#ሮሜዎና_ዡልዬት
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አንድ
#አባ_ሎራና። #ዡልየት ።
#ዡልዬት ።
ይዘኑልኝ ፡ በጣም ፡ አባቴ ፡ አባ ፡ ሎራ ፤
በኔ ፡ ላይ ፡ ዘንድሮ ፡ የመጣው ፡ መከራ ፡
ፍጻሜ ፡ የለውም ፡ ቈርጫለሁ ፡ ተስፋ፤
ይርዱኝ ፡ እባክዎ ፡ ጨርሼ ፡ ሳልጠፋ ።
#አባ_ሎራ ።
አዝኛለሁ ፡ ልጄ ፡ ነገሩን ፡ ሰምቼው ፤
አሁን ፡ መጥቶ ፡ ነበር ፡ፓሪስን ፡ አግኝቼው
ተክሊሉን ፡ ለናንተ ፡ ኀሙስ ፡ እንድሞላ ፡
ለምኖኝ ፡ ነበረ ፡ እንዲህ ፡ በችኰላ ፡
እንደ ፡ ምን ፡ ይሆናል ፡ብዬ ፡ መለስኩለት፤
በነገሩ ፡ በጣም ፡ አዝኛለሁ ፡ በውነት ።
#ዡልዬት ።
እንግዲያው ፡ ከሰሙት ፡ እንሆ ፡ ችግሬ ፤
ሥቃዬ ፡ የጠና ፡ ብርቱ ፡ ነው ፡ አሳሬ
እሄድ ነበር በውነት ሴት፡ ባልሆን' ጠፍቼ
ለፓሪስ ፡ ሊድሩኝ፡ቈርጠው 'ዘመዶቼ
አስጨንቀው ያዙኝ'ይኸው ፡በግዴታ፤
አባትም እናትም የምድር'ሁሉ፡ ጌታ ፡
እግዜር ' የዳረውን ፡ አይችልም ሊያፋታ ።
እኔና 'ሮሜዎን ፡ ሁለቴ ' ሲድረን '
በፊት፡ በጥበቡ' ከልብ' አፋቀረን ፤
ቀጥሎ ፡ በርስዎ ፡ በካህኑ' ሥልጣን ፡
ባርኮ ፡አገናኘን' በተክሊል ፡ ቃል፡ ካዳን ።
አባቴና እናቴ ፡ ይህን ፡ አላወቁ ፤
ለፓሪስ ፡ ሊድሩኝ 'እንሆ 'ታጠቁ '
እንግዴህ ፡ አባቴ ፡ እርስዎ ፡ ከግዜር ፡ ጋራ
በርትተው ፡ ያድኑኝ ፡ ከዚህ ፡ ከመከራ ፡
የማይቻል ፡ ሆኖ ፡ ካልተገኘ ፡ ዘዴ !
ብልሃቱን ፡ መፈለግ ፡ አለብኝ ፡ በግዴ ፡
ይኸው ፡ በዚህ ፡ ጩቤ ፡ ሆዴን ፡ እቀድና ፡
እገላገላለሁ ፡ ከዚህ ፡ ከፈተና
#አባ_ሎራ ።
ኀጢአቱ ፡ትልቅ ነው ከነፍስ ፡ የሚያስቀጣ
በገዛ ፡ እጅሽ ፡ መሞት ባሳብሽ ፡ አይምጣ
ፓሪስን ለማግባት ልብሽ ፡ ካልፈቀደ
ይህን 'ያኽል፡ በውነት ፡ ሆድሽ ፡ ካልወደደ
ግልጥ ፡ አድርጊና ፡ ንገሪኝ አትፍሪ
#ዡልዬት ።
እግዚአብሔር ብቻ ነው መንፈስን መርማሪ
ፓሪስን ፡ ከማግባት ፡ በውነቱ ፡ አባቴ ፡
አሁን ባሁን ፡ ፈጥኖ፡ ይምጣ ጊዜ፡ ሞቴ ፡
ልገረፍ ልሰቀል ፥ በሥቃይ ፡ ልገደል ፤
ወስዳችሁ ፡ ወርውሩኝ ጣሉኝ ወደ ፡ ገደል
የትም ፡ ተረስቼ ፡ ልዋረድ ፡ ልጕላላ ፤
ብትፈልጉ ፡ ዳሩኝ ፡ ለዱር ፡ ወሮ ፡ በላ '
ከዥብ ፡ ጋራ ፡ እሰሩኝ ፡ ከነብር ፡ ካንበሳ ፤
ካፅም 'ጋራ ፡ ቅበሩኝ፣ ከትኵስ'ሬሳ፡
እሳት አንድዳችሁ፡ አሁን ፡ ከቶ ፡ ነፍሴ ፡
አቃጥሉኝ ፡ በቁሜ ፡ ከእግር እስከ ፡ ራሴ
ወደ ፡ አራዊት ፡ ጐሬ ጣሉኝ ፡ ወዶ ፡ ዋሻ ፣
ሮሜዎ ከቀረ ምንም ፡ ባል እልሻ
#አባ_ሎራ ።
እኔም ፡ ባንቺ፡ነገር፡እጅግ፡ተጠብቤ
ልጄ ፡ ሆይ ፡ሐዘንሽ ተሰማኝ፡ ለልቤ ፡
የሚቻልሽ ፡ ቢሆን ፡ ልብሽ ፡ የሚደፍር ፡
አድምጭኝ ልጄ ሆይ ልስጥሽ አንድ ምክር
አሁን ፡ ተመልሰሽ ፡ ስትገቢ ፡ ከቤትሽ ፡
እንደዚህ ፡ በዪና ፡ ንገሪው ፡ ላባትሽ ፡
« ፈቃድህን ፡ ልፈጽም ፡ ፓሪስን ፡ አግብቼ፡
« መጥቻለሁና ፡ ይኸው ፡ ተጸጽቼ ፡
« እንግዴህ ፡ ይደገስ ፡ ሰርጉ ፡ ይሰናዳ »
አባትሽ ፡ ይህነን ፡ ነግረሽው ፡ ሲረዳ '
ይታረቃል ፡ ካንቺ ፡ መንፈሱም ፡ ይረጋል ፤
ከንዴቱ ፡ በርዶ ፡ ይቅርታ ፡ ያደርጋል ።
እኔም ፡ የምሰጥሽ ፡እግዚአብሔር ፡ ቢረዳ
አንድ፡ መድኀኒት ነው ምንም ፡ የማይጎዳ ፡
ልብስሽን ፡ አውልቀሽ ፡ ስትተኝ ፡ ማታ ፡
ደብቀሽ ፡ ሰው ፡ ሳያይ ጠጪው ፡ በቀስታ
ሌሊቱን ፡ ሳትሰሚ ፡ መድኀኒቱ ፡ ሠርቶ ፡
ነገ ፡ ጧት ፡ ከእንቅልፍሽ መነሣትሽ ፡ ቀርቶ
ሞተሽ ፡ ትገኛለሽ ፡ ትንፋሽሽም ፡ ጠፍቶ ፡
ወስደው ፡ ይቀብሩሻል ፡ ሞታለች ፡ ተብሎ
ለቤተ ፡ ሰባችሁ ፡ በሰፊው ፡ ተንጣሎ ፡
አምሮ ፡ በተሠራው ፡በመቃብር ፡ ቤት ፡
ተኝተሽ ፡ ቈይተሽ ፡ ቀንና ፡ ሌሊት ፡
ታዝኖ ፡ ተለቅሶልሽ ፡ ካለቀ ፡ በኋላ ፡
ዐውቀሽ ፡ ትነሻለሽ ፡ አንድ ፡ ቀን ፡ ሲሞላ
እስከዚያ ፡ እሠራለሁ ፡ እኔ ፡ ግን ፡ ተግቼ ፤
ደብዳቤ ፡ እጽፍና ፡ ሮሜዎን ፡ ጠርቼ ፡
እሱም ፡ በቬሮና ፡ ተደብቆ ፡ ገብቶ ፡
ወዳንቺ ፡ መቃብር ፡ ከኔ ፡ ጋራ ፡ መጥቶ ፡
አንቺ ፡ ሳትነሺ 'አጠገብሽ 'ደርሰን ፡
በምስጢር ፡ በፍጥነት ፡ ልብስሽን ፡ አልብሰን አንቺና ፡ ሮሜዎ ከዚህ ፡ ከከተማ
ማንም ሳይጠረጥር ማንም ሰው ሳይሰማ
ወጥታችሁ ፡ሄዳችሁ የትም ፡ በሌላ ፡ አገር
ዕረፍት ፡ አግኝታችሁ ፡ ያለ ፡ ክፉ ፡ ነገር
ኑሩልኝ ፡ በሰላም ፡ በፍጹም ፡ ደስታ ፡
ከናንተ ጋር ይሁን የእግዚአብሔር እርዳታ
ትጠጭው ፡ እንዲሆን ፡ ዡልዬት ፡ ሳትፈሪ'
አስቢና ፡ ቶሎ ፡ ገልጠሽ ፡ ተናገሪ ፡
እኔም ፡ መድኒቱን ልስጥሽ አሁን ፡ ሳልቈይ
ከዚህ በቀር ፡ ዘዴ ፡ የለኝም ፡ ልጄ ፡ ሆይ ።
#ዡልዬት ።
መልካም ፡ ነው ፡ አባቴ ፡ ያላንድ' ቅሬታ' .
ሳልፈራ፡እጠጣለሁ፡ በትልቅ ፡ ደስታ "
እባ፡ ሎራ ፡ ገብተው ጓዳ መድኀኒቱን በብልቃጥ አመጡ
ዶግሞስ በገዛ እጁ ለመሞት ሲቃጣ ከዚህ የተሻለ ምን ዘዴ ሊመጣ ።
እንግዲያውስ፡እንቺ ፡ ይኸው ፡ መድኀኒቱ :
እግዚአብሔር ልብሽን ፡ ያድርግልሽ ብርቱ
#ዡልዬት።
አዝነው ፡ ስለ ፡ ረዱኝ ፡ ልብዎ ፡ ስለ ፡ ራራ
እግዚአብሔር ይስጥልኝ ፡ አባቴ አባ ሎራ
#አባ_ሎራ ።
ግድ ፡ የለሽም ፡ ልጄ ፡ ሳልዘገይ ፡ ፈጥኜ ፡
እንደ ፡ ምንም ፡ ብዬ ፡ አንድ ፡ ቄስ ፡ ለምኜ
ወደ ፡ ሮሜዎ ፡ ዘንድ ፡ጒዳዩን ፡ ሸሽጌ፥
ደብዳቤውን ፡ ጽፌ ፡ በምስጢር ፡ አድርጌ
እልክለታለሁ ፡ በቶሎ ፡ እንዲመጣ '
ዡልዬት ፡ በኔ ፡ ጣዪው ፤ የቀረውን ፡ ጣጣ
#ካፑሌ ፡ #የካፑሌ_ሚስት #ዡልዬት ።
(ዡልዬት ' ከውጭ መጣች)
#ካፑሌ ።
በጣም ያሳዝናል ባሕሪሽ ፡ ተበላሸ ፤
ወዴት ሄደሽ ኖሯል ደግሞ ፡ እንዲህ ፡ ከመሽ
💫ይቀጥላል💫
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አንድ
#አባ_ሎራና። #ዡልየት ።
#ዡልዬት ።
ይዘኑልኝ ፡ በጣም ፡ አባቴ ፡ አባ ፡ ሎራ ፤
በኔ ፡ ላይ ፡ ዘንድሮ ፡ የመጣው ፡ መከራ ፡
ፍጻሜ ፡ የለውም ፡ ቈርጫለሁ ፡ ተስፋ፤
ይርዱኝ ፡ እባክዎ ፡ ጨርሼ ፡ ሳልጠፋ ።
#አባ_ሎራ ።
አዝኛለሁ ፡ ልጄ ፡ ነገሩን ፡ ሰምቼው ፤
አሁን ፡ መጥቶ ፡ ነበር ፡ፓሪስን ፡ አግኝቼው
ተክሊሉን ፡ ለናንተ ፡ ኀሙስ ፡ እንድሞላ ፡
ለምኖኝ ፡ ነበረ ፡ እንዲህ ፡ በችኰላ ፡
እንደ ፡ ምን ፡ ይሆናል ፡ብዬ ፡ መለስኩለት፤
በነገሩ ፡ በጣም ፡ አዝኛለሁ ፡ በውነት ።
#ዡልዬት ።
እንግዲያው ፡ ከሰሙት ፡ እንሆ ፡ ችግሬ ፤
ሥቃዬ ፡ የጠና ፡ ብርቱ ፡ ነው ፡ አሳሬ
እሄድ ነበር በውነት ሴት፡ ባልሆን' ጠፍቼ
ለፓሪስ ፡ ሊድሩኝ፡ቈርጠው 'ዘመዶቼ
አስጨንቀው ያዙኝ'ይኸው ፡በግዴታ፤
አባትም እናትም የምድር'ሁሉ፡ ጌታ ፡
እግዜር ' የዳረውን ፡ አይችልም ሊያፋታ ።
እኔና 'ሮሜዎን ፡ ሁለቴ ' ሲድረን '
በፊት፡ በጥበቡ' ከልብ' አፋቀረን ፤
ቀጥሎ ፡ በርስዎ ፡ በካህኑ' ሥልጣን ፡
ባርኮ ፡አገናኘን' በተክሊል ፡ ቃል፡ ካዳን ።
አባቴና እናቴ ፡ ይህን ፡ አላወቁ ፤
ለፓሪስ ፡ ሊድሩኝ 'እንሆ 'ታጠቁ '
እንግዴህ ፡ አባቴ ፡ እርስዎ ፡ ከግዜር ፡ ጋራ
በርትተው ፡ ያድኑኝ ፡ ከዚህ ፡ ከመከራ ፡
የማይቻል ፡ ሆኖ ፡ ካልተገኘ ፡ ዘዴ !
ብልሃቱን ፡ መፈለግ ፡ አለብኝ ፡ በግዴ ፡
ይኸው ፡ በዚህ ፡ ጩቤ ፡ ሆዴን ፡ እቀድና ፡
እገላገላለሁ ፡ ከዚህ ፡ ከፈተና
#አባ_ሎራ ።
ኀጢአቱ ፡ትልቅ ነው ከነፍስ ፡ የሚያስቀጣ
በገዛ ፡ እጅሽ ፡ መሞት ባሳብሽ ፡ አይምጣ
ፓሪስን ለማግባት ልብሽ ፡ ካልፈቀደ
ይህን 'ያኽል፡ በውነት ፡ ሆድሽ ፡ ካልወደደ
ግልጥ ፡ አድርጊና ፡ ንገሪኝ አትፍሪ
#ዡልዬት ።
እግዚአብሔር ብቻ ነው መንፈስን መርማሪ
ፓሪስን ፡ ከማግባት ፡ በውነቱ ፡ አባቴ ፡
አሁን ባሁን ፡ ፈጥኖ፡ ይምጣ ጊዜ፡ ሞቴ ፡
ልገረፍ ልሰቀል ፥ በሥቃይ ፡ ልገደል ፤
ወስዳችሁ ፡ ወርውሩኝ ጣሉኝ ወደ ፡ ገደል
የትም ፡ ተረስቼ ፡ ልዋረድ ፡ ልጕላላ ፤
ብትፈልጉ ፡ ዳሩኝ ፡ ለዱር ፡ ወሮ ፡ በላ '
ከዥብ ፡ ጋራ ፡ እሰሩኝ ፡ ከነብር ፡ ካንበሳ ፤
ካፅም 'ጋራ ፡ ቅበሩኝ፣ ከትኵስ'ሬሳ፡
እሳት አንድዳችሁ፡ አሁን ፡ ከቶ ፡ ነፍሴ ፡
አቃጥሉኝ ፡ በቁሜ ፡ ከእግር እስከ ፡ ራሴ
ወደ ፡ አራዊት ፡ ጐሬ ጣሉኝ ፡ ወዶ ፡ ዋሻ ፣
ሮሜዎ ከቀረ ምንም ፡ ባል እልሻ
#አባ_ሎራ ።
እኔም ፡ ባንቺ፡ነገር፡እጅግ፡ተጠብቤ
ልጄ ፡ ሆይ ፡ሐዘንሽ ተሰማኝ፡ ለልቤ ፡
የሚቻልሽ ፡ ቢሆን ፡ ልብሽ ፡ የሚደፍር ፡
አድምጭኝ ልጄ ሆይ ልስጥሽ አንድ ምክር
አሁን ፡ ተመልሰሽ ፡ ስትገቢ ፡ ከቤትሽ ፡
እንደዚህ ፡ በዪና ፡ ንገሪው ፡ ላባትሽ ፡
« ፈቃድህን ፡ ልፈጽም ፡ ፓሪስን ፡ አግብቼ፡
« መጥቻለሁና ፡ ይኸው ፡ ተጸጽቼ ፡
« እንግዴህ ፡ ይደገስ ፡ ሰርጉ ፡ ይሰናዳ »
አባትሽ ፡ ይህነን ፡ ነግረሽው ፡ ሲረዳ '
ይታረቃል ፡ ካንቺ ፡ መንፈሱም ፡ ይረጋል ፤
ከንዴቱ ፡ በርዶ ፡ ይቅርታ ፡ ያደርጋል ።
እኔም ፡ የምሰጥሽ ፡እግዚአብሔር ፡ ቢረዳ
አንድ፡ መድኀኒት ነው ምንም ፡ የማይጎዳ ፡
ልብስሽን ፡ አውልቀሽ ፡ ስትተኝ ፡ ማታ ፡
ደብቀሽ ፡ ሰው ፡ ሳያይ ጠጪው ፡ በቀስታ
ሌሊቱን ፡ ሳትሰሚ ፡ መድኀኒቱ ፡ ሠርቶ ፡
ነገ ፡ ጧት ፡ ከእንቅልፍሽ መነሣትሽ ፡ ቀርቶ
ሞተሽ ፡ ትገኛለሽ ፡ ትንፋሽሽም ፡ ጠፍቶ ፡
ወስደው ፡ ይቀብሩሻል ፡ ሞታለች ፡ ተብሎ
ለቤተ ፡ ሰባችሁ ፡ በሰፊው ፡ ተንጣሎ ፡
አምሮ ፡ በተሠራው ፡በመቃብር ፡ ቤት ፡
ተኝተሽ ፡ ቈይተሽ ፡ ቀንና ፡ ሌሊት ፡
ታዝኖ ፡ ተለቅሶልሽ ፡ ካለቀ ፡ በኋላ ፡
ዐውቀሽ ፡ ትነሻለሽ ፡ አንድ ፡ ቀን ፡ ሲሞላ
እስከዚያ ፡ እሠራለሁ ፡ እኔ ፡ ግን ፡ ተግቼ ፤
ደብዳቤ ፡ እጽፍና ፡ ሮሜዎን ፡ ጠርቼ ፡
እሱም ፡ በቬሮና ፡ ተደብቆ ፡ ገብቶ ፡
ወዳንቺ ፡ መቃብር ፡ ከኔ ፡ ጋራ ፡ መጥቶ ፡
አንቺ ፡ ሳትነሺ 'አጠገብሽ 'ደርሰን ፡
በምስጢር ፡ በፍጥነት ፡ ልብስሽን ፡ አልብሰን አንቺና ፡ ሮሜዎ ከዚህ ፡ ከከተማ
ማንም ሳይጠረጥር ማንም ሰው ሳይሰማ
ወጥታችሁ ፡ሄዳችሁ የትም ፡ በሌላ ፡ አገር
ዕረፍት ፡ አግኝታችሁ ፡ ያለ ፡ ክፉ ፡ ነገር
ኑሩልኝ ፡ በሰላም ፡ በፍጹም ፡ ደስታ ፡
ከናንተ ጋር ይሁን የእግዚአብሔር እርዳታ
ትጠጭው ፡ እንዲሆን ፡ ዡልዬት ፡ ሳትፈሪ'
አስቢና ፡ ቶሎ ፡ ገልጠሽ ፡ ተናገሪ ፡
እኔም ፡ መድኒቱን ልስጥሽ አሁን ፡ ሳልቈይ
ከዚህ በቀር ፡ ዘዴ ፡ የለኝም ፡ ልጄ ፡ ሆይ ።
#ዡልዬት ።
መልካም ፡ ነው ፡ አባቴ ፡ ያላንድ' ቅሬታ' .
ሳልፈራ፡እጠጣለሁ፡ በትልቅ ፡ ደስታ "
እባ፡ ሎራ ፡ ገብተው ጓዳ መድኀኒቱን በብልቃጥ አመጡ
ዶግሞስ በገዛ እጁ ለመሞት ሲቃጣ ከዚህ የተሻለ ምን ዘዴ ሊመጣ ።
እንግዲያውስ፡እንቺ ፡ ይኸው ፡ መድኀኒቱ :
እግዚአብሔር ልብሽን ፡ ያድርግልሽ ብርቱ
#ዡልዬት።
አዝነው ፡ ስለ ፡ ረዱኝ ፡ ልብዎ ፡ ስለ ፡ ራራ
እግዚአብሔር ይስጥልኝ ፡ አባቴ አባ ሎራ
#አባ_ሎራ ።
ግድ ፡ የለሽም ፡ ልጄ ፡ ሳልዘገይ ፡ ፈጥኜ ፡
እንደ ፡ ምንም ፡ ብዬ ፡ አንድ ፡ ቄስ ፡ ለምኜ
ወደ ፡ ሮሜዎ ፡ ዘንድ ፡ጒዳዩን ፡ ሸሽጌ፥
ደብዳቤውን ፡ ጽፌ ፡ በምስጢር ፡ አድርጌ
እልክለታለሁ ፡ በቶሎ ፡ እንዲመጣ '
ዡልዬት ፡ በኔ ፡ ጣዪው ፤ የቀረውን ፡ ጣጣ
#ካፑሌ ፡ #የካፑሌ_ሚስት #ዡልዬት ።
(ዡልዬት ' ከውጭ መጣች)
#ካፑሌ ።
በጣም ያሳዝናል ባሕሪሽ ፡ ተበላሸ ፤
ወዴት ሄደሽ ኖሯል ደግሞ ፡ እንዲህ ፡ ከመሽ
💫ይቀጥላል💫