#የተወጋ_ልብ
፡
፡
#ክፍል_ሃምሳ_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
...ትናንትና አስተማሪው የሰጣትን የቤት ሥራ ሊያስረዳት ጀምሮ አቋርጦት ነበር። ቶሎ ብላ መጽሀፏን ደብተሯን ይዛ ከተፍ አለች። የለበሰችው ጉርድ ቀሚስ ነው፡፡ ፀጉሯን በወፍራሙ ጐንጉናዋለች። ታደስ ጥሩ ፀባይ እንዳለው እየተረዳች በመምጣቷ ሰውነቷ መሸማቀቁን ዘንግቶ ዘና ፈታ ማለት ጀምሯል።በአልጋ ላይ በጎኑ ጋደም እንዳለ ማስጠናቱን ቀጠለ... አጥኚና አስጠኚ አለቅጥ ተቀራርበው ነበረና
ልብስ ባልለበሰ ክንዱ ልብስ ያልለበስ ክንዷን ሲተሻሽው ልስላሴዋና ሙቀቷ በክንዱ በኩል ዘልቆ ሁለመናውን አዳረሰው፡ሙቀቱ የፈጠረበት ስሜት ረበሽውና ቀና ብሎ ወደ ጎን አያት፡፡ እሷም እየተሽኮረመመች ወደ ጉን አየችው። ደማቅ የውበት ቀለም የተቀባች መሆኗን አጤነ፡ በቃ! አልቻለም፡፡ያንን ለብዙ ጊዜ ከራሱ ጋር ሲሟገት የቆየበትን ነገር ለማድረግ መገደዱን አመነ፡፡ሳብ አደረገና በክንዶቹ አቀፋት። አልተቃወመችም ሄዳ ልጥፍ አለችበት፡፡ ቀስ ብሎ ከንፈሯን ሳማት። እሷም አፀፋውን
መለሰች። ሲፈላለጉም ሆነ ሲገናኙ የነበረው ሁኔታ ከዚህ በፊት የሚተዋወቁ እንጂ አዲስ ጀማሪዎች አይመስሉም ነበር፡፡ ምግብ አብሳዩ እንጂ አቻው አለመሆኗ እየተሰማት እየተሸማቀቀች ለብዙ ጊዜ የቆየች ቢሆንም አስገዳጁ የጾታ ማግኔት ሳታስበው በስሜት አጋግሉ፣ ሰሜን ጫፍና ደቡብን አሳስቦ በድንገት ሲያስተቃቅፋቸው ምን ታድርግ? ከዚያም እግሮቿን በእግሩ ከታች ወደ ላይ ቢያስፈነጥራቸው ተወርውራ ሄዳ አልጋው ላይ በግራ ጎኑ ወደቀችና ከደረቱ ተጣበቀች፡፡ የአዳም የግራ ጎኑ ሄዋን...ታደሰ ከስድስት ወር የአእምሮ ሙግት በኋላ ዛሬ ዳበሳት... ዙሪያሽ ጨዋነቷን አስመሰከረች. . ልጃገረድ! ...
“ጋሼ ታደስ እኔ እኮ ድሃ የድሃ ልጅ ነኝ ካንተ ጋር እንደዚህ አይነቱን
ነገር መፈፀም አልችልም፡፡ ያለ አቅም መንጠራራት ትርፉ አደጋ ላይ መውደቅ ነው”
“ዙሪያሽ እኔም ድሃ የድሃ ልጅ ነኝ ነገር ግን ወላጆቼ የገንዘብ ድሆች
እንጂ የመንፈስና የሞራል ድሆች አልነበሩም፡፡ ከገንዘብ ድህነት የበለጠ ሰውን የሚጐዳው የመንፈስ ድህነት ነው። ያንቺም ወላጆች የገንዘብ ድሆች ከነበሩ እኔም እንዳንችው የድሃ ገበሬ ልጅ ነኝና ስለአቻነታችን በፍፁም አትጠራጠሪ፡፡ በዚያ በኩል ስላለን ልዩነት አትጨነቂበት” አላት።
“ጋሼ ታደሰ የሞራልና የመንፈስ ድህነት ከአጐቴ ሞት ጋር ተደምረው ጐድተውኛል። አጐቴ... አጐቴ... የሀብታም ልጅ የሆነችውን የትምርት ቤት ጓደኛው እመቤት መስፍንን ወደዳት... እሷም ወደደችው። ፍቅራቸው ግን አቻ አልነበረም፡፡ አጐቴ የድሃ ልጅ በመሆኑ ወላጆቿ አልወደዱትም፡፡ ዘረ ምናምንቴ የድሃ ልጅ እያሉ አንቋሸሹት። ቅስሙን ሰበሩት። ሁለቱ ይፋቀሩ ነበር፡፡ የእሷ ወላጆች ውሻ አደረጉት።ለሀብታም ልጅ ታጭታ ቀለበት እንድታስር አስገደዷት።ጋሼ ሞራሉ ወደቀ፡፡
ብስጩ ሆነ፡፡ እሷ ትወደው ነበር፡፡ እየተዋደዱ ግን ተለያዩ፡፡ጋሼ ጤንነቱ ተቃወሰ፡፡መጨነቅና መጠበብ አበዛ፡፡ ብቸኝነት፣ የሞራል ውድቀት በዚህ ላይ ፍቅር አለ፡፡ እያፈቀሩ ማጣት ሰላም ነሳው። ብስጩነቱ እንዳይታወ
ቅበት ጥረት ቢያደርግም ያስታውቅበት ነበር፡፡ የሃብታም ልጅ ባይወድ ኖሮ ቢጤውን ቢፈልግ ኖሮ ይሄ ሁሉ አይመጣበትም ነበር፡፡ ጋሽ ታደሰ
የኔና ያንተም ተመሳሳይ ነው፡፡ አቻ አይደለንም፡፡ የድሆች ልጆች ብንሆንም በእውቀት እንበላለጣለን፡፡ አንተ የተማርክ ጥሩ ሥራ ጥሩ ደመወዝ ያለህ ሰው ነህ፡፡ እኔ ግን እዚህ ግቢ የማልባል በትምህርት ያልገፋሁ
ገረድህ ነኝ፡፡ ዝቅ ብለህ ከገሪድህ ጋር...እኔ ደግሞ ያለአቅሜ ተንጠራርቼ የሚደረግ ግንኙነት ጥሩ ነው ብለህ ታስባለህ?”
“ዙሪያሽ እንደሱ አታስቢ። በዚች በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ በሚገባ ተጠናንተናል።ያየሽብኝ ጉድለት ካለ ደግሞ ግለጪልኝና ላርም፡፡ በእውነት ነው የምልሽ ዙሪያሽ እኔ ከዚህ በፊት ብቸኛ ነበርኩ ጓደኞቼ አይጦችና
ሽረሪቶች ነበሩ። ቤቴ ብቻ ሳይሆን አእምሮዬ ሸረሪት አድርቶበት ነበር፡፡
ብቸኝነትና የመንፈስ ጭንቀት ነበሩብኝ፡፡ መንፈሴን የሚያስጨንቀኝ ነገር ከሞላ ጎደል መፍትሄ እያገኘ ሃሳቤ እየሰመረ በመምጣቱ ደስተኛ ነኝ፡፡
ወንጀሎች እንዲቀንሱ የበኩሌን ጥረት በማድረጌና ውጤቱን እያየሁ በመምጣቴ ደስተኛ ሆኛለሁ። በዚህ ደስተኛ ብሆንም አንድ ነገር እንደሚጐድለኝ ሁሌም ይታወቀኝ ነበር፡፡በተለይ እንደዚህ እንደአሁኑ ከነ ክብርሽ አገኝሻለሁ የሚል ግምት ባይኖረኝም አብረን በቆየንባቸው ወራቶች ውስጥ
ሳጠናሽ ነበር የቆየሁት። ያንን በጭንቅላቴ ውስጥ አድርቶ የነበረውን የብቸኝነት ድር የበጣጠስሽልኝ ከግማሽ ወደ ሙሉነት የምሸጋገርበት ተስፋ
የፈነጠቅሽልኝ አንቺ ነሽ፡፡ ያደረ የሆቴል ቤት ምግብ ትርፉ ቃር ነው።ከዚያ ነፃ ሆኛለሁ። አፈር አፈር የምትሽተው ኦና ቤቴ ዛሬ ሞቅ ደመቅ ብላ ቄጤማ ተጐዝጉዞባት እጣን ጤሶባት ሽታዋ የሚስብ ሆኗል። የቆሽሽ
ልብሴ ታጥቦ ንፁህ ሆኖ አገኘዋለሁ፡፡ በውጭ እስከዚህ ድረስ ለውጠሽኛል። ነገር ግን የውጭ ለውጥ ብቻውን ዋጋ የለውም፡፡ ውስጤ መለወጥ
አለበት፡፡ ባዶነቴን ብቸኝነቴን ለማስወገድ ለኔ ካንቺ የተሻለ እንደማይኖር በተለይ በዛሬዋ ምሽት በይበልጥ አረጋግጫለሁ። ጥንድነት ለአልጋ ብቻ አይደለም፡፡ችግር ሲያጋጥም የምታማክሪው፣ ደስታና ሀዘንሽን የምታካፍይው፣ የኑሮ ብልሃቱ እክል ሲገጥመው ዘዴ የሚቀይስ የሚያፅናና ጓደኛ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ከሁሉ የሚበልጠው ጓደኛ ደግሞ የቤተሰብ መሠረት የትዳር ጓደኛ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሄዋንን ለአዳም አዳምን ለሄዋን የፈጠረላቸው ይህን ችግራቸውን አውቆ ነውና የታደሰ ሄዋን
አንቺ ዙሪያሽ ብትሆኚለት ምን ይመስልሻል ? በዛሬዋ ምሽት በእምነት ክብርሽን እንደሰጠሽኝ ሁሉ እኔም ንፁህ ፍቅሬን ልሰጥሽ ዝግጁ ነኝ፡፡ ከዛሬዋ እለት ጀምሮ በደንቡና በወጉ ተፈራርመን ገሃድ እስከምናወጣው ድረስ በባልና ሚስትነት አብረን እንኖር ዘንድ ምኞቴን የተቀበልሽው ስለ
መሆኑ ማረጋገጫ..” አለና ከንፈሩን አስጠጋላት፡፡
“ጋሽ ታደሰ እኔ እኮ... እኮ...ደሃ ነኝ ቢጤዬን እንጂ” የታችኛው ከንፈ
ሯን ነከሰች።
“ዙሪያሽ ስለድህነትና አቻ ስላለመሆናችን የምታወሪውን ለመርሳት ሞክሪ፡፡ እንደሱ እያልሽ አታስጨንቂኝ፡፡ ድህነት በደማችን ውስጥ የሚዘዋወር አብሮን የተፈጠረ ወይም እንደሚባለው የአርባ ቀን ዕድላችን አይደለም፡፡ ድህነትን በሥራ ልንደቁሰው እንችላለን፡፡ የእመቤት ወላጆች ሌላ እኔና አንቺ ደግሞ ሌላ ነን። የአጐትሽ ሞት ያስከተለብሽ ሥነ ልቦናዊ ጫና ቀላል እንዳልሆነ ይሰማኛል። የእመቤት ወላጆች የገንዘብ ሃብታሞች ቢሆኑ የእውቀት ድሆች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ከገንዘብ ድህነት የከፋው
ደግሞ የአእምሮ ድህነት ነው። እኔና እነሱን አታወዳድሪን፡፡ ቢያንስም ቢበዛም ፊደል የቆጠርኩ ነኝና የፍቅርና የገንዘብን አንድነትና ልዩነት ጠንቅቄ አውቃለሁ፡፡ ሁለቱም ለሰው ልጅ ህልውና አስፈላጊ ናቸው።
ገንዘብ ያለበት ፍቅር አይጠላም፡፡ ማለፊያ ነው። ፍቅር የሌለበት ገንዘብ ግን ገንዘብ አይደለም፡፡ አያረካም፡፡ እመቤትን ወላጆቿ ገንዘብ ላለው ሰው አሳልፈው ቢሰጧት የምትረካ እንዳይመስልሽ፡፡ ዋናውን ግምት

👍15
#ያልታበሱ_እንባዎች
፡
፡
#ክፍል_ሃምሳ_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ
....ሔዋን በልሁን ስለ አስቻለው ሁኔታ ለመጠየቅ ፈራች። በአንድ በኩል ምላሹን ስትፈራ በሌላ በኩል ትክክለኛውን ሁኔታ ላይነግረኝ ይችላል የሚል ስጋት ያዛት። ነገር ግን ነገሩን ለማንሳት አንድ መላ መጣላትና ወዲያው ተጠቀመችበት።...
«አሁን ነገ ወደ አዲስ አበባ ስንሄድ የትርፌን መሞት ለአስቻለው እንነግረዋለን ወይስ....»ብላ ነገሯን በእንጥልጥል ተወችው።
በልሁ በፍጥነት መለሰላት «ይዋደዱ አልነበር እስካሁን ሆዱ ነግሮት ይሆናል።»አለና ዝም ብሎ በመስታወት ውስጥ ውጭ ውጭ ያይ ጀመር።
«ምናልባት ይደነግጥና አንድ ነገር ይሆናል ብዬ ፈርቼ እኮ ነው።» አለችው ሔዋን ስለ አስቻለው ሁኔታ ምርመራዋን ለመቀጠል።
«እስቲ እዚያው ስንደርስ እንደ ሁኔታው እናደርገዋለን።» እንደገና ፀጥታ። መኪናዋ ግን ሄደች፣ ነጎደች። ጩኮን አልፋ የዲላ ከተማ መዳረሻ ታየ።አንዳንድ ቤቶችም ብቅ ብቅ ማለት ጀመሩ። አንዳንድ ልቦች የፍርሃት ከበሮ ይመቱ ጀመር።መኪናዋ ግን ያለ ሀሳብ ናፍጣዋን እየጠጣች በረረች።የመጨረሻውን የለገዳራ ወንዝ ድልድይ ተሻግራ ከዲላ መውጫ የመጀመርያ ኬላ ፍተሻ ላይ ደረሰች።ደግነቱ ከአዲስ አበባ ወደ ዲላ ሲሄዱ ፍተሻ የለም። ያም የፍተሻ ኬላ ታለፈ። ዲላ ከተማን በሰሜንና በደቡብ ለሁለት የሚከፍለው ዳገተማ የአስፋልት መንገድ ተጀመረ ያም ቢሆን ከደቂቃዎች የበለጠ ጊዜ አልወሰደም። ልክ ሰባተኛ መንገድ ተብሎ በሚጠራው የጠጠር መንገድ ላይ ሲደርሱ በበልሁ አመልካችነት ቶዮታዋ ወደ ቀኝ ታጠፈች።ያ መንገድ በለቀስተኛ ተሞልቷል። ነጠላቸውን ያሸረጡ ሴቶችና ጋቢ የለበሱ ወንዶች አጥለቅልቀውታል። አንዳንዶቹ ወደ ታፈሡ ቤት አቅጣጫ ይሄዳሉ
አንዳንዶቹ ደርሰው የሚመለሱ ይመስላሉ። ሹፌሩ የገባው ነገር ነበርና የመኪናዋን ጡሩንባ ደጋግም ሲያንጧጧው ደርሰው ተመላሽ የነበሩ ለቀስተኞች ፊታቸውን ወደ ታፈሡ ቤት አቅጣጫ ይመለሱ ጀመር።
መኪናዋ ከታፈሡ ቤት የማያደርሰውን የመጨረሻ መንገድ ስትጀምር የታፈሡ ቤት አካባቢ ከነጉድጓዱ ብቅ አለ። ሁለት ድንኳን ተተክሎበታል። የሰው ነጭ ይርመሰመሳል። መኪናዋ ወደ ድንኮኑ ስትጠጋ ትልቅ ፎቶ ግራፍ ይዛ እንደ እብደት እንደ ስካር በሚያደርጋት ሴት እየተመራ ያ ሁሉ ሰው ወደ መኪናዋ ተንቀሳቀሰ። ህዝቡና መኪናዋ ሲገናኙ ሴትየዋ የታፈሡ እንግዳ ሰው፣ የያዘችው ፎቶ ግራፍ ደግሞ የአስቻለው ፍስሃ። ነገሮች ሁሉ ግልፅ ሆኑ፣ መርእድ ድንግጥ ሲል ሔዋን ደሞ ሁለመነዋ ደነዘዘ።መኪናዋ ከህዝቡ አጠገብ ስትደርስ ቀጥ ብላ ቆመች።ታፈሡ ወደ መኪናዋ የዕቃ መጫኛ ስትዞር በልሁ የጋቢናውን በር ከፈተና ዱብ አለ። በሩ ላይ ቆሞ ፈዝዞ ደንገዛ መንቀሳቀስ ያቃታትን ሔዋን እየተመለከተ«ሔዋን ፅኒ እንግዲህ! አስቻለው ሞቷል!» አላት።
ሔዋን ግን የሰማችው አትመስልም፣ ፍጥጥ ብላ ቀረች። በልሁ ትላንት መርዕድን በስልክ ባነጋገረበት ሰአት «ነገ ልንመጣ ተነስተናል»ሲለው 'እሺ ኑ' ብሎ
የመለሰለት በእርግጥም እንዲመጡና ልብ በሽተኛዋ ሄዋን መርዷዋን ከመስማቷ በፊት በእጁ እንድትገባለትና ሊፈጠር የሚችለውን አደጋ በእሱ እገዛ ለማስቀረት አስቦ ነበር። አሁን ግን ከዚያ አደጋ የሚያመልጥ አልመስል አለውና ደነገጠ
የሔዋን ፈዝዞ መቅረት አስፈራው። ብቻ የተቻለውን ያህል ለመሞከር በማሰብ መርእድ ገፋ እንዲያደርግለት ጠየቀውና ይበልጡኑ ግን እሱ እራሱ ስቅስቅ አድርጎ አቀፈና ወደ መሬት አወረዳት።
«ሔዩ» ሲል ጠራት ወደ ታች አዘቅዝቆ እያያት። ሔዋን ግን ዝም። ይልቁንም አይኖቿ ስልምልም እያሉ ከእቅፉ ውስጥ
ወደ ታች ወደ ታች ትንሸራተተበት ጀመር፡፡ በልሁ ፈራና በጩህት«ታፈሥ! ድረሽ ታፈሥ ድረሽ!»እያለ ይጣራ ጀመር። በቃል ታፈሱን እየተጣራ በእጁ ደግሞ ሔዋንን ለማቃናት ይጥራል ታፈሡ አልሰማችውም ። እሷ ራሷ በአስቻለው አስከሬን ሳጥን ላይ
ትንፈራፈራለች። ሔዋንን የሰው መዓት ከበባት። እየሆነች ያለችውን ነገር ለማየት አንዱ በሌላው ትከሻ ሳይ ሲንጠራራ አንዳንዱ ደግሞ «ዘወር በሉ! ገለል በሉ! አየር
ስጧት! አየር.…አየር እያለ ይጮሀል። ነገር ግን ሁሉም ነገር ምንም አልፈየደም፡፡ ሔዋን ላትመለስ እየሄደች ስለመሆኑ ምልክቶች ታዩ፡፡ እንቅስቃሴዋ ሁሉ ቆመ።
መርዕድ ለታፈሡ መልዕክት አድርሶ ኖሯል። ታፈሡ ያንን ሰው ሁሉ እየገፈታተረች ከመሀል ስትገባ በልሁ ቁጭ ብሎ በሁለት እጆቹ መሬት እየመታ ሲጮህ ሔዋን ደግሞ ዝርግትግት ብላ አገአቻቸው::
«ኣ» አለች አፏ ጉድጓድ መስሎ እስኪከፈት ድረስ። «እኮ ምንድን ነው!?» ካለች በኋላ ሜዳ ላይ ዝርር ያለችውን ሔዋንን ልክ እንደ ልጆች ቼ ፈረሴ ጨዋታ ጋለበችና የሔዋንን አገጭ ወዲያ ወዲህ እያገላበጠች አንቺ ሒዩ! አንቺ የኔ! አንቺ ሔዩ! ሐዩ ሔዩ!» ትላት ጀምር። ጀሮዋን በአፍና በአፍንጫ ላይ ብትለትምም ምንም ትንፋሽ አጣች፡፡ ጭራሽ እየቀዘቀዘች ሄደችባት፡፡
ታፈታሡ እንደዚያው ቼ ፈረሴ እንደጋለበቻት በሁለት እጆቿ ግራና ቀኝ መሬት እየመታች ዋይ! ዋይ! ዋይ! ዋይ አሁንም ደግማ «ዋይ! ዋይ! ዋይ! ዋይ!» ለሶስተኛ ጊዜ “ዋይ! ዋይ! ዋይ! ዋይ!» በዙሪያው ያለው ሕዝብ ሁሉ
በለቅሶ ተንጫጫ።
የሆነው ሁሉ ሆኗልና ቀጥሎ መሆን ያለበት መሆን ጀመረ፡፡ የሔዋን አስክሪን ከበልሁና ከታፈሡ እጅ ወጣ፡ የመጨረሻ ዝግጅት ለሚያደርላት
ለገናዦቿ ተላልፎ ተሰጠ። በታፈሡ ቤት በር ፊትለፊት በሚገኘው ሰፊ መንገድ ላይ የሚደረገው ረግዶ ግን ነዳጅ እንደተጨመረበት እሳት ይበልጥ ተቀጣጠለ፡፡
ከቀኑ ወደ ስድስት ሰዓት አካባቢ ሌላ አዲስ ከስተት ታየ፡፡ ትናንት በልሁ በመስሪያ ቤት ጓደኞች በኩል የእስቻለውን ሕይወት ማለፍ ለታፈሡ እንዲነገራት አድርጎ ነበርና ታፈሡም በተሰማት መሪር የሀዘን ስሜት መሀል የሔዋን አባትና እናት ትዝ ብለዋት ልጃቸውን ያላቅሷት ዘንድ በሔዋን በኩል ታውቀው በነበረ
የስልክ አድራሻ መልዕክቱ እንዲደርሳቸው አድርጋ ኖሯል። የሔዋን እናትና አባት መርዶውን እንደሰሙ ይበልጥ ያዘኑት ለልጃቸው ነበር፣ ሀዘኑን እንዴት
ትችለዋለች በማለት፡፡ መርዶውን ማታ እንደ ሰሙ ወደ ዲላ ለመብረር ሲዘጋጁ አድረው ክብረ መንግስት ወደ አለታ ወንዶ፡ ከዚያም ወደ ዲላ በመጓዝ ስድስት
ሰዓት አካባቢ በታፈሡ ደጅ እሚወርደው ሙሾ መሀል ገቡ፡፡ የሔዋን እናት ክንፋቸውን ዘርግተው እየሮጡ ወደ ሕዝቡ ሊቀላቀሉ የሚያሰሙት ጨኸት
«ልጄ! ልጄስ...! ልጄን አሳዩኝ! እሙዬን አገናኙኝ..» እያሉ ነው::
ምን እያሉ እንደሆነና ለጊዜሉ የራሳቸውን ማንነት ሕዝቡ ያልተረዳላቸው ቢሆንም ነገር ግን ቆየት እያለ ምስጢሩ ሲታወቅ የታፈሡ ጎረቤቶች ጠጋ ጠጋ
አሏቸው። ክንዳቸውን ከወዲያና እወዲሀ በመያዝ ቀስ ይበሉ! ረጋ ይበሉ ይሏትው ጀመር። እሳቸው ግን አሁንም «ልጄ የታለች? እሙዩ የታለች።ማለታቸውን ቀጠሉ። ባለቤታቸው አቶ ተስፋዬም ከኋላ ከኋላቸው እየተከተሉ ልክ እንደ ሔዋን እናት ይጮሀሉ፡፡ ያለቅሳሉ።
የታፈሡ ጎረቤቶች ሰብሰብ አሉና የሔዋንን እናት ወደ አንድ ገለጥ ወዳለ ቦታ ወስደው ትንሽ ለማረጋጋት እየሞከሩ በኋላ ስለሆነው ነገር ፍንጭ ሰጧቸው፡፡

👍13
#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_ሃምሳ_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
...ሁለት ሦስት ቀን ቆይቶ ሚስተር ካርላይል ለዌስትሊን ነዋሪዎች ያዘጋጀው ንግግር በአካባቢ ጋዜጦች ወጣ ። ግድግዳዎቹ ሁሉ “ ካርላይልን ምረጡ! ምን
ጊዜም ካርላይል ! በሚሉ ፀባለ ልዩ ልዩ ቀለም ጽሑፎች አጌጡ " ...
ትንግርቶች ማብቂያ የላቸውም ። መገረምም የሰው ልጅ ዕጣ ነው » ሰር ፍራንሲስ ሌቪሰንን የሚያውቁት ሰዎች ሰር ፍራንሲዝ ሌቬሰን ከነበረበት ልማድና ጠባይ ራሱን አላቅቆ እሳት የላስ ፖለቲከኛ ሆነ ሲባል ስምተው እጅግ አድርገው ተደነቁ
ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ወደ ፖለቲካ ዓለም የዞረው የጠቅላይ ሚኒስትርነት
ቦታ ተሰጥቶት ወይም ከቁም ነገራም ሰዎች ጋር እንዲሰለፍ ሕሊናው ወቅሶት አይደለም " የገንዘብ ችግር ደረሰበት ። ስለዚህ ደኅና ገንዘብ የሚገኝበት ምንም የማይሠራበት አንድ የሚደገፍበት ነገር አስፈለገው "
የገንዘብ ችግር ! በቅርቡ ከፍተኛ ሀብት የወረሰ ሰው እንዴት ካሁኑ ችግር
ላይ ሊወድቅ ይችላል » የሚል ጥያቄ መነሣቱ አይቀርም " ፍራንሲዝ ሌቪሰን ሚወዳቸውን መዝናኛዎች ለሚወዱ ሁሉ ለክስረት ከዚህ የቀለለ መንገድ አያገኙም " ያጎቱን ማዕረግና ሀብት ሲወርስ እሱ ከጠበቀው የበለጠ ዕዳና ኪሣራ መክፈል ግድ ሆነበት " ሰር ፒተርም በመብቱ ማግኘት ከሚገባው በላይ አንዲት ቤሳ አልተወለትም ዕዳውን በሙሉ ከፍሎ የተረፈውንም ቢሆን በእጁ ከመግባቱ ገና በግራና በቀኝ ይበትነው ጀመረ ጋብቻው ለጥቂት ጊዜ ቢገታውም ተጨማሪ ወጭ ከማስከተሉ በቀር ምንም አላዳነውም " የገንዘብ ዐቅሙን መጥኖ በመኖር ፈንታ እሱና ሚስቱ ከዐቅማቸው በላይ መኖር ጀመሩ ከዚህ ሌላ ከጋብቻው ወዲህ በፈፀረስ
አሽቅድድም በቁማሮችና በልዩ ልዩ ውርርዶች ሁሉ መግባት ጀመረ " ያ ሁሉ
ገንዘብ ያስወጣ ነበር።
በዚህ ዐይነት ጊዜም ሔደ፤ሁኔታዎችም እስኪያቅታቸው ድረስ ተጓዘና ቆሙ።ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን በዚህ ጊዜ ነቃ " የነበረው ገንዘብ አንድ ሺልንግ እንኳን ሳይቀር አለቀ ዕቃው ሁሉ ተያዘ ። በነሱ ምትክ ዕዳና ዕዳ ጠያቂዎች ብቻ ቀሩ።
ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ባሮኑ የውርስ ተስፈኛ ከነበረዉ ከተራው ፍራንሲዝ
ሌቪሰን የበለጠ ተጨነቀ
ሥራው ሁሉ እንደ ሟቹ ሎርድ ማውንት እሰቨርን ነበር ነገር ግን ፡ ኧርሉ
የሆነ ብልሃት እየፈጠረ ጉዱን እስከ ጊዜ ሞቱ አለባብሶት ዐለፈ " ይኽኛው ግን ጕዱን ይዞ ከችግርና ካስቸጋሪዎች ጋር ተፋጠጠ የሚያደርገው ሲጠፋው ቁማር ቢጀምርም ዕድል ፊቷን አዞረችበት እንደ ምንም አለና ከፈረስ እሽቅድድም ውድድር
ገባ ነገሩ እንኳን ለጥቂት ቀን ይደግፈው ነበር ሆኖም እሱም አቅጣጫውን ለቀቀና እንዲያውም የተጨማሪ ዕዳ ተጠያቂ አደረገው " በመጨረሻ ብዙ ገንዘብ የሚገኝበት ብዙ የማይሠራበት የመንግሥት ሥራ ለመፈለግ በሕግ መወሰኛ የነበሩትን
ሚኒስትሮችን እንደልቡ ለሚያቀያይረው ለሎርድ
ሄድሎት ጸሐፊ ለመሆን የተስፋ ፍንጭ አገኘ " ተስፋው ግን ተጨባጨጨ ሊሆን የሚችለው ሰወየው በመጀመሪያ ፓርላማ የገባ እንደፀሆነ ብቻ ነው " ከዚያ በኋላ ለተጠየቀ ሥራ ብቁ መሆኑ ይገመገማል " ይህ ሁኔታ ነው ወደ አሁኑ ታሪክ ያመጣን ።
በአንድ ፀሐያማ ድኅረ ቀትር ኢቶን አደባባይ ላይ ከነበረ ቤት በጣም ያማረ ሳሎን
ውስጥ አንዲት መልኳ ስልክክ ያለ መልከ መልካም ልጅ እግር እመቤት ተቀምጣለች " በመልካሙ ፊቷ የቁጣና የኩርፊያ መልክ ይታይባታል " በሚያምረው እግሯ ሥጋጃውን ትመታለች ይህች ሴትዮ የሰር ፍራንሲዝ ሌቪስን ባለቤት ናት።
አንድ ሥራ መልካምም ሆነ ክፉ ይዋል ይደር እንጂ ለሠሪው ፍሬውን አያሳጣወም " ነገሩ ብዙ ዘመን አልፎታል ፍራንሲዝ ሌቪሰን 'ብላንሽ ሻሎነር በተባለች ቆንጆ ልቡ ይጠፋል በፍቅር። ከመኻል ላይ አቋርጦ ለእመቤት ላቤላ ሲል ቸለል ብሏት ይቆያል እንደገና ሳቤላን ጣል አድርጎ ወደ እሷ ተመልሶ የምስጢር ግንኙነት ያደርጋሉ " በምስጢርም ይተጫጫሉ " የብላንሽ እህት ሊዲያ ሻሎነር ትጠራጠርና እኅቷን ትጠይቃታለች ከሌቪሰን ጋር መተጫጨቷን ምላ ተግዝታ ትከዳለች » በዚህ ሁኔታ እንዳሉ ዘመናት ዐለፉ " ምስኪን ብላንሽ በፍቅሯ ማተብ እንደጸናች ጠበቀች ዕዳውን የገንዘብ ችግሩን ቸልታውን ከሳቤላ ካርላይል ጋር ኰብለላውን ሁሉ እያወቀች ትወደው ነበር ከልቧ ታምነው ነበር ውርሱን ካገኘ በኋላ ወደ ለንደን እንደ ተመለሰ የነበረው ወዳጅነታቸው እንደገና ቀጠለ " ግን በሱ
በኩል የነበረው ፍቅር እንደ ወትሮው ሳይሆን ቀዝቃዛና ጭብጥ የሌለው ቢሆንም
ብላንሽ እንደሚያገባት ትተማመን ነበር አሁንም ከሷ ጋር የነበረው ግንኙነት
እንዲያው ያዝ ለቀቅ ነበር » በምስጢር አለሁልሽ አንለያይም እያለ ' ከቤትም እየዘለቀ ይጠይቃት ነበር " ምናልባትም ግንኙነት ማቆሙን ቢነግራት እብድ እንደምትሆንበት በማወቅ ስለ ፈራ ይሆናል " ብላንሽ እንደ ምንም ብላ ጨከነችና ጋብቻው በቶሎ እንዲሆን ጠየቀችው መቸም ቀጣፊዎች ፈሪዎች
ናቸው ሰር ፍራንሲዝም ግልጽ ያለ ነገር እንዳይናገር ጋብቻው በቅርቡ እንደሚሆን ደኅና ሆኖ በማይሰማ አነጋገር እያልጐመጐመ ነገራት "
እኅቷ ሊድያ ሻሎነር ባሏ ሲሞት በተወላት ገንዘብ እየተረዳች ሚስዝ ዌሪንግ
ተብላ ደኅና ኑሮ ትኖር ነበር" ልጆቹ የሙታን ልጆች ስለ ነበሩ እኅቷ ብላንሽ ሻሎነርንም እሷ ያዘቻት ብላንሽ ወደ ሠላሳ ዓመቷ መቃረቧን የሚጠቁሙ አንዳንድ ምልክቶች ይታዩባት ጀመር ዓመቶቹ ሳይሆኑ የማያቋርጡ የተስፋ እንቅፋቶችና
የሐሳብ ጭንቀት ዱካዎች ይታዩባት ጀመር " ጸጉሯ ሳሳ ፊቷ ምጥጥ ሙግግ አለ"
የሚያምረው የሰውነቷ ቅርጽ ጠፋ „ “ ኧረ ወዲያ ደሞ ይችን ነው የማገባ !
አለ ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ለራሱ "
አሊሽ ሻሎነር የኻያ ዓመት ቆንጆ የነበረች ታናሽ እኅታቸው ለገና በዓል ልትጠይቃቸው መጣችና ሚስዝ ዌሪንግ ቤት ሰነበተች " በመልኳ ከትልቅ እህቷ ከብላንሽ ሻሎነር በጣም የላቀች ነበረች ገና አንዲት ፍሬ ልጅ ሳለች የተለያት ፍራንሲዝ ሌቪሰን አሁን እንደዚያ አምራና ዳብራ ሲያያት ጊዜ ከሷ ጋር ፍቅር ያዘው ፍቅርም ሲባል ወግ አለው እሱማ ልክ እንደ ጥላዋ እየተከተለ ደስ ደስ የሚሉ የፍቅር ቃላት በጆሮዋ እያንቆረቆረ ልቧን ከማረከ በኋላ ለጋብቻ ጠየቃት " ሳታቅማማ
እሺ አለችው " የጋብቻው ዝግጅት ወዲያው ተጀመረ ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን
ዝግጅቱን አጣደፈው እሷም ቶሎ መጋባቱን አልጠላችውም "
ከተራ ጓደኝነት የተለየ በፍቅር በጋብቻ መተሳሰር ለሚባል ነገር ጭራሽ
እንደማያውቅ ነገራት በዚህ ረገድ የሰጣትን ተስፋና የገባላትን ቃል
ጭልጥ አድርጎ ካዳት "
መረጃ ማቅረብ አልቻለችም " ከሱ የተጻፈላት ቁራጭ ወረቀት ወይም አንድ
የፍቅር ቃል ሲተነፍስላት ሰማሁ የሚል የጠላትም ሆነ የወዳጅ ምስክር አልነበራትም እሱ በጣም ተጠንቅቆበታል " እሷም ራሷ ምስጢር የጠበቀች መስሏት ከፍራንሲስ ሌቪሰን ምንም 0ይነት ግንኙነት እንዳልነበራት ለእኀቷ አረጋግጣላት ነበር ስለዚህ ለመዳን ተስፋ በሌለው ሁኔታ በመስጠም ላይ ባለች መርከብ ላይ አንደ

👍14😁2
#ተአምራተ_ኬድሮን
፡
፡
#ክፍል_ሃምሳ_ሰባት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////
ቫይብሬት ላይ የተደረገ ሞባይል ስልክ ላይ ሲደወል እንዳለ ንዝረት ተንቀጠቀጥችና አዕምሮዋን ከንስሯ ጋር አላቀቀች…
ሰላም ወደኬድሮን ተንደርድራ መጥታ እግሯ ሰር ድፍት አለችና‹‹በጣም አመሰግናለሁ….እግዜር ይስጥሽ››
‹‹ተነሺ ..እኔን አታመስግኚ…እሱ በጣም ስለለመነኝ ነው እንዲህ ያደረኩልሽ…››አለቻት
‹‹ኤርሚ እግዜር ይስጥልኝ….አንተንም በጣም ነው የማመስግንህ..ምን አይነት ሰላም በውስጤ እንደተሰራጨ አትገምትም››አለች ወደመቀመጫዋ ተመልሳ በመቀመጥ
‹‹በነጋራችን ላይ በጣም ነው የሚያፈቅርሽ …እንደነገረኝ ከሆነ ከልጅነቱ ጀምሮ አንቺን ሲያፈቅርሽ ነው የኖረው….አንድም ቀን አንቺን ማፍቀር አቁሞ አያውቅም..ግን በኑሮ ደራጃ ስለምትለያዩ እሺ አትለኝም የሚል ፍራቻ በውስጡ ስላለ ካንቺ ሲሸሽ ነው የኖረው››አፈረጠችለት
ባለማመን አንዴ ኬድሮንን አንዴ እሱን በማፈራረቅ ማየት ጀመረች..ኤርምያስም የተቀመጠበት ወንበር ላይ አንገቱን ወደወለሉ እንደደፋ ሚገባበት ጠፍቶታል እጆቹን እያፍተለተለ ነው…
‹‹አላውቅም ነበር…ኤርምያስ እኔን ማፍቀር….…?››
‹‹አዎ….ኤርምያስ አንቺን…››
‹‹እሺ ጥሩ ነው…አሁን ምን እናደርግ …ኤርሚ እርዳኝ ለእድር ሰዎች ንገራቸው…አባቴ ዛሬውኑ እንዲቀበር እፈልጋለሁ….››
‹‹አረ እሺ… ችግር የለውም… አሁኑኑ ነግሬያቸው ልምጣ …ስልካቸውን ስለማላውቅ እናቴ ጋር ሂጄ …››ብሎ ተነሳ
ኬድሮን የተለየ ሀሳብ አመጣች‹‹ቆይ መጀመሪያ የሬሳ ሳጥን እንግዛና አባትሽኝ በሳጥኑ ውስጥ በማድረግ ማዘጋጀት አለመብን..አሁን ዕድርተኛው መጥተው ጓደኞቸው ተሰብስበው እንገንዝ ማለታቸው አይቀርም …እንደዛ ከሆነ ደግሞ ሌላ ሀሚት ላይ ይጥልሻል…በህግም ሊያስጠረጥርሽ ይችላል››
‹‹ታዲያ ምን እናድርግ››አለች ግራ ገብቷትና ያለሳበችውን ነገር ስላነሳው ደንግጣ
‹‹ግድ የለም እኔና ኤርሚ ሳጥኑን ይዘን እንምጣ..ሁሉንም ከጨረስን ብኃላ ለሌላው ሰው እንናገራለን….››
‹‹አስቸገርኮችሁ አይደል…?››
‹አረ አትጨነቂ …እኔን እንደእህትሽ ቁጠሪኝ… ኤሪሚም ያው ያንቺው ነው..››አለችና ምትናገረው ጠፍቷት በመቁለጭለጨ ላይ ሳለች የደነዘዘውን ኤርሚያስን ይዛው ወጣች…
መኪናው ውስጥ ገብተን የሬሳ ሳጥን ወደሚሸጥበት ቦታ እያመሩ ሳለ…
‹‹ምን አይነት ተአምር ነው ያደረግሽው……?.››ሲል ጠየቀት
‹‹ያው ላንተ ስል ነው››
‹‹በጣም ነው የማመሰግንሽ….ግን እንደማፈቅራት ለእሷ ባትነግሪያት ጥሩ ነበር››
‹‹ለምን…?››
‹‹ያው አንደኛ መንገሩ ምንም ውጤት አይኖረውም ሁለተኛ እኔ እና አንቺ……››
‹‹አይ እኔና አንቺ የሚባል ነገር የለም…አኔን እርሳኝ…እኔ ሁለት ቀን ብቻ ነው የቀረኝ..››
‹‹ምን ለመሆን…?››
‹‹ለመብረር…››
‹‹እንዴ የት አሜሪካ ወይስ አውሮፓ……?››
‹‹በለው ከሁለት አንዱ….ስለዚህ እሷኑ ጠበቅ አድርግ.ደግሞ በትክክል ይሳካልሀል….
እንደምታፈቅራት ስነግራት የልቧን ምት በደንብ ታዝቤያለሁ. ዋናው ከዚህ ሀዘን እስክትወጣ ከስሯ አትለይ …….
‹‹እንዴ ወዴት ነው የምለየው….ከእሷ የሚበልጥ ምን ሌላ ጉዳይ ይኖረኛል››
‹‹ምንም ››
‹‹አንቺ ልትበሪ መሆንሽን መስማቴ ግን ቅር አሰኝቶኛል››
‹‹እኔን እርሳኝ አልኩህ እኮ››
‹‹እኮ እንዴት አድርጌ ልርሳሽ…?››
/////
የሰላምን አባት የቀብር ሁኔታ ካመቻቸችና ከተጠናቀቀ በኃላ ሁለቱንም አንድ ላይ ከለቀስተኞች ጋር ጥላቸው እናም በውስጧ ለመጨረሻ ጊዜ ተሰናብታቸው መልካሙን ሁሉ እየተመኘችላቸው ወደቤቷ ነው የተመለሰችው…ድክምክም ብሏት ነበር…ግቢውን አስከፍታ ስትገባ ግን ድካሟን ሁሉ ከላዮ የሚያበንላት አስደሳች ሁኔታ ነው የጠበቃት…
ግቢው መሀል ላይ ባለች ክፍት ቦታ ጠራጴዛ እና ወንበር ወጥቷል፤…ጠረጵዛው በልዩ ሌዩ ምግቦችና መጠጦች ተሞልቷል …ከዛ አልፎ ዙሪያው በየጥጋጥጉና በየቦታው የዛፍ ቅርንጫፎች ላይም ሳይቀር የተለያዩ የምግብና የፍራፍሬ አይነቶች ተቀምጠዋል…የተለያዩ ጥራጥሬዋች በየቦታው ተበትኗል….በጊቤዋ ውስጥ ያሉ እንስሳት ብቻ ሳይሆኑ እንግዳ የሆኑ ወፎች ሳይቀሩ ግቢውን ወረውት የተበተነላቸውን ጥራጥሬ በደስታ ይለቅማሉ… ጦጣና ዝንጆሮዎቾም ሙዙን እየላጡ ይውጣሉ …የማይፈነጭ እና የማያስካካ ፍጥረት በግቢው አይታይም.. የሆነ እንስሳት አግብቶ ሌሎቹ ሠርግ ተጠርተው አሼሼ ገዳሜ ላይ ያሉ ነው የሚመስለው….ሌላው ይቅር እያንዳንዱ ተክል ስሩ ተኮትኩቶና አፈር ታቅፎ ውሃ ጠግቦ እስኪተፋ ድረስ ጠጥቶ ይታያል….በቃ በግቢው አንድም ያልተደሰተ ፍጥረት አልነበረም..ይሄ ሁሉ በፕሮፌሰሩ የተደረገው እነሱ በተደሰቱበት መጠን እኔ እንደምደሰት በደንብ ስለሚያውቁ ነው፡፡
‹‹አትመጪም… ይሆን ብዬ በስጋት ላይ ነበርኩ …እንኳን በሰላም መጣሽ››አሏት ከእድሜ ጫና የተነሳ ያጎበደድት ፕሮፌሰር…
‹‹አይ እፈልግሻለሁ ብለውኝ የለ..…….?በዛ ላይ አንድ ቀን ብቻ ነው የቀረኝ …ማታ ወደ እናቴ እሄዳለሁ.አዎ ነገ ሙሉውን ቀን ከእሷዋ ጋር ነው ማሳለፍ የምትፈልገው………››
‹‹ጥሩ ጥሩ..ነይ እዚህ ጋር ቁጭ በይ›› ብለው ምግብ በሞላበት ጠረጴዛ ዙርያ ከበው ከተቀመጡ ወንበሮች ውስጥ አንድን ሳቡላት… አመስግና ተቀመጠች፡፡
የእጅ ውሀ አመጡላት …‹‹አረ እራሴ እታጠባለሁ›› ብላ በራሷ ተጣበች… ሳሀን ስባ ምንም እንኳን የምግብ ፍላጎት ባይኖራትም እሷቸውን ለማስደሰት ስትል ብቻ መብላት ጀመረች… እሳቸውም ከፊት ለፊቷ ተቀምጠው በስስት እያዮት መመገብ ጀመሩ…
‹‹የሚጠጣ ምን ልቅዳልሽ…….?››
‹‹ውሀ ››
‹‹ወይን ወይም ሌላ ነገር አይሻልሽም…….?››ካለወትሮዋ ዉሀ ማለቷ አስገርሞታል
‹‹አይ ውሀ ነው የምፈልገው….››
‹‹እሺ ካልሽ ››ብለው ውሀ ቀዱላት፡፡
‹‹ጋሼ በዚህ ምድር በኖርኩበት ዓመት የተረዳሁት ነገር ቢኖር ምድር መተኪያ የሌላቸው ሁለት ነገሮች መታዳሏን ነው ….አዎ እናትና ውሃ የዚህ ዓለም ሁለት ልዩዎች ናቸው…››
‹‹እንዴት ልጄ..…….?እንዴት እንደዛ ተረዳሽ…?››
‹‹እናታችን መጀመሪያ ገነታችን ነች..ከተፈጠርንበት ቀን አንስቶ እስክንወለድበት ቀን ድረስ በእናታችን መሀፀን ውስጥ ገነታዊ ኑሮ ነበር የምነኖረው… ያ ስፍራ ሁሉ ነገር በፍፅምና እንከን አልባ ስፍራ ነበር..ሁላችንም ከዛ ያለፍላጎታችን ተገፍትረን ስንወጣ(ስንወለድ) እሪ ብለን ለቅሶችንን የምንለቀው ምን እንዳጣን በደመነፍስ ስለሚገባን ነው…አዳም እና ሄዋን በሰሩት ሀጥያት ከገነት ወደምድር ተባረሩ የሚባለው ሌላ አይደለም ከእናት መህፀን ወደምድር ተገፍትሮ መውጣት ነው…ከዛ በኋላም ቢሆን እናት ምን ጊዜም እናት እንደሆነች ነው ምትቀጥለው… እንዳላረጀን እና እንዳላበቃልን የሚሰማን እናታችን በሰላሳ አመታችንም እንደ ህፃን ስትቆጣን ስናይ ነው..ጭንቅላታችንን ስትዳብስልን…ተይ አንቺ ልጅ ብርድ ይመታሻል ስትለን ነው፡፡

👍91❤8👏4😢4🔥2🥰2🤔1