አትሮኖስ
281K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
481 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ነገ ምን አይነት ችግር ይገጥመኝ ይሆን ብየ ፈርቻለሁ ተጨንቂያለሁ። ቢሆንም ግን ከፍሪ ታውን በመውጣቴ እና ድጋሚ ወታደር ከመሆን ስላመለጥኩ ደስ ብሎኛል። በዚህ ተፅናናሁ፤ የቀረኝን ሩዝ ከሻንጣየ በማውጣት መብላት ጀመርኩ። ከ እኔ ትንሽ ራቅ ብሎ አንዲት ሴት ከሰባት አመት የማይበልጡ ወንድ እና ሴት
ልጆቿ ጋር ተቀመጣለች፡፡ ሌሎች ሰዎችን ላለመረበሽ ቀስ ብላ ለልጆቿ ተረት ታንሾካሽካለች። እጆቿን ስታንቀሳቅስ ልጅ ሁኜ ብዙ ጊዜ የሰማሁት አንድ ተረት ትዝ አለኝ።

ለሊት ነበር እና እሳት ዳር ቁጭ ብለን እጆቻችንን ወደ ነበልባሉ እያስጠጋን እየሞቅን ተረት እናዳምጣለን። ጨረቃ እና
ኮኮቦች ሲርቁ እናያለን፡፡ ቀይ ፍም ፊታችንን ሲያበራ ጭሱ ወደ
ሰማይ ተግተልትሎ ይወጣ ነበር። ከ ጓደኞቼ የአንዱ አያት የሆነው አባ ሲሳይ በዛ ምሽት ብዙ ተረቶችን ነግሮናል። ግን
የመጨረሻ ተረቱን ሲነግረን ደጋግሞ “ ይሄ በጣም ጠቃሚ ተረት ነው” ይል ነበር። ጎሮሮውን ጠራረገና ጀመረ።
“ዝንጀሮ ለመግደል ወደ ጫካ የወረደ አዳኝ ነበር። ዘወር ዘወር ብሎ ሲቃኝ የዛፍ ቅርንጫፍ ላይ ተደላድሎ የተቀመጠ ዝንጀሮ አየ።ዝንጀሮው የአዳኙ ኮቴ በደረቅ ቅጠሎች ሲያልፍ ድምፅ ቢያሰማም እስኪጠጋው ድረስ ብዙም ትኩረት አልሰጠውም::አዳኙ ዝንጀሮ በደንብ ወደ ሚታይበት ቦታ ሲደርስ መሳሪያውን
አዘጋጅቶ አነጣጠረ፡፡ ምላጩን ከመሳቡ በፊት ግን ዝንጀሮው እንዲህ ሲል ተናገረ:
ከተኮስክብኝ እናትህ ትሞታለች ፤ ካልተኮስክ ደግሞ አባትህ ይሞታል።” ዝንጀሮው ተስተካክሎ ተቀመጠ እና ምግቡን ማለመጥ፣ እራሱን ማከክ እና ሆዱን ማሻሸት ቀጠለ።

አዳኙ አንተ ብትሆን ምን ታደርግ ነበር?”

እኔ በአደኩበት መንደር ይሄ ተረት ለወጣቶች በአመት አንዴ ይነገራል። ተረት ተናጋሪው ሽማግሌ ተረቱን ከተናገረ በኋላ
ይህን ለመመለስ የሚያስቸግር ጥያቄ በህፃናቱ ወላጆች ፊት ነበር የሚያቀርበው። ሁሉም ልጆች አንድ በአንድ መልሳቸውን እንዲያቀረቡ ይጠየቃሉ። ወላጆቻቸው ከጎናቸው ስለሚሆኑ አንድም ልጅ መልሶ አያውቅም:: ተረት ተናጋሪውም መልሱን
ተናግሮ አያውቅም:: በእንደዚህ አይነት ስብስብ መልስ እንድሰጥ ስጠየቅ ሁሌም መልሴ ላስብበት ነበር። አጥጋቢ መልስ
አልነበረም::በእነዚህ ስብስቦች እኔ እና ጓደኞቼ ወላጆቻችንን ከሞት የሚያስቀር መልስ ለማግኘት የተለያዩ መልሶችን እናስብ ነበር።ግን አንድም አልነበረም:: ዝንጀሮ ከተውነው አንድ ሰው
ይሞታል፤ ዝንጀሮን ከገደልነው ደግሞ ሌላ ሰው ይሞታል።ያ ምሽት ግን በአንድ መልስ ተስማማን ግን ተቀባይነት
አላገኘም:: አባ ሲሳይን አዳኙ እኛ ከሆን ዝንጀሮዎች ለማደን አንወጣም ብለን ነገርናቸው:: “ለአደን የሚሆኑ ሌሎች እንስሳት ብለን ነገርናቸው።
ለምሳሌ አጋዘን “በፍፁም ይሄ ተቀባይነት የሌለው መልስ ነው” አሉ:: መሳሪያውን አነጣጥሮ ውሳኔ ስለቀረው ሰው ነው የምናወራው” አሉ የወይን እቃቸውን ከፍተው ከመጠጣታቸው በፊት ፈገግ
አሉ።
የሰባት ዓመት ልጅ እያለሁ ለዚህ ጥያቄ መልስ ነበረኝ። እናቴ ምን ይሰማታል በሚል ግን ለማንም ተናግሬው አላውቅም:: ለራሴ የደመደምኩት ግን አዳኙ ብሆን ዝንጀሮውን እገድለው እና
ሌሎች አዳኞች በእንደዚህ አይነት ቅርቃር ውስጥ እንዳይገቡ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ እታደጋቸው ነበር።


ተፈፀመ

ውድ #የአትሮኖስ ቻናል ተከታታዬቼ #የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ ይህን ይመስላል ብዙዎቻቹ አስተያየታችሁን በየክፍሉ ሰታችሁኛል የተመቸውም ያልተመቸውም አለ በኔ በኩል ያለኝን አስተያየት በየግል ስልክ ነበር አሁን ላይ ጠቅለል ሳደርገው ፅሁፉ በጣም የተመቸኝ እውነተኛ ታሪክ ነው ለዛም ነው ለናተ ያቀረብኩት #ያልተመቸኝ ነገር ከናንተ የመጣ ነገር ባይኖርም #ተርጓሚው ላይ ቅሬታ አለኝ ሲተረጎም የቃላት አጠቃቀም ላይ ለኛ ትርጉሙን የሚያዛባ አንዳንዴ ከሌላ ቋንቋ ወደእኛ ቀጥታ ሲተሮገም ስሜት የማይሰጡ አረፍተ ነገሮች አሉ እነሱ በዚ ታሪክ ላይ ብዙ አጋጥመውኛል አንዳንዴ የታሪክ ፍሰቱም መዘባረቅ ነበረበት እኔም ባለችኝ አቅም ለማስተካከል ሞክሪያለው...አስቲ እናንተም በታሪኩ ላይ እንዲሁም ከላይ ባነሳሁት ላይ ያላችሁን አስተያየት አድርሱኝ።

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ ለወዳጆ #Share እያደረጉ