A:
#የወድያነሽ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል
....እሑድ ከሰዓት በኋላ.….ስለ ለጎ ሐይቅ ከተማና አካባቢዋ ኣንድ ባንድ ካወራችልኝ በኋላ የሕሊናዋን ትዝታ ወደ ደሲ መልሳ ስለ በርበሬ ገንዳ ሙጋድ፣ ዳውዶ ገራዶ፣ ሆጤ፤ ሶሳ፣ አዘዋ ገደል ሰኞ ገበያ…. ነገረችኝ፡፡ «ቆየኝ ደግሞ ሥራዬን ጨርሼ ልምጣና አወራልሃለሁ» ብላ ካልጋው ጫፍ ላይ ሸርተት ብላ ሔደች፡፡ ከግማሽ ሰዓት በኋላ ሥራዋን አጠናቃ ከተፍ አለች::ነጣ ያለ ቦላሌና ሰማያዊ ሸሚዝ ለብሼ አልጋው ላይ በጀርባዬ ተንጋልዬ
የጋሻዬነህን ሥዕል አንጋጥጬ ስመለከት ደረሰች፡፡ ሲሠውረኝ አላየችብኝም፡፡
ትከሻዬ ሥር ጣል አድርጌ ተኛሁበት፡፡ አልጋው ጫፍ ላይ ተቀምጣ በሆዴ
ላይ እጂን አሻግራ በመመርኮዝ ከደረቷ ዘንበል አለች፡፡ ትከሻዋ ላይ የነበረችው ባለ አረንጓዴ ጥለት ያንገት ልብስ ተንሸራተተችና የተዘረጋችውን እጅዋን ሸፈነቻት፡፡ ከደረቴ በታች የሆዴ አካባቢ በድንኳን ውስጥ ያላ ነጭ አግዳሚ መቀጫ መሰለ፡፡
ያን በሆዴ ላይ ዐልፎ አልጋው ላይ እንደ ካስማ የተተከለውን እጅዋን በቀኝ እጄ እያሻሽሁ ምናልባት ቅር ይላት ይሆን? በማለት ስፈራ ስቸር ከቆየሁ በኋላ የወዲያ፣ አንድ ነገር ብጠይቅሽ ቅር ይልሻል?» አልኳት፡፡ አሽቆልቁላ ዐይን ዐይኔን ትክ ብላ እያየች ምንስ ነገር ብትጠይቀኝ ምን ብዬ እቀየማለሁ? ስል ጠይቀኝ ልንገርህ? ብላ አቀማመጡዋን አመቻቸች።
ለሁለት ደቂቃ ያህል ውስጥ ውስጡን ሐሳቢን አንቀረቀብኩ፡፡ እንግዲህ
ያለችውን ትበል አልኩና «የወዲያ! ለምን አስታወስከኝ ኣትበይና፣ እናትና
አባትሽ ሲሞቱ የስንት ዓመት ልጅ ነበርሽ?» አልኳት። ፈገግታዋን የቅሬታ
ደም ስለ በረዘው ፊቷ ፈዞ የክረምት ዋዜማ መሰለ፡ ውስጥ ውስጡን ራሴን
«ጌታነህ! የተዳፈነ የኅዘን ረመጥ ጫርክ፣ ያንቀላፋ ኀዘን ቀሰቀስክ» ብዩ ወቀስኩ፡፡ ደቂቃዎች ሠገሩ። ትንሽ ፈነከነክ ብላ «ምነው ምን ነካሀና ኖረሀ ኖረህ ጠየቅኸኝ?» ብላ ፊቷን የትካዜ ዐመድ ነሰነሰችበት፡፡ ካኣሁን አሁን ትጀምራለች በማለት አሰፍስፌ ጠበቅሁ፡፡ ያን እንደ አተር እምቡጥ እበጥ ብሎ የቆየ የታች ከንፈሯን በላይኛው ውብ ጥርሷ ረመጠጠችው። አንድ ጊዜ
አፈትልኮ የተነገረን ሐሳብ መልሶ መዋጥ የማይቻል በመሆኑ ችሎታዩ ከዝምታ ሊያልፍ አልቻለም። እየር ስትስብና ስታስወጣ ከፍና ዝቅ የሚለውን
ደረቷን በመመልከት ላይ እንዳለ «አባቴ ሲሞት አንዲት ፍሬ ልጅ ነበርኩ
አሉ፡፡ ትንሽ ትንሽ እንደ ሕልም ትዝ ይለኛል፡፡ እናቴም አባትሽ ከልጆቹ
ሁሉ አንቺን ይወድሽ ነበር፡፡ ሳይንት እሚባል አገር ካሉት ዘመዶቹ መኻል
የሚወዳትን አክስቱን ስለምትመስዪ የእርሷ ነገር ሆነበትና 'የወዲያነሽ የወዲያ
ሰው ብሎ ስም አወጣልሽና የወዲያዬ የወዲያነሽ አልንሽ ብላ ነገረችኝ። ልጅ
ስለ ነበርኩ ሁሉንም ኣላስታውስም እንጂ አባቴ ብዙ ጊዜ ታሞና ማቆ ማቆ
ነው የሞተው። የሞተ ዕለት ሰዎች ሁሉ ሲያለቅሱ አይቼ እኔም ትንሽ
አልቅሻለሁ፡፡ ሞት ምን እንደሆነ ስለማላውቅ ሄዶ የሚመለስ እንጂ በዚያው የሚቀር አይመስለኝም ነበር፡፡ ሬሳውን በአልጋ ይዘው ከቤት ሲወጡ ምንም ስላልመሰለኝ ጉድሮዬን እያዘናፈልኩ ከመንደሩ ልጆች ጋር እቦርቅ ነበር፡፡
ታናሽ እኅቴ እማዋይሽ ክርስትና የተነሣች ዕለት መጥተው የነበሩት ቄሶች ራሱ የቀብሩም ዕለት መጥተው ስለነበር ለደስታ የመጡ እንጂ ለሌላ ነገር
የመጡ አልመሰለኝም። እያደር ግን ዋል አደር ስል ዕንጨት ለቀማም ይሁን
ዋርማ ይዤ ጅረት ስወርድ ጓደኛቼ እንደ ቀልድ 'አንቺዬ ማሳዘኗ' አንድ ቀን እኮ የሞቱት የዚች አባት ናቸው” እያሉ ሲያንሾካሽኩ እየሰማሁ ግራ ግብት ይለኝ ነበር። አባቴ ከሞተ በኋላ እዚያው አገር ቤት ከእናቴና ከእኅት ወንድሞቼ ጋር ቆየሁ፡፡ ከዚያ በኋላ ግን የእናቴ ታላቅ እኅት ከአገር ቤት ወደ ከተማ ይዛኝ መጥታ ትምህርት ቤት አስገባችኝ ብላ ዝም ስላለች ያ በኀዘን ጉም ተሸፍኖ የቆየው ዐይኔ ቦግ ብሎ ወደ የወዲያነሽ ዐይኖች ተወረወረ፡፡እንባዋ እንደ አሸንዳ ጠፈጠፍ እየተንከባለለ በጉንጯ ላይ ተንኳለለ፡፡ ልብሴ ላይ የተንጠባጠበውን ዕንባዋን ደረቁ ሸሚዜ እንደ ግንቦት አፈር ጠጣው፡ የደቀነችውን ወሬ ለመጨረስ እንባዋን ካባበሰች በኋላ «አሁንም ቢሆን እነዚያ የትምህርት ቤት ጓደኞቼ ትዝ ይሉኛል። እነ የሻረግ፣ ዘነበች፡ አሚናት፡
ይመር፣ አያሌው፣ ገበያነሽ፣ ሰኢድ ኧረ ስንቱ ስንቱ... እክስቴ ከልጆቹ ሁሉ እኔን መርጣ የወሰደችኝ የረጋች ልጅ ነች፣ ደስ ትለኛለች» ብላ ነበር። ሁለት ሦስት ጊዜ ላግባ ባይ መጥቶ ሲጠይቅ ቆይ እስኪ ጥቂት ተምራ ነው ነፍስ ትወቅ» ብላ እምቢ አለቻቸው፡፡
እኔና እርሷ ብቻችንን ተቀምጠን በምናወራበት ጊዜ ግን፡ ያም የሸማኔ ልጅ ነው፣ ያኛው መናጢ ዘረ ድሃ ነው፣ የዚያኛውም እናት ዘር ማንዘሯ ሸክላ ሠሪ ነው የጠዳ የጨዋ ልጅ እስኪመጣ ሰጥ ብለሽ ትምርትሽን ተማሪ» ትለኝ ነበር፡፡ አክስቴ ከምላሷና ከንዝንኳ በስተቀር ሆዷ ባዶ ነው::ባልዋ አይዋ ዘለቀ አንድ ሲናገሩ ሁለትና ሦስት ነበር የምትመልስላቸው:: ችለው ችለው አንድ ቀን የተነሡ ለታ ግን ቀሽልደው ቀሽልደው ሲለቋት ውሃ ውስጥ የገባች አይጥ ትሆናለች። እሷ ታዲያ የሳቸውን እልክ በኔ ላይ ነበር የምትወጣው::
«አንቺ መድረሻ ቢስ ግንባረ ነጭ» ብላ ከጀመረች በርበሬ ሳታጥነኝና በጥርሷ ሳትበተብተኝ እንገላገልም፡፡ «አፈር ብይ! አፈር ያስበላሽ! ያባትሽን ቀን ይስጥሽ» ስትለኝ ግን አይመኙ ነገር ያስመኘኝ ነበር። ለጎ-ሐይቅ በሔድኩ በአራተኛው ዓመት አገር ቤት ወረርሽኝ ገባ ተባለና እናቴ በጠና ታመመች።ያኔውኑ ትምህርት ቤት በመዘጋቱ ካልሔድኩ ብዬ አገር አመስኩ፡፡ ቢሉኝ ቢፈጥሩኝ እዚያቹ ከናቴ
ጋር እሞታታለሁ እንጂ እይደረግም ብዬ
አስቸገርኩ፡፡ በማይረባው ነገር ሁሉ ካክስቴ ጋር መነታረኩ መሮኝ ስለ ነበር
ለጥቂት ጊዜም ቢሆን ከፊቷ ገለል ብዬ እፎይ ማለት ፈልጌ ነበር። ወሬ
አበዛሁብህ መሰል? ላሳጥርልህ፣ እናቴ ቡሄ በዋላ ልክ በሳምንቱ ሞተች። ያን
እለት የሆንኩትን አኳኋን ግን ባትሰማው ይሻላል። እናቴ ፀሐይነሽ አማረ ትባል ነበር። ከዘመዶቻችን ጋር ዕርባዋን አውጥቼ ትምህርት ቤት የተከፈተ
በሳምንቱ ከዚያቹ ከአክስቴ ጋር ወደ ከተማ ተመለስኩ፡፡ ከዚያ በኋላ ግን ወደ
አገር ቤት አልተመለስኩም» ብላ ጋደም አለች፡፡ ያ የቀድሞ ውበታዋም ርዝማኔውን ሊይዝ ጥቂት የቀረው የሴትነቷ ግርማ የሆነው ዞማ ጸጉሯ በአንገቷ ዙሪያ በተንተን ብሎ ተነሰነሰ። ድንገት
ቀና ብላ እግሯን ኮርምታ ተቀመጠች፡፡ «አልጨረስኩልህም እኮ» ብላ
ቀጠለች። በበኩሌ የሕይወቷ ምሬት አንገፍግፎኝ ነበር፡፡» ያክስቴ ባል ዘኃ
ነጋዴ ነበሩ። ከደሴ ዘኃ ያመጡና፣ ከሐይቅ ደግሞ አንጋሬና ቆዳ ይዘው
ይመለሳሉ። የኋላ ኋላ ግን ደሴ መሬት ገዝተው ቤት ስለሠሩና ንብረት ስላበጁ ሁላችንም ወደዚያው ሄድን። ደሴ ወይዘሮ ስሒን ትምህርት ቤት አምስተኛ ክፍል ገባሁ፡፡ ያነዩ ገና ዐሥራ አራት ዓመቴ ነበር፡፡ አክስቴ ውሃ ቀጠነ፣ ጪስ በነነ፣ እያለች ስለምትነዛነዝ ይብስ እሳትና ጭድ ሆንን። እልህ ማብረጃ አረገችኝ፡፡ ስወጣም ስገባም ስድብና ዱላ ሆነ፡፡
ለጊዜውም ቢሆን ሌላ የሚያስጠጋኝና የምገባበት ዘመድ ስላልነበረኝ ያለችውን ብትል ታግሼ ዝም አልኩ፡፡ እንደ ምንም ብዬ ተፍጨርጭሬ ሰባተኛ ክፍል እንደ ገባሁ ከነከተቴው ሒጂልኝ! ውጪልኝ! ዐይንሽን ላፈር! ማለት አመጣች። ንግግሯ ሁሉ አንገሸገሸኝ፡፡ የዓመቱ ትምህርት ባሳር በመከራ ካለቀልኝ በኋላ ብሞትም ልሙት ብዩ ቆርጬ ተነሣሁ አንድ ቀን
ጎረቤታችን የነበሩ አንድ የጦር

👍7
#የተወጋ_ልብ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
....በዝናሙ ምትክ ፀሃይዋ ክርር ያለ የሚያቃጥል ጨረሯን መፈንጠቅ
ጀምራለች። ዶሮዎች በየስራስሩ፣ በየበረቱ አጥር ስር እየተሹለከለኩ ይለቃቅማሉ.. አልፎ አልፎ ከቤት ወስጥ የታሰሩ ጥጆች ድምጽ ይሰማል።
ከብቶች በየዛፉ ጥላ ስር ቆመዋል፡፡ ከዚህ ሌላ ግን ምንም አይነት ድምፅ አይሰማም፡፡ ጭር... ያለ ጭውው…. ያለ ፀጥታ!! የጌትነት መንደር በሬሳ! ሰሞኑን ጤናዋ በይበልጥ የተቃወሰውና ሃሳብ ያመነመናት አስካለ ልብሷን እንደለባበሰች ከአልጋዋ ላይ ጋደም ብላለች። ዘይኑ ከቤት አልነበረችም፡፡ ከወዲያኛው መንደር ተልካ ሄዳለች፡፡
"ካ ካ.!ካ ኩ!ኩ.ኩ!.ካ!.ካክ! ኩ! ኩክ! " ዶሮዎቹ ተንጫጩ።
“ድመት!ድመት! ሸለምጥማጥ! ሽለምጥማጥ ወስዳት ይዟት ሮጠ" የወይዘሮ አስካለ ጎረቤት የወይዘሮ ተዋበች ትንሿ ሴት ልጅ ጮኽች።
የአስካለ ዶሮ ናትኮ! ጠልፏት ሄደ? እነሱ ቤት የሉም እንዴ? እዚህ ቤቶች! ዘይኑ ኽረ ዘይኑ!.ማንም ሰው የለምንዴ?" ወደ በሩ ተጠጉ፡፡
"ማነው? ይግቡ አለሁ ይክፈቱት በሩን..." አለች በደከመ ድምፅ፡፡
“ምነው? ባሰብሽ እንዴ? አይይ.. በጣም አሞሻል ለካ?! ደምሽ ሁሉ ከፊትሽ ላይ ምጥጥ ብሎ የለምንዴ?! ዘይኑ የለችምንዴ? እኔ ኮ አሁን ልጅቷ ዶሮዋን ወስዳት ብላ ስትጮህ ነው የወጣሁት። እሳት ላይ ምናምን ጥጃለሁ"
"ምን ወስዳት?” አለች በቀሰስተኛ ድምጽ።
"ሽለምጥማጥ ነዋ! ድመት! ድመት! ስትለኝ ሮጬ ብወጣ ይዟት ቁልቁል
ሲሮጥ አየሁት። ለትንሽ አመለጠኝንጂ ቀድሜ ብወጣ ኖሮ አስጥለው ነበር። ደግሞ መርጦ ያንን ወስራውንኮ ነው የጠለፈው"
"ይልቀማቸው ጥርግ ያድርጋቸው!.." አለች በታከተ አነጋገር፡፡
"አንቺ ሴት ራስሽ ነሽኮ ይሄንን ሁሉ ችግር በራስሽ ላይ የምታመጪው። ከበሽታው የበለጠ የጎዳሽ ሀሳቡ ነውኮ! ለመሆኑ ከዚያ ወዲህ ስለ ጤንነቱ የሰማሽው ነገር አለ?"
“ምን እስማለሁ እትዬ ተዋቡ?ጋሼ አለሙም ይኸውና ብቅ አላሉም፡፡
ምን አባቴ እንደማደርግ ግራ ግብት ብሎኝኮ ነው። አገሩን አያውቅ ሰው
አያውቅ አንድ ቶሎሳን ብሎ ነው እኮ እንደ ወፍ ብርር ብሎ የወጣው።
እኔን ብርር ያድርገኝ፡፡ እኔ ልንከራተት። የአባቱ ሀዘን ከአንጀቱ ሳይወጣለት ከአገሩ ወጥቶ ሄዶ በማያውቀው አገር ቶሎሳ ደጅ አውጥቶ ከጣለው ምን ይውጠዋል እትዬ ተዋቡ? ምን አልኩት ፈጣሪዬን? አይይ”በትኩስ እንባ ምክንያት ማዲያት በጀማመረው ፊቷ ላይ እምባዋ ክንብል አል።
ተይንጂ የጌትነት እናት ምን እያደረግሽ ነው? በደህና ውለሽ እኔ ስመጣ ነውንዴ የሚብስብሽ? እስቲ ምን ሰማሁ ብለሽ ነው እንዲህ የምትሆኚው? ለትንሽዋም ቢሆን እዘኝላት እንጂ! ባንቺ ለቅሶ ትጨነቅ? በወንድሟ ናፍቆት ትጨነቅ? ወይስ በአባቷ ሀዘን? ተይ የኔ እህት እንደዚህም አይደል ጠና ጠና እያልሽ የሆድሽን በሆድሽ ይዘሽ ሀዘንሽን ደብቀሽ
ደስተኛ መስለሽ እሷንም አጽናኛትንጂ!. ዘይኑ ዕድሜዋ ትንሽ ሆነንጂ
አስተሳሰቧ ትልቅ ነው። ወይኔ አባቴ ወይኔ እናቴ እንድትል አታድርጊያት፡፡ አመዛዝኝ
“አይ እትዬ ተዋቡ መቼ እሱን ሳላስበው ቀረሁ ብለው ነው? ሆዴ እያረረ ጥርሴ ለመሳቅ እየታገለ አቃተኝንጂ፡፡ እንቅልፍ በዓይኔ አልዞር እያላ እህል አልዋጥልሽ እያለ አስቸገረኝንጂ ጉልበቱ ጥናቱ ከዳኝንጂ ለዘይንዬ መቼ ሳላስብ ቀረሁ? እህህህ.."
“በይ ነግሬሻለሁ ለቅሶሽን አቁሚ! ፈጣሪሽን እየለመንሽ አንተ ርዳው
እያልሽ በፀሎትሽ መበርታት ነው የሚያስፈልገው፡፡ ደስ ደስ ሲልሽ ደስ
የሚል ዜና ትሰሚያለሽ፡፡ በበሽታሽ ላይ ሌላ በሽታ መጨመሩ ላኔ አይታየኝም፡፡ እስቲ በወጉ ጋደም በይና የሚቀመስ እህል ይዤልሽ ልምጣ ነጠላውን አለባበሷትና ወጡ። ወዲያውኑ ዘይኑ ከተላከችበት ተመለሰች::
“እማምዬ ምን ሆነሽ ነው ዐይንሽ ያበጠው? አልቅሰሻል አይደለም?” አኮረፈች።
አይደለም! አላለቀስኩም! ዶሯችንን ሸለመጥማጥ ይዟት ሲሮጥ እሷን
ለማስጣል ስወጣ ጨረር ዐይኔን ወጋኝ መሰለኝ" ልትዋሻት ሞከረች::
"አላውቅም ውሽትሽን ነው፣ ውሸትሽን ነው እያለቀስሽ ነው ፊትሽ እንደዚህ የተበላሸው።አንቺ እያለቀስሽ ለመሞት ነው የምትፈልጊው" ከንፈሯን የበለጠ ጣለች፡፡
“ዘይንዬ አላለቀስኩም ስልሽ? ለምን አለቅሳለሁ? ደስ ይለኛልንጂ! አሁን
ጋሼ አለሙ ሲመጡ ጌትዬ የጻፈልንን ደብዳቤ ይዘውልን ይመጣሉ።
ከቶሎሳ ጋር ታርቀናል ሥራም ይዣለሁ ብሎ የጻፈውን ደብዳቤ ይዘውልን እንደሚመጡ አትጠራጠሪ! ከዚያም ጌትዬ አንቺን አዲስ አበባ ወስዶ
ሲያተምርሽ ይታየኛል” እንደ ልማዷ እቅፍ አድርጋ ስታረሳሳት የእናቷ ጉያ ሞቃት። ፀጉሯን እያከከችላት እቅፍ ስታደርጋት በዚያው ልጥፍ እንዳለችባት እንቅልፍ ያባብላት ጀመር፡፡
“እማምዬ ወንድም ጋሻ ሥራ ሲይዝ ሁለታችንም እሱ ጋ አዲስ አበባ
ሄደን አብረን እንኖራለን አይደል?" የሟች ባለቤቷን የአደራ ቃል አስታወስቻት አስካልዬ ባለተራ ሆነሽ ወደኔ ስትመጪ ከጎኔ እንዳትርቂ አደራ! " ከባሏ ጋር ብዙ ትዝታ ያሳለፈችባትን ጎጆ ጥላ የትም እንደማትኖር ታውቀዋለች፡፡ ሬሳዋ ከዚያው ባለቤቷ ካረፈበት አልጋ ላይ እንደሚነሳ በልቧ ቢታወቃትም ዘይኑን ልታስደስታት ፈለገች።
“ታዲያስ ምን ጥርጥር አለው? ጌትዬ ሥራ ይዞ እኔንም አንቺንም አዲስ አበባ ወስዶን ደስ ብሎን አብረን እንኖራለን ምን ይጠየቃል?”
ስትላት ዘይኑ በደስታ ተፍነከነከች። በዚሁ መሀል.. "ሴቶች" አሉና ገቡ።
ወይዘሮ ተዋቡ ነበሩ።
“ዘይኑ መጣሽ እንዴ? በይ እስቲ ቀና በይ የጌትዬ እናት ይህችን ቅመሽ በሽሮ ፈትፈት አድርገው ያመጡትን እንጀራ በግድ ያጎርሷት ጀመር መቼም ከሩቅ ዘመድ የቅርብ ጎረቤት መድሀኒት ነው የሚባለው እውነት ነው። የምግብ ፍላጎቷ ጠፍቶ ባዶ ሆዷን ነበረች፡፡
አይ እትዬ ተዋቡ ምን አሳሰበሁ? አልበላ አለኝንጂ ዘይንዬ የሰራችው ሽሮ ነበርኮ አይ የርስዎ ነገር?” የምግብ ፍላጎቱ ባይኖራትም የሚያስቡላት ጎረቤቷን ላለማስቀየም ስትል ጎራረስች፡፡ እናቷ በጤናዋ ምክንያት እንደ ልቧ ወዲህ ወዲያ ማለት ባለመቻሏ ከትምህርት ቤት ሰዓት ውጭ ዘይኑ ወደ ገበያ ትሄድና ሽንኩርቱን፣ ድንቹን፣ ቃሪያውን፣ ጎመኑን እየሽጠች በምታገኛት ሳንቲም እናቷን ታስታምማለች። ካሉት ሁለት ላሞች
መካከል አንዷ የምትታለብ ስለሆነች ወተቷን ያጠራቅሙና ከተናጠ በኋላ
ለአናት የሚሆን ቅቤ በኩባያ እያደረጉ ወደ ገበያ ይወጣሉ፡፡ አሬራው ይቀ
ቀልና አይቡ ይሽጣል። አጓቷን እነሱ ይጠጣሉ፡፡
“እማማ ይህቺ እማዬን ለምንድነው የማይመክሯት? ሁልጊዜ እያለቀስች ፊቷን አበላሸችውኮ የምሰራላትን ደግሞ አልበላም እያለች ታስቸግረኛለች፡፡ ሁል ጊዜ ቡና ብቻ ነው የምትጠጣው" እንደ ልማዷ ከንፈሯን ጣል አድርጋ ወቀሳዋን ሰነዘረች። ወይዘሮ ተዋቡ የልጅቷ ነገር አንጀታቸውን በላው። ዘይኑ በአስተሳሰቧና በአነጋገሯ የአስራ ሁለት ዓመት ልጅ
አትመስልም፡፡ ነገረ ስራዋ እንደ አዋቂ ነው።
"የውልሽ የጌትነት እናት እንኳን እኛ አሮጊቶቹ ትንሽዋ ልጅሽ የምትልሽን ትሰሚያለሽ? እሷኮ እየበለጠችሽ ነው። መኩሪያንም ቢሆን መከራሽን አይተሽ አስታመሽው የግዜር ፈቃዱ ሆኖ ነው ወደ እውነቱ ቦታ የሄደው፡፡ መቼም ሰው ጊዜው ከደረስ ምን ይደረጋል? በሀዘን ብዛት
በለቅሶ ብዛትም ከአፈር የሚነሳ የለም፡፡ ጌትነትንም ቢሆን የልቡ እንዲሳካለት መርቀን የሸኘነው ራሱን ችሎ ላንችም አለኝታ እንዲሆንሽ ነው።
ባለበት ጤና ይሁን እንጂ ምን እንዳይሆን ብለሽ ነው? ሰው ሆኖ ችግርን
የማይቀምስ የለም ችግርን አሽንፎ ደካማ እናቱን መጦር እህቱን ማስተማር እንዲችል በፀሎትሽ ያለመርሳትንጂ

❤1👍1
#የተወጋ_ልብ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_በትክክል_ገና
ለተከታታይ ቀናት ድርሰቶቹን ባለመልቀቄ
ይቅርታ እጠይቃለው የ Telegram app Update መደረግ እንዳለበት text ይመጣልኝ ነበር ባለማድረጌ አንድ ሁለት ቀን እስከሚስተካከል አስቸግሮኝ ነበር አሁን ግን የተስተካከለ ይመስለኛል እንቀጥላለን መልካም ንባብ።👇
.....“ጎንቻ! ቂጥህን ጠርጌ አሳድጌህ አንተም ሰው ሆንክና ለዚህ አበቃኸኝ?!” አለው በሚርበተበት ድምፅ፡፡ ጎንቻ ብልጭ! አለበት። “አንተም ሰው ሆንክና?” የሚለው የንቀት አነጋገር የንዴት ክብሪቱን በላዩ ላይ ጫረበት። መታገስ አቃተው፡፡ ከመቅፅበት እጁ በወገቡ ላይ ከዚያም
ከቶላ አንገት ጋር ተዋህዶ ጭንቅላቱ እያሽካካ ከበሩ ላይ ሲወድቅ የነበረው ፍጥነት እግዚኦ! የሚያሰኝ ነበር፡፡ ይህንን ትዕይንት ለሚያዩ እናትና ልጅ ጥናቱን ይስጣቸው እንጂ ጎንቻ ዶሮ ያረደ እንኳ አልመሰለውም፡፡
አወራረደውና እንጣጥ እንጣጥ….እያለ የወደቀውን አንገት ተራምዶት ሄደ ...
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ከማህፀኗ በወጣው ጉድ እንደ እሳት እየተለበለበች ነጋ ጠባ እንደተሸበረች የከረመችው ወልአርጊ ለጥቂት ጊዜ ሰላም ሰፍኖባት ነበር። ዛሬ ግን የተፈጠረው ትርዒት ከወትሮው ለየት ያለ በመሆኑ መከራዋና ሀዘኗ ሁሉ መሪር ሆኗል፡፡ እናትና ልጅ ከአልጋ ጋር ተጠፍረው ታስረው አኖቻቸው እየተቁለጨለጩ የቶላ አንገት ሲቀላ ተመለከቱ..ጩኸቱ ከአንደኛው ጎጆ ወደ ሌላው ከዚህኛው መንደር ወደዚያኛው መንደር አስተጋባ።ብራቅ...ከወልአርጊ ዘወትር ፊቷ ወደማይፈታው በጭጋግ ወደ
ተሸፈነችው ወደ ሞዬ መንደር ደረሰ፡፡ ከዚያም ወደ አኖሌ...ከዚያም ወደ ዩያ...መቼም በዘረፋው በኩል በትንሹ ፍየል ያልተሰረቀበት ጥቂቱ በመሆኑ ሁሉም ንብረቱን በዐይነ ቁራኛ በመጠባበቅ ብርቱ ጥንቃቄ በማድረግ ላይ ነው፡፡ ዛሬ የተከሰተው በአይነቱ ለየት ያለ ከተራ ሌብነት የዘለለና ለመንደሪቱ ነዋሪዎች እጅግ አስደንጋጭ የሆነ ግድያ የታከለበት የከብቶች ዝርፊያ ወንጀል ነበር። ወልአርጊ አሰቃቂውን መርዶ ለማርዳት እኩለሌሊት ለሊቱን ስታምጥ አንግታ ከጠዋቱ አሥራ ሁለት ሰዓት አካባቢ ጭንቀቷን በእሪታ ተነፈሰችው...ከአጋም የተጠጋ ቁልቋል ዘላለም ሲያለቅስ ይኖራል ሆነና የሐጂ ቦሩ ጎረቤት ቶላና ቤተሰቦቹ በጎንቻ ምክንያት በተደጋጋሚ ከማንባት ባለፈ የቶላን የህይወት ዋጋ እስከማስከፈል
የደረስ ጥቃት ሰለባዎች ሆኑ፡፡ በቶላ ቤተሰቦች ጩኽት ምክንያት የተቀሰቀሰው ህዝብ ለመስቀል በዓል እንደሚጎርፍ ምእመን ተመመና የቶላን ግቢ አጨናነቃት። የጎንቻ ወላጆች ምጥ በምጥ ሆኑ፡፡ እህ! እህ! ጭንቀት
በጭንቀት። ቀስ በቀስ ቤታቸውን አራቁቶ ከብቶቹን ሸጦ ከጨረሰ በኋላ
በአብዛኛው የሚተዳደሩት በትላልቅ ልጆቻቸው ድጎማ ነበር፡፡ ሽብር የተቀላቀለበት ዘረፋ መፈፀም የጀመረው ልጃቸው እያጎረሰ፣ ጭንቅላቱን እየደባበስ፣ ንፍጡን እየጠራረገ እንደ ወላጅ ያሳደገው ቶላን በአሰቃቂ ሁኔታ
አንገቱን እንደ ጎመን ቀንጥሶት ሄደ መቼም የእናቱ የወይዘሮ ዋሪቴ ሁኔታ አይነሳ፡፡እግራቸው መሬቱን ቆንጥጦ መያዝ አቃተውና ተብረከረኩ፡፡ የህዝቡ ዋይታና ለቅሶ በነሱ ላይ መዓቱን ያውርድባችሁ በሚል የእርግማን ጩኸት የተሞላ ነበር፡፡
“ጎንቻ! ጎንቻ! በላን! ፈጀን!የአውሬ የጅብ እናት! የአውሬ አባት! እግዚአብሔር ይይላችሁ! አይዞህ እያላችሁ በሌብነት አሳድጋችሁ አስፈጃችሁን! የዚህ ሁሉ ቁጣ የዚህ ሁሉ ግፍ ተጠያቂዎች እናንተ ናችሁ! ጥፉ ያጥፋችሁ!” የማይል የአልቃሽ አንደበት አልነበረም።
ሐጂ ቦሩ በባለቤታቸው ምክር መስረት ዘመድ አዝማዱን እየተማፀኑ
ወደ ቤቱ እንዲመለስ ሽማግሌ ልከው የሚያስለምኑበትን ቀን በተስፋ
ሲጠባበቁ፣ ገበየሁን ገድሎ መሸፈቱ ተሰማ፡፡ በዚህም ምክንያት ተስፋ
ቆርጠው ዕለተ ሞቱ እንዲቃረብ፣ የጅብ ራት ሆኖ እንዲቀርና በመቃብሩ ላይ አልቃሽ እንዳይቆምለት ፈጣሪያቸውን ሲለምኑ እሱ ግን በአቋራጭ መጣና ልክ እንደ ትንሽ ወንድማቸው የሚወዱት የክፉ ቀን ወዳጃቸው ቶላን እንደ በግ አርዶ ሄደ፡፡ ማን ያውቃል? ነገ ተነገወዲያ ደግሞ ተራው የእናትና የአባቱ ሳይሆን ይቀራል? “ያዳቆነ ሰይጣን ሳያቀስስ አይቀርም”
ነውና ጎንቻ በውስጡ ያበቀለው ቀንዳም ጋኔን ቀጥሎ የሚጠማው የዘመዶቹን ደም አለመሆኑን ማን በእርግጠኝነት መናገር ይችላል? የሰው ልጅ የማስተዋልና የማመዛዘን ችሎታው ሲዛባ፣ ከስነ ምግባር ማንነቱ ሲወጣ፣ በክፉና በመልካም ድርጊት መካከል ያለውን ልዩነት ከሚገነዘብበት የአእምሮ ብቃት ሊሸሽ፣ ራሱን ከመጠን በላይ በመውደድ መስገብገብ ሲጀምር ወደ አውሬነት መለወጡ የማይቀር ነውና ጎንቻ ከሰውነት ባህሪው ወጥቶ የክፉ ስግብግብ አውሬ ባህሪን ተላበሰ፡፡ በዚህ አካሄዱ ለሳቸውም ቢሆን እንደማይመለስላቸው የጠረጠሩት ሐጂ ቦሩ የጎንቻ ጩቤ በአንገታቸው ላይ እስከሚስካ፣ የተስበቀ ጦሩ በደረታቸው ላይ እስከሚቀረቀር ድረስ ለመጠበቅ ትዕግስት አጡ፡፡ የህዝቡን እርግማንና ጥላቻ በመቋቋም የከፈሉት ዋጋ ሳያንሳቸው የክፉም ሆነ የበጎ ጊዜ ወዳጃቸው የሚስጥረኛቸው የቶላ አሰቃቂ ግድያ በልጃቸው በጎንቻ እጅ ተፈፅሞ ማየት ግን ፍፁም ሊቋቋሙት የማይችሉት ጥቃት ሆነባቸውና በራሳቸው
እርምጃ ለመውሰድ ቆረጡ። አሮጊቷ እናትም ማህፀናቸው ጭራቕ በማፍራቱ መፈጠራቸውን ጠሉት፡፡ እግዚአብሔርን ወቀሱት። በስተመጨረሻ የተገኘው ጉድ ሰይጣን ጎብኝቷቸው እንደሆነ እንጂ እውነትም ከሐጂቦሩ የተገኘ ፍሬ መሆኑን ተጠራጠሩ፡፡ ለሁሉም ነገር አቅም አጡ፡፡ ለዋይታና ለእሪታው ልሳናቸው ተዘጋ፡፡ እምባቸው ደረቀ።
“እህህ..ጎንቻ ፈጣሪ የስራህን ይስጥህ!ከልጆቼ ሁሉ አስበልጬ አቀማጥዬ አሳድጌህ እንደሆነ ውለታውን ከሱ አትጣው! በስተርጅና በመውደቂያ ዘመኔ እናቴ ምን ልርዳሽ? ብለህ ጎኔን ልትደግፍ ተስፋ ልትሆነኝ በሚገባህ ሰዓት ከሰው እንዳልቀርብ የአውሬ እናት እየተባልኩ
ሰው እንዲሽሽኝ በመቃብሬ ላይ አልቃሽ እንዳይቆም ላደረግህልኝ ውለታ
ሼህ ሀና ሁሴን ብድሩን ይክፈሉህ! የእጅህን አትጣው።ወንድ ነኝ ብለህ
እንደፎከርክ ወንድ ይዘዝብህ...!” ብለው አለቀሱ። ከወዳጅ ዘመዶቻቸው አቆራርጦ ስማቸውን የቡና መጠጫ ባደረገው ልጃቸው የተሰማቸውን ምሬት ለፈጣሪያቸው በእምባ ገለፁ።እህቶቹና ወንድሞቹ የሚኖሩት ሩቅ ቦታ ቢሆንም ጎንቻ በየጊዜው ስለሚፈፅመው አሰቃቂ የውንብድና ተግባር እየሰሙ ተበጥብጠዋል።እነሱ ብቻ ሳይሆኑ የአካባቢው ባለስልጣን ባላባት ጉደታም ውንብድናው ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገና የጥቃት አድማሱን እያሰፋ በመጣው በጎንቻ አስከፊ ወንጀል ምክንያት ከህዝቡ በሚቀርብለት እሮሮ አእምሮው እረፍት እስከሚያጣ ድረስ ተበጥብጧል። ባልታሰበ ጊዜ ከተፍ ይልና ያምሳል፣ ያስለቅሳል፣ ያንጫጫል። አንዴ ከተሰወረ ደግሞ መኖሩ እስከሚያጠራጥር ድረስ ደብዛውን ያጠፋል። ደግሞ ሳይታሰብ ከተፍ ይልና የተለመደውን ጫጫታና ዋይታ ያስቀጥላል፡፡
የቶላ የቀብር ሥነ ሥርዓት በተካሄደ ዕለት ባላባት ጉደታ ህዝቡን በአንድ ትልቅ ዋርካ ጥላ ስር ስብስቦ የሚከተለውን ንግግር አሰማ፡፡

👍4
#ያልታበሱ_እንባዎች
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ
...«አስቻለው!» አለችው ሔዋን፤ የዘመቻ ጥሪ ደብዳቤ በደረሰው አምስተኛ ቀን ላይ በዕለተ አርብ ከጠዋቱ ሦስት ሰአት አካባቢ ከቤቱ በመገኘት።
«ወይ!» አላት አስቻለው አልጋው ላይ ጋለል ብሎ ተኝቶ ከጎኑ ቁጭ
ያለችውን ሔዋንን ቀና ብሎ እየተመለከታት።
«ሰሞኑን የምሰማው ወሬ ምንድነው?» ስትል ዓይን ዓይኑን እያየች ጠየቀችው።
«ምን ሰማሽ?»
«ጥሩ ያልሆነ ወሬ::»
«ንገሪኛ!» አላት አስቻለው ፈገግ ብሎ እያያት፡፡
«ሳታውቀው ቀርተህ ነው?»
«ብዙ ይወራ የለ! የትኛውን ማለቴ ነው፡፡»
«በመሥሪያ ቤትህ በኩል ለስድስት ወር ያህል ዘመቻ ሂድ ተብለህ እምቢ ማለትህን ሰማሁ፡፡» አለችው በፍርሀት አስተያየት እያየችው።
«አዎ! አልሄድም ብያለሁ፡፡ አሁንም አልሄድም፡፡»
«ግን ለምን?»
«እንደማልሄድ የነገሩሽ ሰዎች
ምክንያቴንም ሳይነግሩሽ የቀሩ
አልመሰለኝም፡፡ አንቺም አትደብቂኝ፡፡» አላት የሔዋንን ግራ እጅ ይዞ እየደባበሳት፡፡
«ነግረውኛል። ግን ሆዴ በጣም ፈራ»
«ለምን ብለሽ?»
«ግዳጅ ላለመቀበልህ ምክንያቷ እኔ የምሆን ስለመሰለኝ፡» አለችና ሔዋን ዓይኖቿ ላይ ያቀረረ እንባዋን በለበሰችው ስከርፍ ጥርግ አደረገች።
«አይዞሽ ሔዩ፣ አትፍሪ! ምንም አይመጣም፡፡»
«ተው እስቹ ምንም አይመጣም አትበል። ኑሮህ ሁሎ ይበላሻል፡፡ ለአንተ ኑሮ መበላሽት እኔ ምክንያት መሆን የለብኝም፡፡ የአንተ ከተበላሸ የኔም ይበላሻል»
አለችና እንባዋን አሁንም በጉንጯ ላይ ታወርደው ጀመር።
“አታልቅሺ የኔ ፍቅር። የኔ ሕያወት የሚበላሸው አንቺን ከአጣው ብቻ
ነው:: ዘመቻ ከሄድኩ ደግሞ አንቺን ላጣሽ እችላለሁ። ስለዚህ አልሄድም»
«አንተ ዘመቻ ብትሄድ እኔ የት እሄድብሃለሁ?»
«እህትሽ እና ባርናባስ እየሰሩልሽ ያለውን መንገድ እጣሽውና ነው ወይስ አልገባሽ ይሆን?»
አውቃለሁ። ገብቶኛል::»
“ታዲያ የኔ ዘመቻ መሄድ እንዴት አንቺን አያሳጣኝም ብላሽ ትገምቻለሽ»
«ፈጽሞ አስቻለው ፈጽሞ አያለያየንም።
«እንዴት?»
«እኔም ላጣህ አልፈልግምና!»
«ወደሽ ሳይሆን ያስገድዱሻል»
«አንድ ነገር አትርሺ ሒዩ! ያለሽው በእህትሽ ቤት፤ የምትበይው
የምትጠጪው የእሷን፡ በዚያ ላይ ባርናባስን የሚያህል የፖለቲካ ስልጣን ያለው ወዳጅ አላት።
በዚሁ ላይ ያቀረቡልሽ ወዳጀ በከተማው ውስጥ አለ የተባለ ሀብታም 'በድሉ አሽናፊ' የባርናባስ ስልጣንና የበድሉ ገንዘብ ከተባበሩ እንዴት እኔና አንቺን
መለያየት ያቅታቸዋል?» አለ አስቻለው ከተንጋለለበት ቀና ብሎ ሔዋንን ፊትለፊት እያያት፡፡
«ይህን ሁሉ ግን የታመነ ልብ ያሸንፈዋል::» አለችው ሔዋን የአስቻለውን ደረት እየደባበሰች።
«ፈጽሞ፡ በበኩሌ ማመን ያስቸግረኛል።»
«ስማ አስቻለው!»
«ወይ የኔ ፍቅር»
«እኔንም አንተንም ለአደጋ የሚያጋልጥ አጋጣሚ የሚፈጠረው አንተ ዘመቻ አልሄድም ብለህ የቀረህ እንደሆነ ነው::»
«እንዴት?»
«ዘመቻ ካልሄድክ ከሥራ ያስወጡሃል! ወይም ያስሩሃል። ምናልባት ሊገድሉህ ወይም ሊያስገድሉህ ይችላሉ። አየህ አስቹ! ሥራ ከሌለህ ገንዘብ
አይኖርህም። ገንዘብ ከሌለህ ደግሞ ችግር ያበሳጭህና ለችግርህ ምክንያት በሆኑ
ሰዎች ላይ አደጋ አድርስህ በሌላ የከፋ ችግር ወስጥ ልትገባ ትችላለህ:: ያኔ ልብህ ለጭካኔ እንጂ ለፍቅር ቦታ አይኖረውም፡፡ ዞሮ ዞሮ ለኔ አልሆንከኝም። ታስረህ ማየቱም ለአዕምር'ዩ አይመቸውም፡፡ ብትሞትም ሀዘኔ መራርና የዕድሜ ልክ ነው፡፡
ግን ይህ ሁሉ ይወገድ ዘንድ ግዳጁን ተቀብለህ መሄድ ስትችል ለምን ሁለታችንም እንቸገራለን?» አለችው በትካዜ ውስጥ ሆና ዓይን ዓይኑን እያየች።
«ሔዩ የኔ ችግር አልገባሽም፡፡»
«ገብቶኛል። ግን እሱም ቢሆን መላ አለው::»
«ምን ታየሽ?»
«በቃ እኔ ከእት አበባ ቤት እወጣና አንተ በምትቆርጥልኝ ገንዘብ ከትርፍዬ ጋር በአንተ ቤት ውስጥ እኖራለሁ፡፡ ግዳጅህን ፈጽመህ ስትመለስ እኔና አንተ ራሳችን በምንደግሰው ሰርግ ተጋብተን አብረን መኖር እንችላለን:: ለኔና
ለአንተ ፍቅር የሚበጀው ይሄ ብቻ ነው።
ከዚህ በኋላ ሁሉቱም ትካዜ ወስጥ ገቡ። ሁለቱም በየበኩላቸው ያስቡ ጀመር
በየልባቸው ያለውን ነገር በማስታወስ።
እሷ አላወቀችም እንጂ ዛሬ ሔዋን ያቀረበችው ሀሳብ አስቻለው ራሱ
በተካፈለበት ጉባዔ ላይ የተቀየስ አቅጣጫ ነበር፡፡ እርግጥ ነው የአስቻለው የዘመፍቻውን ግዳጅ ያለመቀበል ውሳኔው እጅግ ጠንካራ ነበር፡፡ ነገር ግን ታፈሡና
በልሁ መርእድን ጨምሮ ሀሳቡን እንዲቀይር ብዙ ታግለውታል የስድስት ወር ጊዜ አጭር
መሆኗን ዘመቻውን ባለ መቀበሉ
ከሥራ መባረር ምናልባት እስር፣ ከዚያም ያለፈ ክፉ ነገር ሊመጣ እንደሚችል እየጠቀሱ ሊያግባቡት ሞክረዋል በዚያው በራሱ ቤት መርዕድና በልሁ ጫት እየቃሙ ታፈሡ ራሷ እስከ ውድቀት ሌሊት ድረስ አብራቸው በመቆየት በዚሁ ጉዳይ ላይ ከአስቻለው ጋር የተፋጩት ገና ደብዳቤው በደረሰው ማግስት
በአስቻለው ግዳጅ የመቀበልና
ያላመቀበል ውይይት ወቅት ጉልህ ሥፍራ ተሰጥቶት የነበረው የአስቻ ለውና የሔዋን ፍቅር ጉዳይ ነበር።
ለአስቻለው ለግዳጅ መመልመል የባርናባስ ሚና ወሳኝ ሊሆን እንደሚችል ሁሉም አምነውበታል እሱ ደግሞ ከራሱ ፍላጎት በተጨማሪ ሸዋዬ የምትጥልበትን
አደራ ለመወጣት ጭምር አስቦና ተገፋፍቶ የፈጸመው ስለመሆኑ አይጠራጠሩም።ሁለቱ ሰዎች የአስቻለውን አለመኖር ተጠቅመው ሊፈፅሙት ያቀዱት ነገር በሁሉም አእምሮ ውስጥ አለ። ሔዋንን ከበድሉ አሸናፊ ጋር ሊያላምዱ ነው። ይህ ደግሞ በአስቻለውና በሔዋን ፍቅር ላይ ጥላውን ሊያጠላ ነው።
ይህን አደጋ ለመከላከል ይቻል ዘንድ መላ መልምለዋል። በአንድ ወይም በሌላ መንገድ ሔዋንን ከሸዋዬና ከባርናባስ መዳፍ ውስጥ ፈልቅቀው ማወጣት፣
ዋሽቶም ለምኖም ሔዋንን የችግሩ ፈቺ አንድ አካል ማድረግ፡፡ በዚህ ጉዳይ አስቻለውን ጨምሮ ሁሉም ተስማምተዋል። ሔዋንን የማሳመን ጉዳይ ለታፈሡ እንግዳሰው ተሰቷት እሷም የተጣለባትን ሃላፊነት ለመወጣት አልዘገየችም፡፡ለአስቻለው የዘመቻ ትእዛዝ በደረሰው አራተኛ ቀን ላይ ነበር ሔዋንን ከመሰረተ ትምህርት ሥራዋ ስትመለስ ወደ ቤቷ ጎራ እንድትል የጠየቀቻት፡፡ሔዋንም
ጥያቄውን ተቀብላ ከታፈሡ ቤት ተገኘች።
«ሔዩ ተቸግረናል» ነበር ያለቻት ታፈሡ ሔዋንን ሶፋ ላይ አስቀምጣ እሷም ከፊትለፊቷ በመቀመጥ፡፡
«ምን ሆናችሁ?»
«አስቻለው በመሥሪያ ቤቱ በኩል ዘመቻ ታዝዞ ነገር ግን አልሄድም
በማለቱ እኔም በልሁና መርዕድም ተጨንቀናል፡፡»
«ዘመቻ?»
«አዎ»ለስድስት ወር ብቻ ለሚቆይ የሙያ ዘመቻ ወደ ኤርትራ እንዲሄድ በደብዳቤ ታዟል።እሱ ግን ሔዋንን በሸዋዬ ቤት ውስጥ ትቼ አልሄድም እያለ አስቸግሮናል»
«ኤርትራ ማለት የጦርነቱ አገር አይደል?»
«አዎ፣ እሱ ግን የሚሄደው ሊዋጋ አይደለም በጦርነቱ ለሚጎዱ ቁስለኞች የህክምና አገልግሎት ሊሰጥ ነው።»
«ታዴያ አንዴት ይሻላል?»
«ችግሩ ያለ አንቺ አይፈታም»
«ምን አድርጌ እፈታዋለሁ?»
«አስቹ የሚለው ወደዚህ ዘመቻ እንድሄድ ያደረጉኝ ሸዋዬና በርናባስ ናቸው። ዓላማቸውም ሔዋንን ለበድሉ አሸናፊ ሊድሩ አስበው ነው።ስለዚህ ፍቅሬን ከማጣት እነሱ ላይ አደጋ አድርሼ እስር ቤት ብገባ ይሻለኛል እያለ ድርቅ አለብን»

👍12