አትሮኖስ
280K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
477 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

//
ራሄል በወላጆቿ ቤት ከመዋኛ ገንዳ አጠገብ ከእናትና አባቷ ጋር ተቀምጣ የጥዋት ፀሀይ እየሞቀች ነው፡፡

ፀጋ   ‹‹ አበባ ስጪኝ?››ስትል እህቷን ጠየቀች፡፡

ራሄል ከተቀመጠችበት ተነሳችና   የፀሐይ መነፅሯን ወደ ጭንቅላቷ ገፋ በማድረግ   እህቷ የፈለገችውን  አበባ ቀነጠሰችና በትናንሽ እጆቾ ውስጥ አስቀመጠችላት…ፀጋ በደስታ ፈነጠዘች፡፡
ሮቤል እና አዲሷ ረዳት የፋውንዴሽኑን ስራ ከአሰበችው በላይ  በጥሩ ብቃት እየመሩላት እንደሆነ ለሁለት ቀን ወደቢሮ ተመልሳ ባደረገችው የስራ ግምገማ መረዳት ችላለች፡፡
…እህቷን ለማስታመም በሆስፒታል ባሳለፈቻቸው አስር ቀናት ውስጥ ምንም የጎደለ እና ሳይሰራ የተወዘፈ ስራ አልነበረም…እና አሁንም ለሌላ አንድ ሰምንት ታናሽ እህቷ በደንብ እስክታገግም አብራት እንድትሆንና ቀለል ያሉ  ስራዎችን እዛው እቤት ሆና እንድትሰራ ፈቅደውላት እሷም ተስማምታ  ወላጇቾ ቤት ነው ያለችው፡፡

‹‹ኤሊ እመጣለሁ ያለው መቼ ነው?››ወ.ሮ ትርሀስ  መጽሃፏቸውን  ከጎኗቸው  ባለ የመስታወት ጠረጴዛ ላይ አስቀምጠው ራሄልን  ጠየቋት።

‹‹ከሶስት እስከ  አራት ሰዓት እመጣለሁ ነበር ያለው ፡፡ ››መለሰች…ጸጋ  ራሷ ቀጥፋ የሰጠቻትን አበባ  ፀጉሯ መካከል ሻጠችላት…ራሄል  በፈገግታ እህቷን ወደራሷ ሳበችና ጉንጮን በመሳም‹‹ትንሿ እህቴ ..እንዲህ ስላሳመርሺኝ አመሰግናለው››አለቻት፡፡
በዛው ቅፅበት ወደግዙፉ ግቢ እየቀረበ የሚመጣ የመኪና ድምፅ ተሰማ ፡፡

‹‹የምትጠብቂው ጓደኛሽ  አለ እንዴ?››አቶ ቸርነት ጠየቁ፡፡

‹‹ አይ አይመስለኝም?››ራሄል እርግጠኛ ባለመሆን ጠየቀች፡፡

‹‹እንግዲያው አለም መጥታ ማንነቱን እስክታሳውቀን እንጠብቅ  ?››በማለት እናቷ ሳቁ።

አለም ወዲያው እየተፍለቀለቀች መጣች…‹‹ራሄል  ነይ እንግዳሽን ተቀበይ››

‹‹ማን ነው?››

‹‹አትንገሪያት ተብያለው…እራስሽ መጥተሸ እይው››አለችና ወደኪችኗ ተመለሰች፡፡

ራሄል.‹‹ማነው በወላጆቼ ቤት ከእኔ ጋር እንዲህ አይነት ጫወታ ለመጫወት የደፈረው?››በማለት ተነስታ ፀጋን ይዛ   ሄደች።ራሄል እና ፀጋ  ወደ ግቢው የመኪና ማቆሚያ አካባቢ ሲሄዴ ኤሊ ወደ ውስጥ ሲገባ ተመለከቱት  ።ራሄል እንዳየችው  በውስጧ የደስታ ማዕበል አጥለቀለቃት።

ባለመኪና ስትጠብቅ ባለሞተር ሰው በማየቷ ተደንቃ ‹‹ሄይ፣ እንዴት እዚህ ደረስክ? የሞተር ሳይክልህን ድምፅ አልሰማሁም።››አለችው…

ዔሊ ጎንበስ ብሎ በቀስታ ሳማት እና ፀጋን አንስቶ ካቀፋት በኃላ‹‹ሌላ አይነት  የመጓጓዣ ዘዴ ነው የተጠቀምኩት.››ሲል መለሰላት፡፡

‹‹ሞተርህ ተበላሸች እንዴ ?›› አለችና አይኖቾን ወደመኪና ማቆሚያ አዞረች  ከእሷ   ቀይ መኪና  አጠገብ የቆመ ባለ ሰማያዊ ቀለም  መኪና እያየች ግራ ተገባች።

‹‹ ያን መኪና  ከማን ነው የተዋሰከው? ወንድምህ እንደዚህ አይነት መኪና የለውም።››

ዔሊ ተነፈሰ። ‹‹እነሆ፣ ወ.ሮ ራሄል  ሞተሬን ሸጥኩት።››

ራሄል መኪናዋን በድጋሜ  ተመለከተች፣ ‹‹ሞተር ሳይክልህን አስወገድከው !አየህ እኔ ስለ አንተ የምወደው ያን  ነው ። ቆንጆ እና ፈጣን ተማሪ ነህ….ግን ለምን?››

…‹‹ደህና፣ በአንድ ወቅት አንድ ሰው እንዴት አንድ ኃላፊነት የሚሰማው ለዛውም የህፃናት ሀኪም የሆነ ሰው ሞተር ሳይክል ይነዳል ? የሚል  ጥያቄ ጠየቀኝ። እና ለእሱ መልስ ለመስጠት ብዬ ነው መኪና የገዛሁት፡፡››

ራሄል ወደ መኪናው ሄዳ እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ  ትንሽ ነካችው፣ ከዚያም ወደ ዔሊ ተመለሰች፣ ››

‹‹አስደንቀኸኛል ››አለችው

‹‹ስለሞተር ሳይክሎች ያለሽን ስሜት ስለማውቅ  እናም የፍራቻሽም ምክንያት በከፊል ትክክል መሆኑን ስላመንኩበት  ነው...››

እዛው የሳሎኑ በረንዳ ላይ ካሉ ወንበሮች አንዱን እንዲቀመጥ ሳበችለት ፀጋን በክንዱ እንዳቀፈ ተቀመጠ….ከጎኑ ሌላ ወንበር ስባ ተቀመጠች፡፡

ከዛ ሳታስበውና ምንም ሳትዘጋጅበት ትልቅ  ቁም ነገር ከአንደበቱ አፈትልኮ ወጣ  ‹‹ይህን ሁሉ  በትክክለኛው መንገድ ይፋ   ማድረግ ፈልጌ ነው …ራሄል፣ ላገባሽ እፈልጋለሁ።››አላት፡፡

ጆሮዎቾን ማመን አልቻለችም…ልቧን  ደረቷን ሰንጥቆ እንዳይወጣ የፈራች ይመስል ደግፋ ያዘችው ። በውስጧ የሚንተከተከው ደስታ እና ፍቅር እና ምስጋና መውጫ ለማግኘት እየሞከሩ በአንደበቷ ላይ ተንገዋለሉ….ማልቀስ ብቻ ነው የቻለችው፡፡

‹‹ሄይ እኔ ያን ያህል መጥፎ ነገር አልተናገርኩም….ለምን ታለቅሻለሽ?››

‹‹በጣም ደስ ብሎኝ ነው…..››ስትል በለሆሳሳ መለሰችለት፡፡‹‹እወድሀለሁ ኤሊ›› ወደ እሱ ተሳበችና ጉንጩን ሳመችው..ታፋው  ላይ የተቀመጠችው ፀጋ  በደስታ እጆቿን እያጨበጨበች በሳቅ ተንከተከተች። የእሷ ሳቅና ደስታ ወደ እነሱም ተጋባ፡፡

‹‹መጀመሪያ ዝም ብዬ ለአንቺ ምንም ሳልነገርሽ ወደቤተሰቦችሽ ሽማግሌ ለመላክ አቅጄነበር …››

‹‹እንዴ የእኔን ሀሳብ ሳታውቅ ሽማግሌ ልከህ እምቢ ብልህስ?››

‹‹ያው ምን አደርጋለው የተሰበረ ልቤን  ይዤ  የብቸኝነት ኑሮዬን ቀጥላለዋ !!››ብሎ ትከሻውን ነቀነቀ።ራሄል ጣቷን ከንፈሩ ላይ አድርጋ ሳቀች።

‹‹ ስለነርከኝ ደስ ብሎኛል፣ደግሞ ስትነግረኝ  ፀጋ በመሀከላችን መገኘት በመቻሏ  ደስታዋ ድርብ  ሆኗል … ለነገሩ እኛን አንድ ያደረገች እሷ ነበረች.››

‹‹እሺ ስላልሽኝ ደስ ብሎኛል…:በዚህ ምክንያት በህይወቴ ለሆነው ነገር እግዚአብሔርን በየቀኑ አመሰግነዋለሁ:: በአንቺ ምክንያት ህይወቴ መሉ ሆኗል››

‹‹አንተ ስጦታዬ ነህ ኤሊ ›› አለችና አቀፈችው።

‹‹አሁን እናትና አባትሽን እንፈልግ።››

ተስማሙና …ተያይዘው በአረንጓዴ ተክሎች ወደተሸፈነው ግዙፉ ጊቢ  ተያይዘው እየተሳሰቁ ሄዱ፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
80👍18
አንደኛ ሰርጋቸውን ከሁለት ወር ባነሰ ጊዜ እንዲደረግ ማድረግ፡፡ሁለተኛ  ደግሞ ሰርጋቸው ተደግሶ ባል እና ሚስት ተብለው አንድ ቤት ተጠቃለው እስኪገቡ ድረስ ይሄንን ፀጋ ልጁ እንደሆነች የሚገልፀውን ደብዳቤ እንዳያገኘው ማድረግ፡፡
እነዚህን ውሳኔዎች ከወሰነች በኃላ ነው የተወሰነ መረጋጋት ስለተሰማት እንቅልፍ የወሰዳት፡፡

ተፈፀመ

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
35👍10🤔4
#የፀሎት_ፉክክር
.
ለረጅም ዘመናት
እግዚአብሔር ይስጥልኝ እየተባለበት፤
በእያንዳንዱ ሠው አፍ እግዜር ዕዳ አለበት፤
እያሉ ሠምቼ
ይኸው መጥቻለሁ
እሱ ይስጥህ እያሉ ሲልኩኝ ወዳንተ፤
በል እግዜር መፅውተኝ
ምሰፍርበት አጣሁ
ምድሩን ዘር ዘርተውት
እንኳን ለኔ ቀርቶ ቦታ የለም ላንተ፤
.
ብዛ ተባዛባት
ምድሪቱንም ሙላት ብለህ ስትልከኝ፤
ምን አስበህ ይሆን?
እንደሚታነቅ ሰው ባዶ ኪስ የላክከኝ?፤
.
ፍቃድ ትዕዛዝህን
ላከብር ልበዛ ኑሮ ልጀምር ስል፤
እንዳልከው አልሆነም
አብስትራክት ሆኗል የዚህች ምድር ምስል፤
.
ፈጣሪ ሆይ ፍረድ!
በደላቸው በዛ ትዕግስትህን አይተው፤
የገዛ መሬትህን
እየሸጡልኝ ነው በስንዝር ለክተው፤
.
ወይ ምድርህን ስጠኝ
ወይ ስንዝሩን ቀማ፤
መሬቴን ብቻ ሆኗል
የዚህች ምድር ዜማ፤
እኔ አላማረኝም
መሬትህን ውሰድ በሠው ሳትቀማ፤

🔘ልዑል ሐይሌ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍2010
?ወይስ እግዚያብሄር…?›› ትንፋሽ ወሰደችና ንግግሯን ቀጠለች….‹‹….ልጄ  ወተት ያስፈልጋታል...እኔም መብላት ባልችልም ቀምሼም ቢሆን ማደር አለብኝ...እናቴም አየር ስባ ብቻ አይደለም የምትኖረው….አንገታችን የምናስገባበትን እና ጎናችንን የምናሳርፍበት ደሳሳ ጎጆም  ከመንግስት በችሮታ የተሰጠን ሳይሆን በ6000 ብር የተከራሁት ነው..ነው ወይስ አራስ ልጄን  እና ደህነት እና በሽታ ተባብረው  ያደቀቋትን እናትኔን  ይዤ ጎዳና በመውጣት መንገድ ጠርዝ ጨርቅ አንጥፌ ልለምን?ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው አሉ….ዳሩ ወንድ አይደለህ.. ማስታቀፍ አንጂ መታቀፍ ምን እንደሆነ ጣጣውን እና መዓቱን የት ታውቃለህ?፡፡››

በንግግሯ ደነዘዝኩ ..ጭንቅላቴን ራስምታት ሲወቅረኝ ይታወቀኛል‹‹ይቅርታ ..ስሜታዊ ሆኜ ነው… አሁን ልጅሽን ማን ነው የሚጠብቀልሽ?››ስል ቀዝቀዝ ብዬ ለስለስ ባለ የድምፅ ቃና ጠየቅኳት፡፡

‹‹እናቴ››

‹‹አይቸገሩም?››

‹‹ታስቸግራለች..ግን ብዙ ጊዜ አዳር አልሰራም… ሁለትም ሆነ ሶስት ሰዎችን አግኝቼ ሾርት ከሳራው በኋላ ያገኘኋትን ብር ይዤ ስድስትም ሳባትም ሰዓት ወደቤቴ እገባ ነበር… ዛሬ ግን እንደዛ ስላልቀናኝ ነገ ደግሞ የግድ የቤት ኪራዬን መክፈል ስላለብኝ እና ለዛ የሚሆን በቂ ብር እጄ ላይ ስለሌለ ነው አዳር ለመስራት የወሰንኩት፡፡››

‹‹ሞባይሌን አወጣሁና ሰዓቴን አየው 5፡25 ይላል..ኪሶቼን በረበርኩና ጥዋት ለታክሲ ይሆነኛል ብዬ ሀምሳ ብር ብቻ አስቀረሁና ሌላውን መዳፎ ላይ አስጨበጥኳት.. ከተስማማንበት ሂሳብ ቢያንስ በእጥፍ ይበልጣል….

‹‹በቃ… ለልጅሽ ሂጂላት››

‹‹ለምን?››

‹‹በቃ ሂጂላት››

‹‹ቢያንስ አንዴ ተጠቀምና  ልሂድ››

‹‹አይ አልችልም ስሜቴ ደፈራርሷል››

ለመጀመሪያ ጊዜ ፈገግ አለች..ለሽርፍራፊ ሰከንድ ቢሆንም ውስጧ ያለችው አሮጊት ስትከሳ እና ከውጭ የሚታየው ወጣትነቷ ሲፈካ ታዘብኩ‹‹ በጣም ነው ማመሰግነው..በእውነት ከጭንቀት እና ከስጋት ነው የገላገልከኝ….፡፡በድኔ ብቻ ነበር እዚ ያለው…፡፡ ስጋዬም  ነፍሴም ልጄ ጋ ነበር፡፡››እየመረቀችኝ ልብሶቾን ለበሰች… ሞባይሌን ተቀብላ ቁጥሯን መዘገበች ና መለሰችልኝ‹‹ቁጥሬ  ነው ብትደውልልኝ ደስ ይለኛል›› አለችኝ፡፡

‹‹እሺ እደውልልሻለው.. ለማንኛውም አንቺ በርቺ››

‹‹ወድጄ እበረታለው..››አለችኝና ንግግሯን ቀጠለች‹‹በጣም ይገርማል ››አለችኝ፡፡

‹‹ምኑ?››

‹‹ወንዶች ስትባሉ  እንደየመልካችሁ  ባህሪያችሁም ብዛቱ ..ስንቱ አውሬ እና ማሰብ የተሳነው የአእምሮ ድኩማን አለ መሰለህ… እነሱን አስበህ በአዳም ልጆች ተስፋ ልትቆርጥ ስትል ደግሞ እንደ አንተ አይነት በግ  ያጋጥማሀል፡፡››

‹‹በግ?››አልኰኳት … ደንግጬም ተገርሜም፡፡

‹‹ይቅርታ በግ ስልህ ሞኝ ለማለት ፈልጌ አይደለም… ፡፡የዋህ እና መልካም ሰው  ለማለት ነው ..ለማኛውም ብትደውልልኝ ደስ ይለኛል ፡፡ቆንጆ እና የምታምር ልጄንም አሳይሀለው››

‹‹እሺ አይልሻለሁ..››

‹‹እሺ ቻው››ብላኝ  በራፉን ከፋታ በመውጣት መልሳ ዘጋችልኝና ሄደች፡፡እርምጃዋ ቀስ እያለ እየደበዘዘ..እየደበዘዘ ለጆሮ እየሳሳ በስተመጨረሻ ጭልም ብሎ ሲጠፋ ተሰማኝ…፡፡

ግን ነገ ወይ በማግስቱ እደውልላት ይሆን? በውስጤ የተጫረ ጥርጣሬ የወለደው ጥያቄ ነበር፡፡ልደውልላትማ ይገባል….ስለዚህች ልጅ ታሪክ ጠለቅ ብዬ ባውቅ ደስ ይለኛል.. ?እንደዛ አይነት ጉጉት በውስጤ ተፀንሷል፡፡

ተፈፀመ

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍3224