ዐውደ ምሕረት
3.66K subscribers
932 photos
24 videos
271 files
195 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
“የጽዮን ልጅ ሆይ አትፍሪ እነሆ ንጉሥሽ በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ይመጣል"የተባለው ተፈፀመ
ት.ዘካ 9÷9

ይህ በነቢዩ ዘካሪያስ አስቀድሞ በትንቢት የተነገረ አማናዊ ቃል የተፈፀመው በኢየሩሳሌም ከተማ ደብረ ዘይት አቅራቢያ ቤተ ፋጌ በምትባል መንደር ነው::ጊዜው በግምት 2000ዓመት ገደማ ይሆናል::ከተማዋ በደስታ ታምሳለች የኢየሩሳሌም ከተማ በተለያዮ ጊዜያት ልዮ ልዮ ነገስታት በሰረገላ ተቀምጠው ጎብኝተዋታልች፣ገስተዋታል የዛሬው ግን ልዮ ንጉሥ ነው ስለ ፍቅር ሲል የእሳት ሰረገላውን ትቶ አህያን የመረጠ አበ ትህትና(የትህትና አባት)መድኃኒት የሆነ ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው::ሕዝቡም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመምጣት ላይ እንዳለ ሲያውቅ ሊቀበለው ወጣ አጠገቡም ሲደርሱ ልብሳቸውን በአህያዪቱ ውርንጭላ ላይ አንጥፈው አስቀመጡት፡፡ አንዳንዶች ያልፍበት በነበረ መንገድ ልብሳቸውን እንዳንዶቹ ደግሞ የዘንባበ ዝንጣፊ ያነጥፉ ነበር፡፡ማቴ 21÷1-17 ከፊትና በኋላ ያሉት ብዙ ሰዎችም “ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ! በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው! ሆሳዕና በአርያም!” እያሉ ይጮኹ ነበር።
ሆሳዕና ማለት መድኃኒት ማለት ነው ሕዝቡም እንዲ ማለታቸው አቤቱ አሁን አድን ብሎ መዝሙረኛው ዳዊት የተናገረውን ንግግር ሲገልጡ ነው ።አህያይቱ ተሰርቃ ከነ ልጆ ከነ(ውርንጭላዋ) ታሰረች ነበር ያሰራት ሰው ሌባ ነወ የሌላ ሰው ንብረት እንደ ንብረቱ አድርጎ ከደጃፉ አስሯታልና ሌባው በቤቱ ያቆያት 5ቀን ተኩል ነው" የማታ የማታ እውነት ይረታ" እንዲሉ አበው እውተኛ ፈራጅ በወጣ ጊዜ አህያዋ ከእስራቷ እንድትፈታ አደረገ ::አህያዋ ና ውርንጫላዋ አዳምና ልጆቹ ሲሆኑ ሌባው ዲያቢሎስ ነው: በአሰት ንግግር እግዚአብሔርን ከመሰለ አምላክ ገነት ከምታክል ቦታ ለይቶ ለ5ቀን ተኩልያክል ጊዜ በሲዖል አስሮናል::
5500 ዘመን ሙሉ በእግረ አጋንንት ተይዘን ሰንጨነቅ መድኃኒት ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ማንም አልደረሰልንም ነበርና ስለዚህ በደስታ ተሞልተው የሆሳዕና አሉ ::

ለምን በአህያና በአህያ ወርንጭላ ላይ ተቀመጠ ቢሉ?


እናቲቱ አህያ የብሎይ ውርንጭላይቱ የአዲስ ኪዳን ምሳሌ ናቸው በሁለቱ መቀመጡ ኦሪትን እንዳልሻረ ወንጌልንም እንደሰጠ ሲያጠይቅ አንድም እናቲቱ አህያ ሸክም የለመደች ነች አዲሲቱ ውርንጫይቱ ግን ሽክም ያለመደች የቤተ አሕዛብና የቤተ እስራኤል ምሳሌ ናቸው::ኦሪት ከባድ ወንጌል ግን ቀሊል ናትና አንድም ሕግ የለመዱና ሕግ ያለመዱ እዝቦች ናቸውና:: አንድም አህያ በወለደችሁ ታርፋለች እንዲሉ ኦሪትም በወንጌል ታግዛ ጸንታለችና ነው::ሌላው
👉ፋረስና በቅሎ ለጦርነት ይሁላሉ አህያ ግን አትውልም ጥንት ነቢያት ክፉ ትንቢትና ክፎ ወሬ ይዘው ሲመጡ ማቅ ለብሰው ትቢያ ነስንሰው በፈረስ ወይም በበቅሎ ተቀምጠው ወደ ከተማ ይባሉ መልካም ዜናና ትንቢት ይዘው የመጡ እንደሆነ ደግሞ በአህያ ላይ ተቀምጠው ይመጣሉ ሕዝቡም መቀመጫቸውን አይቶ መልካም ዜና እንዳመጡ ተረድቶ በደስታ ይበቀላቸው ነበርና ጌታችንም መልካም የድኅነት ዜና ሆኜ መጣው ሲል ከቤተ ፋጌ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ በአህያ ላይ ተቀመጠ::
👉በአህያ ተቀምጦ እንደሚመጣ በኦሪት የተነገሩ የኢሳይያስና የዘካሪያስን ትንቢት' ለመፈጸም ነው::(ትንቢቱን ለመፈጸም) ዘካ9÷9
👉ከእኔ ተማሩ እኔ የዋህ በልቤም ትሁት ነኝና እንዳለ ትዕትናን ለማስተማር ማንንም አትናቁ ሲል ማቴ11÷29 ዮሐ13÷1
👉በፈረስና በበቅሎ ያለን ሰው ማንም አይደርስበትም በአህያ ያለን ሰው ግን በቶሎ ይደርሱበታል ስለዚህ እኔ የቅርብ አምላክ ነኝ እንጂ የእሩቅ አምላክ አይደለሁም ከፈለጋችሁን በቅርብ ታገኙኛላችሁ ለማለት በአህያ ተቀመጠ ኤር 23÷23


🌴ሕዝቡ የዘንባባ ዝንጣፊ መያዛቸው🌴

🌿- ይስሐቅ በተወለደ ጊዜ አብርሃም ደስ ብሎት ዘንባባ ይዞ እግዚአብሔርን አመስግኖበታል (የደስታ መግለጫ በመሆኑ አንተ ደስታ የምትሰጥ ሃዘናችንንም የምታርቅ አምላክ ነህ ሲሉ ነው)
🌿- ዘንባባ ደርቆ እንደገና ህይወት ይዘራል የደረቀ ሕይወታችንን የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው
🌿- ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው የሰላም አምልክ ነህ ሲሉ ነው
🌿- ዘንባባ እሾሃማ ነው አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው
🌿- ዘንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጅ ጌታም አንተ ባህርይህ የማይመረመር ነው ሲሉ ነው
🌿- ዘንባባ የነፃነት ምልክት ነው ከባርነት ነፃ የምታወጣን አንተነህ ሲሉ ነው ይህንኑ አርአያ አድርገን እኛም እንዲሁ እናደርጋለን

"እነሆ ዛሬ እኛ ክርስቲያኖች እግዚአብሔር የሰራትን ቀን ይህች ነችና ሐሴትን እናድርግ " መዝ 117 (118) ÷ 24....ይቆየን
እንደ አህያይቱ እኛም ከእስራታችን ሁሉ ተፈተን የሰላም ባለቤት የሆነውን መዳኃኔ ዓለም ክርስቶስን በልባችን ከተማነት የምናሳድር እውነተኛ ክርስቲያኞች ያደርገን ዘንድ የእርሱ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን ለዘለዓለሙ አሜን❤️


ሀሳብ ጥቆማ ጥያቄና አስተያየታችሁን @YEAWEDIMERITE ላይ አድርሱን።

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
እንደምን ዋላችሁልን ውድ የዓውደ ምህረት ቤተሰቦች እነሆ ሰዓቱን ጠብቆ የምን እንጠይቅልዎ ፕሮግራማችን ጀመረ::ከአሁኗ ሰዓት ጀምሮ ባውቀው ቢመለስልኝ የሚሉትን የእርሶን መማንኛውም መንፈሳዊ ጥያቄዎች በአድራሻችን መላክ ይችላሉ::እኛም ከአባቶች የተማርነውን ከመጻሕፍት የቃረምነውን ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን የወረስነውን እንደ አቅማችን ምላሽ እንሰጥበታለን ::ስለ ሁሉም የአምላካችን ፍቃድ የእመቤታችን እረዳትነት አይለየን ለዘለዓለሙ አሜን::🙏


ጥያቄዎቻችሁን በዚህ ይስደዱልን
👇👇👇👇👇👇👇
@YEAWEDIMERITE
@YEAWEDIMERITE

ዓውደ ምህረት የእናንተ
Forwarded from Deleted Account
selam walachehu 'makfl' selmibalw ngr bdnb betngerun ?????
አክፍሎት የሰሞነ ሕማማት አንዱ ሥርዓት መሆኑ ይታወቃል ስለዚህም አክፍሎትን ብቻ ሳይሆን መሰል ተያያዥ ጉዳዮችን(ሥርዓቶችን )ማየቱ ተገቢ ነው

በሰሞነ ሕማማት የሚሰሩ ሥርዓቶች


በዐቢይ ጾም ከሰርክ ሆሳዕና ጀምሮ እስከ ትንሳኤ ሌሊት ያሉት ዕለታት የሚገኙበት ሳምንታት ሰሙነ ሕማማት ይባላል፡፡ ዕለታቱም የዓመተ ፍዳ፣ የዓመተ ኩነኔ መታሰቢያ ናቸው፡፡ በእነዚህ ዕለታት ውስጥ የተለያዩ ትውፊታዊ እና ሃይማኖታዊ ክንዋኔዎች አሉ፡፡ ከነዚህ ክንዋኖዎች ውስጥ አለመሳሳም፣ አክፍሎት፣ ቄጤማ ማሰር፣ ጥብጠባ፣ ጉልባን እና ሕፅበተ እግር ይገኙበታል፡፡ ስለእነዚህ ክንዋኔዎች በቅድስት ቤተ ክስቲያን ስላለው ትውፊታዊ አፈፃፀም መዛግብት አገላብጠን እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡

አለመሳሳም፡–
በሰሙነ ሕማማት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች መስቀል እንደማይሳለሙት ሁሉ መጨባበጥ፣ መሳሳምን የትክሻ ሰላምታ መለዋወጥን አይፈጽሙም፡፡ ሰላምታ የማንለዋወጥበት ምክንያት አይሁድ ጌታን ለመስቀል ሰኞ እና ማግሰኞ መከሩ አልሰመረላቸውም፡፡ ምክረቸው የተፈጸመው ረቡዕ ነው፡፡ ስለዚህ አይሁድ እያንሾካሾኩ እንሰቀለው ፤እንግለው ብለው ይማከሩ ነበር፡፡በዘመነ ፍዳ ወቅት ሠላምና ፍቅር አለመኖሩን የሚገልፅልን በመሆኑ ያንን ለማስታወስ ስላምታ አንለዋወጥም፡፡ መስቀልም አንሳለምም፡፡ ሳምንቱ የክፋት ምክር የተመከረበት እንጂ የፍቅርና የደስታ ሳምንት የታየበት ባለመሆኑ ይህንን በማሰብ ሰላምታ አንለዋወጥም፡፡ አይሁዳ ጌታን በጠላቶቹ ለማስያዝ እኔ የምስመው እርሱ ነው ያዙት ብሎ በሰላምታው ምልክት ሰጣቸው ይህ ሰላምታ አምሐ ቅድሳት አይደለም ተንኮል የተሞለበት እንጂ፡፡ የዲያቢሎስም ሰላምታ ተመሳሳይ ነው፡፡ ሔዋንን ስላም ለኪ ብሎ ነው ያታለላት የይሁዳም ሰላምታ ሰይጣናዊ ነው፡፡ ስለዚህ ይህንን ወቅትና ሁኔታ ለማሰብ በሰሙነ ሕማማት ሰላምታ ልውውጥ የለም፡፡ ዛሬ እየተስተዋለ ያለው ይኽው ሰላምታ ያለመለዋወጥ ሁኔታ ስርወ መሰረቱ ይህ ነው፡፡ ከጥንት ጀምሮ እዚህ ትውልድ ላይ ደርሷል፡፡ ይቀጥላልም፡፡
ሕፅበተ እግር፡-
ጌታ በፍጹም ትህትና የደቀ መዛሙርቱን እግር ያጠበበት፣ ከሐዋርያት ጋር ግብር የገባበትና የክርስትና ህይወት ማሕተም የሆነውን ምስጢረ ቁርባን ያከናወነበት ዕለት ነው ጸሎተ ሐሙስ ሕፅበተ እግር ጌታችን በዚህ እለተ እናንተ ለወንድማችሁ እንዲሁ አድርጎ ለማለት የደቀ መዛሙርቱን አግር በማጠቡ ምክንያት የተሰጠ ምሳሌ ነው፡፡ ይህም የሚያሳየው እኔ ለእናንተ እንዳደረኩ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁና እውነት እውነት እላችኋለሁ ባሪያ ከጌታው አይበልጥም መልእክተኛም ከላከው አይበልጥም ይህን ብታውቁ ብታደርጉትም ብጹዓን ናችሁ፡፡ ዮሐ 13፡16-17 በማለት ትህትናውን አሳይቷል ጌታ በዚህ እለተ የደቀ መዛሙርቱን እግር ሲያጥብ እኔ መምህራችሁ ስሆን እግራችሁን ካጠብኳችሁ አርአዬን ሰጥቻችኋለሁ እናንተም የወንድማችሁን እግር ታጥቡ ዘንድ ይገባል፡፡ ነገር ግን ከእናንተ አንዱ ለሞት አሳልፎ ይሰጠኛል አለ ደቀ መዛሙርቱም ማንይሆን አሉ፡፡ ጌታም ህብስት ቆርሼ፣ ከወጡ አጥቅሼ የምሰጠው እርሱ ነው አላቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ደንግጠዋል ይሁዳን ማመልከቱ ነበር ለጊዜው አልገባቸውም፡፡ ጌታችን መዳኃኒታችን የሐዋርያቶቹን እግር በማጠብ ትሕትናን ካስተማረቸው በኋላ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን የሰጣቸው የኦሪትን መስዋዕት የሻረው እና መስዋዕተ ሐዲስን የሠራው በዚሁ እለት ነው፡፡
አክፍሎት፡-
በሰሙነ ሕማማት እለተ ዓርብ ከስግደት በኋላ ምእመናን በየቤታቸው ጥቂት ነገር ለቁመተ ሥጋ ቀምሰው እስከ እሁድ /የትንሳኤ በዓል/ ይሰነብታሉ፡፡ ይህ አክፍሎት ይባላል፡፡ ከዓርብ እስከ ቅዳሜ ሌሊት ለእሁድ አጥቢያ ማክፈል የብዙዎች ነው፡፡ አንዳንዶች ግን ከሐሙስ ጀምረው ያከፍላሉ፡፡ ይህም እመቤታቸን ያዕቆብ እና ዩሐንስ የጌታን ትንሳኤ ሳናይ እህል ውኃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤ መቆየታቸውን ተከትሎ የመጣ ትውፊት ነው፡፡ ይህንን ትውፊት አስመልክቶ ሄሬ ኔዋስ አውሳብዩስ የተባሉ ጸሀፍተ ሐዋርያት በስሙነ ህማማት ከደረቅ ዳቦ እና ከትንሽ ውሃ በቀር እንደ ማይመገቡ እና ከሐሙስ ጀምረው እንደሚያከፍሉ ጽፈዋል፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን ሐዋሪያት ሌሎቹንም እንዲያከፍሉ እንዳሳሰቡና ከሐሙስ ጀምሮ ያልተቻለው ቢያንስ ከዓርብ ጀምሮ እንዲያከፍል ማዘዛቸውን ጽፈዋል፡፡ የእኛ ቤተ ክርስቲያን ትምህርትም ይኽው ነው፡፡ ቅዳሜ ይበላል ማለት ግን ቅዳሴው ሌሊት ስለሆነ በልቶ እንደ ማስቀደስ እና በልቶ እንደመቁረብ ይቆጠራል፡፡ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ተከታዮችም ይህንኑ ትውፊት ሲከውኑ አያሌ ዘመናት ተቆጥሯል፡፡
ጉልባን እና ቄጠማ፡-
ጉልባን ከባቄላ ክክ፣ ከስንዴ ወይንም ከተፈተገ ገብስ ጋር አንድ ላይ ተቀቅሎ የሚዘጋጀና የጸሎት ሐመስ እለት የሚበላ ንፍሮ ነው፡፡ የጉልባን ትውፊት እስራኤላውያን ከግብጽ ተሰደው በሚነጡበት ጊዜ በችኮላ ስለነበር አቡክተው ጋግረው መብላት ያለመቻላቸውን ሁኔታ ያመለክታል፡፡ ያን ጊዜ ያልቦካው ሊጥ እያጋገሩ ቂጣ መብላት ንፎሮም ቀቅለው ስንቅ መያዝ ተግባራቸው ነበር፡፡ ይህን ለማሰብ በሰሙነ ሕማማት ቂጣና ጉልባን በማዘጋጀት በዓል ይታሰባል፡፡ በጸሎተ ሐሙስ ይህንን መሰረት በማድረግ የሚዘጋጀው ጉልባን እንዲሁም ቂጣ ጨው በዛ ተደርጎ ይጨመርበታል፡፡ ጨው ውሃ የሚያስጠማ በመሆኑ የጌታን መጠማት ያስታውሳል፡፡ ይህ ትውፊታዊ ስርዓት በእስራኤላውያን የመጣ ሲሆን በኢትዮጵያ አብዛኛዎቹን የትውፊት ክንዋኔዎች የብሉይ ኪዳን መነሻ ስላላቸው ስርዓቱ ዛሬም ይከበራል፡፡
ጥብጠባ፡-
በሰሙነ ሕማማት እለተ የዓርብ ስቅለቱ መታሰቢያ ነው፡፡ ምእመናኑ በሰሙነ ሕማማት የሰሩትን ይናዘዛሉ፡፡ ካህናቱን በወይራ ቅጠል ትከሻቸውን እየጠበጠቡ ቀን ከስገዱት ስግደት በተጨማሪ ሌላ ስግደት ያዟቸዋል፡፡ ጥብጠባው የተግሳፅ ምሳሌ ነው፡፡ ጥብጠባው የሚደረግለት ሰው በህማማቱ ወቅት የፈጸማ በደል ወይም ኃጢአት ካለ ይህንኑ በመናገር የስግደቱ
ቁጥር ከፍ እያለ እንዲል ያደርጋል፡፡ ይህ በስቅለተ ቀን የሚፈጸም ስነ ስርዓት ሲሆን ጥብጣቤ ማለት ቸብ ማድረግ ማለት ነው፡፡ ህዝብ ክርስቲያኑ በእለተ ስቅለት ሲሰግድ ሲጸልይ ሲያነብ ከዋለ በኃላ ሰርሆተ ህዝብ (የህዝብ መሰነባበቻ) ከመሆኑ በፊት በወይራ ቅጠል እያንዳንዱን ምዕመን ጀርባ ቸብ ቸብ መደረጉ የጌታን ግርፋት ያስተውሳል፡፡ ማቴ 26፡26 ማቴ 19፡1-3
ቄጠማ(ቀጤማ)፡-
በቀዳም ስዑር ቀሳውቱን ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለ አዋዲ/ እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሳኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠ እና ትንሳኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመኑም ለቤተ ክርስቲን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ ቀጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሰሩበትን ድርጊት የሚያስተውስ ነው፡፡ በዚህ እለት ልብስ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲቆናትን ቄጠማ ተሸክመው ቃጭል ሲቃጭሉ መታየታቸው እለተ ትንሳኤውን ለሚናፍቅ ምእመን ትልቅ ብስራት ነው፡፡
ቄጠማው የምሥራች ምልክት ተደርጐ የተወሰደው በኖህ ዘመን
ከተፈጸመው ታሪክ ጋር በማቆራኘት ነው፡፡ ቅዱስ መጽሐፍ
እንደሚነግረን በጻድቁ ኖኅ ዘመን የነበሩ ሕዝቦች ከሕገ እግዚአብሔር
ውጪ ሆነው እጅግ የሚያሳዝን ኃጢአት በሠሩ ጊዜ በንፍር ውኃ
ተጥለቅልቀዋል፡፡ በወቅቱ ጻድቁ ኖኅ ወደ መርከብ ይዞአቸው ከገባው
እንስሳት መካከል የ
ውኃውን መጉደል ለመረዳት ርግብን በመርከብ
መስኮት አሾልኮ ይለቃታል፤ እርሷም ቄጠማ በአፍዋ ይዛ ትመልሳለች፡፡
ዘፍ.9-1-29፡፡ ኖኅም በዚህ ቄጠማ የውኃውን መድረቅ ተረድቶ
ተደስቷል፡፡
«ቄጠማ»፣ ለጥፋት ውኃ መድረቅ የምሥራች መንገሪያ እንደሆነ
አሁንም በክርስቶስ ሞት ሞተ ነፍስ ከሰው ልጆች ተወገደ ስትል ቤተ
ክርስቲያን ለልጆቿ ቄጠማ ታድላለች፡፡ ምእመናንም የምሥራች
ተምሳሌት የሆነውን ቄጠማ በግንባራቸው ያስሩታል፡፡
የክርስቶስ ተከታዮች ሁሉ ከጨለማ ወደ ብርሃን ከሚያቃጥለው ዋዕየ
ሲኦል /የሲኦል ቃጠሎ/ ወደ ልምላሜ ገነት ጥንተ ማኅደራቸው
መመለሳቸውን በዚህ አኳሃን እየገለጡ በዓለ ትንሣኤን በቅድስት ቤተ
ክርስቲያን ያከብራሉ፡፡


ዐቢይ ምንጭ :-የኦ/ተ/ቤ/ክ
ሰላምሽ ዛሬ ነው
<unknown>
🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴

🌴እንኳን ለበዓለ ሆሳዕና በሰላም🌴

🌴አደረሳችሁ።🌴

🌴 #መዝሙር #ሰላምሽ_ዛሬ_ነው 🌴

🌴#በወንድማችን #ዳዊት_ክብሩ🌴

🌴#መሰንቆ #በወንድማችን
#ሀብታሙ_ሽፈራው
🌴#ክራር #በወንድማችን
#አቤኔዘር_ማሙሸት

ሰላምሽ ዛሬ ነው ኢየሩሳሌም
ወደአንች መጥቷልና አምላክ ዘላአለም/2/ 

ሆሳዕና በአርያም እያሉ ዘመሩ 
ሕፃናት በኢየሩሳሌም 

አንቺ ቤተልሄም የዳዊት ከተማ/2/ 
የሕዝቦችሽ ብርሃን መጣልሽ በግርማ/2 

ኪሩቤል መንበሩን የሚሸከሙለት/2/ 
መስቀል ተሸከመ ሊሆነን መድኃኒት /2/

የኢየሱስን ሕማም ደናግልም አይተው/2/ 
እያለቀሱለት ሄዱ ተከትለው/2/ 

ሆሳዕና እያሉ አመሰገኑት
በኢየሩሳሌም አእሩግ ሕፃናት/2/


🌴 @AwediMeherit 🌴
🌴 @AwediMeherit 🌴
🌴 @AwediMeherit 🌴

🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴
Audio
አሥራ ሦስቱ ሕማማተ መስቀል
በሰሙነ ሕማማት ጠቅለል ባለ መልኩ የምናስባቸው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሕማማት አሥራ ሦስት ናቸው፡፡ እነርሱም አሥራ ሦስቱ ሕማማተ መስቀል ይባላሉ፡፡ ለክርስቲያኖች እነዚህን ሕማማተ መስቀል ማወቅና ዘወትር ማሰብ ተገቢ በመሆኑ እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡
1. ተኰርዖተ ርእስ (ራስና በዘንግ መመታት)፤
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን በዘንግ መመታቱንና መቀጥቀጡን የሚገልጥ ነው፡፡ ‹‹ተኰርዖት›› የሚለው ቃል ኩርዐ -
መታ ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ነው፡፡ ርእስ ደግሞ ራስ ማለት ነው፡፡ አገረ ገዥው ጲላጦስ ‹‹እኔ ከዚህ ጻድቅ ሰው ደም ንጹሕ ነኝ›› ብሎ እጁን ከታጠበ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ገርፎ ለካህናት አለቆችና ለሽማግሎች አሳልፎ ሰጥቶት ነበር፡፡ በአይሁድ ሕግ የተገረፈ አይሰቀልም፤ የሚሰቀል ደግሞ አይገረፍም፡፡ እርሱ ጲላጦስ ግን ከገረፈው በኋላ፣ የበደል በደል፣ እንዲሰቅሉት አሳልፎ ሰጣቸው (ማቴ 27¸24፤ ማር 15¸15፤ ሉቃ 23¸25፤ ዮሐ 18¸39)፡፡
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተላልፎ ከተሰጠ በኋላ የእሾህ አክሊል ጐንጉነው ራሱ ላይ ደፍተውበታል፡፡ ራሱንም በዘንግ መትተውታል (ማር 15¸19)፡፡ የሰው ዘር ከአዳም ጀምሮ በጠላቱ በዲያብሎስ በተጐነጐነ የኃጢአት እሾህ ራሱ ተይዞ ነበርና ይህንኑ ለማስወገድ ከሰማይ የወረደ ሰማያዊ የሆነ ዳግማዊ አዳም ክርስቶስ በጠላቶቹ በአይሁድ ተንኮል የተጐነጐነ አክሊለ ሦክ እንደ ዘውድ ደፋ፡፡ በሲኦል ወድቆ በዲያብሎስ ተረግጦ ራሱ የሚቀጠቀጠውን የሰውን ልጅ ለማዳን መድኃኔዓለም ክርስቶስ ራሱን በመቃ ተቀጠቀጠ፡፡ ከራሱ ላይ በሚወርደው ደም ፊቱ ተሸፈነ፡፡
2. ተፀፍዖ መልታሕት (በጥፊ መመታት)፤
አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እጃቸው በደም፣ ጣቶቻቸው በበደል በረከሰ በአይሁድ እጅ በጥፊ መመታቱን የሚገልጥ ነው፡፡ ‹‹ተፀፍዖ›› የሚለው ቃል ፀፍዐ በጥፊ መታ ከሚለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡
መልታሕት ደግሞ ፊት ጉንጭ ማለት ነው፡፡
ጌታችን ለሊቀ ካህናት ቀያፋ እውነትን መናገር እንደ ስድብ ተቆጥሮበት መላልሰው ፊቱን በጥፊ መትተውታል፡፡ ፊቱንም በጨርቅ ሸፍነው ‹‹ክርስቶስ ሆይ በጥፊ የመታህ ማነው? ትንቢት ተናገርልን›› እያሉ ዘብተውበታል፡፡ በጠላት ዲያብሎስ እጅ ወድቆ በነፍሱ ይቀለድበትና ይንገላታ የበረውን የሰውን ልጅ ለማዳን ብሎ በጠላቶቹ በአይሁድ እጅ ወድቆ ተጐሰመ፤ ተንገላታ፤ በጥፊም ተመታ (ማቴ 27¸27)፡፡ ጲላጦስ አሳልፎ ከሰጠው በኋላም አክሊለ ሦክ በራሱ ላይ አኑረው ቀይ ልብስ አልብሰው ‹‹የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፣ ሰላም ለአንተ ይሁን›› እያሉ እየተሳለቁበት በጥፊ መትተውታል (ዮሐ 19¸2-4)፡፡ አላወቁትም እንጂ እርሱ በመንግሥቱ ሽረት፣ በባሕርዩ ሞት የሌለበት የዘለዓለም አምላክ ነው፡፡
3. ወሪቀ ምራቅ (ምራቅ መተፋት)፤
ርኩሳን አይሁድ በብርሃናዊው የክርስቶስ ፊት ላይ በሚያስጸይፍ ሁኔታ ምራቃቸውን እንደተፉበት የሚገልጥ ነው፡፡ ‹‹ወሪቅ›› የሚለው ቃል
ወረቀ ካለው ግእዛዊ ግሥ የተገኘ ነው፡፡ ትርጉሙም እንትፍ አለ፣ (ተፋ) ማለት ነው፡፡ በነቢዩ በኢሳይያስ መጽሐፍ (ምዕራፍ 5ዐ¸6) ‹‹ፊቴንም ከውርደትና ከትፋት አልመለስኩም›› ተብሎ እንደተነገረ እየዘበቱበት ምራቃቸውን ተፉበት (ማቴ 27¸29-3ዐ፤ ማር 15¸19)፡፡ በኃጢአት የቆሸሸውን የሰውን ሕይወት ለማጥራት የመጣው ንጹሐ ባሕርይ አምላክ ተተፋበት፡፡ በሥራው ከገነት ተተፍቶ፤ ተንቆ፤ ተዋርዶ የነበረውን የሰውን ልጅ ለማዳን ኃጢአትን ይቅር የሚል እርሱ ጌታችን ያለ ኃጢአቱ ተተፋበት፤ ተናቀ፤ ተዋረደ፡፡ እንኳን በአምላክ ፊት በሰው ፊት እንኳን መትፋት እጅግ ያስነውራል፡፡ እርሱ ግን የኃጢአታችንን ነውር ከእኛ ሊያጠፋ ነውር የሆነውን ምራቅ ተቀበለ፡፡
4. ሰትየ ሐሞት ( መራራ ሐሞት መጠጣት)፤
ጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመልዕልተ መስቀል ሳለ ተጠማሁ ባለ ጊዜ መራራ ሐሞት መጠጣቱን የሚገልጥ ነው፡፡ ‹‹ ሰተየ›› ማለት ጠጣ ማለት ነው፡፡ ሐሞት የሚለውም አሞት ተብሎ በቁሙ ይተረጐማል፡፡ በመዝሙር 68 ቁጥር 21 ላይ ‹‹ለመብሌ ሐሞት ሰጡኝ፣ ለጥማቴም ሆምጣጤ አጠጡኝ›› ብሎ ነቢዩ ዳዊትን ትንቢት ያናገረ የነቢያት አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ የመጽሐፉ ቃል ይፈጸም ዘንድ ‹‹ተጠማሁ›› ባለ ጊዜ ሆምጣጤ ተሞልቶበት ተቀምጦ ከነበረው ዕቃ ሆምጣጤውን በሰፍነግ ሞልተው ወደ አፉ አቀረቡለት፡፡ ውኃ አጠጡኝ ቢላቸው በሐሞት የተደባለቀ የወይን ጠጅ ሊጠጣ አቀረቡለት፡፡ ቀምሶም ሊጠጣው አልወደደም (ማቴ 27¸34)፡፡ ጌታችንም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ ‹‹ተፈጸመ›› አለ፡፡ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ (ማቴ 27¸48፤ ማር 15¸36፤ ሉቃ 23¸36፤ ዮሐ 19¸29)፡፡
ቢጠጡት ለዘለዓለም የማያስጠማ ውኃ የሚሰጥ አምላክ፤ የተጠማችውን ነፍስ የሚያረካ ጌታ፤ ለዘለዓለም የሚፈልቅ የሕይወት ውኃ ምንጭ የሚያድል ፈጣሪ በተጠማ ጊዜ የፈጠረውን ውኃ እንኳን የሚያጠጣው የሚያቀምሰውም አላገኘም (ኢሳ 55¸1)፡፡ አርባ ዓመት ሙሉ በቃዴስ በረሃ ኳትነው ለነበሩ አባቶቻቸው ከሰማይ መና አውርዶ የመገባቸው፤ ከአለት ላይ ውኃ አመንጭቶ ያጠጣቸው ክርስቶስ በተጠማ ጊዜ ቀዝቃዛ ውኃ ነፈጉት (ዘዳ 16¸1-2ዐ፤ 1ቆሮ 1ዐ¸3)፡፡ የዝናማት፤ የባሕርና የውቅያኖስ ጌታ በውኃ ጥም ተቃጠለ፡፡
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሲኦል በረሃ ወድቀው በሕይወት ውሃ ጥም የተቃጠሉትን ነፍሳት ለማርካት ሲል እርሱ ተጠማ፡፡ በኃጢአት ወድቀው፣ በበደል ረክሰው፣ በነፍሳቸው ተጐሳቁለው፣ መራራ መከራን የሚቀበሉትንና ምረረ ገሃነም አፉን ከፍቶ ሆዱን አስፍቶ የሚጠብቃቸውን ሁሉ ለማዳን መራራ ሐሞትን ቀመሰ፤ ሆምጣጣውንም ጠጣ፡፡ የመረረውን የሰው ልጆችን ሕይወት ለማጣፈጥ የመረረውን መጠጥ ተቀበለ፡፡
5. ተቀሥፎ ዘባን (ጀርባን መገረፍ)፤
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጀርባው እስኪላጥ ያለ ርኅራኄ የመገረፉን ነገር የሚገልጥ ነው፡፡ ‹‹ ተቀሥፎ›› የሚለው ቃል ቀሠፈ- ገረፈ ካለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ነው፡፡ ‹‹ ዘባን›› ደግሞ ጫንቃ፣ ትከሻ፣ ጀርባ ማለት ነው፡፡ ከላይ እንደተገለጠው የተገረፈ አይሰቀልም፡፡ የሚሰቀል ደግሞ አይገረፍም ነበር፡፡ ጲላጣስ ግን ኢየሱስ ክርስቶስን አስገረፈው፡፡ ከደሙ ንጹሕ ነኝ ብሎ ከታጠበ በኋላ ክርስቶስን ያለ ኃጢአቱ በመግረፍ ለአይሁድም አሳልፎ በመስጠት ‹‹ታጥቦ ጭቃ›› እንዲሉ የታጠበ እጁን መልሶ አቆሸሸው (ማቴ 27¸28፤ ማር 15¸15፤ ዮሐ19¸1)፡፡
መድኃኒታችን መንፀፈ ደይን ወድቆ በእግረ አጋንንት ተጠቅጥቆ በእሳት አለንጋ የሚገረፈውን የሰው ልጅ ለማዳን ሲል ጀርባውን ለግርፋት ሰጠ፡፡ ሥጋው አልቆ አጥንቱ እስኪቆጠር ተገረፈ፡፡ አይሁድ አገረ ገዥያቸው ጲላጣስ ላቀረበላቸው ምርጫ ይፈታላቸው ዘንድ ነፍሳትን ከሲኦል የሚያወጣውን ክርስቶስን ሳይሆን ራሱን እንኳን ከምድራዊ ወህኒ ማውጣት ያልቻለውን ወንበዴውን በርባንን መረጡ፡፡ መገረፍ ይገባው የነበረ በርባን ተለቀቀ፡፡ በነቢዩ በኢሳይያስ ‹‹ጀርባዬን ለገራፊዎች፣ ጉንጬንም ለጠጉር ነጪዎች ሰጠሁ›› (በኢሳ 5ዐ¸6) ተብሎ እንደተነገረ ጀርባውን ለገራፊዎች አሳልፎ ሰጠ፤ ጽሕሙንም ተነጨ፡፡ ይህ ሁሉ የሆነው የሰው ልጅ ከሚያድነው አምላክ ይልቅ የሚገርፈውንና የሚዘርፈውን ወንበዴ መርጦ ስለተገኘ ነው፡፡
6. ተዐርቆተ ልብስ (ከልብስ መራቆት)፤
አምላካችን ኢየሱስ ክርስስቶስ ልብሱን መራቆቱን የሚገልጥ ነው፡፡ ‹‹ ተዐርቆተ›› ማለት ታረዘ፤ ተራቆተ ማለት ነው፡፡ ፀሐይና ከዋክብትን ብርሃን አልብ
ሶ የፈጠረ አምላክ ተራቆተ፡፡ ጸጋውን ለዕሩቃን የሚያለብስ አምላክ ልብሱን ተገፍፎ ዕራቁቱን ቆመ፡፡ ጨለማን ለብሶ ጨለማን ተንተርሶ ይኖር የነበረውን ሰው መልሶ ብርሃን ያለብሰው ዘንድ የብርሃናት ጌታ፣ የጸጋ ሁሉ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ተገፈፈ፤ ተራቆተ፡፡
የሲኦል ወታደሮች የሆኑት አጋንንት የሰውን ልጅ ጸጋ ገፍፈውት ነበርና ጲላጦስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አሳልፎ በሰጣቸው ሰዓት ወታደሮች ልብሱን ገፍፈውታል (ማቴ 27¸27)፡፡ የሰው ልጅ ለቀረበለት ምርጫ የሰው ምላሽ ዘራፊው፤ ገራፊው ወንበዴ በርባን እንዲፈታለት ነበር፡፡ ‹‹አቅረብኩ ለከ እሳተ ወማየ፣ ደይ እዴከ ኅበ ዘፈቀድከ! እነሆ እሳትና ውኃን አቅርቤልሃለሁ፣ እጅህን ወደ ፈቀድከው ስደድ›› ሲባል የሰው ልጅ እጁን ወደ እሳት ሰደደ፡፡
7. ርግዘተ ገቦ (ጎንን መወጋት)፤
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ከሰጠ በኋላ ጎኑን በስለታም ጦር መወጋቱን የሚገልጥ ነው፡፡ ‹‹ርግዘት›› የሚለው ቃል ረገዘ- ወጋ ከተሰኘ የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ገቦ ማለት ደግሞ ጎን ማለት ነው፡፡ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ አጠገብ፣ በግራና በቀኙ ሁለት ወንበዴዎች ተሰቅለው ነበር፡፡ ሥጋቸው በሰንበት በመስቀል ላይ እንዳይኖር ጭናቸው ተሰብሮ እንዲወርዱ አይሁድ ጲላጦስን በለመኑት መሠረት ጭፍሮቹ የሁለቱን ወንበዴዎች ጭን ጭናቸውን ከሰበሩ በኋላ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ሲመጡ ፈጽሞ እንደሞተ አይተው ጭኑን አልሰበሩም፡፡ ነገር ግን ከጭፍሮቹ አንዱ ጎኑን በጦር ስለወጋው ወዲያው ከጎኑ ደምና ውኃ ፈሰሰ (ዮሐ 19¸33)፡፡
አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል ያደርገው ዘንድ ሞተ፤ የሰው ልጅ በዘለዓለማዊ ሞት ተይዞ ነበርና፡፡ ትልቁ ሞት በኃጢአት ምክንያት ከእግዚአብሔር መለየት ነው፡፡ በጌታችን ሞት ግን ሞት ራሱ ድል ተነሣ፡፡ የሞት መውጊያ በሆነ ኃጢአት የሞተውን ሰው ለማዳን ጎኑን በጦር ተወጋ፡፡ በሰው ልቡና ተተክሎ የነበረውን ኃጢአት ከነሥሩ ነቅሎ ስለጣለው ‹‹ሞት ሆይ መውጊያህ የት አለ?›› ተባለ፡፡ የሞት መውጊያው ኃጢአት ነበርና (1ቆሮ 15¸54-55፤ ኢሳ 25¸8፤ ሆሴ 13¸14)፡፡
ከተወጋው የጌታችን ጎን ደምና ውኃ መፍሰሱም የእግዚአብሔርን ልጅነትና የዘለዓለምን ሕይወት አጥቶ የነበረው ሰው ልጅነቱና ሕይወቱ እንደተመለሰለት የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ምክንያቱም ከጎኑ በፈሰሰው ውኃ ተጠምቆ ልጅነትን፣ ደሙንም ጠጥቶ የዘለዓለም ሕይወትን ያገኛልና (ዮሐ 3¸5፤ ዮሐ 6¸54)፡፡
8. ተአሮተ ድኅሪት (ወደ ኋላ መታሠር)፤
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት እጆቹን ወደኋላ የፊጥኝ መታሠሩን የሚገልጥ ነው፡፡ ‹‹ ተአሥሮት›› የሚለው ቃል አሠረ (ሲነበብ ይላላል) ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም አሠረ ማለት ነው፡፡ ‹‹ ድኅሪት ›› የሚለው ቃል ደግሞ ተድኅረ- ወደኋላ አለ ከሚለው ግሥ የወጣ ነው፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጊዜው በደረሰ ሰዓት ራሱን ለአይሁድ አሳልፎ በሰጠባት በዚያች ዕለትና ሰዓት ሻለቃውና ጭፍሮቹ የአይሁድም ሎሌዎች እጁን የኋሊት አሥረው መሬት ለመሬት ጎትተውታል፡፡ አፍገምግመውታል (ዮሐ 18¸12)፡፡
በኃጢአት ሰንሰለት የኋሊት ታሥሮ ጠላት ዲያብሎስ የሚያፍገመግመውን የሰው ልጅ ለማዳን፣ ሰውንም ከኃጢአት እሥራት ይፈታ ዘንድ ሲል መድኃኔዓለም ክርስቶስ በጠላቶቹ በአይሁድ እጅ የኋሊት ታሠረ፡፡
9. አምሥቱ ቅንዋተ መስቀል፤
መድኃኒታችን በመስቀል ላይ የተቸነከረባቸውን ጠንካራ የብረት ችንካሮች (ምስማሮች) የሚገልጥ ነው፡፡ ‹‹ ቅንዋት›› የሚለው ቃል
ቀነወ- ቸነከረ ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ነው፡፡ መስቀል ማለት ደግሞ ዝም ብሎ የቆመ ግንድ ሳይሆን አሁን በየሥፍራው እንደምናየው ምልክት የተመሳቀለ እንጨት ነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቸነከረባቸው አምስቱ ችንካሮች ሳዶር፣ አላዶር፣ዳናት፣ አዴራ፤ ሮዳስ ይባላሉ፡፡ እነዚህም የአምሥቱ አዕማደ ምሥጢራት ምሳሌዎች መሆናቸውን አበው ያስተምራሉ፡፡
ሐዋርያው ቶማስ ከትንሣኤ በኋላ ወንድሞቹ ሐዋርያት ስለ ትንሣኤው በነገሩት ጊዜ ‹‹የችንካሩን ምልክት በዓይኖቼ ካላየሁ፣ ጣቴንም በችንካሩ ምልክት ካላስገሁ፣ በእጄም የተወጋውን ጎኑን ካልዳሰስኩ አላምንም›› ማለቱ በብረት ቀኖት በመቸንከሩ ነበር (ዮሐ 2ዐ¸25)፡፡ መድኃኒታችን በኃጢአት ቀኖት (ምስማር) ተይዞ የነበረውን ሰው ለማዳን በብረት ቀኖት ተቸነከረ፡፡
እንግዲህ አሥራ ሦስቱ ሕማማተ መስቀል የሚባሉት እነዚህ ናቸው፡፡ ድሀ ያይደለ ጌታ፤ ፍጡር ያይደለ የፈጠረውን ሥጋ ገንዘብ ያደረገ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጅ ብሎ ተናቀ፡፡ የሕማም ሰው፤ ደዌንም የሚያውቅ ሆነ፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ፡፡ ሕማማችንንም ተሸከመ፡፡ ይህም የሰውን ልጅ ለማዳን ማለትም እኛን ከደዌ ሥጋ ከደዌ ነፍስ ይፈውሰንና ከሕማመ ሥጋ ከሕማመ ነፍስ ሥቃይ ያሳርፈን ዘንድ ነው፡፡ ቁስለ ኃጢአታችንን ያደርቅልን ዘንድ ስለ መተላለፋችን ቆሰለ፡፡ በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን፡፡ በደላችንን ይደመስስ ዘንድ ስለ በደላችን ደቀቀ፡፡ ሊያረጋጋን ተጨነቀ፡፡ ሊያሣርፈን ተሠቃየ፡፡ አፉንም አልከፈተም፡፡
የእግዚአብሔር የመሥዋዕቱ በግ ኢየሱስ ክርስቶስ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት በሸላቾቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ እንዲሁ አፉን አልከፈተም፡፡ መልካምን እንጂ ግፍን አላደረገም ነበር፡፡ ልብንና ኩላሊትን የሚመረምር አምላክ ወሰብእ ወልድ ዋህድ ኢየሱስ ክርስቶስ በጲላጦስ በተመረመረ ጊዜ በአፉም ተንኮል አልተገኘበትም፡፡ በፈቃዱ ነፍሱን ስለ እኛ መሥዋእት አደረገ፡፡ ፋሲካችን ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሥጋውን ቆረሰልን፣ ደሙንም አፈሰሰልን (ኢሳ. 53¸1-13፤ ዮሐ. 10¸18፤ ዮሐ. 19¸30፤ 1ኛቆሮ. 5¸7)፡፡ በዚህ የተቀደሰው ሳምንት ይህንን የጌታን ውለታና የድኅነት ሥራ እናስተውል፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡


ምንጭ :-ማህበረ ቅዱሳን ዕለተ ቀዳሚት ሰንበት

ዓውደ ምህረት የእናንተ
ጀርመናዊያን ከጀርሙ(virus ) ባሱብን



COVID- 19 እውነትም እያሰተዛዘበን ነው:: ጀርመናዊያን የበሽታውን መድኃኒት አገኝተናል ነገር ግን ፍቱንነቱ ይረጋገጥ ዘንድ አፍሪካዊያን ላይ ሙከራ እንዲደረግ አፍሪካዊያን ወንድሞቻችን ሊተባበሩን ይገባል የሚል ምሁርነታቸውን ጥያቄ ውስጥ የሚከት ጆሮንም ጭው የሚያደርግ ንግግርን አስደምጠውናል ::
እንኳን አይደለም ጥቁር ሕዝብ ላይ ቀርቶ መልኳን መሠረት አድርጎ ጥቁር አይጥ ላይ የማረጋገጫ ሙከራ ማድረግ አጸያፊ ነው ባለ አእምሮም አያሰኝም ምክንያቱም እርሷም ነፍስ ናትና ከእንዲ አይነት ቅስም ሰባሪ ንግግር እራሱ የኮረና ቫይረስ ቢፈጀን ይሻለናል"፤ ጥበበኛ የት አለ? ጻፊስ የት አለ? የዚች ዓለም መርማሪስ የት አለ? እግዚአብሔር የዚችን ዓለም ጥበብ ሞኝነት እንዲሆን አላደረገምን? "
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1: 20)
" እጅግም ስዕለት ይቀዳል አፎት
እጅግም ዕውቀት ያደርሳል ከሞት "
ነገሩ ዘረኝነትን የተላበሰ መንፈስ ያለው መሆኑ ግልጥ ነው ዕውቀታቸው ከዘር አስተሳሰብ ካላወጣቸው ምኑን ባለ አእምሮ ሆኑ
"፤ እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ # ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው፤ ዓመፃ ሁሉ፥ ግፍ፥ መመኘት፥ ክፋት ሞላባቸው፤ ቅናትን፥ ነፍስ መግደልን፥ ክርክርን፥ ተንኰልን፥ ክፉ ጠባይን ተሞሉ፤ የሚያሾከሹኩ፥ ሐሜተኞች፥ አምላክን የሚጠሉ፥ የሚያንገላቱ፥ ትዕቢተኞች፥ ትምክህተኞች፥ ክፋትን የሚፈላለጉ፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥"፤ የማያስተውሉ፥ ውል የሚያፈርሱ፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ምሕረት ያጡ ናቸው፤ "፤ እንደነዚህ ለሚያደርጉት ሞት ይገባቸዋል የሚለውን የእግዚአብሔርን ሕግ እያወቁ እነዚህን ከሚያደርጉ ጋር ይስማማሉ (ወደ ሮሜ ሰዎች 1 : 32
አስቀድሜም እንዳልሁ፥ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም። "
(ወደ ገላትያ ሰዎች 5: 21)
በሕማማት ላይ ሕማማት

ይህ ያለንበት ሰሞን የኮረና ቫይረስ ወረሽኝ የተከሰተበት ብዙ ሺህ ዎችን ወደ ሞት ጉድጓድ ያወረደ ለዓለም ሁሉ ሥጋት የሆነበት ጊዜ ላይ ነን የሚገርመው በቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ ውል ጊዜ በየ ዓመቱ ከሚከበረው የሰሞነ ሕማማት ሳምንት ላይ መግጠሙ ነው ::

እንደ ቤተ ክርስቲያን ትምህርት ሰሙነ ሕማማት የሕማማት ሳምንት ማለት ነው፡፡ ሰሙን የሚለው ቃል “ሰመነ” ስምንት አደረገ ከሚለው የግሥ ዘር የወጣ ነው፡፡ ሕማማት የሚለው ቃል ብዛትን የሚያመለክት ሆኖ “ሐመ” ታመመ ከሚለው የግሥ ዘር የተገኘ ነው:: በዚህ በሰሞነ ሕማማት ታድያ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የጌታችንን ሕማማት ታስባችዋለች የጌታችን ሕማም ሲባል ሰው ሰውኛውን ለእኛ የሚሰማን ዓይነት ሕመም፣ ማለትም የራስ ምታት፤ የሆድ ቁርጠት፤ የእጅ የእግር ቁርጥማት ሳይሆን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ዘር ሁሉ ከዲያብሎስ ቁራኝነት ለማላቀቅና ከሲኦል ባርነት ነጻ ለማውጣት ወዶ ፈቅዶ የተቀበላቸውን ጸዋትወ መከራ የሚያመለክት ነው፡፡

በዚህ ወቅት የተከሰተው ይህወረሽኝ በሳይንሳዊው ስያሜ 2019 Novel corona (COVID -19) እየተባለ ይጠራል የዚህ በሽታ መንስኤ ከሀያላን ሀገራት አንዷ እንደሆነችው በሚታመነው የሩቅ ምሥራት ሀገሯ ቻይና ከምትገነው ሁሀንግ ግዛት ነው ሰበቡም በመጻሕፍ አስቀድመን እንዳንበላቸው የተከለከልናቸውን የማይበሉ እንሰሳትን መመገብ ነው :: ዘዳ11÷114
ቅዱሳት መጻሕፍት ክንፍና ቅርፊት የሌላቸውን እንዲሁም ሰኮናቸው የተሰነጠቀውን እና የሚያመነስኩ(የሚያመነጅጉ) እንሰሳት ብሉ ከዛ ውጪ የሆኑትን ግን አትብሉ ሲል ስማቸውንም ጠቅሰው ነግረውናል :: ታድያ ቻይና ለዚህ ሕመም መንስኤ ለመሆን የበቃችው የመጣችበት ክርስቶስ አልባ ሥልጣኔና የተጋነነ የርሃብ ታሪኳ ያመጣባት ተጽህኖ በግንባር ቀደምትነትጠሊጠቀስ ይችላል ያን የርሃቧን ጊዜ ለማለፍ እባቡን ጊንጡን የለሊት ወፉን አህያውን ውሻውን ከዛም አልፋ የሰው የደረቀ ቆዳ ጫማ የተበላሸ የወንዝ ውኃ መመገቧና መጠጣቷ ነው :: ሕመም ወይም በሽታ እንደ ቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ በሚከተሉት ነገሮች ሊከሰት ይችላል የመጀመሪያው ደዌ ዘኃጢያት ይባላል በኃጢያት ምክንያት የሚመጣ የደዌ ዓይነት ሲሆን ለምሳሌ እንደ ሙሴ እህት ማርያምን እና ዘኁ 12÷10 በአዲስ ኪዳንም መጻጎዕን የመሠለ ድዊ ሰው በአጢያት ምክንያት የታመሙ ሰዎችን ማየት ይቻላል የሕመማቸው ምክንያት ኃጢያት መሆኑ በምን ታወቀ ቢሉ ከተፈወሱ በኃላ ደግማችሁ አትበድሉ ደግማችሁ ኃጢያትን አታድርጉ ተብለዋልና ነው ዮሐ 5÷5 ዮሐ 8÷11 ሁለተኛ ሕማም ወይም ደዌ ደዌ ዘንጽሕ ይባላል በንጽሕና ምክንያት የሚመጣ የደዌ ዓይነት ሲሆን እንደነ ኢዮብ ሳይበድሉ በንጽሕናቸው በፍቃደ እግዚአብሔር የሚመጣ ነው መ.ኢዮ 1÷1 ሦስተኛው ደዌ ዘፀጋ ሲባል ሕማሙ እንደ ጸጋ እንደ ማንቂያ ደውል ሆኖ የተሰጣቸው እንደነማ ቢሉ እንደነ ቅዱስ ጳውሎስ ያለ ነው 2ቆሮ12÷8 ደዌ ዘሰይጣን ሌላኛው የደዌ ዓይነት ነው በእርኩሳት መናፍስት ምክንያት የሚመጣ ነው ማቴ 9÷32 (12÷22) ማር 9÷17 ሉቃ 4÷23 ደዌ ዘክብር (ደዌ ዘሃሴት) የሚሉትም የደዌ ዓይነት አለ እንደ አባታችን እንደ ተክለ ሃይማኖት ያለ ለክብር ለሃሴት የሆነ ደዌ ነው ::

ታዲያ ይህ በዘመናችን የተከሰተው COVID-19 NOVEL CORONA VIRUS ከዘረዘርናቸው የደዌ ዓይነቶች የትኛው የሕማም ዓይነት ወይም በየትኛው ምክንያት የመጣ እንደሆነ ባይታወቅም ከተጠናወተን የዘር ቆጣሪነት የአጥንት ለቃሚነት የመተራረድና የመጠላላት ቤተ ክርስቲያን የማፈራረስ ካህናትን የማረድ ምህመናንን የማፈናቀል የሰውን ልጅ የማፈን እኩይ ተግባራች ምክያት የመጣ ደዌ ዘ ኃጢያት መሆኑን ለመገመት አይቸግርም:: በሽታው ወይም ወረሽኙ በጠባዮ ከሰሞነ ሕማማት ጋር የሚስማማ ነው በሰሞነ ሕማማት የጌታችንን 13ቱን ሕማማት እያሰብን የማንሳሳም የማንጨባበጭ የማንስቅ የማንደሰትበት ወቅት ነው COVID-19 ኝም ከሚተላለፍበት መንገዶች ዋነኞቹ መነካካት፣ መጨባበጥ ፣ መሳሳም ፣ አፍ ለአፍ ገጥሞ ማውራት ነው :: በሽታው የአደጉ ሀገራት ሴራ የላብራቶሪ ውጤት ሊሆን እንደሚችል የሚገምቱ አካላት ኃያሌ ናቸው የCORONA VIRUS የእግዚአብሔር ቁጣ ነውን ወይስ የነ አሜሪካ ቁጣ የሚለው ጉዳይ የራሱ የሆነ ጥናት ወይም መገለጥ የሚጠይቅ ጉዳይ ቢሆነም በሽታው ከተነሳበት ጊዜ ጀምሮ መንግሥት ሕዝቡ እንዳይሰበሰብ ለሰላምታ ማንም ለማንም እጅ እንዳይሰጥ እንዳይሳሳም ላልተወሰነ ጊዜ ከቤት እንዳይወጣና ሥራውን እቤቱ እንዲሰራ እንዲያስገድድ አድርጎታል :: በዚህ ሕመም ሳቢያ ከመንግሥት መሥራ ቤቶች በተጨማሪ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ የአብያተ ክርስቲያናት ሃይማኖታዊ በህላት እንዲታጠፉሁ የአብነት ትምህርተ
ት ቤት ወንበር እንነሳ አድርጓል ጊዜው ደግሞ ሰሞነ ሕማማት ጊዜ በመሆኑ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ያደርገዋል:: ለዚህም ነው የጽሁፋችን ርዕስ በሕማማት ላይ ሕማማት ያልነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ጊዜ የማዳኑን ሥራ ፈጽሞልናል ከዚህች በዕለተ አርብ ከተፈጸመልን የድኅነት ሥራ ተሳታፊዎች ለመሆን እንድንችል ግን እኛም የራሳችን የሆነ ድርሻ አለን ሰው በነፍሱ ይድን ዘንድ ሥጋውን አስቀድሞ ከሥጋ በሽታ ይታደግ ይገባዋል በርግጥ ሰው CORONAም ሆነ በHIV ወይም በሆድ ሕመም ታሞ ቢሞት CORONA እና HIV የያዘው ሲዖል በአንቤባና በተቅማጥ የሞተ ደግሞ ገነት ይግባ አይባልም በአጥሩ ሰው በሕመም ተይዞ ታሞ መሞቱ ከድኅነት አያጎለውም ግን ንስሐ ሳይገባ ከአምላኩ ሳይታረቅ ወደ ገሐነም እዲወርድ ምክንያት ሊሆን ይችላል በመሆኑም ለሥጋን ጤና መጠበቅ ለነፍስም ጭምር ይጠቅማል ሰው እግዚአብሔር ከፈፀመለት የድኅነት ሥራ ተሳታፊ ይሆን ዘንድ ማድረግ ያለበት የራሱ ድርሻ እንዳለው ቅዱሳት መጻሕፍት አስተምረውናል ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በፊልጵስዮስ መልዕክቱ እንዲ ብሏል "፤ ስለዚህ፥ ወዳጆቼ ሆይ፥ ሁልጊዜ እንደ ታዘዛችሁ፥ በእናንተ ዘንድ በመኖሬ ብቻ ሳይሆን ይልቁን አሁን ስርቅ፥ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤ " (ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2: 12) ከአስከፊው የCORONA VIRUS ይድን ዘንድ ለነፍሱም ድኅነት አሰተዋጽኦ ያደርግ ዘንድ የባለ ሙያዎችን ምክር መፈጸም ተገቢ ነው በየ ጊዜው እጅን በሳሙና መታጠብ የእራስን መዳን መፈጸም ነው አካላዊ እርቀትን መጠበቅ የእራስን መዳን መፈጸም ነው አለመሰብሰብ አለ መተፋፈግ የራስን መዳን መፈጸም ነው ሲስሉ(ሲያስሉ) በክርን አፍንና አፍንጫን መሸፈን የራስን መዳን መፈጸም ነው ከቤት አለመውጣት የራስን መዳን መፈጸም ነው ::የእራሳችንን መዳን እንፈጽም ለዚህም የልዑል እግዚአብሔር ቅዱስ ፋቃዱ እና የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃና ጸሎት ከኛ ጋር ይሁን ቤተ ክርስቲያንንም ከዚህ የበለጠ በሕማም ላይ ሕማም እንዳይደራረብባት በንስሐ ወደ ፈጣሪያችን ተመልሰን በንጽሕና ሆነን እንመላለስ አሜን ይቆየን
"፤ በእርሱ እኖራለሁ የሚል እርሱ እንደ ተመላለሰ ራሱ ደግሞ ሊመላለስ ይገባዋል። "
(1ኛ የዮሐንስ መልእክት 2: 6)
ስለ ከበረው ሃሳብዎ ጥቆማና አስተያየቶ ይህ ይጠቀሙ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@YEAWEDIMERITE
@YEAWEDIMERITE


አዘጋጅ:- ተርቢኖስ ሰብስቤ ኃ/ማርያም
ሚያዝያ06/2012ዓ.ም ዕለተ
Forwarded from ዐውደ ምሕረት