አትሮኖስ
280K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
459 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ልጩህበት !


#ክፍል_አንድ


#ድርሰት_በጥላሁን

ስራዬን በጀመርኩ በ ሀያኛው ቀን ላይ እንደተለመደው እራቴን በልቼ ቡናዬን ጠጥቼ ከምሽቱ 3:15 ላይ ወደ ስራ ወጣሁ እስከ ምሽቱ አምስት ሰአት ድረስ ሲዝናኑ ካመሹት መሀል ከፊሉን ከመጠጥ ቤት ወደ ቤታቸው ከፊሉን ከመጠጥ ቤት አልጋ ወደያዙበት ሌላ ሆቴል ከፊሉን ከመጠጥ ቤት ወደ ሌላ መጠጥ ቤት ሳገላብጥ ቆየሁ።

ከምሽቱ 5:10 አከባቢ አንድ
ቀን ቀን ሆቴል ሆኖ ማታ ማታ ቅልጥ ወዳለ ጭፈራ ቤት ወደ ሚቀየር ሆት-ጭፈራ ቤት ከውስጥ የሚወጣ እና ትራንስፖርት መጠቀም የሚፈልግ ሰው እስኪወጣ ለመጠባበቅ ጠጋ ብዬ እንደቁምኩ አይኔ አንዲት ከራስ ፀጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ የሚጣል ነገር የሌላት በዛው ሰአት ሰማይ ላይ እንዳለችው ጨረቃ ደስ የሚል ውበት ያላት ልጅ መግቢያ በሩ በስተቀኝ ብርዱን ለመቋቋም ከጡቶቿ በታች እጆቿን አጠላልፋ በማጣመር ቆማለች።
ሁኔታዋ ሲታይ ግራ ግብት ያላት ትመስላለች እዛው ቆማ አንዴ ቁልቁል አንዴ ሽቅብ ትገላመጣለች ።

እድሜዋ በግምት በ 19 እና በ21 መካከል ቢሆን ነው ይቺን የመሰለች ልጅ በዚህ ሳአት ሊያውም ብቻዋን እንዴት? ትልቁ የውስጤ ጥያቄ ነበር ።
አከባቢው ለኔ አዲስ ባይሆንም ልጅቷ ግን ለአከባቢው እዲስ ሳትሆን አትቀርም ከዚህ በፊት አይቻት አላውቅም ከባጃጄ ወርጄ ምነው ብቸሽን ልበላት አልበላት እያልኩ ከፍርሀቴ ጋር ስነታረክ አንዱ ስልክ ሊያናግር ከውስጥ ወደ ውጪ ወጣና ወድያው ስልኩን አናግሮ እንደጨረሰ አብረን እንግባ ብሎ ልጅቷ ላይ ሙዝዝ አለባት ከዛ በፊት እንደማይተዋወቁ ከሁኔታዋ ተረዳሁ።

ድርቅ ሲልባት ብስጭት ብላ ውዝውዝ ቅንጥስ ብጥስ እያለች ቀጥታ ወደኔ ባጃጅ መጣች ከመድረሷ በፊት ባላየ ፊቴን ወደ ፊት ለፊት አዞርኩ።
ደርሳ " ይቅርታ ወንድም ግቢ ትወስደኛለህ? ኮንትራት "
አለች ዩንቨርስቲ ማለቷ ነው ልጅቷ የዩንቨርስቲ ተማሪ እንደሆነች ለማወቅ ግዜ አላጠፋሁም ዩንቨርስቲው ደግሞ ከከተማው ትንሽ ወጣ ይላል
200 ብር ትከፍያለሽ አልኳት
ግማሽ ፊቷ ላይ ዘንፈል ብሎ ጋደም ያለውን ፀጉሯን በቀኝ እጃ ሁለት ጣቶች ወደ ጀርባዋ ብትን አደረገችና
"200 ብር ለተማሪ አይበዛም ወንድሜ ቤተሰብ በወር የሚልክልኝ እኮ 300 ብር ነው !" አለችኝ

መጀመሪያ አሳዘነችኝ !

ቆይቼ ደግሞ ታድያ አርፈሽ ትምህርትሽን አታጠኝም በዚህ ሰአት እዚህ ምን ትሰሪያለሽ ?!ልላት ፈለኩና እሷን እንዲህ ለማለት ምንም አይነት መብት እንደሌለኝ ቶሎ በማስታወሴ ምላሴን ሰበሰብኩ።

"እ ምናልክ " አለችኝ ።

በደንብ ተመለከትኳት። ውስጤ ተላወሰ ።
እሺ ግቢ እንሂድ አልኳት
"በስንት?" አለችኝ
ደስ ያለሽን ትከፍያለሽ ዘላ ገባች ። ትንሽ በዝምታ እንደተጓዝን ድንገት ዘወር አልኩና•••
•••ሂሳብም አስቀንሰሽ ዝምም ብለሽ አያዋጣኝም !
"ኦኬ እእእእእ ግን ይቅርታ በናትህ ከሚከብዱኝ ነገሮች አንዱ ጫወታ ቀድሞ መጀመር ነው" አለች እየተቁነጠነጠች
ምን አይነት ጫወታ ? አልኳት
"ያው ወሬ ነዋ ሌላ ምን አለ?"
ኧረ ብዙ አይነት ጫወታ አለ ተጫውተሽ አታውቂም እንዴ?
"እንዴ ! ክክክክክ እሱማ ብዙ አይነት ጫወታ አለ እኔ ለማለት የፈለኩት ግን ወሬውን ነው"
ሳቋ ልክ እንደ ህፃን ልጅ ሳቅ ደስ የሚል ለዛ አለው ።
ምን አይነት ጫወታ ይቀልሻል? ወይም ትወጃለሽ?
"እቃቃና እኩኩሉ ልበልህ "
ተሳሳቅን ሳቋን ወደድኩት።
ወደ ዩንቨርስቲው እየተቃረብን ነው።
እሺ እኔ ጫወታ በመጀመር ላግዝሻ?
"ከዚህ በላይ እሄው ጀመርከው እኮ! አለችኝ
እኔ ግን ጥያቄ ነበረኝ
የዩንቨርስቲ ተማሪ ሆነሽ በዚህ ሰአት ብቻሽን እዛ ጭፈራ ቤት በር ላይ ለምን ቆምሽ ወይ ገብተሽ አልተዝናናሽ
በረጁሙ ተነፈሰች ቀጠል አርጋም •••
አንድ ነገር ልንገርህ እንኳን ለኮንትራት ለምንም የሚሆን አምስት ሳንቲም ኪሴ ውስጥ የለም የፈለከውን አርገኝ!
ሲጢጢጢጢጥ ባጃጇን ከመቅፅፈት ቀጥ አድርጌ ስዞር ሽምቅቅ ብላለች

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ።
​​#ልጩህበት !


#ክፍል_ሁለት


#ድርሰት_በጥላሁን

...በረጁሙ ተነፈሰች ቀጠል አርጋም •••
አንድ ነገር ልንገርህ እንኳን ለኮንትራት ለምንም የሚሆን አምስት ሳንቲም ኪሴ ውስጥ የለም የፈለከውን አርገኝ!
ሲጢጢጢጢጥ ባጃጇን ከመቅፅፈት ቀጥ አድርጌ ስዞር ሽምቅቅ ብላለች••
••••
እንደፈራች ገባኝ
እኔ ሽምቅቅ ልበልልሽ አልኩ በሆዴ
ዝም ብዬ ሳያት ሳቋ መጣ ፍርሀት የተቀላቀለበት ሳቅ ሳቀች

የፈለከውን አርገኝ ስትይ?

"በቃ ብዙ ሳናወራና ሳንቀራረብ ልንገርህ ብዬ ነው "

እኮ የፈለከውን አርገኝ ስትይ ምን ለማለት ነው?

"እየተጫናነኩኝ ነበረ እኮ እይታይክም እንዴ በቃ ሲጨንቀኝ ነው እንጂ አንተ ባጃጅ ውስጥ የገባሁት ምንም ብር የለኝም ለዛ እኮ ነው ጨንቆኝ እኮ ነው ዝም ብዬ ግንቡን ተደግፌ ስቆም የነበረው"
ከጥያቄዬ እየሸሸች ስትቀበጣጥር የኔም ሳቅ መጣ ቢሆንም ለሶስተኛ ግዜ ጥያቄዬን ሰነዘርኩ
በዚህ መሀል መልሷን በጉጉት እየጠበኩ
አንድ ሰካራም ለሱ ያቆምኩ መስሎት ነው መሰለኝ ኬት መጣ ሳይባል ግራ ቀኝ እየተጋጨ ከውሃላ ገብቶ አጠገቧ ተቀመጠ።

ድንገት ስለገባ ደንግጣ •••

"እማ"

ብላ እየተጣራች ከነበረችበት መሀል ወደ ጥግ ተጠጋች ከሰውየው ራቅ ለማለት።
እሱም መደንገጧን አይቶ ዘወር አለና ወደሷ •••
በመሀል በመሀል ስቅ እያለው•••

"አይዞሽ የኔ ቆንጆ አስደነገጥኩሽ አደል ይቅርታ አንቺኮ - ሀበሻ ሴት ስለሆንሽ ብቻ በጭለማ ውስጥ ያለሽ የ-የ-የ-የ የብርሀን ጭላንጭል ነሽ አይገርምሽም"
አይገርማትም አሁን ባጃጁን ያቆምኩት ላንተ አይደለምና ውረድ አልኩት ድንገት በንዴት!።
ለኔ ንዴት ቦታም አልሰጠው •••
"ለኔማ ነው ያቆምከው! ለሌላ የቆምክ መስሎህ ነው እንዴ?
እኔን እኮ ነው እዛ ጋር ቆሜ ያየከኝ። ሌላ ሰው ቢኖር ለምን እስካሁን አልመጣም? ይልቅ አንተ ስራህን ስራ ከልጅቷ ጋር ላውራበት" ብሎ ሲመልስልኝ ልጅቷ ሳቋን ለቀቀችው።

ሰካራሙ ሰውዬ አንገቱን ከኔ ላይ መንጭቆ በፍጥነት ወደሷ ዞረና•••
"ምን ምን ምን ምን እስቲ በናትሽ ሳቅሽን ድገሚው የተኮረኮረ ህፃን ልጅ እኮ ነው እምትመስይው !
ወይኔ ልጄ ለምን እንደምጠጣ ታውቂያለሽ የልጄን ናፍቆት ለመርሳት !
ልጅ በልጅነት ሲሉ ሰምቼ ምንም ሳይኖረኝ ወልጄ ፍቅረኛዬ እኔ ላይ ጥላብኝ ስትሄድ እኔ ደግሞ አሮጊቷ እናቴ ላይ ጥየባት መጣሁ።

እናቴ ግን መጣያም ቢኖራት የሚጥል አንጀት የላትም እና እኔን ፍዳዋን በልታ ያሳደገችኝ እንዳይበቃት ላስርፋት ሲገባኝ እረፍት እምትነሳ የአንድ አመት ህፃን ልጅ ጥየባት ከመጣሁ ስድስት አመት ሞላኝ አንዴ ብቻ ነው ልጄን ያየሁዋት!!
ግን ግን በናትሽ ካላስቸገርኩሽ ያሁኑን ሳቅ አንዴ ድገሚልኝ !"

ተበሳጨሁ።

ስማ የሷ ሳቅ ስትጋት ያመሸከው ጠጅ መሰለህ እንዴ እሚደገመው አሁን እምትወርድ ከሆነ በፀባይ ውረድልኝ? አልኩት።
"ጠጅ አልጠጣሁን አረቄ ነው ጠጅ ስጠጣ አይተሀል? ነበርክ? ደሞ ሳቅ እንጂ ሌላ ነገር ድገሚኝ አላልኳት ምን አቃጠለክ ኪኪኪኪ " ብሎ ሳቀና ደሞ ወደሷ ዞሮ
"እኔኮ ተሳፋሪ መስለሽኛል ! ፍቅረኛሽ ነው እንዴ ለካ! በቅናት አንገበገብኩልሻ አንበሳ ነኝ አደል አንበሳ••••" እያለ ሳቁን ቀጠለው።
ትግስቴ አለቀ ጎትቼ ላወርደው ተፈናጥሬ ስወርድ•••
"በናትህ ተው እንዳትጣላ " ብላ ጮከች ልጅቷ እጇን እያውለበለበች እና እንዴ ወደኔ አንዴ ወደሱ እየተመለከተች
"አፌ ቁርጥ ይበልልሽ አንቺ ባትኖሪ ምን ይውጠኝ ነበር
ሆሆሆሆ ሊበላኝ ነው እንዴ?
እውነቴን ነው እድሜ ለሴቶች እንበል እናንተ ባትኖሩ እኮ እኛ ወንዶች እሄን ግዜ እንደ ዳይኖሰር እርስ በርስ ተበላልተን ከምድረገፅ በጠፋን ነበር!
አሁን እራሱ ኮረና ያላጠፋን ለምን እንደሆነ ታውቂያለሽ? አታውቂም?
እንደኔ ከሆነ ኮረና ድምጥማጣችንን ያላጠፋን ኢትዮጲያዊያን ሴቶች ጨዋዎች ስለሆናችሁ ነው
እድሜ ለናንተ!
እውነቴን ነው አሁን እኔ ልሙት እንኳን ማክስ ሱሪስ እምታስወልቁን እናንተው አደላችሁ ።
እናንተ ጨዋ ባትሆኑ ማነው ማክስ አላወልቅም የሚለው እንደ ብራዚል ሴቶች ብትሆኑ ማን ይተርፋል ? አልቆልን ነበር ሙች እውነቴን ነው!
እሱ ይለፈልፋል እሷ ትስቃለች !
ሰውየው የባጥ የቋጡን እየቀባጠረ ደሜን ቢያፈላውም ለምን እንደሆነ ባላውቅም በሱ ንግግር የምትሰቀውን ልጅቷን ማየት ስላስደሰተኝ ነው መሰለኝ ሳላስበው ብዙ ታገስኩት
አሁን ትወርዳለህ አትወርድም አልኩት ወደሱ እየተጠጋሁ
"እራስህ እኮ ነህ አቁመህ የጫንከኝ !"
ላንተ አልቆምኩም አልኩህ እኮ!
"ታድያ ለማን ነው የቆምከው?"
ለሷ!
"ለሷ ካካካ እሷኮ አብራህ ነው የመጣችው••••
እሀሀሀ ልታወርዳት ነበር እንዴ የቆምከው ገባኝ !
ታድያ ምን አጣደፈህ ቀስ ብለህ አትቆምም ብቻሽንማ አትወርጂም ነይ በይ እንውረድ!"
ሲላት•••
ሳላውቀው በንዴት ውስጥ ሆኜ ሳቄ መጣብኝ እንደምንም ላለመሳቅ እየታገልኩ ኮሌታውን ይዤ ጎትቼ ላወርደው ስል•••
"እባክህ ተወው እንደዛ አታድርግ ! ቆይ የት ነው መሄድ እምትፈልገው አንተ ?!" አለችው።
"ብዙ አርቅም እኮ እሄኛው መጠጥ ቤት ስለተዘጋብኝ እቅዴ ደሞ አዳሬን መጠጣት ስለሆነ ቤት ልቀይር ነው እዛች ጋ ያለችው ግሮሰሪ ደሞ ካልታሸገች በስተቀር አትዘጋም ወደዛ ነው እምሄደው " ሲላት
"በናትህ ጣል አርገነው እንለፍ ?" እለችኝ ባይኗ እያባበለች
ምነው በሱ ምክንያት የምታመልጪ መሰለሽ እንዴ እሱን አውርጄው የጀመርነውን እንጨርሳለን እሺ አልኳት ኮስተር ልልባት እየሞከርኩ።
ባጃጁን አስነስቼ ከነፍኩ።
"ምን አርጊ ነው እምትላት እነጨርሳለን እንጫረሳለን እያልክ ታስፈራራለህ እንዴ?" አለ
እስቲ ዝምበል ስለው ጭራሽ ባሰበት•••
"ዝም አልልም እንደውም እሱን ተይው አንቺ ብቻ ፍቀጅልኝ?"
"ምን ?"
"አንዴ ልጩህ በናትሽ ?"
"እንዴ ለምን ምን ሆንክ?" አለችው ግራ ተጋብታ ሰውየው መች ያልቅበትና እኔ በማታ ስራ ብዙ ሰካራም ጭኛለሁ እንደዚህ ሰውዬ ግራ ያጋባኝ ሰው አልገጠመኝም ቀጠለ••
"አንቺ ምን ስትሆኚ ነው እምትጮሂው?"
"ምን አይነት ጩኸት?"
"እሄውልሽ እኔ ደስ ሲለኝም እጮሀለሁ ሲጨንቀኝም እጮሀለሁ በናትሽ አሁን አንዴ ልጩህ ? ፈቀድሽልኝ አለና
በጣም በሚያስፈራ ድምፅ አቀለጠው።
እሷም ደነገጠች እኔም ባጃጁን አቁሜ በደምፍላት ወደሱ ዞርኩና
አንተ ሰውዬ እብድ ነህ እንዴ?ስለው
"የፈለከውን በለኝ ግን በናትህ ልጩህበት ተወኝ ?"
እስቲ ወንድ ነህ ድገመው አልኩት። የጉድ ቀን አይመሽም አሉ ዛሬ የጉድ ለሊት አይነጋም ሆነብኝ እሷ በኔና በሱ ሁኔታ ትስቃለች ሰውየው ቀጠለ
ልጩህበት ተወኝ ተወኝ ልጩህበት
በአፌ ቢወጣ የውስጤ እንፋሎት
ለየልኝ እሄ ሰውዬ አላበዛውም እንዴ ግጥምህንም አንተንም አልፈልግም ውረድልኝ
እቺን ግጥም ሳልጨርስልህማ አልወርድም
ታድያ ልጩህ እንጂ ሌላ ምን እላለሁ
የገዛ ጩኸቴ ለኔ እየተሰማ
ንዴቴን
ብሶቴን
ናፍቆቴን ባከስመው
እኔ እየጮህኩኝ እኔ እራሴ ልስማው!!
••••አለ። ጨረስክ አልኩት ።አፍጦ እያየኝ•••
"አዎ ግጥሜን ጨርሻለሁ ግን አንተም ዝም ብለህ አትጩህ እሺ

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍21