#ራሳችንን #የምናይበት #አስገራሚ #ታሪክ
አንዲት ወጣት ሴት ለጉዞ ኤርፖርት ውስጥ ተቀምጣለች አውሮፕላኑ እንደሚዘገይ ባወቀች ጊዜ ኤርፓርት ውስጥ ካሉት ሱቆች ኩኪስና
መጽሐፍ ገዛች።ወደ VIP (የተመረጡ ሰዎች) ብቻ ወደ የሚስተናገዱበት ክፍል ገብታ ለንባብ ምቹ ወደ ሆነው መደገፊያ ወንበር አመራች
ተደላድላ ተቀምጣ ማንበብ ጀመረች አጠገቧ እንድ ሰው መጽሐፍ ያነባል
በሁለት መደገፊያ ወንበሮች መሐል ኩኪስ ተቀምጧል በንባቧ መካከል መተከዢያ ሆኗታል ታዲያ ከኩኪሷ አንድ ስታነሳ ሰውየውም አንድ አነሳ ገረማት ሳያስፈቅዳት መውሰዱ
አስደነቃት ግን ዝም አለች
ቀጥላ እርሷ አንድ ስትወስድ እርሱም ሌላ
ወሰደ አሁን ተበሳጨች። ድፍረቱ አናደዳት።
በዚህ አላበቃም እስከ መጨረሻው ቀጠለ።
ቅጥል አለች! ግን ንቃ ተወችው።
በአካባቢው ያሉ ሰዎችን አትኩሮት መሳብ
አልፈለገችም። ለዚህ ብቻ አይደለም በኩኪስ
ምክንያት ጸብ ረብሻ መፍጠር
አልፈለገችም።እንዲህ እንዲህ እያለ
የመጨረሻ አንድ ኩኪስ ቀረች። " ይሄ
የተረገመሰው ምን ያደርግ ይሆን? " ስትል
አሰበችና በቀስታ ማየት ጀመረች። ከዚያም
ሰውየው ኩኪሷን ሁለት ቦታ ከፈላትና ግማሹን
ወሰደ። ለድፍረቱ ጥግ አጣችለት። ከልክ ያለፈ
ስርዓት የለሽ እንደሆነ ደመደመች።ሰዓቱ
ደርሶ አውሮፕላን ላይ እንደተሳፈረች መነጽር
ለማውጣት ቦርሳዋን ስትከፍት አይኗን
ማመን አልቻለችም። ያልተከፈተው
የታሸገው ኩኪሷ ቦርሳዋ ውስጥ አለ። በጣም
አፈረች ተሸማቀቀች። ለካስ የራስዋን ኩኪስ
ቦርሳዋ ውስጥ ረስታ የሰውየውን ነበር
ስትበላ የቆየችው። ከሁሉም በላይ በጣም
ያጸጸታት ሰውየው እስከ መጨረሻው አንዲት
ኩኪስ እስክትቀር ድረስ ያካፍላት የነበረው
ምንም ሳይቆጣና ሳይመረር በደስታ መሆኑ
ነበር።የራሱን ኩኪስ እየበላች በሰውየው ላይ
ስትበሳጭበት በመቆየቷ እጅግ አፈረች።
አሁን ይቅርታ ለመጠየቅ እንኳን ጊዜው
አልፏል። እርሱም በሌላ አውሮፕላን ወደ
ሐገሩ አቅንቷል። እርሱን የማግኘት አንድ
ተጨማሪ እድል እንኳን የላትም። ብዙ ተመኘች ማመስገን፣ ይቅርታ መጠየቅ፣ ጉዳዩን ማብራራት፣ .....ግን ሁሉም እሷው ጋር ቀሩ አልፏል።
#አራት #የማይጠገኑ #ነገሮችን #አሰበች
👉 ድንጋይ ከተወረወረ በኋላ
👉 ቃላት ከተናገርናቸው በኋላ
👉ድርጊቶች ካመለጡን በኋላ
👉ጊዜ ካለፈ በኋላዋጋ እንደሌለው እኛም
ምንም ነገር ከመናገራችን ከመፈፀማችን
በፊት መጀመሪያ ራሳችንን እንይ
ዛሬ ልናመሰግናቸው ዋጋ ልንሰጣቸው
ልናከብራቸው የሚገባን ወዳጆቻችን የትዳር
አጋሮቻችንን ጀግኖቻችን ጊዜው ሳያልፍ
እናመስግናቸው።
#መልካም #ቀን
አንዲት ወጣት ሴት ለጉዞ ኤርፖርት ውስጥ ተቀምጣለች አውሮፕላኑ እንደሚዘገይ ባወቀች ጊዜ ኤርፓርት ውስጥ ካሉት ሱቆች ኩኪስና
መጽሐፍ ገዛች።ወደ VIP (የተመረጡ ሰዎች) ብቻ ወደ የሚስተናገዱበት ክፍል ገብታ ለንባብ ምቹ ወደ ሆነው መደገፊያ ወንበር አመራች
ተደላድላ ተቀምጣ ማንበብ ጀመረች አጠገቧ እንድ ሰው መጽሐፍ ያነባል
በሁለት መደገፊያ ወንበሮች መሐል ኩኪስ ተቀምጧል በንባቧ መካከል መተከዢያ ሆኗታል ታዲያ ከኩኪሷ አንድ ስታነሳ ሰውየውም አንድ አነሳ ገረማት ሳያስፈቅዳት መውሰዱ
አስደነቃት ግን ዝም አለች
ቀጥላ እርሷ አንድ ስትወስድ እርሱም ሌላ
ወሰደ አሁን ተበሳጨች። ድፍረቱ አናደዳት።
በዚህ አላበቃም እስከ መጨረሻው ቀጠለ።
ቅጥል አለች! ግን ንቃ ተወችው።
በአካባቢው ያሉ ሰዎችን አትኩሮት መሳብ
አልፈለገችም። ለዚህ ብቻ አይደለም በኩኪስ
ምክንያት ጸብ ረብሻ መፍጠር
አልፈለገችም።እንዲህ እንዲህ እያለ
የመጨረሻ አንድ ኩኪስ ቀረች። " ይሄ
የተረገመሰው ምን ያደርግ ይሆን? " ስትል
አሰበችና በቀስታ ማየት ጀመረች። ከዚያም
ሰውየው ኩኪሷን ሁለት ቦታ ከፈላትና ግማሹን
ወሰደ። ለድፍረቱ ጥግ አጣችለት። ከልክ ያለፈ
ስርዓት የለሽ እንደሆነ ደመደመች።ሰዓቱ
ደርሶ አውሮፕላን ላይ እንደተሳፈረች መነጽር
ለማውጣት ቦርሳዋን ስትከፍት አይኗን
ማመን አልቻለችም። ያልተከፈተው
የታሸገው ኩኪሷ ቦርሳዋ ውስጥ አለ። በጣም
አፈረች ተሸማቀቀች። ለካስ የራስዋን ኩኪስ
ቦርሳዋ ውስጥ ረስታ የሰውየውን ነበር
ስትበላ የቆየችው። ከሁሉም በላይ በጣም
ያጸጸታት ሰውየው እስከ መጨረሻው አንዲት
ኩኪስ እስክትቀር ድረስ ያካፍላት የነበረው
ምንም ሳይቆጣና ሳይመረር በደስታ መሆኑ
ነበር።የራሱን ኩኪስ እየበላች በሰውየው ላይ
ስትበሳጭበት በመቆየቷ እጅግ አፈረች።
አሁን ይቅርታ ለመጠየቅ እንኳን ጊዜው
አልፏል። እርሱም በሌላ አውሮፕላን ወደ
ሐገሩ አቅንቷል። እርሱን የማግኘት አንድ
ተጨማሪ እድል እንኳን የላትም። ብዙ ተመኘች ማመስገን፣ ይቅርታ መጠየቅ፣ ጉዳዩን ማብራራት፣ .....ግን ሁሉም እሷው ጋር ቀሩ አልፏል።
#አራት #የማይጠገኑ #ነገሮችን #አሰበች
👉 ድንጋይ ከተወረወረ በኋላ
👉 ቃላት ከተናገርናቸው በኋላ
👉ድርጊቶች ካመለጡን በኋላ
👉ጊዜ ካለፈ በኋላዋጋ እንደሌለው እኛም
ምንም ነገር ከመናገራችን ከመፈፀማችን
በፊት መጀመሪያ ራሳችንን እንይ
ዛሬ ልናመሰግናቸው ዋጋ ልንሰጣቸው
ልናከብራቸው የሚገባን ወዳጆቻችን የትዳር
አጋሮቻችንን ጀግኖቻችን ጊዜው ሳያልፍ
እናመስግናቸው።
#መልካም #ቀን
👍3❤1