#የድንግሊቷየ_አፍቃሪዎች
፡
፡
#ክፍል_ሶስት
፡
፡
#ድርሰት_ዘሪሁን_ገመቹ
===============
ላዳዋ ይዛቸው ትንሽ እንደተጓዘች
‹‹እሺ ምን ገጠመህ?››ሲል አለማየሁ የመጀመሪያውን ጥያቄ ጠየቀ፡
አላዛርም‹‹ሰውዬው እየሞተ ነው መሰለኝ….፡፡››ሲል በደፈናው መለሰ፡፡
ሁሉም የአላዛር መልስ አልገባቸውም‹‹የትኛዬው ሰውዬ?››ሲል ሁሴን ጠየቀ፡፡
‹‹አባት ተብዬው፡፡››
‹‹በስመአብ..?ማን ነገረህ?››ሰሎሜ በድንጋጤ ጠየቀች፡፡
‹‹አንድ ሴትዬ ነች..ሚስቱ ነኝ አለችኝ..አላውቃትም፡፡››
‹‹ጋሽ ተሰማ አግብተዋል እንዴ?››ሁሉም በመገረም ጠየቁት..፡፡
‹‹እኔም ዛሬ ነው የሰማሁት፡፡››
‹‹አይዞህ አትደንግጥ ምንም አይሆኑም››ሰሎሜ ልታፅናናው ሞከረች፡፡
በንዴት በሚርገበገብ ድምፅ ‹‹ለምንድነው የምደነግጠው…? ቢሞት እንደውም ግልግል ነው፡፡››ሲል መለሰላቸው፡፡
‹‹ባክህ አታስመስል..ባትደነግጥ በዚህ ምሽት እኛንም ቀስቅሰህ ልታያቸው ትሄድ ነበር?፡፡››
ሰሎሜ ነች ተናጋሪው፡፡
‹‹አንቺን አልቀሰቀስኩም..ብቻዬን ከምሆን አሌክስን ብቻ ነው አካሂደኝ ያልኩት..አንቺና ሁሴንን አልጠየቅኳችሁም፡፡››
‹‹እና እናንተ ጓደኞቼ አይደላችሁም እያልከን ነው?››አለው ሁሴን በንዴት፡፡
‹‹አንተ ደግሞ ሁሌ ነገር ማጣመም ትወዳለህ፡፡››አላዛር ተበሳጨ፡፡
ሰሎሜ በድጋሜ‹‹ዝም ብለህ ስታስመስል ነው..ምንም ቢሆን አባትህ ናቸው፡፡››አለችው ፡፡
‹‹ዝም በሉኝ በቃ… ሌላ ወሬ አውሩ››ተቆጣ ፀጥ አሉ…
አላዛር ሰፈሩን እንጂ ቤቱን እርግጠኛ አይደለም..ከአመት በፊት ነው አንድ ጓደኛው ጋር በዛ ሰፍር ሲያልፉ ‹‹የአባትህ ቤት ይሄ ነው›› ብሎ ያሳየው….በወቅቱ እቤቱን በጨረፋታ ተመልክቶ ከመገርም ውጭ ለነገረው ልጅ እንኳን መልስ አልመለሰለትም ነበር፡፡ግን እቤቱ እንደፈራው አልጠፋውም፡፡ሲደርሱ ከላዳዋ ወርደው ወደአጥሩ በራፍ እየሄዱ በተደወለለት ስልክ መልሶ ደወለ፡፡
‹‹ሄሎ አላዛር››ቀጭንና ልስልስ ድምፅ፡፡
‹‹መጥተናል በራፉን ክፈቺልን፡፡ ››
‹‹ክፍትነው ግፋውና ግባ፡፡››
እንዳለችው ገፋ ሲያደርገው ተከፈተ፡፡ሶስት ጓደኞቹን አስከትሎ አልፎ ወደውስጥ ሲገባ የሳሎኑ በራፍ ሲከፈት ተመለከተ.. በፍጥነት ተጠጉ..አንድ በእሱ እድሜ ያለች ገጠር ቀመስ ግን ደግሞ ውብ ሴት እየተንቀጠቀጠች ትታያለች፡፡የአራቱም ዓይኖች በመላ አካሎ ላይ ተንከባለሉባት፡፡
‹‹የደወልሽልኝ አንቺ ነሽ?››
‹‹የአባቴ ሚስት አንቺ ነሽ ?››ብሎ መጠየቅ ነበር የፈለገው…..ምክንያቱም ይሄቺን የመሰለ ትንቡክቡክ ያለች ውብ ገራገር ወጣት ያንን ያበቃለትን የሰው አውሬ ብሎ የሚያስበውን አባቱን እንዴት ታገባለች ብሎ ይገምት?››
‹‹አዎ ግቡ ግቡ ››በማለት ይዛቸው ወደውስጥ ገባች….እቤቱ ሳሎንና አንድ መኝታ ክፍል ያለው ባለሁለት ክፍል ነው፡፡አባትዬው ሳሎን ባለ አንድ አሮጌ ሶፋ ላይ ዝርግትግት ብሎ ትኝቷል፡፡ተጠጋውና በመጠየፍ አንገቱን ይዞ አወዛወዛው.. ለበድንነት የቀረበ ሁኔታ ላይ ነው ያለው፡፡
አለማየሁ‹‹ቶሎ ብለን ሀኪም ቤት እንውሰዳቸው››ብሎ ቀድሞ ሄደና ሰቅስቆ አቀፋቸው…ሁሴን የተንንዘላዘለ እግራቸውን በመደገፍ ሊያግዘው ሞከረ፡፡ሰሎሜ ተከተለችው…፡፡አላዛር ወደኃላ ቀረና
‹‹..አንቺ እዚሁ ጠብቂን…አይዞሽ ሰውዬው በቀላሉ የሚሞት አይነት ሰው አይደለም…አትጨናነቂ››አላት፡፡
የንግግሩ ይዘት አልገባትም፡፡ግራ በመጋባት አይኖቾን አቁለጨለጨችበት፡፡ ትከሻዋን በእጆቹ ቸብ..ቸብ እያደረገ‹‹አይዞሽ አትጨነቂ አልኩሽ እኮ…ያለውን ነገር እየደወልኩ አሳውቅሻለሁ፡፡ የሚያስተኙት ከሆነ ጥዋት መጥቼ ወደተኛበት ሆስፒታል ወስድሻለው››ሲል ቃል ገባለት፡፡
ምርጫ ስላልነበራት
‹‹እሺ..አመሰግናለሁ..እግዜር ይስጥልኝ› ›ስትል መለሰችለት፡፡
አላዛር ፊቱን አዞረና ወጥቶ ሄደ..ጓደኞቹ አባትዬውን ላዳ ውስጥ አስገብተውት ነበር የጠበቁት….፡፡
አለማሁ ቀልቡ እዛ ቤት የቀረችው ወይዞሮ ላይ ተጣብቆ ስለቀረ ዝም ብሎ ላዳዋ ውስጥ ሊገባ አልቻለም፡፡
‹‹ እሷ አትመጣም እንዴ?››ሲል አላዛርን ጠየቀው…፡፡
‹‹ምን ትሰራላች ላዳዋ ለእኛም እኮ አትበቃንም፡፡››
‹‹አይ ድንጋጤ ላይ ስላለች ብቻዋን ትፈራለች ብዬ ነው፡፡››ለእሷ ይሄን ያህል ምን እንዳሳሰበው አያውቅም፡፡ግን ድንገት በጨረፍታ እንዳያት በዛው እስከወዲያኛው ሊረሳት አልፈለገም፡፡
አላዛርም ስጋቱ ተጋባበትና‹‹ለምን ከሶስታችሁ አንዳችሁ አብራችኋት አትሆኑም?››የሚል ሀሳብ አስከተለ፡፡ ሰሎሜን፤ ሁሴንንና አሌክስ እርስ በርስ ተያዩ…‹‹አንተ አብረሀት ሁን..ሁለት ሴት አብረን ከመፍራት ውጭ ምን እረዳታለው?ሁሴንም ቢሆን ወረቀት የሌለበት ቤት ያቃዠዋል››ስትል ሰሎሜ የራሷን ሀሳብ አቀረበች ፡፡
አለማየሁ በቀረበው ሀሳብ በመደሰት‹‹በቃ እሺ… እኔ አብሬት ሆናለው…ግን ያለውን ነገር በስልክ አሳውቁኝ፡፡››በማለት መስማማቱን አሳወቀ፡፡
አላዛርም‹‹አመሰግናለው አሌክሶ›› አለና ገቢና ገባ ፡፡ሰሎሜ ና ሁሴን ከኃላ አባትዬውን ከግራና ቀኝ ደግፈው ተቀመጡ… አሌክስ መልሶ ወደ ጊቢው ሲገባ ላዳዋ ተነቀሳቀሰች፡፡
አለማየሁ ወደጊቢ ገብቶ የሳሎኑን በር ሲቆረቁር…ወዲያው ብርግድ ተደርጎ ተከፈተ..ከበራፉ ጋር.. ያልጠና የወጣትነት ልቡም ነበር አብሮ የተበረገደው፡፡እሷ በራፉን ስትከፍት አላዛርን ነበር የጠበቀችው…ጓደኛው ሆኖ ስታገኘው ግን ግራተጋብታ
‹‹ምነው…ምን እረሳችሁ?››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹አይ ምንም አረሳንም…ብቻሽን እንዳትሆኚ አብረሀት ሁን ብለውኝ ነው››
ነበር?››አለችው ከግራ መጋባቶ ሳትላቀቅ‹‹ውይ እኔ ምን ሆናለው ?እነሱን ብትረዳቸው አይሻልም፡፡
‹‹ሶስት እኮ ናቸው..እንደውም ከባለላዳው ጋር አራት ናቸው..እሱም የሰፈር ልጅ ስሆነ ያግዛቸዋል፡፡››
‹‹ጥሩ እሺ ግባ››ብላ በራፉን ለቀቀችለት፡፡በዝግታ እርምጃ ገባና ፊት ለፊት ያለ አሮጌ ሶፋ ላይ ተቀመጠ፡፡እሷም በራፉን ዛጋችና ከእሱ በአምስት ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ኩርሲ ላይ ጭብጥብጥ ብላ ተቀመጠች፡፡ለተወሰነ ደቂቃዎች ዝም ተባባሉ፡፡
ከገባችበት ሀሳብ እንደመባነን ብላ‹‹ወይኔ በእግዚያብሄር ዝም አልኩህ አይደል…?ሻይ ላፍላ ብና?››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹አረ ችግር የለውም….ከቻልሽ ውሀ ስጪኝ››አላት
‹‹ እሺ››ብላ ወደውስጥ ገባችና ውሀ በብርጭቆ አምጥታ ሰጠችው….ተመልሳ ወደ ጓዲያ ገባችና የተጣጠፈ ጋቢ እየዘራጋች መጥታ ‹‹ብርድ ነው ትከሻህ ላይ ጣል አድርገው›› አለችውና አቀበለችው… ተቀበላትና ለበሰው፡፡
‹‹የአላዛር ጓደኛው ነህ?››
‹‹አዎ ጎረቤት ነን..አብረን ነው ያደግነው..ወንድም በይኝ››
‹‹እሳቸውንም ታቃቸዋለህ ማለት ነዋ?››
‹‹ጋሽ ተሰማን…አዎ ለእኔም አባቴ በያቸው፤ግን መቼ ነው የተጋባችሁት…?›ሲል የገረመውን ጥያቄ ጠየቃት፡
‹‹ብዙም አልቆየን… አንድ ሰባት ወር ቢሆነን ነው…፡፡››
‹‹ትዳር ታዲያ እንዴት ነው?፡፡››
እንደማፈር አለችና ተሸኮረመመች‹‹ችግር የማያደርግህ ነገር የለም፡፡የምደገፍበት ቤተሰብ የማኮርፍበት ዘመድ ስላልነበረኝ እሷቸው ላግባሽ ሲሉኝ እምቢ ማለት አልቻልኩም፡፡..ምንም እንኳን በእድሜ ከአባቴ ሚበልጡ ሰውዬ እንደሆኑ ባውቅም….አምላክ ከፈቀደው ምንም አይደል እንደአባት ይንከባከቡኛል እንደባል ያስደስቱኛል ብዬ እሺኝ አልኩና ገባሁበት፡፡የተደበቀ አመላቸው አፈትልኮ ለመውጣት ግን አንድ ወር እንኳን አልፈጀበትም…፡፡በቃ ትንሽ መጠጥ ከቀመሱ ሙሉ በሙሉ ሌላ ሰው ሳይሆን ሌላ አውሬ ነው የሚሆኑት፡፡ከዛሬ ነገ ይሻሻላሉ በማለት