#ፍቅር_ከፈላስፋ
፡
፡
#ክፍል_ስድስት
✍
፡
፡
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
፡
፡
#ፍስሀ
===
ስልኬን አነሳውና ደወልኩ አስተዳደሩ ቢሮ
‹‹…ሄሎ የሴት ድምጽ ነው››
‹‹ማነች ፀሀፊዋን ቢሮ ባስቸኮይ ነይ በያት››
‹‹ፀሀፊዋ ነኝ››
‹‹እንግዲያው ቶሎ ነይ…ከአለቃሽ ጋር..አሁኑኑ ››ጆሮዋ ላይ ጠረቀምኩባት…ልክ አስገባቸዋለው..ሁለቱንም ለድፍረታቸው ተገቢውን ትምህርት ሰጪ ቅጣት ያገኟታል…
እኛ ኢትዬጵያውያን ለወሬ ያለን ፍቅር ለራሳችን ካለን ፍቅር በብዙ እጥፍ ይበልጣል፡፡እንደህዝብ ብቻ ሳይሆን በከፍተኛ ደረጃ ተምረዋል በሚባሉት የህብረተሰብ ደረጃ ጨምር የ<critical thinking >ልምምድ የለንም… የሰማነውን ወሬ ‹‹ለምን?›› ‹‹እንዴት?›› ‹‹የት?›› ‹‹ መቼ?›› ብለን በመጠየቅ የነገሩን ብልት በታትነን ለማየት የምናደርገው ጥረት ለዜሮ የቀረበ ነው፡፡የሰማነውን ወሬ ወይም መረጃ በዚህ መጠን መመርመር ደግሞ የመረጃዎችን ጥራት ለመጨመር..እርግጠኝነቱን አስተማማኝ ለማድረግ እና እወነተኝነቱን በአስተማማኝ መንገድ ለማረጋገጥ ወሳኝ መንገዶች ናቸው፡፡ ሰምተን ሳንጨርስ ለሌላው መናገር እንጀምራለን፡፡
መጡ‹‹ዝጉትና ቁጭ በሉ…››
ፊት ለፊት ተቀመጡ
‹‹ምን እየተሰራ ነው አቶ ሰይፉ››
‹‹ምን አጠፋን ጌታዬ…››በሚርበተበት አንደበት
‹‹እንደዚህች አይነት ሰራተኛ ይልኩብኛል…ነው ወይስ ይህንን እንድታደርግ እርሶ ነዎት የላኳት››
በቆሪጥ የእሷን መርበትበት ለማየት አይኖቼን ወደእሷ ስልክ ጭራሽ የምለውንም እየሰማች አይመስልም…ዘና ብላ የእጆቾን ጣቶች እየዘረጋችና እያጠፈች ከራሷ ጋር ትጫወታለች፡፡
<አረ እኔ…ለመሆኑ ምን አጠፋች?››
<በቃ ቡኃላ አናግሮታለው ከእሷ ጋር ልጨርስ> አመሰግናለው››
‹‹እሺ አቶ ፍሰሀ››ሹክክ ብለው ወጥተው ሄዱ…
ምን ልበላት እንድትደነግጥ እንዴት ልጩህባት እያልኩ በውስጤ ቃላት ስምርጥ
‹‹አንድ ነገር ልምከርህ›› አለቺኝ….
ይህቺ ልጅማ ጤነኛ አይደለችም…‹‹ምን አልሺኝ››
በምንም አይነት ሁኔታ ተራ ሰራተኞች ፊት የማናጅመንት አባላቶችህን እንዲህ ዝቅ አድርገህ አትናገር..ስህተት ቢሰሩም ጥፋት ቢኖርባቸውም ብቻቸውን ጠርተህ ነው ማነጋገር ያለብህ..ምክንያቱም አንተ ስታበሻቕጣቸው ያየ የበታች ሰራተኛ በትክክል ሊታዘዛቸው አይችልም. ያ ደግሞ ዞሮ ዞሮ የካማፓኒውን እፊሸንሲ ያወርደዋል…ያ ማለት ደግሞ ዞሮ ዞሮ በሰተመጨረሻ ያንተኑ አፈፃፀም ነው የሚጎዳው››
‹‹ጨረሽ››
‹‹አዎ ጨርሼያለው…ለምንድነበር የፈለከኝ?››
‹‹ማን ስለሆንሽ ነው ያለዘዝኩሽንን የሰራሽው?››
‹‹ምነው..? ላግዝህ ብዬ ነው››
‹‹ማን ስለሆንሽ ነው ምታግዤኝ?››
<አንድ ሰውን ለማገዝ እኮ ማንም መሆንን አይጠይቅም …ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው..››
ባክሽ አትቀባጥሪ ..ያ ሽማጊሌ ነው አይደል እንዲህ እንድታደርጊ የነገረሽ?..››…..በጥቂት ቀን ውስጥ ማን መሆኔን አሳየዋለው..አንቺ ግን ለእንጀራሽ ስትይ አደብ ግዤ>>
<<አንተም ለካንፓኒው ህልውና ሆነ ለራስህ የስራ ስኬት ስትል ምክሬን ስማ…..ደግሞ ለሽማግሌው ክብር ይኑርህ..ቅድም በስልክ ስታበሻቅጣቸው ላብ ሲያሰምጣቸው ነበረ…ለእሳቸው ሳይሆን ለራስህ ስትል አክብራቸው ..ደህና ሁን..››ብላኝ መቀመጫዋን ለቃ ወጥታ በራፍን በላዬ ላይ ዘግታ ሄደች…
አሁን አልተናደድኩም ..በጣም ደነገጥኩ…..ምንድነች ይህቺ ልጅ ..?ማንን ተማምና ነው እንዲህ መስመር የለቀቀችው…?እራሴን አመመኝ …ከዚህ በላይ ማሰብ ስላልቻልኩ ቢሮዬን ለቅቄ ወጣው ..ልጠጣና ልረሳት..እና ነገ አባርራታለው››
===
በጥዋት እንደገባው…አስጠራዋት….
‹‹እሺ ይህቺን ደብዳቤ ፃፊልኝ››
ቃል ሳትተነፍስ ተቀበለቺኝና ላፓቶፑ ፊትለፊት ተቀመጠችና መፀፋ ጀመረች…እየተከታተልኳት ነው….ስትባሳጭ ስትደነግጥ ለማየት ነበር በትኩረት እየተከታተልኮት የነበረው…ምንም አይነት የስሜት ለውጥ አልታየባትም …ደብዳቤው ስለ እሷ እንደሆነ አልገባትም ማለት ነው…ስሞን እያነበበች እንዴት አይገባትም…..?
‹‹ለወ/ሪት ፌናን ገመዳ
ጉዳዩ ፡ከስራ መሰናበትን ይመለከታል፡፡
ከላይ በርዕሱ ለመግለጽ እንደተሞከረው ካምፓኒውን ወደተሻለ ደረጃ ለማሳደግ አንድአንድ ለውጦች ማድረግ የግድ አስፈላጊ ስለሆነና ለለውጡ የሚመጥኑ ሰራተኞችና ማሰማራት የግድ በመሆኑ ይህ ደብዳቤ ከደረሶት ቀን አንስቶ ከስራ የተሰበናበቱ መሆንን አሳውቃለው፡፡
‹ከሰላምታ ጋር›
ፍሰሀ
ዋና ስራ አስኪያጅ
**
ይንን ነበር እንድትጽፍ የሰጠዋት..ለትዕቢተኛ እና ለስረአት አልበኛ ምህረት እንደሌለኝ እሷንም ሆነ ቀሪ ሰራተኞችን ማስተማር እፈልጋለው..እርግጥ የሰራችው ስራ ስህተት መሆኑን ተረድታ ይቅርታ ከጠየቀቺኝ ..በመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ልምራት እችላለው..አሁን ሳያት ግን ይቅርታ ለመጠየቅ ማሰቧን የሚጠቁም ምንም አይነት ምልክት አላየውም፡፡
‹‹ጨርሼያለው ፕሪንት ላድርገው››አለችኝ ጭራሽ የደሞዝ ማሻሻያ ደብዳቤ እንደደረሰው ሰራተኛ ፈገግ ብላ
‹‹አዎ አድርጊውና ልፈርም››
አዘዘችና ወደሚቀጥለው ክፍል ሄደች..ፕሪንተሩ ያለው የሚቀጥለው ክፍል ነው፡፡
ይዛ መጣችና አቀበለቺኝ… ልትወጣ ስትል‹‹ቆይ ልፈርምና መዝገብ ቤት ትወስጂዋለሽ››አልኳት ቆማ ትጠብቀኝ ጀመር..
በዚህ አይነት ስሜት ውስጥም እያለው የተመዘዘ ቁመቷን አለማድነቅ አልቻልኩም…..
ከመፈረሜ በፊት ማንበብ ጀመርኩ…‹‹እንዴ ምንድነው የጻፍሺው…?››እስኪ የሰጠውሽን ረቂቅ ስጪኝ…ወረቀቱን ልታነሳ ጎንበስ ስታል ጡቷቾ ተጋልጠው እይታዬ ውስጥ ገቡ..እርግጠኛ ነኝ ጡት ማስያዥ አላደረገችም….ብታደርግማ ይሄን ሁሉ የጡቶን ክፍል በግልፅ ማየት አልችልም ነበር……ከጠረጳዛው ላይ አነሳችና ሰጠቺኝ….
ከስራ መሰናበትን ይመለከታል ነው የሚለው..አንቺ የ30 ቀን ማስጠንቀቂያ መስጠትን ይመለከታ ብለሽ ነው የጻፍሺው…
ዝም ብለህ በፀባይ ብትጠይቀኝ ኖሮ ከነገ ጀምሮ ቀርልህ ነበር….ግን ነገም በሌላ ሰራተኛ ላይ ተመሳሳዩን ላርግ ስለምትል ህጉን እያስተማርኩህ ነው…‹‹ዝም ብለህ በፈለከው ሰዓት የፈለከውን ሰራተኛ ማባረር አትችልም….አንደኛ ይሄን ስራ ያንተ ሳይሆን የአስተዳደሩ ስለሆነ ለእሳቸው ብትተውላቸው….በስልጣንህ ተመክተህ አይ እኔ መስራት አለብኝ የምትል ከሆነ ደግሞ አንደኛ የሀገሪቱን የአሰሪና ሰራተኛ ህግ ሁለተኛ ሰራተኞች ከካንፓኒው ጋር የገቡትን የቅጥር ውል አንብበህ በውሉ ላይ በሰፈረው ህግ እና ደንብ መሰረት ነው እርምጃ መውሰድ የምትችለው…እንደ አንድ ማናጀር ሰውን ሳይሆን ኮንትራትን ነው ማስተዳደር ያለብህ …
በቃ ውጪልኝ..ደብዳቤውን ቀዳድጄ ቅርጫት ውስጥ ከተትኩና ቤሮውን ለቅቄ ወጣው ..በዚህ ስሜት ሌላ ምንም አይነት ስራ መስራት አልችልም….
ምን እየሆንኩ ነው…..አንድ ተራ ፀሀፊ መስመር ማስገባት ያልቻልኩ ሌሎቹን ምክትል ስራአስኪያጁን ጨምሮ የየክፍል ሀላፊዎች እንዴት አድርጌ ልመራ ነው…?አካሄዴንማ ማስተካከል አለብኝ...
💫ይቀጥላል💫
Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ
ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን መልካም ምሽት🙏

👍1
#ፍቅር_ከፈላስፋ
፡
፡
#ክፍል_ሰባት
✍
፡
፡
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
፡
፡
❤️ፌናን
===
ጥሎብኝ ውበት አድናቂ ነኝ፡፡ውበት ግን ምንድነው…?እኔ እንጃ ፡፡በስሜት ህዋሳታችን ተጠቅመን ወደ ውስጣችን ያስገባነው መረጀ ልባችን እና አዕምሮአችን ላይ በእኩል ጊዜ ሲደርስ እና መልሶ ወደ ስሜት ህዋሳታችን በመመለስ እንድንፈግ ወይም እንድንስቅ.. ወይ ደግሞ ጆሮአችን እንዲቆም ወይ ደግሞ በእግር ጥፍራችን የሚያቆም አይነት መደመም ላይ ሚጥለን ነገር ሲሆን ውበት ሚለውን ቃልን ልንጠቀም እንገደዳለን ፡፡
===
የእኔ ነገር … አሁን ስለውበት የእኔን ፍልስፍናዊ እሳቤ ልተነትንላችሁ ፈልጌ ሳይሆን ስለአዲሱ አለቃችን
ልነግራችሁ ስለፈለኩ ነው እንደዚህ ዙሪያ ጥምዝ ምሽከረከረው፡፡
ልጁ በጣም ያምራል…. በቃ የሆነ አትኩረው እንዲያዩት የሚያስገድድ ማግኔት ነገር ግንባሩ ላይ አለው…ለሆነ ሰከንዶች ያህል ደግሞ አትኩረው ሲያዩት አይን ደክም እንዲል ወይም እንዲርገበገብ የሚያደርግ አዚም አለበት….አዎ በአቅራቢያው ሲሆኑ ደግሞ ልብ በደቂቃ መምታት ከሚገባት ምት ወይም ማሰማት ከሚገባት ድውድውታ በሆነ ፐርሰንት እንዲጨምር የሚያደርግ ስውር ኃይል አለው፡፡
ጅኔራላይዝድ አረኩት አይደል…ይሄ ስሜት ስለአዲሱ ሀለቃዬን በተመለከተ እኔን የተሰማኝ ነው እንጂ የቢሮ
ሴት ሁሉ እንደዚህ እያሰባል ወይም እንዲህ ይሰማዋል ልላችሁ አይደለም….
ግን ገና ግማሽ ብስል ግማሽ ጥሬ ነገር ነው…ሙሉበሙሉ ለመብሰል ብዙ እንጨት መፍጀቱ አይቀርም… የዕውቀት ችግር የለበትም ….ያለበት የልምድ ችግር ነው፡፡ደግሞ ነፍሱ በፍራቻ እየተንፈራፈረች መሆኗን በደንብ ያስታውቅበታል…እርግጥ ይሄንን ከእኔ በስተቀር ያወቀበት ሰው የለም…ሌላው የቢሮ ሰራተኞች ስለኃይለኝነቱ….ተቆጪና ተናዳጅ ስለመሆኑ ብቻ ነው የሚያወሩት…..
አንደኛ ቁጣውም ሆነ ጩኸቱ አርቴፊሻል መሆኑን ከንግግሩ ድምጸት እና ከሰውነቱ እንቅስቃሴ በቀላሉ መረዳት ይቻላል…… ኃይለኛና ተፈሪ ለመሆን እየጣረ ነው..ሀይለኛ እና ተፈሪ መሆን የፈለገው ደግሞ ይህንን ካምፓኒ በትክክል መምራት እንደሚችል እራሱን አላሳመነም….ግን ደግሞ ሌሎቹን በቁጣና በማስፈራራትና ሊያሳምን እየጣረ ነው… እያደረገ ያለው ይሄንን ነው….፡፡ግን በዚህ መንገድ ፍጽም አይሳካለትም… ምክንያቱም ቀድሞ እራሱን መሳማን ሳይችል እንዴት ነው ሌላውን ሊያሳምን የሚችለው…?ይሄ የብዙ ሰዎች ባህሪ ነው..ሁልጊዜ የሌላው ፀባይ እንዲስታካከል..ሌላው ሰው እንዲለወጥ…ሌላው ሰው ወንጀል መስራት እንዲያቆም..እነዛ ብድኖች ከሙስና እራሳቸውን እንዲያቅብና ሀቀኛ ዜጋ እንዲሆኑ በፍትህ ታጋይ ስም እንጠይቃለን… ዜጋ ሁሉ በሀቀኝነት ለሀገር ተገቢውን ግብር እንዲከፍል እንፈልጋለን..ለዛም ባለማሰላስ ብዙዎቻችን እንጮኸለን…እንጽፋለን፡፡ግን የጥያቄያችን መንገድ የተሳሳተ ነው……እኛስ እራሳችንን ሀቀኛ ለማድረግ ወስነናል ወይ .. …?እኛስ በገዛ ቤታችን ዲሞክራሲ ለማስፋት መስራት ጀምረናል ወይ……?በዚህ አመት ገቢያችንን ሳንደብቅ ለመንግስት ተገቢውን ግብር ለመክፈል ወስነናል..…?ከቀበሌ መታወቂያ ለማውጣት ስንል የእጅ መንሻ አንከፍልም ለማለት ቁርጠኞች ነን ወይ……?
ሁላችንም በዛ መንገድ አይደለም የምናሰበው..ጉዞችን ወደ ውጤት የሚመራን አይነት አይደለም…ሌላውን ሰው የሆነ ነገር እንዲያደርግ ለማበረታታት ውጤታማው ዘዴ መጀመሪያ አድርጎ በተግባር ማሳየት ብቻ ነው….እና ይሄ አለቃዬ እራሱ ውስጡን ሳያሳምን ሰራተኞቹን በግድ እንደዛ አስቡ እያላቸው ነው…ቢሆንም እኔ እረዳዋለው…ይሄንን ካምፓኔ በብቃት የመምራት ችሎታ እንዳለው ውስጡ እንዲያምን አደርገዋለው…ግን ለምን እረዳዋለው…? እኔ እንጃ ..እንደውም እሱን ከመርዳት ይልቃ ላለመርዳት በቂ ምክንያ ነበረኝ….ምን አይነት ምክንያት…? ካላችሁኝ አሁን አልነግራችሁም….በደፈናው ግን ይሄን ካምፓኒ የመምራት ጉዳይ ባይሳክለት እኔ ተጠቃሚ ነኝ፡፡
ይሄን ሁሉ ምስቅልቅል ሀሳብ እያብሰለሰልኩ ያለውት ቢሮዬ ቁጭ ብዬ ነው….ሀሳቤን የገታውት አቶ ሰይፉ ከውጭ እያለከለኩ መጥተው በመሰላቸት መንፈስ ወንበራቸው ላይ ዝርፍጥ ብለው ረጅም የእፎይታ ትንፋሽ ሲተነፍሱ ሳይ ነው ፡፡
‹‹ምነው ጋሼ…?››እኔም ደንግጬ ጠየቅኳቸወ
‹‹ባክሽ ከእዚህ ልጅ ጋር እንዴት እንደምሰራ ግራ እየገባኝ ነው››
‹‹አይዞት ጋሼ …ጥቂት ጊዜ ነው… ይስተካከላል፡፡››
‹‹አይመስለኝም….ጡረታ መውጫ ጊዜዬ ደርሷል መሰለኝ››
‹‹አይ… ይሄን አይነት መሸነፍማ ከርሶ አልጠብቅም…አሁን ምን ተፈጠረ…?››
‹‹የሰራተኞች አመታዊ በዓል ለማክበር የተበጀተውን በጀት አላፀድቅም አለ››
‹‹ለምን አለ……?››
‹‹ብክነት ነው የሚል አመለካከት ነው ያለው…ይሄንን በዓል ላለፉት አስር አመት ስናከብር ቆይተናል.. ሰራተኞቻችን ከልጅ እስከ አዋቂው ይሄንን ቀን ልክ እንደ ሀይማኖታዊ ክብረበዓል ነው። የሚጠብቁት….ለዛውም እኮ በፕሌን ባህር ዳር ነበር ዕቅዱ..ግን ይሄንን ፈርቼ ከባጀቱ ላይ መቶ ሺ ብር ቀንሼ ወደቢሾፍቱ አዘዋውሬ ነበር ያቀረብኩለት››
‹‹እና ቁርጥ አድርጎ አይሆንም አለ…?››በብስጭት ስሜት ለማረጋገጥ ጠየቅኳቸው
‹‹አዎ ብሏል…››
‹‹የበጀቱን ሰነድ ይስጡኝ››
‹‹ምን ይረባሻል…?››
‹‹አስፈርመዋለዋ››
‹‹ጭራሽ አንቺ……?እንዴት እንደሚጠላሽ አታውቂም እንዴ……?እንድትባረሪ እንደሚፈልግ እኮ ነግሮኛል››
‹‹አውቃለው …እኔን በተመለከተ ባለው ስሜት ላይ ግራ መጋባት ውስጥ ስላለ ነው እንጂ አይጠላኝም …እንደውም ተቃራኒውን ነው…››
‹‹አይ አንቺ ልጅ…አንዴት እንደተንገሸገሸብሽ ስላላየሽ ነው….››
ከመቀመጫዬ ተነሳውን ወደ እሷቸው ወንበር ተጠጋው
‹‹ስጡኝ››
‹‹ቀዳዶ ፊትሽ ላይ እንደሚበትነው እያስጠነቀኩሽ ነው…በዛ ላይ ባንቺ የተነሳ ዳግመኛ እንዲናገረኝ አልፈልግም››
‹‹ግድ የሎትም… እርሶ ሳያዩ ከጠረጵዛ ላይ እንደወሰድኩት ነገረዋለው…››ብዬ እራሴው ወረቀቱን አነሳውና ቢሮውን ለቅቄ ወጣው…
እንደደረስኩ እንግዳ እያስተናገደ መሆኑን ፀሀፊው ስለነገረቺኝ ቁጭ ብዬ መጠበቅ ጀመርኩ..በነገራችን ላይ ፀሀፊው ከሄደችበት ለቅሶ ተመልሳለች…ከ7 ደቂቃ ቡኃላ ባለጉዳዩ ሲወጣ በዝግታ አንኳኩቼ ገባው….በተቀመጠበት ወንበር ወደኃላ ተለጥጦ ሲያዛጋ ነበር የደረስኩት….በራፉን ዘግቼ ወደወንበሩ በመሄድ ቁጨ አልኩ …ማዛጋቱን ጨረሰና እንደመስተካከል ብሎ ለሆነ ሰከናዶች ያህል ዝም ብሎ በገረሜታ ሲያየኝ ከቆየ ቡኃላ
‹‹ምነው የስራ መልቀቂያ ልታስገቢ ነው እንዴ የመጣሽው……?››አለኝ...
💫ይቀጥላል💫
Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ
ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን

👍3