አትሮኖስ
282K subscribers
112 photos
3 videos
41 files
492 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#አንቺ #ሰትስሚኝ😘

የምትዞርው አለም ባንዴ ትቆማለች
እሩቁዋ ጨርቃ ያኔ ትቀርባለች
ምድርም የዛኔ በእኛ ትደምቃለች ........................ ታሸበርቃለች
ልጆችዋ ነን እና እኛን ትድራለች አንቺ ሰትስሚኝ!!!!! ከተራራ እንደ መውደቅ ሰልጣን እንደ መልቀቅ ተሰቅሎ እንደ መታነቅ ሱሪ እንደ መውለቅ
ነብሴ ትጨነቃለች ልቤ ትመታለች አንቺን አንቺን ፍቅርን ትፈራለች አንቺ ሰትስሚኝ!!!!! ሞቶ እንደ መነሳት የወደቀ እንደ ማንሳት በጥይት እንደ መሳት ችግር እንደ መርሳት
ህይወቴ ታድሳ ብሩህ ትሆናለች
ጎዶሎዋ አለም ያኔ ትሞላለች አንቺ ሰትስሚኝ!!!!
ወፎች ያዜማሉ ኮዋክብት ይርግፍሉ
አማልክት ይወርዳሉ አራዊት ይታደማሉ
መንግሰታት መግደል ያቆማሉ ................ታክሲዋች ይጭናሉ ...............አዋቂዋች ይታዘላሉ
.................ነጋዴዋች ያተርፋሉ አንቺ ሰትስሚኝ!!!! ጽልመት ይባርራል ሰልጣንም ያርጃል
ህፃን ልጅም ያድጋል ግጥምም ያልቃል 
#አንቺ_ኮርቻ_ሰሪ

አንች ኮርቻ ሰሪ
ሳንቃውን አቅልይ፣ጠርዙን አለስልሺ
ያንዱ ፍጡር ወንበር
ላንዱ ፍጡር ቀንበር
መሆኑን አትርሺ።
#የይቅርታ_ልክ

#አንቺ
በፍቅር ገለሽኝ ገንዘሽ ቀብረሽኝ
አፈር አልብሰሽኝ ሔደሻል ትተሽኝ።
ነፍሴ ፤
በፈጣሪዋ ዘንድ
አትሙት ያላላት የተሰጣት ክብር
ዳግም ነፍስ ዘርታ
ሞትሽን ድል ነሳች ወጣች ከመቃብር፡፡
#እኔ
ከጥልቁ ጉድጓድ በነፃነት ወጣህ-
ያለሽበት ድረስ ልፈልግሽ መጣሁ፡፡
እኔ እንደአንቺ አይደለህ
ስለፍቅር ብዬ ይቅር ብዬሻለሁ፡፡
ልቤንም አፅድቼ
እጆቼን ዘርግቼ
እንደድሮ ላቅፍሽ መንገድ ጀምሬያለሁ፡፡
አደራ ፍቅርዬ
ደመ ነብስሽ ነግሮሽ
ድንገት ቀና ብለሽ ስትመለከቺ
ከርቀት ብታዪኝ ስመጣ ወደ አንቺ
ሙት መንፈስ መስዬሽ እንዳ ደነግጪ
ይኸውልሽ ካላመንሽ ቆይ እጅሽን አምጪ
ደረቴ ሥር አርገሽ
የልብ አመታቴን ከልብሽ አድምጪ
መላው አካላቴን
ዳብሰሽ በጣቶችሽ ዳሰሽ አረጋግጪ፡፡
እኔው እራሴ ነኝ!
ያጠፋሁት ካለ
ለሠራሁት ስህተት ፍቅሬ ይቅር በይኝ
ይቅርታ ቢስ ከሆንሽ
በይ እንደለመድሽው ካሰኘሽ ግደዪኝ፡፡
እሞትልሻለሁ!
እንዳንቺ አይደለሁም በፈጣሪ አምናለሁ።
ሞትሽን ድል ነስቼ ዳግም እነሳለሁ።
ሺ ጊዜ ብትገዪኝ
እልፍ አዕላፍ ጊዜ ይቅር እልሻለሁ ፤
ምክንያቱም ፍቅሬ
በንፁህ ልቦና እኔ አፈቅርሻለሁ፡፡

🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
#አንቺ_እና_እኔ

#አንቺ
“ጠፊ አላፊ ናቸው ጥላቻና ውበት
ግና ግና
ሕያው ሆኖ ኗሪ ምንግዜም ባለበት
ገንዘብ ማይረታው
ሁኔታ ማይፈታው
ሥፍራ ማይቀይረው ዕድሜ ማይጫጫነው
ፅኑ አምድ በዓለም በፍቅር ማመን ነው፡፡”

#እኔ

ስትዪኝ አምኜ
“ገዳሜ ነሽ ብዬ ባንቺ ሥር መንኜ
እንደጥላሽ ሆኜ
ስትሔጅ ስከትልሽ
አልቅስ አልቅስ ሲለኝ ደስ ደስ ሲልሽ
እንደሰው ኖርሽብኝ፤ እንደሰው ኖርኩልሽ፡፡
አንቺ- እንቆልልህ!.. እኔ - ምናውቅልሽ!..

🔘ፋሲል ተካልኝ🔘
#አንቺ_ሙቺ ...

ኑርልኝ ብትይኝ
እንዳሻሽ ኖርኩልሽ፣
ሙትልኝ ስትይኝ
እንዴት ልቀበልሽ፣
እኔ ከሞትኩ ወድያ
ማን ያሞላቅሽ፣
ይልቅ አንቺ ሙቺ
ልውጣ ከእስርሽ !

🔘ሀብታሙ ወዳጅ🔘
👍1
#አንቺ_ተኝተሽ..

ሰርቄ ልቀፍሽ ፤ ሰርቄ ልሳሞሽ፤
ከባልሽ በፊት ነው ፣ ልቤ የሚያስብሽ።
ለልቤ...
ከባልሽ በፊት ነው ፣ ላንቺ የዳርኩለት፤
እንደወዶ ገባ የተበረከለት፤
የተገበርኩለት፤
ባክኖ ቀረ ሲሉኝ ፣ እንደተራ ስለት፤
እናደው ጀመረ ፤ እፈርሰወ ጀመረ፤
ወድጄ መሰለሽ
የሳሙትን ከንፈር ፣በሌላ ሲወዛ፣
ያሳደጉትን ነፍስ ፣ በተንኮል ሲገዛ፣
መታዘብ ያበሽቃል፤
እኔ ጋር ስትመጪ ፣ መበሸቄ ይወድቃል።
ባልሽን እርሺልኝ!
መንትፊ ልቀፍሽ ፤ ደብቀሽ እቀፊኝ፤
ጨለማን ስናስስ ፣ ከብርሃን ስፊኝ።
ልርሳው መነጠቁን፤
ከመውደቄ ይልቅ ፣ እኔን የሚገለኝ ፣ ያረዳኝ መወደቄን፤
መስረቅ ቢኾን ኀጢአት ፣ በሰወ የሚያስነቅፍ
እንዴትሞ አልሰማ፣ጆሮዬ ካንቺ እቅፍ።
እቅፍቅፍ ...
እጥሞጥሞ...
ትጥምጥም...
ሞቴ ባንቺ ሰጥሞ፡፡
አበጀሁሁሁሁ ሰረቅኩሽ፤
እሞጳ!!!
ይኸው ሳሞኩሽ።
እሠይ እዘርፋለሁ ፤ መቃብር እስክኾን፤
ማነው የሚያውቅልኝ
ባልሽስ ራሱ ፣ ከኔ ዘርፎሽ ቢኾን?
ኧረ..
ትዳር በቀደመ?
ይቅድመኝ፤
ግድ የለኝ።
የሰው ነሽ እያልኩኝ ኑሪልኝ ከእቅፌ፤
እንኳንና ሞቴ ፣ አይመጣም እንቅልፌ።
ሰርቄ ልቀፍሽ ፤ ሰርቄ ልሳሞሽ፤
ከባልሽ በፊት ነው ፣ ልቤ የሚያስበሽ፤
በይ...
ደርቢ እንዳይበርድሽ።
... አስክትነቂ ተጻፈ

🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
👍1
#አንቺ. . .

እንደዘመኑ ሴት፤
መኪና ላለው ወንድ ጭንሽን ማትከፍቺ ኑሮን ለማሸንፍ፣
የምትታትሪ የምትሟሟቺ
አንቺ. . !

በአቋራጭ ሄደሽ ቁማር ሳትቆምሪ በጉልበት በላብሽ፤
የራስሽን ህይወት ምታስተዳድሪ ቤተክርስቲያን ብለሽ፤
ከቦርጫም ሰውዬ ጋ ክለብ የማታድሪ
አንቺ .. !

የሄዋን ምሳሌ የሴትነት ልኩ
መልካም ፀባይ ያለሽ የጨዋነት መልኩ

ዘመንሽ ይለምለም ...
በበረከትና በፀጋ ተከቦ
መልካሙ ፈጣሪ ፤
መልካሙን በሙሉ ጀባ ይበልሽ አቦ! ! !

🔘እዮብ🔘
🥰41👍172