አትሮኖስ
282K subscribers
112 photos
3 videos
41 files
492 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#አንቺ_ተኝተሽ..

ሰርቄ ልቀፍሽ ፤ ሰርቄ ልሳሞሽ፤
ከባልሽ በፊት ነው ፣ ልቤ የሚያስብሽ።
ለልቤ...
ከባልሽ በፊት ነው ፣ ላንቺ የዳርኩለት፤
እንደወዶ ገባ የተበረከለት፤
የተገበርኩለት፤
ባክኖ ቀረ ሲሉኝ ፣ እንደተራ ስለት፤
እናደው ጀመረ ፤ እፈርሰወ ጀመረ፤
ወድጄ መሰለሽ
የሳሙትን ከንፈር ፣በሌላ ሲወዛ፣
ያሳደጉትን ነፍስ ፣ በተንኮል ሲገዛ፣
መታዘብ ያበሽቃል፤
እኔ ጋር ስትመጪ ፣ መበሸቄ ይወድቃል።
ባልሽን እርሺልኝ!
መንትፊ ልቀፍሽ ፤ ደብቀሽ እቀፊኝ፤
ጨለማን ስናስስ ፣ ከብርሃን ስፊኝ።
ልርሳው መነጠቁን፤
ከመውደቄ ይልቅ ፣ እኔን የሚገለኝ ፣ ያረዳኝ መወደቄን፤
መስረቅ ቢኾን ኀጢአት ፣ በሰወ የሚያስነቅፍ
እንዴትሞ አልሰማ፣ጆሮዬ ካንቺ እቅፍ።
እቅፍቅፍ ...
እጥሞጥሞ...
ትጥምጥም...
ሞቴ ባንቺ ሰጥሞ፡፡
አበጀሁሁሁሁ ሰረቅኩሽ፤
እሞጳ!!!
ይኸው ሳሞኩሽ።
እሠይ እዘርፋለሁ ፤ መቃብር እስክኾን፤
ማነው የሚያውቅልኝ
ባልሽስ ራሱ ፣ ከኔ ዘርፎሽ ቢኾን?
ኧረ..
ትዳር በቀደመ?
ይቅድመኝ፤
ግድ የለኝ።
የሰው ነሽ እያልኩኝ ኑሪልኝ ከእቅፌ፤
እንኳንና ሞቴ ፣ አይመጣም እንቅልፌ።
ሰርቄ ልቀፍሽ ፤ ሰርቄ ልሳሞሽ፤
ከባልሽ በፊት ነው ፣ ልቤ የሚያስበሽ፤
በይ...
ደርቢ እንዳይበርድሽ።
... አስክትነቂ ተጻፈ

🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
👍1