አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
569 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሀገሬ... 🇪🇹
:
:
በከባድ ንፋስና የዝናብ ሰዐት ትልልቅ ዛፎችን ዐይታችሁ ታውቃላችሁ ? የቅጠሎቹን ሳያቋርጡ መርገፍገፍ፤ የቅርንጫፎቹን መንቀጥቀጥ ስታዩ፤ "ይሄ ዛፍ ካሁን ካሁን ወደቀ...ካሁን አሁን ተገነደለ..." ብላችሁ ሰግታችሁ ይሆናል።

ቅርንጫፎቹ ቅንጥስ እያሉ ቢወድቁም፤ ቅጠሎቹ ባድነት ቢረግፉም፤ ግንዱን ብትመለከቱ ግን አይነቃነቅም።

ምክንያቱም ስር የሰደደ ነው።

ምክንያቱም መሬትን ቆንጥጦ ያየዘ ነው።

ምክንያቱም ጠንካራ ነው።

ምክንያቱም ግንድ ነው። እና...እኔ ፤ ሀገሬ ግንዱን ትመስለኛለች። ቅርንጫፎቹ መንግስታቷን። ቅጠሎቹ ደግሞ ማለዳ እንደ አዲስ በቅለው ማምሻውን እንደ አሮጌ የሚረግፉ ባለስልጣናቷን።

እና...

ሀገሬ ምን ጋኖች አልቀውባት በምንቸቶች ብትሞላ፤ ምን ለአንዱ በስንዝር ለሌላው በሄክታር ብትታደል፤ ዘወትር በእመቤት ወግ ባትኖር፤

በጭጋጋማ ቀናት ብትሸነፍም፣ በውርጭ ብትንዘፈዘፍም ፣ በብርቱ ንፍስ ብትናወጥም፣ በዶፍ ዝናብ ብትደበደብም

ሀገሬ ግንድ ናትና ንቅንቅ አትልም።

ዐውሎ ንፋስ በተነሳ ቁጥር ፣ ከባድ ዝናብ በጣለ ቁጥር፣ ትልቅ ዛፍ ሁሉ ቢወድቅ ዛፍ አይኖርም ነበር።

ነውጥ በተነሳ ጊዜ ሁሉ፣

ፈተና በበዛ ሰዓት ሁሉ፣

ሀገር የምትወድቅ ቢሆን ኖሮ #ኢትዮጵያ አትኖርም ነበር።

#ኢትዮጵያ ግን ቅርንጫፍ ስላልሆነች በቀላሉ አትቀነጠስም።

ቅጠል ስላልሆነች እንደዋዛ አትረግፍም።

ይልቅስ ፣ ለዘላለም ስር እንደሰደደች ትኖራለች።

💚ኢትዮጵያ 💛ለዘላላም ❤️ትኑር
#ሀገሬ_ከየት_ነው?

ከከረን ነች እሷ የኔ ቤት ባድማ
ፍሬ ሰቶን ጌታ ከባዕድ አውድማ
ጠየቀን በጊዜው ማደግ አይቀርማ
ሀገራችን የትነው ልጠይቅሽ እማ?
ልጄም አይጠረጥር መልካችንን ቢያየው
ነጠላ ለብሳለች ጃኖ ደርቤያለሁ
ውዳሴ ማሪያምን እሷም ታነባለች
እኔም እደግማለሁ
የት ብዬ ልናገር ሀገሬ ከየት ነው??

ቶናና በረካን አቦሉን ሳናስቀር
ቡና ጠጡ ማለት ባህላችን ነበር፤

መውጫዬ ከሷ ቤት ጓዳዋ ከኔ ጋር
ለብዙ አመት ባንድ ላይ ስንኖር
ሁለት ቁማርተኞች እጣ ተጣጣሉ
ነብሳችን ይዘው ይዋጣልን አሉ፤
እኔም ወንድሜ ላይ ጥይቱን ተኩሼ
ያሸነፍኩኝ መሰለኝ እራሴን አፍርሼ ፤

ልጄስ ምን ይለኛል ለማን ይነገራል
ሀገሬ ሁለት ነው ገና ስል ያመኛል
ያመኛል ያመኛል........……
አልናገር ነገር እምባ ይቀድመኛል !
ዛሬ ግን......
ነገን በመናፈቅ ስቆጥር ዘመኑን
ፀፀት እየፈጀኝ ሳላቀው ሀገሬን
ይኸው አፉን ፈታ የት ብዬ ልናገር
መላው ካንቺ ጋር ነው ተናገሪ ምድር
ድምፅሽን አሰሚኝ የ ት ነ ው የ ኛ ሀ ገ ር
#ሀገሬ_ኀምሳ_እግር_ናት

የሀገሬ ወንዝ ዋናው ካነገባሩ ሲዘረዘር በንዴት እበግናለሁ።ፉት እንለው፣ ለቅለቅ እንልበት ውሃ ፍለጋ ከከተማ እስከ ገጠር
የምንማስነውን እኛን አስቤ ብግን እላለሁ፡፡

የሀገሬ ቀንድ ከብት ቁጥር፣ ከአፍሪካ አንደኛ” ተብሎ ሲጠራ በንዴት እንተከተካለሁ፡፡ ወተት እየተራጨን በማደግ ፈንታ የላም ወተት የዋልያ ወተት ይመስል ብርቅ የሆነብንን እኛን አስቤ ትክን እላለሁ፡፡

የሀገሬን ስፋት ሳስብ እናደዳለሁ፡፡ የእኔ የምንለው ክብሪት ሣጥን ታክል ቦታ አጥተን በየፊውዳሉ ቤት በጭሰኝነት የልጅነት ሀብታችንን ለምንገብረው እኛ ተቆርቁሬ፣ በንዴት እንገረገባለሁ፡፡

ይሄ ሁሉ እያላት ለእኛ ያልተረፈችው ሀገሬ፣ ሀብት እያላት ድሃ ናት፡፡ ሀገሬ ኀምሳ እግር ናት፡፡

ያ..... ሁሉ...... እግር እያለው ዘልአለም እንደሚድኸው ቆሞ እንደማያውቀው ኀምሳ እግር፡፡

ከምትድህበት አንስቶ በኀምሳውም እግሯ የሚያቆማት ጎበዝ እስክታገኝ ሀገሬ ኀምሳ እግር ናት፡፡

#በሕይወት_እምሻው
#ሀገሬ

ሀገሬ ውበት ነው፣
ለምለምና ነፋስ የሚጫወትበት፣
ፀሃይ የሞላበት፣ ቀለም የሞላበት።
ሀገሬ ቆላ ነው፣ ደጋ ወይና ደጋ፣
እዚያ ብርሃን አለ ሌሊቱ እስኪነጋ።
ሀገሬ ተራራ ሸለቆ ረባዳ፣
ሀገሬ ጅረት ነው ገደልና ሜዳ፣
ውበት ነው በበጋ ፀሃይ አትፋጅም፣
ክረምቱም አይበርድም፣
አይበርድም፣ አይበርድም።
ሀገሬ ጫካ ነው፣
እንሰሳት አራዊት የሚፈነጩበት፣
በወጥመድ ሳይገቡ ሳይነካቸው ጠላት።
እዚያ አለ ነፃነት፣
በሀገር መመካት፣
በተወላጅነት፣
በባለቤትነት፣
እዚያ አለ ነፃነት።
ሀገሬ ሃብት ነው፤
ጎመኑ ስብ ጮማ፣ ቆሎው ክትፎ ስጋ፣
ድርቆሹ ፍትፍት ነው፣ ቃሪያው ሙክት ሠንጋ፣
ጠጁ ነው ወለላ፣
ከኮኛክ ያስንቃል የመንደሩ ጠላ።
እህሉ ጣእም አለው እንጀራው ያጠግባል፣
ከቢራ ከሻምፓኝ ውሃው ይጣፍጣል፣
በዓሉ ይደምቃል፣
ሙዚቃው ያረካል፣
ጭፈራው ዘፈኑ ችግርን ያስረሳል።
እዚያ ዘመድ አለ፣
ሁሉም የናት ልጅ ነው፣
ሁሉም ያባት ልጅ ነው፣
ጠላትም አንዳንዴ ይመጣል መቃብር፣
ባለጋራም ቸር ነው “ያገር ልጅ ሲቸገር” ፤
ገነት ነው አገሬ።
ምነው ምን ሲደረግ ?
ምነው ለምን እንዴት ?
ዘራፊ ቀማኛ ምቀኛ ወንበዴ፣
ጥርኝ አፈር በጁ ስንዝር ወሰን አልፎ፣
የተቀደሰውን ያፍሪቃ ላይ ደሴት፣
ባያገኝ ለማርከስ ጠላት ይመኝ እንዴት።
እምቢኝ አሻፈረኝ፣
አሻፈረኝ እምቢ፣
መቅደስ ነው
ሀገሬ
አድባር ነው
ሀገሬ
እናትና አባት ድኸው ያደጉበት፣
ካያት ከቅደም አያት የተረካከቡት፣
አፈር የፈጩበት፣
ጥርስ የነቀሉበት።
ሀገሬ ዓርማ ነው፣ የነጻነት ዋንጫ፣
በቀይ የተጌጠ ባረንጓዴ ቢጫ።
እሾህ ነው
ሀገሬ
በጀግናው ልጅ አጥንት የተከሰከሰ፣
ጠላት ያሳፈረ አጥቂን የመለሰ።
ሀገሬ ታቦት ነው ፣ መቅደስ የሃይማኖት፣
ዘመን የፈተነው በጠበል በጸሎት።
ለምለም ነው
ሀገሬ
ውበት ነው
ሀገሬ
ብሞት እሄዳለሁ ከመሬት ብገባ፣
እዚያ ነው አፈሩ፣ የማማ ያባባ።
ስሳብ እሔዳለሁ ቢሰበርም እግሬ፣
አለብኝ ቀጠሮ ከትውልድ
ሀገሬ
አለብኝ ቀጠሮ
ከትውልድ አገሬ፣
ካሳደገኝ ጓሮ።

©🔘ገብረ ክርስቶስ ደስታ🔘
👍1
#ሀገሬ

የድልሽ ውብ ምስል
ሰንደቅሽ ላይ ሲሳል
በልጆችሽ ገድል
የጎጥ ካብ ይፈርሳል።

🔘ኢዛና መስፍን🔘
👏228👍8
#ሀገሬ_ኀምሳ_እግር_ናት

የሀገሬ ወንዝ ዋናው ከነ ገባሩ ሲዘረዘር በንዴት እበግናለሁ።ፉት እንለው፣ ለቅለቅ እንልበት ውሃ ፍለጋ ከከተማ እስከ ገጠር
የምንማስነውን እኛን አስቤ ብግን እላለሁ፡፡

የሀገሬ ቀንድ ከብት ቁጥር፣ ከአፍሪካ አንደኛ” ተብሎ ሲጠራ በንዴት እንተከተካለሁ፡፡ ወተት እየተራጨን በማደግ ፈንታ የላም ወተት የዋልያ ወተት ይመስል ብርቅ የሆነብንን እኛን አስቤ ትክን እላለሁ፡፡

የሀገሬን ስፋት ሳስብ እናደዳለሁ፡፡ የእኔ የምንለው ክብሪት ሣጥን ታክል ቦታ አጥተን በየፊውዳሉ ቤት በጭሰኝነት የልጅነት ሀብታችንን ለምንገብረው እኛ ተቆርቁሬ፣ በንዴት እንገረገባለሁ፡፡

ይሄ ሁሉ እያላት ለእኛ ያልተረፈችው ሀገሬ፣ ሀብት እያላት ድሃ ናት፡፡ ሀገሬ ኀምሳ እግር ናት፡፡

ያ.....    ሁሉ......  እግር እያለው ዘልአለም እንደሚድኸው ቆሞ እንደማያውቀው ኀምሳ እግር፡፡

ከምትድህበት አንስቶ በኀምሳውም እግሯ የሚያቆማት ጎበዝ እስክታገኝ ሀገሬ ኀምሳ እግር ናት፡፡

🔘በሕይወት እምሻው🔘


#Subscribe #Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ተባበሩ #Subscriber
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👏21👍145