‹‹እየወጣህ ነው?››ዔሊ በትከሻው አሻግሮ ወደ ኋላ ተመለከተ። ሊፍቱ ቆሞ ነበር እና በሮቹ ክፍት ነበሩ። አንድ ትልቅ ወንድ እና ሴት በዋናው ፎቅ ኮሪደሩ ላይ ቆመው በፈገግታ እየተመለከቷቸው ነበር። ራሄል እራሷን አላቀቀችና ‹‹ይቅርታ›› ስትል አጉተመተመች።
‹‹ይህ ይቅርታ የሚያስጠይቅ ነገር አይደለም›› አለ ሰውዬው… ሚስቱን መስማማቷን በፈገግታዋ ገለፀች፡፡
ራሄል ሳቀች፣ ከዛ ዔሊን እጁን ይዛ ከአሳንሰሩ አወጣችው። በዝግታ ጎን ለጎን መራመድ ጀመሩ፡፡ግራ መጋባቱን አየችና ‹‹ምን ፈልገህ ነው?›› ብላ ጠየቀችው።
‹‹ለብቻችን ሆነን በአግባቡ የምንነጋገርበት ቦታ ››
ራሄል እግሩ ላይ ቆማ በፍጥነት እና ጠንክር ያለ ስሞሽ ሳመችው። ‹‹ኤሊ እወድሃለሁ። እና ማንም ቢያውቅ ወይም ቢያየን ግድ የለኝም። ለትክክለኛው ነገር ግድ የለኝም እና ከየት እንደመጣህ ግድ የለኝም። ወዴት እንደምንሄድ ግድ የለኝም ከአንተ ጋር መሆን ብቻ ነው የምፍልገው።››ዔሊ ራሱን በአግራሞት ነቀነቀ እና እጁን በወገቧ ዙሪያ ጠመዘዘ እና አቀፋት።
‹‹እኔም እንዲሁ። ግን ያለ ተመልካቾች አንዳንድ ተራ ውይይት ማድረግ እመርጣለሁ።››ራሄል ወደ እሱ ተጠግታ ቃተተች።‹‹ የዚያህን ቃል ድምፅ ወድጄዋለሁ።ታዲያ ወዴት እንሂድ?››
‹‹የወላጆችሽ ቦታስ? ያን ያህል ሩቅ አይደለም››
‹‹ይህ የግል ጉዳያችን አይመስልህም..ለእኛ የሚሆን ድብቅ ቦታ እዛ የምናገኝ ይመስልሀል? ›› አለች ራሄል ፡፡
‹‹እየቀለድሽ ነው? በዚያ ቦታ ቢያንስ 20 ክፍሎች አሉ…።››
‹‹ሀያ አይደለም …አስራስምንት ብቻ ነው››ስትል አረመችው፡፡ ‹‹ከእነዚያም አንዳንዶቹ የአገልጋዮች መኖሪያ ናቸው።››ስትል አከለችበት
‹‹ይቅርታ አድርጊልኝ››አለ ኤሊ እየሳቀ። ‹‹ግን ለመነጋገር ልንጠቀምበት የምንችለው ጸጥ ያለ ቦታ ከአስራስምንቶቹ ክፍሎች በአንዱ ውስጥ እንደምናገኝ እርግጠኛ ነኝ።››
‹‹እንደምንችል እገምታለሁ..የራሴ መኝታ ቤት እስከአሁንም ባለበት እንዳለ አትርሳ" አለችው እና እጇን ከእጁ ጋር አቆላልፋ ወደእሷ መኪና ገብታው ከሆስፒታሉ ወጡ።
✨ይቀጥላል✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

👍40❤12
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ…
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
//
ራሄል በወላጆቿ ቤት ከመዋኛ ገንዳ አጠገብ ከእናትና አባቷ ጋር ተቀምጣ የጥዋት ፀሀይ እየሞቀች ነው፡፡
ፀጋ ‹‹ አበባ ስጪኝ?››ስትል እህቷን ጠየቀች፡፡
ራሄል ከተቀመጠችበት ተነሳችና የፀሐይ መነፅሯን ወደ ጭንቅላቷ ገፋ በማድረግ እህቷ የፈለገችውን አበባ ቀነጠሰችና በትናንሽ እጆቾ ውስጥ አስቀመጠችላት…ፀጋ በደስታ ፈነጠዘች፡፡
ሮቤል እና አዲሷ ረዳት የፋውንዴሽኑን ስራ ከአሰበችው በላይ በጥሩ ብቃት እየመሩላት እንደሆነ ለሁለት ቀን ወደቢሮ ተመልሳ ባደረገችው የስራ ግምገማ መረዳት ችላለች፡፡
…እህቷን ለማስታመም በሆስፒታል ባሳለፈቻቸው አስር ቀናት ውስጥ ምንም የጎደለ እና ሳይሰራ የተወዘፈ ስራ አልነበረም…እና አሁንም ለሌላ አንድ ሰምንት ታናሽ እህቷ በደንብ እስክታገግም አብራት እንድትሆንና ቀለል ያሉ ስራዎችን እዛው እቤት ሆና እንድትሰራ ፈቅደውላት እሷም ተስማምታ ወላጇቾ ቤት ነው ያለችው፡፡
‹‹ኤሊ እመጣለሁ ያለው መቼ ነው?››ወ.ሮ ትርሀስ መጽሃፏቸውን ከጎኗቸው ባለ የመስታወት ጠረጴዛ ላይ አስቀምጠው ራሄልን ጠየቋት።
‹‹ከሶስት እስከ አራት ሰዓት እመጣለሁ ነበር ያለው ፡፡ ››መለሰች…ጸጋ ራሷ ቀጥፋ የሰጠቻትን አበባ ፀጉሯ መካከል ሻጠችላት…ራሄል በፈገግታ እህቷን ወደራሷ ሳበችና ጉንጮን በመሳም‹‹ትንሿ እህቴ ..እንዲህ ስላሳመርሺኝ አመሰግናለው››አለቻት፡፡
በዛው ቅፅበት ወደግዙፉ ግቢ እየቀረበ የሚመጣ የመኪና ድምፅ ተሰማ ፡፡
‹‹የምትጠብቂው ጓደኛሽ አለ እንዴ?››አቶ ቸርነት ጠየቁ፡፡
‹‹ አይ አይመስለኝም?››ራሄል እርግጠኛ ባለመሆን ጠየቀች፡፡
‹‹እንግዲያው አለም መጥታ ማንነቱን እስክታሳውቀን እንጠብቅ ?››በማለት እናቷ ሳቁ።
አለም ወዲያው እየተፍለቀለቀች መጣች…‹‹ራሄል ነይ እንግዳሽን ተቀበይ››
‹‹ማን ነው?››
‹‹አትንገሪያት ተብያለው…እራስሽ መጥተሸ እይው››አለችና ወደኪችኗ ተመለሰች፡፡
ራሄል.‹‹ማነው በወላጆቼ ቤት ከእኔ ጋር እንዲህ አይነት ጫወታ ለመጫወት የደፈረው?››በማለት ተነስታ ፀጋን ይዛ ሄደች።ራሄል እና ፀጋ ወደ ግቢው የመኪና ማቆሚያ አካባቢ ሲሄዴ ኤሊ ወደ ውስጥ ሲገባ ተመለከቱት ።ራሄል እንዳየችው በውስጧ የደስታ ማዕበል አጥለቀለቃት።
ባለመኪና ስትጠብቅ ባለሞተር ሰው በማየቷ ተደንቃ ‹‹ሄይ፣ እንዴት እዚህ ደረስክ? የሞተር ሳይክልህን ድምፅ አልሰማሁም።››አለችው…
ዔሊ ጎንበስ ብሎ በቀስታ ሳማት እና ፀጋን አንስቶ ካቀፋት በኃላ‹‹ሌላ አይነት የመጓጓዣ ዘዴ ነው የተጠቀምኩት.››ሲል መለሰላት፡፡
‹‹ሞተርህ ተበላሸች እንዴ ?›› አለችና አይኖቾን ወደመኪና ማቆሚያ አዞረች ከእሷ ቀይ መኪና አጠገብ የቆመ ባለ ሰማያዊ ቀለም መኪና እያየች ግራ ተገባች።
‹‹ ያን መኪና ከማን ነው የተዋሰከው? ወንድምህ እንደዚህ አይነት መኪና የለውም።››
ዔሊ ተነፈሰ። ‹‹እነሆ፣ ወ.ሮ ራሄል ሞተሬን ሸጥኩት።››
ራሄል መኪናዋን በድጋሜ ተመለከተች፣ ‹‹ሞተር ሳይክልህን አስወገድከው !አየህ እኔ ስለ አንተ የምወደው ያን ነው ። ቆንጆ እና ፈጣን ተማሪ ነህ….ግን ለምን?››
…‹‹ደህና፣ በአንድ ወቅት አንድ ሰው እንዴት አንድ ኃላፊነት የሚሰማው ለዛውም የህፃናት ሀኪም የሆነ ሰው ሞተር ሳይክል ይነዳል ? የሚል ጥያቄ ጠየቀኝ። እና ለእሱ መልስ ለመስጠት ብዬ ነው መኪና የገዛሁት፡፡››
ራሄል ወደ መኪናው ሄዳ እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ ትንሽ ነካችው፣ ከዚያም ወደ ዔሊ ተመለሰች፣ ››
‹‹አስደንቀኸኛል ››አለችው
‹‹ስለሞተር ሳይክሎች ያለሽን ስሜት ስለማውቅ እናም የፍራቻሽም ምክንያት በከፊል ትክክል መሆኑን ስላመንኩበት ነው...››
እዛው የሳሎኑ በረንዳ ላይ ካሉ ወንበሮች አንዱን እንዲቀመጥ ሳበችለት ፀጋን በክንዱ እንዳቀፈ ተቀመጠ….ከጎኑ ሌላ ወንበር ስባ ተቀመጠች፡፡
ከዛ ሳታስበውና ምንም ሳትዘጋጅበት ትልቅ ቁም ነገር ከአንደበቱ አፈትልኮ ወጣ ‹‹ይህን ሁሉ በትክክለኛው መንገድ ይፋ ማድረግ ፈልጌ ነው …ራሄል፣ ላገባሽ እፈልጋለሁ።››አላት፡፡
ጆሮዎቾን ማመን አልቻለችም…ልቧን ደረቷን ሰንጥቆ እንዳይወጣ የፈራች ይመስል ደግፋ ያዘችው ። በውስጧ የሚንተከተከው ደስታ እና ፍቅር እና ምስጋና መውጫ ለማግኘት እየሞከሩ በአንደበቷ ላይ ተንገዋለሉ….ማልቀስ ብቻ ነው የቻለችው፡፡
‹‹ሄይ እኔ ያን ያህል መጥፎ ነገር አልተናገርኩም….ለምን ታለቅሻለሽ?››
‹‹በጣም ደስ ብሎኝ ነው…..››ስትል በለሆሳሳ መለሰችለት፡፡‹‹እወድሀለሁ ኤሊ›› ወደ እሱ ተሳበችና ጉንጩን ሳመችው..ታፋው ላይ የተቀመጠችው ፀጋ በደስታ እጆቿን እያጨበጨበች በሳቅ ተንከተከተች። የእሷ ሳቅና ደስታ ወደ እነሱም ተጋባ፡፡
‹‹መጀመሪያ ዝም ብዬ ለአንቺ ምንም ሳልነገርሽ ወደቤተሰቦችሽ ሽማግሌ ለመላክ አቅጄነበር …››
‹‹እንዴ የእኔን ሀሳብ ሳታውቅ ሽማግሌ ልከህ እምቢ ብልህስ?››
‹‹ያው ምን አደርጋለው የተሰበረ ልቤን ይዤ የብቸኝነት ኑሮዬን ቀጥላለዋ !!››ብሎ ትከሻውን ነቀነቀ።ራሄል ጣቷን ከንፈሩ ላይ አድርጋ ሳቀች።
‹‹ ስለነርከኝ ደስ ብሎኛል፣ደግሞ ስትነግረኝ ፀጋ በመሀከላችን መገኘት በመቻሏ ደስታዋ ድርብ ሆኗል … ለነገሩ እኛን አንድ ያደረገች እሷ ነበረች.››
‹‹እሺ ስላልሽኝ ደስ ብሎኛል…:በዚህ ምክንያት በህይወቴ ለሆነው ነገር እግዚአብሔርን በየቀኑ አመሰግነዋለሁ:: በአንቺ ምክንያት ህይወቴ መሉ ሆኗል››
‹‹አንተ ስጦታዬ ነህ ኤሊ ›› አለችና አቀፈችው።
‹‹አሁን እናትና አባትሽን እንፈልግ።››
ተስማሙና …ተያይዘው በአረንጓዴ ተክሎች ወደተሸፈነው ግዙፉ ጊቢ ተያይዘው እየተሳሰቁ ሄዱ፡

❤59👍14