«ዣን ቫልዣ ናቸው» ተብሎ በጥርጣሬ መያዛቸው ምን ዓይነት አጋጣሚ እንደሆነ አስደነቀው:: ስለወደፊት ሕይወቱ እንደገና አሰበ። ራሱን ያጋልጥ! ግን ስንቱን ሰው ሜዳ ላይ ጥሎ፣ ስንቱን ሰው ወደኋላ ትቶ! ራሱስ ቢሆን
ያን ሁሉ ከበሬታ፣ ሀብት፣ የሰው ፍቅር የምቾት ኑሮና መንደላቀቅን ትቶ እስር ቤት ገብቶ በእግር ብረት ይታሰር! ጨለማ ቤት ይግባ፤ ይልፋ ፤ ይሰቃይ፧ ከቀዝቃዛ ስሚንቶ ላይ ይተኛ:: የእስር ቤት ኑሮ ስቃይ ምን እንደሆነ ለአሥራ ዘጠኝ ዓመት ያየውና ተንገሽግሾ የወጣበት ነው:: የምን ርግማን ነው እባካችሁ! የሕይወት ብያኔም እንደ አዋቂ ተንኮለኛና እንደ
ሰው ልብ ምቀኛ ይሆናል? ሰው እንዲህ ያለ ወጥመድ ውስጥ ገብቶ መውጫ ያጣል? መንግሥተ ሰማይ ገብቶ ሰይጣን መሆን ወይስ ገሃነም ገብቶ መልኣክ መሆን? የፈጣሪ ያለህ፣ የቱ ይመረጣል? ምንስ ይደረጋል?
ስቃዩ እንደገና አዲስ ሆኖ አስጨነቀው፡፡ ሳፋ ላይ እንደተቀመጠ ውሃ በአሳብ ዋለለ፡፡ ተስፋ ሲቆርጡ የሚታየውና በቃላት ለመግለፅ የሚያዳግተው እንዲያው ዝም ብሎ ቅርጽ የሚያወጣው የተምታታ ዓይነት ነገር ከፊቱ ድቅን አለ። ከመዳህ ቆሞ መሄድ እንደጀመረ ሕፃን ተንገዳገደ..
ጉልህ ሆኖ የሚታየው ነገር አልነበረም፤ ሁሉም ደብዛዛ ሆነበት:: ከአንጐሉ የሚወጡ አሳቦች ሁሉ እንደጢስ የተነኑ እንጂ ተሰብስበው ቅርጽ ያላቸው
አልሆኑም:: ቀኝም ነፈሰ ግራ፣ ግልጽ ሆኖ የታየው ነገር ቢኖር የቁም ስቃይ መቀበሉን ነበር፡፡ በሕይወት እያሉ መሞት! እየተነፈሱ መቀበር
እንደገና ከጀመረበት ተመለሰ፡፡ ይህ ያልታደለ ነፍስ ከአሳብ አለንጋ
ግርፊያ መላቀቅ ስላቃተው በአሳብ መዋተቱን ቀጠለ፡፡
ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ሆነ፡፡ አምስት ሰዓት ሙሉ ቂጡ መሬት ሳይነካ
ከወዲህ ወዲያ እያለ ቆየ:: በዘጠኝ ሰዓት ሰውነቱ ዛለ ከወንበሩ ላይ አረፍ አለ፡፡ ወንበር ላይ እንደተቀመጠ ለካስ እንቅልፍ ወስዶት ኖሮ ይቃዥ ጀመር::
እንደማንኛውም ቅዠት በሕልሙ ያየው ቀደም ሲል ሕሊናውን
ስላስጨነቀው ጉዳይ ነበር፡፡ ሕልሙ ምንም እንኳን ቅዠት ቢሆንም በይበልጥ
እንዲያስብና እንዲጨነቅ አደረገው:: ወደ ኣራስ ከመሄዱ በፊት በእጁ ፅፎ ያስቀመጠውን አሳብ ነበር በሕልሙ ያየው:: ምናልባት በወረቀቱ ላይ
ተጽፎ የነበረውን አሳብ ቃል በቃል ገልብጠን ብናስቀምጠው ሳይጠቅመን አይቀርም::
የዚህን ሕልም ፍሬ ሀሳብ ሳናክል ብናልፍ ደግሞ በዚያን እለት ምሽት የሆነውን ታሪክ በቁንጽል ማስቀረት ይሆናል፡፡ ሕልሙ አንዲት የታመመች ሴት ስለገጠማት ውጣ ውረድ የሚያወሳ ነበር:: ታሪኩ እንደሚከተለው ሲሆን በፖስታው ላይ የተጻፈው ቃል «በዚያን እለት ምሽት ያየሁት ሕልም» የሚል ነው::
ከአንድ እርሻ ውስጥ ነበርሁ:: የሚያሳዝነው ከእርሻ ውስጥ ሳር
እንኳን አልበቀለም:: ጊዜው ቀን ይሁን ማታ አይታወቅም::
ከወንድሜ ጋር አብረን እንጓዛለን፡፡ የልጅነት ወንድሜ ነው:: ስለዚህ
ወንድሜ ብዙም የማውቀው ነገር የለም፡፡ ከነአካቴው መልኩ እንኳን
በቅጠ ትዝ አይለኝም፡፡እናወራለን፣ ከእኛ ጋር የሚጓዙ ሌሎች ሰዎች
አየን፡፡ ድሮ ስለምናውቃትና ዘወትር መስኮት ስለምትከፍት ጎረቤታችን ቤት ነው የምናወራው፡፡ እያወራን ሳለ በዚያ በተከፈተ መስኮት በኩል
አድርጎ በሚገባ ነፋስ የተነሳ ብርድ ብርድ አለን፡፡
ከእርሻው ቦታ ዛፍ አልነበረም:: አንድ ሰው በአጠገባችን ሲያልፍ
አየነው:: ራቁቱን ነው ፤ ምንም ነገር አልለበሰም:: ሰውነቱ በጣም
ጠቋቁሮአል። አፈርማ ቀለም ካለው ፈረስ ላይ ተቀምጧል። ሰውዬው መላጣ ሲሆን ከራስ ቅሉ ውስጥ ያሉ የደም ሥሮች በጉልህ ይታያሉ፡፡ እንደ ብረት የከበደ ዱላ ይዟል፡፡ ምንም ሳይናገር በአጠገባችን አለፈ::
«ጭር ባለው በዚያኛው መንገድ እንሂድ» አለኝ ወንድሜ፡፡
እርሱ ያለውን መንገድ ተከትለን ሄድን፡፡ የሚያደናቅፈን እንኳን ዛፍ
ቁጥቋጦ አልነበረም:: ቀይ አፈር ብቻ ነው የሚታየው:: ጥቂት
እንደተራመድን ለምሰጠው አስተያየት መልስ የሚሰጠኝ አጣሁ:: ዞር ብል ወንድሜን ከአጠገቤ ኣጣሁት:: በሩቅ ወደሚታይ መንደር አመራሁ::
እኚያ ካህን የታሠሩበት ከተማ መሰለኝ::
ወደ ከተማው ከሚያስገባው መንገድ ስጠጋ ጭር ማለቱን ተገነዘብኩ::ወደ ሌላ አቅጣጫ አቋርጬ ሄድኩ፡፡ ከሁለት መንገዶች መገናኛ አጠገብ
አንድ ሰው ግድግዳ ተደግፎ ቆሞአል:: «ይህች ከተማ ማን ትባላለች? ስል ጠየቅሁት፡፡ ሰውዬው መልስ አልሰጠኝም፡፡ የአንድ ቤት በር ሲከፈት
ስላየሁ ቤቱ ውስጥ ገባሁ፡፡»
ከፊት ለፊት ከነበረው ክፍል ውስጥ ሰው አልነበረም:: ወደሚቀጥለው ክፍል አመራሁ:: አንድ ሰው ግድግዳ ይዞ ቆሞአል:: «የማን ቤት ነው?
እኔስ የት ነው ያለሁት?» ስል ጠየቅሁት፡፡ መልስ አልሰጠኝም:: ከአጥር ግቢው ውስጥ የአትክልት ቦታ ነበር፡፡
ወደ አትክልቱ ሥፍራ ወጣሁ:: ጭር ያለ ሥፍራ ነበር፡፡ አንድ ሰው
ዛፍ ተደግፎ ቆሞአል:: «ይህ ቤት የማነው? እኔስ የት ነው ያለሁት?» ስል ጠየቅሁት:: መልስ አልሰጠኝም::
ቶሎ ብዬ ከዚያ ቤት ወጥቼ ሄድኩ፡፡ በየመንደሩ ተዟዟርኩ፡፡ መንገዱ ሁሉ ጭር ብሏል፡፡ የየቤቱ በር ግን ክፍት ነበር፡፡ መንገድ ላይ ወፍ እንኳን
ዝር አይልም:: ድምፅ የሚባል ነገር ፍጹም አይሰማም:: ነገር ግን ከየመንገዱ ጥግ፣ ከየቤቱ ግድግዳ ሥር ሰው ቆሞአል፡፡ ሆኖም ማንኛቸውም ቢሆኑ
ቃል አይናገሩም:: የሚደንቀው ደግሞ ማንኛውም ሰው ቢሆን ከቆሙት ሰዎች መካከል ሁለቱን በአንድ ጊዜ ማየት አይችልም፤ እነርሱም አይተያዩም::
በእያንዳንዱ ሰው አጠገብ ባለፍኩ ቁጥር አተኩረው ያዩኛል፡፡ ከከተማው ወጣሁና ወደ ሜዳው መንገዴን ቀጠልኩ፡፡ ጥቂት እንደተጓዝኩ ወደኋላ ብል ሠራዊት ተከትሎኛል፡፡ በየመንገዱና በየጥሻው ሥር ቁመው የነበሩ
ሰዎች መሆናቸውን ተገነዘብኩ፡፡ የፊት ገጽታቸው የተለየና አስገራሚ
ፍጡሮች ናቸው፡፡ የተቻኮሉ አይመስሉም፣ ግን ከእኔ ይበልጥ ነበረ የሚራመዱት፡፡ ሲራመዱ ድምፅ አያሰሙም፡፡ በድንገት ሲከቡኝ አየኋቸው::ፊታቸው ቀይ አፈር ይመስላል፡፡ ወደ ከተማው ስገባ በመጀመሪያ ያነጋገርኳቸው ሰውዬ 'ወዴት ነው የምትሄደው? ከሞትክ መቆየትህን አላወቅህም እንዴ? ሲሉ ጠየቁኝ፡፡ መልስ ለመስጠት አፌን ስከፍት ከአጠገቤ ሰው አጣሁ»
መሴይ ማንደላይን በጣም በርዶት ከእንቅልፉ ነቃ፡፡ ውርጭ ያዘለ ነፋስ ተከፍተው የነበሩትን መስኮቶች ያወዛውዛል፡፡ እሳቱ ጠፍቷል፡፡ አሁንም እንደጨለመ ስለሆነ አልነጋም፡፡ ተነስቶ ወደ መስኮቱ ሄደ፡፡ ሰማይ ላይ
ከዋክብት አይታዩም፡፡ ወደ ውጭ ተመለከተ፡፡ አንድ የሚያቃጭል ድምፅ ዓይኑን ሳበው:: የጋሪ ኮቴ ነበር የሰማው::
«በዚህ ሰዓት ደግሞ የምን ጋሪ ነው?» ሲል ራሱን ጠየቀ:: «ማነው
ገና ሳይነጋ በጋሪ የሚሄደው?»
ወዲያው የነበረበት ክፍል በር ሲንኳኳ ሰማ:: ከእግር እስከ ራሱ
አንድ ነገር ወረረው፧ በጣም ደነገጠ፡፡
‹‹ማነህ?»
አንድ ሰው መልስ ሰጠ፡፡
«ክቡር ክንቲባ፣ እኔ ነኝ፡፡»
አሮጊትዋ የቤት ሠራተኛ እንደሆነ አወቀ፡፡
«ምነው፧ ምን ፈለጉ?» ሲል ጠየቃቸው::
«ከንጋቱ አሥራ አንድ ሰዓት ሆኖአል ጌታዬ!»
«ታዲያ ምን አለበት!»
«ክቡር ከንቲባ፣ ረሱት እንዴ! ጋሪ በጠዋት እንዲመጣ ብለው
አዝዘው ነበር እኮ!»
«ይቅርታ፣ አዎን አዝዤ ነበር፡፡»
አሮጊትዋ ቢያዩት ይደነግጥ ነበር:: የሻማ ማንደጃዎቹን ተመለከተ።
የቀለጠውን ሻማ ጠራረገ:: አሮጊትዋ በር ላይ ቆመው ይጠብቃሉ።

👍10👏3😁3
ሲዘገይባቸው «ጌታዬ ባለጋሪውን ምን ልበለው?» ሲሉ እንደገና ጠየቁ፡፡
«ጠብቅ ይበሉት! መጣሁ አንድ ደቂቃ!»
ጋሪው አራስ ከተማ ሲደርስ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ይሆናል፡፡ እስካሁን ታሪኩን የተከታተልነው ሰው ከጋሪው ወርዶ ወደ ከተማ በእግሩ ተጓዘ፡፡
ከተማውን ከዚያ በፊት አያውቀውም፡፡ ለአገሩ ባዳ ለሰዉ እንግዳ ነው፡፡ ብዙ ስለተጓዘ ለመመለስ መንገዱ ጠፋው፡፡ ከዚያ አካባቢ ፍርድ ቤት
እንዳለ እየፈራ አንዱን መንገደኛ ጠየቀው፡፡ «ጌታዬ» አለ ሰውዬው
«የፍርድ ቤት ሙግት ለመመልከት ፈልገው እንደሆነ ጊዜው መሽቷል፡፡
ሥራ የሚያቆሙት በአሥራ ሁለት ሰዓት ነው::
አደባባይ ካለበት ሲደርሱ ፍርድ ቤቱ ከአንድ ትልቅ ሕንፃ ውስጥ
እንደሆነ አመላከተው::
«ጌታዬ እድለኛ ነዎት፧ የፍርድ ቤቱ መብራት አልጠፋም፤ አሁንም
ዳኞች ችሎት ላይ ናቸው ማለት ስለሆነ መግባት ከፈለጉ ሊገቡ ይችላሉ፡፡
ብርቱ ክርክር ገጥሞዋቸው ይሆናል እስካሁን የቆዩት፡፡»
ወደ ፍርድ ቤቱ አመራ:: ቤቱ ጢም ብሎ ሞልቷል፡፡ ከጠበቆች
አነስተኛ ድምፅ በስተቀር ብዙ ጫጫታ የለም:: ፍርድ ቤቱ ቀደም ሲል የሌሎች ሰዎችን ጉዳይ ካየ በኋላ አሁን የሚነጋገረው «ፍራፍሬ ሰርቀዋል» ስለተባለው ስለሻምፕማትዩ ነው:: እኚህ ሰው በእርግጥ ፍራፍሬ
ለመስረቃቸው ማረጋገጫ አልተገኘም:: ማረጋገጫ የተገኘለት ወንጀላቸው
ግን ከእስር ቤት መጥፋታቸው ነበር፡፡ ምርመራው ቀጥሎ የምስክሮች ቃል ተሰምቷል፡፡ አሁን የሚጠበቀው የአቃቤ ሕግ ክርክርና የዳኞች ውሳኔ ነበር፡፡ በአዝማሚያው እንደታየው በሰውዬው ላይ እንደሚፈረድ ነበር።ጠበቃቸው ግን በጣም ጎበዝ ሲሆን ከዚያ በፊት በያዘው ጉዳይ ተረትቶ አያውቅም:: ሰውዬው ጠበቃ ብቻ ሳይሆን ጥሩ ጸሐፊም ነበር፡፡ የጠባቂዎች ኃላፊ በሩን ከፍቶ ብቅ አለ፡፡
«ጎበዝ እንዴት ነው፧ ልገባ እችላለሁ?»
«አይቻልም» አለ የጠባቂዎች ኃላፊ::
«ምነው?»
«ምክንያቱም ቤቱ ከአፍ እስከ ገደፍ ጢም ብሎ ሞልቶአል»
«ምን ማለትዎ ነው፤ አሁን አንድ መቀመጫ ጠፍቶ ነው?»
«አንድ መቀመጫ! በሩ የተዘጋው ለዚሁ ነው:: ካሁን በኋላ ሰው
አይገባም::››
የጠባቂዎች ኃላፊ ጥቂት ቆይቶ «እርግጥ ዳኞች ከተሰየሙበት አካባባ ሁለት ወይም ሦስት ሰው የሚያስቀምጥ ቦታ ነበር፤ ነገር ግን ከዚያ ቦታ እንዲቀመጡ የሚፈቀደው ለመንግሥት ባለሥልጣኖች ብቻ ነው፡፡»
ኃላፊው ይህን እንደተናገረ ፊቱን አዙሮ ሄደ፡፡ ይህን ጊዜ ኃላፊው
ያነጋገረው ሰዉ ጥቂት አሰበና ከኪሱ ወረቀትና ብዕር አወጣ፡፡ መብራቱ ወደነበረበት ጠጋ አለ፡፡ «መሴይ ማንደላይን የሞንቴስ ሱር ሞንቴስ ከንቲባ ብሎ ከጻፈ በኋላ የጠባቂዎች ኃላፊ ወደሄደበት አቅጣጫ ፈጠን ብሎ
ሕዝቡን አልፎ ሄደ:: ብጣሹን ወረቀት ለጠባቂዎች ኃላፊ ሰጠውና «ይህ ወረቀት ለዳኛው ስጣቸው» አለው::
የጠባቂዎች ኃላፊ ጽሑፉን ከተመለከተ በኋላ ለመሀል ዳኛው ወስዶ ሰጣቸው::
የሞንቴስ ሱር ሞንቴስ ከንቲባ ሳይታወቀው ሰው ያከበረውና ያደነቀው መሰለው:: ባለፉት ሰባት ዓመታት ዝናው በሚኖርበት አካባቢ ብቻ ሳይሆ በመላ ሀገሪቱ ውስጥ ተሰምቶ ነበር፡፡ ቢያንስ እርሱ ከነበረበት ክፍለ ሀገር
በየአቅጣጫው እስከ ሁለትና ሦስት ክፍለ ሀገሮች ዝናው ዘልቆ ሄዶ ነበር
የሻምፕማቲዩን ጉዳይ የያዙት መሐል ዳኛ ወረቀቱን ሲያዩ ሰውዬው የሚያውቁትና የሚያደንቁት ሰው እንደሆነ አወቁ፡፡ የጠባቂዎች ኃላፊ
ወረቀቱን ለዳኛው ሲሰጣቸው ከወረቀቱ በተጨማሪ በቃሉ «እኚህ ሰው የምስክርነት ቃላቸውን ሊሰጡ ይፈልጋሉ» አላቸው:: ወዲያው ዳኛ ለጠባቂዎች ኃላፊ «አስገባው» ሲለ ትእዛዝ ሰጡት::
ይህ ታሪኩን የምንከታተለው አሳዛኝና የተከፋ ሰው ወረቀቱን ከሰጠበት ሥፍራ አልተነቃነቀም::
«ጌታዬ ይከተሉኝ» አለው:: ቀደም ሲል ፊቱን ያዞረበት ዘበኛ አሁን
ለጥ ብሎ እጅ ነስቶ ነው «ይከተሉኝ» ያለው:: የጠባቂዎች ኃላፊ ወዲያው በተራው አንድ ብጣሽ ወረቀት ብጤ ሰጠው:: ጽሑፉም «የመሐል ዳኛው
የአክብሮት ሰላምታውን ያቀርባል» የሚል ነበር፡፡
ወረቀቱን ጭምድድ አድርጎ ኪሱ ውስጥ ጨመረው፡፡ ወረቀቱ አቻ
ዓይነት ትዝታ ቀሰቀሰበት:: የጠባቂዎች ኃላፊን ተከትሉ ሄደ፡፡ ወንበር ተከልለው ከተቀመጡበት ሥፍራ ደረሱ::
«ጌታዬ ይቀመጡ» አለው የጠባቂዎች ኃላፊ:: ሰውዬው እንዲሄድለት ግድግዳውን ተደግፎ ቆመ፤ አላበው፧ መተንፈስ አቃተው፤ ሰውነቱ ተንቀጠቀጠ፡ እንደገና ቁጭ አለ፡፡ የተቀመጠበት ቦታ ትንሽ ዞር ያለ ስለነበር ለሰው በግልፅ አይታይም
💫ይቀጥላል💫

👍17❤5
#መኖር_የሚያስመኝ
ሀዘን ደስታ ሲዘባረቅ
እንባ ሲቀር ጥርስ ሲስቅ
አመት መንፈቅ ሲፈራረቅ
ኑሮ ለሕይወት መልስ ሲሰጥ
በሀሴት ተሞልቶ ባሕር ሲሰመጥ
ያፀላው ፅልመት ሲገለፅ
ተስፋ ሲያንዣብብ ሀሳብ ሲቀረፅ.............
ያኔ ነው እንጂ መኖር የሚያስመኝ
ልብ የሚጠግን የራስ ሰው ሲገኝ::
🔘ከቃልኪዳን ወርቁ🔘
ሀዘን ደስታ ሲዘባረቅ
እንባ ሲቀር ጥርስ ሲስቅ
አመት መንፈቅ ሲፈራረቅ
ኑሮ ለሕይወት መልስ ሲሰጥ
በሀሴት ተሞልቶ ባሕር ሲሰመጥ
ያፀላው ፅልመት ሲገለፅ
ተስፋ ሲያንዣብብ ሀሳብ ሲቀረፅ.............
ያኔ ነው እንጂ መኖር የሚያስመኝ
ልብ የሚጠግን የራስ ሰው ሲገኝ::
🔘ከቃልኪዳን ወርቁ🔘
❤20👍6
#ምንዱባን
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አራት
፡
፡
#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ
....«ጌታዬ ይቀመጡ» አለው የጠባቂዎች ኃላፊ:: ሰውዬው እንዲሄድለት ግድግዳውን ተደግፎ ቆመ፤ አላበው፧ መተንፈስ አቃተው፤ ሰውነቱ ተንቀጠቀጠ፡ እንደገና ቁጭ አለ፡፡ የተቀመጠበት ቦታ ትንሽ ዞር ያለ ስለነበር ለሰው በግልፅ አይታይም
ቁጭ እንዳለ አሳቡን የመለወጥ ዝንባሌ ታየበት:: “እስቲ አሁን ማን
አስገድዶኝ ነው የመጣሁት» ሲል አሰበ:: ነገር ግን እንዴት እንደሆነ
ሳያውቀው ቶሎ ብድግ ብሎ በመራመድ ችሎቱ ውስጥ ዳኞች ከነበሩበት አካባቢ ተጠጋ::
አካባቢውን በሚገባ ቃኘው:: ዳኞች ከፊት ለፊት ከፍ ካለው ሥፍራ ተቀምጠዋል:: ጠበቆች አፍጥጠዋል:: ጠባቂ ወታደሮች በየጥጉ ተበታትነው ቆመዋል:: የዳኞች ጠረጴዛ በደማቅ ጨርቅ ተሸፍኖአል:: የበሮች እጄታ
አካባቢ በእድፍ ጠቁሯዋል:: «
ስው ሰራሽ ሕግ እውነትን ያወጣል» በሚል እምነት ከዚያ የነበረ ሁሉ በጥሞና ያዳምጣል:: የሰው ብዛት ከመጠን በላይ
ስለነበር እርሱን ማንም ልብ አላለውም:: ሰው ሁሉ ይመለከት የነበረው ከወንጀለኞች መቆሚያ ላይ በሁለት ጠባቂዎች ታጅቦ ቆሞ የነበረውን ሰው
ነው::
በሁለት ጠባቂዎች ታጅበው የቆሙት ተከሳሹ ሻምፕማቲዩ ነበሩ፡፡መሴይ ማንደላይን አተኩሮ ተመለከታቸው:: በመልክ መመሳሰላቸውን ተገነዘበ፡፡ በእድሜ ግን ከእርሱ በጣም ያረጁ ይመስላል::
እየቀረበ ሲሄድ የመሐል ዳኛውና አቃቤ ሕጉ በጉልህ ስላዩትና
ስለለዩት በአንገት ሰላም አሉት:: ዳኞቹን፣ ሕግ አስከባሪውና እዚያ የነበሩ ጠበቆችና ጠባቂዎች ከሃያ ሰባት ዓመት በፊት ያያቸው መሆኑን አስታወሰ፡፡
አሁንም ከስንት ዓመት በኋላ ከእነዚህ ሰዎች እጅ ሊወድቅ በመሆኑና ውሳኔያቸው ስለአስፈራው ዓይኑን ጨፈነ፡፡ ከፊት ለፊቱ የቆሙት ተከሳሽ
«ዣን ቫልዣ ናቸው ተብለው ነው የተከሰሱት» የሚል አሳብ ስለተሰረጸበትና ሕሊናው እንደ መሳት ስላለ ቶሎ ብሎ ተቀመጠ፡፡ እንደተቀመጠ ዣቬርን በዓይኑ ፈለገው ፤ አላገኘውም፡፡ ሕግ አስከባሪው መንገድ ላይ ስለተቀመጠ ምስክሮችን ሊያያቸው አልቻለም:: ክፍሉም ቢሆን በመጠኑ ጨለምለም
ያለ እንጂ ቦግ ብሉ የበራ ብርሃን አልነበረውም::
ክርክሩ የፈጀው ወደ ሦስት ሰዓት ገደማ ሲሆን ተከሳሹ ኣንደበተ
ርቱዕ ስልነበሩ የተከሰሱበትን ይካዱ እንጂ በሚገባ አላስረዱም:: እንዲያውም
ብዙውን ጊዜ ጣራ ጣራውን ነበር የሚያዩት:: ሲያዩዋቸው ቂላቂልና
ጅላጅል ቢጤ ይመስላሉ፡፡ ቀደም ሲል እንደተጠቀሰው በእኚህ ሰው ዝምታ የተነሣ ሰው ሁሉ የጠበቀው ከባድ ቅጣት ነው።
ሕግ አስከባሪው የሚከተለውን ተናገረ::
«ተከሳሹ በቅድሚያ ክስ የቀረበባቸው በፍራፍሬ ስርቆት ወንጀል ነበር፡፡ ክሱ ሲመሠረት የቀረበው ማስረጃ 'የሠረቁት ፍሬ ከእነቅጠሉ በእጃቸው ላይ ተገኝቷል' የሚል ነበር፡፡ ሆኖም ይህ ብቻ እንደ ማስረጃ
ተቆጥሮ ለመስረቃቸው ማረጋገጫ ሊሆን አይችልም:: ተከሳሹ ከየት እንዳገኙት ሲጠየቁ ከመሬት ነው ያነሳሁት' ብለዋል፡፡ እርግጥም የፍራፍሬውን
ዛፍ ሌባ ቀጥፎ መንገድ ሊጥለው ይችላል፡፡ ስለዚህ ፍሬዎችን የያዘ
ቅርንጫፍ በመስበር የሰረቁት ሻምፕማትዩ ናቸው ለማለት ያስቸግራል።
ይህም በመሆኑ በዚህ ጉዳይ ሊከሰሱ አይችሉም፡፡ ነገር ግን ከእስር ቤት ያመለጠ ወንጀለኛ ለመሆናቸው በማስረጃ ተረጋግጧል፡፡ ምንም እንኳን
ዣን ቫልዣ ለመሆናቸው ምስክሮች ቢያረጋግጡም ተከሳሹ እስከመጨረሻው ክደዋል፡፡ ክህደቱን ትተው የፍርድ ቤቱን አስተያየት ቢጠይቁ የሚሻላቸው
ለመሆኑ ቢገለጽላቸውም አሻፈረኝ ብለዋል፡፡ በተከሳሹ አመለካከት ስለካዱ ከቅጣት የሚያመልጡ መስሎአቸው ይሆናል፡፡ በዚህ በኩል ተሳስተዋል፡፡ሆኖም ይህ ከእውቀት ማነስ እንጂ ሆን ብሎ የተደረገ ሊሆን አይችልም፡፡
ተከሳሹ በእርግጥ ንቃት ይጉድላቸዋል፡፡ ይህም የሆነው ምናልባት ለረጅም ጊዜ እስር ቤት ቆይተው በመሰቃየታቸው ከዚያም በኋላ ብዙ ስለተንከራተቱ
ሊሆን ይችላል፡፡ ወይም ደግሞ በሌላም፣ በሌላም ምክንያት ሊሆን ይችላል።ሆነም ቀረም የእርሳቸው አነጋገር አለማወቅ ወይም ችሎታ ማነስ ከሚሰጠው
ብያኔ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር አይገባም:: ነገር ግን ተከሳሹ ዣን ቫልዣ እንደሆነና የቅጣት ዘመናቸውን ሳይጨርሱ አምልጠው ለመጥፋታቸው
ጥርጥር የለውም:: ስለዚህ ተከሳሹ ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው በወንጀለኛ
መቅጫ አንቀጽ መሠረት ተገቢውን ቅጣት ይቀበላሉ፡፡»
ሕግ አስከባሪው ዳኞች ስለሰጡት አስተያየትና ስለፈጸሙት ጥልቅ
ምርምር በቅድሚያ ምስጋናውን አቅርቦአል፡፡ ተከሳሹን ግን የዳኞቹን ትንተና መሠረት በማድረግ በጣም ነቅፎዋቸዋል፡፡ ተከሳሽ ዣን ቫልዣ እንደሆነ
ስለመረጋገጡ ሲያስረዳ «ዝም ማለታቸው ነገሩን አምነው እንደተቀበሉ ያሳያል» አለ፡፡
«ቀደም ሲል ግን ክደው ነበር:: ለመሆኑ ዣን ቫልዣ ማነው? ዣን ቫልዣ የተተፋ፣ አገር የጠላውና ሌላም ሌላም ሰው ነው፡፡»
ሕግ አስከባሪው ይህን ሲናገር ከዚያ የነበረ ሰው ሰውነት ሁሉ
ስቅጥጥ አለ፡፡ «ሻምፕማንቲዩ ማለት ዣን ቫልዣ ነው» ተብሎ ክስ
ሲመሠረት «ዦርናል ደ. ለ ፕሪፊትየር የተባለ ጋዜጣ ዣን ቫልዣ ማን እንደሆነ ሲያስረዳ «ዣን ቫልዣ ማለት ወሮበላ፣ ለማኝ፣ ቀጣፊ፣ መተዳዳሪያ
የሌለው አውደልዳይ፣ ሕይወቱን ወንጀል በመሥራት የሚመራ እንዲሁም ሌላም ሌላም ቅጽል ሊሰጠው የሚገባ ነው» ብሎ እንደጻፈ ተናገረ፡፡
«ይህ ሰው ፍራፍሬ ሠርቆ ቢያዝም አድራጐቱን ክዷል፡፡ እንዲሁም ከእስር ቤት ለማምለጡም ከሕግ ፊት ክዷል፡፡ የሚገርመው የገዛ ስሙን
እንኳን የካደ ሰው ነው:: ምን ያልካደው ነገር አለ! ሕልውናውን ጨምሮ ነው የካደው ለማለት ይቻላል፡፡ ነገር ግን እርሱ ሽንጡን ገትሮ ቢክድም አራት ምስክሮች መስክረውበታል: የተከበሩትና ውሽት የማያውቁት የፖሊስ
አዛዥ ዣቬር እንኳን በእርሱ ላይ መስክረዋል፡፡ እስር ቤት ውስጥ ከተከሳሹ ጋር አብረው ታስረው ከነበሩት ሰዎች መካከል ሦስት እስረኞችም መስክረውበታል፡፡ እነዚህ ምስክሮች ከመሰከሩበት በኋላ እንኳን ወንጀሉን አምኖ ይቅርታ አልጠየቀም:: ስለዚህ ማኅበራዊ ኑሮን ሊያፋልስ ታጥቆ
የተነሣ ወንጀለኛ ስለሆነ ቅጣቱ ሊቀልለት አይገባም፡፡»
ሕግ አስከባሪው ይህን ማብራሪያ ሲሰጥ ካህኑ ተከሳሽ አፋቸውን
ከፍተው በመገረምና በመደነቅ አዳመጠ፡፡ ሕግ አስከባሪው አንደበተ ርቱዕ በመሆኑ ቢያደንቁትም በማያውቁት ነገር እንደዚያ ስለወረደባቸው ከልብ
ረገሙት:: ግራ ቀኙን ከቃኙ በኋላ ተከሳሹ ራሳቸውን ነቀነቁ፡፡
ሕግ አስከባሪው ትችቱን በመቀጠል «ማንም ሰው ወንጀል ሊሠራ ወይም ውሸት ሊናገር ይችላል፡፡ ግን ከሕግ ሊያመልጥ አይችልም፡፡ ይህ ሰው ግን ወንጀል ከመፈጸም አልፎ ከሕግ ለማምለጥ ሞክሮአል፡፡ ይህም
ከባድ ወንጀል በመሆኑ በእድሜ ልክ እስራት እንዲቀጣ አሳብ ኣቀርባለሁ::»
«ስለተሰጠው አስተያየት የምትሰጠው መልስ አለ?» ሲሉ ዳኛው ተከሳሹን ጠየቁዋቸው:: ቆባቸውን ያፍተለትሉ የነበሩት ተከሳሽ ምንም ነገር እንዳልሰማ ዝም አሉ::
ዳኛው ጥያቄውን ደገመላቸው::
አሁን ግን ጥያቄውን ስለሰሙ ዳኛው ምን ማለት እንደፈለጉ ገባቸው::ከእንቅልፍ እንደነቃ ሰው ከወዲያ ወዲህ ተመለከቱ፡፡ ዳኞቹን፣ ሕግ አስከባሪውን፣ ጠበቆቹንና ተመልካቹን ሕዝብ አፍጥጠው ካዩ በኋላ ከፊት
ለፊት የነበረውን መከለያ ብረት አጥብቀው ይዘው በድንገት በከፍተኛ ድምፅ መናገር ጀመሩ፡፡ ቃላት ተሽቀዳድመው «እኔ ልቅደም፧ የለም እኔ ልቅደም» ያልዋቸው ይመስል እየተቻኮሉ በጣም በፍጥነት ተናገሩ፡፡

👍19❤4
«የምለውን በጥሞና አድምጡኝ:: ከመሴይ ባሉፕ ሱቅ ውስጥ ለጋሪ
የሚሆን የብረት ተሽከርካሪ ሰራተኛ ነኝ፡፡ ብረት መቀጥቀጥ በጣም ከባድ ሥራ ነው:: ሥራውን እንሰራ የነበረው ከቤት ውጭ ሲሆን አሠሪያችን ይህን ያህል ለሠራተኞች ደኅንነት ደንታ አልነበራቸውም.: ደግ የሆነ አሠሪ
ለሠራተኞቹ በማሰብ ለስራ የሚሆን የተለየ ቤት ይሠራል፡፡ እኛ ግን ሜዳ ላይ ነበር የምንሠራው:: ቆፈን ሲይዘን ሥራችንን አቁመን በትንፋሻችን እጃችንን ያሞቅን እንደሆነ አሠሪያችን በጣም ይቆጣናል፡፡ ለምን የሥራ
ጊዜ ታባክናላችሁ' እያሉ ይጮሁብናል፡፡ በተለይ በክረምት ከባድ በረዶ በሚጥልበት ጊዜ ብረት መቀጥቀጥ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ የደረሰበት
ያውቀዋል፡፡ ሰውነትን በአጭር ጊዜ አሟምቶ በልጅነት ያስረጃል፡፡ በዚህ ሥራ የተሰማራው ሰው በአርባ ዓመቱ የሰማንያ ዓመት ሽማግሌ ነው የሚመስለው፡፡ እኔ በበኩሌ አምሳ ሦስት ዓመት ከሞላኝ በኋላ ብዙ ያመኝ ነበር፡፡ አሠሪዎች ያረጀ ሽማግሌን መቅጠር ስለማይወዱ እኔም ላይ
ጨከኑ፡፡ ሰው ሲያረጅ አሮራጌ ውሻ ብለው ነው የሚጠሩት፡፡ በእርጅናዬ ዘመን በቀን ሰላሳ ሱስ ነበር የማገኘው:: ገንዘቡ በጣም አነስተኛ ቢሆንም ምንም ምርጫ ስላልነበረኝ በዚህ ደመወዝ ሠራሁ:: በዚያን ጊዜ አንዲት
ልብስ አጣቢ ልጅ ነበረችኝ፡፡ ይህቺ ልጅ ልብስ እያጠበች ጥቂት ገንዘብ ታመጣ ነበር:: እርስዋ እየለፋች የምታመጣውን ገንዘብ በማዳመር እየተንገዳገድን እንደማይኖር የለምና እኛም እንዳቅማችን ኑሮ ካሉት
መቃብርም ይሞቃል እንዲሉ ኖርን፡፡ እድሜያችንን በዚህ ዓይነት ገፋነው:: ዶፍ ቢወርድ፤ ሐሩር ቢያቃጥል ልጂ ወደኋላ ሳትል ቀኑን ሙሉ ልብስ ታጥባለች:: ልብስ ቶሉ ቶሉ ማጠብ ነበረባት፡፡ አብዛኞቹ ደምበኞችዋ
ብዙም ቅያሪ የነበራቸው አይደሉም:: ስለዚህ የሚሰጥዋት ልብስ በእለቱ ታጥቦና ተተኩሶ የሚመለስ ነበር፡፡ ጥያቄያቸው ካልተጠበቀ ሁለተኛ ተመልሰው አይመጡም:: የልብስ አጣቢ ሰውነት ከእግር እስከ ጭንቅላት
ይርሳል፡፡ ልብሶቹን ታጥብ የነበረው እቤት ሳይሆን ወንዝ ወርዳ ነው::ከወንዝ የምትመለሰው አንዳንዴ ጀምበር ከጠለቀች በኋላ ነበር፡፡ ወዲያው
እንደመጣች መደብዋ ላይ ትዘረራለች፡፡ በጣም ይደክማታል፡፡ ባልዋ እኔ ፊት እንኳን ጠዋት ማታ ይቀጠቅጣታል:: ዛሬ እርስዋ ከዚህ ሁሉ ተገላግላ አንድ ቀን እንኳን ሳይደላት ሞታለች:: መኳንንቶቼ ውሸቴን አይደለም፤
የምናገረው ነገር ሁሉ እውነት ነው:: እኔ ማን እንደሆንኩ መሴይ ባሉፕን ጠይቁ፡፡ አሁኑኑ ሂዱና ጠይቋቸው:: ከዚህ ይበልጥ ከእኔ ምን እንደምትፈልጉ
አላውቅም::
ሰውዬው ንግግራቸውን አቆሙ፤ ቁጭ ግን አላሉም:: የተናገሩት
በቁጭትና በብሽቀት ነበር፡፡ ንግግራቸውን ሲጨርሱ ከእዚያ የነበረው ሰው ሁሉ ሳቁባቸው፡፡ የሚስቁትን ሁሉ ቀና ብለው ተመለከትዋቸው፡፡
እርሳቸውም ምክንያቱ ምን እንደሆነ ሳያውቁ አብረው ይስቁ ጀመር፡፡የሚያስፈራና የማይገባ ነገር ነው ፧ አይደለም! የመሐል ዳኛው ቅን መንፈስ ያላቸው፣ ለሰው የሚያዝኑ ዓይነት ሰው ነበሩ:: ድምፃቸውን ከፍ
አድርገው «ይሄ መሴይ ባሉፕ የተባለውን ሰው ተከሳሽ ቀደም ብሎ የጠቀሰው ስለነበር ተፈልጎ ሊገኝ አልቻለም:: በሥራው ስለከሰረ አገር ጥሎ ኮብልሏል» ካለ በኋላ ወደ ተከሳሹ ዞር ብለው «ቢበቃህ ያሻላል፡፡
ሆኖም በመጨረሻ እንድትመልስልኝ የምጠይቃቸው ሁለት ጥያቄዎች አሉ፡፡ እነርሱም አንደኛ «ዩሪናሪ ሰርቀሃል ወይስ አልሰረቅህም? ሁለተኛ
እስር ቤት ያመለጠውና ወንጀለኛው ዣን ቫልዣ” ማለት አንተ ነህ ወይስ አይደለህም?
የሚናገረው ሁለ አጥርቶ እንደሚያውቅና የተናገሩትን በትክክል የገባው ሰው እንደሚያደርገው ሁሉ ራሳቸውን ነቀነቀ፡፡ ወደ መሐል ዳኛ
ው ፊታቸውን አዙረው የሚከተለውን ተናገሩ::
«በመጀመሪያ ደረጃ» ካለ በኋላ ቀና ብለው ጣራውን ከዚያም ከቤቱ፡ውስጥ የተቀመውን ሁሉ ቃኘ::
«ምን ወዲህ ወዲያ ትላለህ? የተጠየቅንውን መልስ እንጂ:: በራስህ ላይ እኮ ነው የምትፈርደው» አለ ሕግ አስከባሪው::
ተከሳሸ ወዲያው ቀና ብለው በአፋጣኝ ተናገሩ፡፡
«ክፉና ጨካኝ ሰው ነዎት፤ ማለቴ እርስዎ አሁን የተናገሩት:: እኔ
የምሠራውንና የምናገረውን አውቃለሁ:: ፍሬ የሚባል ነገር አልሰረቅሁም፡፡ስርቆት የሚባል ነገርም አይነካካኝም፡፡ የእለት እንጀራ እንኳን የማላገኝ
ሰው ነኝ፡፡ ገላዬን ከወንዝ ታጥቤ ስመለስ መንገዱ ሁሉ ጭቃ ሆነብኝ::
ከጭቃ ለመሸሽ ጥግ ጥጉን ስሄድ ፍሬ የያዘ ቅርንጫፍ አየሁ:: 'የወደቀን አንሱ፤ የሞተን ቅበሩ ነውና አነሳሁት:: ያነሳሀት ይህን ሁሉ መከራና ስቃይ ያስከትልብኛል ብዬ አልነበረም:: ኣሁን ግን በዚያ ሰበብ ከታሠርኩ
ሦስት ወሬ ነው:: ከዚያ ወዲያ የምናገረው ታሪክ የለኝም:: አንተ ታዲያ ክፉ ሰው በመሆንህ ትሰድበኛለህ፤ በእኔ ላይ ትፈርዳለህ:: የጠባቂዎች ኃላፊ ግን ደግ ሰው በመሆኑ ወደ ጆሮዬ ጠጋ ብሎ በትህትና 'መልስ ይስጡ እንጂ እያለ ይመክረኛል:: እኔ እንደሆነ ብዙ ባለመማሬና ድሃ በመሆኔ ንግግር ኣላውቅም:: ኣሳቤን በቁርጥ ማቅረብ ይሳነኛል፡፡ ሆኖም ቀረም እዚህ
ያላችሁት ሁሉ አለመስረቄፀን ለማየት ባለመቻላችሁ ተሳስታችኋል፡፡ ስለዣን
ቫልዣ ትናገራላችሁ:: እኔ ይህ ሰው ማን እንደሆነ አላውቀውም፡፡ እኔ
እሠራ የነበረው ከመሴይ ባሉፕ ዘንድ ሲሆን ስሜ ሻምፕማቲዩ ይባላል፡፡ጎበዞች ብትሆኑ ኖሮ የት እንደተወለድኩ ትጠይቁኝ ነበር፡፡ ያም ሆነ ይህ ስለ ራሴ ብዙ አላውቅም:: እያንዳንዱ ሰው የተወለደበት አገር ወይም ቤት
ሊኖረው ይችል ይሆናል:: እኔ ግን የት እንደተወለድኩ እንኳን አላውቅም፡፡እናትና አባቴ ዘላኖች ስለነበሩ የሚኖሩት ከቦታ ቦታ እየተዘዋወሩ ነበር፡፡
ስወለድ 'ማሙሽ እያሉ ነበር የሚጠሩኝ:: አሁን ደግሞ ሽማግሌው እየተባልኩ ነው የምጠራው:: አሁን ያሉኝ ስሞች የክርስትና ስሞች ናቸው::
አንተ ደግሞ እንደፈለግክ በላቸው:: ብቻ እመነኝ እኔ ሌላ ሰው አይደለሁም::
እኔ እባ ሻምፕማትዩ ነኝ:: የኖርኩትም አአሀገሪዩ ከመሴይ ባሉ ቤት ነው፡፡ እኔ አሁን የሰለቸኝ እናንተ የምትሉትን ታሪክ መስማት ነው:: ልክ እብድ ውሻ እንደሆንኩ ዓይነት ሰው ሁሉ እኔን የሚከታተልበት ምክንያት
አይገባኝም፡፡»

👍13❤9👏1
እንዴት እንደመጣሁ ፣ እንዳትጠይቂኝ፤
ለምን?
ስለምትናፍቂኝ።
አውቀዋለሁኛ!
አንድ የበደለሽ ሰው ፣ ናፍቀሽኛል ቢልሽ፣
ላንቺ...
ፌዝ ነው የሚመስልሽ፤
ግን ናፍቀሽኛል።
አዎ!
በድያለሁ በግፍ፤
ደግሞም...
ናፍቀሽኛል በእጥፍ።
ማርያምን የሞሬን ፣በዝቷል መናፈቄ!
የትም እገኛለሁ፤
የትም እስቃለሁ ፤ግን ያለቅሳል ሣቄ!!
ብራመድ በሀገሩ ፣ብከንፍ እንኳ ብበር
ተከፍቶ ዐያለሁ ፣ቆለፍኩት ያልኩት በር።
ቀን የከረቸምኩት፣
ሌት በምን ከፈትኩት?
በሌሊትሽ መጣሁ፤
ዓለሜን ስላጣሁ።
ከትናንት የባሰ ፣ እንደማጣሽ ሳስብ
በደሌን ዐየሁት ፤ እጥፍ መውደድ ሲስብ።
አንቺዬዋ ውዴ...
የበደል ሁሉ ፣ አይናፍቅም እንዴ?
ማቀፍ እንኳ ባልችል፣ምሕረት ባለምንም፣
አትሳቂብኝ እንጂ!
ግጥሙን እያነበብኩ ናፈቅሽኝ አሁንሞ፡፡
ፀሐይዋን ከተትኳት፤
ዐይንሽን ለማየት ፣ከቤቴ እየወጣሁ፤
የበደለ ዐይኔን...
እንዳታዪኝ ብዬ ፣ በጨለማ መጣሁ።
ደረስኩኝ ከደጀስ ፤ መፍራቴ በነነ፤
እሠይ አገኘሁሽ ፤ ናፍቆቴ ሰው ሆነ።
እከንፋለሁ ይኽው፤ስደርስም አልሳሞሺኝ፤
አጃኢብ ሰው መሆን!
ሳጠፋ ጊዜ ነው ፣ጭሪሽ የናፈቅሽኝ።
አጥፍቻለሁ አዎ! መውደዴን ቀብሬ፤
አትሣቂብኝ እንጂ...
ልክ ስበድልሽ ፣ ጨመረበኝ ፍቅሬ።
ናፈቅሽኝ!
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
👍17❤15
#ምንዱባን
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አምስት
፡
፡
#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ
እኔ እባ ሻምፕማትዩ ነኝ:: የኖርኩትም አአሀገሪዩ ከመሴይ ባሉ ቤት ነው፡፡ እኔ አሁን የሰለቸኝ እናንተ የምትሉትን ታሪክ መስማት ነው:: ልክ እብድ ውሻ እንደሆንኩ ዓይነት ሰው ሁሉ እኔን የሚከታተልበት ምክንያት
አይገባኝም፡፡»
አቃቤ ሕጉ የመሐል ዳኛን እያየ ተናገረ፡፡
«ጌታዬ፣ ይህ ሰው አላዋቂ በመምሰል የጮሌ ተግባር እየፈጸመ ነው:: ሆኖም የጀመረው የብልጠት ሥራ ፍሬ እንደማያፈራለት አውቃለሁ::
አሁንም የዚህን ሰው ብልጠት ለማክሸፍ የፍርድ ቤቱ፡ መልካም ፈቃድ ከሆነ አራቱ ምስክሮች ተጠርተው እንደገና በአንድነት እንዲመሰክሩበት
ይደረግ ዘንድ በአክብሮት እጠይቃለሁ::»
«አቃቤ ሕጉን ለማሳሰብ የምፈልገው ግን የፖሊሱ አዛዥ ዣቬር የምስክርነት ቃሉን ከሰጠ በኋላ አጣዳፊ ሥራ ስለነበረበት ይቅርታ ጠይቆ ሄዷል፡፡ የሄደውም ፍርድ ቤቱ ስለፈቀደለት ነው» አሉ የመሐል ዳኛው::
«እውነት ነው» አለ አቃቤ ሕጉ፧ መሴይ ዣቬር እዚህ ሊገኙ
አይችሉም፤ ሆኖም እርሳቸው ለፍርድ ቤቱ ያሰሙት የምስክርነት ቃል በድጋሚ ማሰማት ይቻላል:: መሴይ ዣቬር የተከበሩ ሰው ናቸው::ሥራቸውን የሚያከብሩና ለእውነት የቆሙ ሰው ናቸው:: ስለዚህ እርሳቸው የሰጡት የምስክርነት ቃል የሚጠራጠሩት አይሆንም:: እርሳቸውም ሲናገሩ
«የተከሳሹን ክህደት ለማስተባበል የመሐላ ቃል ወይም የተለየ ማረጋገጫ አያስፈልገንም:: ይህን ሰው በግልጽ ለመለየቴ ጥርጥር የሌለው ነው። የዚህ ሰው ስም ሻምፕማቲዩ ሳይሆን ወንጀለኛውና እጅግ የሚፈራው ዥን ቫልዣ ነው:: ቱሉን ውስጥ የሚገኘው እስር ቤት ዘቦች እዛዥ በነበርኩበት ጊዜ ሰውዬውን ብዙ ጊዜ አይቼዋለሁ:: ቃሌን እንደገና ብደግም ገና ሳየው ነው ያወቅሁት» ብለዋል፡፡
የዚህ ሰው አገላለጽ በዳኞቹና ከዚያ በነበረ ሕዝብ ላይ የማሳመን
ኃይል ነበረው፡፡ የመሴይ ዣቬርን የምስክርነት ቃል አስተዋጽኦ ካሰማ በኋላ ከእስር ቤት የመጡት እስረኞች ቃላቸውን በድጋሚ እንዲሰጡና አንዳንድ ጥያቄ እንዲቀርብላቸው አቃቤ ሕጉ ጠየቁ፡፡
የጠባቂዎች ኃላፊ ምስክሮችን በድጋሚ እንዲያስገባ ዳኛው አዘዙ።ዣን ቫልዣ ከእስር ቤት ካመለጠ በኋላ የእስራት ዘመኑን ጨርሶ የወጣውን ብሪቬት የተባለው ሰው በመጀመሪያ ተጠራ:: ብሪቬት እድሜው ስልሣ
ዓመት ነበር፡፡
«ብሪቬት» አሉ ዳኛው፤ «
ለመድገም የሚቀፍ የረጅም ጊዜ ቅጣት ተቀብለሃል፤ ስለዚህ መሐላ ለመማል አትችልም» ሲሉት ብሪቬት አቀረቀረ፡፡
ሆኖም» በማለት ዳኛው ንግግራቸውን ቀጠሉ፤ «አንድ ሕግ ያዋረደውና ሥራው ያስቀጣው ወንጀለኛ በውስጡ ሌላውን የማክበርና የሌላውን
መብት የመጠበቅ ስሜት ይኖረዋል፡፡ ምናልባት ቀደም ሲል በሰጠኸው የምስክርነት ቃል በሕሊናህ ዳኝነት የምታሻሽለው ነገር ቢኖር እንድታሰማን
እጠይቅሃለሁ፡ ተከሳሹም ተነስቶ እንዲቆምና መስካሪውም ተከሳሹን እያየ እንዲናገር እንዲሁም ጊዜው በመቆየቱ መስካሪው አስቦና አሰላስሎ አሳቡን እንዲሰጠን እያስታወስኩ ይህ ሰው ቀደም ብላችሁ እስር ቤት ውስጥ አብራችሁ የነበራችሁት ዣን ቫልዣ የሚባል እስረኛ ለመሆኑ አረጋግጠህ
በድጋሚ ለመመስከር ትችል እንደሆነ የምስክርነት ቃልህን እንድትሰጥ በድጋሚ እጠይቃለሁ፡፡
ብሪቬት እስረኛውን አተኩሮ ተመለከታቸው:: ከዚያም ፊቱን ወደ ዳኞቹ አዞረ:: ብሪቬትና ሻምፕማትዩ ዓይን ለዓይን ተፋጠጡ፡፡
«አዎን ጌታዬ፤ ይህ ሰው ዣን ቫልዣ ለመሆኑ በመጀመሪያ የለየሁት እኔ ነኝ፡፡ አሁንም ቢሆን ቃሌን አልለውጥም:: ይህ ሰው ዣን ቫልዣ ራሱ ነው:: ቱሉን ከሚገኝ ወህኒ ቤት የገባው በ1796 ዓ.ም ሲሆን ከዚያ ያመለጠው በ1815 ዓ.ም. ነው:: እኔ ከእስር ቤት የወጣሁት እርሱ ባመለጠ በዓመቱ ነበር፡፡ ሰውዬው አሁን ሲያዩት በመጠኑም ቢሆን ለውጥ አለው:: ግን ይህ
ከእድሜ ጋር የሚሄድ በመሆኑ ያሳየው ለውጥ ሊያሳስተኝ አይችልም፤ዣን ቫልዣ ራሱ ነው፡፡»
«ቁጭ በል» አሉ ዳኛው:: ተከሳሹ ግን እንደቆመ ይቆይ::
ሸነልዲዩ የሚባል ምስክር እንዲገባ ተደረገ፡፡ ቱሉን ውስጥ ከሚገኝ እስር ቤት የእድሜ ልክ እስረኛ ነው:: የምስክርነት ቃሉን እንዲሰጥ ነው ከእስር ቤት የተጠራው:: ቁመቱ አጠር ያለ የሃምሣ ዓመት አዛውንት
ነው:: ምንም እንኳን ፊቱ የተጨማደደ ቢሆንም በሁኔታው ነቃ ነቃ ያለና ተቅበጥባጭ ሰው ነው፡፡ ዳኛው ለብሪቬት ያሉትን ለእርሱም ደገሙለት:: «በሠራኸው ወንጀል
የተነሣ በመማል ቃልህን ታከብራለህ ለማለት ስለማያስደፍር መማል
አትችልም» ሲሉት ሻምፕማቲዩ ቀና ብለው ተመልክተው ከዚያ የነበረውን ተመልካች በዓይን ቃኙት:: ዳኛው አሳቡን እንዲሰበስብና እስረኛውን በትክክል ያስታውሰውና ያውቀው እንደሆነ ጠየቁት፡፡
ሺኒልዲዩ ከት ብሎ ሳቀ፡፡
“ታውቀው እንደሆነ አሉኝ! አምስት ዓመት ሙሉ በአንድ ሰንሰለት
እኮ ነው ታስረን የነበረው አንተ በአንድ ብረት ታስረን አልነበረም?
‹‹ቁጭ በል» አሉ ዳኛው፡፡
የጠባቂዎች ኃላፊ ኮሽፔል የተባለውን መስካሪ አስገባ፡፡ ይህም ሰው የእድሜ ልክ እስራት የተፈረደበት እስረኛ ሲሆን ኮሽፔል ከብቶችን የሚያግድ ገጠሬ ነበር፡፡ ወደኋላ ግን ከብት ማገዱን ትቶ ወደ ሽፍትነት የተዘዋወረ ሰው ሲሆን ይህ ሰው ሲያዩት ከተከሳሹ ይበልጥ የቂላቂል መልክ ነው
ያለው፡፡ ገና ሲፈጠር ተፈጥሮ ፊትዋን ያዞረችበት፧ የአውሬ መልክ ያለውና እስር ቤት እጣ ርስቱ የሆነ ፍጡር ይመስላል፡፡ ዳኛው ለሌላቹ ያሉትን የተናገሩትን በመድገም እርሱንም ጠየቁት::
«ይህ ከፊትህ የቆመውን ሰው ሳትጠራጠርና ሳታወላውል ትለየዋለህ፤ ታውቀዋለህ?»
«ዣን ቫልዣ ነው» አለ ኮሽፔል፡፡ «ዣን ቫልዣ እያለም ሰዎች
ይጠሩት ነበር፡፡ ጉልበት ያለው ሰው ነው::»
እያንዳንዱ መስካሪ በተናገረ ቁጥር ከዚያ የነበረ ሁሉ ተከሳሸ «ዣን ቫልዣ ነው ወይስ አይደለም» የሚለውን ጥርጣሬ እየተወ ወደ ማመን ደረጃ እየተቃረበ ሄደ፡፡ ሁሉም በየፊናው አጉረመረመ፡፡ መስካሪዎች ተመሳሳይ የሆነ የምስክርነት ቃላቸውን ሲሰጡ ሰው በይበልጥ ተንጫጫ፡፡ ሁሉም በያለበት በሻምፕማቲዩ ላይ ፈረደ:: ኣንድ ምስክር ያለወን ሌላው
እያጠናከረው ሲሄድ ተከሳሹ ጆሮአቸውን ማመን ተስኖአቸው በይበልጥ ፈዘዙ፡፡ የመጀመሪያው ምስክር ቃሉን እንደሰጠ «አያ ግድ የለም፧ ሌላ ምስክር አለ» በማለት እርስ በራሳቸው ሲነጋገሩ ከአጠገባቸው የነበረው
ምስክር ሰማቸው:: የሁለተኛው ምስክር ቃሉን ሲሰጥ ድምፃቸውን ትንሽ ከፍ አድርገው «ይሁና፣ ጥሩ ነው» አለ:: የመጨረሻውና ሶስተኛው ምስክር ቃሉን ሲሰጥ በጣም ጮክ ብለው «በጣም ጎበዝ ሲሉ ተናገሩ፡፡
ዳኛው ወደ ተከሳሹ ፊታቸውን አዞሩ፡፡
«መስካሪዎች ያሉትን ሰምተዋል፤ ታዲያ ምን ይላሉ?
«ምን እላለሁ! ሁሉም ጎበዞች ናቸው!»
ሁሉም በያለበት ተንጫጫ ፤ ሁሉም በየፊናው የግሉን ፍርድ
በመስጠት ይህ ሰው አለቀለት» አለ፡፡
«ፀጥታ እባካችሁ» አሉ ዳኛው፤ «አሁንስ አጠቃልለን የውሳኔ አሳብ
መስጠት ይኖርብናል፡፡»
ዳኞች ከተቀመጡበት አካባቢ ጎርነን ያለ ድምፅ ተሰማ፡፡
«ብሪቬት፣ ሽኔልዲዩና ኮሽጌል እስቲ አንድ ጊዜ ወደዚህ ተመልከቱ፡»
መስካሪዎች ገና ድምፁን ሲሰሙ ክወ አሉ:: በጥፊ የተመቱ መሰላቸው፡፡ ሦስቱም በአንድ ጊዜ ፊታቸውን አዞሩ:: ባለስልጣኖች
ከሚቀመጡበት ወንበር ላይ ተቀምጦ የነበረ አንድ ሰው ተነስቶ ወደ ችሎቱ፡፡መሐል ቀረበ፡፡ የመሐል ዳኛው፣ ሕግ አስከባሪውና ሌሎች አንድ ሃያ
የሚሆኑ ሰዎች ይህ ሰው ማን እንደሆነ አወቁት::
«መሴይ ማንደላይን!»

👍15👎1
በእርግጥ ራሱ ነው:: አሁን ከቆመበት አጠገብ በርቶ የነበረው
መብራት ፊቱን በጉልህ አሳየ:: ቆቡን በእጁ ይዞአል:: ሽክ ብሎ ነው የለበሰው:: የካፖርቱን ቁልፍ አስተካክሎ ቆለፈ:: ፀጉሩ ሸብቷል፡፡ ሁሉም ወደርሱ አፈጠጠ፡፡
የሰውዬው ድምፅ ሁሉንም ሰው አፈዘዘ፡፡ «ምንድነው ነገሩ› እያለ
ሰው ሁሉ ግራ ተጋባ፡፡ ሰውዬው በጣም ረጋ ያለ ሰው ነው፡፡ ይህ ደግሞ እርጋታን የተካነ ከሚመስል ፍጡር እንደዚያ ያለ ሰንጥቆ የሚሄድ ድምፅ ወጣ በማለት ከእዚያ የነበረ ሁሉ ማመን አቃተው፡፡
ዳኛውና ሕግ አስከባሪው ቃል ከመተንፈሳቸውና የጠባቂዎቹ ኃላፊ
«መልሱት» ብለ ትእዛዝ ከመስጠቱ በፊት መሴይ ማንደላይን ፈጠን ብሎ
ምስክሮቹ ወደ ተቀመጡበት ሥፍራ ሄደ::
«ብሪቬት፤ ኮሽፔል፤ ሽኔልዲዩ እኔን አታውቁኝም?» ሲል ጠየቃቸው::
ሦስቱም ፈዘው አዩት:: ጭንቅላቶቻቸወን በማወዛወዝ
አለማወቃቸውን አሳዩት:: ኮሽፔል በጣም ስለፈራ ተነስቶ እጅ ነሳው::
መሴይ ማንደላይን ፊቱን ወደ ዳኞች አዙሮ በለሰለሰ አንደበት ተናገረ፡፡
«የተከበራችሁ ዳኞች፤ ተከሳሹን ልቀቁት:: ክቡርነትዎ እኔን ግን
ያዙት' ብሎ ትእዛዝ ይስጡ:: የምትፈልጉት ዣን ቫልዣ ማለት እኔ ነኝ»::
ቤቱ ፀጥ፣ ረጭ አለ:: አንድ ሰው እንኳን ከተቀመጠበት ተነቃንቆ
ወንበር አላንቋቋም:: እያንዳንዱ ሰው ቤቱ ውስጥ ፍትህ የሰፈነ መሰለው፡፡
የመሐል ዳኛው ፊት በሀዘን ተዋጠ:: ከአቃቤ ሕጉ ጋር ዓይን ለዓይን ተያዩ፡፡ ሕግ አስከባሪው የግራ ቀኝ ዳኞች ጋር ዝግ ባለ ድምፅ ቃላት ተለዋወጠ:: ወደ ተመልካች ዞር ብሎ «ከመካከላችሁ ሐኪም ይገኛል?»
ሲል ጠየቀ፡፡ ሕግ አስከባሪው ቀጠለ፡፡
«የተከበራችሁ ዳኞች፣ አሁን የምንሰማው ነገር በጣም የሚከነክንና የሚረብሽ ነው፡፡ በግል እውቀት ባይሆን በዝና ያሞንቴስ ሱር ሞንቴስ
ከንቲባ መሴይ ማንደላይንን እናውቃቸዋለን፡፡ እባካችሁ በመካከላችን ሐኪም
ካለ ለክብራቸውና ለዝናቸው ስትሉ እርዱዋቸው::»
ሕግ አስከባሪው ንግግሩን እንዲቀጥል መሴይ ማንደላይን እድል አልሰጠውም፡፡ በተረጋጋና ጆሮን በሚስብ ድምዕ ንግግሩን አቋረጠበት::
ከፍርድ ቤቱ ውስጥ የነበረ የዓይን ምስክር የጻፈውንና መሴይ ማንደላይን የተናገሩትን ሙሉ ቃል ቀጥለን ምንም ሳንለውጥ እናቀርበዋለን፡፡ ጸሐፊው
ንግግሩን በጽሑፍ ያሰፈረው ችሎቱ እንደተነሳ ወዲያው ነበር፡፡
«ሕግ አስከባሪውን ከልብ አመሰግናለሁ:: ግን እኔ ሕሊናዬን
አልሳተኩም፡፡ ይህንንም ትንሽ ብትታገስ ራስህ ታየዋለህ:: ስህተት ላይ ልትወድቅ ነበር፡፡ ሰውዬውን ልቀቁት፡፡ እኔ የሚጠበቅብኝን ተግባር
እየፈጸመኩ ነው:: የተከፋው ወንጀለኛ ማለት እኔ ነኝ፡፡ እውነቱን በትክክል ለማየት የቻልኩት እኔ ብቻ ነኝ፡፡ የምናገረው ሁሉ ደግሞ እውነት ነው፡፡አሁን የማደርገው ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ከላይ ሆኖ ያየዋል፡፡ ከመዳፋችሁ
ሥር ስለሆንኩ ልትይዙኝ ትችላላችሁ፡፡ እስከዛሬ ማንነቴን ለመደበቅ በብዙ ዘዴ ተጠቅሜአለሁ፡፡ ስሜን ለወጥኩ፤ ብዙ ሀብት አፈራሁ፤ የአንድ ከተማ
ከንቲባ ሆንኩ:: አሁን ግን ከእውነተኞችና ከታማኞች ጉራ ለመግባት ፈለግሁ፡፡ ይህ ግን በቀላሉ የሚፈጸም ጉዳይ ሆኖ አላገኘሁትም:: ለማንኛውም ልገልጽላችሁ የማልፈቅዳቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ ዝርዝር የሕይወት
ታሪኬን ለመናገር አልፈልግም፡፡ አንድ ቀን እናንተም ትደርሱበታላችሁ።
ከአንድ ጳጳስ ቤት የተከበሩ እቃዎችን ሠርቄአለሁ:: ይህ እውነት ነው።የአንድ ሕፃን ልጅ ገንዘብ ዘርፌኣለሁ:: ይህም እውነት ነው:: ዣን ቫልዣ
ማለት የተረገመ ፍጡር ማለት ነው ያላችሁት ስህተት አይደለም፡፡ ሆኖም ነቀፌታው ሁሉ እንደተባለው ሙለ በሙሉ ትክክል ላይሆን ይችላል፡፡
«ክቡራትና ክቡራን፤ ነገሬን በጥሞና አድምጠኝ፡፡ እንደ እኔ ያለ ዝቅተኛ ፍጡር ፈጣሪን የማምንበት ወይም ለሰው ልጅ ትምህርት የምሰጥበት
ኃይልም ሆነ እውቀት የለኝም፡፡ ነገር ግን የማሳስባችሁ ነገር ቢኖር ከገባሁበት የውርደት ማጥ ለመውጣት ባደረግሁት ጥረት ሳልወድ በግድ ሌሎችን
መጉዳቴ ነው:: ወህኒ ቤት ወርበላዎችን ያፈራል፡፡ ወህኒ ቤት ከመግባቴ በፊት አንድ ያልተማረ ምስኪንና የዋህ ገበሬ ነበርኩ፡፡ ወህኒ ቤት ግን ለወጠኝ:: ሕሊናዬን አደድቦ እቡይ፤ ደንቆሮና ክፉ ሰው አደረገኝ፡፡ ልቡ
ደነደነ፡፡ ስለሕይወት የነበረኝን አመለካከት በዚህ ዓይነት ለውጦ ያደረግሁትን አደረግሁ:: ይህን በማገናዘብ ይቅርታ ታደርጉልኝ ዘንድ እለምናለሁ።
ምናልባት የምናገረው ነገር ላይገባችሁ ይችላል፡፡ ከዛሬ ሰባት ዓመት በፊት ከአንድ ሕፃን ልጅ የነጠቅሁት ስልሳ ሱስ እቤቴ ብትሄዱ አመድ ውስጥ
ታገኙታላችሁ፡፡ ከዚህ ይበልጥ የምለውም የለኝ፤ ያዙኝ፤ እሰሩኝ፡፡»
«ሕግ አስከባሪው እንዴት ነው ራሳቸውን የሚነቀንቁት፡፡ ቀደም ሲል መሴይ ማንደላይን አብዷል' ብለው ነበር፡፡ አሁንም ቢሆን የምለውን የተቀበሉ አልመሰለኝም:: እርግጥ ነው፧ ለማመን ያስቸግራል፡፡ ብቻ በዚያ
ወንጀለኛ የተነሳ አሁን በያዛችሁት ሰው ላይ አትፍረዱ፡፡ ግን እኮ! እነዚህ ሰዎች እኔን አያውቁኝም እንዴ? ዣቬር እዚህ በኖረ! ወዲያው ነበር የሚያስታውሰኝ፡፡»
አሁንም ሁሉም ዝም አለ፡፡
የገለጸው አቀራረብ የሚያፈዝና
የሚያሳዝን እንጂ አስቆጥቶ መልስ ለመስጠት የሚያነሳሳ አልነበረም::ቀደም ሲል አብረውት ወደነበሩ እስረኞች ዞር አለ፡፡
«ታዲያስ ብሪቬት፤ እኔ በሚገባ አስታውስሃለሁ፤ አንተስ ታስታውሰኛለህ?»
ይህን ጥያቄ ጠይቆት ለጥቂት ሰኮንድ መልስ ይሰጠው እንደሆነ
ጠብቆት መልስ ሲያጣ ቀጠለ፡፡
«እስር ቤት ውስጥ የነበሩህን የቼስ ጨዋታ መጫወቻህንና የልብስ መጠቀሚያ እቃ ማንጠልጠያዎችህን ታስታውሳቸዋለህ?»
ብሪቬት እንደመደንገጥ አለ፡፡ ከእግር ጥፍር እስከ ራስ ፀጉር በማጤን አፍጥጦ ከንቲባውን አየው:: መሴይ ማንደላይን ቀጠለ፡፡
«ሺኔልዲዩ፧ የቅጽል ስምህ እንኳን ዝ.………ዲያ ነበር፡፡ ግራ ትከሻህ
ከላይ እስከታች ተቃጥሎ በጣም ጠቋራ ነው:: ኤፍ ፒ ተብሎ የተጻፈብህን ምልክት አጠፋለሁ ብለህ ያቃጠልከው አይደል? ፊደሎቹ ግን አሁንም አሉ አልጠፉልህም:: ተናገር እስቲ፤ ይህ እውነት ነው ወይስ ውሽት?»
«እውነት ነው» አለ ሺኔልዲዩ በዝግታ::
ወደ ኦሽፔል ዞረ፡፡
«ኮሽፔል ግራ እጅህ ላይ ከአንዲት ጠባሳ አጠገብ በሰማያዊ ቀለም
የተጻፈ ቀን አለ አይደል? ይህ ቀን ንጉሡ ኬንስ ከተባለ ሥፍራ የገቡበት ቀን ሲሆን እለቱ ዐ1 ማርች 1815 ዓ.ም ነው:: እስቲ የልብስህን እጅጌ ከፍ
አድርገው:: »
ኮሽፔል የግራ እጅጌውን ጠቀለለ:: በአጠገቡ የነበረ ዓይን ሁሉ ወደ ተገለጠውና::ራቁቱን ወደ ቀረው እጁ ተመለከቱ። የጠባቂዎች ኃላፊ መብራት ይዞ ተጠጋ እንደተባለዉ ልዩ ምልክቱ፡ ቁልጭ ብላ ታየ::
እድለቢሱ ሰው ፊቱን ፈካ አድርጎ ወደ ዳኞቹ ዞረ፡፡ ያን ፊት ያየ
ሁሉ ልቡ ውሃ ይሆንበታል፧ አንጀት የሚበላ ዓይነት አመለካከት ነበር፡፡
«የራስ መውደድ ስሜቴን አሸነፍኩ» ብሎ በአንድ በኩል ደስ ሲለው በሌላ በኩል ደግሞ «በራሴ ላይ መፍረዱና መቀመቅ መውረዴ ነው» በማለት
ተስፋ ሲቆርጥ ይህን በሀዘንና በደስታ መካከል የተመሰቃቀለ አመለካከት ውስጡን ዘልቆ ለማየት ለቻለና ሩህሩህ ልብ ላለው መያዣና መጨበጫ
የሚያሳጣ ነበር፡፡
«አሁን ገባችሁ፤ ዣን ቫልዣ መሆኔን አወቃችሁ አለ::

👍9👏1
መፋጠጥ ብቻ ሆነ፡፡ ዳኞቹ፣ ሕግ አስከባሪው፤ ከሳሾቹና ጠባቂዎች
ሁሉ ስለተወናበዱ ሥራቸውን ዘንግተው ዝም አሉ፡፡ አቃቤ ሕጉ እንኳን ሁኔታውን መከታተል እንደነበረበት ዘነጋ:: የመሐል ዳኛም መሴይ ማንደላይን
የተናገሩትን ከቀረበው ክስ ጋር በማያያዝ ሥነ ሥርዓቱን መምራት
እንደሚገባቸው ረሱ:: ሁለቱም በሀዘኔታ ፈዝዘዋል:: የከሳሸ ጠበቃም ክርክሩ መንገዱን ሲስት መቃወም እንደነበረበት ረስቶ ዝም አለ::
የሚገርመው ከዚያ ከነበረ ማንኛውም ባለሥልጣን ጣልቃ ለመግባት ወይም ጥያቄ ለመጠየቅ የደፈረ አልነበረም:: ሁሉም ግራ ተጋብቶ ቁጭ ብሎአል።
ተፈላጊወ ዣን ቫልዥ ከፊታቸወ: እንደቆመ ግን ማንም
አልተጠራጠረም:: ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት እንደዚያ አወዛጋቢና ድብቅ የነበረው የዣን ቫልዣ ምሥጢር ገሃድ ወጣ፡፡ የእርሱን ጽዋ ሊቀምስ
የነበረውን ሰው ከገደል አፋፍ አውጥቶ ራሱን በማጋለጥ በነገሩ ሁሉም አመኑ፡፡ ያ በጉልህ የቀረበው እውነታ ጥርጣሬንና ዝርዝር ጥያቄን አስወገደ።
«ከዚህ ይበልጥ የፍርድ ቤቱን ሥነ ሥርዓት ማወክ አልፈልግም።
'ይያዝ፤ ይታሠር የሚል ትእዛዝ ስላልተሰጠ መሄዴ ነው:: ማሠሪያ
ያላደረግሁላቸው ብዙ ሥራዎች አሉብኝ:: ሕግ አስከባሪው የት እንደምገኝ ያውቃሉ፡፡ እርሳቸው በፈለጉት ሰዓት ሊያሲዘኝ ይችላሉ:: ››
ይህን እንደተናገረ መሴይ ማንደላይን ወደ በሩ አመራ:: ማንም ደፍሮ ቃል አላሰማም ፧ ማንም ደፍሮ የጦር መሣሪያ አንስቶ ከመሄድ አላገደውም።
አንድ ዓይነት ኃይል በራሱ ላይ እንዲሰፍን ያደረገ ይመስል ሁሉም ወደ ኋላ አፈግፍጎ መንገዱን ለቀቀለት:: ዝግ ብሎ ተራመደ:: በሩን ማን እንደከፈተው
ሳይታወቅ ከበሩ አጠገብ ሲደርስ በሩ ክፍት ሆኖ አገኘው:: ልክ በሩ አጠገብ ሲደርስ ፊቱን አዙሮ፤ «አቃቤ ሕግ! በፈለጉኝ ጊዜ ከመዳፍዎ ስር እሆናለሁ
ካለ በኋላ ከዚያ ሥፍራ ወደ ተሰበሰበ ሕዝብ ዞር ብሎ እንዲህ ሲል ተናገረ
«ወንድሞቼና እህቶቼ፣ አሳዘንኳችሁ መሰለኝ:: አሁን ያደረግሁት በማድረጌ ሰዎች ይቀኑብኛል ብዬ አምናለሁ:: ሆኖም አሁንም ቢሆን የሆነው
ነገር ባይሆን ደስ ይለኝ ነበር::
ከቤቱ፡ ወጥቶ ሄደ:: መልካም ሥራ የማሰሩ ሁለ የሕብረተሰቡን
አድናቆት ስለሚያገኙ እነርሱን የሚያገለግልና የሚረዳ አያጠፋምና በሩ በተከፈተበት ዓይነት ተመልሶ ተዘጋ::
ከዚያም ከአንድ ሰዓት ውይይት በኋላ አባ ሻምፕማቲዩ ከወንጀሉ ነፃ ሆነው ተለቀቀ:: እኚህ ሰው ከፍርድ ቤቱ የወጡት ተወናብደው ነው::ከዚያ የነበሩ ሁሉ እብዶች መሰልዋቸው:: በእለቱ የሆነው ነገር አንዱም ሳይገባቸው ነበር የሄዱት::.....

❤16👍13
#ጌትዬ
አመመኝ
ከመውደቄ ብዛት ፣ መነሣት ደከመኝ፤
አትመርምረኝ
ማረኝ፤
ምራኝ፤
ጥራኝ፤
ለዓለም አልሆንኩም ፣ ለዓለሞህ ሥራኝ፤
ኝ የማበዛብህ
ኝ የምጠራብህ
እኝኝ ያለ ዘመነ ነፍሴን ቢያደክሞብህ፤
ብትጠራኝ ብዬ
ጠራሁህ ጌታዬ፤
እስቲ ወዬ በላኝ
አንተን ዘነጋሁኝ ሰው እየደለለኝ ቦታህን
ሲወርሰው፤ተአብየና እብሪት ራሴን
ስለኩስ ፤ በገሃነብ ክብሪት
ስነድ እያየከኝ
ዝም ለምንድን አልከኝ?
ይኸው ስንት ኖርን?
ይኸው ስንት አኖርን?
ስለኖርን ምን አመጣን?
ከምላስ ቤት መቼ ወጣን?
ላንተ እንለው አጣን፤
ቁጣው ተውና ፣ በቁንጥጫ ቅጣን፤
አባትም አይደለህ ጨክነህ አትጨክን
እናትም አይደለህ ፣ ፍቅር አታባክን፤
ልክ ነህ ትክክል
ካንተ ሌላ ክልክል፤
ፍጹም ነው ዐመልህ፤
አንተን ምን ሊያክልህ፤
አንተን ማን ሊያክልህ፤
አንደ መስመር ኑሮ፣
ሲቸከቸክ ዞሮ
ቃል እየደገመ፧
ሥጋ እየታመመ፤
ነፍስ እየጠመመ፤
ሐቅ እየዘመመ፤
ቀን ከተበላሸ
ነገ ተኮላሸ፤
የከበቡ ሁሉ፤
ወዳጅ ተባባሉ፤
እኔስ ለብቻዬ፤
መጮኸ ነው ጌታዬ፤
እዬዬ ... እዬዬ
ጀማ ሁነኝ ብዬ፤
አሁንስ ደከመኝ፤
እዚህ እውነት የለም ፤ አንተጋር አስቅመኝ፤
አትመርምረኝ፤
ማረኝ፤
ምራኝ፤
ጥራኝ፤
ለዓለም አልሆንኩሞ፣ ለዓለምህ ሥራኝ፤
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
አመመኝ
ከመውደቄ ብዛት ፣ መነሣት ደከመኝ፤
አትመርምረኝ
ማረኝ፤
ምራኝ፤
ጥራኝ፤
ለዓለም አልሆንኩም ፣ ለዓለሞህ ሥራኝ፤
ኝ የማበዛብህ
ኝ የምጠራብህ
እኝኝ ያለ ዘመነ ነፍሴን ቢያደክሞብህ፤
ብትጠራኝ ብዬ
ጠራሁህ ጌታዬ፤
እስቲ ወዬ በላኝ
አንተን ዘነጋሁኝ ሰው እየደለለኝ ቦታህን
ሲወርሰው፤ተአብየና እብሪት ራሴን
ስለኩስ ፤ በገሃነብ ክብሪት
ስነድ እያየከኝ
ዝም ለምንድን አልከኝ?
ይኸው ስንት ኖርን?
ይኸው ስንት አኖርን?
ስለኖርን ምን አመጣን?
ከምላስ ቤት መቼ ወጣን?
ላንተ እንለው አጣን፤
ቁጣው ተውና ፣ በቁንጥጫ ቅጣን፤
አባትም አይደለህ ጨክነህ አትጨክን
እናትም አይደለህ ፣ ፍቅር አታባክን፤
ልክ ነህ ትክክል
ካንተ ሌላ ክልክል፤
ፍጹም ነው ዐመልህ፤
አንተን ምን ሊያክልህ፤
አንተን ማን ሊያክልህ፤
አንደ መስመር ኑሮ፣
ሲቸከቸክ ዞሮ
ቃል እየደገመ፧
ሥጋ እየታመመ፤
ነፍስ እየጠመመ፤
ሐቅ እየዘመመ፤
ቀን ከተበላሸ
ነገ ተኮላሸ፤
የከበቡ ሁሉ፤
ወዳጅ ተባባሉ፤
እኔስ ለብቻዬ፤
መጮኸ ነው ጌታዬ፤
እዬዬ ... እዬዬ
ጀማ ሁነኝ ብዬ፤
አሁንስ ደከመኝ፤
እዚህ እውነት የለም ፤ አንተጋር አስቅመኝ፤
አትመርምረኝ፤
ማረኝ፤
ምራኝ፤
ጥራኝ፤
ለዓለም አልሆንኩሞ፣ ለዓለምህ ሥራኝ፤
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
❤19👍13👏2🤔1
#ምንዱባን
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስድስት
፡
፡
#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ
አጸፋ
ምሽቱ አልቆ ሊነጋጋ ስለነበር የምሥራቅ ፀሐይ ውጋጋን ታየ፡
ፋንቲን በኃይል እያተኮሳትና እንቅልፍ ሳይወስዳት ነበር ያደረችው::አስታማሚዋ ሴር የፋንቲንን ሁኔታ በማየት መድኃኒት ለመፈለግ ሄዱ፡፡መድኃኒቱን እየፈለጉ ሳለ ዞር ሲሉ መሴይ ማንደላይንን በድንገት
በማየታቸው ሳያስቡት ይጮሃሉ:: መሴይ ማንደላይን እርሳቸው ከነበሩበት ክፍል ገና መግባቱ ነበር፡፡
«መጡ እንዴ ጌታዩ!» አሉ፡፡
«ያቺ ምስኪን እንዴት ናት?
«አሁን ትንሽ መለስ ብሉላታል:: በጣም ሲያማት ጊዚ ተጨንቀን
ነበር፡፡ ፋንቲን ግን ክቡር ከንቲባ ከዚህ የጠፉት ልጄን ሊያመጡ ቢሄዱ ነው ብላ በማመንዋ ነው መለስ ያለላት በማለት ለመሴይ ማንደላይን ሴርዋ አስረዱ:: ሴርዋ ምንም እንኳን ወደ ልጅትዋ አለመሄዱን ቢያውቁም ጥያቄ
መጠየቅ ኣልደፈሩም::
“ደህና ናታ!›› አለ፡፡
“ታዲያ አሁን ልጅዋን እለማምጣትዎን እንዴት እድርገን ነውዐየምንነግራት? » ሲሉ ሴርዋ ጠየቁ፡፡
ጥቂት አሰበና «እሱ ይመራናል» አላቸው::
ግን መዋሸት የለብንም» አሉ ሴርዋ በዝግታ፡
መስኮት ስለተከፈተ የመሴይ ማደላይን ገጽታ በጉልህ ታየ
«እንዴ፣ ምን ሆነዋል!» አሉ አስታማሚዋ:: (ገጸዎ በጣም
ተለዋውጧል::»
«ተለዋውጧል!» አለ፡፡
መስታወት አነሱ:: እርሱም መስታወቱን ተቀብለ መልኩን ከየ::
«እውነትም ተለዋውጫለሁ!» ሲል አረጋገጠ፡: ግን ይህን ያለው
አሳቡ ለሁለት ተከፍሎ እንደሆነ ያስታውቅበት ነበር::
ሴርዋ አነጋገሩና ጠቅላላ ሁኔታውን ሲያዩ ቀፈፋቸው:: መሴይዐማንደላይን ሊከፍተው ሲል አልከፈት ስላለህ በር አስተያየት እየሰጠ
ፋንቲን ከነበረችበት ክፍል ገባ፡፡ የመስኮት መጋረጃዎችን ገለጠ፡፡ ወደ ፋንቲን ጠጋ ብሎ አያት፡፡ እንቅልፍ ወስዷት ነበር፡፡ ስትተነፍስ እያቃሰተች ነው:: ፊትዋ ፍም መስሎአል፡፡ ቆዳዋም ገርጥቶአል::
መሴይ ማንደላይን ሳይነቃነቅ ከአልጋዋ አጠገብ ቆሞ አተኩሮ
ተመለከታት፡፡ አንዴ ወደ እርሱ አንዴ ደግሞ ከግድግዳ ላይ ተሰቅሎ ወደ ነበረውና ክርስቶስ ወደ ተሰቀለበት መስቀል ተመለከተ፡፡ ከሁለት ወር
በፊት ፋንቲን አሞአት ከዚያች ክፍል ውስጥ ስትተኛ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊጠይቃት ሲሄድ እንቅልፍ ወስዷት እንደተመለከታት ዓይነት ነበር አሁንም ያያት:: አሁንም እንደዚያኑ እለት እርሱ ሊጸልይላት እርስዋ እንቅልፍ ወስዷት ተኝታለች:: ልዩነቱ ከሁለት ወር በኋላ የእርስዋ ፀጉር በይበልጥ
ሽበት ጣል ጣል ሲያደርግበት የእርሱ ፀጉር በሽበት ተሸፍኖ ነጭ ሆኖአል።
ሴርዋ አብረው ወደ ክፍሉ አልገቡም:: ሰውዬው በአንድ እጁ
ከንፈሮቹን ይዞ ነው የቆመው:: ፋንቲን ዓይኖችዋን ስትገልጥ አየችው::
ፈገግ ብላ፡
«ኮዜትስ?» ስትል ጠየቀችው::
«ኮዜትስ» ብላ ስትጠይቀው ልክ ይዞአት እንደመጣ አረጋግጣ በማመን ስለነበር ምን ብሎ እንደሚመልስላት ባለማወቁ ዝም ብሉ ተገትሮ ቀረ።
ይህን ጊዜ እርስዋ ንግግርዋን ቀጠለች፡፡
«ልጄ ጋ እንደሄዱ ተስፋ አደርጋለሁ:: እንቅልፍ ወስዶኝ ነበር፤ ግን አይቼዎታለሁ:: ብዙ ጊዜ አይቼዎታለሁ:: ሌሊቱን በሙሉ ዓይኔ እርስዎ
ተከትሎ ነው የሄደው:: መላዕክትም እርስዎን ተከትለው ሲሄዱ ነበር ግርማ ሞገስዎ ደግሞ በጣም... በጣም ደስ ነበር የሚለው፡፡
ቀና ብሎ ከሴትዮዋ ራስጌ የተንጠለጠለውን መስቀል አየ፡፡
‹ግን ንገሩኝ እስቲ፣ ኮዜት የት አለች? ከእንቅልፌ ስነቃ እንዳያት
ለምንድነው ከአጠገቤ ያላስተኛችሁዋት?»
ሳያስበው በድንገት አንድ ነገር ተናገረ፡፡ ደግነቱ ምን እንዳለ በትክክል ሳይሰማ ሐኪሙ በር ከፍተው ገቡ::
«የእኔ ልጅ» አሉ፤ «ረጋ በይ! ልጅሽ መጥታለች፡፡»
የፋንቲን ዓይን እንደ ብርሃን በራ:: በደስታ ብዛት መላ ሰውነትዋ
ተቅበጠበጠ፡፡ እጇን በኃይል አሻሸችው::
«ወይ ልጄ! አምጡልኝ ልያት?» ስትል ጠየቀች፡፡
ያኔ እንደተወቻትና እሽሩሩ እንደምትባል ፉልቁ ሕፃን እንደሆነች አድርጋ በመገመት ልታቅፋትና እሽሩሩ ልትላት ፈለገች::
«አትቸኩይ» አሉ ሐኪሙ፤ «ሰውነትሽ እንደዚህ ደክሞ ከእርስዋ ጋር መጫወት አትችይም፡፡ ከልጅሽ ጋር አሁን በድንገት ብትገናኙ ሲቃ
ይዞሽ ክፉ ነገር ላይ ሊጥልሽ ስለሚችል ትንሽ ብትታገሽ፡፡ መጀመሪያ እኛ አንቺን በቅጡ ማዳን አለብን፡፡
መሴይ ማንደላይን ከአልጋው አጠገብ ወንበር ላይ ተቀምጦአል፡፡
ፋንቲን ወደ እርሱ ዞር ብላ «ግሩም ድንቅን ኣለች:: ስታየው መንፈስዋን
በጣም አረጋግታ ስለነበር ምናልባት «አሁንስ ተሽሉአታል፤ ልጅዋን ብታይ ምንም አትሆንም» ብሎ ያስባል ብላ ከእርሱ ጋር ጨዋታ ቀጥላ በጥያቄ
አጣደፈችው::
«ታዲያ መንገዱ ደህና ነበር? እንዴት የተባረኩ ሰው ቢሆኑ ነው
ለልጄ ብለው ከእዚያ ድረስ መልፋትዎ? መቼም እኔን እንኳን ሳትረሳኝ አትቀርም:: ልጆቹ እኮ ቀላል ፍጡሮች አይደሉም:: የለበሰቻቸው ልብሶች ንጽህናቸው የተጠበቀ ነው? እነሚስተርና ሚስስ ቴናድዬ በንጽህና ነበር
የያዝዋት? ሰውነትዋስ እንዴት ነው? እንዴት ነው የናፈቀችኝ! ቆንጆ ልጅ አይደለችም ክቡር ከንቲባ? በጨለማ ስትጓዘ መንገድ ላይ እኮ ብርድ ሳይጉዳችሁ አልቀረም:: አንድ ጊዜ ብቻ እንዳያት ለአንድ አፍታ ልታስጉቡዋት አትችሉም? ወዲያው ትሄዳለች፡፡ የቤቱ ጌታ- እርስዎ ኖት ፤ ታዲያ ይህን
አይፈቅዱልኝም? መሴይ ማንደላይን እጅዋን ያዘ፡፡ «ኮዜት በጣም ቆንጆ ናት» አለ:
“ጤነኛ ናት ፤ አትቆዩም ፤ ታያታላሽ:: አሁን ግን ብዙ አትናገሪ ! ይደክምሻል:: ደግሞም ሳልሽ እንዳይቀሰቀስ አትገለጭ::
እርሱ ይህን እንዳለ በሃይል አሳላት:: እጅዋን እንደያ፤ በጭንቀት ዓይን ተመለከታት:: አባበ የደረሰበትን ሊነግሪ ት ነበር፡፡ ግን በዚህ ሁኔታ እንዴት ብሎ ይንገራት! ሐኪሙ ካያት በኋላ ወጥቶ ሄደ:: ሰርዋ ከክፍሉ ውስጥ አብራቸው ቆዩ:: ሁሉም ዝም፣ ዝም ተባብለው ነበር
ፋንቲን በድንገት ጮኸች::
«ድምፅዋን ሰማሁት፤ ወይኔ ልጄ! ድምፅዋን ሰማሁት!»
በአካባቢው የጎረቤት ልጅ ነበረች፡፡ ያጋጣሚ ነገር ይህች ልጅ፤ብቻዋን እያወራች ትሮጣለች:: ትምህርት ቤት የተማረችውን ዘፈን እያዜመች
ነበር የምትሮጠው:: ፋንቲን የሰማችው የዚህችን ልጅ ድምፅ ነበር፡፡
«ውይ. ይ፧ የእኔይቱ ኮዜት እኮ ናት! ድምፅዋንኮ አውቀዋለሁ
አለች::
የልጅትዋ ድምፅ እየራቀ ሄደ:: ድምፆዋ ቢርቅም ፋንቲን ለመስማት ሞከረች:: ድምፁ ጨርሶ ሲጠፋ ጥላ የተጠለለባት መሰላት፡፡ «ምን የተረገሙ
ሐኪም ናቸው፤ ልጄን እንዳላይ የሚከለክሉኝ» አለች በማጉረምረም።
ሆኖም ውስጥ ውስጧን ደስ ብሎአታል፡፡ ትራስዋን በእጅዋ አቅፋ ይዛ እርስ በራስዋ መነጋገርዋን ቀጠለች፡፡ «እንዴት ደስ ብሎኝ ነው የምኖረው
የአትክልት ቦታ ይኖረኛል፡፡ መሴይ ማንደላይን እንደሚሰጡኝ ቃል ገብተውልኛል፡፡ ልጄ ከሳሩ ላይ እየፈነደቀች ትጫወታለች፡፡ ከዚያ ቁጭ ብለን ደግሞ
«ተረት ተረት» እያልን እንጫወታለን፡፡ ኮዜት ቢራቢሮ ለመያዝ ስትሮጥ እኔ ቁጭ ብዬ አያታለሁ፡፡ ታዲያ ይሄ መቼ ይሆን የሚሆነው?»
በጣቶችዋ መቁጠር ጀመረች:: «አንድ፣ ሁለት፣ ሦስት፣ አራት፡፡
ሰባት ዓመት ይሆናታል ማለት ነው:: ከአምስት ዓመት በኋላ እኮ አንገትዋን መስበር ትጀምራለች:: ያኔማ እህትዋ ናት ነው የምትባለው::»
በአሳብዋ ተገርማ መሳቅ ጀመረች፡፡

👍17
መሴይ ማንደላይን የፋንቲንን እጅ ለቀቀ:: የሚነፍስ ነፋስን እንደሚሰማ ሰው ፋንቲን የተናገረችውን አቀርቅሮ አዳመጠ፡፡ ፋንቲን በድንገት ንግግርዋን አቆመች፡፡ ቀና ብላ አካባቢዋን ቃኘች:: ሰውነትዋ በፍርሃት ተንቀጠቀጠ፡፡
ከዚያ በኋላ ቃል አልተነፈሰችም:: ከተኛችበት አልጋ ቀና አለች።
ከደረትዋ በላይ ራቁትዋን ሆነች:: ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት እንደዚያ ልብ ዘርታ ትጫወት የነበረችው ሴትዮ አሁን በድንገት ተለዋወጣ ዝልፍልፍ አለች::
«ያንተ ያለህ! ምነው ፋንቲን፤ ምን ነካሽ?» ሲል መሴይ ማንደላይን
ጠየቃት::
መልስ አልሰጠችውም:: አፍጥጣ ትመለከትበት ከነበረው አቅጣጫ
ዓይንዋን አላዞረችም:: በአንድ እጅዋ የመሴይ ማንደላይንን እጅ ጨብጣ በሌላው እጅዋ ወደኋላው እንዲያይ አመለከተችው::
ፊቱን አዞረ:: ዣቬርን ከዚያ ቆሞ አየው::....

❤9👍2
#ምንዱባን
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሰባት
፡
፡
#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ
....ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት እንደዚያ ልብ ዘርታ ትጫወት የነበረችው ሴትዮ አሁን በድንገት ተለዋወጣ ዝልፍልፍ አለች::

ፊቱን አዞረ:: ገናቬርን ከዚያ ቆሞ አየው::
ከዚያ በኋላ ምን እንደሆነ እንመልከት::
በጣም ከመሸ ነበር መሴይ ማንደላይን ፍርድ ቤቱን ለቅቆ የወጣው::ወዲያው እንደወጣ ከበራፍ ይጠብቀው በነበረው ሠረገላ በቀጥታ ወደ ቤቱ
ተመለሰ፡፡ ሊነጋጋ ሲል ነበር ሞንቴስ ሰር ሞንቴስ ከተባለ ሥፍራ የደረሰው::ከዚያም እንደደረሰ ለመሴይ ላፌት ደብዳቤ ከላከ በኋላ ነበር ፋንቲንን
ለመጠየቅ ወደ ተኛችበት ክፍል የሄደው::
ፍርድ ቤቱ ሻምፕማቲዩን በነፃ ካሰናበተ በኋላ ሕግ አስከባሪውና
ዳኞቹ ተመካከሩ፡፡ የተመካከሩት መሴይ ማንደላይንን ያሳሰሩት ወይም አያሳስሩት እንደሆነ ነበር፡፡ መታሰር እንዳለበት ወስነው በአለበት እንዲያዝ ትእዛዝ ሰጡ፡፡ ሕግ አስከባሪው በአስቸኳይ ወደ ከተማው ፖሊስ አዛዥ
ወደ ዣቬር ወዲያውኑ መልክተኛ ልኮ ከንቲባውን እንዲይዝ ትእዛዝ
አስተላለፈለት::
ዣቬር ጠዋት ከእንቅልፉ ሲነሳ መልእክተኛው ደርሶ ትእዛዙን
ሰጠው:: መልእክተኛው የፖሊስ አባል ሲሆን ይህም መለዮ ለባሽ ፍርድ ቤቱ ውስጥ ምን እንደተከሰተ ለዣቬር ባጭሩ አስረዳው::
የትእዛዙ ፍሬ አሳብ «የሞንቴስ ሱር ሞንቴስ ከንቲባ መሴይ ማንደላይን ከእስር ቤት ያመለጠው ዣን ቫልዣ መሆኑ ስለታወቀ የፖሊሱ ኣዛዥ
በቁጥጥር ስር እንዲያውለው ፍርድ ቤቱ አዟል» የሚል ነበር፡፡
ዣቬር አንድ የአስር አለቃና አራት ወታደሮችን አስከትሎ ከከንቲባው
ቤት ሄደ:: መሴይ ማንደላይን ፋንቲን ከነበረችበት ክፍል መሆኑን ጠይቆ ከተረዳ በኋላ በቀጥታ ወደዚያ ሄዶ በሩ ላይ ተሰክቶ በነበረው ቁልፍ በሩን ቀስ ብሎ ከፍቶ ገባ፡፡
እንደ እውነቱ ከሆነ በሩን ከፈተው እንጂ ወደ ውስጥ ለመግባት
አልደፈረም:: ካፖርቱን እስከ አንገቱ ግጥም አድርጎ ቆልፎ ቆቡን አጥልቆአል፡፡ወደ ክፍሉ ያስገባው መላ ሰውነቱን ሳይሆን አንገቱን ብቻ ነበር፡፡ ሆኖም
በሩ ስለተከፈተ ማን እንደሆነ በግልጽ ይታያል፡፡ እንደዚያ ሆኖ ምናልባት ለአንድ ደቂቃ ያህል ዝም ብሎ ቆሞ ይሆናል:: ይሄኔ ነው ፋንቲን አይታው
ለመሴይ ማንደላይን የጠቆመችው፡፡ ሁለቱ ተያዩ:: ዣቬር አልተነቃነቀም:: ያ ግዙፍ ሰውነቱ እንኳን ካፖርት ደርቦበት እንዲሁም ይከብዳል፡፡ ፊቱን አጠቋቁሮ ፧ ጥርሱን አግጥጦና
ዓይኑን አፍጥጦ «አገኘሁህ» በማለት ሲያይ በጣም ያስፈራል፡፡
በመጨረሻ ዣን ቫልዣን በመያዙ አካሉ ውስጥ የነበረው ያንን ሰው
አሳድዶ የመያዝ ጽኑ ፍላጎትና ምኞት ተጎልጉሎ ወጥቶ ገጹ ላይ ታየ:: «ዛሬስ ድል መታሁ» የሚለው ደስታው ደግሞ ከዚያች ከጠባብ ግምባሩ ላይ በጉልህ ወጣ፡፡
ዣቬር በዚያች ቅጽበት መንግሥተ ሰማይ ገብቷል፡፡ የዣቬርን
ቁመናና ሁኔታ ረስተን የዘወትር ፍላጎቱና ምኞቱ ምን እንደሆነ ብናጤን «ትክክለኛ ፍርድ ፤ እውነትና ብርሃን የክፉ ሥራ አጥፊዎች ናቸው የሚል ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ እነዚህም የሕግ፣ የሥልጣን፣ የሕሊናና
የመሳሰሉት የበቀል መሣሪያዎች ናቸው፡፡ ከዚያ ክፍል ውስጥ ቆሞ : የሚታየው ይህን ለማስፈጸም ነበር፡፡ በእርሱ ዓይን ርህራሄ፣ ፍርሃትና ይሉኝታ የሕግ ጠላቶችና የትክክለኛ ፍርድ እንቅፋቶች ሲሆኑ ይህ ሰው
ፍርድን ላለማዛባት ምንም ነገር ያደርጋል፡፡ የዘወትር እምነቱ ከህብረተሰብ መካከል ቅጥፈት፣ ተንኮልና ወንጀል ጨርሶ ማስወገድ ሲሆን ይህን
ከማስፈጸም ወደኋላ ስለማይል «የነገሮች መነሻዎች ምንድናቸው» የሚል አስተያየት አያውቅም:: ዓላማውና ምኞቱ ሕግን ማስከበር ነው:: ይህ
እምነቱ ነው ፊቱ ላይ እየታየ ገና ሲመለከቱት የሚዋጋ በሬ ያስመሰለው።
መሴይ ማንደላይን ከመንጋጋው ፈልቅቆ ካወጣት ወዲህ ፋንቲን
ዣቬርን አላየችውም፡፡ ስለዚህ በጠዋት የመጣው እርስዋን ለመያዝ እንጂ ለሌላ ነገር ነው ብላ አልገመተችም:: ፊቱ ያስጠላታል፡፡ የእርሱን ፊት
ለረጅም ጊዜ ካየች ሞትዋ የተቃረበ ይመስላታል:: ስለዚህ ፊትዋን በእጅዋ ሽፈነችው::
«መሴይ ማንደላይን ያድኑኝ፧ ከዚህ ጉድ ያወጡኝ» ስትል ጮኸች፡፡
«አይዞሽ፣ አንቺን ሳይሆን እኔን ፍለጋ ነው የመጣው::»
ከዚያም ወደ ዣቬር ዞር ብሎ «ምን እንደምትፈልግ አውቃለሁ
አለው::
ዣቬር «ፈጠን በል» ሲል መለሰ፡፡
ዣቬር ይህን ሲናገር ከቆመበት አልተነቃነቀም:: ግን ዘወትር
የጠላቸውን በሚያይበት ዓይን ነበር ዣን ቫልዣን ያየው:: ከሁለት ወር በፊት ፋንቲንን ያያት ልክ እንዳሁኑ አጥንት ሰርስሮ በሚገባ ዓይነት አስተያየተ ነበር፡፡ ለዚህ ነው አሁንም የፈራችውና «አድነኝ ብላ» የጮኸችው::
ዣቬር እንድ እርምጃ ወደፊት ተራመደ::
«እንሂድ፣ ምነው ወደኋላ!» ሲል ጠየቀ፡፡ ያቺ የተከፋች ሴት ኣካባቢዋን ቃኘች፡፡ ከክፍሉ ውስጥ የነበሩት ሴርዋና ከንቲባው መሆናቸውን ተገነዘበች፡፡
ይህ ሰው የመጣው «እኔን ሊወስድ እንጂ ለሌላ ሰው አልመጣም» ብላ ስለደመደመች ሰውነትዋ ተንቀጠቀጠ፡፡ ሆኖም ወዲያው ጨርሶ የማይታሰብ
ነገር አየች:: ያየችው ነገር በእውን ሳይሆን በቅዠት እንኳን ሊታያት
የማይችል እንደሆነ ገመተች::
የፖሊሶ አዛኝዥ ዣቬር የመሴይ ማንደላይንን ማንቁርት ይዞ ሲጎትትና መሴይ ማንደላይን አንገቱን ሲደፋ ተመለከተች:: ዓለም ከፊትዋ የተደፋ
መሰላት::
ዣቬር ሰላሣ ሁለት ጥርሶቹን በመሉ እያሳየ ከት ብሎ ሳቀ::
«የእኛ ከንቲባ!» በማለት በይበልጥ አንቆ ያዘው::
መሴይ ማንደላይን አንገቱን ለማስለቀቅ አልሞከረም፡፡ ግን «ዣቬር» ሲል ተናገረ::
ዣቬር ጣልቃ በመግባት አቋረጠው:: ክቡር የፖሊስ አዛዥ ብለህ ጥራኝ» አለው::
«ክቡር» አለ ዣን ቫልዣ ፧ ብቻችንን ብንሆን አንድ የምጠይቅህ ነገር
ነበረኝ::
«ጮክ በል፣ ድምፅህን ከፍ ኣድርገህ ተናገር:: ሰዎች እኔን ሲያናግሩ ጮክ እያሉ ነው የሚያነጋግሩኝ» አለ ዣቬር፡፡
ድምፁን ዝቅ አድርጎ ዣን ቫልዣ ንግግሩን ቀጠለ::
«አንተን በግል የምለምንህ ጉዳይ አለኝ፡፡››
‹‹ጮክ ብለህ ተናገር ብዬህ እኮ ነበር፡፡»
«ግን የምነግርህ ነገር እኔና አንተ እንጂ ሌላ ሰው መስማት ስለሌለበት ነው::
“ጉዳዩ መሰለህ፤ በአንተ ጉዳይ እኔን ምን አስጨነቀኝ፣ አልሰማም::
ዣን ቫልዣ ጠጋ ብሎ በችኮላ አሁንም ድምፁን ዝቅ እድርጎ
የሚከተለውን ተናገረ::
« ሦስት ቀን ብቻ ስጠኝ! የዚህች የተከፋች ሴት ልጅ ሄጄ ላምጣላት::የሚያስፈልገውን ወጪ በሙሉ እኔ እከፍላለሁ:: ከፈለግክ አብረን ልንሄድ እንችላለን፡፡
«በእኔ ላይ ነው የምታሾፈው» አለ ዣቬር፡፡ «እስከዚህ ሞኝ
አትመሰለኝም ነበር:: ሦስት ቀን ስጠኝና የዚህችን ሴት ልጅ ላምጣ' ትለኛለህ:: በጣም ታስቃለህ፡፡»
የፋንቲን ሰውነት ተንቀጠቀጠ፡፡
«ልጄን» ስትል ጮኸች፡፡ «ልጄ ዘንድ ሊሄዱ ነዋ! ወይኔ ልጄ፧
አልመጣችም ማለት ነዋ! ሲስተር ይንገሩኝ፤ ልጄ የት ናት? መሴይ
ማንደላይን፤ ክቡር ከንቲባ ልጄን እፈልጋታለሁ!»
ዣቬር ከፍተኛ ድምፅ በማሰማት መሬቱን በጫማው ረገጠው::

👍18
«ይህቺ ደግሞ ምን ትለፈልፋለች፧ አፍሽን ዝጊ፡፡ ይህች የተረገመች
አገር ገና ብዙ ታሳየናለች:: ይገርማል! ከእስር ቤት ያመለጡ ሽፍቶች የሚዳኙበት፧ ሸርሙጦች እንደ ልዕልት የሚንቀባረሩበት አገር! ይህ ሁሉ ይለወጣል፣ እንዳለ አይቆይም፣ የጊዜ ጉዳይ ነው:: ፋንቲንን አፍጥጦ እያየ የዣን ቫልዣን ክራባትና ኮሌታዎች በይበልጥ አጥብቆ ያዘ፡፡
«ከአሁን ወዲያ ክበር ከንቲባ ወይም መሴይ ማንደላይን የሚባል ሰው የለም:: ይህ ከእጄ የገባው ፍጡር ዣን ቫልዣ የተባለ ሌባ፣ ቀጣፊና ሽፍታ ነው:: ከአሁን በኋላ እንደለመደው አያመልጠኝም፤ አግኝቼዋለሁ፡፡»
ፋንቲን ወገብዋን በሁለት እጆችዋ ደግፋ ቀና ኣለች:: ዣን ቫልዣን
ኣየችው፡፡ ከዚያም ዣቬርን ተመለከተች፡፡ ቀጥላም ዓይንዋን ሴርዋ ላይ ተከለች፡፡ ለመናገር እንደፈለገ ሰው ኣፍዋን ከፈተች:: ንግግር አይሉት ማጉረምረም ቃል ከአፍዋ ወጣ፡፡ ጥርሶችዋ እንደገጠሙ ናቸው:: የደከሙ
እጆችዋን ዘረጋች፡፡ ግን ቀስ እያለ ባህር ውስጥ እየሰጠመ እንደሚሄድ ሰውነት ዝግ እያለች ከትራሱ ላይ ዘፍ አለች፡፡ የአልጋው ድጋፍ ጭንቅላትዋን መታት:: በጀርባዋ ከአልጋው ላይ ተደፋች:: አፍዋ አረፋ ደፈቀ፡፡ ዓይንዋ
ፈጥጦ ቀረ፡፡ ነፍስዋ ከሥጋዋ ተለየች::
ዣን ቫልዣ አንቀው ከያዙት የዣቬር እጆች ላይ እጆቹን እሳረፈ።እንደ ሕፃን ልጅ እጆች በቀላሉ በማስለቀቅ ከለበሳቸው ልብሶች ኮሌታ የዣዜርን እጆች አላቀቀ፡፡ ከዚያም ይህችን ሴት ገደልካት» ሲል ጮህበት፡፡
"ገደልካት ኣልክ!!» ብሎ በማንጓጠጥና በንዴት ተናገረ:: «እኔ ያንተን ልፍለፋ ለመስማት አልመጣሁም:: ወታደሮች ከምድር ቤት ይጠብቁኛ
ከቤቱ ጥግ ትልቅ የብረት ዱላ ተቀምጦ ነበር፡: ዣን ቫልዣ ትልቁን
የብረት ዱላ አነሳ፡፡ ዣቬር ወደ በሩ ሽሸ፡፡ ዣን ቫልዣ ዱላውን እንደ ያዘ ወደ ፋንቲን ሄደ:: ከዚያም በቀላሉ በማያስማና በጣም ዝግ ባለ ድምፅ ዣቬርን እያየ ተናገረ::
«አሁን ባትረብሸን ይሻልሃል፡፡»
የፖሊሱ የዣቬር ሰውነት በእርግጥ ነፋስ እንደሚያወዛውዘው ቅጠል
ተንቀጠቀጠ፡፡ ወታደሮቹን ለመጥራት ፈለገ:: ግን ዣን ቫልዣ በእድሉ የሚጠቅም መሰለው:: ስለዚህ የበሩን መቃን ተደግፎ ዓይኑን ከገዣን ቫልዣ
ሳያነሳ ከነበረበት ቆሞ ቀረ::
ዣን ቫልዣን ይዞት በነበረው የብረት ዱላ ክርኑን አስደግፎና ግንባሩን በእጆቹ ይዞ በድንዋን ፋንቲን አፍጥጦ ተመለከታት:: ቃል ሳይተነፍስ እንደዚያ ሆኖ በተመስጥኦ ለረጅም ጊዜ ቆየ:: ባይናገርም ለፋንቲን ምን
ያህል እንዳዘነ መላ ዕውነቱ ይመሰክራል፡፡
በተመስጥኦ ሕሊናውን ረስቶ ከቆየ በኋላ ረጋና ዝቅ ባለ ድምፅ ወደ ጆሮዋ ጠጋ ብሎ በማንሾካሾክ ፋንቲንን አናገራት::
ምን አላት? ይህ የተፈረደበት ወንጀለኛ በሞት ከዚህ ዓለም ለተለየች ሴት ምንስ ሊል ይችላል? የተናገራቸው ቃላት ምን ነበሩ? ማንም አልሰማም፤
አላወቀምም:: ሟችዋ ፋንቲን ሰምታው ይሆን? ማን ያውቃል?
ዣን ቫልዣ የፋንቲንን ጭንቅላት በሁለት እጆቹ ይዞ ከትራስ ላይ
አስተካክሎ አስተኛው:: ሲያስተኛው አያያዙ ልክ አንዲት እናት ልጅዋን በጥንቃቄ እንደምታስተኛ ዓይነት ነበር፡፡ የለበሰችውን ፒጃማ አስተካከለ
በኋላ ከአንገትዋ ላይ የነበረውን ማሰሪያ አጥብቆ አሰረላት:: ከዚያም ግንባርዋን በፀጉርዋ ሸፈነው:: ሞት ወደ ታላቅ ብርሃን የሚወስድ ጕዳና ስለሆነ አተኩሮ ሲመለከታት ፊትዋ የሚያበራ መሰለው::
የፋንቲን እጆች ከአልጋው ግራና ቀኝ ተንጠልጥለሆኑ ነበር ዣን
ቫልዣ ተንበርክኮ አንድ እጅዋን ቀስ አድርጎ አንስቶ ሳመው ከዚያም ከአልጋው ላይ አሳረፈው:: ቀጥሉ ብድግ ብሎ በመነሳት ዣቬርን አየው
«አሁን ልትወስደኝና ልታስረኝ ትችላለህ» አለው::
ፋንቲን ማንም ሰው ከሚቀበርበት የመቃብር ቦታ ተቀበረች፡፡
መቃብራቸው ላይ ስማቸው ከማይጻፍና እነማን እንደሆነ ከማይታወቁ ሰዎች መቃብር አጠገብ ነበር የተቀበረችው:: መቃብርዋ የዘላለም አልጋዋ
ሆነ::...

😢10👍7
#ጉዞ_ወደ_ፍቅር
ቀድሞም አምን ነበር
አካላቴ እንደኾንሽ ፤
ቀድሞም ዐውቀው ነበር
ለ'ኔ እንደተፈጠርሽ።
ይኸው . .
በጉዘቴ መኻል መንፈሴ ተረታ
ድንገት ባጋጣሚ ፣ ታየኝ ውብ ፈገግታ።
የዘላለም ሣቅሽ በቅጽበት ተሰማኝ
ግብሬን ዘነጋኹት እንደኾንኩኝ መናኝ።
ቢኾንም ዐውቃለኹ . .
ብዙ ጊዜ አይወስድም ባ'ንቺ በኩል ብኼድ
ፍቅር አይደለም ወይ ? የፈጣሪስ መንገድ።
🔘ተስፋኹን ከበደ🔘
ቀድሞም አምን ነበር
አካላቴ እንደኾንሽ ፤
ቀድሞም ዐውቀው ነበር
ለ'ኔ እንደተፈጠርሽ።
ይኸው . .
በጉዘቴ መኻል መንፈሴ ተረታ
ድንገት ባጋጣሚ ፣ ታየኝ ውብ ፈገግታ።
የዘላለም ሣቅሽ በቅጽበት ተሰማኝ
ግብሬን ዘነጋኹት እንደኾንኩኝ መናኝ።
ቢኾንም ዐውቃለኹ . .
ብዙ ጊዜ አይወስድም ባ'ንቺ በኩል ብኼድ
ፍቅር አይደለም ወይ ? የፈጣሪስ መንገድ።
🔘ተስፋኹን ከበደ🔘
❤16👍10🥰1
ፈላስፋ አይደለሁ...
ገባሽ አነባለሁ፤
ያውም እልፍ አእላፍ፤
ስለማነብ ነው፤ ነገር ሁሉ የማልፍ።
ማለት...
በሄድሽበት ሁሉ፣
"እሱ ጥጋብ ሙሉ"
ስትዪኝ...
ዝም ጭጭ መልሴ፤
"አሳቢ አያወራም" ፧ እያልከት ለራሴ።
ገባሽ .. አነባለሁ፤
በሄድሽበት ሁሉ፣ መንገዱ ሲቀናሽ፣
"የትሞ የሚጋደሞ፣ እሱ ታላቅ ቅናሽ"
እያልሽኝ... ዝም ጭጭ የምለው፣
የመሀሙድ ዘፈን፣ስለሞሰማ ነው።
(ዝሞታ ነው መልሴ)
ነጋልሽ መሰለኝ ፣ ጆሮ ልታደሚ፤
እኔን ካላነሣሽ ፣ ስለማትሰሚ።
አሁን ይኸው አሁን ፣ ሴት አቅፌ እያየሽ
"አንቺ ስንተኛው ነስ?"
ትያለሽ?
የሷን ቁጥር ትተሽ፣
የሪስሽን ባወቅሽ።
(አንቺ ስንተኛ ነሽ?)
አቤት ያንቺ ዲስኩር ፣ እኔን ለመጠርጠር፤
እንደ ዕድር ዕቃ ፣ መመዝገብ መቆጠር።
(ስትወጂ)
እንደዉ ሙች ልበልሽ
ከሴት ሁሉ ጋራ
ስሜ ቢብጠለጠል ፣ በነገር ቢሸፈን፣
አንቺ ጋር ማ ሊደርስ
ቆዳዬን ነው እንጂ ፣ አንሶላ መች ገፈን።
ኤጭ
ስካንስ ለፈፍኩኝ ፣ ላልችል አባብዬ፤
መናገር ድካም ነወ ፧በ ጂብራል ተብዬ።
የትሞ ስሕተኛኹ፣ የትም ተኛ ብለሽ፣
በሄድሽበት ሁሉ ፣ ጥንብ እሩክሴን ጥለሽ፣
አፍሽ ስሜን ወስዶ ሲያመሰቃቅለው፣
ዝም ጭጭ የምለው፣
ማንሞ ጋር ብተኛ
«እኔኮ የማውቀው ፣ አለማወቄን ነው።»
(የሚል አንብቤ ነው)
ገባሽ.… አነባለሁ።...
ሕይወት እስከሞቱ
ንፁህ ስላልሆነ ፣ ብሽቀት ስለበዛው
እውቀት ቀባብቶ ነው
የስሕተቱን አመድ ፣ ምሁር የሚያወዛው፤
ገባሽ? ...
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
ገባሽ አነባለሁ፤
ያውም እልፍ አእላፍ፤
ስለማነብ ነው፤ ነገር ሁሉ የማልፍ።
ማለት...
በሄድሽበት ሁሉ፣
"እሱ ጥጋብ ሙሉ"
ስትዪኝ...
ዝም ጭጭ መልሴ፤
"አሳቢ አያወራም" ፧ እያልከት ለራሴ።
ገባሽ .. አነባለሁ፤
በሄድሽበት ሁሉ፣ መንገዱ ሲቀናሽ፣
"የትሞ የሚጋደሞ፣ እሱ ታላቅ ቅናሽ"
እያልሽኝ... ዝም ጭጭ የምለው፣
የመሀሙድ ዘፈን፣ስለሞሰማ ነው።
(ዝሞታ ነው መልሴ)
ነጋልሽ መሰለኝ ፣ ጆሮ ልታደሚ፤
እኔን ካላነሣሽ ፣ ስለማትሰሚ።
አሁን ይኸው አሁን ፣ ሴት አቅፌ እያየሽ
"አንቺ ስንተኛው ነስ?"
ትያለሽ?
የሷን ቁጥር ትተሽ፣
የሪስሽን ባወቅሽ።
(አንቺ ስንተኛ ነሽ?)
አቤት ያንቺ ዲስኩር ፣ እኔን ለመጠርጠር፤
እንደ ዕድር ዕቃ ፣ መመዝገብ መቆጠር።
(ስትወጂ)
እንደዉ ሙች ልበልሽ
ከሴት ሁሉ ጋራ
ስሜ ቢብጠለጠል ፣ በነገር ቢሸፈን፣
አንቺ ጋር ማ ሊደርስ
ቆዳዬን ነው እንጂ ፣ አንሶላ መች ገፈን።
ኤጭ
ስካንስ ለፈፍኩኝ ፣ ላልችል አባብዬ፤
መናገር ድካም ነወ ፧በ ጂብራል ተብዬ።
የትሞ ስሕተኛኹ፣ የትም ተኛ ብለሽ፣
በሄድሽበት ሁሉ ፣ ጥንብ እሩክሴን ጥለሽ፣
አፍሽ ስሜን ወስዶ ሲያመሰቃቅለው፣
ዝም ጭጭ የምለው፣
ማንሞ ጋር ብተኛ
«እኔኮ የማውቀው ፣ አለማወቄን ነው።»
(የሚል አንብቤ ነው)
ገባሽ.… አነባለሁ።...
ሕይወት እስከሞቱ
ንፁህ ስላልሆነ ፣ ብሽቀት ስለበዛው
እውቀት ቀባብቶ ነው
የስሕተቱን አመድ ፣ ምሁር የሚያወዛው፤
ገባሽ? ...
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
👍15🤔6🥰1