አትሮኖስ
279K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
458 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
የራሄል  አይኖች ግን ፀጋ ላይ ብቻ ነበር የተሰኩት። ከአንድ ትከሻዋ ላይ የወረደ የሆስፒታል ጋዋን ለብሳ አልጋው ላይ እንዳለች ትንሽ አሻንጉሊት ትመስላለች። ሌላ ነገር ማየት አልቻለችም። በፀጋ አፍ ውስጥ የገባውን ቱቦ ያስፈራል፣ የምትተነፍስበት የመተንፈሻ አካል ጩኸት ሰቅጣጭ ነው፣ ህይወቷን ህልውና የሚቆጣጠሩ የተለያዩ ማሽኖች የሚያሰሙት ድምፅ ለራሄል በጣም ቀፋፊ የሚባል ነው  ፡፡ ከደረቷ እና ክንዷ በሌሎች ማሽኖች አማካኝነት በአልጋዋ ላይ ተንጠልጥለው ከከረጢት ፈሳሽ እየመጠጡ ወደሰውነቷ ያስገባሉ...ከጥቂት ሰዓታት በፊት ይህቺ ምስኪን  በራሄል እቅፍ ውስጥ ነበረች፡፡፡አሁን ግን ህይወቷ በበርካታ  መሳሪያዎች ተደግፎ ይገኛል ...አንድ የታወቀ ድንጋጤ ደረቷን ሲሰነጣጥቃት  ታወቃት። ‹‹እዚህ መሆን አልቻለችም። በዚህ የተደራጁ የቧንቧ እና የመቆጣጠሪያ መሳሪያዎች የታጠረችውን  ተወዳጇን ይህችን  ትንሽ  አቅመቢስ ህጻን  ማየት አልቻለችም። የዚችን ትንሽ ልጅ ነፍስ ከደካማ አካሏ ስትለይ ማየት አልቻለችም።››…ኪሩቤል ልክ እንደእሷ በማሽን ቁጥጥር ስር ሆኖ  ሲያጣጥር  ‹‹በቂ አየር እያገኘሁ አይደለም…መተንፈስ እያቃተኝ ነው።››እንዳላት ታስታውሳለች….ይህቺ ትንሽ ፍጡርም አንደበቷን አላቃ መናገር ባትችልም…ምን አልባት መተንፈስ በጣም ከብዷት ሊሆን ይችላል ስትል አሰበች፡፡

ራሄል ከእይታዋ እየጨለመባት መጣ ..ቀስ ብላ  በእጇ የወንበሩን ጀርባ ያዘች እና እራሷን ዝቅ አደረገች።ቀስ ብላ ተንበረከከች…እጇን በዝግታ ዘረጋች ፣የፀጋን እጅ ስታገኝ አቆመች፣ ከፀጋ አውራ ጣት ጋር የተጣበቀውን የኦክስጂን መቆጣጠሪያ እንዳትነቅል እየተጠነቀቀች  ጣቶቿን በዙሪያው አንሸራተተች።ከእጇ ጋር ያለው ቅጽበታዊ ግንኙነት በልቧ ውስጥ የተስፋ ጭላንጭል ፈነጠቀባት።

‹‹ኃይሌ በድካም ፍጹም ነው›› የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ወደ አእምሮዋ ገባ እና ራሄል ደጋግማ ደጋግማ አነበነበችው፣ የቀረውን ክፍል ብታስታውስ ደስ ይላት ነበር፣ መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ ረገድ  እሷ በጣም ከልምምድ ውጪ ሆና ቆይታለች ፣ ቢሆንም ግን አሁን ማድረግ የምትችለው ብቸኛው ነገር  መፀለይ ነው።ለዛ ነው ሰራተኛዋ አለምን ከቤት መፅሀፍ ቅዱስ እንድታመጣላት ያደረገችው፡፡ምን አልባት የምታደርገው ፀሎት ያቺን ሚስኪን ህፃን ሊጠቅም ይችላል?የሚል ከፊል እምነት በውስጧ በቅሏል… የምትወደው ሰው አልጋ አጠገብ ተቀምጣ በሀዘን በተሰበረ ድምፅ  ስትፀልይ ይሄ የመጀመሪያ ጊዜዋ አልነበረም ።ነገር ግን ሀሳቡ በአእምሮዋ ውስጥ ሲንሸራሸር ውስጧ ሙሉ በሙሉ አልተቀበለውም. ፀጋን ወደቤተክርስቲያን ይዛት ከሄደች ቀን ጀምሮ እግዚአብሔርን ዳግመኛ በልቧ ውስጥ የማግኘት ስሜት ተሰምቷት ነበር። ሕልውናውን መካድ አልቻለችም። የምትኖርበት የሱ አለም እንደሆነ  ታውቀዋለች።

ጭንቅላቷን በአልጋው ሀዲድ ላይ ባለው ቀዝቃዛ ብረት ላይ አስደገፈች፣ ዓይኖቿ ፀጥታ ባለው የታናሽ እህቷ አካል ላይ እንደተተከሉ ነው ፣ ፍፁም እርዳታ የለሽ፣ ድካም እና ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ስሜት እየተሰማት ነው።መፅሀፍ ቅዱስን ከፍታ እያነበበች መጸለይ ጀመረች።

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
54👍9
‹‹ቆንጆ ትመስያለሽ.››አላት… ቃላቶቹ ከሱ አምልጠው ነው የወጡት… ሊያቆማቸው አልቻለም።ራሄል ጭንቅላቷን ቀና አደረገች…፣  በግንባሯ ላይ  ብስጭት ይታያል። አልወቀሳትም። ከሁለት ቀን በፊት ወደ እሱ መጥታ የልቧን ልትገልፅለት ፈልጋ ነበር…በምላሹም እሷን ከቤቱ አስወጥቶ ነው ያባረራት ፡፡

ግን ሌላ ምን ማድረግ ይችል ነበር?በወቅቱ የራሱ ህይወት ተዘበራርቆበት ነበር፣ ትዝታው ከእሱ ተሰርቋል፣ ባወቀው ነገር ተበሳጭቷል ፡፡እሱ ተራ ሆኖ ሳለ እንዴት እንደ ራሄል ያለችን ሴት እንዴት ሊጠይቅ ይችላል?

ራሄል እሱ እያሰበ ካለው ሀሳብ ፍፅም ተቃራኒ  የሆነ ጥያቄ ድንገት ጠየቀችው፡፡

‹‹ግልፅ ሆነህ…ምንም ሳትደብቀኝ…ፀጋ ምን ችግር እንዳለባት ልትነግረኝ ትችላለህ?›› የንግግሩን ርዕሰ ጉዳይ ወደ ጋራ ጉዳያቸው ቀየረችው…።

ዔሊያስ እጁን ዘርግቶ ጣቱን ከንፈሯ ላይ በማሳራፍ ከአፏ የሚወጣውን የጥፋተኝነት ፍሰት አቆመ።

‹‹ አሁን ማድረግ የምንችለው መጠበቅ ብቻ   ነው….ከዛ ውጭ ምንም የሚጠቅምሽን  ነገር ልነግርሽ አልችልም ››

አላት….ዝም አለች…በሀሳብ ርቃ እንደሄደች ከሁኔታዋ ማወቅ ችሏል…ሊያቋርጣት አልፈለገም…ከዚህ በፊት እላፊ ቀርቧት በሁለቱ  መካከል የሆነ ነገር እንዳለ እንድታስብ አደረጋት።እና አሁን? ምን እንደሚያስብ እርግጠኛ አልነበረም። በአንድ ወቅት በደንብ ይቆጣጠረው የነበረ   ህይወቱ አሁን  ተገለባብጦበታል ።ነገሮችን ወደቦታቸው ለመመለስ ጊዜ ያስፈልገዋል። ቢሆንም ግን አሁን ከፊት ለፊቱ የተቀመጠችውን ሴት በጣም እንደሚፈልጋት እርግጠኛ ነው፡፡

ድንገት መናገር ጀመረች‹‹ለአመታት በፀሎት ማመን አቁሜ ነበር ።››

‹‹ታዲያ አሁን  ምን ተለወጠ?››

‹‹ህይወቴ.›› በጥንቃቄ ፈገግታ ሰጠችው። ‹‹ሁሉንም ነገር የምቆጣጠር መስሎኝ ነበር፣ እና ለተወሰነ ጊዜ  ነገሮች እኔ በምፈልገው መንገድ እያስኬድኳቸው መስሎኝ ነበር። የምፈልገው አይነት  ስራ እና የምወደው አይነት የመኖሪያ ቦታ እና ትክክለኛ ህይወት ነበረኝ። የኪሩቤልን ሞት ለመርሳት ለማደርገው ጥረት መሸሸጊያ አግኝቼ ነበር። አሁን ግን ፀጋ  ታማለች።›› ራሄል ተነፈሰች። ‹‹አዎ. እና ፈራሁ. እና አዝኛለሁ. ወደ ህይወቴ ባትገባ ኖሮ ብዬ እመኛለሁ እና አጣብቂኝ ውስጥ ገብቼያለው… በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ሆኜ በራሴ ኩራት የምኮፈስበት ምንም አይነት አቅም የለኝም….እና እግዚያብሄር እጅ ላይ ወድቄለው….ይህንንም በግልፅ ማወጅ የምችለው ቀጥታ ከእሱ ጋር በመነጋገር ነው….በፀሎት››

የሚላት ሌላ ነገር ስለጠፋው‹‹ ጥሩ ነገር  ያደረግሽ ይመስለኛል…ግን ዳግመኛ እንድትጎጂ አልፈልግም?››አላት፡፡

‹‹አንዳንዴ መጎዳት ጥሩ ነው… ስጎዳ በህይወት መኖሬን አውቃለሁ። ኪሩቤል ከሞተ በኋላ ስብርብር ስል ሁሉም ሰው ነገሮችን እያጋነንኩ እንደሆነ ነበር የሚያስቡት ። አውቃለው እንደዛ ልጎዳ አይገባም ነበር ። አየህ  ችግሩ ለኪሩቤል ሞት እራሴን ነበር ተጠያቂ ያደረኩት… የዛን ቀን  ባንጣላ ኖሮ በብስጭት ጥሎኝ አይሄድም ነበር …ባይበሳጭ ኖር ደግሞ በተሻለ ትኩረት ያደርግ ነበር፣ እናም በዛ ሰካራም ሹፌር አይመታም ነበር፣ ….አይገርምም .. ከእኔ አንደበት የሰማቸው የመጨረሻ ቃላቶች  ስለዛ ሞተር ሳይክል የተሰነዘረ  ትችት እና ቁጣ ነበር…. ‹‹ሞተር እየነዳህ ሁለተኛ ወደእኔ እንዳትመጣ ››ነበር ያልኩት….፡፡

‹‹ራሄል እንደዚያ አታስቢ። ጥፋቱ ያንቺ አልነበረም።››

‹‹ አሁንማ አውቃለሁ,… ግን ለዓመታት, እንደዛ ነበር የማስበው … እሱን አፈር ውስጥ እንዲገባ አድርጌ እኔ ግንኙነት የመጀመር መብት የለኝም   ብዬ እራሴን ስቀጣ ነበር የኖርኩት … ከዚያም ባላሰብኩት አጋጣሚ ድንገት  ፀጋ ወደ ህይወቴ ገባች….ተስፋዬን አደሰችው …ጨለማ ጎኔን ሸንቁራ ብርሀን እንዲፈስበት አደረገች …ከእንደገና በጣም እንዳፈቅር አበረታታችኝ…ነገን እንድናፍቅና  ከስራ ውጭ ስላለ ህይወቴ እንዳሰላስል አደረገቺኝ…እንደገና እየወለደችኝ እንዳለ ነው የሚሰማኝ…አንድ ነገር ከሆነችብኝ እንዚህን ሁሉ በጎ ስሜቶች መልሼ እንዳላጣቸው ፈራለሁ…ስጋቴ ዳግመኛ እንዳልሞት ነው ››በእንባ እየታጠበች ቢሆንም   ፈገግ አለች፣ የእፎይታ ትንፋሽ ወሰደች።‹‹ እናም ለዛም ነበር ከአንተ የራቅኩት እና ስለፈራሁ ይቅርታ።››

‹‹ ራሄል እባክሽ ለዚህ ይቅርታ አትጠይቂ››በነገረችው ነገር ልቡ አዘነ። የሆነ ነገር ለመናገር አስባ ..ተወችው…ከንፈሯ እየተንቀጠቀጠ ነው። ዔሊያስ ከዚህ በላይ ሊቋቋመው አልቻለም። ጠጋ ብሎ ወደ እቅፉ አስገባት።ደረቱ ላይ ለጠፋት፣ እንባዋ በገላው ላይ ሲንጠባጠብ  ሙቀት ተሰማው።

‹‹ ፈራሁ ኤሊ። በጣም ፈርቻለሁ። እና እንደዚህ አይነት ስሜት እንደገና እንዲሰማኝ አልፈልግም ነበር። ›› ድምጿ ተሰባበረ እና ወደ እሱ ተጣበቀች።

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
62👍14
ዔሊያስ ‹‹ፀጋ አሁን ደህና ናት…ወላጆችሽ አሁን አሉ እና ነርሶች ሁል ጊዜ አጠገቧ ናቸው.››

‹‹አውቃለሁ።››አጠገቧ ያለውን መቀመጫ እየደበደበች ቀና ብላ ተመለከተችው።

‹‹እባክህ መጥተህ እዚህ ተቀመጥ …አንድ ነገር ልነግርህ እፈልጋለሁ ››አለችው፡፡
በጣቷ ላይ ያለውን ቀለበት እያሽከረከረች  በጎን  ተመለከተችው። በወቅቱ ያጠለቀችው  ብቸኛው ጌጣጌጥ እንደሆነ ተገነዘበ።የሚገርመው እጁን በራሷ ያዘች።

ፈራ ተባ እያለ ወደእሷ ተጠጋና ግማሽ ሜትር ያህል ክፍተት ትቶ ከጎኗ ተቀመጠ፡፡ጥቂት የፅሞና ጊዜ ወሰደችና  መናገር ጀመረች‹‹ዛሬ ጥዋት አንተ ባልነበርክበት ጊዜ  አንድ ሰው  ጎብኝቶኝ  ነበረ - ወንድምህ ቢንያም። ስለ ወላጇችህ  ነገረኝ። በቅርብ ስለእነሱ ያወቅከው ነገር እንደጎዳህ አስረዳኝ።››
በኤልያስ ፊት  ላይ ብስጭት ታየ።‹‹ወንድሜ ሚስጥር መጠበቅ የማይችል ወንፊት  መሆኑን አላውቅም ነበር.››

‹‹አንተን ፈልጎ  ነበር የመጣው…እድሉን ሳገኝ ላናግረው ፈለኩ..እኔ ነኝ የወተወትኩት።››ራሄል ፣እጇን ወደእሱ   ዘረጋችና በእጁ ላይ ያለውን ጠባሳ በትንሹ ተጫነችው። ያለፈውን ጊዜ የሚያስታውሰው ምልክት ነው፡፡
‹‹ስለ አንተ ልጠይቀው ፈልጌ ነበር።››

‹‹ለምን?››

‹‹ያን ቀን ልጠይቅህ የመጣሁት  በዝግጅቱ ቀን  ስለእኛ  ስህተት እንደሰራሁ ልነግርህ ነበር ። እንዳልኩት በህይወቴ ውስጥ ሌላ ሰው ላለመፍቀድ በጣም ፈርቼ ነበር። ኪሩቤልን ማጣት ከባድ ነገር ነበር፤ ነገር ግን እነዚያ ቀናት ከአንተ የሰማሁት ነገር የበለጠ ከባድ ነበር፣ እናም ከዚህ በኋላ መጎዳት አልፈልግም - ምናልባት ወንድምህ ሊያውቅ ይችላል ብዬ አስቤ ነበር።

‹‹ለሕይወቴ እቅድ ነበረኝ›› አለ ኤሊያስ። ጣቶቹን ከጣቶቾ አቆላለፈ። ሊለቃት አልፈለገም።

‹‹ቤት ለመስራት  ብድር መበደር ነበረብኝ  ፡፡እዳዬን አስክከፍል ድረስ ቢያንስ ለአንድ ወይም ለሁለት አመት የምጨነቅለትን ሰው  ወደህይወቴ ማስገባት አልፈልግም ነበር ።›› በለሆሳስ ሳቀ፣ ‹‹ከዚያም አየሁሽ፤ ቀድመሽ መጣሽ።››የራሄል የጨለማ አይኖች እየፈኩ ቢሄዱም  ዞር ብላ አላየችም።‹‹ኤሊ ምን እያልክ ነው?››

‹‹ራሄል ላንቺ አስባለሁ:: ከማንም በላይ ህይወቴን ቀይረሽዋል:: ግን ስለ ወላጆቼ ካወቅኩ በኃላ ነገሮች ተገለባበጡብኝ… ምን ማሰብና ምን ማድረግ እንዳለብኝ  አላውቅም. ››

‹‹ወላጆችህ ከእኛ ጉዳይ ጋር ምን አገናኛቸው?››

‹‹... ሌሎች ወላጆች እንዳሉኝ እያወቅኩ ነው ያደግኩት እድሜዬን ሙሉ ወላጆቼ ድንቅ ሰዎች ናቸው ብዬ ነበር የማስበው ›› አለና የተገናኙትን እጆቻቸውን እያየ።
‹‹እርግጥ ያደኩት በሚያስደንቅና እንክብካቤ እና  በፍቅር በተሞላ ቤት ውስጥ ነው፣ነገር ግን ሁልጊዜ የማስታምማቸው ሌሎች ትዝታዎች ስለነበሩኝ፣ለአሳዳጊ ቤተሰቦቼ  በቀላሉ ሊረዱት የሚከብድ አስቸጋሪ  ልጅ ሆንባቸው ነበር።ቢንያም በማደጎ የተወሰደው በጣም ህፃን ሆኖ ስነበር  ወደኋላ ሚጎትተው የስጋ ወላጆቹ ምንም ትዝታ ስላልነበረው ለእነሱ መልካም ልጅ ሆኖ ማደግ ችሏል፡፡እና አሁን ድንገት ስጓጓለት ስለኖርኩት ስለስጋ  ወላጆቼ ታሪክ ካወቅኩ በኃላ በጣም ተናደድኩ  …የተከዳው አይነት ስሜት ነው ተሰማኝ ።"

‹‹ለዛ ነው የዛን ቀን ፎቶዎቹን የጣልካቸው፡፡››

‹‹አዎ…››

‹‹አሳዳጊ ወላጆችህ   ስለስጋ ወላጆችህ ታሪክ ያውቁ ነበር ብለህ ታስባለህ?››

‹‹አይ. አሁን አንኳን እንደዛ  ለማሰብ ይከብደኛል ..ምናልባት እነሱ ለእኔ ውለታ እየሰሩኝ እንደሆነ አድርገው እያስቡ ይሆናል. ነገር ግን እኔ ወላጆቼ ዙሪያ  ህልም  ፈጠርኩ. እኔ ከእውነተኛ ወላጆቼ ጋር ብሆን ኖሮ የተሻለ ህይወት እንደምኖርና የተሻለ ፍቅር እንደማገኝ አስብ ነበር ስለዚህ ፎቶዎቹን ድንገት ሳገኝ  በጣም አስፈላጊ ከሆነው የሕይወቴ ክፍል ጋር የተገናኘሁ ያህል ተሰማኝ። ፍለጋዬ ግን በቀላሉ እራሴን ጎትቼ ማውጣት ወደማልችልበት ቅርቃር ውስጥ ነው ያስገባኝ -በወላጆቼ ላይ ባለኝ ንዴት አሳዳጊዎቼ ላይ  በማመፅ ስጎዳቸው እንደኖርኩ መገንዘቤ ሌላ ፀፀት ላይ ነው የጣለኝ…››
‹‹ከአሳዳጊዎችህ ጋር ያለህን ግንኑኙነት ለማሻሻልና እንሱን ይቅርታ ለመጠየው እኮ አሁንም ጊዜው አረፈደም… እነሱ ድንቅ ወላጆች ናቸው፣አንተን አሳድገው ለዚህ ደረጃ አብቅተውሀል..ስለዚህ መመስገንና የሚገባቸውን የአንተን ፍቅር ማግኘት ይገባቸዋል፡፡ ›› አለችኝ ቀና አድርጋ ጉንጩን እየዳሰሰች።

‹‹ትክክል ነሽ…እንደዛ ነው የማደርገው…››አላት

‹‹ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ እግዚአብሔር ከእኔ የሚፈልገውን ለማወቅ በመጸለይ ብዙ ጊዜ አሳልፌአለሁ፣ እና አላውቅም። ፀጋን ሊራራላት ወይም ሊወስዳት እንደሆነ አላውቅም። ታገልኩት። በቃ ጠንክሬ ከጸለይኩ፣ ነገሮች በፈለኩት መንገድ ይከሰታሉ ብዬ በማሰብ የምችለውን ሁሉ እያደረኩ ነው…እኛ የሰው ልጆች በወቅቱና በሰዓቱ ማድረግ የምንችለውን ነገር ሁሉ ማድረግነው የሚጠበቅብን …ፀፀትና ቁጭት  ነፍሳችንን የሚያከሳ በሽታ ነው….እንደዛ ይመስለኛል፡፡››

‹‹‹ሙሉ በሙሉ ትክክል ትመስይኛለሽ.››አላትና አቅፎ ጉንጮን ሳማት፡፡ፊቷ ቀላ፡፡
ለተወሰኑ ደቂቃዎች ዝም ተባባሉ፡፡ከዛ እንደምንም አማጠና‹‹ታዲያ ይህን እንዴት እናደርጋለን ራሄል?ማለቴ የእኔና የአንቺ ጉዳይ …በፀጋ ሁኔታ ላይ የተመሰረተ ነው ?››ሲል ስጋቱን ጠየቃት፡፡
በጥንቃቄ ፈገግ  አለችና ‹‹አሁንም በእሷ ላይ ስለሚደርስባት  ነገር እፈራለሁ፣ ምንም እንድትሆንብኝ አልፈልግም… ነገር ግን በዝግታም ቢሆን መልቀቅን እና በእግዚአብሔር እጅ ማስቀመጥን እየተማርኩ ነው። እናቴ ቅድም የተናገረችው ነገር ልቤ ላይ አርፏል፡፡ ፀጋ  ለእኔ ለአንተ ፤ለአባቴ እና ለእናቴ ለሁላችንም  ከእግዜር የተሰጠችን አደራችን ነች፣ከእኛ የሚጠበቀው አብራን እስካለች ድረስ እሷን መንከባከብ፤መጠበቅና ምቾት እንዳይጓደልባት ማድረግ ነው…ሌላውን ለእሱ ለባለቤቱ መተው አለብን…አዎ እንደዛ ማድረግ የሚገባን ይመስለኛል…ወደጥያቄህ ስመለስ የእኔ እና የአንተ ጉዳይ ላይ ምንም ችግር እንደማያመጣ ነው የማስበው፡፡  ››ዔሊያስ በዚህች አስደናቂ ሴት እየተደመመ ፊቷን በጣቶቹ ዳሰሰ። ከዚያም ሳያስበው፣ ጠጋ ብሎ ሳማት። ተጣበቀችበት።

‹‹እዚህ ስላመጣሀኝ ደስ ብሎኛል››አለች ..ወዲያው መልሷ ይስማት ጀመር…ድንገት በሩ ተከፍተ …በድንጋጤ ተለያዩ::
አንድ  ነርስ ነበረች ‹‹ይቅርታ ደ/ር  ፀጋ በጭንቀት ላይ ነች።››ሁለቱም በምን ፍጥነት ተፈትልከው ፀጋ ወደተኛችበት ክፍል  ደደረሱ እነሱም አያውቁትም፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
88👍16
‹‹እየወጣህ ነው?››ዔሊ በትከሻው አሻግሮ ወደ ኋላ ተመለከተ። ሊፍቱ ቆሞ ነበር እና በሮቹ ክፍት ነበሩ። አንድ ትልቅ ወንድ እና ሴት በዋናው ፎቅ ኮሪደሩ ላይ ቆመው በፈገግታ እየተመለከቷቸው ነበር። ራሄል እራሷን አላቀቀችና   ‹‹ይቅርታ›› ስትል አጉተመተመች።

‹‹ይህ ይቅርታ የሚያስጠይቅ ነገር አይደለም›› አለ ሰውዬው… ሚስቱን መስማማቷን በፈገግታዋ ገለፀች፡፡

ራሄል ሳቀች፣ ከዛ ዔሊን እጁን ይዛ ከአሳንሰሩ አወጣችው። በዝግታ ጎን ለጎን መራመድ ጀመሩ፡፡ግራ መጋባቱን አየችና ‹‹ምን ፈልገህ ነው?›› ብላ  ጠየቀችው።

‹‹ለብቻችን ሆነን በአግባቡ የምንነጋገርበት ቦታ ››

ራሄል እግሩ ላይ ቆማ በፍጥነት እና ጠንክር ያለ ስሞሽ  ሳመችው። ‹‹ኤሊ እወድሃለሁ። እና ማንም ቢያውቅ ወይም ቢያየን  ግድ የለኝም። ለትክክለኛው ነገር ግድ የለኝም እና  ከየት እንደመጣህ ግድ የለኝም። ወዴት እንደምንሄድ ግድ የለኝም ከአንተ ጋር መሆን ብቻ ነው የምፍልገው።››ዔሊ ራሱን በአግራሞት  ነቀነቀ እና እጁን በወገቧ ዙሪያ ጠመዘዘ እና አቀፋት።

‹‹እኔም እንዲሁ። ግን ያለ ተመልካቾች አንዳንድ ተራ ውይይት ማድረግ እመርጣለሁ።››ራሄል ወደ እሱ ተጠግታ ቃተተች።‹‹ የዚያህን  ቃል ድምፅ ወድጄዋለሁ።ታዲያ ወዴት እንሂድ?››

‹‹የወላጆችሽ ቦታስ? ያን ያህል ሩቅ አይደለም››

‹‹ይህ የግል ጉዳያችን አይመስልህም..ለእኛ የሚሆን ድብቅ ቦታ እዛ የምናገኝ ይመስልሀል? ›› አለች ራሄል ፡፡

‹‹እየቀለድሽ ነው? በዚያ ቦታ ቢያንስ 20 ክፍሎች አሉ…።››

‹‹ሀያ አይደለም  …አስራስምንት  ብቻ ነው››ስትል አረመችው፡፡  ‹‹ከእነዚያም አንዳንዶቹ የአገልጋዮች መኖሪያ ናቸው።››ስትል አከለችበት

‹‹ይቅርታ አድርጊልኝ››አለ ኤሊ እየሳቀ። ‹‹ግን  ለመነጋገር  ልንጠቀምበት የምንችለው ጸጥ ያለ ቦታ ከአስራስምንቶቹ  ክፍሎች በአንዱ ውስጥ እንደምናገኝ እርግጠኛ ነኝ።››

‹‹እንደምንችል እገምታለሁ..የራሴ መኝታ ቤት እስከአሁንም ባለበት እንዳለ አትርሳ" አለችው እና እጇን ከእጁ ጋር አቆላልፋ ወደእሷ መኪና ገብታው  ከሆስፒታሉ ወጡ።

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍4112
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

//
ራሄል በወላጆቿ ቤት ከመዋኛ ገንዳ አጠገብ ከእናትና አባቷ ጋር ተቀምጣ የጥዋት ፀሀይ እየሞቀች ነው፡፡

ፀጋ   ‹‹ አበባ ስጪኝ?››ስትል እህቷን ጠየቀች፡፡

ራሄል ከተቀመጠችበት ተነሳችና   የፀሐይ መነፅሯን ወደ ጭንቅላቷ ገፋ በማድረግ   እህቷ የፈለገችውን  አበባ ቀነጠሰችና በትናንሽ እጆቾ ውስጥ አስቀመጠችላት…ፀጋ በደስታ ፈነጠዘች፡፡
ሮቤል እና አዲሷ ረዳት የፋውንዴሽኑን ስራ ከአሰበችው በላይ  በጥሩ ብቃት እየመሩላት እንደሆነ ለሁለት ቀን ወደቢሮ ተመልሳ ባደረገችው የስራ ግምገማ መረዳት ችላለች፡፡
…እህቷን ለማስታመም በሆስፒታል ባሳለፈቻቸው አስር ቀናት ውስጥ ምንም የጎደለ እና ሳይሰራ የተወዘፈ ስራ አልነበረም…እና አሁንም ለሌላ አንድ ሰምንት ታናሽ እህቷ በደንብ እስክታገግም አብራት እንድትሆንና ቀለል ያሉ  ስራዎችን እዛው እቤት ሆና እንድትሰራ ፈቅደውላት እሷም ተስማምታ  ወላጇቾ ቤት ነው ያለችው፡፡

‹‹ኤሊ እመጣለሁ ያለው መቼ ነው?››ወ.ሮ ትርሀስ  መጽሃፏቸውን  ከጎኗቸው  ባለ የመስታወት ጠረጴዛ ላይ አስቀምጠው ራሄልን  ጠየቋት።

‹‹ከሶስት እስከ  አራት ሰዓት እመጣለሁ ነበር ያለው ፡፡ ››መለሰች…ጸጋ  ራሷ ቀጥፋ የሰጠቻትን አበባ  ፀጉሯ መካከል ሻጠችላት…ራሄል  በፈገግታ እህቷን ወደራሷ ሳበችና ጉንጮን በመሳም‹‹ትንሿ እህቴ ..እንዲህ ስላሳመርሺኝ አመሰግናለው››አለቻት፡፡
በዛው ቅፅበት ወደግዙፉ ግቢ እየቀረበ የሚመጣ የመኪና ድምፅ ተሰማ ፡፡

‹‹የምትጠብቂው ጓደኛሽ  አለ እንዴ?››አቶ ቸርነት ጠየቁ፡፡

‹‹ አይ አይመስለኝም?››ራሄል እርግጠኛ ባለመሆን ጠየቀች፡፡

‹‹እንግዲያው አለም መጥታ ማንነቱን እስክታሳውቀን እንጠብቅ  ?››በማለት እናቷ ሳቁ።

አለም ወዲያው እየተፍለቀለቀች መጣች…‹‹ራሄል  ነይ እንግዳሽን ተቀበይ››

‹‹ማን ነው?››

‹‹አትንገሪያት ተብያለው…እራስሽ መጥተሸ እይው››አለችና ወደኪችኗ ተመለሰች፡፡

ራሄል.‹‹ማነው በወላጆቼ ቤት ከእኔ ጋር እንዲህ አይነት ጫወታ ለመጫወት የደፈረው?››በማለት ተነስታ ፀጋን ይዛ   ሄደች።ራሄል እና ፀጋ  ወደ ግቢው የመኪና ማቆሚያ አካባቢ ሲሄዴ ኤሊ ወደ ውስጥ ሲገባ ተመለከቱት  ።ራሄል እንዳየችው  በውስጧ የደስታ ማዕበል አጥለቀለቃት።

ባለመኪና ስትጠብቅ ባለሞተር ሰው በማየቷ ተደንቃ ‹‹ሄይ፣ እንዴት እዚህ ደረስክ? የሞተር ሳይክልህን ድምፅ አልሰማሁም።››አለችው…

ዔሊ ጎንበስ ብሎ በቀስታ ሳማት እና ፀጋን አንስቶ ካቀፋት በኃላ‹‹ሌላ አይነት  የመጓጓዣ ዘዴ ነው የተጠቀምኩት.››ሲል መለሰላት፡፡

‹‹ሞተርህ ተበላሸች እንዴ ?›› አለችና አይኖቾን ወደመኪና ማቆሚያ አዞረች  ከእሷ   ቀይ መኪና  አጠገብ የቆመ ባለ ሰማያዊ ቀለም  መኪና እያየች ግራ ተገባች።

‹‹ ያን መኪና  ከማን ነው የተዋሰከው? ወንድምህ እንደዚህ አይነት መኪና የለውም።››

ዔሊ ተነፈሰ። ‹‹እነሆ፣ ወ.ሮ ራሄል  ሞተሬን ሸጥኩት።››

ራሄል መኪናዋን በድጋሜ  ተመለከተች፣ ‹‹ሞተር ሳይክልህን አስወገድከው !አየህ እኔ ስለ አንተ የምወደው ያን  ነው ። ቆንጆ እና ፈጣን ተማሪ ነህ….ግን ለምን?››

…‹‹ደህና፣ በአንድ ወቅት አንድ ሰው እንዴት አንድ ኃላፊነት የሚሰማው ለዛውም የህፃናት ሀኪም የሆነ ሰው ሞተር ሳይክል ይነዳል ? የሚል  ጥያቄ ጠየቀኝ። እና ለእሱ መልስ ለመስጠት ብዬ ነው መኪና የገዛሁት፡፡››

ራሄል ወደ መኪናው ሄዳ እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ  ትንሽ ነካችው፣ ከዚያም ወደ ዔሊ ተመለሰች፣ ››

‹‹አስደንቀኸኛል ››አለችው

‹‹ስለሞተር ሳይክሎች ያለሽን ስሜት ስለማውቅ  እናም የፍራቻሽም ምክንያት በከፊል ትክክል መሆኑን ስላመንኩበት  ነው...››

እዛው የሳሎኑ በረንዳ ላይ ካሉ ወንበሮች አንዱን እንዲቀመጥ ሳበችለት ፀጋን በክንዱ እንዳቀፈ ተቀመጠ….ከጎኑ ሌላ ወንበር ስባ ተቀመጠች፡፡

ከዛ ሳታስበውና ምንም ሳትዘጋጅበት ትልቅ  ቁም ነገር ከአንደበቱ አፈትልኮ ወጣ  ‹‹ይህን ሁሉ  በትክክለኛው መንገድ ይፋ   ማድረግ ፈልጌ ነው …ራሄል፣ ላገባሽ እፈልጋለሁ።››አላት፡፡

ጆሮዎቾን ማመን አልቻለችም…ልቧን  ደረቷን ሰንጥቆ እንዳይወጣ የፈራች ይመስል ደግፋ ያዘችው ። በውስጧ የሚንተከተከው ደስታ እና ፍቅር እና ምስጋና መውጫ ለማግኘት እየሞከሩ በአንደበቷ ላይ ተንገዋለሉ….ማልቀስ ብቻ ነው የቻለችው፡፡

‹‹ሄይ እኔ ያን ያህል መጥፎ ነገር አልተናገርኩም….ለምን ታለቅሻለሽ?››

‹‹በጣም ደስ ብሎኝ ነው…..››ስትል በለሆሳሳ መለሰችለት፡፡‹‹እወድሀለሁ ኤሊ›› ወደ እሱ ተሳበችና ጉንጩን ሳመችው..ታፋው  ላይ የተቀመጠችው ፀጋ  በደስታ እጆቿን እያጨበጨበች በሳቅ ተንከተከተች። የእሷ ሳቅና ደስታ ወደ እነሱም ተጋባ፡፡

‹‹መጀመሪያ ዝም ብዬ ለአንቺ ምንም ሳልነገርሽ ወደቤተሰቦችሽ ሽማግሌ ለመላክ አቅጄነበር …››

‹‹እንዴ የእኔን ሀሳብ ሳታውቅ ሽማግሌ ልከህ እምቢ ብልህስ?››

‹‹ያው ምን አደርጋለው የተሰበረ ልቤን  ይዤ  የብቸኝነት ኑሮዬን ቀጥላለዋ !!››ብሎ ትከሻውን ነቀነቀ።ራሄል ጣቷን ከንፈሩ ላይ አድርጋ ሳቀች።

‹‹ ስለነርከኝ ደስ ብሎኛል፣ደግሞ ስትነግረኝ  ፀጋ በመሀከላችን መገኘት በመቻሏ  ደስታዋ ድርብ  ሆኗል … ለነገሩ እኛን አንድ ያደረገች እሷ ነበረች.››

‹‹እሺ ስላልሽኝ ደስ ብሎኛል…:በዚህ ምክንያት በህይወቴ ለሆነው ነገር እግዚአብሔርን በየቀኑ አመሰግነዋለሁ:: በአንቺ ምክንያት ህይወቴ መሉ ሆኗል››

‹‹አንተ ስጦታዬ ነህ ኤሊ ›› አለችና አቀፈችው።

‹‹አሁን እናትና አባትሽን እንፈልግ።››

ተስማሙና …ተያይዘው በአረንጓዴ ተክሎች ወደተሸፈነው ግዙፉ ጊቢ  ተያይዘው እየተሳሰቁ ሄዱ፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
69👍18
አንደኛ ሰርጋቸውን ከሁለት ወር ባነሰ ጊዜ እንዲደረግ ማድረግ፡፡ሁለተኛ  ደግሞ ሰርጋቸው ተደግሶ ባል እና ሚስት ተብለው አንድ ቤት ተጠቃለው እስኪገቡ ድረስ ይሄንን ፀጋ ልጁ እንደሆነች የሚገልፀውን ደብዳቤ እንዳያገኘው ማድረግ፡፡
እነዚህን ውሳኔዎች ከወሰነች በኃላ ነው የተወሰነ መረጋጋት ስለተሰማት እንቅልፍ የወሰዳት፡፡

ተፈፀመ

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
2