አትሮኖስ
280K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
459 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#አንዲት_መርፌ_ስንቱን_ቀዳዳ
#ትስፋው?


#አንድ


#በአሌክስ_አብርሃም


ዙቤይዳ ስልክ ደወለችና “አብርሽ…” አለችኝ፤ ድምጿ ውስጥ ምቾት አለ አይጎረብጥም የዙቤይዳ ድምፅ ከዙቤይዳ ቆዳ የተቀመረ ይመስለኛል፤ ቆዳዋ ደግሞ ድምጿን የለበሰ ሁለቱም ነፍሴን ይለሰልሱኛል።

“ወይዬ የኔ ቆንጆ…! የኔ ማር የኔ ለስላሳ... የኔ ሐር! የኔ ፍቅር…የኔ ደስታ…! የኔ .….ሳቅ! ..የኔ ፌሽታ
!…የኔ ሐሴት !የኔ…

ዙቤይዳ ዝም ብላ ስታዳምጠኝ ቆየችና (ዝምታዋ እስክርቢቶና ወረቀት ይዛ ያልኩትን ሁሉ
የምትመዘግብ ነበር የሚያስመስላት) ረጋ ብላ “አባባ ሊያናግሩህ ይፈልጋሉ” አለችኝ።

“ምን…?” ብዬ በድንጋጤ ዝም አልኩ የጨው አምድ ! ይሄማ ቀልድ ነው ። “ ዜድ አንች ደግሞ
በማይቀለደው ትቀልጃለሽ”

“ወላሂ እየቀለድኩ አይደለም አብርሽ” አለችኝ። ረዥም ዝምታ መሃላችን ሰፈነ።

“ምነው ድምፅህ ጠፋ? 'አንበሳ እገድላለሁ የሚለው ባልሽ…ቅጠል ሲንኮሻኮሽ ገደል ገባልሽ' ሂሂሂሂ…” ብላ በሚያምር ሳቋ ተቅጨለጨለች። ይሄው ናት የእኔ ዙቤይዳ፣ በየትኛውም አስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ ብትሆን ወይ ፍንክች ከሳቋ ! የተረጋጋች ! እርጋታዋ ደግሞ የሚያረጋጋ ደግሞ እሷ ላይ ብቻ አይቆምም
ይተላለፋል ..እንደሽቶ ከእርሷ ላይ ይነሳና በመረጋጋት ጠረኑ ነፍስን ያውዳል።

“አባባማ ቅጠል ብቻ አይደሉም ትቀልጃለሽ እንዴ…፤ ግንድ ነው የወደቀብኝ” አልኳት። አባባ
የምትላቸው አባቷን ጋሽ ጀማልን ነው ። በጣም የሚገርመኝና የሚደንቀኝ ነገር የዙቤይዳ እህትና
ወንድሞች በሙሉ አባታቸውን “አንቱ” እያሉ ነው የሚጠሯቸው ! አንድ ቀን ታዲያ ዙቤይዳን
ጠየቅኳት “ዜድዬ እንዴት አባትሽን አንቱ ትያለሽ ?”

“ትልቅ እህቴ ዘሐራ አንቱ ስትል ሰማሁ፤ በዛው ቀጠልኩ። የእኔ ታናናሾችም አንቱ ነው እኮ የሚሏቸው፤”አለችኝ! ትልቅ እህቷ ዘሐራ ጋር (የዛሬን አያድርገውና) እንግባባ ስለነበር ዘሐራንም ጠየቅኳት፣ “ዘሐራ አባት አንቱ ይባላል እንዴ?”

“ትልቅ ወንድማችን አንዋር አንቱ እያለ ይጠራቸው ስለነበር በዛው ለመድኩ።” አለችኝ፤ሲወርድ
ሲዋረድ የመጣ አንቱታ። በጣም የሚያስቀው ታዲያ የመጀመሪያው የአንቱታው ጅማሬ ትልቁ ልጅ
ኡስማን ሲሆን የጋሽ ጀማል ልጅ ሳይሆን ገና ትዳር እንደመሠረቱ ልጅ ሳይወልዱ በፊት አብሯቸው
መኖር የጀመረ የጓደኛቸው ልጅ ነበር። ከዛ በኋላ የተወለዱት ሁሉ አባታቸውን አንቱ እያሉ ቀጠሉ።

የዙቤይዳ አባት ጋሽ ጀማል የተፈሩ፣ የተከበሩ የአገር ሽማግሌ፣በዛላይ አዱኒያ ሞልቶ የተልከሰከሰላቸው ሀብታም ናቸው !በዓመቱ ለረመዳን ዝሆን የሚያካክሉ በሬዎች እያረዱ ሰደቃ ያበላሉ፣ ሚስኪኖችን ያስፈጥራሉ ቤታቸው አስፈሪ ግርማ ሞገስ አለው። ወደ ላይ የአጥሩ ግንብ ርዝመት፣ እንኳን ተራማጅ ፍጥረት በራሪም አዕዋፍት የሚዘሉት አይመስሉም። በዛ ላይ አጥሩ ጫፍ ላይ የተጠማዘዘው ሽቦ … አንዳንዴ የነዙቤይዳን አጥር ስመለከት ከመኖሪያ ቤትነት ይልቅ በሠሩት ወንጀል የዘላለም
እስራት የተፈረደባቸው አደገኛ እስረኞች የታጎሩበት እስር ቤት ይመስለኛል።

ታዲያ ፍቅር የሚባል ጉድ የማያሻግረው ወንዝ፣ የማያዘልለው ከፍታ የለምና መሰላል ሆኖ ይሄን አጥር አዘለለኝ። ምን ማዘለል ብቻ፣ ግቢውን አልፌ፣ የዋናውን ቤት በር በርግጄ እነዙቤይዳ ሳሎን
እዛ የሚያምር ምንጣፍ ላይ ከነጫማዬ ስቆም ቤተሰቡ ተበጣበጠ። ዙቤይዳ የምትባለውን ወርቅ የሆነች ልጃቸውን አፍቅሬ “አገባታለሁ” አልኩ ! ዙቤይዳም ብትሆን የምትይዝ የምትጨብጠውን
እስክታጣ አፍቅራኝ ነበር። ግን ዙቤይዳ እንደ እኔ ማሬ፣ ፍቅሬ ጅኒጃንካ አትልም፤ዝም ብላ ዓለምን በሚያስረሱ ውብ ዓይኖቿ የፍቅር ጅረት እያጎረፈች ነፍሴን በሐሴት ታረሰርሰዋለች።

ዶሮ እንቁላሏን አቅፋ በሙቀቷ ጫጩቶቿን እንደምታስፈለፍል ዙቤይዳም በሩህሩህና ደግ ፀባይ እቅፍ አድርጋኝ ከዚህ ዓለም በሻገተና በክፋት በበሸቀጠ ቅርፊት የተጠቀለልኩ እኔን በፍቅር ትወልደኛለች። በዓይኗ እቅፍ አድርጋ ታሞቀኛለች። ዓይን የተፈጠረው ሁሉን ለማየት ነው ሲሏችሁ አትስሙ። የዙቤይዳ ዓይን የተፈጠረው እኔን ብቻ ለማየት ነው። አቤት ዙቤይዳ ማየት ስትችልበት ! አስተያየቷ
ቅኔ አለው። አስተያየቷ ጀግና ያደርገኛል፤ አስተያየቷ ሁሉ ነገሯን እንደሰጠችኝ የሚያረጋግጥ የብርሃን ፊርማ ነው! ዙቤይዳን በሙሉ ልቤ አፈቅራታለሁ።

እናቷ ቢመክሯት፣ አባቷ ቢዝቱና ቢቆጡ፣ ወንድሞቿ በቀን ሁለት ጊዜ (ጧትና ማታ) ቢሸልሉ ቢፎክሩ… ዙቤይዳ የኔ የፍቅር ሰው ወይ ፍንክች !! “አብርሽን እወደዋለሁ! ወላሂ እወደዋለሁ
ብላቸው እርፍ።

ወንድሟ የዙቤይዳ ነገር አልሆን ቢለው እኔጋ መጣና፣ “ለቀቅ አድርጋት” አለኝ።

"ዜድን እወዳታለሁ! እግዚአብሔርን እወዳታለሁ!” አልኩታ። በዛ በዚህ በመሐላ የታጠረ ፍቅር። በየእምነታችን ለአንድ ፍቅር አምላኮቻችንን ምስክር ጠርተን ወይ ፍንክች አልን። ቤተሰቦቿ ግራ
ሲገባቸው ሳይመርቁንም፣ ሳይረግሙንም ግራ እንደገባቸው በቆሙበት እኛም ፍቅራችንን ዓይናቸው ስር ቀጠልን።

ይሄ የዙቤይዳ እኔን ማፍቀሯና ፍቅሯንም አፍ አውጥታ መናገሯ እነዙቤይዳ ቤት ታላቅ ታሪካዊ
ድፍረት ተደርጎ ተመዘገበ። የቅድም ቅድም ቅድም አያቶቿ ሁሉ ይሄን ድፍረት ቢሰሙ፣ መቃብራቸውን እየፈነቃቀሉ ተነስተው ሃዘን ይቀመጡ ነበር ።
እንደ ቤተሰቦቿ አባባል።

“ይሄ አብርሃም የሚባል ልጅ ፣ወይ አንድ ነገር አስነክቷታል ወይም እህታችንን ኢብሊስት ጠግቷታል”
አለ አሉ ወንድሟ ... ራሷ ዙቤይዳ ናት የነገረችኝ።

“ኢብሊስ ምንድን ነው ዜድዬ?” አልኳት። ዙቤይዳን ስሟን ሳቀናጣው ዜድ አደርገዋለሁ።

“ኢብሊስማ የሸይጧን አለቃ ነገር ነው” አለችና ከት ብላ ሳቀች።

“አሁንስ ወንድምሽ አበዛው! ወይ አንቺ ትርጉሙን አሳስተሽዋል ..ወይ ወንድምሽ ነገር ፈልጎኛል እንዴ ... አሁን ለኔ አለቃነቱን ትቶ ምናለ ተራ ሰይጣን ቢያደርገኝ…”

"ሂሂሂሂሂሂሂ የኔ ቆንጆ ! ተራ ሰይጣንማ ብትሆን እንዲህ በፍቅር አታሳብደኝም” ብላ በፍቅሯ ታሳብደኝና ...በሆነ በምወደው አስተያየት ዓይኖቿን ጣል ታደርግብኛለች። ባየችኝ ቁጥር የሆነ ማዕረግ የተጨመረልኝ ይመስለኛል። የኔ ማር እንዴት እንደማፈቅራት እኮ ! ስትስቅ ብዙ ቀን ምኗን
እንደምስማት ታውቃላችሁ? - ጥርሷን !! ያው ጥርሷን ስሜ ስመለስ አግረ መንገዴን ከንፈሯንም መዘየሬ አይቀርም ታዲያ! እውነቱን ለመናገር ለዙቤይዳ ነፍስህን ስጥ ብባል እሰጣለሁ…፤እሳሳላታለሁ። ሰው ሲያያት የምታልቅብኝ ነው የሚመስለኝ። እንደ ጣፋጭ ከረሜላ ስሟ አፌ ውስጥ ሲሟሟ ይሰማኛል።ፈሳሹ በጉሮሮዬ አድርጎ ልቤን ሁሉ አረስርሶ እስከ እግር ጥፍሬ ውስጤን ሲያጣፍጠው ይታወቀኛል እኔ ራሴ ትልቅ ጣፋጭ የሆንኩ ይመስለኛል፤ንግግሬ ሲጣፍጥ ለራሴ ይሰማኛል !! ዙቤዳ ስሟ
ከፊደላት አይደለም የተፃፈው …. 'አግቹጳርስደፈሬተገፈዴዮ' ከሚባል በገነት ከሚገኝ ፍሬ ጭማቂ ነው ተቀምሞ የተሰራው። ይሄ ፍሬ መልአክቶች ለዓመት በዓል የሚመገቡት ጣፋጭ ፍሬ ነው፤ ቅርፁ የብርቱካን ዓይነት ሆኖ ልጣጩ ከብርሃን የሚሠራ ! እሰይ!! ዙቤይዳዬን እንዲህ ሳደንቃት ሳሞግሳት
ባይወጣልኝም ደስ ይለኛል!ይገባታል! የኔ ውብ !
👍402👎2
#አንዲት_መርፌ_ስንቱን_ቀዳዳ #ትስፋው


#ሁለት


#በአሌክስ_አብርሃም

....የዜድ ፊት ቲማቲም እንደመሰለ እንኳን አልታዘበም አውቃለሁ ስሜ በክፉ ሲነሳ ፊቷ እንዴት እንደሚቀየር እንግዲህ ይሄ ልጅ…ከባለቤቷ የበለጠ አውቃለሁ ብሎ ቡዳ ሲሆን ምን ይባላል? እህታችንን ሲል “ማን ቢወልድ ማን” ትላለች ዙቤይዳ በሆዷ፤ እኔና ዜድ ነቢል ዙቤይዳን እንደሚከጅላት ጠንቅቀን እናውቃለን። እንደውም አንዴ አፍ አውጥቶ ጠይቋታል። አሁን አፉን ሞልቶ እህታችን ሲል አያፍርም ?! እንደውም እዛ ሱቅ ተኮራምቼ ስውል አንዳንዴ ዙቤይዳ እጄን ይዛ ወስዳ “ሻይ ቡና እንበል” ካላለችኝ እግሬን አላነሳም። እንኳን ጫት ቤት ልዞር። እንደው አንዳንዱ ሰው እህ…ብለው ከሰሙት የሚናገረውን አያውቀውም። የነቢል ዘመቻ እንኳን ያው “የገበያ ግርግር ለሌባ ያመቻል”
እንደሚሉት ነው ።

ዙቤይዳን ያወቅኳት እዚህ ቄራ አካባቢ ከቡልጋሪያ ከፍ ብሎ የከባድ መኪና እቃ መለዋወጫ ሱቅ ውስጥ በሻጭነት ተቀጥሬ ስሠራ ነበር። ሱቃቸው ከምሠራበት ሱቅ ጎን ሲሆን ሱቆቻችን የድንጋይ ቤቶች ስለነበሩ ይቀዘቅዛሉ። ጧት ወንበር ውጭጋ እናወጣና ፀሐይ እንሞቃለን። እነዙቤይዳ ሱቅ
ስር ላይ የአንድ ትልቅ ሕንፃ ጥላ ስለሚያርፍ ፀሐይ ፍለጋ እኔ ወደምሠራበት ሱቅ በር ጠጋ ብላ
ነበር የምትቀመጠው። እኔም ወንበር አወጣላትና ጎን ለጎን ተቀምጠን ፀሐያችንን እየኮመኮምን እናወራለን…።

አንዳንዴ እህቷም አብራን ትኖራለች። ብዙ ጊዜ ግን ብቻችንን ነን። ይሄ ቅርርብ ስቦ ስቦ ስጋችን
ፀሐይ፣ ነፍሶቻችንም ፍቅር ይሞቁ ጀመረ። አንድ ቀን ዙቤይዳ ከመሬት ተነስታ፣ “ይሄ ፀሐይ ሱስ
ሆነብኝ” አለችኝ ያዝ እንግዲህ ! በኋላ ፍቅራችን ከለየለት በኋላ “አንተን ማየት ሱስ ሆነብኝ ማለቴ
ነበር፤ የማይገባህ ሆንክ እንጂ” ብላ አስቃኛለች። እሷም ስለማይገባት እንጂ እኔም ሱስ ሆናብኝ ነበር። ዙቤይዳ ከቤት ወጥታ የማታውቅ ውብ ልጅ ነበረች። ፀሐይ ሲነካት ታብረቀርቃለች፣ ቆዳዋ ወርቃማ ነው። አላፊ አግዳሚው ባፍጢሙ እስኪደፋ አንገቱን ጠምዝዞ የሚመለከታት ልጅ ነበረች።
እንደው ስለወደድኳት ሳይሆን ዙቤይዳ ከቤተሰቦቿ አንደኛ ቆንጆ ነበረች መመኪያቸው የቤተሰቡ
መመኪያ !ታዲያ ይችን ልጅ ይዤ ነው ሁልጊዜ ሱቃችንን ዘጋግተን በአፍሪካ ኅብረት መንገድ ክንዴን
ተደግፋ በፍቅር የምንንሳፈፈው አቤት ያንን መንገድ ስንወደው!

አባቷ ጋሽ ጀማል ታዲያ መከረውም ዘክረውም በዘመድ አዝማድ ልጃቸውን አስመክረውም አልሆን ሲላቸው ረጋ ብለው ሲያስቡ ቆዩና፣

“ዙቤይዳ!” አሏትልጃቸውን።

“አቤት አባባ!”

“እስቲ ልጁን ጥሪውና እንየው” አሉ። ወንድምና እህቶቿ ተበሳጩ።

“እንዴት አንድ ዱርዬ ቤት ድረስ ይምጣና ላናግር ይላሉ አባባ” አሏቸው።

“እንኳን ፊት ሰጥተውት ልጁ አይናውጣ ነገር ነው አባባ” አለች የዙቤይዳ እህት… ሚሊየን ጊዜ ስለ አይናፋርነቴ ነግራኛለች በፊት ፀሐይ ስንሞቅ ዛሬ ተጣላንና ግዴለም)።

“ቢሆንስ እንየው ማለት ምን ጉዳት አለው? እኔም እናታችሁም እናናግረውና የምንወስነውን
እንወስናለን” ብለው ቆጣ አሉ። ልጆቹም ደንገጥ ብለው ዝም አሉ

“ግን አባባ እስከዛሬ እንዴት አላወቁትም፣ቄራ ሱቃችን ጎን ተቀጥሮ የሚሠራው ልጅ እኮ ነው።” አለች ዘምዘም የምትባለው ሁለተኛዋ ልጅ።

ጋሽ ጀማል አሰቡ አሰቡና፣ “አሃ ይሄ ቀይ መኪና የሚይዘው ልጅነው ?” ብለው ጠየቁ (ቀይ መኪና የሚይዘው አሠሪዬ ነው)።

“ኧረ አባባ እሱ እንኳን መኪና ሊይዝ ለእግሩም ደህና ጫማ የለውም፤ የሆነ አንጀት የራቀው ላንጌሳ ነገር ነው” አለች ዘሐራ።

“አንች እንዲህ አይባልም… ዱኒያ ተአላህ ዘንዳ ነው። የምን ትዕቢት ነው” አሉ የዙቤይዳ እናት በቁጣ።
ዘሐራ ደንግጣ ዝም አለች። ይች ጉረኛ! የዘሐራ ጉራ ልክ የለውም፣ ትዕቢቷም በጓደኞቿ ሁሉ የታወቀ
ነው። ስለ ሁሉም ነገር ከእኔ በላይ አዋቂ የለም የምትል ልጅ ነበረች። እኔንማ ጥምድ አድርጋ ነው
የያዘችኝ። ሴት ልጅ ጉረኛ ስትሆን እንዴት ያስጠላል?! ባይሆን ኩሩ ስትሆን ይሻላል።

የሆነ ሆኖ የዙቤይዳ አባት ሊያናግሩኝ ወስነው እንድጠራ አዘዙ፡፡ ዙቤይዳም ጠራችኝ። አባቷ ሊያምኑ መንገድ መጀመራቸውን ገምታ ነበር። ታዲያ ዜድዬ ጋር ተገናኝተን ወደ ቤታቸው መንገድ ስንጀምር ቀድማ መከረችኝ፣

“አብርሽ!”

“ወይ ዬዜድ!”

“አይዞህ...ቤት ስትገባ ጫማህን አውልቅ እሺ ?”

"እሺ”

“ደግሞ ማስቲካ በአፍህ እንዳትይዝ፤ አባባ ማስቲካ የሚያላምጥ ሰው አይወዱም።”

"እሺ” ብዬ በአፌ የያዝኩትን ማስቲካ ልተፋው ስል፣

“ማን አሁን አለህ? ቤት ስትደርስ ነው ያልኩህ” አለችና ሳቀች። እኔ አልሳቅኩም፣ተጨናንቄ ነበር።
ማስቲካዬን ወደ አፌ መልሼ ምክሯን ማድመጥ ጀመርኩ።

“ደግሞ አብርሽዬ ብዙ እንዳታወራ፣ በእኔ ለምደህ እንዳትቀባጥር የኔ ማር" ፈገግ አለች፤ “እ…ሌላው ነገር…አዎ ነገር ለማለሳለስ ብለህ አንድም ነገር እንዳትዋሽ። የሆነውን የተሰማህን ነገር ብቻ ሃቋን ተናገር።”

"ሃቋን ”

“አዎ ሃቋን ! በተረፈ በጣም ስለምኮራብህና ምንም ነገር ቢፈጠር እኔ ስለማፈቅርህ እንዳትፈራ የኔ ቆንጆ፤ እሺ አብርሽዬ…”

“እሺ…”

"ሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂ ... ውይ እሺ እሺ ስትል አሳዘንከኝኮ የኔ ሚስኪን "ሂሂሂሂ” አለችና ጉንጬን
ግጥም አድርጋ ሳመችኝ። በዙቤይዳ ሙጥቅላ መኪና ወደ ቤታቸው መንገድ ጀመርን። በቃ ልቤን በድፍረት ሞልታ ሳሎናቸው ውስጥ ወደ ቆመው ችሎት ላከችኝ። ቤታቸው ስደርስ ተንሸራታቹ በር እንደባቡር እየተጎተተ ተከፈተ። የመቃብሬ ድንጋይ የተከፈተ ነበር የመሰለኝ ልቤ ይፈራገጣል።
ዙቤይዳ ወደ ግቢው ከመግባታችን በፊት በእጇ እጄን ጭምቅ አድርጋ ለቀቀችኝ። የዜድ እጅ አፍ ሆኖ ተናገረ፣ የእኔ እጅ ጆሮ ሆኖ አደመጠው።

የተናገረችው ሃቅ ነበር !!
ወደ ግቢው ስገባ ደነገጥኩ። እንዲህ ያምራል ብዬ አላሰብኩም ነበር ጀነት ! እንዴት ደስ ይላል።
እዚህ ግቢ አድጎ እንዴት ሰላማዊ አለመሆን ይቻላል። ዘሐራ ሌላ ቦታ መሆን አለበት ያደገችው እች
ነገረኛ። አሁን ትኖር ይሆን ?

የሳሎኑ በር ሲከፈት አስፈሪው ምንጣፍ አዳራሽ ከሚያክል በር ጋር ጠበቀኝ። እናትና አባቷ በግራ
በኩል ከዛም በፊት ከዛም በኋላ አይቼው የማላውቀው አረቢያን መጅሊስላይ ተቀምጠዋል። አረቢያን መጅሊስ ማለት እግር የሌለው ሶፋ ማለት ነው።

ጫማዬን በር ላይ ላወልቅ ሳጎነብስ በአፍጢሜ ልደፋ ነበር። ፍርሐት ከኋላ ገፍቶኝ ሳይሆን አይቀርም..ሳላስነቃ ራሴን ተቆጣጥሬ ጫማዬን አወለቅኩ። ለዚሁ ፕሮግራም የገዛሁት ነጭ ካልሲ እንደበረዶ።ተንቦገቦገ ኡፍፍፍፍፍፍ ፈርቼ ነበር፣በጣም ፈርቼ ነበር!

በዙቤይዳ መሪነት ኳስ ሜዳ በሚያክለው ምቹ ምንጣፍ ላይ እየተራመድኩ አባትና እናቷፊት ቆምኩ። (የቁርጥ ገን ) በፈገግታ ተቀበሉኝ። በአክብሮት ጎንበስ ብዬ በሁለት እጄ አባቷን ጨበጥኳቸው::
እሳቸው ግን የቀኝ እጄን መዳፍ ወደ ራሳቸው ሳብ አድርገው አይበሉባዬን ሳሙኝና እንደተጨባበጥን የእሳቸውን መልሰው ወደኔ አስጠጉ፣ እጃቸውን ሳምኩ፣ መልሰው ሳሙኝ፣ መልሼ ሳምኳቸው
👍241🔥1😁1
#አንዲት_መርፌ_ስንቱን_ቀዳዳ_ትስፋው


#ሶስት(መጨረሻ)


#በአሌክስ_አብርሃም



እኔ ይሄን ስድብ በፀጋ ተቀብዬ እግር ማየቴን መቼም አላቆምም። የሴት ልጅ እግር የውበት ጥጌ
ነው። ለሰርጌ ቀን አይበለውና እግሯ የሚያምር ግን አንገቷ የተቆረጠ ሴት ጎኔ አምጥተው ሚስትህ ናት ቢሉኝ፣ “በደስታ ይሁን በሐዘን…” ብዬ ከመፈረም አልመለስም። እንዲህ የምንሰፈሰፍለት፣የምማልልለት፣ የምልከሰከስለት፣ ልክስክስክስ የምልለት የሴት ልጅ እግር እንደኔ እንደኔ በሁለት ትላልቅ ክፍል ይከፈላል፣

1ኛ የዓለም ሴቶች እግር ሁሉ በአጠቃላይ ማለት ነው።
2ኛ. የዙቤይዳ እግር ! በቃ እኔን የሚያልከሰክሰኝ፣ በምኞት አፌን የሚያስከፍተኝ፣ ሳመው ሳመው
የሚለኝ ይሄ ሁለተኛው እግር ነው። እናም ድንገት ከቀሚሷ ወጣ ብሎ ፍም የመሰለ ተረከዟ፣የሕፃን
ልጅ ጣት የመሳሰሉ ጣቶቿ፣ ውሃ የመሰሉ (መስተዋትም ይመስሉኛል) ጥፍሮቿ፣ ምንም ቀለም ሳይቀቡ ደግሞ የቁርጭምጭሚት አጥንቶቿ ብይ ብይ መስለው ጠቆር ያለው አረቢያን መጅሊስ ላይ
እንደ እሳት ሲንቀለቀሉ ሳይ ቀልቤን ሳትኩ። ዜድዬ እኮ ለእኔ ሰርክ አዲስ ነች። አይቼ አልጠግባትም ።ተንደርድሬ ሄጄ እግሮቿን ብስማቸው ደስታዬ፤ የሆነ ነገር ሂድ ሂድ እያለ ይገፋኛል።

እ.? ”አሉኝ የዜድ አባት

“እ?…” አልኳቸው እኔም፣ የተናገሩትን ባለመስማቴ አፍሬም ደንግጬም ነበር፤(ታዲያ ምን ላድርግ እኔ የብቸኝነት፣ የክህደት፣ የውሸት፣ የማስመሰል፣ የጥቅም ማሳደድ እና የዝሙት ቆፈን በሚያቆራምደው ከተማ፣ የፍቅር እሳታቸውን ወልደው እሳት ውስጥ ቆሜ እንዴት ያሉትን ልስማ…? )

“እናቴዋ…ቀልቡን ወሰድ ያደርገዋል አንዳንዴ እንደ አብዱ” አሉ የዜድ እናት (ጎበዝ ኧረ ይሄ አብዱ ማነው…?) ዙቤይዳ ቡፍ ብላ ሳቀች። እናቷም ሰውነታቸው እስኪረግፍ ሳቁ። አባቷግን ኮስተር እንዳሉ ፂማቸውን በመዳፋቸው እየዳሰሱ ዝም ብለው ቆዩ። በዝምታው ውስጥ ድምፃቸው የሚያማምር ሕፃናት ከሩቅ በስርቅርቅ ድምፃቸው ቁርዓን ሲቀሩ ይሰማል። ለምን እንደሆነ ባላውቅም የሕፃናቱ ድምፅ፣ የአባቷ ዝምታ፣ የዙቤይዳ አቀርቅራ በክሪሟ መጫወት ተዳምሮ ዜድን ላጣት ከዜድ ጋር
ልንለያይ ሴኮንዶች የቀሩ መሰለኝ። ምፅአት መሰለኝ። ድንገት ነው በቃ እንደዚህ የተሰማኝ። እንባዬ
ሁሉ ይታገለኝ ጀመረ እልህ ውስጤ ተንተከተከ።

የዜድዬ እናት ድንገት ዝምታውን ሰብረው፣ “ዘምዘም…” ብለው ተጣሩ ።

“አቤትእማማ ! ብላ የዙቤይዳ እህት ከውስጠኛው ክፍል የግቢ በር የሚያክለውን በጌጥ የተሽቆጠቆጠ ባለሁለት ተከፋች የጣውላ በር ከፍታ ገባች። ዘምዘም ቁመቷ የትየለሌ ነው። በዛ ቁመት ላይ ሙልት ያለ ሰውነቷ ተጨምሮበት ክብድ የሚል ነገር አላት። ሳሎኑ ውስጥ መጥታ ስትቆም የሆነ ረዥም ማማ
ነገር የቆመ ነበር የሚመስለው፣ አንጋጥጬ ሽቅብ ተመለከትኳት። ኮስተር አለችብኝ። አሁን የመረረው
ባላጋራ መጣ አልኩ በሆዴ። በተቻለኝ መጠን ዘምዘምን ላለማየት ወደ ዙቤይዳ ዞርኩ፤ ፈገግ አለችልኝ ወደ ዘምዘም በድፍረት ዞርኩ ቡትሌ አክላ ታየችኝ፡፡አስማተኛው የዜድ ፈገግታ እንኳን አንዲት ሴት ኪሊማንጃሮን በፊቴ ጠጠር ያሳክለዋል። ከፍቅር የሚገዝፍ ነገር የለማ !

“ምሳ አልደረሰም እንዴ? እንግዳ ጠርታችሁ በራብ ልትገሉት ነው እንዴ” አሉ እማማ። ዘምዘም
ክፉ ደግ ሳትናገር ወደ ውስጥ ተመልሳ ገባች። እኛም በዝምታችን እንደፀናን በሩ ተበረገደና የምግብ መፈክር ያነገቱ ሰላማዊ ሰልፈኞች ወደ ሳሎኑ ተግተልትለው ገቡ አራት እህትና አንዲት ሠራተኛ።
ዘሐራም ከሰልፈኞቹ አንዷ ነበረች። የያዘችውን ሰሐን በትኩረት ተመለከትኩት። “እሷ ከያዘችው ሰሐን አልበላም” አልኩ ለራሴ። ሠራተኛዋ ምንጣፉ መሐል ላይ አንድ ሰፊ ክብ ላስቲክ አነጠፈች። ከዛ የምግብ ዓይነት በሚያማምር ሰፋፊ የሸክላ ሰሀኖች ተደረደሩ። ላስቲኩ ላይ ዙሪያውን የተደረደሩትን
ነጫጭ ሰሀኖች በክብ ተደርድረው ስመለከት በፀሐይ ዙሪያ ምህዋራቸውን ተከትለው የሚሽከረከሩ ፕላኔቶች ሥዕል ትዝ አለኝ።

ሰልፈኞቹ ወጡና ሌላ ሰሐን ይዘው ተመለሱ(ምንድን ነው ይሄ ሁሉ ጉድ)። ብስኩቱ፣ ጣፋጩ፣ ስሙን
የማላውቀው ነገር ሁሉ በዓይነት ተደረደረ። አንድ ነገር ውስጤን በሐዘን ሞላው። ዙቤይዳ ሱቅ ፀሐይ ልንሞቅ ስንቀመጥ የምጋብዛትን ቦንቦሊኖ ለመብላት ቁርስ ሳትበላ ትመጣ እንደነበር አስታወስኩ።እውነቴን ነው ይሄን ማዕድ ስለ ፍቅር ረግጣ፣ “አብርሽ ኧረ ርቦኛል ቦንቦሊኖ ግዛልኝ…” ትላለች።ፀሐያችንን እየሞቅን ፊት ለፊታችን ካለች ሻይ ቤት ቦንቦሊኖ አዝዘን እየተጎራረስን በሻይ እንበላለን።እንደውም አንድ ጊዜ አረፋ በዓል ሆኖ የነዙቤይዳ ሱቅ ዝግ ነበር፤ እኔ ተቀጥሬ የምሠራበት ሱቅ ደግሞ
አልተዘጋም፤ ዙቤይዳ ከቤቷ ሹልክ ብላ መጥታ በበዓሉ ቀን እዛች ሻይ ቤት ሄድንና ቦንቦሊኖ በሻይ በላን። ለረመዳን ሙሉ ቀን ዙቤይዳ ስለማትበላ እኔም ሳልበላ የምውልባቸው ቀናት ይበዙ ነበር።

የዙቤይዳ እናት “በልና ወዲህ፣ ዙቤይዳ ነቅነቅ በይ እንጂ መታጠቢያ ቤቱን አሳይው” አሉ። ዙቤይዳ እየመራች በሚያምረው በር አልፋ ወደ መታጠቢያው ወሰደችኝ። አንዳንድ ነገሮች አሉ በአክብሮት ሲደረጉ ስድብ የሚሆኑ። የነዙቤይዳ መታጠቢያ ቤት ስፋት የአባቴን መኝታ ቤት ያክላል። የመታጠቢያ
ሸክላዎቹ ንጣት፣ የቤቱ አስደሳች ጠረን አፍ አውጥቶ የሰደበኝ መሰለኝ፣ “አንተ አመዳም ደሀ ልካችንን እየው…" የሚለኝ መሰለኝ። ዙቤይዳ ፈዝዤ መቆሜን ስታይ “ታጠብ…” አለችኝና ዞር ብላ ወደ ኋላዋ
ተመልክታ ማንም አለመኖሩን ካረጋገጠች በኋላ ጉንጬን ሳመችኝ። ከንፈሯ ይሞቃል። የሆነ ርጥበቱ ጉንጩ ላይ የቀረ መሰለኝ። ስትስመኝ ድንጋጤው ይሁን ንዝረቱ አስበረገገኝ። “ብቻችንን ከሆንን አያስችለኝም ቶሎ ውጣ” አለችኝ እየሳቀች። እና ራሷ እጇን መታጠብ ጀመረች። በመስተዋቱ ውስጥ ዓይኖቿ አፍጥጠውብኝ ነበር። የመታጠቢያ ቤቱ ውበት ውበቷን አጉልቶት ነው መሰል፤ ዙቤይዳ
በጣም አማረችብኝ። ለዚህች ልጅማ አንድ ሰውና አንድ ጥይት እስኪቀር ታጥበን ወጣን።

ወደ ሳሎን ስንመለስ የዙቤይዳ እናት ኖር.. አሉኝ፣ አባቷ ግን አሁንም ፂማቸውን እያሻሹ ዝም
ብለው ተቀምጠዋል። እንደውም ከቅድሙ በላይ ፊታቸው ተቀያይሮ ቁጣ ነበር ከግንባራቸው
የሚስፈነጠረው። ወደ መታጠቢያ ቤቱ እንደገባን የዜድ እናት ጋር የሆነ ነገር እንደተነጋገሩ ገመትኩ።
እንዴት ይጨንቃሉ። ዘሐራ ጭልፉ ይዛ ስትገባ፣ እኛ ታጥበን ስንወጣ አንድ ሆነ። እንደው ይህች ልጅ
ደንቃራ ነገር ናት ልበል። በግርምት እግሬን ተመለከተችኝ። ዓይኗን ተከትዬ ወደ እግሬ ስመለከት ወደ
መታጠቢያ ቤት ስገባ ያደረግኩት የዙቤይዳን ሰንደል ጫማ ነበር። ያውም ብዙ ጊዜ ኡዱ ስታደርግ
የምትጫማውን። እሾህ ! ዓይኗ የማያየው ነገር የለም። እኔ ራሴ ጫማ ላድርግ፣ በእግሬ ልሁን ትዝ
ያለኝ አሁን ነው።

አንዲት ትንሽ ትራስ ነገር ከተሰደረው ምግብ ፊት ዙቤይዳ አመቻቸችልኝና ተቀመጥኩ። አባቷ
ከምግቡ ክምር ወዲያ፣ እኔ ወዲህ። ምግብን ድንበር አድርገን የተፋጠጥን ጠላቶች። (አንቱ ወዲያ ማዶ፣ እኔ ወዲህ ማዶ፣ አንገናኝም ወይ ተራራው ተንዶ..) መብላት አልቻልኩም። አባቷ ዓይኔን ላለማየት ሲሸሹ ምግቡ ዘጋኝ። በቤታቸው ምግብ አቅርበው ፊታቸውን ሲያጠቁሩብኝ ለልመና የመጣሁ እስኪመስለኝ አፈርኩ ተሳቀቅኩ። ዙቤይዳ ገብቷታል። ምንም ነገር ሳትፈራ ሰሀኔ ላይ እንጀራና ንጣቱ
👍19👏2