ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
929 photos
24 videos
271 files
192 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
ከሞተ ሰው አፍ ውስጥ ጽጌ ሬዳ አበባ በቅሎ ተገኘ
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
ከኢየሩሳሌም በቅርብ እርቀት ላይ በምትገኘው በኢያሪኮ ደሰት የሚኖር እመቤታችንን እጅግ አብዝቶ የሚወድ ስመ " አስቴራስ " የሚባል አንድ ዲያቆን ነበር ከሴቶች ሁለ ተለይተሽ #የተባረክሽ_ድንግል_ማርያም_ሆይ_አምላክን_በድንግና_ጸንሰሽ_በድንግልና_ትወልጃለሽና_ደስ_ይበልሽ እያለ #ቅዱስ_ገብርኤል_ያበሰራትንና ያቀረበላትን ሠላምታ ሳያቆርጥ ዘወትር ይጸልይ ነበር :: ሉቃ 1÷26 -29
ከዕለትም በአንዲቱ ቀን ለሥራው ወደ እሩቅ ሀገር ሲሄድ እርህራኄ የሌላቸው ሰዎች በመንገድ አገኙትና ገድለው ሳይቀብሩት ሄዱ። ነገር ግን ሊሎች ሰዎች በመንገደድ ሲያልፉሁ አስክሬኑን አይተው ከመንገዱ ጥግ መቃብር ቆፍረው ቀብረውት ሄዱ።
ከተቀበረም ከሦስት ቀይ በኃላም ክፉ ሰዎች ባሉባት በዚያች ሀገር ባለች ቤተ ክርስቲያን ቅንነት ለሚያገለግል አንድ ዲያቆን እመቤታችን በእራይ ተገልጻ ወዳጄ ሆይ ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለገለና ጸሎቱ በእኔና በልጄ ዘንድ እጅግ የተወደደችለት አንድ ዲያቆንን ስለገደሉት ሰዎች አዝኛለሁ ጓደኞችህ ዲያቆናትን ይዘህ በመንገድ ጥግ ወደ ተቀበረው ዲያቆን ሂዱና መቃብሩን ቆፍራችሁ አስክሬኑን አውንታችሁ በቤተ ክርስቲያን ቅጥር ቅበሩት አለችው ። ዲያቆኑም እመቤታችን እንደ ነገረችው አጓደኞቹ ጋር ሄዶ መቃብሩን ቆፍረው አስክሬኑን ባወጡ ጊዜ " #ርሔ " እንደሚባል ሽቶ መዐዛው እጅግ ደስ የሚያሰኝ ከአፉሁ የበቀለ አንድ የጽጌ ሬዳን አበባ አገኙ " #መንክር_እግዚአብሔር በላይለ ቅዱሳኒሁ " # እግዚአብሔር_በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው " ተብሎ በነቢይ የተነገረውንም አስበው ፈጽመው አደነቁ መዝ 67÷ 65 ክዎች ሰዎች ከገደሉት ከዲያቆን "አስቴራስ " አስክሬን አፍ የጽጌ ጌዳ አበባ በቅሎ መገኘቱን ያዮና የሰሙ ሰዎችም ሁሉ ይህስ ከዚህ በፊት በዐይናችን ያላየነውና በታሪክም ያልሰማነው አዲስና አስደናቂ ነገር ነው እያሉ በማድነቅ ለዲያቆን እንደሚገባ አድርገው እንደ ሥርዓቱ አክብረው በቤተክርስቲያን ቅጥር ቀበሩት ::
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
ልመና ክብሯ አማላጅነቷም እስከ ዘላለሙ ድረስ ከና አይራቅብን አሜን!
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
ምንጭ:-
በምሥራቅ ጎጃም ሞጣ ደብረ ገነተ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ያለ የብራና ተአምረ ማርያም ገጽ 223 ጠቅሶ የጻፈው ማህሌተ ጽጌ የተሰኘው ትንሽዬ መጻሕፍ ነው
👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
ኃ/ማርያም
ጥቅምት 2/2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
     +++🙏  የጉጠቱ ፍም 🙏+++
 🙏 እግዚአብሔርን በመለኮቱ ልዕልና ያየው ማንም የለም ነገር ግን እርሱን መስለው ለኖሩ ቅዱሳን በአቅማቸው ልክ ይገለጥላቸዋልያናግራቸውማል።
ለአብርሃም በሽማግሌ ፣ ለሙሴ በሃመልማል እንዲሁም ለእነ ዳንኤል ዕዝራ ኢሳይያስ አይቶ በቃላት ድርድር ማስረዳት በማይቻልበት ክብር ተገልጦላቸዋል።
    🙏የጉጠቱን ፍም ስናስብ ከክርስቶስ ልደት በፊት ንጉስ ዖዝያን የሞተበትን ዓመት እናስታውሳለን መጽሐፍ እንደሚነግረን የይሁዳ ሕዝብ እስራኤልን እንዲመራ ዖዝያንን ገና የ16 ዓመት ጎልማሣ እያለ ነበር የቀቡት የንግስናን ዘውድ ደፍተው የወርቅ ካባን የደረቡለት።በንግስናውም ዘመን መልካሙንም ክፋውንም አሳልፏል።ከፍልስጥኤማውያን ጋር በነበረው ጦርነት እግዚአብሔር ረድቶት እነርሱን ድል አድርጎል በኋላ ዝናው እና ስሙ በዓለም ሁሉ ተሰማለት በደስታውም ተነሳስቶ ሦስት መቶ ሰባ ሺ አምስት መቶ ለሚሆኑ ጭፍሮቹ ልዩ ልዩ የሆኑ ጋሻና ጦር ቀስቶችን ሰርቶ አስረከባቸው ነገር ግን ይህን ሁሉ የስኬት ጫማ ሲጫመት የረዳውን አምላክ በመዘንጋቱ ልቡ ታበየ አምላኩንም በደለ በዙፋኑ በቀኝ አብሮት የሚቀመጠውን ካህኑን አዛርያስን ለምን በቀኜ ትቀመጣለህ በማለት ሠማያዊ ወምድራዊ ሥልጣን ካለው ጋር ይፎካከር ጀመረ እርሱም መልሶ "ካህን ይነብር በየማንከ(ካህናት በቀኝ ይቀመጣሉ)" ይልብሀል ህጉ ይለውና ደንቡን ነግሮ ዝም የስብለዋል ቀኝ የክብር መገለጫ ነውና።ኋላ ግን ዖዝያን በድፍረት ቤተመቅደስ ገብቶ ያለ ሥልጣኑ በዕጣን መሰዊያ ላይ አጠነ ያኔ እግዚአብሔር አምላክ በለምጽ መታው ከሰው ተለይቶ  በተለየ ቤት ለምጻም ሆኗልና ተቀመጠ ጊዜውም ደረሰና የንግስናውን ዘውድ ለልጁ አስረክቦ ከዚች አለም በሞተ ተለየ።
     🙏ንጉስ ዖዝያን በሞተበት አመት ልጁ ኢዮአታም በምትኩ በነገሰበት ዘመን ነበር ነብዮ ኢሳይያስ እግዚአብሔርን ከፍ ባለ በሚያስፈራ ዙፋን የልብሱ ዘርፍ መቅደሱን ሞልቶት የተመለከተው። ቅዱሳን የቅድስናቸው ደረጃ ጥግ ሲደረስ እግዚአብሔርን የማያት ክብር ላይ ይደርሳሉ። እንዴት መታደል ነው! እግዚአብሔርን ማየት! ማነው ይህንን ክብር'ስ የማይፈልግ? ነቢዩ በዙፋኑ ላይ ለማመን የሚከብዱ ከሰው ልጅ አዕምሮ በላይ የመጠቁ ዕጹብ የሚያስብሉ ድንቆችንም ተመልክቷል፤ሃያ አራቱ ካህናተ ሠማያ ስድት ክንፍ ያላቸው በመቅደሱ ዙሪያ ረበው አንተን ማየት አይቻለንም ሲሉ በሁለቱ ክንፋቸው ፊታቸውን ይሸፍናሉ በአንተ ፊት መቆም አይቻለንም ሲሉ በሁለቱ ክንፋቸው እግራቸውን ሸፍነው በቀሪው ሁለት ክንፋቸው እየበረሩ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ ያመሠግናሉ። ምግባቸው መጠጣቸው ህይወታቸው ምስጋና! የእኛስ ህይወት? በምስጋና የተሞላ ወይስ በማማረር? መልሱን ለእራሳችን ። የሚደንቀው ነገር ሱራፌልም እኛም እርሱን ብናመሰግን ለእግዚአብሔር የምንጨምረው የምንቀንሰው ባለመኖሩ ነው ይልቁንስ አመስግነን መንግስቱን እንወርሳለን እንጂ።
🙏በመላእክቱ የምስጋና ቃል ጩኸት የመድረኩ መሠረት ተናወጠ ቤቱም በጢስ ተሞላ ነብዪም ተጨነቀ እጅግም ፈራ “እንዲህም ሲል ተናገረ፦ ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው በመሆኔ፥ ከንፈሮቻቸውም በረከሱባቸው ሕዝብ መካከል በመቀመጤ ዓይኖቼ የሠራዊትን ጌታ ንጉሡን እግዚአብሔርን ስለ አዩ ጠፍቻለሁና ወዮልኝ! "
ትሁት አነጋገር! እግዚአብሔርን አይቻለሁ በቅቻለሁ ብሎ አልታበየም ነብዩ ኢሳይያስ ዖዚያን ከብርያለው ገንኛለሁ ብሎ እንደታበየ ይልቁን እራሱን ከነፈሮቻቸው በረከሱባቸው ሰዎች ጉባኤ መሀል ወረወረ ራሱን ዝቅ አደረገ የሠራዊት ጌታ ዝቅታውን ፀፀቱን ተመልክቶ አንዱን ሱራፌል ላከለት ያም መልአክ በእጁ ከመሠዊያው በጉጠት ፍም ወስዶ አፋንም ዳሰሰለት ቀጠለና ታላቅ የድኅነት ቃል አሰማው " እነሆ፥ ይህ ከንፈሮችህን ነክቶአል፤ በደልህም ከአንተ ተወገደ።” በነብዩ ኤርሚያስ የተነገረው “እግዚአብሔርም እጁን ዘርግቶ አፌን ዳሰሰ፥ እግዚአብሔርም፦ እነሆ፥ ቃሌን በአፍህ ውስጥ አኑሬአለሁ” የሚለው ትንቢት ተፈጸመ።
     🙏+ ጌታ ሆይ እንደ ነብዩ የተተረኮሰ አንደበት ስጠን ለእርሱም የላከውን ፍም እሳት ላክና ከአርያም የሚያቃጥለንን በደል ኃጢአት የሚያሰራንን በውስጣችን ያለውን እንክርዳድ አቃጥልልን። +
    15/02/2014
     ድሬዳዋ ኢትዮጵያ
       ተጻፈ በባሮክ ዘ አሚን
ዐውደ ምሕረት
Photo
እንግዲህ ምን እንላለን!
#ከጸሎተኛው_አፍ_በሚወጣ_አበባ ያመኑ ሽፍቶች
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
ከሮም ነገሥታት ወገን የሆነ ስሙ ዘካሪያስ የሚባል ጎልማሳ ሰው ነበር ከዕለታት አንድ ቀን #ቤተ_ክርስቲያን ገብቶ #ከእመቤታችን ሥዕል ፊት ሲጸልይ ከሥዕሏ ማማር የተነሳ እጅግ ደስ አለውና ለዚህች ሥዕል ምን ዐይነት እጅ መንሻ ላቅርብላት እያለ ሲያወጣና ሲያወርድ ወራቱ የጽጌ ጌዳ ወራት ነበርና ፶ (50) የጽጌ ጌዳ አበባ ወስዶ ዘውድ አስመስሎና አክሊል ሰርቶ ከሥዕሏ እራስ ላይ ወስዶ በክብር አቀዳጃት ይህ ሰው እንዲ እያደሰገ ሲጸልይ ከቆየ በኃላ የጽጌ ወራት ባለፈ ጊዜ ግን ለሥዕሏ ክብር የሚያቀርብላት የጽጌ ሬዳ አበባ በማጣቱ እጅግ አዝኖ ወደ #ቤተ_ክርስቲያን ሄደና #እመቤቴ ሆይ የጽጌ ሬዳ፣ የአበባ ወራት እንዳለፈ አንቺ ታውቂያለሽ በ፶ (50)ው የጽጌ ሬዳ አበባ ፈንታ (ምትክ) ፶ (50)ጊዜ #በሠላመ_ቅዱስ_ገብርኤልን የሚለውን ጸሎትሽን ወይም ሠላምታሽን እጸልያለው በማለት እንዲ አለ " #እመቤቴ_ማርያም_ሆይ_በመላእኩ_በቅዱስ_ገብርኤል_ሠላምታ_ሠላም_እልሻለሁ_እግዚአብሔር_ካንቺ_ጋር_ነውና_ደስ_ይበልሽ " እያለ በየቀኑ ፶ (50) ጊዜ ሲጸልይ ኖረ ።
ከዕለታት አንድ ቀን ግን እረስቶ ይህችን ጸሎት ሳያደርስ መንገድ ጀመረ በመንገድም እያለ ይህችን ጸሎት አለማድረሱ ታወሰውና ጉዞውን ገታ አድርጎ ከመንገድም ወጣ ብሎ እንደ ቀድሞው እየሰገደ ሠላምታዋን ፶ (50) ጊዜ በጸሎት ማድረስ ቀጠለ ሲጸልይም ከአፉሁ በእያንዳንዱ ሠላምታ አንድ አንድ ጽጌ ሬዳ አበባ ይወጣ ነበር። #እመቤታችንም አበባው ፶ (50) እስኪሞላ ድረስ ከአፉሁ እየተቀበለች በክንዷ ሰብስባ ትታቀፈው ነበር :: በአካባቢው የነበረ የሽፍቶች አለቃ የሆነ አንድ ሰው ይህንን አይቶ ዘካሪያስ ጸሎቱን እስኪ ጨርስ ድረስ ከአፉሁ የሚወጡትን የጽጌ ሬዳ አበቦች ይቆጥር ጀመር። ዘካሪያስም ጸሎቱን ሲጨርስና አበባዎቹም ፶ ሲሞሉ #እመቤታችን ባርካው አበባዎቹን ይዛ ወደላይ ስታርግ ይህ የሽፍቶች አለቃ አይቶ እጅግ አደነቀና ጓደኛቱይ ጠርቶ " የጌታን ተአምራት ታዮ ዘንድ ኑ " ተብሎ እንደ ተጻፈ "የእመቤታችንን ተአምራት ያዮ ዘንድ ኑ " ብሎ ወደ ዘካሪያስ ወሰዳቸው መዝ 45÷8 ሽፍቶቹም ዘካሪያስን ይህ ድንቅ ተአምራት ምንድ ነው? ብለው ጠየቁት እርሱም እኔ ኃጢያተኛ ከመሆኔ በቀር ሌላ በጎ ሥራ የለኝም ነገር ግን የሠማይና የምድር ንግሥት የሆነች አምላክን በድንግልና ጸንሳ በድንግልና የወለደች የእመቤታችንን በሠላመ #ቅዱስ_ገብርኤል_መላእክ ሠላም እልሻለሁ እያልኩ #በቅዱስ_ገብርኤል ሙሉ ሰላምታ በየ ቀኑ ፶ ( 50)ጊዜ ሠላም እላታለሁኝ አላቸው በዚህ ጊዜ ደስ ብሏቸው ዘካሪያስን ሸኙት እነርሱም ከዛች ቀን ጀምሮ ከክፉሁ ሥራቸው ተመልሰው ወደ ገዳም ሄደው በምንኩስና ሕይወት ተወስነው መኖር ጀመሩ::
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
ምንጭ:-
በምሥራቅ ጎጃም ሞጣ ደብረ ገነተ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ያለ የብራና ተአምረ ማርያም ገጽ 223 ጠቅሶ የጻፈው ማህሌተ ጽጌ የተሰኘው ትንሽዬ መጻሕፍ ነው
ኃ/ማርያም
ጥቅምት 2/2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
“አንቺ ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሽ፥ ተመለሽ፤ እናይሽ ዘንድ ተመለሽ፥ ተመለሺ..።”
#መኃልየ. 7፥1

አዎን ገጸ ምሕረትሽን ወደ አስራት ሀገርሽ ወደ ኢትዮጵያ መልሺ🙏 ተመለሽ እንደ በደላችንም አትሽሺ🙏
ዐውደ ምሕረት
Photo
#ከአልጋ የዋለች ሀገር

የተጻፈ ትዕዛዝ ሳይሰጥ ለምድሩ
ጸንታ የተገኘች በእምነት በምግባሩ
የጲጢፋራን ሚስት ዓለምን ሳትሰማ
ከኃጢአትን እልፍኝ ገብታ ሳትስማማ
የዝሙትን ግብዧ ከቶ ያልተቀበለች
ኢትዮጵያ ኮ ታማኝ ዮሴፍን እኮነች
ታድያ ምን ይዟት ነው ከአልጋው የዋለች?
#እግዚአብሔር በሰጣት ሙሴም በሰራት
ስታቀርብ የኖረች ምሰዋይተ ኦሪት
አፍስሳም የማታውቅ የወንጌላዊ ደም
ማረፊያም የሆነች የቅዱሳን ወደብ
ታዲያ ለምድነው? መጻጉዕ መሆኗ
ሰው አጥታ እንደሆ ክርስቶስ ቶሎና
ይጽናላት ጉልበቷ ትዳን ከደዌዋ
በተራው ይታዘል የብረት አልጋዋ
#እመ_ብርሃንም_ነይ_ድንግል አዛኝቱ
ተኝታልሻለች ያቺ እመቤቲቱ
የዲያብሎስ ጭፍራ ሰልፈኛው በረታ
ጠይቂያት በምሕረት ጎብኛት በይቅርታ

ኃ/ማርያም
አ.አ ኢትዮጵያ
ህዳር 15/2013ዓ.ም
#ከቅዱስ_ሚካኤል_የተማርነው
________________________

"# እኔ_የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ" ኢያሱ 5÷14
ከሊቀ ነቢያት ከሙሴ ቀጥሎ ሕዝበ እስራኤልን ይመራ የነበረው ኢያሱ ነው። ኢያሱ ማለት መድኃኒት ማለት ነው። በትርጉም ኢየሱስ ከሚለው ጋር አንድ ነው። የባሳንን ንጉስ አግን የአሞራዊያንን ንጉሥ ሴዎንን በእግዚአብሔር እረዳትነት በጦርነት ገጥሞ ድል የነሳቸው ጽኑ የእስራኤል መሪ ነበር ። በሰባት ግንብ ታጥራ የነበረችሁ አሮጊቷ ከተማ ኢያሪኮ በደረሰ ጊዜ ግን ይህቺን ከተማ ደግሞ እንዴት ድል ነስቷ ይይዛት ዘንድ እንደሚችል ሀሳብ ገብቶት ግንቧን ተጠግቶ ቁጭ ብሎ ሲያወጣና ሲያወርድ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካዬል የተመዘዘ ሰይፍ በያዘ ጎበዝ ሰው አምሳል ተገልጦ ታየው ኢያሱም ቀርቦም እንዲህ ሲል በችኮላ መላእኩን ጠየቀው " ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ?
" ሊቀ መላእክ ቅዱስ ሚካኤል ግን እንዲህ ሲል መለሰለት “አይደለሁም፤ እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ" አለው ። ይህን ጊዜም ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደለት” ኢያሱ 5፥14 የእግዚአብሔር ሰው የኢያሱ አመጣጥ ወገንተኛነትን ለመጠየቅና ለማወቅና በተሞላ መንፈስ ነበር ።የእግዚአብሔር መላእክ ቅዱስ ሚካኤል ግን እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት ነኝ እንጂ ከእናንተ ወይም ከጠላቶቻችሁ ወገን ነኝ አደለውም ብሎ ልቡን አሳረፈው ። ዛሬ ዛሬ ልባችንን ከሚያደክሙን ጥያቄዎች መካከል ይህ ከማን የወገን ነህ ? የሚለው የኢያሱ ጥያቄ ቀዳሚው ነው ።
ሰባት በዕብራዊያን ፍጽም ቁጥር ነው ኢያሱ ይህን ጥያቄ የጠየቀው እወርሳታለው ብሎ በሚጠባበቃት በሰባት ግንብ በታጠረችሁ በኢያሪኮ አጠገብ ሆኖ ነው ። ዛሬም እንወርሳታለን በምንላት በፍጹሟ የመንግሥተ ሰማይ ደጅ በሆነች በኦርቶዶክሳዊት እምነት ቆመን ግን ወገናዊነትና የዘር ነገር የሚያሳስበን ስንቶች እንሆን ? ከማን ወገን ነህ ስንለው እንደ ቅዱስ ሚካኤል እኔ የእግዚአብሔር ሰራዊት ነኝ ብሎ የሚያሳርፈን እውነተኛ መሪስ እናገኝ ይሆን?
ጎሰኝነት ጎጠኝነት መደርተኝነት ዘረኝነት ወገንናዊነት መንግሥተ ሰማያት አያስገባም

ወንድሞቼ ሆይ፥ በመካከላችሁ ክርክር እንዳለ ስለ እናንተ የቀሎዔ ቤተ ሰዎች አስታውቀውኛልና። ይህንም እላለሁ፦ እያንዳንዳችሁ፦ እኔ የጳውሎስ ነኝ፥ እኔስ የአጵሎስ ነኝ፥ እኔ ግን የኬፋ ነኝ፥ እኔስ የክርስቶስ ነኝ ትላላችሁ። ክርስቶስ ተከፍሎአልን? ጳውሎስስ ስለ እናንተ ተሰቀለን? ወይስ በጳውሎስ ስም ተጠመቃችሁን? 1ቆሮ 1÷11-13


ዛሬም ይህ ክርክር በመካከላችን መለያየትን ፈጥሯል ኦሮሞነት አተሰቀለልንም አማራነትም አላጠመቀንም ወላይታነት ከገሃነም አላዳነንም ትግሬነትም መበላላትና ሞትን እንጂ ትንሳኤ ሙታንን አላወጀልን። ታድያ እኔ ከዚህ ወገን ነኝ ትለ
ላለህ? ከመላእክት አለቃ ከቅዱስ ሚካኤል ተምረህ እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት ነኝ ልትል ይገባል ። የክርስቶስ ተከታይ የክርስቶስ ሐዋርያ በክርስቶስ ክርስቲያን የተሰኘ ሰማያዊ ዘር ያለው እንጂ ምድራዊ ዘር የለውም። ሐዋርያውም መልሶ እኛግን ሀገራችን በሰማይ ነው ያለው ለዚሁ ነው። ኢያሱ የመላእኩን ኢወገናዊ የሆነ አቋም ከሰማ በኋላ ሰግዶለታል ለባሪያህ የምትነግረኝስ ምንድነው ብሎ ጠይቆ ኢያሪኮን ድል ነስቶ ወርሷታል እኛም ሀገረ ሕይወት መንግሥተ ሰማያትን የምንወርሳት ከመላእክት አለቃ ከቅዱስ ሚካኤል እና እርሱን ከመሰሉ የቤተ ክርስቲያን አለቆችን ትምህር ምክርና ተግሳጽ ሰምተን ከዘረኝነት ሀስተሳሰብ የወጣን ጊዜ ነው።
#ይኩን_ሠላም_ለሀገሪትነ_ኢትዮጵያ !


ኃ/ማርያም
ኅዳር 10/2014 ዓ.ም
🙏Thanks Bank of Abyssinia🙏
_______________________________
ክርስቲያኖች የሌሉና የማይሰሩ ብሎም የማይቆጥቡ ይመስል አረብ አረብ የሚሸቱ የባንክ የቁጠባ ሒሳብ ማስታወቂያዎች አሰልችተውን ነበር
#በኩሽ ÷ ኩሻዊያን
#በሳባ ÷ ሳባዊያን
#በኢትዮጲስ ÷ ኢትዮጵያ
#በአቢስ ÷ አቢሲኒያ የተሰኝ ሀገር በቀል ነባር ስም አጠራራችን መስማት ናፍቀን ነበር።

#አሁን_ግን_ተመስገን ልንሰማውና ልናየው የወደድነውን እያየን እየሰማን ነው!

#እውነት_እላችኋለሁ፥ ብዙዎች ነቢያትና ጻድቃን የምታዩትን ሊያዩ ተመኝተው አላዩም፥ የምትሰሙትንም ሊሰሙ ተመኝተው አልሰሙም።”
#ማቴ 13፥17
#መዋዕለ_ጾም

ጾመ ለተወሰነ ጊዜ ከመብልና መጠጥ ተከልክሎ መቆየት ነው፡፡ ለተወሰነ ጊዜ ከምግብ ተቆጥቦ መቆየት ለጤንነት ለሥጋም ለነፍስም ጠቀሜታ አለው፡፡

#ለምን_እንጾማለን?

በደካማ የሥጋ ፈቃድ ምክንያት ሕይወትን በሚዋጋ ሰይጣንና ከሱም ጋር በሚመጡ ፈተናዎች ላይ መንፈሳዊ ኃይልን ለማጠናከር የኃጢኣት ይቅርታና በረከት ለማግኘት ነው፡፡ ሐዋርያት ‹‹ጌታ ሆይ! ይህን ክፉ መንፈስ ልናወጣው ያልቻልነው ስለምንድነው?›› ብለው ጠየቁት ጌታም ‹‹ስለእምነታችሁ ደካማነት ነው……….. ይህ ዓይነት ግን ከጾምና ጸሎት በቀር አይወጣም›› ብሎ መለሰላቸው፡፡ ማቴ17÷21
በመልሱ ‹‹የዚህ ዓይነት›› የሚለው ኃይለ ቃል የጨለማ ኃይሎች የሚለውን ያመለክታል፡፡
‹‹ጦርነታችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለም፤ ከጨለማ ገዢዎች አለቆችና ሥልጣኖች ጋር›› ነው ብሎ ሐዋርያው እንደገለጠው፡፡ /ኤፌ6÷12/

#የጾም_ጥቅም?

የሥጋ ፈቃድ ለነፍስ ፈቃድ ለማስገዛት ይረዳል፤
ሰውነትን በእግዚአብሔር ዘንድ ታዛዥና ትሁት ያደርጋል፤
ታዛዥነትን ያሳያል፤
ለአካላዊ ብቃትና ጤንነትም አስተዋጽኦ አለው፤
ለሰውነት የምግብ መፍጫና ማዋሐጃ ክፍሎች የዕረፍት ጊዜ ያስገኛል፤

#በጾም_ወቅት_የሚወሰዱ_ጥንቃቄዎች

መጾም ከመብልና መጠጥ ብቻ አይደለም፡፡ ሰውን /ራስንም ጭምር/ ከሚጎዱ መጥፎ ነገሮች መታቀብ፣ የሰውነትን ክፍሎች ከጥፋት ሥራ መቆጣጠር ያስፈልጋል፡፡ ከምግብ እንደምንጾም ሁሉ ወደ ክፉ ተግባር ከሚገፋፉ ስሜቶች ሁሉ መከልከል ትልቅ ጾም ነው፡፡

ሌላው የበደሉትን ይቅርታ መጠየቅ የተበደሉትን ይቅር ማለት /መተው ይቅር መባባል ነው፡፡ ይቅር የማይሉ ይቅርታ የላቸውም፡፡ ይቅር አለመባባል ከእግዚአብሐየር ይቅርታ ራስን በፈቃድ ማግለል ነው፡፡

እምነታችን የፍጹምነት ሥራ የሚሰራው በሕይወታችን የምንወደውን ሁሉ አግኝተን ደስ ተሰኝተን ለመኖር ከፍ ብለን የጠቀስናቸው ሁሉ ተስተካክለውና ተሟልተው መጠበቅ ይኖርባቸዋል፡፡
የተሻለ ኑሮ ለመኖር አካሄዳችን ከእግዚአብሔር ጋር እናደርጋለን፡፡

ምንጭ መዝገበ ታሪክ
ክፍል ፩

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit