁሉም በኋላ እንደ ጭንጋፍ ለምሆን ለእኔ ደግሞ ታየኝ። " እንዳለ 1ኛ ቆሮ 15: 8 ይህ ዐይነቱ ትዕትና በቅዱስ ጳውሎስ ብቻ የተገለጠ አይደለም ለምሳሌ እንደ ልቤ የተባለው ቅዱስ ዳዊት እኔ ግን ትል ነኝ ሰውም አይደለውም ብሎ እራሱን አዋርዷል በመሆኑም ይህ የቅዱሳን ሁሉ መገለጫ ነው መዝ 21(22)÷6 "፤ ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል፥ ራሱንም የሚያዋርድ ሁሉ ከፍ ይላል። " ማቴ 23÷12 በመሆኑም እራሱን ለመደበቅ እራሱን ሞኝ አለ፡፡
"፤ ልመካ ብወድስ ሞኝ አልሆንም፥ እውነትን እላለሁና፤ ነገር ግን ማንም ከሚያይ ከእኔም ከሚሰማ የምበልጥ አድርጎ እንዳይቆጥረኝ ትቼአለሁ። " 2ኛ ቆሮ12÷6
2) የዚህች ዓለም ጥበብ ሞኝነት ነውና እርሱ ከዚህ ዓለም የተገኘ በመሆኑ እራሱን ሞኝ ነኝ አለ:- "፤ እንደዚህ ስላለው እመካለሁ፥ ስለ ራሴ ግን ከድካሜ በቀር አልመካም። "
2ኛ ቆሮ12÷ 5
"፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ ብርቱንም ነገር እንዲያሳፍር እግዚአብሔር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤ "
1ኛ ቆሮ1÷ 27
3)በዚህ ዓለም ጥበበኛ ለመሆን ሞኝ መሆን እንደሚገባ ለማስተማር
"፤ ማንም ራሱን አያታልል፤ ከእናንተ ማንም በዚች ዓለም ጥበበኛ የሆነ ቢመስለው ጥበበኛ ይሆን ዘንድ ሞኝ ይሁን። " 1ኛ ቆሮ 3÷18
4) ሁሉን እያወቁ ስለ መንግስተ ሰማያት እራስን ሞኝ ማድረግ ስለሚገባ :-ቅዱሳን ዋርያት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሐዋርያነት ሲመርጣቸው እርሻቸውን ትዳራቸውን ወጥመዳቸውን ቀረጣቸውን ትተው ጨርቄን ማቄን ሳይሉ ተከትለውታል ይህ ለዓለም ሞኝነት ነው ትዳርን መተው ለዓለም ሞኝነት ነው እርሻን መተው ለዓለም ሞኝነት ነው ማጥመድ መነገድ መተው ለዓለም ሞኝነት ነው ቀረጥ መቅረጥን መተው ሞኝነት ነው ለቅዱሳን ግን ጥበብ ነው
"፤ በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ መልሶ። እነሆ፥ እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ፤ እንኪያስ ምን እናገኝ ይሆን? አለው። "
(የማቴዎስ ወንጌል 19: 27) "፤ ኢየሱስም እንዲህ አላቸው። እውነት እላችኋለሁ፥ እናንተስ የተከተላችሁኝ፥ በዳግመኛ ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ፥ እናንተ ደግሞ በአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ስትፈርዱ በአሥራ ሁለት ዙፋን ትቀመጣላችሁ። "
(የማቴዎስ ወንጌል 19: 28) "፤ ስለ ስሜም ቤቶችን ወይም ወንድሞችን ወይም እኅቶችን ወይም አባትን ወይም እናትን ወይም ሚስትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ ሁሉ መቶ እጥፍ ይቀበላል የዘላለምንም ሕይወት ይወርሳል። "
(የማቴዎስ ወንጌል 19: 29)
ስለዚህ ቅዱሳን ሁሉ እያላቸው ስለ ንግሥተ ሰማያት ስለ እግዚአብሔር ሲሉ በዓለም ላይ ምንም እንደሌለው እንደ የዋህ ሁሉ እያላቸው ሁሉ እንደሌላቸው እንደ ሞኝ ሆነው ይኖራሉ
"፤ ያልታወቁ ስንባል የታወቅን ነን፤ የምንሞት ስንመስል እነሆ ሕያዋን ነን፤ የተቀጣን ስንሆን አንገደልም፤ "
(2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6: 9) "፤ ኀዘንተኞች ስንሆን ዘወትር ደስ ይለናል፤ ድሆች ስንሆን ብዙዎችን ባለ ጠጎች እናደርጋለን፤ አንዳች የሌለን ስንሆን ሁሉ የእኛ ነው። "
(2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6: 10)
5) (ከማይረባ ምስጋና) ከከንቱ ውዳሴ ለመራቅ:- ቅዱስ ጳውሎስ እስከ ሦስተኛው ሰማይ የተነጠቀ የበቃ ቅዱስ ሐዋርያ ሆኖ ሳለ ስለ እራሱ ሲናገር ግን በሌላ በሦስተኛ አካል አስመስሎ ተናግሯል ይህም በከንቱ ውዳሴ ከሚመጣ ኪሳራ ለመዳን ጠቅሞታል :: አጠቃቀሙም እራሱን ዝቅ በማድረግ ነው ::
ለታይታ የሚሮጡ ፈሪሳዊያን ተነቅፈዋል ከንቱ ውዳሴም ስለወደዱ ከእግዚአብሔር የሚያገኙት ዋጋ ቀርቶባቸው የሰዎች የማይረባ ምስጋና(ከንቱ ውዳሴ) እንደ ዋጋ ተቆጥሮባቸው ከፈጣሪያቸው የሚያገኙትን ዋጋ አሳጥቷቸዋል ::
"፤ እንግዲህ ምጽዋት ስታደርግ፥ ግብዞች በሰው ዘንድ ሊከበሩ በምኩራብ በመንገድም እንደሚያደርጉ በፊትህ መለከት አታስነፋ፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። "
(የማቴዎስ ወንጌል 6: 2)
"፤ ስትጸልዩም እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ ለሰው ይታዩ ዘንድ በምኩራብና በመንገድ ማዕዘን ቆመው መጸለይን ይወዳሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። "
(የማቴዎስ ወንጌል 6: 5)
...... ይቆየን....
ለሌሎች ጥያቄዎቻችሁ
👇👇👇👇👇👇
@YEAWEDIMERITE
@YEAWEDIMERITE
ዓውደ ምህረት የእናንተ

Forwarded from ዐውደ ምሕረት (Deleted Account)
ኒቆዲሞስ ማነው? ምን ምንስ
አደረገ?
🌕🌖🌗🌒🌑
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ምድር መጥቶ የምስራቹን ቃል ሲያውጅ እስራኤላውያን የተቀበሉት በተደበላለቀ ስሜት ነበር፡፡ በአንድ በኩል ሕዝቡ ለብዙ ዘመናት በባርነት ሲገዛ ስለነበር ከሮማውያን ቅኝ ግዛት ነጻ የሚያወጣቸው መሲህ ይፈልጋሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሕዝቡ ለብዙ ዘመናት በባርነት ቀንበር ስለደከመ ተስፋ በመቁረጥ ተዳክሞ ነበር፡፡
መሲህ ቢመጣ እንኳ ይመጣል ብለው የሚጠብቁት ጦር ይዞ ሰራዊት አስከትሎ ነው ብለው ያምኑ ነበር፡፡ ስለዚህም ነው ክርስቶስን መሲህ ነኝ ብሎ ሲመጣ ለመቀበል ፈቃደኞች አልነበሩም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ጦር ሳይዝ ሰራዊት ሳያስከትል እንዲሁ ባዶ እጁን አርነት ላወጣችሁ መጥቻለሁ እያለ ደጋግሞ ተናግሯልና ነው፡፡ ምንም እንኳ አብዛኛው እስራኤላዊ የክርስቶስን መሲህነት ቢጠራጠርና ባይቀበለውም፣ በፍጹም እምነት እስከ መጨረሻው የተከተሉትም ነበሩ፡፡ ለዚህም ትልቅ ማሳያ የሚሆነን ከፈሪሳውያን ወገን የሆነ ኒቆዲሞስ የተባለ አይሁዳዊ ነው፡፡ቅድስት ቤተክርስቲያንም ይህን ታላቅ ሰው ለማዘከር የዐቢይን ጾም ሰባተኛ እሁድ በእርሱ ስም ሰይማ ታከብረዋለች ፡፡ ተከታዮቿ ምዕመናንም የእርሱን አሰረ ፍኖት እንዲከተሉ ትመክራለች ታስተምራለችም፡፡
ኒቆዲሞስ ማነው?
፩. ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ ነው ዮሐ 3-1
የእስራኤላዊያን ለብዙ ዘመን በባርነት መኖር የሕዝቡን የአኗኗር ሁኔታ ቀይሮታል፡፡በግዞት ጊዜ ከአሕዛብ የቀሰሟቸው አጉል ትምህርቶች በእምነትም በአስተሳሰብም እጅግ እንዲለያዩና እንዲራራቁ ምክንያት ሆኗል፡፡ አይሁዳዊ ሳምራዊ፤ ከአይሁድም ሰዱቃዊ ፣ ፈሪሳዊ ፣ ጸሐፍት ፣ ኤሴያዊ ብለው እንዲከፋፈሉ ከዚህም እጅግ ወርደው ገሊላዊ ናዝራዊ እንዲባባሉ ያበቃቸው ከአህዛብ ጋር የነበራቸውን ግንኙነት ፈር ባለማስያዛቸው ነበር፡፡ ፈሪሳዊያን ደግሞ ሕግን በማጥበቅ ሕዝቡን የሚያስመርሩ ቀሚሳቸውን በማስረዘም እነሱ የማይፈጽሙትን ሕግ በሕዝብ ላይ የሚጭኑ ራሳቸውን ከሌሎች በላይ ከፍ ከፍ የሚያደርጉ አባታችን አብርሐም እያሉ የሚመጻደቁ የአባታቸው የአብርሐምን ስራ ግን የማይሰሩ ክፍሎች ናቸው ዮሐ 8-39፡፡ ታዲያ ኒቆዲሞስ ምንም እንኳ ከፈሪሳዊያን ወገን ቢሆንም ራሱን ከዚህ ሕዝብ ለይቶ ክርስቶስን ፍለጋ በፍጹም ልቡ የመጣ ፈሪሳዊ ነው፡፡ ቀድሞ አባታችን አብርሀምን ከቤተሰብህ ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ሂድ ያለው አምላክ ኒቆዲሞስን ከፈሪሳዊያን ለይቶ ጠራው፡፡ ዘፍ 12
፪. ኒቆዲሞስ የአይሁድ አለቃ ነው ዮሐ 3-1
ሮማውያን ሕዝቡን የሚያሥተዳድሩት ከላይ ያለውን ዋና ሥልጣን ተቆናጠው ታች ያለውን ሕዝብ ደግሞ ባህላቸውን በሚያውቅ ቋንቋቸውን በሚጠነቅቅ አይሁዳዊ ምስለኔ ነው፡፡ አውሮፓውያንም አፍሪካን ለመቀራመት የተጠቀሙበት ስልት ይህን ዓይነት ነበር፡፡ ኒቆዲሞስም ምንም እንኳ ፈሪሳዊ ቢሆን አለቃ እንዲሆን በሮማውያን የተሾመ ባለሥልጣን ነው፡፡
፫. ኒቆዲሞስ መምህረ እስራኤል ነው ዮሐ 3-10
ጌታ ምስጢረ ጥምቀትን በገለጸለት ጊዜ ሲደናገር አይቶ «አንተ የእስራኤል መምህር ስትሆን ይህን አታውቅምን? » ብሎታል፡፡ ይህ የሚጠቁመን ኒቆዲሞስ አለቅነትን ከመምህርነት የያዘ በአይሁዳውያን የታፈረና የተከበረ ሰው እንደነበረ ነው፡፡ መምህር ቢሆንም የሚቀረኝ ያላወቅሁት ያልጠነቀቅሁት ብዙ ነገር አለ በማለት የመምህርነቱን ካባ አውልቆ የተማሪነትን ዳባ ለብሶ ከክርስቶስ ሊማር መጣ፡፡
፬. ኒቆዲሞስ ምሁረ ኦሪት ነው ዮሐ 7-51
አንዳንዴ ሳያውቁ አወቅን ሳይማሩ እናስተምር የሚሉ ደፋር መምህራን አይጠፉም፡፡ ኒቆዲሞስ ግን ከዚህ በተለየ አለቅነትን ከመምህርነት መምህርነትን ከምሁርነት አስተባብሮ የያዘ ዕውቀትን ከትህትና ምሁርነትን ከደፋርነት አንድ አድርጎ የያዘ ሰው ነበር፡፡ የኦሪት ምሁር መሆኑን የሚጠቁመን ደግሞ ከካህናት አለቆች ጋር ያደረገውን ክርክር ባስታወስን ጊዜ ነው፡፡
ኒቆዲሞስ ምን አደረገ?
ለምስጢረ ጥምቀት መገለጥ ምክንያት ሆነ ዮሐ 3 1-21
የአይሁድ የፋሲካ በዓል እየቀረበ ሲመጣ ክርስቶስ ቀኑ እንደደረሰ ለሐዋርያቱ ተናግሮ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፡፡ እንደ ሰውነቱ ሰለቸኝ ደከመኝ ሳይል ሕዝቡን ቀንና ሌሊት በትምህርትና በተዐምራት ያገለግል ነበር፡፡ በዚህ ሰዐት ነው ኒቆዲሞስ በሌሊት ገስግሶ ወደ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመጣው፡፡ በፊቱ ቀርቦም «መምህር ሆይ » ብሎ የእርሱን አላዋቂነት የክርስቶስን ማእምረ ኅቡዐትነት (የተሰወረን አዋቂነት) መሰከረ፡፡ ጌታችንም አመጣጡ ከልብ መሆኑን አውቆ ምሥጢረ ጥምቀትን (ዳግም ውልደትን) ገለጸለት፡፡ ምስጢሩ የኦሪት ምሁር ለነበረው ኒቆዲሞስ ለጆሮ የከበደ ለመቀበል የሚቸግር ሆነበት፡፡ የከበደውን የሚያቀል የጠበበውን የሚያሰፋ አምላክ ምሥጢሩ ለኒቆዲሞስ እንደከበደው ስለተረዳ ቀለል አደረገለት፡፡ ዳግም ውልደት ከእናት ማኅፀን ሳይሆን ከውሃና ከመንፈስ ቅዱስ እንደሆነ አብራራለት ፡፡
አዋቂ ነን የሚሉትን አሳፈራቸው ዮሐ 7-51
ወቅቱ የአይሁድ የፋሲካ በዓል የቀረበበት ጻፎችና የካህናት አለቆች ጌታን ለመያዝ፣ እንደሙሴም ህግ ሊያስፈርዱበት የቋመጡበት ጊዜ ነበር፡፡ የሙሴ ፈጣሪ መሆኑን መቸ አወቁና? የካህናት አለቆች ተሰብስበው ክርስቶስን ለመያዝ በሚመካከሩ ጊዜ ከሙሴ መጽሐፍ ሕግ ጠቅሶ ሊቃውንተ ኦሪትን አፍ ያስያዛቸው እሱ ነበር፡፡በዚህም የተነሳ ሳይስማሙ ወደየቤታቸው እንዲበታተኑ ምክንያት የሆነ ታላቅ ሰው ነው፡፡
ጌታን ለመገነዝ በቃ ዮሐ 19-38
ጌታችን በቀራንዮ አደባባይ ራሱን ለዓለሙ ቤዛ አድርጎ ሲሰጥ እስከ ሞት ከአንተ አንለይህም ያሉት ደቀ መዛሙርቱ ሲበታተኑ ፣ከዮሐንስ በቀር ፣በዘጠኝ ሰዐት ቀራንዮ የነበረ ኒቆዲሞስ ነበር፡፡ከአርማትያሱ ዮሴፍ ጋር ሆኖ የክርስቶስን ስጋ ከአለቆች ለምኖ፣ የገነዘ፣የክርስቶስን ክቡር ሥጋ ከርቤና የእሬት ቅልቅል ያርከፈከፈለት ወደ ሐዲስ መቃብር ያወረደውም ኒቆዲሞስ ነበር፡፡
ከኒቆዲሞስ ምን እንማር?
አትኅቶ ርእስ
በቅዱስ ወንጌል ላይ በተደጋጋሚ የምናገኘው የፈሪሳውያንን ግብዝነትና የጌታችንን ተግሳጽ ነው፡፡ ማቴ 9 10፣ ማቴ 23፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚሆነን የፈሪሳዊውና የቀራጩ ጸሎት ምን ይመስል እንደነበር መመልከት ነው ሉቃ 18 9፡፡ ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ፣ የአይሁድ አለቃ ፣መምህረ እስራኤል ፣ምሁረ ኦሪት ቢሆንም ራሱን ዝቅ አድርጎ ከጌታ እግር ስር ቁጭ አለ፡፡ ሕዝብን ከመምራትና ከማስተማር ይልቅ ቁጭ ብሎ መማር ምንኛ መታደል ነው! ጌታስ በትምህርቱ «ማርያምም መልካም ዕድልን መርጣለች ከእርሷም አይወሰድባትም » ያለ ለዚህ አይደል ሉቃ 10 42፡፡ ብዙዎቻችን ባለን የኑሮ ደረጃ የዕውቀት ደረጃ የስልጣን ደረጃ ራሳችን ሰቅለን የመማር አቅም አጥተናል፡፡ ቁጭ ብሎ መማር ደረጃችንን የማይመጥን የሚመስለንስ ስንቶች እንሆን? አንድ ወቅት አባ መቃርስ ከህጻናት እንቆቅልሽ ለመማር ቁጭ እንዳሉ በእንቆቅልሹም ልባቸው ተነክቶ እያነቡ ወደ በዐታቸው መመለሳቸውን እያወቅን የመማር አቅም ያጣን ስንቶች እንሆን? ማን ያውቃል ከአንድ ሰአት ስብከት ውስጥ እግዚአብሔር ሊያስተመረን የፈለገ አንዲት ዐረፍተ ነገር ቢሆንስ? ትሑት የሚያሰኘው ሳያውቁ አላውቅም ማለት ሳይሆን እያወቁ አላውቅም ማለት ነው፡፡ ሳይማሩ ተምሬያለሁ ማለት ሳይሆን ተምረውም ልክ እንደ ኒቆዲሞስ ለመማር ራስን ዝቅ ማድረግ ነው፡፡
ጎደሎን ማወቅ
መምህርም ምሁርም ሆኖ ቁጭ ብሎ መማር ምን ረብ አለው? ይባል ይሆናል፡፡ ኒቆዲሞስ ምሁረ ኦሪት እንጅ ምሁረ ሐዲስ አይደ

ለም ኒቆዲሞስ መምህረ እስራኤል ዘስጋ እንጅ መምህረ እስራኤል ዘነፍስ አይደለም፡ ክርስትና አለቃና ባሪያን አንድ እንደምታደርግ አያውቅምና የጎደለውን ፍለጋ መጣ ገላ 3 26፡፡ ያለውን ሳይሆን ያጣውን የሞላለትን ሳይሆን የጎደለውን ፍለጋ መጣ፡፡ዕውቀት ብቻውን ምሉእ አያደርግም፡፡ አለቅነትም ቢሆን ገደብ አለው፡፡የሕይወቱን ክፍተት ሊሞላ የሚችል አንድ ክርስቶስ ብቻ ነውና ጎደሎነቱን አምኖ መጣ፡፡ የሚጎድለኝ ምንድን ነው? ብሎ እንደጠየቀው እንደዚያ ሰው ጎደሎን ማመን ምንኛ ታላቅ ነገር ነው ማቴ 18 21፡፡ በአብዛኞቻችን የሚታየውና ክርስትናችንን አገልግሎታችንን ቤተክርስትያናችንን እየተፈታተነ ያለ ችግር ጎደሎዎቻችንን አለማወቅና ምሉእ ነኝ ብሎ ማሰብ ነው፡፡ ምንም እንዳልሆኑ አውቆ ራስን ለክርስቶስ፣ ራስን ለመርዐተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አሳልፎ መስጠት ምንኛ መታደል ነው!
አልዕሎ ልቡና (ልቡናንን ከፍ ማድረግ)
ኒቆዲሞስ ይዞ የመጣው ስጋዊ ህዋሳቱን ነበር፡፡ጌታችን ግን አመጣጡ ለመልካም እንደሆነ አውቆ ለስጋዊ ዕውቀት እጅግ የሚከብደውን ምስጢረ ጥምቀትን ገለጸለት፡፡ መጀመሪያ ይህን ምስጢር ለመቀበል አልተቻለውም ነበር፡፡ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ምስጢሩን ፍንትው አድርጎ ሲያብራራለት ግን ልቡናው ይህን ምስጢር ለመቀበል ከፍ ከፍ አለ፡፡ ምስጢራትን ለመቀበል ልቦናን ከፍ ከፍ ማድረግ ይገባል፡፡የእምነታች መሰረት በስጋ ዓይን ማየት በስጋ ጆሮ መስማት በስጋ እጅ መዳሰስ ብቻ ከሆነ ልክ እንደ እንቦይ ካብ ሆነ ማለት ነው፡፡ ትንሽ ነፋስ ትንሽ ተፅዕኖ ሲያርፍበት መፈራረስ መናድ ይጀምራል፡፡ ኒቆዲሞስም ምስጢሩ መጀመሪያ ቢከብደውም ቅሉ በኋላ ላይ ልቦናውን ወደ ሰማያዊው ምስጢር ከፍ ስላደረገ ምስጢሩ ተገለጸለት፡፡ ቤተክርስቲያንን ሲፈታተኗትና እየተፈታተኗት ያሉ አካላት በሙሉ የስህተታቸው ምንጭ እንደ ግያዝ ከአካባቢያቸውና ከምናየው አካል (ቁሳዊ ዓለም) ውጭ መመልከት አለመቻል ነው 2ነገ 6- 17፡፡ ለዚህም ነው ካህኑ በስርዓተ ቅዳሴ ጊዜ የቁርባኑ ምስጢር እንዲገለጽልን «አልዕሉ አልባቢክሙ (ልቦናችሁን ከፍ ከፍ አድርጉ)» የሚሉን፡፡
የእውነት ምስክር (ስምዐ ጽድቅ) መሆን
ኒቆዲሞስ ያለፍርሐትና ያለ ሃፍረት በካህናቱ ፊት እውነትን መስክሯል፡፡እውነትንና ፀሐይን ፈርቶ የትም መድረስ አይቻልም፡፡ ካህናቱን መጽሐፍ ጠቅሶ እውነትን ተናግሮ አሳፍሯቸዋል፡፡ በመሪዎች ፊት በታላላቅ ሰዎች ፊት እውነትን መመስከር ክርስትናችን የሚያስገድደን ቁም ነገር ነው ሉቃ 12 8፡፡ ቤተክርስቲያን ሰማዕታት እያለች የምትዘክራቸው በሙሉ ለእውነት ብለው ራሳቸውን ለክርስቶስ አሳልፈው የሰጡ ቅዱሳንን ነው፡፡በፍርሐትና በሀፍረት በይሉኝታና በሀዘኔታ እውነትን አለመመስከር በክርስቶስ ፊት ያስጠይቃል እንጅ አያስመሰግንም ማቴ 10 32፡፡ «ለእውነት እንጅ በእውነት ላይ ምንም ማድረግ አንችልም» እንዳለ 2ቆር 13 8፡፡
ትግሃ ሌሊት
እንደ ሌሊት ለመንፈሳዊ ህሊና ለተመስጦ የሚመች ጊዜ የለም ፡፡ ቀን ለስጋ ሲራወጥ የነበረ አካልና መንፈስ ሌሊቱን ለነፍስ በምገዛት ስጋውን መጎሰም አለበት፡፡ ለዚህም ነው ቅድስት ቤተክርስቲያን ቀኑን በቅዳሴ ሌሊቱን ደግሞ በማኅሌት በሰዓታት በኪዳን እግዚአብሔርን ስታምሰግን የምታድረው፡፡ ቅዱስ ማር ይስሐቅ ሌሊትስ ጌታን ለማመስገን የተፈጠረ ድንቅ ጊዜ ነው ያለው፡፡ ጌታችንም ሐዋርያቱን ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ ብሏቸዋል ማቴ 26፡፡ አሁንም ቤተክርስቲያን እንደ ኒቆዲሞስ በሌሊት ገስግሶ ለኪዳን ለማኅሌት ለጸሎት የሚመጣን ምዕመን ትፈልጋለች፡፡
እስከ መጨረሻ መጽናት
ጌታችንን በመዋዕለ ስብከቱ ብዙ ሺህ ሕዝብ ቢከተለውም እስከመስቀሉ አብረውት የነበሩ ጥቂቶች ናቸው፡፡ የተወሰነው ሕዝብ ቀድሞም የተከተለው ለምግበ ስጋ ነበርና ቀራንዮ ላይ አልተገኘም፡፡ ቀራንዮ ላይ ምግበ ነፍስ እንጅ ምግበ ስጋ የለም፡፡ ሌሎችም በቤተሰብ በሀብት በፍርሀት ምክንያትነት መስቀሉ ስር አልተገኙም፡፡ ምንም እንኳ ኒቆዲሞስ በስድስት ሰዐት ባይገኝም የክርስቶስ ስጋ ከነፍሱ በምትለይበት ሰዐት ክርስቶስን ከመስቀል አውርዶ ለሐዲስ መቃብር ያበቃው እሱ ነበር፡፡ በዚህ የመከራ ሰዐት ከዮሐንስና ከእናቱ ከድንግል ማርያም ውጭ ማንም እንዳልነበረ መጻሕፍት ከገለጹልን በኋላ የምናገኛቸው የቁርጥ ቀን ልጆች ዮሴፍንና ኒቆዲሞስን ነው፡፡ ይህም ፈተናውን ሁሉ ተቋቁሞ እስከ መጨረሻው ለመጽናቱ ምስክር ነው፡፡ በክርስትና ሕይወታችንም የምናያቸው ነገሮች ከዚህ የተለዩ አይደሉም፡፡በምቹ ጊዜ የምናገለግል ፈተና ሲመጣ ጨርቃችን(አገልግሎታችንን) ጥለን የምንሮጥ ማር 14-51 ሰበብ አስባብ ፈልገን የምናፈገፍግ ብዙዎች ነን፡፡ ዕውቀት ጣዖት ሆኖበት መሀል መንገድ የቀረው ሀብት ጣዖት ሆኖበት ሩጫ ያቋረጠውን ጊዜ ጣዖት ሆኖበት ቅዳሴ የሚቀረውን ቆጥረን እንጨርሰው ይሆን? ጌታ በትምህርቱ «ለዘአዝለፈ ትዕግስቶ ውእቱ ይድኅን -እስከ መጨረሻው የሚፀና እርሱ ይድናል » እንዳለ ማቴ 2413፡፡ ክርስትና ለጀመሩት ሳይሆን ለጨረሱት ለወጠኑት ሳይሆን ለፈጸሙት የድል አክሊል የምትሰጥ መንገድ እንጅ የመሮጫ መሙን ጠበበን ሩጫው ረዘመብን ለሚሉ ዴማሶች ቦታ የላትም፡፡2ጢሞ 4-9
በአጠቃላይ ከኒቆዲሞስ ህይወት ብዙ ቁምነገሮችን እንማራለን፡፡ የኒቆዲሞስ በሌሊት ገስግሶ መምጣት ለምስጢረ ጥምቀት ትምህርት መገለጥ ምክንያት እንደሆነ ሁሉ በቅዳሴው በኪዳኑ በሰዓታቱ በማኅሌቱ መገኘትና መሳተፍ ረቂቅ የሆነው ሰማያዊ ምሥጢር ፍንትው ብሎ አንዲገለጥልን በምሥጢራት በመሳተፍ ራስን ዝቅ በማድረግ ለታላቅ ክብር እንድንበቃ የእርሱ መልካም ፈቃድ ይሁንልን፡፡ አሜን 👉❤️
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ :-ማህበረ ቅዱሳን መካነ ድህር
ዓውደ ምህረት የእናንተ
አስተያየት ጥቆማና የከበረ ሀሳብዎን በዚህ ይስደዱልን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇

ሦስትነት_ባለው_በእግዚአብሔር.mp3
1.1 MB
#መዝሙር #ሦስትነት_ባለው_በእግዚአብሔር
#በእህታችን #ፋሲካ_ክብሩ
#መሰንቆ #በወንድማችን #ማርቆስ_አለማየሁ
#አጃቢዎች #ወንድሞቻችን #አቤኔዘር እና #ኢዮብ
ሦስትነት ባለው በእግዚአብሔር
ስሙን አምኜ ልዘምር
የመድኃኔዓለም ህማሙን
እንባን በማፍሰስ በሀዘን
እንደ እርሱ ታጋሽ ማንም የለም
ቸሩ አምላካችን መድኃኔዓለም
በጎልጎታ የዓለም ንጉሥ ተንገላታ
አልበደለ እውነተኛው ተሰቀለ ሰጊድ ስብሐት
ድኅነት የሚሰጥ ለፍጥረቱ
የሚገዙለት መላእክቱ
ሁሉን በፍቅር የሚያድነው
ክፉዎች ያዙት ተረባርበው
የሚያዳፉ ውሾች በዙርያው ተሰለፉ
ያለ ዕረፍት አጥንቱ እስኪታይ ገረፉት ሰጊድ ስብሐት
ትዕግስቱ የበዛ ቸርነቱ
የሚመሰገን በፍጥረቱ
ከዓለም ሊያጠፋ የክፋት መርዝ
የአዳምን እዳ ለመሰረዝ
በፈወሰው በጥፊ መታው ያ ክፉ ሰው ሰጊድ ስብሐት
ድኅነትን ሊሰጥ የፈቀደ
በፍቅር ተስቦ የወረደ
ዘላለማዊ ሚሰጥ ጸጋ
አዳምን ሊያድን ከአለንጋ
ግፍ ባልሰራ እየተነሱ በየተራ
ያለዕረፍት አጥንቱ እስኪታይ ገረፉት ሰጊድ ስብሐት
የሁሉ ንጉሥ የዓለም ፈራጅ
በራሱ ፈቃድ ያለ ግዳጅ
ከነገሠበት ከዙፋኑ
ሰይጣንን ሊጥል በስልጣኑ
በፍቅር ነፍሱን ሰዋልን ሞት ሊሽር
ይቅር ባይ ተፈጸመ አለ ኤልሻዳይ ሰጊድ ስብሐት
👇👇👇👇👇👇
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👆👆👆👆👆👆
#በእህታችን #ፋሲካ_ክብሩ
#መሰንቆ #በወንድማችን #ማርቆስ_አለማየሁ
#አጃቢዎች #ወንድሞቻችን #አቤኔዘር እና #ኢዮብ
ሦስትነት ባለው በእግዚአብሔር
ስሙን አምኜ ልዘምር
የመድኃኔዓለም ህማሙን
እንባን በማፍሰስ በሀዘን
እንደ እርሱ ታጋሽ ማንም የለም
ቸሩ አምላካችን መድኃኔዓለም
በጎልጎታ የዓለም ንጉሥ ተንገላታ
አልበደለ እውነተኛው ተሰቀለ ሰጊድ ስብሐት
ድኅነት የሚሰጥ ለፍጥረቱ
የሚገዙለት መላእክቱ
ሁሉን በፍቅር የሚያድነው
ክፉዎች ያዙት ተረባርበው
የሚያዳፉ ውሾች በዙርያው ተሰለፉ
ያለ ዕረፍት አጥንቱ እስኪታይ ገረፉት ሰጊድ ስብሐት
ትዕግስቱ የበዛ ቸርነቱ
የሚመሰገን በፍጥረቱ
ከዓለም ሊያጠፋ የክፋት መርዝ
የአዳምን እዳ ለመሰረዝ
በፈወሰው በጥፊ መታው ያ ክፉ ሰው ሰጊድ ስብሐት
ድኅነትን ሊሰጥ የፈቀደ
በፍቅር ተስቦ የወረደ
ዘላለማዊ ሚሰጥ ጸጋ
አዳምን ሊያድን ከአለንጋ
ግፍ ባልሰራ እየተነሱ በየተራ
ያለዕረፍት አጥንቱ እስኪታይ ገረፉት ሰጊድ ስብሐት
የሁሉ ንጉሥ የዓለም ፈራጅ
በራሱ ፈቃድ ያለ ግዳጅ
ከነገሠበት ከዙፋኑ
ሰይጣንን ሊጥል በስልጣኑ
በፍቅር ነፍሱን ሰዋልን ሞት ሊሽር
ይቅር ባይ ተፈጸመ አለ ኤልሻዳይ ሰጊድ ስብሐት
👇👇👇👇👇👇
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👉 @AwediMeherit 👈
👆👆👆👆👆👆