#እናቴን_ተመኘኋት
፡
፡
#ክፍል_አንድ
፡
፡
#በሜሪ_ፈለቀ
በተለያየ መኝታ በተለያየ እንቅልፍ ውስጥ አንድ አይነት ህልም እንዴት ይታለማል?
የሆነ ሰው ያለፈበት መንገድ እና የደረሰበት ስኬት እንዴት የሌሎች ብዙዎች መንገድና መድረሻ ይሆናል? የሌሎች ብዞዎች ደስታ በአንድ ሰው መዳረሻ እንዴት ይፈጠራል
።።።።።።።።።።።።።።።።።።
“ለግለቱ የሚተኛኝ ወንድ አስጠላኝ፣ ለፍቅር የሚተኛኝ ናፈቀኝ፡፡” ያለችኝ......
ያኔ በአስራ ሁለት ዓመቴ ከርዳዳ ፀጉሬን እየደባበሰች፣ አረቄዋን እየተጎነጨች፣ ከትልልቅ ዓይኖቿ እንባ እየደፋች፣ ተሰባብሮ ሩብ ታክሉ በቀረ ሙሉውን የፊቷን ገፅታ ማሳየት በተሳነው መስታወቷ ተራ በተራ እያንዳንዱን የፊቷን አካላት እያየች ነበር።
“እንደእነ ጥሩዬ በወግ አግብቼ በማግስቱ ሞቴ ቢሆን ግድ
የለኝም::" ብላኝ ነበር በዓይኖቿ እሩቅ እያየች።
"እኔ ሳድግ አገባሻለሁ!!" አልኳት የዛን ዕለት፡፡
ደንገጥ ብላ እጇን ከፀጉሬ ላይ እያነሳች "ኪዳነ ምህረት! አንተ ልጅ ምን ስል ሰማኸኝ?" ብላኝ ከተቀመጥንበት የበረንዳው ደፍ ላይ ዘላ ተነሳች።
"አንተ? እናትህ እኮ ነኝ። በማን ሀገር ነው ልጅ አድጎ እናቱን የሚያገባው? በል ግባና ምሳህን ብላ!!" ብላኝ ወደቤቷ ገባች። ተከትያት ገባሁ። እንደሁልጊዜው ምሳዬን ሰጠችኝ፡፡እንደሁል ጊዜው ለራሷ ጎርሳ ሰሀኑን ገፋ አደረገችልኝ፡፡ እኔ ግን
እንደሁልጊዜው የሰጠችኝን እንጀራ በሽሮ ተስገብግቤ መብላት አቃተኝ።
የማስበው ሁሉ የጥሩዬን ባል አክዬ ወይንሸትን ማግባት ነበር፡
የጥሩዬን ባል መንገድ ሳገኘው ቁመት እለካካዋለሁ።ባል ለመባል ልደርስላት፣ በትልልቅ ዓይኖቿ ማልቀሷን ላስቆማት
የፊቷን አካላት ሁሉ በአንዴ የምታይበት መስታወት ገዝቼ ልሰጣት፣ ህፃን አይጠጣም እያለች የምትከለክለኝን አረቄዋን የበረንዳዋ ደፍ ላይ አብሪያት ተቀምጨ ልጠጣ፣..... የጥሩዬ ባል
ለጥሩዬ እንደሚያደርግላት በእንጨት ማበጠርያ የወይንሽትን ረዥም ፀጉር ላበጥርላት፡፡
#ያኔ......
በገጠራማዋ መንደራችን የተፈራ የታፈረ አባወራ ሳይቀር ጠላ ከምትሽጥባት ትንሽዬ ቤቷ ውስጥ መደቧን አጣቦ ጠላውን እየኮመኮመ ዓይን ዓይኗን ሲያይ የሚያመሽላት ቆንጅዬ ነበረች።
#ያኔ.....
ባለትዳር የሆኑት የመንደሯ ሴቶች ባሎቻቸው ወይንሸትጋ ሲገቡ አይቼ የማላውቃቸም ጭምር ባሎቻችንን አባለገች ብለው የሚኮንኗት፣ በውበቷ እንደማይቀኑ እና የሷን የአለባበስ እና
የሹሩባ አሰራር በየቤታቸው እየኮረጁ እንደማይመስሏት ፊት የሚነሷት ውብ ነበረች።
#ያኔ.....
የመንደሯ ወንዶች ጠላዋን እየጠጡ በጡትና በመቀመጫዋ ለሀጫቸውን እንዳላዝረከረኩ፣ መደቧ ላይ ይዘዋት ወድቀው ከጠላዋ በላይ በስሜት እንዳልሰከሩ 'ዘማዊት'፣ “ኮማሪት' እና
ሌሎችም ፀያፍ ስያሜዎች የሚሰጧት ግን ከደጂ የሚጎትታቸው ስበት ያለ ይመስል የሚመላለሱላት ነበረች።
#ያኔ.....
በየጠዋቱ እያለቀሰች ሳላያት በፊት እንደሌሎቹ የሰፈራችን ህፃናት እናቴ የምትመስለኝ፣ አያቴ የሚበላ ነገር እቤት የሌለ ቀን 'ወይንሸትጋ ሄደህ ቀማምስ' ሲለኝ በጥቂት እርምጃ ከኛ ቤት የሚርቅ ቤቷ ሄጄ የምቅለስለስ፣ መብቴ እንደሆነ ሁላ ከተለያዩ ወንዶች ከወለደቻቸው ሁለት ልጆቿ ጋር ተቃምቼ ቤቷ የምበላ፣ የልጅነት ባሏ ሞቶባት አዲስ አበባ ከርማ ስትመጣ ጠላ ቤት መክፈቷን የሚያወሩላት በልጅነቴ የሞተች እናቴን የምትመስለኝ 'እናቴ' ነበረች።
#ያኔ......
ባል መሆን ምን እንደሚጠይቅ ባይገባኝም “እናቴ በየቀኑ የሚያስለቅሳትን የባል እጦት መሙላት ሆነ ሀሳቤ፡፡ጠላ ሸጣ የምታጠራቅመውን ሳንቲሟን ተማክረው የሚሰርቁባትን ልጆቿን ምንም እንኳን በእድሜም በጉልበትም ቢበልጡኝም አድጌና ጉልበት አውጥቼ እነርሱን ስርዓት ላስይዝላት ሆነ ምኞቴ፡፡
“ቆይ እኔ ልጆቼን አስሬ አላስቀምጣቸው? ምን አድርጊ ነው የሚሉኝ? ያለችኝ......
ያኔ በአስራ ዘጠኝ ዓመቴ የገጠር ከተማ ከሚሏት ከመንደራችን ራቅ ካለ ገበያ የአያቴን ድንች ሸጬ ስመለስ መንገድ ላይ አግኝታኝ፣ የእኔ ማደግ ከሚታየው በላይ የሷን ማርጀት በሚያሳብቅ ሽፋሽፍት የተከበበ ዓይኗን እያፈጠጠች፣ በባዶ እግሯ ውሃ ያቆረውን መሬት እየደለቀች ከሚፈናጠረው ጭቃማ
ውሃ ጋር እየተጫወተች ነበር፡፡
"ንገሪኝ እስኪ ፈልጌ ነው ልጆቼ ሌባና ቀማኛ የሆኑት? ምናለ እንደ ጥሩዬ አንድ ልጅ በማዕረግ አስመርቄ ሞቴ በበነጋው
ቢሆን?" ብላኝ ነበር፡፡ የተናገረችው ነገር ያላሳዘናት ይመስል ፈገግ እያለች፡፡
“ማን ምን አገባው? ቢጣን ያስተማርሻት አንቺ አይደለሽ? አዲስንስ ቢሆን? ......" እቤቷ እያስገባች የምታበላቸውን፣
ከእናቶቻቸው በላይ የምትንከባከባቸውን እና ያስተማረቻቸውን የስፈሩን ማቲዎች
ስም ደረደርኩላት።የመኖሯ ዋጋው
የሚንረው የምትበላውን ቆርሳ እያጎረሰች ላሳደገቻቸው፣ ጠላ ሸጣ ደብተርና እስኪሪብቶ ለምትገዛላቸው የደሀ መንደራችን ህፃናት ነው።
"አንተ? አንተስ አልማር ብለህ እንጂ ላስተምርህ አላልኩም?"
ብላኝ ዓይኗ ካፊያ እንዳዘለ ሰማይ እየዳመነ በመጣችበት መንገድ
ተመለሰች። ወደቤቷ ተከትያት ገባሁ። እንደቅርብ ጊዜ ልምዴ ከገበያ ይዤላት የመጣሁትን የገብስ ዳቦና የምትወደውን ነጭ ማር ሰጠኋት። እንደ ቅርብ ጊዜ ልምዷ እየተከዘች ስትበላ ረዥም መንገድ ሌጣውን የተጓዘ እግሬን በውሃ እያረጠብኩ አያታለሁ።
የመንደራችን ስኬት መለኪያ የሆነው እና እንደ ሁሉም የመንደራችን ቤተሰብ አያቴ እንደሱ እንድሆን ምሳሌ እንደሚያጣቅስልኝ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ገብቶ እንደተመረቀው
የጋሼ ሰላምነህ ልጅ እንድሆን ቢዘገይም ፊደል መቁጠሪያ ቤት ገብቼ ነበር፡፡ አንድ ቀን የጋሼ ሰላምነህን ልጅ አገኘሁት፡፡
ስለትምህርት ጥቅም እሱ ለዓመታት የተማረውን ምራቅ መዋጫ ፋታ ሳይወስድ መከረኝ፡፡
"ከዛስ?" አልኩት።
“ከዛ ስራ ይኖርሃል። ደመወዝ ይከፈልሃል፡፡ ከዛ ሚስት ታገባለህ፡፡ ከዛ ልጆች ትወልዳለህ።" አለኝ፡፡
“ከዛስ?" አልኩት መልሼ።
“ከዛማ በቃ ደስ ብሎህ ትኖራለሃ!"
“ከዛሳ?” አልኩት ደጋግሜ።
"ቂል ነው እንዴ? ደስ ብሎህ ኖረህ ታልፋለሃ:ፈ።"
"በቃ? መጨረሻው በደስታ መሞት ነው?" አልኩት ግራ እየገባው ያየኛል።
“ከመሞት በፊት ብዙ ደስታ አለው።ብዙ ስኬት አለው።ብዙ......" ጠፋበት መሰለኝ ዝም አለ፡፡
“ያው ነው። የሁሉም ጥቅል ደስታ ማግኘት አይደል? ደስ ባይሰኙም ወደማይቀር ሞት በደስታ መሄድ?" ስለው ይብስ ግራ እየተጋባ "እሺ ቆይ ህልምህ ምንድነው?" አለኝ፡፡
“የምን ህልም?" አልኩት፡፡
ስለ ህልም በትክክል እንደገባኝ እርግጠኛ ያልሆንኩትን ነገር ካስረዳኝ በኋላ "ወደፊት እንዲሆንልህ ወይም እንድትሆነው ወይም እንዲኖርህ የምትፈልገው ምንድነው?" አለኝ፡፡
"ወይንሸት። የወይንሸት ባል መሆን፡፡"
ስለው የነገርኳቸው ሰዎች ሁሉ እንደሚደነግጡት ደንግጦ ሀሳቤ የቂል መሆኑን በምሁር አንደበት ደጋግሞ መከረኝ
የጋሽ ሰላምነህ ልጅ ሌሎች ከተማ የሚኖሩ ዘመዶቹ እንዳለሙት
አለመ። የዚህ መንደር ነዋሪዎችም የጋሼ ሰላምነህን ልጅ ህልም እንድናልም ልጆቻቸውን ያስገድዱናል
በተለያየ በተለያየ እንቅልፍ ውስጥ አንድ አይነት ህልም እንዴት ይታለማል? የሆነ ሰው ያለፈበት መንገድ እና የደረሰበት ስኬት እንዴት የሌሎች ብዙዎች መንገድና መድረሻ ይሆናል? የሌሎች
ብዙዎች ደስታ በአንድ ሰው መዳረሻ እንዴት ይጠፈራል?
ሰው ሲይዘው ለማይረካው ደስታ፣ ነገ ለሚለጥጠው ፍላጎቱ፣ ጨብጦ ለማይበቃው በሽቃጣ ስኬት፤ ህልሜ ነው ብሎ እንዴት ይሄዳል? መማር ህልሙ የነበረ ሰው ስራ ይሆናል

👍3
#እናቴን_ተመኘኋት
፡
፡
#ክፍል_ሁለት (የመጨረሻ ክፍል)
፡
:
#በሜሪ_ፈለቀ
#ያኔ.......
በህፃን ልቤ ከተሸከምኳት፣ ባደገች ልቤ ካገዘፍኳት ከኔ በቀር መንደርተኛው ሁሉ ጤንነቷን የማይቀበል ብዙ ጊዜ ብቻዋን
የምታወራ ነበረች።
"ዞር በልልኝ ከዚህ! አንተም እንደመንደሩ ሰው እብድ መሰልኩህ? ዞር በል ብዬሃለሁ።ምን በሀጢያት ተወልጄ?
ሀጢያትን ሳቦካ ብኖር ልጄን የምተኛ ሸርሙጣ ታደርገኛለህ?" ያለችኝ......
ያኔ በሀያ አምስት ዓመቴ በረንዳዋ ላይ እሷ ተቀምጣ በገዛሁላት መስታወት የፊቷ ገፅታ ላይ ይሁን የፊቷ ማድያት ላይ የተሳለ ያለፈ ህይወቷ ላይ አፍጥጣ፣ በእንጨት ማበጠሪያ ረዥሙን እና ሽበት ጣል ጣል የጀመረውን ፀጉሯን እያበጠርኩላት 'ላግባሽ?' ስላት ነበር፡፡
"አንተ ባለጌ!! እናትህ መሆኔ ጠፋህና ለብልግናህ ተመኘኸኝ?"
ብላኝ ነበር እንደልጅነቴ ባለማወቄ ያለመሆኑን ስታውቅ፡፡እየተወራጨች ቢሆንም የምታወራኝ ለዓመታት አመሻሽ ላይ የማበጥርላትን ፀጉሯን ማበጠር እንዳቆም የፈለገች አትመስልም።
"ድንች ሸጩ ባጠራቀምኩት ብር ሰርግ እደግስልሻለሁ፡፡ በወግ ማዕረግ አገባሻለሁ። ባልሽ እሆናለሁ::" አልኳት የዛን ዕለት።
የመቀየም ይሁን የማዘን ያልገባኝን መተራመስ ፊቷ ላይ አሳይታኝ በቀስታ እጄን ከፀጉሮቿ ላይ አንስታ ተነሳች።
አንዳንድ ጊዜ እናቴ የሚያስመስላትን ፊቷን አመጣችው አንዳንዴ እንደሚሆነው የሌላ ሰው ከባድ ሰውነት የተሸከመ
ይመስል እግሯ እየተጎተተ ወደ ቤቷ ገባች። እንደነዚህ አይነት
አንዳንድ ቀኖቿ ላይ እንደማደርገው ተከተልኳት፡፡ ኩርምት ብላ መደቧ ላይ ተኛች፡፡ ትዩዩ ያለው ጠባብ መደብ ላይ ተቀምጬ አያታለሁ። ዓይኖቿ እንባ አቀረሩ።
#ያኔ.......
እቤት ስጠፋ ብቅ ይል የነበረው ያሳደገኝ ብቸኛው ዘመዴ አያቴም ስለሞተ እቤቷ ከኔ ውጪ ማንም አይገባም፡፡ የቀረው
ልጇም ሊዘርፋት የሚችለው ገንዘብ ስላልነበራት መኖሪያውን ከሷ አርቋል፡፡
#ያኔ.......
ነፍስ ያለው ሳቋ ብቸኛ ምንጭ የሆኑት ጤንነቷን በሚጠራጠሩ የመንደራችን ቤተሰቦች በተደጋጋሚ የሚቀጡት ህፃናት እንኳን ሲርባቸው እንዳልበሉ፣ ሲታረዙ በኪሮሿ ሹራብ ሰርታ እንዳላለበሰቻቸው፣ እናታቸው እንዳልነበረች ሁሉ ከቤቷ ቀሩ።
#ያኔ.......
“መካሪ ስለሌለው'፣ “እሱም እንደሷ እብድ ነው'፣ “አሳዳጊ የበደለው ሌላ ብዙ የምባለው እኔ ብቻ በጎጆዋ ነበርኩ፡፡
“የሙሽራ ልብሴን አልብሰኝ፡፡ ቀለበቱን እሰርልኝ፡፡ ወግ ማዕረግ አይታ ሞተች ልባል።" ያለችኝ
#አሁን.....
በጉልምስናዬ በበሽታ እና በሃዘን የደቀቀ ሰውነቷን መደቧ ላይ አሳርፋ፣ በመስታወቷ ልታየው የማትፈልገውን የፊቷን ገፅታ በእጆቿ ሸፍና፣ ከሚቆራረጥ ትንፋሿ እየታገለ በሚወጣ ቀሰስተኛ ድምፅዋ ነበር።
“ልጇን ያገባች ባለጌ ናት እንዲሉኝ አልፈልግም፡፡ ወግ ማዕረግ
ሳታይ ሞተች እንዲሉኝም አልፈልግም። ሊቀብሩኝ ሲመጡ ሙሽራ ሆኜ ያግኙኝ፡፡" አለችኝ፡፡ ግድግዳው ላይ በላስቲክ
ተሸፍኖ የተሰቀለውን ከአዲስ አበባ የገዛሁላትን የሙሽራ ቀሚስ ለመገለጥ በደከማቸው ዓይኖቿ እያየች።
በዚህ ቅፅበት የምላት ስላልነበረኝ ምንም አላልኳትም፡፡ ለገላዋ የወዘፍኩትን ውሃ በርዤ ገላዋን አጠብኳት። የታመመች ሰሞን ታደርግ እንደነበረው ሰውነቷን እንዳላይ አቅሙ ኖሯት አትከለክለኝም።
በአበባነት ዘመኗ እንደምታደርገው ሰውነቷን ውብ ጠረን ባለው ቅባት አሸሁላት፡፡ የሙሽራ ቀሚሷን አለበስኳት፣ ነጩን ጫማ አጠለቅኩላት፣ በሽበት የተወረረ ተነቃቅሎ ያለቀ ፀጉሯን አበጥሬ
በልጅነቴ ስታደርግ እንዳየኋት ጠቅልዬ በክር አስያዝኩላት፣ስታደርግ እንዳየኋት ዓይኗን በኩል ከንፈሯን በቀለም
አሳመርኩላት፣ ጣቷ ላይ ቀለበት አጠለቅኩላት። እንደቆነጀች
መደቧ ላይ አስተኝቻት በልጅነቴ የማውቀውን አሁን እያማጠች
የምትፈግገውን ነፍስ ያለው ፈገግታ አያለሁ፡፡ ከልጅነት እስከ ጉርምስና፣ ከወጣትነት እስከ ጉልምስና
የኖርኩለት ህልሜ እሷ ነበረች።ህልሜ በበሽታ ደቃ ልትሞት እጄ ላይ እያጣጣረች ነው። ከዚህ ወዲያ የምኖረው ለምን ይሆን? ለማንስ ይሆን?
#አሁን......
ላግባሽ ብዬ ስማፀናት “አሻፈረኝ ልጄ ነህ' ያለችኝ ወይንሽት በሞቷ አፋፍ ላይ ቀለበት እንዳደርግላት ጠየቀችኝ፡፡
#አሁን.....
ህልምና ዓለሜ የሷ ባል መሆን ብቻ የነበረው እኔ ህልሜ አብሯት ሊሞት እጄ ላይ ነው። ዓለሜም ሊጨልም እየተንደረደረ ነው።
#አሁን...
ባሏ ልሆን ማደጌን፣ ምኞቷን ልሞላላት መጎርመሴን፣ ማዕረጓን እንድታገኝ መጎልመሴን እንጂ እሷ ሚስቴ እንድትሆን ይሁን እናቴ እንድትሆን የምፈልግ የተዘባረቀብኝ እኔ አንዴ እናቴ ሌላ ጊዜ ወይንሽት የምትሆንብኝ ዓለሜ ልትሞት ነው፡፡ ሞታ ልትገድለኝ ነው።
#አሁን......
የወለደቻቸው፣ ያሳደገቻቸው፣ ያበላቻቸው፣ ያለበሰቻቸው፣ ያባበለቻቸው፣ የመከረቻቸው፣ በፍቅር ጉያዋ የተጠለሉ ህፃናት ሁላ አድገዋል። አይፈልጓትም። ሌላ የሚጠለሉበት ጉያ
ተሸሽገዋል።መሀን አድርገዋታል። ሊያለቅሱላት ግን ይመጣሉ።
እናታችን ነበረች ሊሉ።
#አሁን......
አግብተዋት ባሏ ያልነበሩ፣ በባልና በመሽማ ስም የተጣቧት፣
በውበቷ ፍሰሃ ያገኙ፣ ባለፈው እሷነቷ ውስጥ የነበሩ፣ የልቧን ዙፋን
የተቀራመቱ፣ በሴትነቷ የሰለጠኑ.... እነሱም አይፈልጓትም።ስግብግብ ምኞታቸውን አሟልተውባታል።
አሁን የሚቦጠቡጡት ጥቅም እሷጋ የለም። እነዚህም በእድሜና
ምቾት የሰባ ስጋቸውን አስቀድመው እና ፀጉር አልባ ራሳቸውን እየነካኩ ይመጣሉ። ሊያለቅሱላት፡፡ ወዳጃችን ነበረች፣ ፍቅራችን ነበረች፣ እያሉ ሊያለቅሱላት።
#አሁን......
ባሏ እንዳልሆን በልጅነቴ የሰለጠኑባት ባል መሳዮች ሲያበግኑኝ በጉርምስናዬ በግድ ያለፍላጎቷ አግብቻት እንዳለፉት ባሎቿ እንዳልመዘብራት ፈርቼ፣ በወጣትነቴ ፍላጎቷን አክብሬ፣ በዙፋኗ
ልትሾመኝ እንዳላመነችኝ ገብቶኝ ታግሼ፣ በጉልምስናዬ ደግሞ ባሏ ሆኖ ሙቀቷን ከመጋራት እና እናቴ ሆና ከምጠብቃት
የትኛውን እንደምመርጥ ግራ እየገባኝ ህልሜ፣ ዓለሜ......የመኖሬ ምክንያት የሞቷ አፋፍ ላይ ናት፡፡
አለቅስላታለሁ፡፡ እናቴ ሞተች ብዬ የልጆቿን ሁሉ አለቅስላታለሁ። ሚስቴ ሞተች ብዬ የሰውነቷን ጥፍጥና
የቀመሱትን ለቅሶ ሁሉ አለቅስላታለሁ። እኔ ህልሜ ሞተች ብዬ የራሴን አለቅስላታለሁ።እንደባል የሰለጠኑባትም እንደ ልጅ የተጠለሉባትም የተዋት
መታመሟ ያላመማቸው የሁሉም የነበረች እሷ በሞቷ ዋዜማ እጄ ላይ ናት።የእኔ እጅ ብቻ ላይ ሙሽራዬ!!!
✨አ...ለ...ቀ✨
በዚህስ ድርሰት ላይ ምን ውስጣቹ ተብላላ? አሳውቁኝ።
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ቀን። 🙏