ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
929 photos
24 videos
271 files
192 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
#ከቅዱስ_ሚካኤል_የተማርነው
________________________

"# እኔ_የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ" ኢያሱ 5÷14
ከሊቀ ነቢያት ከሙሴ ቀጥሎ ሕዝበ እስራኤልን ይመራ የነበረው ኢያሱ ነው። ኢያሱ ማለት መድኃኒት ማለት ነው። በትርጉም ኢየሱስ ከሚለው ጋር አንድ ነው። የባሳንን ንጉስ አግን የአሞራዊያንን ንጉሥ ሴዎንን በእግዚአብሔር እረዳትነት በጦርነት ገጥሞ ድል የነሳቸው ጽኑ የእስራኤል መሪ ነበር ። በሰባት ግንብ ታጥራ የነበረችሁ አሮጊቷ ከተማ ኢያሪኮ በደረሰ ጊዜ ግን ይህቺን ከተማ ደግሞ እንዴት ድል ነስቷ ይይዛት ዘንድ እንደሚችል ሀሳብ ገብቶት ግንቧን ተጠግቶ ቁጭ ብሎ ሲያወጣና ሲያወርድ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካዬል የተመዘዘ ሰይፍ በያዘ ጎበዝ ሰው አምሳል ተገልጦ ታየው ኢያሱም ቀርቦም እንዲህ ሲል በችኮላ መላእኩን ጠየቀው " ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ?
" ሊቀ መላእክ ቅዱስ ሚካኤል ግን እንዲህ ሲል መለሰለት “አይደለሁም፤ እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ" አለው ። ይህን ጊዜም ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደለት” ኢያሱ 5፥14 የእግዚአብሔር ሰው የኢያሱ አመጣጥ ወገንተኛነትን ለመጠየቅና ለማወቅና በተሞላ መንፈስ ነበር ።የእግዚአብሔር መላእክ ቅዱስ ሚካኤል ግን እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት ነኝ እንጂ ከእናንተ ወይም ከጠላቶቻችሁ ወገን ነኝ አደለውም ብሎ ልቡን አሳረፈው ። ዛሬ ዛሬ ልባችንን ከሚያደክሙን ጥያቄዎች መካከል ይህ ከማን የወገን ነህ ? የሚለው የኢያሱ ጥያቄ ቀዳሚው ነው ።
ሰባት በዕብራዊያን ፍጽም ቁጥር ነው ኢያሱ ይህን ጥያቄ የጠየቀው እወርሳታለው ብሎ በሚጠባበቃት በሰባት ግንብ በታጠረችሁ በኢያሪኮ አጠገብ ሆኖ ነው ። ዛሬም እንወርሳታለን በምንላት በፍጹሟ የመንግሥተ ሰማይ ደጅ በሆነች በኦርቶዶክሳዊት እምነት ቆመን ግን ወገናዊነትና የዘር ነገር የሚያሳስበን ስንቶች እንሆን ? ከማን ወገን ነህ ስንለው እንደ ቅዱስ ሚካኤል እኔ የእግዚአብሔር ሰራዊት ነኝ ብሎ የሚያሳርፈን እውነተኛ መሪስ እናገኝ ይሆን?
ጎሰኝነት ጎጠኝነት መደርተኝነት ዘረኝነት ወገንናዊነት መንግሥተ ሰማያት አያስገባም

ወንድሞቼ ሆይ፥ በመካከላችሁ ክርክር እንዳለ ስለ እናንተ የቀሎዔ ቤተ ሰዎች አስታውቀውኛልና። ይህንም እላለሁ፦ እያንዳንዳችሁ፦ እኔ የጳውሎስ ነኝ፥ እኔስ የአጵሎስ ነኝ፥ እኔ ግን የኬፋ ነኝ፥ እኔስ የክርስቶስ ነኝ ትላላችሁ። ክርስቶስ ተከፍሎአልን? ጳውሎስስ ስለ እናንተ ተሰቀለን? ወይስ በጳውሎስ ስም ተጠመቃችሁን? 1ቆሮ 1÷11-13


ዛሬም ይህ ክርክር በመካከላችን መለያየትን ፈጥሯል ኦሮሞነት አተሰቀለልንም አማራነትም አላጠመቀንም ወላይታነት ከገሃነም አላዳነንም ትግሬነትም መበላላትና ሞትን እንጂ ትንሳኤ ሙታንን አላወጀልን። ታድያ እኔ ከዚህ ወገን ነኝ ትለ
ላለህ? ከመላእክት አለቃ ከቅዱስ ሚካኤል ተምረህ እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት ነኝ ልትል ይገባል ። የክርስቶስ ተከታይ የክርስቶስ ሐዋርያ በክርስቶስ ክርስቲያን የተሰኘ ሰማያዊ ዘር ያለው እንጂ ምድራዊ ዘር የለውም። ሐዋርያውም መልሶ እኛግን ሀገራችን በሰማይ ነው ያለው ለዚሁ ነው። ኢያሱ የመላእኩን ኢወገናዊ የሆነ አቋም ከሰማ በኋላ ሰግዶለታል ለባሪያህ የምትነግረኝስ ምንድነው ብሎ ጠይቆ ኢያሪኮን ድል ነስቶ ወርሷታል እኛም ሀገረ ሕይወት መንግሥተ ሰማያትን የምንወርሳት ከመላእክት አለቃ ከቅዱስ ሚካኤል እና እርሱን ከመሰሉ የቤተ ክርስቲያን አለቆችን ትምህር ምክርና ተግሳጽ ሰምተን ከዘረኝነት ሀስተሳሰብ የወጣን ጊዜ ነው።
#ይኩን_ሠላም_ለሀገሪትነ_ኢትዮጵያ !


ኃ/ማርያም
ኅዳር 10/2014 ዓ.ም