አትሮኖስ
281K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
481 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ውድ #የአትሮኖስ ቻናል ተከታታዮች
በ ኔትዎርክ እና በአንዳንድ ምክንያቶች የተነሳ ረዘም ላለ ግዜ ተጠፋፍተን ቆይተናል አሁን እንደተለመደው ለናንተ ያልነውን ሁሉ ይዘን መተናል እና አብሮነታቹ ይቆየን .
👍5
እንዴት ናቹ ውድ #የአትሮኖስ ቻናል ተከታታዬች ተጠፋፋን አይደል ትንሽ ችግር ገጥሞኝ ነው አሁን እንደተለመደው በየለቱ አሪፍ አሪፍ ድርሰቶችን ይዤ ለመቅረብ እሞክራለሁ እናተም እንደተለመደው አስተያየታችሁን አድርሱኝ።

#የተበረገደ_ልብ
:
:
ልቤ ድው ድው፣ ዐይኔ ቦግ ቦግ፣ ጆሮዬ ቆም ቆም፣ ምላሴ ዝርክር አለብኝ- ሃብሉን ሲሰጠኝ።

ልብ እና ቁልፍ አንድ ላይ ያንጠለጠለ ሃብል የው። አቤት ማማሩ፣ አቤት ማብረቅረቁ። ከዚያ ሁሉ ደግሞ አቤት ትርጉሙ!

"የልቤ ብቸኛ ቁልፍ ያለው አንቺ ጋር ብቻ ነው! ለማለት ነው። ገባሽ አይደል?" አለኝ እኔ ረጅም ፀጉሬን በሁለት እጆቼ ከአንገቴ እያባረርኩ፣ እሱ ከጀርባዬ ቆሞ ልቡን እና ቁልፉን ሲያጠልቅልኝ።

ሳልሞት ያረግኩ መሰለኝ። ዕርግ ያልኩ!

"ዐውቄአለሁ" አልኩት፣ በጡቶቼ መሀል ያለው ገደል ውስጥ የገባውን ባለቁልፍ ልቡን አጎንብሼ እያየሁ። ከልቤ በቅርብ ርቀት መቀመጡን እያስተዋልኩ - "ዐውቃለሁ" አልኩት እየተስለመለምኩ።

ድል አድራጊነት ተሰማኝ።

ፍጹም ድል አድራጊነት ተስማኝ።

አማንን መሳይ ቆንጆ ፣ አማንን መሳይ ጎበዝ ወንድ ፣ ልቡን ከነቁልፉ እንዲሰጠኝ ማድረግ መቻሌ ኩራት ኩራት አለኝ። ይሄ ሁሉ ወንዳወንድነት የኔ አይደለም ወይ...ኩራት አይለኝም ወይ!

መሬትን በእግሬ ጨፍልቄ፣ ፀሐይን በቀኝ እጄ ፣ ጨረቃን በግራ እጄ የጨበጥኩ ያህል ድል አድራጊነት ተሰማኝ።

ሳምንት አላለፈም።እንጃ አምስት ቀንም መሙላቱ። እዛ አስቤዛ የማደርግበቶ ቤት ቲማቲም ልገዛ ስገባ የድሮ ፍቅረኛውን አገኘኋት። ስም ይንሳትና ስሟ ቤቴልሄም ነው። "ቤቲ በይኝ" ትለኛለች ደሞ፣ አርባ ቦታ ይበታትናትና። ቡቱቶ ነገር።

ቢሆንልኝ፣ "አንቺ ቡቱቶ" ብላት ደስ ይለኛል። በየቦታው ከፈላ ቤት ለምን እኛ አስቤዛ የምናደርግበት ቦታ እንደምትመጣብኝ አይገባኝም። ሰፈሯ አቧሬ ነው። አቧራ ይድፋባትና። ታድያ ነገር ፍለጋ ካልሆነ ከዚያ ድረስ ለቲማቲምና ሽንኩርት ጉርድ ሾላ ድረስ ምን ያመጣታል? ጎዶሎ!

እንደናፈቀችኝ ሁሉ ሳመችኝ። በኔ በኩል ያመለጣትን ፍቅሬን ልትስም ነው...? በዙሪያ ጥምጥም ከንፈሩን ልታገኝ ነው...? ብነክሳት ደስ እያለኝ እሷን የምስም አስመስዬ እንደ ሳትኳት ሁሉ በዙሪያዋ ያለውን አየር ሳምኩ ። እንኳን እሷ የከበበችው አየር ደስ የማይል ነገር ይሸታል።

"በይ እሺ..." ብዬ ወደ ቲማቲሜ ልሄድ ስል "እንዴ...ቆይ ቆይ አንዴ...." አለችና እጄን አፈፍ አደረገችው። እጇ እንደ ገበሬ እጅ ይሻክራል።

አማንዬ ምን ሆኖ ነው ከዚህች ባላገር ጋር ላይ ታች ሲል የኖረው? ምን ሲል ወደዳት...? መተት ብታደርግበት ነው። ቡቱቷም መተተኛ።

ዞሬ ሳልጨርስ "ቆይ አንዴ...ሃብልሽ... እስቲ ሃብልሽን ልየው! " ብላ ልብና ቁልፍ ሃብሌን ልትጎትት : ያንን የገበሬ እጆን ስትሰድ ባላሰብኩት ፍጥነት ገፏሆት።

"እንዴ ምን ሆነሻል?" አለችኝ።

"ምንም...እንዳትበጥሺብኝ ነው...ስፔሻል ሃብል ነው ሃብሌን ሁለት እጆቼን ጋሻ አስመስዬ እንደጋረድኩ መለስኩላት።

"ላየው እኮ ነው...ለምን እበጥሰዋለሁ...? ሣቀችብኝ ። በዚያ ቢጫ ቀለም የተቀባ በሚመስል ጥርሷ ሣቀችብኝ።

ነደደኝ።

"አማንዬ ነው የሰጠኝ... ዝም ብሎ ሃብል አይደለም...ዕይው... ቆይ...አትንኪው እዛው ሆነሽ ዕይው...ልብ አለው። አብሮ ደግሞ ምን እንዳለው ታውቂያለሽ...?" አልኳት ጠብረር - ገንተር ብዬ ጠጋ እያልኳት።

"ቁልፍ?" አለችኝ አፍታም ሳትቆይ።

ደነገጥኩ።

"እንዴት አወቅሽ?" አልኳት ብልጭ እያለብኝ።

መልስ ትሰጠኛለች ብዬ ስጠብቅ ለቢትልስነት ትንሽ የቀረው አስቀያሜ ሹራቧን በግድ ከአንገቷ ወደ ጡቶችዋ እየገፋች ምዝዝ አድርጋ አወጣችው።

የእኔን ሃብል። ራሱን የእኔን ሃብል። ባለ ልብና ባለ ቁልፉን ቁጭ እራሱን።

ዞ..ር.. አለብኝ።

"ሃ ሃ ሃ! በማርያም ልገምት! ሲሰጥሽ ምን አለሽ...? ''የልቤ ብቸኛ ቁልፍ ያለው አንቺ ጋ ብቻ ነው ለማለት ነው'' አለሽ?" አለችኝ የሚያነፍር ሳቋን ሳታቋረጥ።

"እ...አዎ...በምን አወቅሽ....?

"አንቺ ደግሞ አሪፍ መስለሽ ገና እርጥብ ነሽ ልበል...! ለኔም እንደዛ ብሎ ስለሰጠኝ ነዋ!"

"አማንዬ... አማን... ይሄን ሃብል ላንቺም እንዲህ ብሎ ልክ እንደኔ... ልክ እኔን እንዳለሽ ብሎ ሰጠሽ...?" አልኳት እየተንተባተብኩ። እፍረቴን ትቼ ቡቱቶ ፊት ላለቅስ ነው መሰለኝ።

"ወይ የእኔ እናት...! ከኔ በፊት ላለችው ልጅ... ማነው ስሟ ያቺ...ሃዊ ናት ሂዊ...? ውሃ ይብላትና...ይህኑኑ ሃብል እንዲህ ብሎ ሰጥቷት ነበር። አሳይታኝ ነበር" አለችኝ መሣቅ አቁማ።

ሳላሳዝናት አልቀረሁም።

የምንቃት ቡቱቶ የምጠየፋት ቡቱቶ ለኔ ትዘንልኝ? ወይኔ ልጅት! አማንዬ... ይሄ አማን... ቡትቶ ለኔ እንድታዝን የሚያደርግ ሁኔታ ውስጥ ይቀላቅለኝ....?

ይድፋው። ክልትው ያድርገው።

ቤቲ ሳትቆይ የምትገዛውን ነገር ገዝታ ሄጀች። እኔ ግን ነፍዤ ቀረሁ። እግሬ ከአስቤዛ ቤቱ መሬት ገር የተለሰነ ይመስል ተገትሬ ቀረሁ።

በስተሆላ ወደ ቤቴ የመመለስ ጉልበት አግኝቼ ስመለስ የማስበው ግን ይሄን ብቻ ነበር።

"ለዚህ ሁሉ ሴት ቁልፉን የሚሰጥ ከሆነ ልቡን መቆለፍ ምን አስፈለገው? በርግዶ አይተወውም? የሚበረግድ ይበርግደውና... ይሄ ቁሌታም። ይሄ ሸርሙጣ...አማን ብሎ ሰው ። ጆፌ አሞራ ይልቀቅበትና...."

🔘አለቀ🔘

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍3
እንዴት ናቹ #የአትሮኖስ ቻናል ቤተሰቦች እንደሚታወቀው #ሁቱትሲ የተሰኘው ድርሰት በትላንትናው እለት ተጠናቋል ያላችሁንም አስተያየት በውስጥ መስመር እየገለፃችሁልኝ ነው ለዚህም ከብዛቱ የተነሳ ለሁሉም መልስ መስጠት ስላልቻልኩ ይቅርታ እየጠየኩ ባጠቃላይ ግን ሁላችሁንም ከልቤ ማመስገን እፈልጋለሁ። 🙏

ሌላው በቅርብ ቀን ልንጀምረው ያሰብነው
ረጅም ታሪክ አለ ከነዚህም ውስጥ ለጊዜው 3 አሉ ከነዚህ ውስጥ አንዱን መርጦ ለመጀመር የናተ ከፍተኛ ትብብር ያስፈልጋል

መጀመርያ ከታች ከማስቀምጣቻው ምርጫዎች ውስጥ በናተ በከፍተኛ መጠን የተመረጠውን ቅድምያ አቀርባለው

ሌላው #MUTE አድርጋችሁ የምትጠቀሙ የቻናሉ ቤተሰቦች ፅሁፍ ማዘጋጀት በጣም ከባድ ነው አንዳንድ ቻናሎች ላይ እንደምታዩት ሌላ ቻናል ላይ ያሉትን ታሪኮች Cope paste አደለም የማደርገው በተቻለ መጠን አዳዲስ ታሪኮችን ይዤ ለመምጣት እሞክራለሁ ለዚህም ደሞ ለናተ በሚመች መልኩ ለማቅረብ ከፍተኛ ልፋት አለው እንዲህ የተዘጋጀውን ደሞ እናተ ካላያችሁት ልፋት ብቻ ነው የሚሆነው እናም እባካችሁ #UNMUTE አድርጋችሁ ተጠቀሙ እኔም ሳልሰለች ለናተ ምርጥ ምርጥ ታሪኮችን ይዤ እመጣለሁ

ከታች ካሉት ምርጫዎች ቅድምያ ይቅረብ የምትሉትን በመምረጥ ተሳተፉ

💚 #ፍቅር_እስከ_መቃብር

💛 #ሮዛ

❤️ #የአና_ማስታወሻ
ውድ #የአትሮኖስ ቻናል ተከታታዬች እንደሚታወቀው #ሮዛ ቁጥር-1 በቅርቡ ተጠናቋል በውስጥ መስመር ብዙዎቻችሁ #ሮዛ- ቁጥር-2 ይቀጥል ብላችኋል ነገር ግን የሁላችሁንም ሃሳብ ለመቀበል ሃሳባችሁን ስጡን በናተ የተመረጠውን እናቀርባለን ሶስት ልቦለዶች ለምርጫ አቅርቢያለው

💚 #ምንዱባን
💛 #ሳቤላ
❤️ #ሮዛ- ቁጥር-2
እንዴት ናችሁ #የአትሮኖስ ቻናል ተከታታዮች ሁሉ ሰላም ነው እኔ የሚወጣው ሰው ብዝዝዝት አለብኝና ምንድን ነው ነገሩ ይሄ ሁሉ ሰው ተገዶ ነው ወደ ቻናሉ የገባው ወይስ ምን አጠፋው ብዬ #ቁዝዝዝም ብያለሁ እስቲ ካላችሁት መሃል ምክንያቱን የሚያውቅ ቢያሳውቀኝ ወረታውን እከፍላለው😃

ሌላው ከዚ በፊት በቻናላችን ላይ #ሁቱትሲ የተሰኘ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ሰለ ሩዋንዳ የዘር ፍጅት የሚያወሳውን መፅሐፍ በተከታታይ ማቅረባችን ይታወሳል አብዛኛችሁም አንብባችሁ አስተያየት ሰታችሁኛል አሁን አገራችን ያለችበትን ሁኔታ እያወሱ ስጋታቸውንም የገለፁ አሉ።አሁን ደሞ በ #ኢስማይል ቤህ የተፃፈውን አስከፊውን የሴራሊዮን የእርስ በእርስ ጦርነት የሚያሳይ #የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ የሚለውን መፅሀፍ በተከታታይ ላቀርብላችሁ ፈልጌ ነበር ግን የቻናሉ ቤተሰቦች በየቀኑ ሲቀንስ ሳይ ሃሳብ አስቀየረኝ ምክንያቱም ማዘጋጀቱ በጣም አድካሚ ነው ተከታታዩ ከሌለ ደሞ ዋጋ የለውም አሁን የናንተን አስተያየት እፈልጋለው ምን ያህላችሁስ የመከታተል ፍላጎት አላችሁ ከታች VOTE እንድታደርጉ አስቀምጠዋለሁ በተጨማሪም በአስተያየት መስጫው አስተያየታችሁን እጠብቃለሁ

#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ የሚለው መፅሀፍ

#ይቅረብ 👍

#አይቅረብ 👎

ለአስተያየት👉 @atronosebot
👍2
ነገ ምን አይነት ችግር ይገጥመኝ ይሆን ብየ ፈርቻለሁ ተጨንቂያለሁ። ቢሆንም ግን ከፍሪ ታውን በመውጣቴ እና ድጋሚ ወታደር ከመሆን ስላመለጥኩ ደስ ብሎኛል። በዚህ ተፅናናሁ፤ የቀረኝን ሩዝ ከሻንጣየ በማውጣት መብላት ጀመርኩ። ከ እኔ ትንሽ ራቅ ብሎ አንዲት ሴት ከሰባት አመት የማይበልጡ ወንድ እና ሴት
ልጆቿ ጋር ተቀመጣለች፡፡ ሌሎች ሰዎችን ላለመረበሽ ቀስ ብላ ለልጆቿ ተረት ታንሾካሽካለች። እጆቿን ስታንቀሳቅስ ልጅ ሁኜ ብዙ ጊዜ የሰማሁት አንድ ተረት ትዝ አለኝ።

ለሊት ነበር እና እሳት ዳር ቁጭ ብለን እጆቻችንን ወደ ነበልባሉ እያስጠጋን እየሞቅን ተረት እናዳምጣለን። ጨረቃ እና
ኮኮቦች ሲርቁ እናያለን፡፡ ቀይ ፍም ፊታችንን ሲያበራ ጭሱ ወደ
ሰማይ ተግተልትሎ ይወጣ ነበር። ከ ጓደኞቼ የአንዱ አያት የሆነው አባ ሲሳይ በዛ ምሽት ብዙ ተረቶችን ነግሮናል። ግን
የመጨረሻ ተረቱን ሲነግረን ደጋግሞ “ ይሄ በጣም ጠቃሚ ተረት ነው” ይል ነበር። ጎሮሮውን ጠራረገና ጀመረ።
“ዝንጀሮ ለመግደል ወደ ጫካ የወረደ አዳኝ ነበር። ዘወር ዘወር ብሎ ሲቃኝ የዛፍ ቅርንጫፍ ላይ ተደላድሎ የተቀመጠ ዝንጀሮ አየ።ዝንጀሮው የአዳኙ ኮቴ በደረቅ ቅጠሎች ሲያልፍ ድምፅ ቢያሰማም እስኪጠጋው ድረስ ብዙም ትኩረት አልሰጠውም::አዳኙ ዝንጀሮ በደንብ ወደ ሚታይበት ቦታ ሲደርስ መሳሪያውን
አዘጋጅቶ አነጣጠረ፡፡ ምላጩን ከመሳቡ በፊት ግን ዝንጀሮው እንዲህ ሲል ተናገረ:
ከተኮስክብኝ እናትህ ትሞታለች ፤ ካልተኮስክ ደግሞ አባትህ ይሞታል።” ዝንጀሮው ተስተካክሎ ተቀመጠ እና ምግቡን ማለመጥ፣ እራሱን ማከክ እና ሆዱን ማሻሸት ቀጠለ።

አዳኙ አንተ ብትሆን ምን ታደርግ ነበር?”

እኔ በአደኩበት መንደር ይሄ ተረት ለወጣቶች በአመት አንዴ ይነገራል። ተረት ተናጋሪው ሽማግሌ ተረቱን ከተናገረ በኋላ
ይህን ለመመለስ የሚያስቸግር ጥያቄ በህፃናቱ ወላጆች ፊት ነበር የሚያቀርበው። ሁሉም ልጆች አንድ በአንድ መልሳቸውን እንዲያቀረቡ ይጠየቃሉ። ወላጆቻቸው ከጎናቸው ስለሚሆኑ አንድም ልጅ መልሶ አያውቅም:: ተረት ተናጋሪውም መልሱን
ተናግሮ አያውቅም:: በእንደዚህ አይነት ስብስብ መልስ እንድሰጥ ስጠየቅ ሁሌም መልሴ ላስብበት ነበር። አጥጋቢ መልስ
አልነበረም::በእነዚህ ስብስቦች እኔ እና ጓደኞቼ ወላጆቻችንን ከሞት የሚያስቀር መልስ ለማግኘት የተለያዩ መልሶችን እናስብ ነበር።ግን አንድም አልነበረም:: ዝንጀሮ ከተውነው አንድ ሰው
ይሞታል፤ ዝንጀሮን ከገደልነው ደግሞ ሌላ ሰው ይሞታል።ያ ምሽት ግን በአንድ መልስ ተስማማን ግን ተቀባይነት
አላገኘም:: አባ ሲሳይን አዳኙ እኛ ከሆን ዝንጀሮዎች ለማደን አንወጣም ብለን ነገርናቸው:: “ለአደን የሚሆኑ ሌሎች እንስሳት ብለን ነገርናቸው።
ለምሳሌ አጋዘን “በፍፁም ይሄ ተቀባይነት የሌለው መልስ ነው” አሉ:: መሳሪያውን አነጣጥሮ ውሳኔ ስለቀረው ሰው ነው የምናወራው” አሉ የወይን እቃቸውን ከፍተው ከመጠጣታቸው በፊት ፈገግ
አሉ።
የሰባት ዓመት ልጅ እያለሁ ለዚህ ጥያቄ መልስ ነበረኝ። እናቴ ምን ይሰማታል በሚል ግን ለማንም ተናግሬው አላውቅም:: ለራሴ የደመደምኩት ግን አዳኙ ብሆን ዝንጀሮውን እገድለው እና
ሌሎች አዳኞች በእንደዚህ አይነት ቅርቃር ውስጥ እንዳይገቡ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ እታደጋቸው ነበር።


ተፈፀመ

ውድ #የአትሮኖስ ቻናል ተከታታዬቼ #የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ ይህን ይመስላል ብዙዎቻቹ አስተያየታችሁን በየክፍሉ ሰታችሁኛል የተመቸውም ያልተመቸውም አለ በኔ በኩል ያለኝን አስተያየት በየግል ስልክ ነበር አሁን ላይ ጠቅለል ሳደርገው ፅሁፉ በጣም የተመቸኝ እውነተኛ ታሪክ ነው ለዛም ነው ለናተ ያቀረብኩት #ያልተመቸኝ ነገር ከናንተ የመጣ ነገር ባይኖርም #ተርጓሚው ላይ ቅሬታ አለኝ ሲተረጎም የቃላት አጠቃቀም ላይ ለኛ ትርጉሙን የሚያዛባ አንዳንዴ ከሌላ ቋንቋ ወደእኛ ቀጥታ ሲተሮገም ስሜት የማይሰጡ አረፍተ ነገሮች አሉ እነሱ በዚ ታሪክ ላይ ብዙ አጋጥመውኛል አንዳንዴ የታሪክ ፍሰቱም መዘባረቅ ነበረበት እኔም ባለችኝ አቅም ለማስተካከል ሞክሪያለው...አስቲ እናንተም በታሪኩ ላይ እንዲሁም ከላይ ባነሳሁት ላይ ያላችሁን አስተያየት አድርሱኝ።

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ