አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ምንዱባን


#ክፍል_አንድ


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ

ቀና ሰው

በ1815 መሴ ቻርለስ ብየንቬኑ መሪል የሞንቴስ ሱር ሞንቴስ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ነበሩ፡፡ እድሜያቸው 75 ሲሆን የሞንቴስ ሱር ሞንቴስ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ሁነው የተሾሙት በ1806 ዓ.ም ነበር፡፡ ጳጳሱ ወደ ሀገረ
ስብከታቸው ሲመጡ እህታቸው ወ/ት ባፕቲስታን አብረዋቸው ነበር
የመጡት:: እህትዬዋ ምንም እንኳን ትዳር ባይዙም እድሜ የጠገቡ ሲሆኑ ወንድማቸውን በአሥር ዓመት ይበልጧቸዋል፡፡

ከጳጳሱ ቤት ውስጥ ሌላም ሴት ነበሩ፡፡ እኝህ ሴት የወ/ት ባፕቲስታን እኩያ ናቸው:: ሴትዬዋ ወ/ሮ ማግልዋር ይባላሉ:: ሴትዮዋ ቀደም ሲል የሌላ ሰው አገልጋይ ሆነው ሠርተዋል፡፡ አሁን ደግሞ የወ/ት ባፕቲስታንና
የጳጳሱ ቤት ጠባቂ ሁነው ተቀጥረው ይሠራሉ፡፡

ጳጳሱ ከሀገረ ስብከታቸው እንደደረሱ በሀገሩ ደምብ መሠረት ከፊልድ ማርሻል ቀጥሎ ያለውን ሹመት ይሰጣቸዋል፡፡ የክፍለ ሀገሩ መሪና የማዘጋጃ ቤቱ ሹም ከቤታቸው ሄደው «እንኳን ደህና መጡ» በማለት እጅ ይነስዋቸዋል፡፡ አቡኑም በተራቸው ከዚያ ለተገኙ ከፍተኛ ባለሥልጣኖች ቡራኬ ይሰጣሉ፡፡ የከተማው ሕዝብ በአጠቃላይ አዲስ የተሾሙለትን ጳጳስ
ለማየት በጉጉት ሲጠባበቅ ነበር፡፡

የጳጳሱ ቤት ከአንድ ሆስፒታል አጠገብ ሲሆን ቤቱ እጅግ በጣም
ሰፊና ያማረ ነው:: ሆስፒታሉ ይገኝ የነበረው ከረባዳ ሥፍራ ላይ ሲሆን ግቢው እንደ ጳጳሱ ቤት አይሰፋም:: ጳጳሱ ወደዚያ ሲሄዱ በሦስተኛው ቀን ሆስፒታሉን ይጎበኛሉ:: ከጉብኝቱ በኋላ የሆስፒታሉ አስተዳዳሪ ከቤታቸው
ድረስ መጥቶ እንዲያነጋግራቸው ይጋብዙታል:: አስተዳዳሪው ከጳጳሱ ቤት ይሄዳል::

በሆስፒታሉ ውስጥ «ስንት በሽተኞች አሉ? » ሲሉ አስተዳዳሪው ጠየቁ::

«ሃያ ስድስት» ሲል መለሰላቸው::

«ልክ እኔ እንደቆጠርኳቸው ናቸው አልተሳሳትክም» አሉ ጳጳሱ::
ጳጳሱ የቤታቸውን አዳራሽ በዓያናቸው ቃኙ:: አመለካከታቸው
አዳራሹን በዓይነ ሕሊናቸው የሚለኩና የሚያከፋፍሉ ይመስሉ ነበር ።

«ይህ ክፍል ብቻ ሀያ አልጋ ይይዛል» አሉ እርስ በራሳቸው? ሲነጋገሩ።
ከዚያም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው የሚቀጥለውን ተናገሩ::

«ወዳጄ የምለውን አጢነህ ስማኝ፡፡ እዚህ ቦታ አንድ ስህተት የተፈጸመ ይመስላል፡፡ እናንተ አምስት ወይም ስድስት ጠባብ ክፍሎች ናቸው ያሏችሁ::
ከዚያ ውስጥ ሃያ ስድስት ሰዎች ይተኛሉ፡፡ እኛ እዚህ ሦስት ሰዎች ብቻ ነን፡፡ ያለው ቦታ ግን ለስልሣ ሰው የሚበቃ ነው:: ታዲያ ይህ የአደላደል ስህተት አይመስልህም? የእኔን ቤት አንተ ብትወስድ ፤ የአንተን ደግሞ እኔ
ብወስድ ይሻላል፡፡›

በሚቀጥለው ቀን ሃያ ስድስቱ በሽተኞች ወደ ጳጳሱ ቤት ተዛወሩ፡፡
ጳጳሱም ሆስፒታሉን ተረከቡ:: ወሬው በከተማው ተነዛ፡፡ በጥቂት ቀናት ውስጥ የጳጳሱን በጎ ምግባር በመከተል ለበጎ ተግባር የሚውል እርዳታ ይጎርፍ ጀመር፡፡ በየቀኑ ከጳጳሱ ቤት በር የሚያንኳኳ ሰው ቁጥር እየበዛ
ሄደ፡፡ ሆኖም የሚመጣው ሰው ሁሉ እርዳታ ለማድረግ ብቻ ሳይሆን ምፅዋት ለመቀበልም ነበር፡፡ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ጳጳሱ የብዙ ችግረኞች ቀላቢ፣ ምፅዋት ሰጪና ገንዘብ ሰብሳቢ ሆነ፡፡ ብዙ ገንዘብም ከጳጳሱ እጅ እየገባ ለድሃ ይሰጥ ጀመር:: የሚገኘው ገቢ ግን ልክ ከደረቀ
አፈር ላይ እንደሚፈስ ውሃ ገና ከመገኘቱ ወጪ ሆኖ በቶሎ ያልቃል፡፡ጳጳሱ ገንዘብ ቢያገኙም ከተገኘው ገቢ ጥቂቱን እንኳን ለራሳቸው ወደኋላ አላሉም፡፡ እንዲያውም ከነአካቴው የራሳቸውንም ይዞ ይሄድ ጀመር፡፡
ጳጳሳትን ከስማቸው አስቀድሞ ንጽህናቸውን ለማረጋገጥ ብፁዕ ወቅዱስ እያሉ መጥራት የተለመደ ቢሆንም በዚያ አካባቢ ይገኙ የነበሩት ነዳያን ፍቅራቸውንና ቅርበታቸውን ለመግለጽና የጳጳሱን ደግነት ለማውሳት ብፁዕ ወቅዱስ በማለት ፈንታ «አባ ደጉ» እያሉ ይጠርዋቸዋል፡፡

እኚህ ደግ ሰው በ1815 ዓ.ም ምንም እንኳን 75 ዓመት ቢሞላቸወም ከስልሣ ዓመት በላይ የሆናቸው አይመስሉም ነበር:: ቁመታቸው እጅግም ረጅም ሳይሆን መጠነኛ ሆኖ ሰውነታቸው ደልዳላ ነው:: ክብደታቸውን
ለመቆጣጠር በእግር መሄድ ያዘወትራሉ:: ሲራመዱ መሬት በኃይል እየረገጠ ከወገባቸው ትንሽ ጎበጥ ይላሉ::

የልጅ ፈገግታ በተጎናጸፈ አንደበት ሲናገሩ ከግርማ ሞገሳቸው ብዛት
የሰማቸው ሁሉ የመንፈስ እርካታን ያገኛል:: ከመላ ሰውነታቸው ደስታ
የሚንፀባረቅ ይመስላል፡፡ ደግነት የተቆራኘው አካላቸውና ወተት የመሰለው ጥርሳቸው ፈገግ ሲል እኚያ «ጨዋ ሰው ፤ እድሜ የተቸረ ሽማግሌ፤ ደግ ሰው» በማለት ለደጋግ ሰዎች የምንሰጠው ቅጻል ሁሉ በእኚህ ሰው ላይ ጎልቶ ይታያል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ላያቸው እንኳን ስለብቃታቸውና
ስለደግነታቸው አይጠራጠርም:: ነገር ግን አንድ ሰው ለጥቂት ሰዓት ከጳጳሱ ጋር ቢቆይና በአሳብ ባህር ተወጠው ቢያያቸወ ቀስ በቀስ
መለወጣቸውን ይገነዘባል፡: ግርማ ሞገሳቸው በቃላት ለመግለጽ በማይቻል ሁኔታ ያስፈራል፡፡ ሰፊውና ኮስታራው ፊታቸው እንዲሁም ሻሽ የመሰለው
ፀጉራቸው ክብር የተጎናጸፈ ለመሆነ በግልጽ ይታያል:: ግርማ ሞገስ ከውስጣቸው እየፈለቀ ሲወጣ የሚያልቅ ቢመስልም የእንዐባራቂነት ኃያል
እንዳለው አያጠራጥርም:: እንዲያውም አንድ ሰው ሁኔታቸውን በጥሞና ሲመለከት «አንድ መልአክ በፈገግታ አጊጦ ያየኛል» የሚል ስሜት
ያድርበታል፡፡ እኚህ ሰው የሚያሰላስሉት ስለ ክቡር ጉዳይ እንጂ ስለርካሽ ነገር ላለመሆኑ ጥርጣሬ አይገባውም::

ጸሎት ማድረስ፤ ምፅዋት መስጠት፧ የመንፈስ ስቃይ የደረሰበትን ማጸናናት፤ ወንድማማችነትን መስበክ፤ ራስን ለሌሎች መስዋዕት ማድረግ፤
በእምነት ራስን መግራት የጳጳሱ የእለት ተዕለት ኑሮ ሲሆን ይህም ኑር በበጎ አሳብ፤ በምርጥ ቃላትና በበጎ ተግባር የተሞላ ነበር፡፡

ክረምት ይሁን በጋ ሁለቱ ሴቶች ሲተኙ ብፁዕነታቸው ወደ ጓሮ
ሄደው አትክልት ውስጥ ለአንድ ወይም ለሁለት ሰዓት ፈጣሪያቸውን በማሰብ ከዚያ ካልቆዩ ኑሮአቸው የተሟላ አይመስላቸውም:: አሳባቸውን
ሰብስበውና የመንፈስ እርጋታን አግኝተው የምሽቱን ሰላምና ፀጥታ ከሰዎች የመንፈስ እርካታ ጋር እያነፃፀሩ የከዋክብትን ብዛት በመመልከት ከአትክልቱ
ውስጥ ይንሸራሸራሉ፡፡

በዚያች ሰዓት አበቦች ያለመስገበገብ የሚለግሱትን መልካም መዓዛ እየማጉ ጥቅጥቅ ካለ ጨለማ ውስጥ እንደበራ ሻማ ብቻቸውን በፍጥረታት
መካከል በደስታ የተዋበው ነፍሳቸውን ዘርግተው ይቆማሉ:: አእምሮአቸው ውስጥ ምን እንዳለ ራሳቸውን ቢጠይቁ መልሱን አያውቁትም:: ሆኖም ከሰውነታቸው ውስጥ አንድ ነገር ወጥቶ እንደሚሄድና አንድ ነገር ደግሞ ከሰውነታቸው ላይ እንደሚያርፍ ይሰማቸዋል ፤ አንድ ዓይነት ምሥጢር መከናወኑን ይገነዘባሉ::

እኚህ እድሜ የጠገበና ፈጣሪያቸውን የቀረበ ሰው የእረፍት ጊዜያቸውን የሚያጠፉት ቀን ቀን አትክልት በመኮትኮት ሲሆን ማታ ማታ ደግሞ ፈጣሪያቸውን በጸሎት በማመስገን ስለሆነ ሌላ የሚፈልጉት
ነገር አልነበረም:: ምድሩ በአበባ ፤ ሰማዩ ከከዋክብት በማጌጡ የመንፈስ እርካታ ይሰጣቸዋል::

ውድቀት

ጊዜው 1815 ዓ.ም ወሩ ጥቅምት ነው:: ፀሐይዋ ልትጠልቅ አንድ ሰዓት ያህል ሲቀራት አንድ በእግሩ የሚጓገዝ ሰው ወደ ሞንቴስ ሱር ሞንቴስ
👍47😁3👏2👎1🔥1
#ገረገራ


#ክፍል_አንድ


#በታደለ_አያሌው

“እኔ እምልሽ” አለች እናቴ፣ ሆድ ሆዴን እያየች።

“እመት እመዋ?” አልኋት፣ ዳር ዳርታዋ ያልገባኝ ይመስል።

“እምታዋዩኝ ጉዳይ የለሽም ወይ?”

"እ"

በቃ፣ አዉቃብኛለች። ለነገሩማ እንዲህ ሆዴን ገፍጥጬ እንዴት
አይታወቅብኝ? እመዋ አይደለች እንዴ ሴትዮዋ? ለመዋሸትም ለማመንም እያመነታሁ የምንተፍረቴን ሰረቅ አድርጌ ሳያት፣ አሁንም ዓይኗን ከሆዴ
ላይ አልነቀለችውም። በአዛኝቷ! ከቅድሙ ይልቅ አሁን ደግሞ እንዴት ነው ዓይኗ የደፈራረሰው? ጥርሶቿን ልትፈለቅቅ ብትሞክርም፣ እምቢ
እንዳላት ግን ታውቆኛል። እንዲሁ መግቢያ ስታሳጣኝ፣ ዝም ብዬ ወደ ኋላ ሸሽቼ ገረገራውን ተደገፍሁና፣ ኹለተኛ እንኳን የሌለውን የቤተ ክርስቲያኑን ጉልላት ደጋግሜ መቁጠር ጀመርሁ። እንደ ሁኔታዬማ
የተደገፍሁትን ሁሉ ገፍቼ አለመጣሌ አስደንቆኛል።

“ግድየለም ተዬው እሺ፤ ባሰኘሽ ጊዜ ራስሽ ትነግሪኝ አልነበር
እንዲያዉስ? ተዪው በቃ”

“አይ” አልሁ፣ እጄን በዓይኗ እና በሆዴ መካከል ማድረጉን እንደ ተሻለ አማራጭ እየሞከርሁት፡፡ “ጊዜ እየጠበቅሁ ነዉ እንጂ፣ መደበቁን ፈልጌው አልነበረም እኮ እመ። ልደብቀውስ ብል ከእንግዲህ እየገፋ እንጂ እየጠፋ አይኼድልኝ ነገር! መቼስ ጉዴ ፈልቶ የለም አንዴ?”

“እንግዲያው እማትነግሪኝ፤ ንገሪኛ”

“እረ እመዋ ስሞትልሽ”

አንጀቷን ሳልበላው አልቀረሁም። ዓይኖቿን ወደ ዓይኖቼ አምጥታ
በርኅራኄ ስታየኝ ቆየች። እንዲያዉም ለምን እንደሆነ ባይገባኝም፣ ሳቅ ሳቅ እያላት መጣ። ቆይታማ ጭራሽ ስቃ ልታስቀኝ ጭምር ምንም
አልቀራት። እንዲህ ስትሆን ደግሞ እንዲያዉም ከነጭራሹ ያዘነችብኝም አልመስልሽ እያለችኝ መጣች።

“ተንግዲህ አያት መሆኔም አይደል?”

ዝም አልኋት። አያት መሆን የምትጀምረዉ በእኔ ይመስል፣ እንደ ብርቅ ማየቷ አልተዋጠልኝም። እንኳንስ ታላላቆቼ፣ ታናናሾቼ ጭምር አያት
አድርገዋት የለም'ንዴ? ያልሰማሁ መስዬ፣ ዝም አልኋት።

“ሆድሽን አይቼ አንቀጽዋን ልገምት?”

አሁንም ዝም።

“ሴት ናት፤ አይደለችም?”
"ጭጭ"
“ስም ላውጣላት?”
እርጭ፡፡
“ቱናት" ብያታለሁ። ደስ ይል የለ? በቃ ሴት ብትሆንልኝስ፣ ቱናት ነው
እምላት እኔ”

ዓይናማ ድንጋይ እንደ መሰልሁ ቀረሁ፣ በፊቷ። የምለው ቸግሮኝ
እየተንተባተብሁ ሳለ፣ ቄስ ገበዙ ወዳለንበት ቀርበው ሰላምታ አቀረቡልንና ከጉድ አተረፉኝ፡፡ ደራሽ መልአክ መስለዉ ነዉ የታዩኝ። ጎንበስ ቀና እያሉ
በረዥሙ ጤንነታቸውን ከተጠያየቁ በኋላ፣ እመዋን አበመኔቱ እንደሚፈልጓት ነግረዋት ተመለሱ። ወዲያውኑ ፈቃድ እየጠየቀችኝ በሚመስል ሁኔታ፣ ለዐመል ያህል ወደኔ አይታ መልከኛዋን የሥዕል ቤት ኪዳነ ምሕረትን እና ባለ ሞገሱን የበዓታ ለማርያም ገዳም ሕንጻ
ወደሚከፍለው ሰፊ አደባባይ ገባች። እሷ ገና ትንሽ ፈቀቅ ከማለቷ፣ አጭር መልእክት ሲመጣልኝ የእጅ ስልኬ የሚያሰማውን ጺዉጺዉታ
አሰማኝ።

ወጣ አድርጌ ስመለከተዉ፣ ከባልቻ መሆኑን አወቅሁ።

ባልቻ፣ በአሁኑ ጊዜ የሲራክ ፯ ዋና ኃላፊ ሲሆን፣ የላከልኝ መልእክት
(አሁኑኑ እዚያዉ ይላል። በአስቸኳይ ስፈለግ የሚመጣልኝ እንዲህ ያለ መልእክት ነው። የምፈለገው ድንገተኛ ለሆነ አጭር ስብሰባ ወይም ለአንዳች ተልእኮ ወይም ለሌላ ለምንም ጉዳይ ሊሆን ይችላል። ምንም
ቢሆን ምን ግን፣ እንዲህ ያለ መልእክት በደረሰኝ በዐሥር ደቂቃዎች ውስጥ መድረስ ይኖርብኛል። በተለይም የተፈለግሁት እንደ አሁኑ በባልቻ
ከሆነ፣ እኔን የሚፈልግ እጅግ አስቸኳይ ጉዳይ ተፈጥሯል ማለት ነው።ስለዚህ፣ እመዋ አበመኔቱን አነጋግራ እስከምትመለስ ድረስ ለመጠበቅ ቀርቶ፣ በስመ አብ እንኳን የምልበት ጊዜ አይኖረኝም፡፡ ይልቁንስ
አሁኑኑ መሮጥ አለብኝ። ያለበለዚያማ የእመዋ ሰላምታ ብቻውን ጉዞ ፍትሐት ያስጨርሳል። በዚያ ላይ አበመኔቱ የፈለጓት እንዲሁ ለማነጋገር ብቻም ላይሆን እኮ ይችላል። አይበለውና እኔ እዚሁ ከአሁን አሁን መጣች
እያልሁ እሷን ስጠባበቅ፣ ምንጣፎችን እንድታጥብ ወይ ደግሞ የተግባር ቤት ሥራ ቢያዝዟትስ ምን ይዉጠኛል?

ኧረረረ! መሰናበት አለብኝ፡፡ አሁኑኑ።

“እመዋ” አልኋት፣ እንደ መሮጥ ብዬ ከኋላዋ ስደርስባት።
“ምነዉ ምሆንሽ?”
“በቃ ከሰሞኑ ብቅ እላለሁ”
“ምን ልትሆኝ ነው አሁን? ቆዬኝ ይልቅስ ደርሼ መጣሁ”
“አይ፤ ሥራ ቦታ ቶሎ ነይ ተባልሁኝና
“ኤድያ! ያንቺ ሥራ ደሞ። ወይ እንዲህ ነዉ አይሉት፣ ወይ ለእናት
የሚተርፍ ጊዜ አይሰጥ”
“ሰሞኑን እኮ እመጣለሁ”
“ጭራሽ?” አለች ቆጣ ብላ፣ ከቤት እንደ ወጣሁ ማደር ማብዛቴን ጭምር እንደ ከነከናት በሚያስታዉስ ሁኔታ።

“ያዉ የሥራ ነገር አይደል፣ ምን ላድርግ ብለሽኝ ነዉ?”

“እኮኮኮሽ! ብትሄጅስ እዉነት እሱን ሳትነግሪኝ ልትሄጅ ነወይ?”

“የቱን እመ?”

ሆዴ ላይ ዓይኗን ጣለች። ገባኝ፡

“ምን ላድርግ ብለሽኝ ነዉ እመ፤ ያዉ እንጀራ አይደል?”

“ይሁን እሺ። ባይሆን ቶሎ እቤት አትመጭም? ከሥራሽ መልስ?”
አለችኝ፣ በስስት እና በቅያሜ ትንሽ ካስተዋለችኝ በኋላ፡፡

“እሺ” አልኋት፣ ሳላቅማማ። እኔ እንዲያዉም አብሪያት ሆኜ
እየዳበሰችኝም ጭምር፤ ታሳሳኛለች። ለቅጽበት እንኳን የሚለየን ባይኖር ደስታዉን አልችለዉም።

“እሺ እመጣለሁ” አልኋት።

“ትመጫለሽ? በይ ደሞ እንደ ሠለስትናዉ እመጣለሁ ብለሽ ቅሪ አሉሽ።በይ ደህና ዋይ። መኪናሽን ይዘሽ የለ? ቀስ እያልሽ ንጂ ደሞ። ጥድፍ ጥድፍ ትይና ወዮልሽ!”
በዓይኔ ትንሽ ሸኝቻት ሰዓቴን ስመለከት፣ ሦስቱ ደቂቃ እዚሁ ወድሟል።
ቢሆንም የቀረኝ ሰባት ደቂቃ፣ በቂዬ እንደሆነ እያሰብሁ ወደ ግቢዉ መዉጫ በር ዘወር ስል እንደገና ጠራችኝ

"እመት እመዋ?”

“ይቺን ነገር...” ብላ፣ ወደ ጉንፏ እየዳበሰች ወደኔ መለስ ስትል፣ ወደ እሷ ተሽቀዳድሜ ሮጬ ተቀበልኋት። ነገርዮዋ በእራፊ ጨርቅ ስለተጠቀለለች ምን እንደሆነች ላውቃት አልቻልሁም፡፡ የእምነት አፈር ልትሆን እንደምትችል ግን ገምቻለሁ።

“ምን ላድርጋት እመዋ?”

“እቤት አድርሰሽልኝ እለፊማ”

እንደገና በስስት ተሰነባበትንና፣ ወደ ሥዕል ቤት ኪዳነ ምሕረት መለስ ብዬ ተሳለምሁ። ጨርሼ እየወጣሁ፣ ልክ በወንዶች መግቢያ በኩል ስደርስ፣ አንድ ሰዉ በትከሻዬ ትክክል ድንገት በኃይል አስነጠሰብኝ። ሰአሊ
ለነ! ከየት ነዉ እንዴ? ድምፁን ተከትዬ ቀና ብል፣ መትረየስ በበሩ
ትክክል ካነጣጠረ አንድ ወታደር ዓይን ጋር በዓይኔ ገጠምሁ። ክዉ ብዬ ነዉ የቀረሁ። ምንም እንኳን ቅጽረ ቤተ ክርስቲያኑ ከቤተ መንግሥቱ ግቢ ጋር አጥር ብቻ የሚከፍላቸዉ ቢሆንም፣ ጥበቃዉን ግን በዚህ ደረጃ
አልጠበቅሁትም። ቆይ ምንድነዉ የሚጠብቀዉ? ማን ላይ ነዉ እንዲህ ያነጣጠረዉ? ካልጠፋ ቦታ እስከ ታቦቱ መቀመጫ የመቅደስ ክፍል ድረስ
በሚያሳይ ቅርበት ላይ እንዲህ ያለ ማማ? በዚያም ላይ ያጠመደ ወታደር?ስንት ጊዜ እዚህ ስመላለስ፣ ያለ ዛሬ አስተዉየዉ አላዉቅም። የግንብ
አጥሩን ተከትዬ ዙሪያዉን ስመለከት፣ ተመሳሳይ ወታደሮች በተመሳሳይ አኳኋን ዓይናቸዉን የሰጎን ዓይን አስመስለዉ ቆመዉባቸዋል። በሁሉም
የቤተ መንግሥቱ ወሠንተኛ አብያተ ክርስቲያናት እንደዚሁ ነዉ። ልክ እንደ ኪዳነ ምሕረት ሁሉ ወደ ታዕካ ነገሥትም ወረድ ብዬ አየሁ፣ ወደ ግቢ ገብርኤልም አለፍ ብዬ አስተዋልሁ። በሪፐብሊኩ ጠባቂዎች
ተከቧል።
👍582🥰2👏2😁1😱1
#ሳቤላ


#ክፍል_አንድ


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

ዊልያም ቪን በከተማ ውስጥ ከሚገኘው ቤቱ፡ በተለይም ከሚያምረው ሰፊ ቤተ መጻሕፍት ውስጥ በምቹ ወንበር ላይ ተቀምጧል "

አንደኛው እግሩን በወፍራሙ በታጠፈ ጨርቅ ግጥም አርጎ አስሮ ከአንድ
ለስላሳ ትራስ ላይ አሳርፎ ሕመሙን ያዳምጣል ። ገና ዐርባ ዘጠኝ ዓመቱን እንኳን ሳይደፍን ጸጉሩ ሽብቶ ሰፊው ግንባሩ ተጨማዶ ዱሮ ያምር የነበረው ፊቱ ምጥጥ ድርቅ ብሎ ያለ ዕድሜው አርጅቶ ሽማግሌ ሆኗል ።

ዊሊያም ቬን በፖለቲካ ሰውነቱ ወይም በጦር መሪነቱ ወይም በላቀ የሕዝብ አስተዳዳሪነቱ ወይም የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባል እንደ መሆኑ መጠን
በኃይለኛ ተናጋሪነቱና በንቁ ተከራካሪነቱ፡ ሳይሆን በገንዘብ አባካኝነቱ፡በቁማርተኛነቱ በዕለት ደስታ ፈላጊነቱና በደንታ ቢስነቱ፡ በሁሉም ዘንድ የታወቀ ነበር ፡፡

በፊት ኻያ አምስት ዓመት እስኪሞላው ድረስ ዋዛ ፈዛዛ የማያውቅ የያዘውን ተግባር ከዳር ሳያደርስ የማይለቅ ትጉሕና ቁም ነገረኛ ነበር ። ሕግ ሲያጠና
በነበረበት ጊዜ ከትምህርት ቤቱ የሚጠበቅበትን ግዴታ በሚገባ ለመወጣት ሲል አምሽቶ እየተኛ ማልዶ እየተነሣ ተግቶ ማጥናትን የዘወትር ተግባሩ አደረገወዉ ፡፡ ትዕግሥት የሞላበት ጥረቱን የተመለከቱ፡ ጀማሪ የሕግ ተማሪዎች የሆኑ ጓደኞቹ « ዳኛው ቬን » የሚል የቅጽል ስም አወጡለት ። ወጣቱ፡ ዊልያም ቬን ልቡ ሰማይ ነበርና የደረጃ ዕድገቱና የታዋቂነት ምኞቱ ሊሳካለት የሚችለው ዝንባሌውንና ተሰጥዎውን በጥረቱ በማጠናከር መሆኑን ስለተገነዘበ ባልንጀሮቹ ወደ ዕለታዊ ደስታና ወደ ቦዘኔነት ሊመልሱት ያደረጉት ሙከራ ሁሉ ሳይዝላቸው ቀርቷል
ዊልያም ከመልካም ቤተሰብ የተወለደና በዚያን ጊዜ ሽማግሌ ለነበረው የማውንት
እስቨርን ኧርል ወራሽ ዘመድ ቢሆንም ለራሱ ግን ምንም የሌለው ድሀ ነበር ። የሽማግሌው ወራሽ ሆኖ በእግሩ እንዳይተካ እንኳን በዝምድናቸው ቅርበት መሠረት የቅድሚያ መብት የነበራቸው ሌሎች ሦስት ጤናቸው የተሟላ ዘመዶች ነበሩት ።ከሦስቱ ውስጥ ደግሞ በተለይ ሁለቱ፡ ገና ወጣቶች ስለነበሩ ውርሱን በሞት የመልቀቃቸው ተስፋ የመነመነ ነበር ። እሱም ቢሆን : ከነዚያ ሁሉ ዐልፍ ይደርሰኛል የሚል ተስፋ በሕልሙም ሆነ በውኑ መጥቶበት አያውቅም። ነገር ግን ሦስቱም ተከታትለው አለቁ ። አንዱን የሚጥል በሽታ ገደለው ። ሁለተኛዉ ወደ አፍሪካ እንደ ሔደ በንዳድ ሞተ። ሦስተኛዉ ባገሩ በኦክስፎርድ አካባቢ በጀልባ ሲጓዝ ተገልብጦ ሰጠመ። በዚህ ምክንያት፡ የሕግ ተማሪው ዊሊያም ቬን ሳያስበውና ሳያልመውን በድንገተኛ አጋጣሚ የማውንት እስቨርን ኧርልን ማዕረግና ሀብት ወረሰና ! የስልሳ ሺ ፓውንድ ያመት ገቢ ሕጋዊ ባለመብት ሆነ

በመጀመሪያ ሲያስበው ያን ያህል ገንዘብ በየዓመቱ ከገባለት እንዴት አንደ ሚጠቀምበት ጨንቆት ነበር ። ነገር ግን ገና ሳይጀምር ትንሹም ትልቁም የሱ አወዳሽና አሞጋሽ ሆኑ ። በዚያ ሁሉ አንፋሽ አከንፋሽ ብዛት ጭንቅላቱ፡ ያለመዞሩ ያስገርም ነበር ዊልያም በውርሱ ባገኘው ማዕረግና ሀብት ብቻ ሳይሆን ቀድሞውንም የሚያምር መልክና የሚስብ ጠባይ ስለ ነበረው፡ የደመቀና የተደነቀ ሰው ሆነ ።ነገር ግን ያን ምስኪን የሕግ ተማሪ ከትምህርት ቤቱ፡ ብቸኛ ክፍሎች ውስጥ ጠብቆ ይዞት የነበረው አስተዋይነት እርግፍ አድርጐ ከዳውና ሕይወቱን ቅጥ አምባር በሌለው ጥድፊያ ሲመራው የተመለከቱት አንዳንድ አስተዋዮች አንድ ቀን በግንባሩ ተደፍቶ እንደሚቀር ይናገሩ ነበር ። ቢሆንም በዓመት ከፍተኛ ገቢ ያለው ሰው
በቀላሉ ጨርሶ አይወድቅምና እነሆ በጎ ኗሪ መስሎ ከቤተ መጻሕፍቱ ተቀምጧልም የአእምሮ ሰላም የነሡትን ሕይወቱን በቋፍ ያንጠለጠሉትንና እንደማይነቀሉ ሆነው የተጣቡትን ችግሮች ግን አገር ስምቷቸዋል ። ካገር በበለጠም የቅርብ ወዳጆቹ ከነሱ ይልቅ ደግም ባለዕዳዎች ደህና አድርገው ዐውቀዋቸዋል ወደ ዕብደቱ የሚያጣድፈው ሥቃዩ ብቻ የግሉ ድርሻ ስለሆነ ከራሱ በቀር ማንም አላወቀለትም ሊያውቅለትም አይችልም ከብዙ ዓመት በፊት የነገሩን አጀማመር ተመልክቶ
አዝማሚያውን አስተውሎ: መጨረሻው ምን ሊሆን እንደሚችል ለማሰብ ትኩረት
ሰጥቶ ገንዘብ አወጣጡን በቅጡ ለማድረግ ቢሞክር ኖሮ ፡ ክብሩን ለማደስ ይቻላው ነበር ። እሱ ግን ብዙ ብጤዎቹ የዚህ ዐይነቱ ነገር ሲደርስባቸው እንደሚያደርጉት ያቺን እንድ ጊዜ ደርሳ ማጋለጧ የማይቀር ቀን ላልተወሰነ የጊዜ ገደብ ወደ ጐን በመተው በዕዳ ላይ ዕዳ መጨመሩን ቀጠለበት ። ቁርጠኝነቱ የውርደትና የውድቀት ሰዓት ግን ጉዞዋን አላቆመችም ። እየቀረበች መጣች ።

ዊልያም ቬን ከዚህ ምዕራፍ መግቢያ እንደ ተመለከትነው : ከቤተ መጻሕፍት
ተቀምጦ የሚተክዘው ከፊቱ ካለው ጠረጴዛ ላይ ምስቅልቅል ብሎ የተቆለለውን የብዙ ልዩ ልዩ ዕቃዎች ሰነድ እየተመለከተ ይሆናል ።

እንደዚያ ተቀምጦ ሲተክዝ የጋብቻው ሁኔታ ታወሰው “ ግሬትና ግሪን ከሚ
ባለው ቦታ የፈጸመው ጋብቻ ምንም እንኳን ሴትዮዋ የፍቅር አቻው ብትሆንም' አፈፃፀሙ ያልታሰበበትና ምንም ዐይነት ማመዛዘን ያልታከለበት ነበር ። ቢሆንም ሚስቲቱ ያሳያት ከነበረው ቸልታና ይፈጸመው ከነበረው ዕብደት በላይ ትወደው ነበር ። አንዲት ሴት ልጅ ወለደችለት ። ልጁ ዐሥራ ሦስት ዓመት እስኪሞላት ድረስ እናቷ በደንብ ካሳደገቻት በኋላ ሁለተኛ ልጅ ሳትወልድለት ሞትች ። ወንድ ልጅ ለመውለድ ቢታደል ኖሮ ዊልያም ሲመኘው ' ሲመኘው ሳያገኘው የቀረው ነገር ትዝ ሲለው ' እንደማቃሰት ብሎ በረጅሙ ተነፈሰ ከገባበት የችግር ማጥ የሚወጣበትን መንገድ አያጣለትም ነበር ። ልጁ አድጎ፡ ለአቅመ አዳም ሲደርስ ይህን ባባቱ ላይ የወደቀውን የኑሮ ጣጣ ለማስወገድ አብሮት ተሰልፎ....

« ጌቶች » አለ አንድ አሽከር ወደ ውስጥ ገብቶ የጌታውን ከንቱ ምኞት በማቋረጥ። « ከእርስዎ ጋር ለመገናኘት የሚፈልግ እንግዳ መጥቷል ። »

« ማነው እሱ ? » አለው ኮስተር ብሎ " አሽከሩ ከፊቱ ያኖረለትን የስም ካርድ
ልብ አላለውም ። ማንም ሰው ቢሆን እንደ ውጭ አገር አምባሳደር ለብሶና ትልቅ ሰው መስሎ ቢመጣም ሥነ ሥርዓት ሳይጠብቅ ሎርድ (የማዕረግ ስም) ዊልያም ቬን ዘንድ ሰተት ብሎ ይገባል ማለት ዘበት ነበር ። አሽከሮቹም ገንዘባቸው እንዲከፈላቸው ለመጠየቅ ከሚመላለሱት ብዙ ባለዕዳዎች ጋር የረጅም ጊዜ ልምድ ስለ ነበራቸው ትእዛዙን ተጠንቅቀው ነበር የሚያከብሩለት

« ካርዱ እኮ እሱውና ጌታዬ » ዌስት ሊን ያለው ሚስተር ካርላይል ነው "

« ሚስተር ካርላይል ? » እለ ዊልያኛ ቬን እግሩን ሲቆረጥመው እያቃሰት
« ምን ይፈልጋል ? እስኪ አስገባው ። » አሽከሩ እንደታዘዘው እንግዳውን አስገባው ሚስተር ካርላይል ግርማ ሞገስ ያለው የኻያ ሰባት ዓመት ሰው ነው። አጠር ካለ ሰው ጋር ሲነጋገር ራሱን ወደ ሰውየው ዘንበል የማድረግ ልማድ አለው ። የእጅ መንሣት ልማድ ቢባልም ስሕተት አይሆንም ። አባቱም እንደዚሁ ያደርግ ነበር ።ሰዎች ስለዚህ ነገር ሲያነሡበት እንደ መሣቅ ይልና ለራሱ ምንም እንደማይታወቀው ይናገር ነበር ። ሚስተር ካርላይል ፡ ፊቱ ገርጣ ብሎ ጥርት ያለ ጸጉሩ ጥቁር ሽፋሺፍቱ ግጥም ያለ ባጠቃላይ የዐይነ ግቡነቱንና ያስደሳችነቱን ያህል መልከ መልካም ነው ባይባልም፡ ወንዶችም ሴቶችም ሊያዩት የሚፈልጉት ፡ የሚያስከብርና የቅንነት መለኪያ የመሰለ ገጽታ አለው። የካርላይል አባት፡ ትልቁ ካርላይል ጠበቃ ነበርና ልጁም ባባቱ እግር ተተክቶ ጠበቃ ሆነ ። ነገር ግን እንደገጠር ሰው
👍382