አትሮኖስ
281K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
481 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
እንዴት ናቹ ውድ #የአትሮኖስ ቻናል ተከታታዬች ተጠፋፋን አይደል ትንሽ ችግር ገጥሞኝ ነው አሁን እንደተለመደው በየለቱ አሪፍ አሪፍ ድርሰቶችን ይዤ ለመቅረብ እሞክራለሁ እናተም እንደተለመደው አስተያየታችሁን አድርሱኝ።

#የተበረገደ_ልብ
:
:
ልቤ ድው ድው፣ ዐይኔ ቦግ ቦግ፣ ጆሮዬ ቆም ቆም፣ ምላሴ ዝርክር አለብኝ- ሃብሉን ሲሰጠኝ።

ልብ እና ቁልፍ አንድ ላይ ያንጠለጠለ ሃብል የው። አቤት ማማሩ፣ አቤት ማብረቅረቁ። ከዚያ ሁሉ ደግሞ አቤት ትርጉሙ!

"የልቤ ብቸኛ ቁልፍ ያለው አንቺ ጋር ብቻ ነው! ለማለት ነው። ገባሽ አይደል?" አለኝ እኔ ረጅም ፀጉሬን በሁለት እጆቼ ከአንገቴ እያባረርኩ፣ እሱ ከጀርባዬ ቆሞ ልቡን እና ቁልፉን ሲያጠልቅልኝ።

ሳልሞት ያረግኩ መሰለኝ። ዕርግ ያልኩ!

"ዐውቄአለሁ" አልኩት፣ በጡቶቼ መሀል ያለው ገደል ውስጥ የገባውን ባለቁልፍ ልቡን አጎንብሼ እያየሁ። ከልቤ በቅርብ ርቀት መቀመጡን እያስተዋልኩ - "ዐውቃለሁ" አልኩት እየተስለመለምኩ።

ድል አድራጊነት ተሰማኝ።

ፍጹም ድል አድራጊነት ተስማኝ።

አማንን መሳይ ቆንጆ ፣ አማንን መሳይ ጎበዝ ወንድ ፣ ልቡን ከነቁልፉ እንዲሰጠኝ ማድረግ መቻሌ ኩራት ኩራት አለኝ። ይሄ ሁሉ ወንዳወንድነት የኔ አይደለም ወይ...ኩራት አይለኝም ወይ!

መሬትን በእግሬ ጨፍልቄ፣ ፀሐይን በቀኝ እጄ ፣ ጨረቃን በግራ እጄ የጨበጥኩ ያህል ድል አድራጊነት ተሰማኝ።

ሳምንት አላለፈም።እንጃ አምስት ቀንም መሙላቱ። እዛ አስቤዛ የማደርግበቶ ቤት ቲማቲም ልገዛ ስገባ የድሮ ፍቅረኛውን አገኘኋት። ስም ይንሳትና ስሟ ቤቴልሄም ነው። "ቤቲ በይኝ" ትለኛለች ደሞ፣ አርባ ቦታ ይበታትናትና። ቡቱቶ ነገር።

ቢሆንልኝ፣ "አንቺ ቡቱቶ" ብላት ደስ ይለኛል። በየቦታው ከፈላ ቤት ለምን እኛ አስቤዛ የምናደርግበት ቦታ እንደምትመጣብኝ አይገባኝም። ሰፈሯ አቧሬ ነው። አቧራ ይድፋባትና። ታድያ ነገር ፍለጋ ካልሆነ ከዚያ ድረስ ለቲማቲምና ሽንኩርት ጉርድ ሾላ ድረስ ምን ያመጣታል? ጎዶሎ!

እንደናፈቀችኝ ሁሉ ሳመችኝ። በኔ በኩል ያመለጣትን ፍቅሬን ልትስም ነው...? በዙሪያ ጥምጥም ከንፈሩን ልታገኝ ነው...? ብነክሳት ደስ እያለኝ እሷን የምስም አስመስዬ እንደ ሳትኳት ሁሉ በዙሪያዋ ያለውን አየር ሳምኩ ። እንኳን እሷ የከበበችው አየር ደስ የማይል ነገር ይሸታል።

"በይ እሺ..." ብዬ ወደ ቲማቲሜ ልሄድ ስል "እንዴ...ቆይ ቆይ አንዴ...." አለችና እጄን አፈፍ አደረገችው። እጇ እንደ ገበሬ እጅ ይሻክራል።

አማንዬ ምን ሆኖ ነው ከዚህች ባላገር ጋር ላይ ታች ሲል የኖረው? ምን ሲል ወደዳት...? መተት ብታደርግበት ነው። ቡቱቷም መተተኛ።

ዞሬ ሳልጨርስ "ቆይ አንዴ...ሃብልሽ... እስቲ ሃብልሽን ልየው! " ብላ ልብና ቁልፍ ሃብሌን ልትጎትት : ያንን የገበሬ እጆን ስትሰድ ባላሰብኩት ፍጥነት ገፏሆት።

"እንዴ ምን ሆነሻል?" አለችኝ።

"ምንም...እንዳትበጥሺብኝ ነው...ስፔሻል ሃብል ነው ሃብሌን ሁለት እጆቼን ጋሻ አስመስዬ እንደጋረድኩ መለስኩላት።

"ላየው እኮ ነው...ለምን እበጥሰዋለሁ...? ሣቀችብኝ ። በዚያ ቢጫ ቀለም የተቀባ በሚመስል ጥርሷ ሣቀችብኝ።

ነደደኝ።

"አማንዬ ነው የሰጠኝ... ዝም ብሎ ሃብል አይደለም...ዕይው... ቆይ...አትንኪው እዛው ሆነሽ ዕይው...ልብ አለው። አብሮ ደግሞ ምን እንዳለው ታውቂያለሽ...?" አልኳት ጠብረር - ገንተር ብዬ ጠጋ እያልኳት።

"ቁልፍ?" አለችኝ አፍታም ሳትቆይ።

ደነገጥኩ።

"እንዴት አወቅሽ?" አልኳት ብልጭ እያለብኝ።

መልስ ትሰጠኛለች ብዬ ስጠብቅ ለቢትልስነት ትንሽ የቀረው አስቀያሜ ሹራቧን በግድ ከአንገቷ ወደ ጡቶችዋ እየገፋች ምዝዝ አድርጋ አወጣችው።

የእኔን ሃብል። ራሱን የእኔን ሃብል። ባለ ልብና ባለ ቁልፉን ቁጭ እራሱን።

ዞ..ር.. አለብኝ።

"ሃ ሃ ሃ! በማርያም ልገምት! ሲሰጥሽ ምን አለሽ...? ''የልቤ ብቸኛ ቁልፍ ያለው አንቺ ጋ ብቻ ነው ለማለት ነው'' አለሽ?" አለችኝ የሚያነፍር ሳቋን ሳታቋረጥ።

"እ...አዎ...በምን አወቅሽ....?

"አንቺ ደግሞ አሪፍ መስለሽ ገና እርጥብ ነሽ ልበል...! ለኔም እንደዛ ብሎ ስለሰጠኝ ነዋ!"

"አማንዬ... አማን... ይሄን ሃብል ላንቺም እንዲህ ብሎ ልክ እንደኔ... ልክ እኔን እንዳለሽ ብሎ ሰጠሽ...?" አልኳት እየተንተባተብኩ። እፍረቴን ትቼ ቡቱቶ ፊት ላለቅስ ነው መሰለኝ።

"ወይ የእኔ እናት...! ከኔ በፊት ላለችው ልጅ... ማነው ስሟ ያቺ...ሃዊ ናት ሂዊ...? ውሃ ይብላትና...ይህኑኑ ሃብል እንዲህ ብሎ ሰጥቷት ነበር። አሳይታኝ ነበር" አለችኝ መሣቅ አቁማ።

ሳላሳዝናት አልቀረሁም።

የምንቃት ቡቱቶ የምጠየፋት ቡቱቶ ለኔ ትዘንልኝ? ወይኔ ልጅት! አማንዬ... ይሄ አማን... ቡትቶ ለኔ እንድታዝን የሚያደርግ ሁኔታ ውስጥ ይቀላቅለኝ....?

ይድፋው። ክልትው ያድርገው።

ቤቲ ሳትቆይ የምትገዛውን ነገር ገዝታ ሄጀች። እኔ ግን ነፍዤ ቀረሁ። እግሬ ከአስቤዛ ቤቱ መሬት ገር የተለሰነ ይመስል ተገትሬ ቀረሁ።

በስተሆላ ወደ ቤቴ የመመለስ ጉልበት አግኝቼ ስመለስ የማስበው ግን ይሄን ብቻ ነበር።

"ለዚህ ሁሉ ሴት ቁልፉን የሚሰጥ ከሆነ ልቡን መቆለፍ ምን አስፈለገው? በርግዶ አይተወውም? የሚበረግድ ይበርግደውና... ይሄ ቁሌታም። ይሄ ሸርሙጣ...አማን ብሎ ሰው ። ጆፌ አሞራ ይልቀቅበትና...."

🔘አለቀ🔘

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍3