አትሮኖስ
281K subscribers
112 photos
3 videos
41 files
483 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሰን። ፍቅርን አንድነትን መቻቻልን መተሳሰብን እመኛለው። መጪው ዘመን ፀዓዳ የተላበሰ እንደ አደይ ያበበ ይሆንላችሁ ዘንድ መልካም ምኞቴ ነው።
#መልካም #አዲስ #ዓመት! 5/13/10
#ራሳችንን #የምናይበት #አስገራሚ #ታሪክ

አንዲት ወጣት ሴት ለጉዞ ኤርፖርት ውስጥ ተቀምጣለች አውሮፕላኑ እንደሚዘገይ ባወቀች ጊዜ ኤርፓርት ውስጥ ካሉት ሱቆች ኩኪስና
መጽሐፍ ገዛች።ወደ VIP (የተመረጡ ሰዎች) ብቻ ወደ የሚስተናገዱበት ክፍል ገብታ ለንባብ ምቹ ወደ ሆነው መደገፊያ ወንበር አመራች
ተደላድላ ተቀምጣ ማንበብ ጀመረች አጠገቧ እንድ ሰው መጽሐፍ ያነባል
በሁለት መደገፊያ ወንበሮች መሐል ኩኪስ ተቀምጧል በንባቧ መካከል መተከዢያ ሆኗታል ታዲያ ከኩኪሷ አንድ ስታነሳ ሰውየውም አንድ አነሳ ገረማት ሳያስፈቅዳት መውሰዱ
አስደነቃት ግን ዝም አለች
ቀጥላ እርሷ አንድ ስትወስድ እርሱም ሌላ
ወሰደ አሁን ተበሳጨች። ድፍረቱ አናደዳት።
በዚህ አላበቃም እስከ መጨረሻው ቀጠለ።
ቅጥል አለች! ግን ንቃ ተወችው።
በአካባቢው ያሉ ሰዎችን አትኩሮት መሳብ
አልፈለገችም። ለዚህ ብቻ አይደለም በኩኪስ
ምክንያት ጸብ ረብሻ መፍጠር
አልፈለገችም።እንዲህ እንዲህ እያለ
የመጨረሻ አንድ ኩኪስ ቀረች። " ይሄ
የተረገመሰው ምን ያደርግ ይሆን? " ስትል
አሰበችና በቀስታ ማየት ጀመረች። ከዚያም
ሰውየው ኩኪሷን ሁለት ቦታ ከፈላትና ግማሹን
ወሰደ። ለድፍረቱ ጥግ አጣችለት። ከልክ ያለፈ
ስርዓት የለሽ እንደሆነ ደመደመች።ሰዓቱ
ደርሶ አውሮፕላን ላይ እንደተሳፈረች መነጽር
ለማውጣት ቦርሳዋን ስትከፍት አይኗን
ማመን አልቻለችም። ያልተከፈተው
የታሸገው ኩኪሷ ቦርሳዋ ውስጥ አለ። በጣም
አፈረች ተሸማቀቀች። ለካስ የራስዋን ኩኪስ
ቦርሳዋ ውስጥ ረስታ የሰውየውን ነበር
ስትበላ የቆየችው። ከሁሉም በላይ በጣም
ያጸጸታት ሰውየው እስከ መጨረሻው አንዲት
ኩኪስ እስክትቀር ድረስ ያካፍላት የነበረው
ምንም ሳይቆጣና ሳይመረር በደስታ መሆኑ
ነበር።የራሱን ኩኪስ እየበላች በሰውየው ላይ
ስትበሳጭበት በመቆየቷ እጅግ አፈረች።
አሁን ይቅርታ ለመጠየቅ እንኳን ጊዜው
አልፏል። እርሱም በሌላ አውሮፕላን ወደ
ሐገሩ አቅንቷል። እርሱን የማግኘት አንድ
ተጨማሪ እድል እንኳን የላትም። ብዙ ተመኘች ማመስገን፣ ይቅርታ መጠየቅ፣ ጉዳዩን ማብራራት፣ .....ግን ሁሉም እሷው ጋር ቀሩ አልፏል።

#አራት #የማይጠገኑ #ነገሮችን #አሰበች

👉 ድንጋይ ከተወረወረ በኋላ
👉 ቃላት ከተናገርናቸው በኋላ
👉ድርጊቶች ካመለጡን በኋላ
👉ጊዜ ካለፈ በኋላዋጋ እንደሌለው እኛም
ምንም ነገር ከመናገራችን ከመፈፀማችን
በፊት መጀመሪያ ራሳችንን እንይ
ዛሬ ልናመሰግናቸው ዋጋ ልንሰጣቸው
ልናከብራቸው የሚገባን ወዳጆቻችን የትዳር
አጋሮቻችንን ጀግኖቻችን ጊዜው ሳያልፍ
እናመስግናቸው።

#መልካም #ቀን
👍31
📚የአለማየሁ ገላጋይ ድንቅ ድርሰት የሆነው አጥቢያ በ PDF ቀርቦላችኋል #መልካም #ንባብ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
📚የበዉቀቱ ስዩም ድንቅ ድርሰት የሆነው #ከአሜን #በሻገር በ PDF ቀርቦላችኋል #መልካም #ንባብ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
📕የይስማከ ወርቁ ድንቅ ድርሰት የሆነው #ዣንቶዣራ በ PDF ቀርቦላችኋል #መልካም #ንባብ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
#በፍቅር_እንኑር

መነሻ ከሌለው ዝንተ ዓለም ወደ ማይደረስበት ዘላለም ተጓዥ ነን፡፡በሁለቱ መካከል ትንፋሽ መውሰጃ ጊዜ የለም፡፡ምን አልባትም ማይክሮሰከንድ አይኖርም ይሆናል፡፡ነገር ግን ሽርፍራፊዋም ብትሆን ያው የኛ ዕድሜ ነች፡፡በዚህ ዓለም አረፍ የምንልባት(የምንኖርባት እንዳልል ከመጣንበት ዝንት ዓለም እና ከምንሄድበት ዘላለም አንፃር የዕድሜያችን ርዝማኔ መለኪያው ስለማይነፃፀር እና ከዓይን ጥቅሻ ያነሰ በመሆኑ ነው)አንዳአንዴ ያንኑው የጥቅሻ ዕድሜ ያሰለቸናል፡፡ያነጫንጨናል፡፡ምክንያቱም እንደማረፊያ ሳይሆን እንደ ቋሚ መኖሪያ እናስባታለን፡፡እናም ቋም ነገሮችን ለመገንባት እንጣጣራለን...ወደ ውስጥ የሳብነውን አየር መልሰን ወደ ውጭ ሳንበትን የረፍት ጊዜያችን ይገባደድ እና እረጂም..በጣም እረጂም የፀጥታ እና የማይታወቅ ጉዦችንን እንጀምራለን፡፡
እና የዘላለም ተገጓዦች ነን፡፡በምድር ምንገነባው ህንፃ ማረፊያ ድንኳን እንጂ ቋሚ ሀውልት አይደለም፡፡ዘና ብሎ መሳቅ ...በፈገግታ መደሰት እንጂ ፊታችንን አጨማደን… ልባችንን አኮማትረን ..ስለ ኒዩኪሌር ቦንብ መጠበብ በህይወት ስለት ትርጉመ ቢስ ነው
ህይወት እኮ ምትሰለቸን እረፍታችን ምቸት ስለሌለው ነው...ለዚህ ነው የሚቀነቅነን፡፡የአብዛኞቻችን ኑሮ በችግር የታጠረበት ዋናው ምክንያት የጥቂተች ስግብግብነት ነው፡፡መቶ ሺ ዓመት በዚህች ምድር እንደሚኖር ..አንድ ሺ ሰዎች እድሜ ልክ ማኖር የሚችን ንብረት ብቻውን ታቅፎ እና ቀብሮ...እሱ በምቾት እና በስግብግብነት ቅዠት ውስጥ እየኖረ ..ሌሎች ሺ ዋችን በችግር እና በሰቀቀን ቅዠት ውስጥ እንዲኖሩ ማድረግ ትርፉ ምንድነው፡፡
እና እስቲ እንተሳሰብ፡፡ በፍቅር እንኑር፡፡ ጠብታ ጊዜያችንን በክፋት አናጨማልቃት፡፡በፈገግታ ጀምረን...በሳቅ አዋዝተን....በዜማ አጅበን...በደስታ ዘለን...በፍቅር ሰክረን..በእርካታ እንሰናበታት፡፤መጨረሻችን መድረሻ የሌለው ዘላለም አይደል፡፡
ስለዚህ መልካም አልመን ...መልካም ተግብረን...በመልካም ሁኔታ ኖረን..ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ ፀፀት አልባ ሆነን እንድንገጓዝ ከፀለምተኛ አስተሳሰባችን...ከስግብግብ ባህሪያችን...ከመጠላለፍ ምግባራችን እንላቀቅ፡፡ትናንትን አክባሪ...ዛሬን አፍቃሪ...ነገን ናፋቂ እንደሆን ህይወትን ሳንሰለች ሩጫችንን በጥሩ አነሳስ ጀጀምረን በድንቅ አጨራረስ ማጠናቀቅ ይገባናል

#መልካም_ቀን

🔘ከዘሪሁን🔘
👍3
#መልካም_ጋብቻ
:
:
#በሕይወት_እምሻው
:
ከጓደኞቼ ማሀደርና እስከዳር ጋር ፣ ዘናጭ ካፌ ቁጭ ብለን ውድ ማክያቶ እየጠጣን ነበር። ማክያቶ አሪፍ ፣ ጨዋታው ደማቅ ነበር። መርዶዬን እስኪነግሩኝ..."ናሆምና ማርታ ሊጋቡ ነው " እስኪሉኝ።

እንደሰማሁ በድንጋጤ ምራቄ ከአፌ አለቀ። በማካያቶ የሞቀ ሰውነቴ በአንድ ጊዜ ቀዘቀዘ።

ሰበባ ሰበብ ደርድሬ ፣ ራሴን አመመኝ ራይድ ጥሩልኝ ብዬ ካሰብኩት በጣም ቀድሜ ተለየሆአቸውና ቤት ገባሁ።

ናሆም ሊያገባ ነው? የኔ ናሆም ሊያገባ ነው? ያውም ያችን አብረን እንፎግራት የነበረች ዝንጅብል ቅርፅ ማርታን?

ሶፋዬ ላይ ቁጭ ብዬ ጥፍሬንም ነገርም ሳኝክ ፣ ቅናት ሳመነዥግ ፣ ልጆቼ ከባለቤቴ ጋር ከትምህርት ቤት መጡ።

"እንዴት ዋልሽ...? ፊትሽ ጠቋቆረ ምነው?" አለኝ ባሌ።ጉንጮቼን በእጆቹ እየዳበሰ። መልካሙ የአስር ዓመት ባሌ እንኳን ፊቴ በሐዘን ሲከስል ፣ ከፈገግታ ሲለይ ይጨንቀዋል።

"ደህና ነኝ...ትንሽ ደክሞኝ ነው...ራስ ምታት አለኝ. .." ቶሎ መለስኩለት። ትንሽ ቆይቶ፣ ከጉሮሮዬ አልወርድ እያለ የሚታገለኝን ለመክሰስ የተዘጋጀ ጨጨብሳ ለመብላት ለይስሙላ ብቀርብም አልቻልኩም።
"ትንሽ ደክሞኛል አረፍ ልበል እስቲ..." ብዬ ፣ ሚዛኔን ስቼ ደረጃው ላይ ባፍጢሜ እንዳልደፋ በመስጋት ሠወጣጫውን የሙጥኝ ብዬ እንደያዝኩ ወደ መኝታ ቤቴ ወጣሁ።

አልጋዬ ላይ ኩምትር ብዬ ተኛሁ። አልተመቸኝም። ተገለበጥኩ። አሁንም አልተመቸኝም።ብርድ ብርድ አለኝ። ተነሳሁና አንዱን ጋቢ ደርቤ ተመልሼ ተኛሁ። አልሞቀኝም። ከነጋቢዬ ተነስቼ መስኮቱ ጋር ቆምኩ። እንባዬ ያለ ፍቃዴ መፍሰስ ሰውነቴ መርገፍገፍ ጀመረ።

ናሆሜ ሊያገባ ነው?

እርግጥ ነው ፣ ከተያየን ሁለት ረጃጅም፣ ቀለም አልባ እና አታካች ሁለት አመታት አልፈዋል።

እርግጥ ነው ፣ አትድረስብኝ ብዬ ካባረርኩት፣ ከእሱ የሚያገናኘን ድልድይ ከሰበርኩ ሃያ አራት ወራት አልፈዋል።

ግን እንዴት አይነግረኝም? እንዴት ለደቂቃ ደውሎ፣ ከሌላ ሰው እንዳትሰሚው ብዬ ነው ፣ ላገባ ነው። አይለኝም?

ምንስ ቢሆን አብረን ላሳለፍነው ጊዜ ሲባል፣ ለነበረን ደስታ ሲል ይህን እንዴት አያደርግልኝም?

ልደውልለት? አልደውልለትም። እሱ ሳይደውልልኝ እኔ አልደውልለትም። ላግኘው? አላገኘውም። ስለምን ላወራው አገኘዋለው ? ምንስ እለዋለው? ብቻውን ሊያገኘኝ ፈርቶ እየተንቦቀቦቀ ያቺን ማማሰያ እግር ይዞብኝ ቢመጣስ? አላገኘውም።

ደብዳቤ እፅፍለታለሁ።

ምን ብዬ?

ማግባትህን ሰማው...ምነው ደውለህ ሳትነግረኝ?...ቢሆንም እንኳን ደስ አለክ.. መልካም ትዳር...ማርታንም እንዴት ነሽ? እንኳን ደስ አለሽ በልልኝ...እኔና ሶል ከልጆቹ ጋር ዱባይ ለዕረፍት ልንሄድ ነው... ሁለት ሳምንት... ሃምሳ አራት ኪሎ ገባሁ እኮ...በጣም ተሸናቅጫለው ብታይ .. አምሮብሻል...መልካም መሆኔ ምናምን ብዬ...

ሳሎን ወርጄ ሽንጠ ረጅም ወረቀትና እስኪርብቶ ይዤ ወጀ መኝታ ቤቴ ተመልሼ ደብዳቤዬን ጀመርኩ። ወደ ፊት እንጂ ወደሇላ የማላውቅ ጠንካራ ሴት መሆኔን አሳየዋለሁ። በትዳሬ ፍፁም የረጋሁ፣ መልካም እናትና ፍፁም ደስተኛ ቀጭን ሴት መሆኔን የሚያመለክት ደብዳቤ መፃፍ ጀመርኩ።

"ሰላም ናሆም...እንዴት ነህ? መቼም በዚህ ዘመን በእጄ ደብዳቤ ስፅፍልህ ግር ሳይልህ አልቀረም። ልታገባ እንደሆነ ስሰማ ደውዬ ከምረብሽክ(መቼም ያው ደስታ ላይ ስለሆንክ) በደብዳቤ ይሻላል ብዬ ነው። በጣም ደስ ይላል። ደግሞ ከማርታ ጋር መሆኑ በጣም አሪፍ ነው። ገና ከድሮ ጀምሮ ትወድህ እንደነበር አውቃለው። ደስ ይላል...

ለምን ደውለክ እንዳልነገርከኝ ሳስብ ግምቴ አንድ ብቻ ሆነ። ምን አልባት ስሜቷ ይጎዳል ብለህ ይሆናል። ያው ያኔ የነበረኝን ፍቅር አስበህ ምንአልባት የኔ ማግባት ሊያማት ስለሚችል አልነግራትም ብለህ ነው አይደል? እንደዛ ከሆነ በጣም ተሳስተካለል። ትንሽም አዝኜብሃለው። ትንሽ ክሬዲት ልትሰጠኝ ይገባ ነበር። የተፈጠረው ሁሉ ከሆነ በሇላ ቢሆንም ይህን ነገር እናቁም ብዬ የወሰንኩት፣ የተለየሁህ እኔ መሆኔን ትረሳለክ መሰለኝ...ወይ ደግሞ በኔ ሕይወት ውስጥ ያለህን ቦታ አጋነህ ትገምት ይሆናል...ባለትዳር
..የልጆች እናት ሆኜ ካንተ ስለተኛሁ... በስሜት ማእበል ተውጬ እወድሀለው ብዬ ለሁለት አመታት አብሬህ ላይ ታች ስላልኩ፣በልቤ ውስጥ የተለየ ቦታ እንዳለህ ተሰምቶክ አዝነክልኝ ይሆናል ግን ይሄ ስህተት ነው።

በተደጋጋሚ ነግሬህ ነበር...ቦታክን አመልክቼህ ነበር..አሁን ግን ማግባቴ ልቧን ይሰብረዋል ብለህ ማሰብክን ስገምት ላስታውስክ ፈለኩ።

ናሆም፣ አንተ እኮ ደካማ በነበርኩ ቀናት የሰራሁህ ስህተት ነህ። በረጅም የሕይወቴ መፅሀፍ ውስጥ ቢበዛ አንዲት የማትረባ ገፅ ነክ። ብፈልግ ቡጭቅ አድርጌ ልጥልህ የምችል ፣ ስፈልግ ገንጥዬ ላወጣህ የምችል፣የማትረባ አንዲት መናኛ ገፅ ነህ። መጽሐፎቹ ባሌና ልጆቼ ፣ አብረን የገነባነው ቤቴና ህይወቴ ናቸው።

አሁንም መሽቶ በነጋ ነግቶ በመሸ ቁጥር ስላንተ የማስብ፣የምቆዝም መስሎህ ከተሰማክ በጣም ተሳስተካል። ልጆቼን ከትምህርት ቤት ሳመጣ በ 'የ ትራፊክ መብራቱ ላይ የመኪና መሪ ይዤ የማይረሳ አሳሳምህን እያሰብኩ የምብሰለሰል፣ስንቃበጥ የነበረኝን የሀጥያት ደስታ መልሼ መላልሼ እያሰብኩ ፣ እንባ ባይኔ ሞልቶ ከሆላዬ የቆሙት መኪናዎች በጥሩንባ ሂጂ ብለው እስከሚያቧርቁብኝ ድረስ የት እንዳለው የምረሳ ከመሰለክ፣ ተሳስተካል።

ዛሬ ድረስ ከባሌ ጋር ፍቅር ስሠራ ፣ ስምህ ከአፌ እንዳያመልጠኝ የምታገል፣ ፀሃይ እንዳትወጣ የተመኘሁባቸውን እነዚያ ካንተ ጋር ያደርኩባቸው፣አጭርና ስኳር ስኳር የሚሉ ሌሊቶች እያሰብኩ እንባዬን የማብስ መስሎህ ከሆነ...ናሆም በጣም ተሳስተካል።

ጌትነትን አልችል ብሎ የጠገበ ባለትዳር ልቤ ሲዋልል የተራመድኩብህ ሰወርዋራ መንገድ እንጂ ፣ አውራ ጎዳናዬ አልነበርክም።ዋና መንገዴ ሆነህ አታውቅም።

አሁንም አልጋ ውስጥ ገብተን ትንሽዬ የአንሶላ ድንኳን ቀልሰን ብርሃንም ንፋስም ሳናስገባ የምናወራው፣ የምንሰማው፣ የምንደባብሰውን ነገር ሁሌ እያሰብኩ ከእንባዬ የምታገል ይመስልህ ይሆናል።

ለልጆቼ በሶ ሳበሰብስ፣ እዚያች ሚጢጢ ግን የምትሞቅ ቤትህ መጥቼ በሶ በቅቤ ስሠራልህ፤ ሁለመናችን በሶ በሶ እየሸተተ የምንተቃቀፈው፣ሰውነቴ ከሰውነቴ የሚቆላለፈውን እያስታወስኩ የምርበተበትልህ ይመስልህ ይሆናል።

ግን ተሳስተሃል።

አንተ እኮ ደካማ በነበርኩ ቀናት የሠራሁህ ስተት ነህ።በሙሉ ጊዜ ህይወቴ ውስጥ የነበርክ የትርፍ ጊዜ ስራ ነህ። መሪ ሳይሆን አጃቢ ዋና ሳይሆን አስተኔ ገጸ ባሕርይ።

በዛሬው ሕይወቴ፣ስንዝር ቦታ የሌለህ፣ የሕይወት ታሪኬ ውስጥ በእመጫት የገባህ፣ በስርዝ ድልዝ ያስወጣሁህ፣ ምራቂ ሰው ነህ።

እስከዛሬ በፊስቡክ፣ በቫይበርና ፣ በዋትሳፕ የምንላላካቸውን "ሴክስት" እያነበብኩ የምታመም፣ ፎቶህን ከባሌና ልጆቼ በሚስጥር ቆልፌ መታጠብያ ቤት ገብቼ እያየሁት የማለቅስ፤ በፈገግታህ የምታመም፤በናፍቆትህ የምፈረካክስ ይመስልክ ከሆነ ተሳስተሀል።

ትርጉም፣ ጭራና ቀንዱ ጨርሶ እንዳይጠፋብኝ፣በየቀኑ ሐዘን እንደ ቱባ ክር እንደሚተወይረትረኝ የምታስብ ከሆነ በጣም ተሳስተካል።

አንተ እኮ ስምህ በእርሳስ የተፃፈ የማፍርብህ ትላንቴ እንጂ ፣ ዛርዬ ነገዬ አይደለህም።እንጂ፣

በአሸዋ ላይ እንጼ ወድያው ያፈረስኩህ ዛኒ ጋባ ቤት እንጂ፣ቋሚ መኖርያ አይደለህም።

አሻራ አልባ ዱካ የማትረሳ ሰው አይደለህም።

ስለዚህ ማርታን ለማግባት ስትወስን በመደወል ፈንታ፣
👍4