አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
571 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የፍቅር_ሰመመን


#ክፍል_ሀያ_ሁለት



#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን


#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው

መርማሪ ፖሊስ ሚክ ጆንሰን ካርተር በርክሌ ውድ ሽሚዙን በደንብ ማኒኩየር በተሰራው ጣቶቹ በደንብ አድርጎ አስተካከለው:: የዶክተር ሮበርትስ
ታካሚ የሆነው የኢንቨስትመንት ባንከሩ ካርተር በርክሌ ሁሉ ነገሩ ውዷ ነው፡፡ ምርጥ መኖሪያ ቤት፣ ምርጥ ምርጥ የቪንቴጅ ጃንዋር ስፖርት መኪኖች እና ሁሉም ቁጭ ያሉበት በምርጥ ሁኔታ ፈርኒሽድ የተደረገው የቤት ውስጥ ቢሮው እራሱ በጣም ውድ ነው፡፡ እንኳን እቃዎቹ ሲያወራ የሚጠቀምባቸው ቃላቶች ሁሉ በጣም የተመረጡ ናቸው፡፡
እዚህ ቢሮ ውስጥ ቁጭ ብለው እያወሩ እያሉ ካርተር ትላንትና ማታ መኝታ ቤቱ ውስጥ የሆነ ሰው ሊያስፈራራው በማሰብ የሞተ አይጥ አስቀምጦ እንደነበር እየነገረው ነበር። የሞተ አይጥን ማስቀመጣቸው የማፍያዎች ማስፈራሪያ ስልት እንደሆነ ጭምር እያስረዳው ነበር፡፡

“ይሄን ነገር ያደረጉት በእርግጥም እኔን ሊያስፈራሩ አስበው ነው፡፡ደግሞም ተሳክቶላቸዋል። ባይገርምህ መርማሪ ፖሊስ ጆንሰን እናንተ ወደ እኔ ባትመጡ እንኳን እኔ እራሴ ጉዳዩን ለማመልከት ወደ እናንተ መምጣቴ አይቀርም ነበር።

ጆንሰንም ራሱን በአዎንታ በመነቅነቅ የቤቱን ዙሪያ ሲመለከት ዕቃዎቹ
በደንብ ከመወልወልም በላይ የመፅሀፍ መደርደሪያው ሼልፍም ራስን
በመገንባት ላይ እና በፋይናንስ ዙሪያ በተፃፉ መፅሀፍት በሥርዓት
ተጠቅጥቀዋል። አሁን ላይ ካርተር በርክሌይን እየተመለከተው ያለው ጆንሰን
ዶክተር ሮበርትስ ስለ ካርተር ከማስታወሻዋ ላይ ከፃፈችው ነገር ጋር
በመስማማቱ ተናደደ፡፡

ጆንሰን ካርተርን አስመልክታ ኒኪ የፃፈችውን ሲያነብ “መቀወሱ
ያልተረጋገጠ በከንቱ ስሜት ውስጥ የሚናውዝ የሜክሲኮ ወንጀለኞች
ሊገድሉት እንደሚያሳድዱት የሚናገር (ለዚህ ምንም ማረጋገጫ የሌለው)
ለረዥም ጊዜ በጭንቀት ውስጥ የኖረ። ምናልባት በልጅነቱ በደረሰበት ስቃይ
ምክንያት ሊሆን ይችላል? (ወይንም ደግሞ ሜክሲኮ ውስጥ በጉርምስናው
ዘመን ኖሯልና ምናልባት እዚያ የሆነ ነገር ተከስቶ ይሆን?) ውስጡ ያላደገ
ቋሚ የሆነ ፆታዊ ግንኙነት የሌለው እና በግንኙነት አብረውት ያሉ ሰዎችንም በጣም አድርጎ የሚቆጣጠር ነው።” ይላል ማስታወሻው፡፡

ዶክተር ሮበርትስ ካርተር በርክሌን የገለፀችበት መንገድ በሙሉ የተቀበለው ቢሆንም አንድ ነገር ረስታለች እሱም “የሰዎች አትኩሮትን (ታይታን) የሚፈልግ ባህሪ ያለው መሆኑ ነው። ይህንን ደግሞ በእሱ ላይ ያላየችው እሷም የዚህ ልክፍት ስላለባት ነው ብሎ አሰበ፡፡ ለዚህም ነው
ካርተር ከዚህ በፊት በተካሄዱት ግድያዎች ውስጥ ዋነኛ ተፈላጊ ሰው መሆኑን ለማሳየት ያጫወተውን የአይጥ ታሪክ ፈጥሮ ለጆንሰን የተናገረው።


ይሄ ቀሽም ሰው ራሱን እንደተፈላጊ ሰው ያያል ወይንም ደግሞ የሆነ እሱ ስለግድያው የሚያውቀውን ነገር እንዳላውጣጣው እያዘናጋኝ ነው
ብሎም አሰበ፡፡

“ቤትህ ውስጥ ጠባቂዎች አሉህ መሰለኝ?” ብሎ ቅድም ወደ ቤቱ ሲገባ
የተመለከታቸውን ብዙም ስልጠና እንደሌላቸው የሚያስታውቁትን የጥበቃ
ሰዎቹን አልፎ እንደገባ አስታውሶ ካርተርን ጠየቀው። ቤቱ ውስጥ ሲገባ ከጠባቂዎቹ ሌላም የሲ.ሲ.ቲቪ
ካሜራዎችንም አይቶዐካሜራዎችንም በየቦታው ገጥመሃል አይደል እንዴ?”

“አዎን ቤቱ ጥበቃ ስለሚያስፈልገው በጠባቂዎችም፣ በካሜራም ነው
የሚጠበቀው። ግን ዋናው መኝታ ቤቴ ውስጥ ካሜራ አልገጠምኩኝም” ብሎ
መለሰለት፡፡

ጆንሰንም “ለምን ዋናው መኝታ ቤትህ ውስጥ ካሜራ አላስገጠምክም?
ብሎ ጠየቀው፡፡

ባንከሩም እንዴት ይሄ አይገባህም በሚል ሀሳብ ይመስል የጎረምሳ ፈገግታ ከለገሰው በኋላ “እዚህ ጋር የተማረ ሰው ግምት ይኖርሃል ብዬ አስባለሁ። ጠባቂዎቼ ከሁሉም ካሜራዎች በቀጥታ መረጃዎች ይደርሳቸዋል።እኔ ደግሞ በግሌ የማደርጋቸውን ነገሮች ማንም እንዲያውቅብኝ አልፈልግም። ለዚያም ስል ነው በዋናው መኝታ ክፍሌ ውስጥ ካሜራ ያላስገጠምኩት፡፡ በሁሉም ወደ ቤቴ በሚያስገቡ በሮች ላይ ካሜራ
ተገጥሞባቸዋል። እሱ ላይ ብቻ ሳይሆን ፎቅ ላይም ካሜራዎችን
አስገጥሜያለሁ። ስለ እዚህ ወደ እዚህ ቤት የሚገባም ሆነ የሚወጣ ሰው
በካሜራው መታየት ይችላል” ብሎ መለሰ፡፡

“መልካም” አለና ጆንሰን በመቀጠልም “የሞተውን አይጥ መኝታ ቤትህ
ተቀምጦ ካገኘህ በኋላ መቼስ ካሜራዎቹ የቀረፁትን ቪዲዩዎች ተመልክተሀቸዋል አይደል?” ብሎ ጠየቀው፡፡

“አዎን አይቻቸዋለሁ”

“ግን ማንም ሰው አላየህም?”

ቤቴ ውስጥ ከሚሰሩ ሰዎች በስተቀር አንድም ሰውን አላየሁም። ይሄ ታዲያ አይገርምም?” ብሎ የሸሚዙን ኮሌታ በሀይል ጎተተው።

“እና እንዴት ነው ይሄ አንተ የማፍያዎች የማስፈራሪያ መንገድ ነው ብለህ ያሰብከውን የሞተውን አይጥ መኝታ ቤትህ ድረስ ሊያስቀምጡ የቻሉት?” ብሎ ጆንሰን ጠየቀ፡፡

ካርተርም ፊቱ ላይ ግራ የመጋባት ፊት እያሳየው “እኔ ይሄንን በምን አውቃለሁ? መርማሪ ፖሊሱ እንግዲህ አንተ ነህ አይደል? አንተው ንገረኝ
እንጂ” ብሎ መለስ፡፡
“እና ቪድዮው ላይ አዲስ ሰው እስካላየህ ድረስ ቤት ውስጥ የሚሰራ
ሰው ነው አይጡን መኝታ ቤትህ ያስቀመጠው ማለት ነው፡፡ አይመስልህም?”ብሎ ጠየቀው እኔ ጋር አለ ብሎ ባልጠበቀው የራሱ ትዕግስት ጭምር እየተገረመ፡፡

“ይሄማ ሊሆን አይችልም፡፡ ምክንያቱም እኔ እነዚህን ሰዎች ስቀጥር
የበፊት ህይወታቸውን በሚገባ አስጠንቼ እና ተጠንቅቄ ነው፡፡ ስለሆነም
አሁን አንተ የተናገርከው ነገር ሊሆን አይችልም...”

ብሎ ያሰበውን ነገር ተናግሮ ሳይጨርስ ጆንሰን አቋረጠው እና ምናልባት አይጡን ልታሳየኝ ትችላለህ? ስለዚህ አይጡን አንስቼ ምርመራ እንዲደረግበት ማድረግ እችላለሁ” አለው ከወንበሩ ላይ ተነሳ፡፡
“አይጡን ላሳይህ አልችልም” ብሎ መለሰለት፡፡ ጆንሰንም የካርተርን
መልስ ሲሰማ ዶክተር ሮበርትስ “ዝም ብሎ የቅዠት ሀሳብ የሚፈጥር ብላ
የተናገረችው ነገር ትክክል እንደሆነ አወቀ።

ለምንድነው አይጡን የማታሳየኝ?” ብሎ ኮስተር ብሎ ጠየቀው እና ለእንደዚህ አይነት ሰው ዶክተር ሮበርትስ እንዴት በየቀኑ የቴራፒስት ህክምና ልትሰጥ እንደምትችል ራሱን ጠየቀ፡፡ እንደዚህ አይነቶቹ ቴራፒስቶች አፍንጫቸው መመታት የለበትም ታዲያ?

“ትላንትና ማታ ነው አይጡን ያገኘሁት እሱን ደግሞ ነግሬሀለሁ አይደል?” ብሎ ካርተር ክርክሩን በመቀጠል “ቤቴን የምታፀዳው ሴት ደግሞ እስከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ድረስ አልመጣችም ነበር፡፡ እሷ እስክትመጣ ድረስ ደግሞ አይጡን ክፍሌ ውስጥ ልተወው አልችልም፡፡ ምክንያቱም አይጡ ምን አይነት በሽታ ይዞ እንደመጣ ማንም አያውቅም፡፡” ብሎ መለሰለት።

“እና መረጃ የሚሆነንን ነገር ነው የጣልከው?”

“መጣል ነበረብኝ”

“አይጡን ከክፍልህ ስታስወግድ ያየህ ሰው አለ?”

የለም ያው እንዳልኩህ በጣም መሽቶ ነበር” ብሎ ሲመልስለት የጆንሰን
ትዕግስት ተሟጥጦ ስላለቀ አሁንም ከተቀመጠበት ወንበር ላይ ተነሳ፡፡
የታለ ቆሻሻ የምትጥልበት የቆሻሻ ማስቀመጫህ? ምናልባት አይጡ
እዚያው ቆሻሻ መጣያው ውስጥ ይኖር ይሆናል ይሄኔ” አለው ጆንሰን
ይህንን የጆንሰን ጥያቄ ሲሰማ ቢያንስ ካርተር ማፈር ነበረበት፤ ግን እሱ
ይበልጥ ድርቅ ብሎ “አሁን ላይ በእርግጠኝነት ባዶ ነው የሚሆኑት። ቆሻሻ የሚሰበስቡ ሰዎች ዛሬ በጠዋት ነው ያለወትሮ የመጡት። ያንን አስቢ
አይጡን ሌላ ቦታ ማስቀመጥ ነበረብኝ፡፡ ወይም በጣም ነው ያጠፋሁት.”ጆንሰን ወደ ዋናው የፖሊስ ማዘዣ ጣቢያ ለመመለስ መኪናውን በተጨናነቀ መንገድ ላይ ሲያሽከረክር ከአንድ ሰዓት በላይ ፈጅቶበታል ጣቢያውም የደረሰው በሚያስጠላ
👍2
#የወድያነሽ


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#ድርሰት_በኀይለመለኮት_መዋዕል


....የውስጤን ሥቃይና የሕሊናዬን ሰፊ ጠባሳ ጠልቀው ያላዩ የቅርብ
ዘመዶቻችን «ዛሬማ ተበላሽቶ፣ የሱ ነገር እንዲህ ሆኖ ቀረ፡፡ ያየህይራድን የመሰለ
አንበሳ አባት እያለው ወግ ማዕረግ ያለማየቱ...» እያሉ ያጉመተምታሉ፡፡ ከቤት
ውጪ ማደሬ ያለ ማቋረጥ በመዘውተሩ ሁኔታውን መላው ቤተሰብ ከዳር እስከ
ዳር ዐወቀ፡፡ ደግማ ደጋግማ እናቴ እያፈረች፣ እኅቴ በተለይም የእናቴ
ምስጢረኛና የቅርብ ጓደኛ ወይዘሮ አማረች መኝታ ቤት ድረስ እየገቡ፣ ተው
ደግም አይደል የትልቅ ሰውና የጨዋ ልጅ እንዲህ አይደለም፡፡ እናትህ ብታለቅስ
ታደርስብሃለች» እያሉ ለወጉ ያህል ገሠጹኝ፡፡

እኔን የምመክራትና የምዳኛት ወደ ፊትም ሆነ ወደ ኋላ የማስኪዳት እኔው ራሴ ብቻ በመሆኔ የእነርሱን ምክር ሁሉ እንደሚያልፍ የበረዶ ውሽንፍር
ቆጠርኩት። በጠቅላላ መጻሕፍቶቼንና ልብሶቼን ውስጥ ውስጡን አንድ በአንድ
እግዥ ጨረስኩ፡፡ ከሁለትና ከሦስት ቀን አዳር በኋላ ወደ ወላጆቼ ቤት ስገባ ዘና
ብሎ የሚያናግረኝ ሰው አልነበረም፡፡

አባቴም ከቤት ውጪ በተደጋጋሚ ማደሬንና እንደ እናቴም አባባል «መዛተሌን» ቀስ በቀስ ሰማ።

«አግባ! ትዳር ንብረት ያዝ፣ እንደ ማንም የባለጌ ልጅ ሰፈር ለሰፈር
እትልከስከስ፣ ጎጆ ያስከብራል፣ ትዳር ግርማ ሞገስ ነው ያልኩህ ለዚህ ብዬ ነበር፡፡ያለበለዚያ ግን አካለ መጠን ከደረሰ ጐረምሳ ጋር ምን ያታግለኛል» ብሎ
ከነከተቴው ችላ አለኝ፡፡

ዋል አደር ብሎም «አደጋ ብቻ እንዳያገኘው እንጂ ልቡ መለስ
ሲልለትና ያበጠው ልቡ ሲሟሽሽ እንዳረጀች ውሻ ክትት ይላል» አለና ይብሱኑ ስለ እኔ የነበረውን 'አለና የለም ወይ?” እርግፍ አድርጎ ተወ፡፡

የሐሳቤ ተፃራሪ የሆነው አባቴ እንደ አህያ ሬሳ ቢጠላኝም ቅር አላለኝ፡፡ እኔ ግን «ይህ ነው ለሰው ልጅ የሚሰጠው ታላቅ የመኖር ጸጋ ብዬ ከጥላቻው ውስጥ ብርታትና እፎይታ የተሸለምኩ መሰለኝ።
ወደ ወላጆቼ ቤት ባሰኘን ጊዜ ገብቼ ባስፈለገኝ ሰዓት ውልቅ ማለት
ለመድኩ፡፡ እንደ ምኞቴ ሳልዘጋጅና ሳላስበው፣ የኑሮዬንም አዝማሚያ በሚገባ ሳላቅድ ድንገት ባለትዳር በመሆኔ ኑሮ በመጠኑ ተደናገረኝ። ሆኖም ትዳራችን የተመሠረተው በጽኑ ፍቅር ላይ በመሆኑ ፍላጎቴና ጉጉቴ ሁሉ ነጋ ጠባ
ለመሻሻልና አስደሳች ለውጥ ለማግኘት ሆነ። ወትሮ በቀላሉ ደንግጦ ይበረግግ
የነበረው አእምሮዬ የድፍረትና የወኔ ካፈያ ተርከፈከፈበት።

የየወዲያነሽን ቀኝ እጅ ያዝ አደርግና «ዛሬ ምን ያስፈልገናል?» ስላት ዐይን ዐይኔን እያየች እና የኮቴን አዝራሮች በጣቶቿ እየጠራረገች «ካለህማ....ያህል ይበቃኛል» ብላ ገንዘብ ስትጠይቀኝ የትዳርን አያያዝና አመራር ቀስ በቀስ
ለመድነው። በየወዲያነሽ በኩል የተቸገርኩበት ጉዳይ ቢኖር፡ ስትተኛም ይሁን ስትነሣ ስትበላም ይሁን ስትጠጣ አረ ተው ጌታነህ፡ ኧረ ተው! እረ ተው
ልጄን አሳየኝ? ሞቶም እንደሆነ ቁርጡን ንገረኝ ባይኖር ነው እንጂ ቢኖርግ
መቼ እንዲህ ዝም ትለኝ ነበር?» እያለች ስለምትጨቀጭቀኝ ነበር፡፡ ምንም እንኳ
አንዳንድ ነገርን አገላብጠው የማያዩ ቀባጣሪዎች «ጨካኝ አረመኔ ነች» እያሉ
እንደሚያሟትና ወደ ፊትም እንደሚያባጥሏት እያሰብኩ ለጊዜው ብበሳጭም እኔ ከማንም ይበልጥ የእኔዋን እና ቅኗን የወዲያነሽን አሳምሬ ስለማውቃት አባባላቸው ሁሉ ከወሬ እንኳ የነፈሰበት ተራ ወሬ ነው ብዬ እንደ ቤት ጉድፍ ጠራርጌ ጣልኩት።

ያን በማሕፀኗ ዘጠኝ ወር ሙሉ ተሽክማ በስንት የኑሮ ሥቃይ እና ውጣ ውረድ የወለደችውን ልጅዋንና አካሏን ለማየት እያለቀሰች ብታስቸግረኝም
የእናትነት ወጓ በመሆኑ ምንም ቅር አላለኝም፡፡

አንድ ቀን እሑድ ጥዋት ለቁርስ እንደ ተቀመጥን ሳላስበውና
የሚያጋጥመኝን ሳልጠራጠር ከኪሴ እንድ ትንሽ ሰማያዊ ማኅደር አወጣሁ፡፡
በውስጡ የነበሩትን ልዩ ልዩ ሥዕሎች ተራ በተራ ስመለከት የወዲያነሽም
እጅዋን ትከሻዬ ላይ ጣል አድርጋ ትመለከት ነበር፡፡ የልጃችንን ሥዕል ኣየት
እንዳደረገች «ይኸውና» ብላ ባስደንጋጭ ሁኔታ ጮኸች፡፡ ከእጄ ላይ መንጭቃ
ደረቷ ላይ ለጠፈችው።

እነዚያ በእንባ ተኮትኩተው ያደጉት ዐይኖቿ የእንባ ኩልልታ እንጠፈጠፉ፡፡ ሥዕሉን ጠረጴዛው ላይ ወርውራ እግሬ ላይ ዘፍ አለች፡፡ እግሬን ባላት ጠቅላላ ኃይል ቁልቁል ጨምድዳ ስለ ያዘችው ጎትቼ ማላቀቅ አቃተኝ።

«ብዙ ሥቃይና መከራ ያየሁበት፣ ተንገላትቼ የተንከራተትኩበት የበኸር
ልጂ ነውና አለበት ድረስ ወስደሀ እሳየኝ፡፡ እናት አባትሀም ቤት ከሆነ ከሩቅ
ልየው:: ዐይኑን አይቼና ኣንድ ጊዜ ስሜው ልሙት!» ብላ ጫፈ ድልዱሙን
ጥቁር ጫማዩን ዕንባ አርከፈከፈችበት። የምይዘውና የምለቀው ጠፋኝ፡፡ ቁርጡን
ለማወቅ ቆርጣ መነሣቷን ስላወቅሁ ኣበይ ተነሽ ልብስሽን ቀያይሪና እንሂድ!
እይተሽው ለመመለስ እንጂ ይዘነው መምጣት አንችልም» አልኳት። እግሬን
ሳትለቅ አሻቅባ እያየች «እኔም ይዤው ልምጣ አልልም፣ ዐይኑን ብቻ አንድ ጊዜ
ልየው፣ በሕይወት መኖሩን ብቻ ልይ!» ብላ የልቧን አውጥታ ተናገረች።

በጉንጫ ላይ የሚንኳለለው ትኩስ እንባ የልቤን የፍቅር ወለል ቦረቦረው።ተነሥታ ወደ ጓዳ ስትገባ አረማመዷ እንኳ አሳዘነኝ። የባዕድ ሀላፊ አግዳሚ ያህል
እንኳ የማይተዋወቀችን እናትና ልጅ እንዴት አድርጌ እንደማስተዋውቅ ጭንቅ
ጥብብ አለኝ፡፡ እማምዬ እያለ በእናቱ ክንዶች ላይ ያልተዘናከተን' አልቅሶ
ያልተባበለን ሕፃን፣ ዐይኑ አይቶ ሕሊናው ያልመዘገባትን፣ አልቅሶም ይሁን በማቅ
ተንከትክቶ ዕቅፏ ላይ ያልተዘረገፈን ልጅ እንዴት አድርጌ እማማዬ እማማ
ለማሰኘት እንደምችል አጀማመሩም ሆነ አፈጻጸሙ ስማይን መቆንጠር መስሎ
በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ልብሷን ቀይራ ብቅ አለች፡፡ ኣጭር ዞማ ጸጉሯ በሚያምር ሐምራዊ ሻሽ ሽብ ተደርጓል፡፡ ኣጠገቤ መጥታ ቆም ካለች በኋላ በል አታጓጓኝ ይኸው መጣሁ! እንሂድ! » ብላ አሰፈሰፈች፡፡

የረሳችውን ሕፃን፡ ልጅሽ ይኸ ነው ብዬ ሳሳያት፣ ኣቅፋው በደስታ ስታለቅስ እና የልጁም በሁኔታው መደናገጥ ገና ከሩቁ አሽቆጠቆጠኝ፡፡

«የምንሄድበት ቦታ እኮ በጣም ሩቅ ነው» አልኳት፡፡ ግድ የለህም ስለ መንገዱ ሰማይ ጥግ ይድረስ፣ እንሂድ ብቻ' » ብላ ቆርጣ መነሳቷን ወደ በሩ በመራመድ ገለጸች፡፡ ከአስራ አምስት ደቂቃ ጉዞ በኋላ በታክሲ ዕጓለ ማውታ ግቢ ደረስን። ለሁለተኛ ጊዜ ከሴት ጋር ያዩኝ የድርጅቱ ዘበኞችና ሌሉች ሠራተኞች እርስ በርሳቸው በመተያየት ተጎሻሽሙብኝ፡፡
ሕፃናቱ ሁሉ ልዩ ልዩ ቅርዕና መልክ ያላቸው መጫወቻዎችና አሻንጉሊቶች ይዘው በምድረ ግቢው ሜዳ ላይ እንደ እውድማ ዳር ጥሬ ፈስሰዋል፡፡ ኳስ እያንከባለለ የሚጫወተውን፣ ጅዋጅዌ የሚገፈትረውን፣ ወለሉ ላይ
በተሽከርካሪዎቿ እየተገፋች የምትሽከረከር መኪና ይዞ ራን ራን ጵጵ! ቢብ! የሚለውን፣ ሜዳ መኻል እየተሯሯጡ ድብብቆሽ የሚጫወቱትን ሁሉ አየናቸው::

ለጊዜው ልጃችንን ስላጣሁት ዐመዴ ቡን አለ፡፡ እጄን ኮት ኪሴ ውስጥ
ወሽቄ ከቤት እንደ ወጣን የገዛሁለትን ከረሜላ ማሻሸት ጀመርኩ፡፡ የየወዲያነሽ
ዐይኖች በተስፋ ብርሃን ተከበቡ። የናፍቆት ጎተራቸው አፉን ከፈተ። የጉጉቷ ጥም ተንሰፈሰፈ። ዐይኖቿን ቅርብና ሩቅ ድረስ እየላከች ኣየች፡፡ ሰውነቷ የሚንቀጠቀጥ መሰለ። ውሪ ብጤ ሩጭሩጭ እያለ ባጠገቧ ባለፈ ቁጥር ዐይኖቿ እግሮቹን ተከትለው ይጓዙና በዚያው ፈዝዘው ይቀራሉ፡፡

በመኻሉ አንድ አጠር ጠበብ ያለች ነጭ ሱሪ የታጠቀና ዐመድማ ሹራብ
የደረበ ድምቡል ያለ የሚያምር ልጅ ዝንጉርጉር ቢራቢሮ በግራ እጁ ይዞ
እያንደፋደፈና እፍ እያለባት ከፊት
👍3
#የተወጋ_ልብ


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#ድርሰት_በትክክል_ገና

...ሥራ ከጀመረ አንድ ዓመት ሞላው። ከእናትና ከእህቱ ተለይቶ በናፍቆታቸው እየተሰቃየ አንድ ድፍን ዓመት አስቆጠረ። በአማረችና በሱ መካከል የተጀመረው ጓደኝነትም ውስጥ ውስጡን የሚያብከነክን የሚያብስለስል ነገር ግን ገሀድ ያልወጣ ድብቅ ቢሆንባቸውም የሙቀት መጠኑንና የእድገት ደረጃውን ጠብቆ በመጓዝ የአንድ ዓመት ልደቱን አከበረ።

ለአዲሱ አለቃው ለልዑል ሰገድ አስጨናቂና ፈታኝ ሰው እየሆነበት
ከመጣ አንድ ዓመት ሞላው። በዩኒቨርስቲ የሚከታተለው ትምህርት አካውንቲንግ መሆኑ በፍጥነት ወደ ሂሳብ ክፍል ለመዛወር ያስቻለው ቢሆንም አዲሱ አለቃው ልኡልሰገድ በዝውውሩ ደስተኛ አልሆነም። ገናለገና በትምህርት ይበልጠኛል የወደፊት የዕድገት ተስፋዬን ያጨልምብኛል በሚል ፍርሃት ጥምድ አድርጎ ይዞታል። በአንፃሩ ደግሞ ከቀድሞው አለቃው ከሽመልስ ጋር የነበራቸው ግንኙነት ተጠናክሮ ላለፈው
አንድ ሙሉ አመት የሚያስቀኑ ጓደኛሞች በመሆን ዘልቀዋል፡፡ ሁለተኛው ዓመትስ በምን ይቀጥል ይሆን? በሱ በኩል ሁለተኛው ዓመት የእናቱንና የተወለደባት ቀዬውን ናፍቆት ለመወጣት የዓመት እረፍት ፈቃዱን ወስዶ ወደ ባሌ የሚሄድበት፣ ከአማረች ጋር ያለው ግንኙነት ይበልጥ የሚጠናከርበት፡ዘይኑን አምጥቶ አዲስ አበባ ትምህርት እንድትጀምር የሚያደርግበት ዓመት እንደሚሆን ዕቅድ ይዟል::
የጌትነት እናት ኑሮዋ እያማረ ደስታዋ እየጨመረ በመሄዱ “ ተመስገን
ፈጣሪዬ ላንተ ምን ይሳንሀል?"እያለች ፈጣሪዋን ማመስገን ከጀመረች አንድ ዓመት ሞላት። ዛሬ ዕድሜ ለጌትነት ችግር ተወግዷል። በየማሳው ላይ እየዋሉ በፀሃይ መጠበስ ቀርቷል። ደብዳቤው በየጊዜው ይጎርፋል አለሁልሽ የሚላት ልጅዋ ያለማቋረጥ ተቆራጭ አድርጎላታል።"ገበያ እንዳትወጪ አቅም የለሽም እኔ አለሁ አይዞሽ!” ነው የሚላት። ወደ ዓመቱ መጨረሻ ላይ የላከው ደብዳቤ ደግሞ በሚቀጥለው ዓመት ዘይኑን ወስዶ ለማስተማር ያለውን ሀሳብ የሚገልጽ ሆነ፡፡ ከእናቷ መለየቷን ባይወደውም በቅርበት አስፈላጊውን ክትትልና እገዛ እያደረገላት ጥሩ ደረጃ ላይ
እንድትደርስ ሌላ አማራጭ አልነበረውምና ይህንኑ ገልፆ ደብዳቤ ለእናቱ ጻፈላት፡፡
እናቱ አስካለ ደብዳቤው ሲደርሳት አላንገራገረችም፡፡ ሀሳቡን በደስታ ተቀበለችው። ዘይኑ ግን ሀሳብዋ ለሁለት ተከፈለ። የወንድሟን ናፍቆት ለመወጣት መሄዱን ስትፈልገው ከእናቷ መለየቱ ደግሞ ሆዷን አባባውና መንታ መንገድ ላይ ቆመች። ትንሿ ዘይኑ ለአንድና ብቸኛ ወንድሟም ሆነ ምትክ ለሌላት እናቷ ያላት ፍቅር እኩል ነው፡፡ እናት ደግሞ ዘይኑን ማጣቷ ትልቅ ጉዳት ነው። በተለይ "ማታ ማታ እቅፍ እያደረገቻት እስቲ ጀርባዬን እከኪልኝ ከፍ ዝቅ ጎሽ! አዎን እንደሱ!" የምትላት ደክሟት ስትገባ ቤቱን አሟሙቃ የምትጠብቃት ጉድ ጉድ የምትልላት
ሁሉ ሊቀር ነው። ዘይኑም ከዚያ ከምትወደው ከሚሞቃት የእናቷ ጉያ
ልትነጠል ነው፡፡ እንኮኮ እያለ ንፍጧን እየጠረገ ያሳደጋት ታላቅ ወንድሟ
ደግሞ የአባቷ ምትክ አባቷም ወንድሟም ነው። ወሬውን ከስማች በኋላ ልቧ ወደ ወንድሟ ሲጋልብ የእናቷ ፍቅር ደግሞ ሉጋም እየሆነባት በሀሳብ ስትባክን ከረመች፡ የስፈሯ ልጆች አዲስ አበባ ወንድም” አላት እያሉ ሲያደንቁላት ሲያጋንኑላት ትሰማለች፡፡ አዲስ አበባ የሚያምር የሚያጓጓ አገር መሆኑን ስለምትስማ የዘይኑ ትንሽ ልብ በመጨረሻ ላይ አዲስ አበባ በመሄድ ሃሳብ ተማረከች፡፡

"ለመሆኑ ልትልኪያት ወሰንሽ?" አሉ ወይዘሮ ዘለቃ የደብዳቤውን
መንፈስ ከተረዱ በኋላ፡፡
"ምን ይደረግ ታዲያ እትዬ ዘለቃ? ትምህርቷን መቀጠል አለባት። ያለበለዚያ ማቋረጧ ነውኮ፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ ብቸኝነት ነፍሱን ሊያወጣው ነው፡፡ ሄዳ ትማር ሌላ ምንም አማራጭ የለም" አለችና ዘይኑን ትኩር ብላ በጉጉትና በፍቅር አስተዋለቻት፡፡ በዘይኑ ውስጥ አልፋ ጌትነትን ቃኘች እንደ አህያ ጡት ያሏት ሁለት ልጆቿን አንዷን በእውን ሌላውን በምናቧ እያስተዋለች ሳትተነፍስ ለረጅም ጊዜ ፀጥ ብላ ቆየች። ዘይኑ ያንኑ መከረኛ ቡና እያፈላች ነበር፡፡

"አንቺ ዘይኑ አንቺስ ምን አሰብሽ?" ብለው ጠየቋት ወይዘሮ ዘለቃ።

"እኔ ምን አውቃለሁ ሂጂ ካለችኝ እሄዳለሁ ቅሪ ካለችኝ እቀራለሁ" አለች ዘይኑ።
"አየሽ ? አየሽ ?ይቺ መናጢ ልቧ ለመሄድ ከጅሏል ማለት ነው፡፡
እናትሽን ለማን ጥለሽ ነው የምትሄጂው አንቺ?! ትምህርት ቀስ ተብሎ ይደረሳል" አሏት፡፡ አሮጊቷ ልጇን መጨቅጨቃቸውን እናት አልወደደችውም፡፡ ሁለቱ ልጆቿ እርስ በርሳቸው እየተደጋገፉ "ወንድም
ጋሻዬ ዘይንዬ" እየተባባሉ እየተረዳዱ በፍቅር አብረው እንዲኖሩላት ነው
ፍላጎቷ። የራሷ ችግር ብቸኝነቷ አልታያትም፡፡ የነሱ ደስታ ነው ደስታዋ
ወንድሟ ትምጣልኝ ብሎ ከጠየቀ ምንም ማንገራገር አያስፈልግም፡፡ መነሳት ብቻ!

"ይተዋት ባክሁ አልሄድም ብትልስ መቼ እሺ እላታለሁ? ሄዳ ትማር፡፡ ዛሬ ከሁሉ የበለጠው ትምህርት ነው፡፡ ጌትዬም ሰው ሆኖ አለሁልሽ የሚለኝ ቢማር አይደል? ዋ! ልጄ በዚህ ላይ ደግሞ ማን አለው? ብቻውን በሰው ሀገር። ትሂድለትና ልቡ ትንሽ አረፍ ይበልንጂ...
የሱ ልብ ሳያርፍ እኔስ የምተኛው እንቅልፍ ምን እንቅልፍ ይሆነኛል? ትርፉ ቅዠት ነው" ዘይኑ በእናቷ አነጋገር ደስ አላት። በልቧ የአሮጊቷን ንግግር አልወደደችውም ነበር። ወደ ወንድም ጋሻዋ በሃሳቧ ተጓዘች።
አዲስ አበባ! ጓደኞቿ የሚያደንቁት ቆንጆ ከተማ! አዲስ አበባ ሄዳ ከወንድሟ ጋር የመኖሩ ነገር በጉጉት ታያት። ልቧ ወደ መሄዱ አደላ። አቤት የዘይኑ ነገር! ደስታ በደስታ ሆነች። ደግሞ ተደስታ ብዙ አልቆየችም፡፡
የእናቷ ነገር መጥቶ እንደገና ከፊቷ ድቅን አለባትና አለቀሰች። ማን እማምዬ እያለ ጀርባዋን ያሻሻታል? ማን ቡና ያፈላላታል? ማን ቤቱን ይጠራርግላታል? እናቷ በብዙ ነገር እንደምትጎዳባት ታያት። ኦና ቤት
ጣራና ግድግዳ ብቻ! አቤት ጣራና ግድግዳ ሰው ከሌለበት ሲያስጠላ?!
እንኳን ደሳሳ ጎጆ የተንጣለለ ቪላ ቤትም ቢሆን ያለሰው አያምርም። እሷ
እንደዚህ ትጨነቅ እንጂ እናቷ እንደሆነች ቆርጣለች። እህቴ ትምጣልኝ
ብሎ ከጠየቀ ጊዜ ሳታጠፋ ቶሎ ልትልክለት ወስናለች።

እናትነት ሰው በመሆን አስተዋይነት ውስጥ ብቻ ሳይሆን ሳይዘሩ ሳያርሙና ሳይኮተኩቱ በርረው በሚኖሩ አእዋፋት ላይ እንኳ ሚስጥሩ ረቂቅ ነው፡፡ ለልጇ ስትል ከድመትና ከጨለሌ ጋር ጦርነት ገጥማ በክንፏም በጥፍሯም ታግላ የምትከላከል ዶሮ፣ ግልገሏ ወደ ገደል ስትወረወር ረጅዋን ተከትላ ወደ ገደሉ የወረደችው አህያ እናት ለልጅዋ ያላትን
ልቅ ፍቅር የሚገልፅ ነው። ዘይኑም ይህንን በደንብ ታውቀዋለች። የሶስተኛ ክፍል ተማሪ ሆና ባነበበችው የተረት መፅሐፍ ውስጥ በጫካ የምትኖር ዋኔ ጫጩቶችዋን በጉያዋ እንዳቀፈች ከተነሳው የሰደድ እሳት ልታስጥላቸው የከፈለችውን የህይወት ዋጋ ታውቃለች። እሳቱን ፈርታ ሳትደነብር ሳትበረግግ ጫጩቶችዋን ለማዳን እንዳቀፈቻቸው በነበልባሉ ተጠብሳና ተቃጥላ ስትሞት በስሯ የተጠለሉት ጫጩቶች በሙሉ ሳይቃጠሉ መትረፋቸውን አንብባ የእናት ፍቅር ምን ያክል ከባድ እንደሆነ አስ
ደንቋታል። የዚያን ያክል ጥሩ እናቶች እንዳሉ ሁሉ ለልጆቻቸው ደንታ ቢስ የሆኑ ምንም አይነት የልጅ ፍቅር የሌላቸው የወለዱትን እያስራቡ ሆቴል ገብተው ጮማ የሚቆርጡ ወላጆች መኖራቸው የሚካድ ኣይደለም፡፡ አንዳንዴ የእናት አንጀት ከጨከነ ከደነደነ ቦታውን የሚረከበው ክፉ መንፈስ ይሆንና የወለዱትን ልጅ ጫካ ውስጥ እንደ ውሻ ወርውሮ እስከ መጥፋትና በምናምን ጠቅልሎ ሽንት ቤት ውስጥ እስከ መጨመር ያደርሳል
👍4