አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ገረገራ


#ክፍል_ስድስት


#በታደለ_አያሌው

...ወደ መኪናዬ ሽምጥ እየሮጥሁ ሳለ ነበር፣ የንስሐ አባቴን እንኳን
እንዳልተሰናበትኋቸዉ ያወቅሁት፡፡ እንደ ልማዴ በጥድፊያ ወደ ሲራክ፯ አሽከረከርኩ። መቼም ከባልቻ የተደበቀ ነገር የለም፡፡ እሱን አግኝቼ እስከማማክረዉ ድረስ ትንፋሼን እንኳን ወደ ዉስጥ መሳብ አልሆነልኝም፡፡ ቸኩያለሁ። አይደርሱት የለም ደረስሁና ቢሮዉን በርግጄ ስገባ፣ ባልቻ በወንበሩ ላይ ለጠጥ ብሎ እንቅልፍ አሸልቦት አገኘሁት።
በተለይም የሲራክ ፯ ዋና ኃላፊ ከሆነ በኋላ የግል መኖሪያ ቤቱን አይቶት የሚያዉቅ አይመስለኝም። ዉሎዉም አዳሩም እዚሁ ሆኗል። እዚሁ ምግብ ያስመጣል፣ እዚሁ ወንበሩ ላይ ትንሽ ዕረፍት ያደርጋል። ከስንት አንድ ወደ ዉጪ ቢወጣ እንኳን ምክንያቱ ለዚሁ ለሲራክ ጉዳይ ብቻ
ነዉ፡፡

“ባልቻ!” ብዬ ስጮህበት፣ ብርግግ ብሎ ብድግ አለልኝ።
“ዉብርስት?” አለ ተጨናብሶ፣ እጁን ለሰላምታ እየዘረጋልኝ፡፡
“እሰይ! ‹ዉብርስት?” አልሁት፣ ልጃለሜ የሚለዉ ቁልምጫዉ
መቅረቱ ከንክኖኝ፡፡ እኔ ደግሞ ከእሱ ብቻ ሳይሆን ከማንም ቁልምጫ የለመድሁ ሰዉ ነኝ። ቁልምጫዉን ሳይቀር እንደገና በሚያቆላምጥ ቤተሰብ መሀል ነዉ ያደግሁት። ያዉም ዉብዬዋ፣ ‹ዉቤዋ፣ የኔ ዉብ፣ ዓለሜዋ፣ ‹ልጃለሜ› እየተባልሁ። ባልቻ እንዲሁ እንደ ወረደ በስሜ ጠርቶኝ ካለማወቁ የተነሳ፣ ስሜን ሁሉ የሚያዉቀዉ አይመስለኝም
ነበር። ትዝ ሲለኝ እኔ ራሴ ባልቻ ብዬ ነዉ የጠራሁት ለካ። «አባታለም» የሚለዉ ቁልምጫዬስ? የት ተዉሁት?

“ይኸዉ መጣሽ። በስንት ጊዜሽ? ስደዉል ሳታነሺ፣ ሳስጠራሽ ሳትመጪ፣ ስፈልግሽ ሳትገኘ፤ ዛሬ ምን አመጣሽ በይ?”

“እሸቴ ጠፍቷል”

“ጠፋ? ማን እፍ ብሎት ይሆን በናትሽ? ቀድሞስ በርቶ ኖሯል እንዴi” ሲል አላገጠብኝ፡፡

“ማላገጥህ ነዉ?”

“ራስሽ ከመሀል ጀመርሽዋ! እኔና አንቺ እኮ ገና እንደገና መተዋወቅ
አለብን። ቆይ የት አዉቅሻለሁ? አንቺ ታዉቂኛለሽ?”

“በማርያም አባታለም? ፈርቻለሁ። እሽቴ በመንግሥት ደኅንነቶች እጅ
ወድቆ እንዳይሆን ልቤ ሰግቷል”

“እና ምናገባኝ እኔን?”

“ኧረ ባዛኝቱ? እንዴት ነዉ የማያገባህ፤ እሽቴ እኮ ነዉ!”

"የሆነስ እንደሆነ!”

“አዉቃለሁ አሳዝኜሃለሁ። ለዚያም እንዴ ት ይቅርታ መጠየቅ እንዳለብኝ አላዉቅም። ቢሆንም ግን በዚህ መሀል እሸቴ በጨካኞች እጅ ወድቆ
ከሆነ አያሳዝንህም?”

“ያሳዝነኛል”

“እኮ አንድ ነገር አድርጋ”

“ምን ላድርግ?”

“የማታስፈልገዉ?”

“እሺ። አስፈልጌ ሳገኘዉስ?”

“ያንተን አላዉቅም። እኔ ግን ተንበርክኬ ይቅርታ እለምነዋለሁ”

“ለምን?”

“ስለሚገባዉ”

“እሺ። መጀመሪያ ግን እንስማማ”

“ንገረኝ በምን?”

“ተንበርክከሽ የምትጠብቀዉ ከሆነና፣ ተሳክቶልኝ ካገኘሁት ደግሞ ወደ ሆስፒታል ለመሄድ ቃል ከገባሽልኝ.…”

“ይኼዉ!” ብዬ ጉልበቴ ግዉ እስከሚል ድረስ ወድቄ ተንበረከክሁ፡፡
“ብቻ አንተ እሺ በለኝ። እገባለሁ። እሄዳለሁ፤ አሁኑኑ ፈልግልኝ!”

“ዉዉዉ-ዉቤ?” የሚል ድምፅ ከኋላዬ ሰማሁ። ማን በተብታባ ድምፁ እንደ ጠራኝ ለማጣራት ዞሬ ማየት ያስፈልገኝ ኖሯል? ኧረ በጭራሽ በጠረኑ ብቻ አዉቀዋለሁ፡፡ እሸቴ ነዉ፡፡ ወይ ባልቻ! ምን ዓይነት ልብ
ነዉ የታደለዉ ግን? መቼም ጨክኖ ማኩረፉን አያውቅበት! ሆነ ብሎ ኖሯል ለካ እሸቴን ከሁላችንም እይታ እንዲጠፋ ያደረገዉ፡፡ እኔ እንደሆነ
እንዳልሞተ ሰዉ የማራክስዉ ነገር የለኝም፡፡ ጊዜ እንኳን ዉድ
የሚሆንብኝ ካለፈ በኋላ ዞሬ ሳየዉ ብቻ ነዉ። እቃም ቢሆን ከእጅ አምልጦ ካልተሰበረ ወይ ደግሞ ካልተሰረቀ በቀር ዉድነቱ አይታወቀኝም።እሸቴንም ባላጣዉ ኖሮ አልፈልገዉም ነበር። ለዚህ ይመስለኛል ባልቻም
እሸቴን ከዓይኔ እንዲጠፋ ያደረገብኝ። የእሽቴን ዉድነት እንዳምን፣ ከዓይኔ ሠወረብኝ፡፡ እንኳንም ሠወረብኝ፣ እንኳንም ናፈቅሁት፣ እንኳንም
አገኘሁት። ተሳክቶለታል።

ባልቻን በስስትም በኩራትም እያየሁት ሳለ፣ እሸቴ ከፊት ለፊቴ መጥቶ እንደኔዉ በጉልበቱ ወደቀ። ጥዉልግ ብሏል። ከንፈሩ ሳይቀር ኩችር ብሎ ደርቆ ታየኝ፡፡

“እሽቴ?”

“ጨጨጨ ጨከንሽብኝ እኮ
ዉቤ”

“ኹለተኛ አላደርገዉም”

“አአአ አአ አለሽልኝ ግን?”

“አለሁልህ። አለህልኝ?”

የባልቻን መኖር ሁሉ ረስተን፣ አንገት ለአንገት ተቆላልፈን ቆየን፡፡
እንደዚሁ እንዳለን፣ ልክ እሸቴን እንዳገኘልኝ ወደ ሆስፒታል ለመሄድ የገባሁት ቃል ትዝ አለኝ። እስከሚነጋ ቸኮልሁ።

ከአምስት ወር በላይ በሆዴ ፅንስ ይዤ፣ ያዉም እኔ ራሴ የሕክምና
ባለሙያ ሆኜ ፤ እስከ አሁን ግን የሕክምና ክትትል አለመጀመሬ ለግድ የለሽነቱ ወደር የማይገኝልኝ ሴት መሆኔን መስክሮብኛል፡፡ ይኼንን ማንም ሳይነግረኝ አዉቄዋለሁ። ሲሆን ሲሆን እርግዝና ከመፈጠሩ ከዓመት ወይ
ከወራት ቀደም ሲል ጀምሬ ዝግጅት ማድረግ ነበረብኝ፡፡ እንደኔ እንኳን እርግዝናዉ በድንገት ለተፈጠረበትም ቢሆን፣ ከመጀመሪያዉ ጀምሮ
ሙሉ ምርመራ እና ክትትል ማድረግ የግድ ነዉ። እኔ ግን ቢያንስ ቅሪት መሆኔን ያወቅሁት ቶሎ ቢሆንም፣ ይኼዉ 22ኛ ሳምንቴን ጭልጥ አድርጌ ነዉ ገና ነገርዮዉን እንኳን በበጎነቱ የተቀበልሁት።

ዛሬ ነዉ ወደ ሆስፒታል ለመምጣት የወሰንሁት። ዛሬ ገና።

ዛሬ ግን ቆርጬ መጥቻለሁ።

በእናቶች እና ሕጻናት ሕክምና ዝነኛ ወደ ሆነዉ ሐሚያሉ ሆስፒታል ገብቼ ካርድ አወጣሁና ወደ ተጠቆምሁት የዶክተር ክፍል አመራሁ። ብዙም ሳልቆይ ወረፋዬ ደረሰኝና፣ መለስ ያለዉን በር ገፍቼ ወደ ዉስጥ ገባሁ። ሆስፒታሉን በበጎ ስሙ መረጥሁት እንጂ፣ የተለየ የሐኪም ምርጫ አላደረግሁም ነበር። ሆኖም ከዉስጥ የጠበቀችኝን ሐኪም ካየሁ በኋላ፤ ሕይወት የአጋጣሚዎች ጋን መሆኗን አመንሁ።

ሐኪሟ ስንቱን አብራኝ ያሳለፈች፣ የቀድሞ ጓደኛዬ ሆና እርፍ!

“ሸዊት!” አልኋት፣ ለረዥም ደቂቃ እጄን አፌ ላይ ጭኜ ስደነቅ ከቆየሁ በኋላ።

"የፈጣሪ ያለህ! ዉብዬ ?” አለች እሷም፣ አሁንም አሁንም ዓይኖቿን
ጨፍና እየገለጠቻቸዉ። ከመልኬ እኩል በሆዴ ያለዉን አስተዉላለች፡፡ ከነጭራሹ የምንገናኝ፣ ያዉም እንዲህ ሆኜ፣ አልጠበቀችኝም ነበር። ለነገሩማ እኔስ እንዴት ብዬ እጠብቃለሁ? በጎንደር ዩኒቨርስቲ የሕክምና
ዶክትሬት ዲግሪያችንን አብረን በተማርንበት ወቅት የነበረንን ጓደኝነት አይቶ ትንሽ ትልቁ እንደዚያ ከዓይን ያዉጣችሁ እንዳላለን ሁሉ፣ እንደዚህ በአንድ ከተማ መኖራችንን እንኳን እስካለመተዋወቅ ድረስ
መራራቃችን ዋዛ ነዉ፡፡ ምን ሆነን ነዉ ግን? ምንም፡፡ ለነገሩ ዩኒቨርስቲ ካስተዋወቀኝ ወዳጆቼ ማንን አግኝቼ አዉቃለሁ? ከስንት አንድ በአጋጣሚ ካልሆነ በቀር፣ አብዛኞቹ የት እንዳሉ እንኳን አላዉቅም፡፡

“ዋዉ!” አለችኝ፣ እንደ ታቦት እየዞረችኝ፡፡

“እሩ እስኪ ሰላም በዪኝ መጀመሪያ”

“እንኳን ለዚህ አበቃሽ ዉብዬ” ብላ መጥታ አንገቴ ሥር ሰረገች፡፡
እንደገና ሆድ ሆዴን ትኩር ብላ አየችኝና፣ ጭምጭም አድርጋ ሳመችኝ፡፡የምር ደስ ብሏታል። እንባዋ ሳይቀር ጠይም ጉንጮቿን እያራሰ በብርቅዬ አንገቷ በኩል ፈሰሰ።

ሀገር ዉስጥ ነዉ የምትኖሪዉ? ጭራሽ እዚሁ አዲስ አበባ?” አልኋት፣

ደስታዋ እንዲጋባብኝ ልቤን እየደቃሁት።

“አይ፤ ቅርብ ጊዜ ነዉ የመጣሁት። ጀርመን ነበርሁ፣ ትምህርት ላይ”

“ተዪ እንጂ? ጀርመን፤ ምን ስፔሻላይዝ አደረግሽ ታዲያ?”

“ይኸዉ እያየሽኝ? ለእር ግዝና ክትትል አይደል እንዴ እኔ ጋ
የመጣሽዉ?”

“አይ አጅሪት! እንዲያ ነዉ እንጂ የኔ እህት! ደግሞ ጥሩ ምርጫ ነዉ”

“አንቺስ ምን አጠናሽ?”
👍481
#ገረገራ


#ክፍል_ሰባት


#በታደለ_አያሌው


...“በይ እሺ፡፡ በይ ደርሰሽ ነይ”

የምርመራ ማዘዣዎችን ተቀብያት ስወጣ፣ ለአልትራሳውንድ ምርመራዉ ጨመር ያለ ዉሃ መጠጣቱ እንደሚጠቅመኝ ስለማዉቅ፣ ወደ ሆስፒታል
ስመጣ ጀምሬዉ ያጋመስሁትን ኹለት ሊትር ዉሃ እየተጎነጨሁለት
ወደ ቤተ ሙከራዉ ተመለስሁ። እንደ ፈራሁት ስዓቱ ሰዉ የማይበዛበት ሰዓት ሆኖ ይመስለኛል፣ የሚያማርር ወረፋ አልገጠመኝም። በመሆኑም፣
ደሜን ጨምሮ የሚያስፈልጉ ዋና ዋና ናሙናዎችን ሰጥቼ በግማሽ ሰዓት ዉስጥ ዉጤት ደረስልኝ። ዉጤቴን ይዤ እንደገና ወደ ቀድሞዋ የልቤ ሰዉ፣ የአሁኗ ደግሞ ሐኪሜ ቢሮ ወጥሮ የያዘኝን ሽንቴን እንደ
ቆነጠጥሁ ተመለስሁ። ገለጥ አድርጌ እንኳን ወረቀቱን የማየት ሐሳብ ብልጭ አላለልኝም።

ሆስፒታላችሁ ብርሃናዊ አይደል እንዴ አንቺ፣ ፍጥነቱ!”

“ዉጤቱ ደረሰልን?”

“ይኼዉ” አልኋት፣ ጠረጴዛዋ ላይ እንደ ከባድ እቃ በኹለት እጄ
እያስቀመጥሁላት።

“ደፈንሽዉ ኣ?” አለችኝ፣ ትኩረቷን አድርጋበት ከነበረዉ ኮምፒዉተሯ
ወደ ዉጤት ወረቀቴ እያመጣችዉ።

“እረ እኔ ምኑንም አላየሁት”

ለመጨረሻ ጊዜ ሆዴን ሰረቅ አድርጋ አየችዉና ወረቀቱን ገለጠችዉ፡፡ድንገት ፊቷ እብጥ አለብኝ። ዉጤቱ ላይ ደስ የማይል ነገር እንዳገኘች ጠረጠርሁ። ቢሆንም ግን ራሷ እስከምትነግረኝ ድረስ ብጠብቅ ይሻላል ብዬ ያላየኋት መሰልሁ። እሷም ያልደነገጠች ለመምሰል የሆነ ያልሆነዉን ቀበጣጠረች፡፡ እንደገና በሚያደናግር ትኩረት አስተዋለችዉና ወደ አልትራሳዉንድ ክፍሉ እንድከተላት ነገረችኝ፡፡ ስንገባ ያገኘነዉን ራዲዮሎጂስት እንኳን በቅጡ ሰላም አላለችዉም። ቶሎ ብዬ ሆዴን ገልጬ አልጋዉ ላይ እንድንጋለል አዘዘችኝ፡፡ ለወትሮዉ በልዩነት የተማረዉ ባለሙያ ያለበትን አልትራሳዉንድ ይቅርና ተራ ነገርም ቢሆን
ሐኪም ያለሙያዉ ገብቶ አይፈተፍትም፡፡ እሷ ግን እጅግ ከመቻኮሏ የተነሳ እሱን ጨምራ በጥድፊያ ከፍ ዝቅ አደረገችዉ። የእዉር ድንብሯ ወጥቷል። ሌላዉ ቀርቶ ገና በመመርመሪያዉ (ultrasound probe)
እንኳን ሳይዳብሰኝ ነበር ዓይኖቿን ወደ ምስል መከሰቻዉ የተከለቻቸዉ።

ችኮላዋን በበጎ የተረዳት የክፍሉ ባለሙያ፣ ሳይቀየማት የሚደረገዉን ሁሉ አድርጎ የፅንሱን ጥላማ ገጽ ፊት ለፊታችን ባለዉ ዝርግ መከሰቻ አመጣልን። ይኼ ሁሉ ሲሆን የእሷን አድራጎት ብቻ ነበር የምከታተለዉ።
እስኪበቃት ድረስ እያጎላች እና እያሳነሰች ስትመለከተዉ ቆየች። እኔንም እንዳየዉ ጋበዘችኝ፡፡

አየሁት።

ችግር አለ። ከባድ ችግር!
“አይ፤ ያን ያህል እንኳን አንገት የሚያስደፋ አይደለም” አለችኝ፣
ከአልጋዉ ላይ እንድነሳ እየደገፈችኝ። ድንገት ሰዉነቴ እየከዳኝ፣ የበለጠ ድጋፍ እየፈለግሁ መጣሁ። ደግነቷ፣ እጇን አልከለከለችኝም።
“በእርግጥ የማልደብቅሽ ነገር ቢኖር፤ እኔም ልክ የላብራቶሪ ዉጤትሽን ሳየዉ ደንግጫለሁ። በዚያም ላይ ከእኔ ባልተናነስ ስለ ሁኔታዉ ልታወቂ እንደምትችይ ስለማዉቅ በማይመስልሽ ቃል አንቺን አልሸነግልሽም።እንኳንስ የሕክምና ሥነ ምግባር ለማገባት ላንቺ ለጓደኛዬ ይቅርና፣
ለታካሚዎቼ ሁሉ የሆነዉን በግልጽነት የማስረዳት ኃላፊነት አለብኝ። የምልሽ ይገባሻል መቼስ”

ጓደኛዬም ሐኪሜም በሆነችዋ ሸዊት ፊት፣ ግብኔ ብቻ ያልቀረ ለመምሰል ተጣጣርሁ። ጠንካራ ለመምሰል እየሞከርሁ የዉጤት ወረቀቱን እንድትመልስልኝ እና የሆነዉን ሁሉ በራሴ ዓይን እንዳየዉ እጄን ዘረጋሁላት። ሐኪሜ ለምን እንደዚያ እንደሆነች ገባኝ፡፡ ምክንያቱም የፎሊክ አሲድ መጠኑ ከሚጠበቀዉ መጠን እጅግ የወረደ ኖሯል።
እንደዚህ ሲሆን ደግሞ በፅንሱ ላይ የነርቭ ክፍተት የማስከተል ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑን እንኳንስ ሥራዬ ብላ ያጠናችዉ እሷ ትቅርና፣ እኔ ዉብርስትም አዉቀዋለሁ። የፎሊክ አሲድ እጥረት ከተከሰተ፣ የነርቭ
ዘንግ ከአፈጣጠሩ ጀምሮ በወቅቱ እንዳይዘጋ ያደርገዋል። በመሆኑም፣ የፎሊክ አሲድ እጥረት እንዳያጋጥም፣ እርግዝና ከመፈጠሩ አስቀድሞ ወይ ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ ከተመረጡ ምግቦች፣ ወይ ደግሞ ሰዉ ሰራሽ እንክብሎችን መዉሰድ ያስፈልጋል። ያለበለዚያ ይኼዉ በእኔ የምርመራ ዉጤት ላይ እንደ ታየዉ፣ ልክ ያልሆነ ነገር በፅንሱ ላይ ይፈጠራል።

ምን ዋጋ አለኝ? አርፍጃለኋ!

“በእርግጥ ሌሎችም መነሻዎች ስላሉት፣ የፎሊክ አሲድ እጥረቱ ነዉ ይኼን ያመጣዉ ብሎ አፍን ሞልቶ መደምደም አይቻልም። ሆኖም እኔን ደጋግመዉ ከገጠሙኝ ዐሥር የፎሊክ አሲድ እጥረት ያየሁባቸዉ ነፍሰ
ጡሮች፣ ቢያንስ የስድስቱ ወደ ነርቭ ክፍተት ያደርሳል። የነርቭ ክፍተት ስልሽ የተለመዱትን፣ በተለይም ስፓይናቢፊዳ(አከርካሪው ላይ ያለው ነርቭ ወደ ውጭ መውጣት) ማለቴ ነዉ። ይኼ ደግሞ ያልሰለጠነ ሀገር በሽታ እየሆነ መጥቷል። ምክንያቱም የበለጸጉት ሀገራት ምግባቸዉን በጠቅላላ በፎሊክ እንዲበለጽግ ስላደረጉት፣ ብዙም አያጋጥማቸዉም። የእኛን ሀገር ግን አታንሺዉ”

“በናትሽ መፍትሔ አለዉ በዪኝ”

“ደግሞ በኛ ዘመን መፍትሔ የሌለዉ ነገር ምናለና ዉቤ”

“እኮ ምን?”

“በተአምር ታምኛለሽ?”

የጭንቅ ዝልዝል የተንጠለጠለበትን ፊቴን መለስሁላት።

“ተአምር?”

“አሁን አንዴ ፅንሱ ቅርጽ ይዟል። ተአምር ካልተፈጠረ በቀር፣ ሕጻኗ... በነገራችን ላይ ጾታዋን አልነገርሁሽም አይደል ቅድም? ሴት ናት። እና፤ከላብራቶሪም ሆነ ከአልትራሳዉንድ ባገኘነዉ ዉጤት መሠረት፣ በወሊድ ጊዜ ሊገጥሙን የሚችሉ የነርቭ ዘንግ ክፍተቶች ይኖራሉ፡፡ በተለይ
ስፓ ይናባይፊዳ የሚባለዉ ለብቻዉ ወይም ደግሞ ሀይድሮሴፋለስ(ጭንቅላት ውስጥ ውሃ መቋጠር) ጭምር
ሊሆኑ ይችላሉ። ግን እንዳልሁሽ ነዉ፤ ተወልዳ በዓይናችን እስከምናያት ድረስ መቶ በመቶ እርግጠኛ መሆን አንችልም”

“እንዲያዉ አይበልብኝና ይኼ ነገር እዉነት የሚሆን ከሆነ ምንድነዉ
የሚሆነዉ ግን?”

“እንደምታዉቂዉ፤ ለሐቅ የቀረበ ግምት እንጂ ፍጹም የሚባል ያለቀ
የደቀቀ ሐቅ የለም በሳይንስ፡፡ አንቺም ሐሳቤን የምትጋሪዉ ይመስለኛል።ሆኖም አብዛኛዎቹ የዚህ ክፍተት ተጠቂዎች የታወቁ ጉዳቶች ይገጥሟቸዋል። ለምሳሌ ሽንትና ሰገራ ያለመቆጣጠር፣ የእግርና የእጅ ሽባነት፣ የዓይን መንሸዋረር ወይ መጥፋት እና ሌሎችም ጭምር።እንዲያዉም አልፎ አልፎ የከፋዉ ሲመጣ፣ እነዚህ ያልሁሽ ሁሉም አንድ
ላይ የሚከሰቱበት አጋጣሚ ሁሉ አለ። ታዲያ እንዳልሁሽ፣ በኛ ዘመን
መፍትሔ የሌለዉ ችግር የለም። ቢፈጠርም እንኳን ሕክምና አለዉ”

“አለዉ?” አልሁኝ፣ ለእፎይታ ራሴን እያመቻቸሁ። አንደኛዬን ግልብ
ሆኜ የለ አሁንማ? አሁን መሳቅ አሁን ማልቀስ፣ አሁን ማመን አሁን
መካድ። ስስ ሆኛለሁ።

“አዎ። ቀዶ ጥገናም እኮ አለዉ። አንቺን መምከር ሳይገባኝም፣ ከዚህ በላይ መጨነቅ ግን አይኖርብሽም። ጭንቀት ራሱ ሌላ ጣጣ ስላለዉ፣ እዉነታዉን የምነግርሽ እንድትጨነቂበት ሳይሆን ለግልጽነት ብዬ ነዉ።
በዚያ ላይ አንቺ ጠንካራ ሰዉ መሆንሽን ለእኔ ለጓደኛሽ እንዲነግሩኝ አልጠብቅም። አዉቅሻለኋ!”

ቀዝቃዛ ትንፋሽ ተነፈስሁ። ገና ዛሬ፣ አሁን ገና የእግዚአብሔርን ይቅር ባይነት ለመጀመሪያ ጊዜ ተጠራጠርሁት። ወይ ስለ ንስሐ ምንም አላዉቅም፣ ወይ ደግሞ እግዚአብሔር ቂመኛ ነዉ
ስል አሰብሁ። እኔ የተማርሁት ሰዉ ፍጹም ተጸጽቶ ንስሐ ከገባ
ኃጢአቱ ሁሉ ፍጹም ይሰረይለታል የሚለዉን ነበር። ከእግዚአብሔር
ጋር የሚያደረገዉም እርቅ ፍጹም ይሆንለታል ሲባል አዉቃለሁ። ታዲያ እኔ ፍጹም የሆነ ጸጸት ተጸጽቼ ንስሐ አልገባሁም? ቀኖናዬንስ በሚገባ ወይስ እግዚአብሔር ፍጹም አምላክ መሆኑን አላመንሁም?
👍391
#ገረገራ


#ክፍል_ስምንት


#በታደለ_አያሌው

...ክፉ ያሳሰበኝን መንፈስ እከድከ ሰይጣን እያልሁ በልቤ ደጋግሜ ጸልዬ አስታገስሁት። ቀጥዬም ሰላም ለኪን ደገምሁበት እና ከሆስፒታል ወጣሁ። እንደ ወጣሁ የሆነብኝን ሁሉ የምነግረዉ ስፈልግ ከሁሉ ቀድሞ
ሐሳቤ ላይ የገባልኝ ሰዉ ባልቻ ነበር፡ እመዋን አቆይቼ ማለቴ ነዉ።ለእሷስ ያለፈዉ ይበቃታል፡ የሆስፒታሉንም ነግሬ ዳግመኛ ቅስሟን ልሰብረዉ አልፈልግም።

በእርግጥ እህትና ወንድሞቼም ነበሩልኝ። ጓደኞቼ ሁሉ አሉ። እሽቴም ቢሆን እኮ አለ የኖረዉ ቢኖርም፣ በተለይ አሁን ስላንጨዋለለኝ ፈታኝ ጉዳይ ለማማከር ግን፣ ከምድር ማንም እንደ ባልቻ የሚሆንልኝ ሰዉ
አይታየኝም: እሱ ብቻ ነዉ የጭንቄን መጠን ልክ እንደ ነገርሁት፣ እንዲያዉም ከነገርሁት አልፎ የሚገነዘብልኝ። ለማባበል
አይሸነግለኝም። ማባበል ከፈለገም እንደ'ሱ የሚያዉቅበት የለም። ጆሮዉ የተለየ ነዉ። ጭጭ ብሎ ሲያዳምጥ ብቻ ከጭንቅ ይፈዉሳል። እኔ ራሴ
እንኳን ስለ ራሴ የማላዉቀዉን ከእመዋ ቀጥሎ የሚያውቅልኝ ሌላ ሰዉ አላዉቅም: ባልቻ ብቻ:: እንዲያ ቢሆንም ግን፣ እሸቴም መስማት ስላለበት ኹለቱንም ወደማላጣበት ወደ ሲራክ-፯ ማዕከል ሄድሁ።

“አባትዮ” አልሁት፣ ወደ ትልቁ የማኅበሩ ሕንጻ እየተቃረብሁ ሳለ ወደ ባልቻ ስልክ ደዉዬለት።

“አቤት ልጅየዋ”

“ለአንድ አፍታ ፈልጌህ ነበር”

“መቼ”

“አሁን”

“ዉይ፣ አሁን እንኳ አንዲት የጀመርኋት ሥራ አለችብኝ: ባይሆን ይቺን እንደ ጨረስሁ ልደዉልልሽ?”

“በማርያም! አሁኑኑ ነዉ የምፈልግህ፤ ይልቅ ቶሎ ናና ጉዴን ስማልኝ'

“እህ፤ እየነገርሁሽ?”

“ስሞትልህ! ከእሸቴ ጋር እዚሁ አንደኛ ፎቅ ባለዉ ምግብ ቤት
ብትመጡልኝ፣ የምጋብዛችሁ አታዉቁትም: አንተስ ምናለ ለአንዳንዴስ እንኳን ንፋስ ቢያገኝህ? ሁልጊዜ እዚያ ዉስጥ ተቀብረህ” አልሁት፣ ለግብዣዬ ያለዉን ከበሬታ ዘንግቶ ላለመምጣት ሲያቅማማ በዚያም ላይ ሰዓቱ የምሳ ስለሆነ ሦስታችን አብረን የምንበላበት የመጀመሪያ አጋጣሚ ይሆንልናል። እንዳሰብሁት፣ ብዙም ሳያስጠብቁኝ ከእሸቴ ጋር ፊት እና
ኋላ ሆነዉ መጡልኝ፡

“አንቺ፤ ብለሽ ብለሽ ደግሞ እንዴት እንዴት ነዉ ያናገርሽኝ? እንደ ልጅ ና ከረሜላ ልግዛልህ ማለት እኮ ነዉ የቀረሽ አሁንማ አሁንማ” አለኝ በጨዋታ፣ ወንበር ስቦ ከአጠገቤ እየተቀመጠ፡ መልስ ከለከልሁት

“አንቺ? ምንድነዉ ደግሞ ለንቦጭሽ የታላቁን ንጉሥ አወዳደቅ ወድቋልሳ: ገና ለገና እርምሽን ልትጋብዥን ብትይ፣ ከአሁኑ ማኩረፍሽ ነዉ? አየህልኝ እሽቴ? ገና ከአሁኑ እንዲህ ከሆነች፣ ሂሳቡን ስትከፍልማ
እንደ ጨዉ ሟሙታ ወደ መሬት መስረጓ ነዉ በለኛ”

ወድጄ አይደለም ዝም ያልኋቸዉ ሆስፒታል የጀመሩኝ ክፉ ክፉ የሚባሉ ሐሳቦች ሁሉ አሁንም አሁንም ወደ ልቡናዬ እየመጡ ግብግብ ገጥመዉኛል፡ እንደ ምንም ጥርሴን ለመፈልቀቅ ሞከርሁ። የዉጤቱን ወሬ ከምሳ በኋላ መንገሩን ስለመረጥሁ፣ በግድ ፈገግ ለማለት እየታገልሁ
ነዉ፡ ብቻ የሆነ ያልሆነዉን እየቀላቀልሁ የጨዋታ ወሬ ለማምጣት ተዉሸለሸልሁ

“ምንድነዉ ልጄ?” አለ ባልቻ አዉቆብኝ ያልፈሰሰ እንባዬን እያበሰልኝ “ አሃ፤ ዛሬ ከነጋ አላየሁሽም ለካ? የት ዋልሽ?”

አስተናጋጁ እየተሸቆጠቆጠ መጥቶ የምንፈልገዉን ሊታዘዘን አጎበደደ፡ እሰይ! ገላገለኝ። በባዶ ሆዳቸዉ ሐቲታቸዉን ከምበላዉ፣
ምሳችንን በሰላም ብንበላ ለእነሱም ይሻላቸዋል። የቤቱን
የአገልግል ምግብ ከተጨማሪ ሱፍ ፍትፍት ጋር እንዲያመጣልን አዘዝን ሱፍ ፍትፍት የባልቻ የምንጊዜም ምርጫ መሆኑን
ከእሱ ጋር ለአንዴም
ቢሆን ማዕድ የተጋሩ ሁሉ ያዉቁለታል። የሚበላም የሚጣጠም ሲጠየቅ
ቀድሞ የሚመጣለት ነገር ሱፍ ነዉ። በሀገር ዉስጥ ምግብ ቤቶች ብቻም ሳይሆን፣ አንዴ ሩስያ አብረን የሄድን ጊዜ ሁሉ ቀዝቀዝ ያለ ሱፍ ፍትፍት ይኖራችኋል? ብሎ ሩስያዊቷን አስተናጋጅ ሲጠይቃት
ሰምቼዉ፣ የሳቅሁትን ሳቅ ሞቼም መርሳቴን እንጃልኝ! እስከ አሁን ትዝ ባለኝ ቁጥር ስቄ አይወጣልኝም: ሱፍ አዝዞ የለም ከተባለ፣ ለሆቴሉ የሚኖረዉ ግምት ሁሉ ወርዶ እንዴት እንደሚያደርገዉ አያድርስ ነዉ።
ይኼ ደግሞ ሆቴል ነዉ? ሱፍ ፍትፍት እንኳን የሌለበት ቤት! ብሎ
ሲያጣጥል ብዙ ጊዜ ሰምቼዋለሁ። ለእኔ ግን የሚበላ ይሁን እንጂ ምንም ቢሆን ያን ያህል አላማርጥም: በተለይ አሁን በኃይል ሞርሙሮኛል። ለወትሮዉ እንዲህ ድባቴ ዉስጥ ስሆን እንኳንስ ሊርበኝ ይቅርና የምግብ
ሽታ ሁሉ አይደርስብኝም ነበር አሁን ግን ምራቄ ኩችር ብሎ፣
ትንፋሼም ሳይቀር ሽታዉ እንደ ተለወጠ ለእኔም ታዉቆኛል።

“ችግር አለ እንዴ ዉቤ?” አለ እሸቴ፣ ከበላን በኋላ ከሁላችን በኋላ እጁን ታጥቦ ከመመለሱ፡
“ፊትሽ በፍጹም ልክ አይደለም” አለ፣ ባልቻም ተደርቦ፡
“ሆስፒታል ሄጄ ነበር''
“እ?” አሉ ኹለቱም፣ እኩል። የሆነዉን እና በሐኪሟ የተባልሁትን ሁሉ አንድም ሳላስቀር ነገርኋቸዉ። በየመሀሉ በድንጋጤ ከአሁን አሁን
ራሳቸዉን ይስታሉ ብዬ ስጠባበቅ፣ እነሱ ከመጤፍ ሳይቆጥሩት ቀሩብኝ ጭራሽ ባልቻማ ሊስቅብኝ ምንም አልቀረዉ፡ እሸቴም ቢሆን የምጠብቅበትን ያህል ጸጸት ቀርቶ ሐዘኔታ እንኳን አላሳየኝም፡

“ለዚህ ነዉ እንዴ ፊትሽን እንዲህ የክረምት ሰማይ ያስመሰልሽዉ?
“ከዚህ በላይ ምን አለና አባታለም?”
“ኧረ ዝም በይ! ደም አርግቶ የፈጠረንን አምላክ ለምናመልክ ለኛ፤ ይኼንን ጉዳይ ብለሽ … ምን እና ምኑ ተገናኝቶ፣ ሰዉ ሆነን እንደ
ተፈጠርን ጠፍቶሽ ነዉ? ልጄ ሙች! ካንቺ ይኼን አልጠብቅም”

ድንገት የእጅ ስልኩ ጮኸ፡ ወዲያዉ ፈገግታዉንም ተግሳጹንም አቋርጦ ስልኩን አነሳና፣ ለቅጽበት ያህል ከወዲያ በኩል አዳመጠ። ወዲያዉም
የምግቡን ሂሳብ ለመክፈል ኪሱን መፈታተሽ ሲጀምር አስቸኳይ ሁኔታ እንደ ተፈጠረ ገባኝ። ቀድሜዉ ሦስት ድፍን ድፍን መቶ ብሮች ጠረጴዛዉ ላይ አስቀመጥሁ።

“ምን ተፈጠረ?” አለ እሸቴ፣ እሱም እንደኔ ጥድፊያዉን በጥሞና እየተከታተለዉ ቆይቶ።
“ዕረፍት ያስፈልግሽ ነበር እዴ ዉቤ? አንድ መጥፎ ወሬ ደርሶኛል”

“ምነዉ ምን ተፈጠረ? ከየት ነዉ?”
“መስጊድ ላይ እሳት ተነስቷል ነዉ የሚሉኝ”
“የ..ት?” አለ እሸቴ፣ ልለዉ የነበረዉን ከአፌ ነጥቆኝ።
“ተከተሉኝ” ብሎ ከምግብ ቤቱ የመሮጥ ያህል ተራምዶ ወጣ፡ በእሱ ፍጥነት እግር በእግር ተከትለነዉ አሳንሠሩ ዉስጥ ገባንና ቁልፉን ተጭነን ወደ ላይኛዉ ፎቅ ጋለብን፡ በጠመዝማዛዉ መንገድ ገብተን
የለመድናቸዉን የደኅንነት ኬላዎች ሁሉ አልፈን በዚሁ ሕንጻ ወደ
ተሠወረዉ የሲራክ ፯ ማዕከል ስንደርስ፣ ሁሉም በየጥፍራቸዉ ቆመዉ አገኘናቸዉ እንኳንስ የጭንቅ ወሬ ተሰምቶበት፣ እንዲያዉም የዕረፍት
አልባዎች ቤት ነዉ ማዕከሉ
“እስኪ የታለ?” አለ ባልቻ፣ ከወገብ በላይ በግድግዳዉ ዙሪያ ወደ ተንጣለለዉ ዝርግ መከሰቻ ዓይኑን እያነጣጠረ፡
ደዉሎ የጠራዉ ልጅ የባልቻ ጥያቄ ስለገባዉ፣ የሚነካዉን ነካክቶ በርከት ያሉ ተንቀሳቃሽ ምስሎች በሰፊዉ መከሰቻ ከዳር እስከ ዳር ደረደረልን እስከ ሚናራዉ ድረስ በኃይለኛ እሳት ሲንቀለቀል የሚያሳዩ
የመስጊድ ምስሎች ናቸዉ። ወላፈኑ እዚህ ያለንበት ድረስ በሚለበልብ እሳት ሲነድ ይታያል። ብዙ ሰዎችም እሳቱን ለማጥፋት ዙሪያዉን ሲዋደቁ ይታያሉ እንደ እሳቱ አያያዝ ግን መስጊዱን ማትረፍ የሚቻል አይመስለኝም:: ባይሆን ዙሪያዉን ባልተዛመተ እና በአካባቢዉ ተጨማሪ ዉድመት ባልደረሰ ስል በልቤ ጸለይሁ
👍352👎1
#ገረገራ


#ክፍል_ዘጠኝ


#በታደለ_አያሌው


...ባለ ዲጂኖዉ ትንፋሹ ሳይቀር የሚሰማበት ቅርበት ላይ ከአጠገቤ ደርሷል። ምኔን ቢወጋኝ አንድ ምት እንደሚበቃኝ እያማረጠ ይመስለኛል ትንሽ ፋታ ስጠኝ። ዓይኔን ጨፍኜ ብቻ ስንቱን እንዳሰብሁት በዚች ቅጽበት! ሞት እንዲህ አብሮኝ ኖሯል ለካ። “ቁልቁል ወደ ምድር
ለመዉረድ የፈጀነዉን ያህል፣ የሩብ ሩቡን እንኳን ሽቅብ ወደ ሰማይ ለመዉጣት አንፈጀዉም” ትላለች እመዋ። እዉነቷን አይደል? እንዲያዉ ማርያም ብላዉ የምጡ ጭንቅ ቀለል ያለ ቢሆን እንኳን፣ ለመወለድ ቢያንስ ቢያንስ ለዘጠኝ ወራት በማሕጸን ዉስጥ መክረም የግድ ነዉ።ለመሞት ግን ይኸዉ አንዲት ቅጽበት እና ዲጂኖ ያለዉ ገዳይ በቂ የሚሆኑበት ጊዜ አለ።

ግንባሬን ይለኛል ጸጥ እላለሁ። አበቃልኝ።

እንደ ዛሬ ሞትን ቀርቤ፣ ትንፋሽ ለትንፋሽ ተሻትቼዉ አላዉቅም: በዓይነ ኅሊናዬ የመጡልኝን ሁሉ በልቤ ተሰናብቼ ራሴን ለሞት አደላደልሁ።እመዋ፣ ባልቻ እና እሸቴ ነበሩ ቀድመዉ ትዝ ያሉኝ፡ በእርግጥ በየመሀሉ
የመጡልኝን ሌሎች ማኅበርተኞቼን እና ጓደኞቼን ሁሉ አዳርሻለሁ።በመጨረሻም፣ በሆዴ ወደ ተሸከምሁት ፅንስ እጆቼን ሰድጄ ደባበስሁት፡ እህ? ለካንስ ሐኪሟ ፅንሱ የሴት ነዉ ብላኛለች፡ ሴት ከሆነች ደግሞ እመዋ ስም አዉጥታላታለች: ማን ብላ? ቱናት። ቱናትን በዳሰሳ ተሰናበትኋት፡ ፀእንዲያዉ ነዉ የተሰናበትኂት እንጂ፣ መቼስ እኔ ሞቼ
ቱናት አትተርፍ፡ አብረን ወደ ሞት ተጓዦች ነን

“ዉብርስት?” የሚል ቃል ድንገት አጠገቤ ሰማሁ ገዳዬ አይደል? እንደ ምንም የአንድ ዓይኔን ሽፋሽፍት ፈልቅቄ ስገልጥ፣ ገዳዬ ቆሞበት በነበረ ሥፍራ ቢራራ ቆሞበታል እንደገና ጨፈንሁና ብገልጥም፣ ከቢራራ በቀር ማንም በፊቴ የለም፡፡

“የት ገባ?”

“ማ ?”

“ባለ ዲጂኖዉ?”

ፍርስ ብሎ የንቀት ሳቁን ለቀቀብኝ፡ “ለካ ስ እንዲህ ፈሪ ነሽና” እያለ
እንደ መሽኮርመም እያደረገዉም ጭምር አሁንም አሁንም አሽካካብኝ::እዉነትም ገና ድንጋጤዬ አለቀቀኝም: ድንገት እርም እርም የሚል የብዙ
ሰዉ ሆታ ሰማሁና፣ ዞር ስል ሰዎች ወደ ቤተልሔሙ እና ወደ ግምጃ
ቤቱ ይሯሯጣሉ፡ አንዳንዱ አፈር፣ አንዳንዱ ዉሃ፣ አንዳንዱ ደግሞ
ቅጠል እየያዘ ይራወጣል ያ ይባስ ያ ይቅደም ያን ተወዉ. እዚህ
ጋ አምጣዉ የሚል የተለያየ ሰዉ ድምፅ ተሰማኝ፡

እሳቱ! አሁን ገና ወደ ልቡናዬ ተመለስሁ፡

“እሳቱ! ወይኔ ወይኔ! ቤተልሔሙን ፈጀዉ” ስል ጮኹኩ፣ በሚርገበገብ ድምፅ ብሞትስ ቆይ!? ደግሞ እኮ ለሰማዕትነት ዝግጁ ነኝ እያልሁ ስመጻደቅ ነበር እንደ ደህና ሰዉ በቤተ ክርስቲያን ከመጡብኝ እንኳንስ
ሌላ፣ ሞትንም አልፈራ ባይ ነበርሁ ሐሰት ይኼዋ ልኬን አወቅሁት መስዋእትነቱም ይቅርና፣ ከራሴ ቀድሜ የማተርፈዉ ምንም ነገር
አለመኖሩን ነዉ ያየሁት ቢሆንም ግን ቀደም ብዬ የደወልሁት ደወል
የጠራቸዉ ምዕመናን እንደ ደራሽ ጎርፈዉ፣ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ እሳቱን በአጭር አስቀረተዉታል። ቢራራም አጠገቤ ቆሞ በእኔ የሚስቀዉ፣ የእሳቱን መጥፋት ካረጋገጠ በኋላ እንደሆነ ገባኝ፡
ሰአሊ ለነ!

“ቆይ ግን ገዳዬ የት ተሰለበ? አሁን እኮ እንዲህ ብሎ ቆሞ ነበር''
አልሁት ቢራራን፣ እጄን ጦር እንደሚወረዉር አዳኝ አድርጌ እያሳየሁት እሺ እሳቱስ ከምኔዉ ጠፋ? ይኼ ሁሉ ሲሆን እንዴት እንደሆነ የማስታዉሰዉ ምንም ነገር የለኝም:: የሚደንቀዉ ደግሞ አሁንም ገና ድንጋጤዉ ጨርሶ አልለቀቀኝም: ቆመች ቆመች እንደሚባልላት ጨቅላ
የሚያደርገዉን የጉልበቴን መንቀጥቀጥ ማንም እንዳያይብኝ ተሳቀቅሁ፡ቢራራ ከፊቴ እስከሚሄድልኝ ድረስ በዝምታ ብጠባበቀዉም አልሄድልሽ
አለኝ፡ ባለሁበት ቁጢጥ አልሁና ወደ ልቡናዬ ለመመለስ፣ መድኃኒቴ የሆነችዋን ጸሎቴን በለሆሳስ አደረስሁ: ከቅድሙ አንጻር ልቤም የሚመታበት ፍጥነቱ በረድ ቢልም፣ ጨርሶ ግን ልክ ሊሆንልኝ አልቻለም

"እና ፈርቼ ነዉ?” አልሁት ቢራራን፣ ፈቀቅ ብሎ ወዳለዉ የእንጨት
መቀመጫ እየጎተትሁት።

“እንክት!” አለኝ፣ በእርግጠኝነት

“በእርግጥ ፈተና ባይኖር ሁሉ ተማሪ፣ ጠያቂ ባይኖር ሁሉ አስተማሪ መባሉን አዉቃለሁ: ግን እንደዚያ ነበርሁ ወይ እኔ? ተሞክሬ ባላዉቅ ነዉ
እዉነት? በጅቦች መካከል፣ በጨለማ አካፋይ ሞትን ተፋጥጬዉ አላዉቅም? ሌላዉ ሌላዉ ቢቀር፣ ሲራክን ከተቀላቀልሁ እንኳ ን
ይኼዉ ኹለተኛ ዓመቴን ጨልጫለሁ: እስከ አሁንም ድረስ ሐሞቴን የሚፈትኑ ስትና ስጓት ተልእኮዎች በየዕለቱ ከማዕከሉ እቀበላለሁ:: እንዲያዉ ምን ብረሳ ብረሳ በታላቁ ቤተ መንግሥት የገጠመኝን እረሳዋለሁ? እዉነት አተስ ያን ጀብዱ ሳትሰማ ቀርተህ ነዉ?” አልሁት፣ ቤተ መንግሥቱን መጥቀሴ ክፋት እንደ ሌላዉ በማስተዋል እኔ አሁን ጀብዱ ስለምለዉ ነገሬ ላይሰማ ቢችልም፣ ማዕከላችን ሲራክ ፯ በቤተ መንግሥት ምስጢር እንዳለዉ ያወቅነዉ ግን አብረን ነበር

“ሳትሰማ ቀርተህ ነዉ እዉነት ቢራራ?” አልሁት፣ ባለማመን። ይኼ ታሪክ ከተፈጸመ በኋላ፣ እንደኔ ላሉ የሲራክ ፯ መረጃ ሰብሳቢዎች በነበረዉ ወቅታዊ ስልጠና ጭምር ለምሳሌነት ተጠቅሶ እንደ ነበር
በማስታወስ፡
“በታላቁ ቤተ መ ግሥት?”
“ታዲያስ!”
“እንደምታዉቀዉ፣መአከላችን ሲራክ ዋና ዋና በሚባል
የመንግሥት…ብዬ ጀመርሁለት። እዉነትም አልሰማም ኖሯል
እየተቁነጠነጠ አዳመጠኝ።
እንደምታዉቀዉ፣ ማዕከላች ሲራክ ዋና ዋና በሚባሉ የመንግሥት እና ዓለም አቀፍ ዋና በሚባሉ የመንግሥት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ዉስጥም እጅግ ቁልፍ ሥራ ያላቸዉን ዳሳሾች (Sensors) እና ካሜራዎች በሥዉር አስቀምጧል: አንዳንዶቹ ድምፅ፣ አንዳንዶቹ ምስል፣ አንዳዶቹ ደግሞ እንቅስቃሴ በድብቅ እየዳሰሱ እና እየቀዱ ወደ ማዕከላችን የመረጃ ቋት
በቀጥታ የሚልኩ ናቸዉ:: ስለሆነም እነዚህ መሣሪያዎች በተሸሸጉበት አካባቢ ሁሉ የተፈሳችም ሆነ የተተነፈሰች ነገር ሲራክን አምልጣ ?
አታዉቅም: ምንም እንኳን መተዳደሪያ ሥነ ሥርዓቱ ስለማይፈቅድልኝ በየትኛዉ ቦታ ስንት ዳሳሽ መሣሪያ እንደ ተተከለ የማዉቅበት ደረጃ ላይ ባልሆንም፣ ከዐሥር ሺ ያላነሱ ዘመናዊ ዳሳሾች በተለያዩ ቦታዎች
እንደሚኖሩ እገምታለሁ: ለግምቴ ደግሞ በቂ ምክንያት አለኝ” አልሁት፣ የማዳመጥ ጉጉቱን ቀና ብዬ እያስተዋልሁበት ቋምጧል።

“ሰኞ ይሁን ማክሰኞ ቀኑን ዘነጋሁት እንጂ…”

ሰኞ ይሁን ማክሰኞ ቀኑን ዘነጋሁት እንጂ፣ የዛሬ ሰባት ወር ገደማ
ለአንድ ተልእኮ እንድዘጋጅ በራሱ በቀድሞዉ የሲራክ ፯ ኃላፊ ታዘዝሁ። “ ስለ ምንነቱ በዝርዝር ከመንገሩ በፊት፣ ስለ አደገኛነቱ አጥብቆ ሊያስረዳኝ ከሞከረ፡ እኔም ተልእኮዉ ምን ይሁን የት ይሁን ገና ሳላዉቀዉ፤ ምንም
ሥጋት እንዳይገባዉ በልበ ሙሉነት ገለጽሁለት።

“የለም የለም፣ የገባሽ አልመሰለኝም” አለኝ እንደገና፣ ጉዳዩን ማቃለሌ ገርሞት ባላስተዋልኋቸዉ ነገሮችም ሳይታዘበኝ የቀረ አይመስለኝም።
እንዲሁ ላይ ላዩን ፍርጥም አለብኝ፡ እዉነትም ከእሱ ጋር ቃል እየተመላለስሁ መሆኑን ራሱ ያስተዋልሁት ዘግይቼ ነበር
“ለወትሮዉ ማንኛዉንም ተልእኮ የምቀበለዉም ሆነ ተልዕኮዬን በተመለከተ የምነጋገረዉ ከቅርብ ኃላፊዬ ጋር ብቻ ነዉ። ሲጀመር የቀድሞዉን ዋና “ ኃላፊ ለመጀመሪያ ጊዜ በቅርበት ያየሁት ራሱ፣ በዚሁ ዕለት ባልቻ
👍385🥰1