#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሶስት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
==================
ሰሎሜ አላዛር ሱቅ መስራት ከጀመረች ከከስድስት ወር በኃላ
እለቱ ሰኞ ነው፡፡የሳምንቱ መጀመሪያ፡፡አላዛር ድንገት ተከሰተና ሱቁን ዘግተው እንዲወጡ አደረገ፡፡ቀጥታ ወደ መዝናኛ ቦታ ወስዳት፡፡ሲዝናኑ አመሹና አረፍ ብለው እየተጫወቱ ሳለ፡፡
‹‹አንድ ሰዓት ሆነ እኮ ወደቤት አንሄድም እንዴ?፡፡››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹ወደቤት ስትይ?››
‹‹እንዴ ምኑ ነው ያልገባህ…?ወደየቤታችን ነዋ!!››
‹‹ቤት እንደገዛው ነግሬሻለሁ አይደል?››አላት
‹‹አዎ..በጣም ደስ ብሎኛል..በአጭር ጊዜ ስኬታማ እየሆንክ ነው..ጠንካራ ሰራተኛ ስለሆንክ ይገባሀል፡፡››
‹‹አይ ጠንካራ ሰራተኛ ስለሆንኩ ብቻ አይደለም የተሳካልኝ..እድለኛም ጭምር ስለሆንኩ ነው፡፡አያቴ ያወረሰቺኝ ገንዘብ …ቀላል አልጠቀመኝም..ይሄንን የኮንስትራክሽን ስራ ከጀመርኩ በኃላ ደግሞ አሪፍ የተባሉ ሶስት ፕሮጀክቶችን አገኘሁ…ረጅም አመት በስራው የቆዩ ኮንትራክተሮች እንኳን ይሄንን ያህል ስራ በቀላሉ አያገኙም፡፡››
‹‹ቢሆንም ያገኙትን እድልም በስርአት መጠቀምና ውጤታማ መሆንም እኮ ትልቅ የጥንካሬ ምልክት ነው፡፡››
‹‹እዛ ላይ እንኳን ትክክል ነሽ…ያገኘሁትን እድል ላለማባከን የተቻለኝን ሁሉ ከማድረግ አልሰንፍም››አላት በእርግጠኝነት፡፡
‹‹አዎ…ታዲያ እቤቱን መች ነው የምታሳየን?››
‹‹አሁን ጥቂት የሚስተካከሉ ነገሮች ስላሉ እያሳደስኩት ነው…እንዳለቀ ወስጄ አሳይሻለሁ››ሲል ቃል ገባላት፡፡
‹‹እና ሲያልቅ ጎረቤታችንን ልናጣ ነዋ፡፡››አለችው
‹‹ማለት?››
‹‹ያው ኮንደሚኒዬሙን ለቀህ ..አዲሱ ቤትህ ስትገባ ጓረቤት መሆናችን ይቀራል ማለቴ ነው››
‹‹አይ ..እንደዛ እንኳን አላደርግም..እሺ ካልሺኝ አብረን እንገባበታለን…ካልሆነም እሱን አከራይቼ እዛው ጎረቤትሽ ሆኜ መኖሬን ቀጥላለሁ፡፡››ብሎ ያልጠበቀችውን ነገር ነገራት፡፡
‹‹አልገባኝም…እኔ ደግሞ ለምንድነው አብሬህ የምገባው?››
‹‹አንድ ወንድና ሴት አንድ የጋራ ቤት ውስጥ ለምንድነው አብረው የሚገቡት?››ሲል መልሶ ጠየቃት፡፡
‹‹ቆይ ቆይ…..እየጀነጀንከኝ ነው እንዴ?››
‹‹ከተሳካልኝ አዎ››
‹‹ይገርማል ከዚህ ሁሉ አመት መጓተት በኃላ ድንገት ምን ተፈጠረ?››
ወደልቡ በሌባ ጣቱ እየጠቆመ ‹‹ሁሌም ሀሳቡ እዚህ ውስጥ ነበር ..ልዩነቱ አሁን ከአንደበቴ ምውጣቱ ነው››አላት፡፡
‹‹ቀልድ ጨምርሀል…ባይሆን አንዷን ጥበስና ደግሼ ልዳርህ!››
‹‹አይ ይቅርብኝ ..እኔ አንቺን ማግባት ካልቻልኩ እስከወዲያኛው መመልኮስ ነው የምፈልገው፡፡››
በድንጋጤ አፏን በመክፈት አፍጥጣ አየችው›‹‹እየቀለድክብኝ ነው እንዴ?››
‹‹አረ የምሬን ነው››
‹‹እኔን ጓደኛህን ማግባት ትፈልጋለህ?››
‹‹አዎ በደንብ፡፡››
‹‹ለምን? ››
‹‹ስለማፈቅርሽ ነዋ!!››
‹‹ከመቼ ጀምሮ››
‹‹እኔ እንጃ …ነፍስ ካወቅኩበት ጊዜ ጀመሮ አንቺን እንደማፈቅቅር ነው የማውቀው››
‹‹ይሄኔ ነው መሸሽ….እና እስከዛሬ ለምን ሳትነግረኝ?››
‹‹ስለምፈራሽ..ዛሬ እራሱ እንዴት እንደነገርኩሽ አላውቅም…››
ዝም አለችው…ምን እንደምትለው ምንም ሀሳብ አልመጣላትም..አስባበት ስለማታውቅ በእሷ በኩል ለእሱ ተመሳሳይ ስሜት ይኑራት ወይስ አይኑራት ማወቅ አልቻለችም፡፡
‹‹በል… አሁን ተነስ እንሂድ፡፡››
‹‹እሺ›› ብሎ …ከተቀመጠበት ተነሳ ና ተከተላት፡፡
ለሶስት ወር ያህል በጉዳዩ ላይ መልሰው በማንሳት አልተነጋሩበትም ነበር…
ከሶስት ወር በኃላ ሱቅ ስራ ላይ እያለች ስምንት ሰዓት ላይ መጣና ‹‹ሱቁን እንዝጋውና ..የሆነ ቦታ እንሄዳለን››አላት፡፡
‹‹የት?››
‹‹ሰርፕራይዝ ነው፡፡››
ተስማማችና ሱቁን አብረው ዘጋግዘው በፒካፕ መኪናው ተያይዘው ሄዱ…ወደ ላፍቶ ነው የወሰዳት ፡፡አዲስ የገዛው አፓርታማ ቤት ውስጥ ነው ይዞት የገባው……ሙሉ ዕቃው የተሞላ እጅግ ውብ ቤት ነበር፡፡
‹‹ይሄ የእኔ ቤት ነው እንዳትለኝ?››አለችው በመደነቅ ፈዛ፡፡
‹‹አይ የእኔ አይደለም የእኛ ቤት ነው፡፡››
‹‹በጣም እኮ ነው የሚያምረው፡፡››
‹‹ስለወደድሽው ደስ ብሎኛል፡፡››
‹‹ትቀልዳለህ እንዴ ..?እንዴት ላልወደው እችላለሁ? ቤተ መንግስት እኮ ነው የሚመስለው፡፡››
‹‹እንግዲህ እንዳልሺው ቤተ መንግስት ከሆነ ንግስት ይፈልጋል ማለት ነው፡፡››
‹‹እሱን ጫወታ ለጊዜው ትተን ሁሉንም ክፍል እየዞርን እንየው፡፡››
‹‹ይቻላል››ብሎ እየመራ ወደፎቁ ይዞት ወጣ፡፡ንግግሩን ጠንከር ብላ ስላልተቃወመችው ደስ ብሎታል፡፡ፈፅሞ ጥያቄው እስከወዲያኛው ላለመቀበል ወስና ቢሆን ኖሮ ቁርጥ አድርጋ ምንም አንደበቷን ሳያደናቅፋት ‹‹አይሆንም ››ትለው ነበር፡፡አሁን ግን …ለጊዜው እንተወው ››ነው ያለችው፡፡
//
እቤቱን ወስዶ ካስጎበኛት ከ15 ቀን በኃላ ድንገት‹‹በሚቀጥለው ሳምንት እቴቴ ጋር ሽማግሌ ልልክ ነው››ብሎ አስደነገጣት፡፡
‹‹ምን?››
‹‹አዎ …ሽማግሎዎችን አነጋግሬ አዘጋጅቼዋለሁ..በኃላ አዲስ እንዳይሆንብሽ ብዬ ነው አሁን የነገርሽው፡፡››
‹‹ያምሀል እንዴ…?እኔ መች እሺ አልኩህና ነው ሽማግሌ የምትልከው?፡፡››
‹‹ችግር የለውም…ሽማግሌ እልካለሁ…የማትፈልጊ ከሆነ ከእናትሽ ተማክረሽ ለሽማግሌዎች አይ አልፈልገውም ማለት ትቺያለሽ፡፡››
‹‹እንደዛ ብል እና በሽማጊሌዎች ፊት መዋረድ አይሆንብህም››
‹‹ግድ የለኝም….ዋናው አንቺን ለማግኘት ከልቤ መሞከሬ ነው፡፡››
‹‹ከዛ በኃላ ግን እዚህ መስራት አልችልም…››
‹‹እ ..እሱን በተመለከት በውሳኔሽ ተፅእኖ እንዳያሳድርብስሽ ስለፈለኩ ቅድመ ዝግጅት አድርጌለሁ፡፡››
‹‹የምን ቅድመ ዝግጅት?››
ፊት ለፊቱ ያለውን አጀንዳ አንሳና…‹‹ይሄንን ዝርዘር ተመልከችው..እዚህ ሱቅ ውስጥ ያለው እቃ ነው፡፡ይሄ ደግሞ ውል ነው..ይሄንን ሱቅ ከአሁን ወዲያ አልፈልገውም….ሁሉንም ዕቃ ትረከቢኝና ቀስ እያልሽ በሁለት አመት ውስጥ ትከፍይኛለሽ…ይሄ ማለት ይሄንን ውል ከፈረምሽ በኃለ የእኔ ሰራተኛ አይደለሽም ማለት ነው፡፡የራስሽን ንግድ ፍቃድ አውጥተሸ በራስሽ መስራት ትቀጥያለሽ ማለት ነው፡፡እናም ያ ማለት እንደከዚህ ቀደሙ በፈለኩ ጊዜ ወደሱቅሽ ዘው ብሎ መምጣትና ወደውስጥ ዘልቆ መግባት አልችልም ማለት ነው….እና ሽማግሌዎች ሲመጡ አሺ አገባዋለሁ ብትይም አላገባውም ብለሽ ብትነግሪያቸውም፤ከዚህ ሱቅና ከስራሽ ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም፡፡በይ ቸው››ብሏት ጥሎት ወጥቶ ሄደ፡፡
እንዳለው በሳምንቱ ሽማግሌ ላከ ….በሚቀጥለው እሁድ ተመልሰው እንዲመጡና መልሳቸውን የዛን ጊዜ እንደሚያገኙ ተነገራቸው፡፡የሰሎሜ እናት እቴቴ አንድ ብቸኛ ልጇን አስቀምጣ ጠየቀቻት፡፡
‹‹ልጄ ለመሆኑ ከአላዛር ጋ መቼ ነው የጀመራችሁት?››
‹‹ምንድነው የጀመርነው?››
‹‹ሽማጊሌ ልኮ እያየሽ ምን ትይኛለሽ እንዴ?››
‹‹አይ እቴቴ..እንደሚወደኝ ነገረኝ እንጂ ምንም የጀመርነው ነገር የለም …መልስ እንኳን አልሰጠሁትም፡፡››
‹‹ለምን?››
‹‹እኔ እንጃ እያሰብኩበት ነበር፡፡››
‹‹ምንድነው የምታስቢው…አትወጂውም?››
‹‹እኔ እንጃ… የምወደው ይመስለኛል፡፡››
‹‹አዎ ..እኔም ምትወጂው ይመስለኛል፡፡››
ሰሎሜ በእናቷ ንግግር ተገርማ‹‹እንዴት የምወደው ሊመስልሽ ቻለ?››ስትል ጠየቀቻት፡፡
‹‹ባትወጂውና ባትፈልጊው ኖሮ ወዲያውኑ ነበር አልፈልግም ብለሽ መልስ ምትሰጪው….እንደሚወድሽ ከነገረሽ ቀን አንስቶ እስከዛሬ ጉዳዩን እያብላላሽውና እያሰብሽበት ከሆነ ሌላ ምንም ትርጉም ልሰጠው አልችልም፡፡››

👍65❤14😁8
#አላገባህም
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሶስት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
////
ሚካኤል ከወህኒ ቤት እንደመጣ ቀጥታ ወደሰፈር ነው ያመራው፡፡ወደቤት ሲገባ አዲስ አለም ከልጇ ጋር እየተዳረቀች ሳሎን ውስጥ ቢያገኛትም ማንኛቸውንም ምንም ሳያናግር ቀጥታ ወደመኝታ ቤት ነበር የተንደረደረው፡፡
‹‹ሚኪ…ምን ሆነሀል.?.ዛሬ ደግሞ ሰላምታ የለም እንዴ?››
‹‹መጣሁ..››ብሎ ብቻ ወደመኝታ ቤት ገባ…አባቱ የነገሩትን ፎቶ ከግድግዳ ላይ አነሳ ..ከግድግዳው ጋር ተመሳስሎ የተሰራ ነው…በቀላሉ በእጅ የሚፈረከስ አይነት አይደለም…ከእንደገና ተነደርድሮ ወጣና በጓሮ በኩል ወደ ገራጅ በመሄድ መዶሻ እና መሮ ይዞ መጣ….‹‹አዲስ አለም ቅዱስን ከወለሉ ላይ አንስታ አቀፈችውና ወደመኝታ ቤቱ ተንቀሳቀሰች…እሷ ከመድረሷ በፊት ሚካኤል ወደውስጥ ገብቶ ከውስጥ ዘጋባት
‹‹እንዴ ሚኪ….ምን እየሆንክ ነው…?ለምንድነው የምትዘጋብን?››
‹‹አዲስ..እባክሽ ጥቂት ደቂቃዎችን ስጪኝ……››ብሎ መሮውንና መዶሻውን በመጠቀም ግድግዳውን መቆርቆር ጀመረ…ግድግዳ ውስጥ የተቀመጠውን የአባቱን ሚስጥራዊ እቃ ለማግኘት 3 ደቃቃ ያህል ፈጀበት…በላስቲክ በስነሰርአት የተጠቀለለ ነው፡፡አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠና የላስቲኩን እሽግ ፈቶ አልጋው ላይ ዘረገፈው፡፡….አምስት የሚሆኑ ፎቶዎች አንድ ሜሞሪ ካርድ ..አንድ ደብዳቤ ነው፡፡፡
መጀመሪያ ፎቶዎቹን አነሳና ተራ በተራ መመልከት ጀመረ…የመጀመሪያው ፎቶ ላይ አናትዬው የሆነ ሰው ክንድ ላይ ተደግፋ በፈገግታ ስትፍለቀለቅ ይታያል..ጭንቅላቱን የሆነ መርፌ ነገር ጠቅ አደረገው….ይሄ ሰው በህይወት ዘመኑ አይቶት አያውቅም…የእናቱን ዘመዶች ሁሉንም ያውቃል…ታዲያ ይሄ ማን ነው?፡፡ሁለተኛውን ፎቶ ገለጠና ተመለከተ…እናትዬው እነሱን ከመውለዷ በፊት ገና ጨቅላ ወጣት ሆና የተነሳቸው ፎቶ ነው..ግን አሁንም ያው ሰው አንገቷ ላይ ተጠምጥሞ በፍቅር ጉንጯን ሲስማት ይታያል…ፎቶውን ገለበጠው…ልቅም ባለ የእጅ ፅሁፍ በአንድ መስመር የተፃፈ ፅሁፍ አለ ‹‹ንጥፍ ወርቅ ፍቅሬ በጣም አፈቅርሻለው….ያንቺው ለሚ በቀለ፡፡››ይላል፡፡
ሁሉንም ፎቶዎች በየተራ እየገለባበጠ ተመለከተው…ተመሳሳይ የሁለቱ ፎቶ ነው…ሲላፉ ሲሳሳሙ….ሲጎራረሱ የተነሱት ፎቶ ነው፡፡
ቤታቸው የወላጆቻቸውን ትዝታ የሚዘክሩ ሁለት ግዙፍ የፎቶ አልበሞች እዳሉ ያውቃል….እናትና እህቱ በአሰቃቂ ሁኔታ ከሞቱ በኃላ በጣም ሲከፋውና ትዝ ሲሉት ለብቻው ክፍል ዘግቶ ተደብቆ ይመለከት ነበር፡፡እና እዛ አልበም ውሰጥ ዘጠና ፐርሰንት ፎቶ የእሱና የእህትና ወንድሙ ፎቶዎች ፤የበዓል ዝግጅት ፤ የህፃናቱ የልደት በዓል ማስታወሻ ናቸው የሞሉት..እናትና አባቱ በልጆቹ የደስታ ድባብ ውስጥ እንደድምቀት እዚህም እዛም ጣል ተደርገው የተነሱት ነው እንጂ እንዲህ እናቱ ከሌላው ሰውዬ ጋር እንዳደረገችው አይነት አማላይ ፎቶዎች ተነስተው አላየም፡፡
ፎቶውን አስቀመጠና ወረቀቱን አንስቶ አነበበው…
ይድረስ ለምወድሽ ፍቅሬ ንጥፍ ወርቅ …
ይህንን ደብዳቤ ስፅፍልሽ ከአይኖቼ እንባ ሳይሆን ደም እያፈሰስኩ ነው፡፡ ታውቂያለሽ እኔ ከኤለመንተሪ ጀምሮ በጣም ነው የማፈቅርሽ..አንቺም እንደምታፈቅሪኝ አውቃለው፡፡ብዙ አቅድና ብዙ ፕሮግራም ነበረን፡፡በቅርብም ለመጋባት ተነጋግረንና ተማምለን ነበር፡፡አሁን ግን ያንን ቃሌን ማክበር አልችልም፡፡አባዬ ምን ያህል ኃይለኛ እና ጥብቅ ሰው እንደሆነ ታውቂያለሽ ..አሁን አሜሪካ ካለው ወንድሙ ጋር ተነጋግሮ አሜሪካ እንድሄድ ወስኖ ሁሉም ፕሮሰሶች ጨርሶ ሊልከኛ ነው…ማለቴ… አሁን ይሄ ደብዳቤ ሲደርስሽ ምን አልባት እኔ በርሬም ሊሆን ይችላል፡፡
ይቅር በይኛ…..ያንቺው ለሚ በቀለ፡፡ይላል
እዛ ደብዳቤ ላይ ብዙ የተንጠባጠቡ የእንባ ጠብታዎች ይታያሉ፡፡ሚካኤል ያየውም ሆነ ያነበበው ነገር ምንም እየገባው አይደለም..ከውጭ ደግሞ አዲስአለም የመኝታ ቤቱን በራፍ እየቆረቆረች እየረበሸችው ነው፡፡ከተቀመጠበት ተነሳና ሄዶ በራፉን ከፈተ፡፡ በራፉ ላይ ልጇን አቅፋ ተገተትራ በድንጋጤ በድን የሆነችውን አዲስ አለም ላይ አፈጠጠባት፡፡
‹‹አዲስ ምንድነው?››
‹‹እንዴት መኝታ ቤቱን በላይህ ላይ ዘግተህ ምን እያደረክ ነው?››በስጋትና በፍራቻ ተወጥራ ጠየቀችው፡፡
ዠ
‹‹ኡፍ …ስራ ይዣለሁ ስልሽ አትሰሚም…..ባክሽ አትረብሺኝ››በማለት አንቧረቀና መልሶ ዘጋባት፡፡ከዛ ወደአልጋው ተመለሰ፡፡አዲስአለም በመጀመሪያ ከደነገጠችውን በላይ ደነገጠች…ሚካኤል ምንም ባልገባት ነገር እንዲህ አመናጭቋት አያውቅም፡፡
ወደሳሎን ተመለሰችና ፀአዳ ጋር ደወለችላት፡፡
ስታወራ ድምፃ ይንቀጠቀጣል‹‹ሄሎ ፀዲ..አሁኑኑ ወደቤት ነይ››
‹‹እንዴ ምን ሆንሽ..?
ቅዱስ አመመው እንዴ?››
‹‹አይደለም..አባትዬው ነው፡፡››
ፀአዳ በጣም ደነገጠች‹‹እንዴ ሚኪ ምን ሆነ?››
‹‹እኔ እንጃለት… ቅድም አንቺ ጋር የመጣሁ ጊዜ አባቱን ለመጠየቅ ወህኒ ቤት ሄዶ ነበር…ከዛ ሲመለስ እንደእብድ አድርጎት መኝታ ቤቱ ገባ..ከዛ ወጣና መዶሻና መሮ ይዞ ገብቶ በራፉን ከውስጥ በመዝጋት ግድግዳውን ሲነድለው ነበር…አንኳኩቼ ምን እንደሆነ ስጠይቀው አጓርቶብኝ መልሶ ዘጋው…እህቴ ቶሎ ድረሺኝ…የቀትር ጂኒ ሳያጠናግረው አይቀርም››
‹‹ስለአባቱ መጥፎ ነገር ሰምቶ ይሆን እንዴ?››
‹‹መሰለኝ….ወይ በፈጣሪ ምን አልባት እዛ ሲደርሰ ገድለዋቸው እንዳይሆን ነው የምፈራው..እንደዛ ቢሆንስ በራፍ አስዘግቶ ግድግዳ ያስንዳል እንዴ…?››
‹‹በቃ መጣሁ ..እስከዛው ተረጋጊ››አለቻትና ስልኩን ከመዝጋቷ በፊት ቦርሳውን አንጠለጠለችና መንገድ ጀመረች፡፡
ሚካኤል ሜሞሪውን አነሳና ስልኩ ውስጥ ከተተው፡፡ሁለት ፎልደሮች አሉት፡፡አንደኛውን ከፈተ ….በምስሉ በቅድሚያ ምትታየው እናቱ ነች፡፡አዎ ቡቲክ ቤታቸው ውስጥ ሆና ልብሶችን ሰታስተካከል ይታያል…ወዲያው አንድ በእሷ እድሜ ያለ ሰው መጣ …የሰውዬው ጀርባው ነው ሚታዬው እናትዬው ግን በሰውዬው መምጣት ስትደነግጥ ይታያል፡፡
‹‹ለሚ እንዴት መጣህ?››አገላብጣ እየሰማችው ትጠይቀዋለች፡፡
‹‹እንዴት መጣህ ነው እንኳን ደህና መጣህ ነው የሚባለው?እዚህ ስብሰባ ነበረን …ሳላይሽ ተመልሼ መሄድ አልቻልኩም›››
‹‹እንዴ ከሶስት ቀን በኃላ ቀጠሮ ነበረን እኮ…››
‹‹እሱም እንዳለ ነው…ግን እኔ እኮ በየቀኑ ላገኝሽ ነው የምፈልገው…እንደውም ሙሉ በሙሉ የእኔ እንድትሆኚ ነው የምፈልገው፡፡››
‹‹እሱንማ አስረግዘኘኝ ጥለኸኝ አሜሪካ ከመሄድህ በፊት ማሰብ ነበረብህ፡፡››
‹‹ይሄንን እኮ ብዙ ጊዜ ተነጋግረንበት ሁኔታውን አስረድቼሽ ይቅር ብለሽኛል..አይደል እንዴ የእኔ ፍቅር?››
‹‹አዎ ግን …ይቅር አልኩህ ማለት ለአመታት የገነባሁት ትዳሬንና ልጆቼን በትኜ ወደአንተ ለመመለስ እፈልጋለው ማለት አይደለም፡፡››
‹‹ልጆችሽን በትኚ አልልኩም እኮ ….ባልሽን ፍቺና ልጆቹን ይዘሽ ነይ ነው፡፡›››
‹‹አይ ያንን ሳደርግ ቅጣው እጁን አጣጥፎ የሚቀመጥ ይመስልሀል….?እሱ ምንም እንከን የማይወጣለት ድንቅ አባትና ምርጥ ባል ነው፡፡ልጆቹን እንዴት እንደሚወድ እና እንዴት እንደሚንከባከብ ብታውቅ እንዲህ ለማለት አትደፍርም..በተለይ ትርሲትን በልዩ ሁኔታ ነው የሚወዳት…ሲጠራት እኮ እናቴ ነው የሚላት…እሷስ ብትል..?››
‹‹ግን እውነተኛ ልጁ አይደለችም…ትርሲት የእኔ ልጅ ነች፡፡››
ሚካኤል በሚሰማው ነገር ሆዱ ሲገለባበጥ ይታወቀዋል…አረ እንደውም ሊያስታውከው እየተናነቀው ነው፡፡
‹‹አረ ድምጽህን ቀንስ..ድንገት ሰው ቢሰማህስ?››

👍63❤12
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ…
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሶስት
፡
፡
#ድርሰተ_በዘሪሁን_ገመቹ
___
//
ዛሬ ጠዋት ሎዛን ከስራ መባረሯን ለመናገር ፀጋን ይዛ ወደ ፋውንዴሽን ቢሮ ሄዳ ነበር፡፡
የሎዛ ክህደት አሁንም እያመማት ነው፣እሷን በመገላገሏ ደስ ብትሰኝም ከእስከአሁኑ በባሰ ሁኔታ፣ የስራ ጫናው ሊጠነክርባት እንደሚችል ተሰምቷታል።እሷ የምትፈልገውን ስራ በእቅዳቸው መሰረት እንዲከወንላት ከፈለገች ሁለት ተጨማሪ ጥንድ እጆች፣ አይኖች እና ጆሮዎች ያስፈልጋታል።
ራሄል በቁጭት እና በንዴት ቢሮ ቁጭ ብላ ከሮቤል ጋር እያወራች ነው፡፡
‹‹ ሮቤል በሆነው ነገር በጣም አዝኛለው…የማፍያ ፀባይ ካላቸው የበጎ አድራጎት ድርጅተች ጋር ተመሳጥራ በእኔ ድርጅት ስም ልትዘረፍ ስትል ነው የያዝኳት››
‹‹አዎ..ከዚህ በፊት የምታደርጋቸው አንዳንድ ሁኔተዎች ሳላላማሩኝ ጥንቀቄ እንድታደርጊ ጠቆም አድርጌሽ ነበረ….ይመስለኛል እንደቁምነገር ወስደሸሽ አላዳመጥሽኝም››
‹‹አዎ ትክክል ነህ…በጣም እኮ ነበር የማምናት››
‹‹ለማንኛውም ከፍተኛ ኪሳራ ሳታስከትል በጊዜ ስለደረሽባት ጥሩ ነገር ነው….ለወደፊቱ ትምህርት ይሆንሻል››አላት፡፡
‹‹ አዎ ትክክል ነህ…ለማንኛውም አሁን ሌላ ጎበዝ እና ታማኝ ረዳት ማግኘት አለብኝ ፡፡››
‹‹ያንን ስራ በንዑስ ኮንትራት ማሰራት የሚሻል ይመስለኛል››የሚል ምክር ሰጣት፡፡
‹‹አይ ይህ በራሴ ማድረግ አለብኝ።ብቻ በፋውንዴሽኑ ላይ ሌላ ጉዳት እንዳላደረሰች ተስፋ አደርጋለሁ።››
የቢሮውን ስራ ለሮቤል በአደራ ሰጥታ ፀጋን ይዛ ከቢሮ ወጣችና ወደሆስፒታል ነው የሄደችው፡፡ፀጋ ታማ ሳይሆን መደበኛ ክትትል የምታደርግባትን ቀን ስለሆነ ነበር ወደ ሆስፒታል የወሰደቻት..ከዛ በኋላ ነው ወደቤታቸው የተመለሱት፡፡
ራሄል በምትወደው ሶፋ ላይ ተቀምጣ ትራስ በመደግፋ ወረቀቶች እያገላበጠች ሳለ ስልኳ ጠራ..አነሳችና አየችው፡፡አባቷ ናቸው፡፡በጭኗ ላይ ያሉትን ወረቀቶች ማገለባበጧን ሳታቆም አባቷን ማውራት ጀመረች፡፡
‹‹አባዬ እንዴት ነህ..እማዬስ?››
‹‹እናትሽ በጣም ቆራጥ ነች እና ዶክተሮቹ በጤናዋ መሻሻል በጣም ተደስተዋል.››አላት አባቷ፡፡
‹‹ደስ ብሎኛል አባዬ..እኛጋም ነገሮች ጥሩ ናቸው….ስራዬንም ወደቤት አዘዋውሬ አንተ ቢሮ ስሰራ ነው ምውለው››
‹‹አንዳንድ ስራዎችሽን አሁን ለቀጠርሻቸው ረዳቶችሽ መስጠት አልቻልሽም?››ሲሉ ጠየቋት፡፡
ስለ ሎዛ እስካሁን አልነገረቻቸውም። አሁን በትከሻቸው ላይ ምንም ተጨማሪ ሸክም ልትጭንባቸው አልፈለገችም።
‹‹አባዬ ስራውን ለሌሎች ለማከፋል እየሞከርኩ ነው..ቢሆንም ታውቃለህ አመታዊው የገቢ ማሰባሰቢያ በአላችን እየደረሰ ነው..በዚህ ጊዜ ስራ ይበዛብናል›› አለች.፡፡
‹‹በዛ ላይ እህትሽን መንከባከቡ በጣም ፈታኝ ስራ ነው››
‹‹ኖ…ኖ አባዬ….አሁን ከእህቴ ጋር በጣም እየተግባባን ስለሆነ ነገሮች የምታስበውን ያህል ከባድ አይደሉም…እናንተ ምንም አታስቡ››
‹‹ይሁን ልጄ…በጣም ነው የምኮራብሽ››
‹‹አመሰግናለው አባዬ…ለመሆኑ ዶክተሮቹ እናቴ ከሆስፒታል መች ትወጣለች ብለው ያስባሉ?››
‹‹ግምቱን አሻሽለዋል፤ከአሁን በኋላ ቢያንስ ሁለት ሳምንት ሳያቆዬት አይቀርም፡፡ ከፀጋ ጋር መነጋገር እችል ይሆን?››
‹‹ይቅርታ አባዬ አሁን ተኝታለች ››
.የእለቱ ተግባራቸውን ሁሉ አከናውነው ወደ ቤት እስኪመጡ ድረስ የፀጋ ባህሪ ከንጭንጭ የራቀና በፈገግታ የተሞላ ሆኖ በመታየቱ አመስጋኝ ነበረች። ግን ወደቤት ከተመለሱ በኃላ መነጫነጭ ጀመረች ከዛ ሰውነቷን አጥባ እራቷን ካበላቻት በኋላ አልጋ ላይ አስቀመጠቻት… ከዛ ትንሿ ልጅ በሰከንዶች ውስጥ ተኛች። ይህም ራሄል ምስኪኗን ልጅ ከወዲህ ወዲያ እያሽከረከረች ስታንገላታት ስለዋለች የጥፋተኝነት ስሜት እንዲሰማት አድርጎታል።..እና አሁን ልትቀሰቅሳትና የበለጠ ልታበሳጫት አልፈለገችም፡፡
አባቷን ለተጨማሪ ጥቂት ደቂቃዎች አወራቻቸው፣ አባቷን ስትናገር እንኳን ስራዋ እያንገበገበባት ነበር ..ትኩረቷን የሚከፋፍልባት ምንም ነገር ባይኖር ደስተኛ ነች ።ወዲያው ሌላ ስልክ ተደወለላት.. ቃተተች እና ማን እንደሚደውል ሳታረጋግጥ አነሳችው..ቁጣ በሚመስል የድምፅ ቃና ‹‹ራሄል ነኝ.››አለች
‹‹ሄይ ራሄል… እንዴት ነሽ?››ዔሊያስ ነበር…ፍስስ የሚለውን ድምፁን ስትሰማ ብስጭቷን አቃለላት። ራሄል ዛሬ ወደቤት ከተመለሰች በኋላ ዔሊን ለማየት ፈልጋ ከአሁን አሁን በራፉን ያንኳኳል እያለች በናፍቆት ስትጠብቅነበር፡፡
‹‹ስልክሽ ለረጅም ጊዜ ተይዞ ነበር››
‹‹ከአባቴ ጋር እያወራው ነበር ››አለችው።
‹‹ነገሮች እዛ እንዴት እየሄዱ ነው…?ሄጄ ካየዋቸው እኮ ሳምንት ሊያልፈኝ ነው››
‹‹እናቴ ጥሩ እያገገመች ነው። ግን እስከሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ወደ ቤት እንደማትመጣ ነው የሰማሁት››
‹‹አይዞሽ…ዋናው የመዳን ሂደታችው እድገት እያሳየ መሄዱ ነው››
‹‹እሱስ እውነትህን ነው….ታዲያ አሁን ምን እያደረክ ነው? ››ብላ ጠየቀችው
‹‹ምንም…ሶፋዬ ላይ ጋደም ብዬ ስለአንቺና ስለፀጋ እያሰብኩ ነበር››አላት፡፡
ደስ አላት‹‹እየፎገርክ ነው?››
‹‹አረ እውነቴን ነው…መቼስ ማል አትይኝም››
‹‹መምጣት ትፈልጋለህ?›› ቃላቶቹ ድንገት ነው ከአንደበቷ ያመለጧት….የአእምሯዋን ሳይሆን የልቧን ምኞት ነው አንደበቷ ያሳበቀባት….
‹‹ከስራ ከወጣው በኋላ ከሶስት ጊዜ በላይ ልመጣ ተነስቼ ነበር ከዛ ‹‹አረ ኤልያስ እግርና አብዝተሀል…..ሰዎቹን እያጨናነቅካቸው እንዳይሆን ››ብዬ ራሴን በመገሰፅ ያቆምኩት፡፡
‹‹እባክህ ና:: እዚያ ባገኝህ ደስ ኀይለኛል።›› ድጋሚ አመለጣት…በራሷ ሽምቅቅ አለች፡፡
‹‹እንዲህ ከሆነ››አለ ዔሊ በፈገግታ ‹‹ መምጣት የምችል ይመስለኛል….››
‹‹ቆንጆ እራት ሰርቼ ጠብቅሀለው››
‹‹በጣም ደስ የሚል ነገር ነው..በዛውም የሞያ ብቃትሽ ይፈተሻል››
‹‹አንተ የእማዬ ልጅ እኮ ነኝ..በሞያዬማ ምንም ጥርጣሬ ሊገባህ አይገባም››
‹‹እኮ ላየው አይደል?››
‹‹አይ ዛሬ እንኳን አታየውም…ይሄንን ዙሪያዬን የተቆለለ ወረቀት ባለበት ጥዬ ኪችን አልገባም››
‹‹እና እራቱ የለም እያልሺኝ ነው?››
‹‹እሱማ አለ ..ግን አለም ነች የምትሰራው››
‹‹ይሁን እሺ…..እስክንገናኝ ቻው››
‹‹ቻው››ስልኩን ዘጋች፡፡እንደገና ዘና ያለ ስሜት ተሰማት ፡፡
አለምን ተጣራችን እንግዳ ስለሚመጣ ቆንጆ እራት እንድታዘጋጅ አዘዘቻት እና ትኩረት ሰበሰበች እና ወደ ስራዋ ተመለሰች፡፡
///
ረዳቷ ሮቤል ወደእነ ራሄል ቤት መጥቶ አባቷ ቢሮ ውስጥ ተቀምጠው ስለፋውንዴሽኑ አመታዊ የገቢ ማሰባሰ
ቢያ ዝግጅት እየተወያዩ ነው፡፡
‹‹የትኛውን ስራ በማን እንደማሰራ እና …የተወሰኑ ስራዎችን ውክልና መስጠት ከየት እንደምጀምር አላውቅም።››ራሄል በንዴት ተነፈሰች።
‹‹ እኔም ስለእሱ እያሰብኩነበር…ሁሉንምነገር በራስሽ ለመስራት በመሞከር በራስሽ ላይ አላስፈላጊ ጫና ማሳደር የለብሽም…እኔ አለሁ››
‹‹እኔ ካንተ የበለጠ ጊዜ አለኝ ብዬ አስባለሁ… ።››
ሮቤል ንግግሯ አልተዋጠለትም፡፡ቢሆንም ብዕሩን በፋይሉ ላይ ሰክቶ እያዳመጣት ነው፡፡በሁሉም ነገር ትዕግስት እያጣ እንደመጣ በሁኔታው መታዘብ ይቻላል፡፡
‹‹ራሄል እህትሽን በመንከባከብ እንደተጠመድሽ አውቃለሁ…የደከመሽ ትመስላያለሽ ።አሁን የሎዛን ስራ የሚሰራ ሌላ ሰው መፈለግ አለብሽ እና ጊዜ እንደሌለሽ አውቃለሁ። ››በማለት የሚያስበውን በግልፅ ነገራት፡፡

❤57👍1🔥1😁1
#ቋጠሮ_ሲፈታ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሶስት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
////
አለም መተኛት አቅቷት እየተገለበጠች ባለችበት ጊዜ ነበር ስልኩ የጮኸው፡፡ሰዓቱ እኩለ ለሊት በመጠጋቱ የተነሳ ጥሪው በጣም ነበር ያስደነገጣት ። የራስጌ መብራቱን በማብራት የስልኩን እጄታ አነሳችና ጆረዋ ላይ ለጥፋ ጎላ ባለ ድምፅ "ጤና ይስጥልኝ" አለች፡፡ቀደም ብሎ ስታለቅስ ስለቆየች ድምጿ የሻከረ ነበር
"ሰላም ››መለሰላት፡፡
"አወቅሽኝ ወ.ሪት አለም "
ልቧ በደስታ ዘለለ፣"አንተ እንደገና? በዚህ ውድቅት ለሊት ከእንቅልፍ ያስነሳኸኝ ደህና ነገር ልትነግረኝ እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ" አለችው።እምቢተኛ ምስክሮች ብዙ ጊዜ የሚናገሩትን ነገር አስፈላጊነት ሲጠቀስላቸው ለመናገር እንደሚበረታቱ ከልምድ ታዝባለች፡፡
"ከኔ ጋር ድብብቆሽ አትጫወቺ …. ማወቅ የምትፈልጊውን በጠቅላላ አውቃለሁ። "
"ለምሳሌ ምን?"
"ለምሳሌ እናትሽን ማን እንደገደላት››
አለም አተነፋፈስዋን በመቆጣጠር ላይ ትኩረት አደረገች።
" ይመስለኛል ዜናው አስደምሞሻል››
"ታዲያ ንገረኝ ማን ነበር?"
"እመቤት ደደብ እመስልሻለሁ እንዴ? ኩማንደሩ ቀደም ሲል ስልክሽን አለማስጠለፉን በምን አውቃለው ?"
"ይመስለኛል….በጣም ብዙ ፊልሞችን አይተሃል?››
‹‹ተረቡን አቁሚና ይልቅ በፅሞና አድምጪኝ ….ነገ ማታ አንድ ሰዓት ሸዋበር የሚገኘው ደንበል ሆቴል እንገናኝ" በማለት ሰዓቱንና ቦታውን ነገራት፡፡
"እንዴት ላውቅህ እችላለሁ?"
"እኔ አውቅሻለሁ"
ሌላ ነገር ከመናገሯ በፊት ስልኩን ዘጋው። አለም በአልጋው ጠርዝ ላይ ለጥቂት ጊዜ ተቀምጣ ጨለማውን እያየች ደርቃ ቀረች። ልትጎዳ እንደምትችል የነገራትን የኩማንደሩ ማስጠንቀቂያ አስታወሰች። የእርሷ ምናባዊ አእምሮ በሴት ላይ ብቻ ሊደርስ የሚችለውን አሰቃቂ ነገር ሁሉ አስተናገደ። በተኛችበት ሆና በላብ ተጠምቀው ነበር።
///
የከተማው የፖሊስ አዛዥ እንፋሎት የሚትገለግበትን ቡናውን አንስቶ ጠጣ። ምላሱን አቃጠለው። ግን ግድ አልነበረውም። በጣም በከፋ መንገድ የካፌይን ማነቃቂያ ያስፈልገዋል
‹‹ስለማን ነው የምናወራው?›› ሲል በግል ቢሮው ደጃፍ ላይ ቆሞ የነበረውን ምክትሉን ጠየቀ ..
" ስለአቃቢ ህግ ፅ/ቤት ነው››
"ስለ ወ.ሪት አለም እያወራህ ነው ?" ምክትሉ መለሰ " አዎ ጌታዬ ስለእሷ ነው።" "እሺ ምን አዲስ ነገር አለ?"
" የእናቷን የሬሳ ምርመራ መዝገብ አስወጥታ ዠለመመርመር ወደ ተክለሀይማኖት ቤ/ክርስቲያን ሄዳለች ››
"ምን?"
"አዎ ጌታዬ እንዲከታተሏት የመደብናቸው ፖሊሶች ናቸው ደውለው የነገሩኝ፡፡››
‹‹በል አሁኑኑ ደውልላቸውና ወደእነሱ እየመጣሁ እንደሆነ ንገራቸው››
ገመዶ ኮቱን ከተሰቀለበት አንስቶ ቢሮውን ለቆ ወጣ…፡፡ ትምህርት ቤቶችን እና አብዛኛዎቹን የንግድ ድርጅቶች እንዲዘጉ ያደረጋቸውን የፀጥታ ችግር ቢኖርም ግድ አል ነበረውም። ሰልፈኛውን እየሰነጠቀ እና ወንበር እያሳበረ ወደሆስፒታል ነዳው፡፡
"የት ነው ያለችው?" እንደደረሰ ኩማንደሩ ጮኸ፣..አንድ አነስተኛ ቢሮ መሰል ክፍል ውስጥ ቁጭ ብላ ከአስተዳዳሪው ጋር ስታወራ ተመለከታ…ወደእዛው ተንደርድሮ ሄደ፡፡
ምንም ፍቃድ ሳይጠይቅ ሰተት ብሎ ገባና " ምን እየሰራሽ ነው ?"አንቧረቀባት፡፡ "እንደምን አደርክ ኩማንደር"አለችው ለስለስ ብላ፡፡
"ጥያቄዬን መልሺልኝ?"
‹‹ምን እያደረኩ እንደሆነማ በደንብ ታውቃለህ?››
"በአንቺ ምክንያት ሴትዮዬ ስራዬን መስራት አልቻልኩም….ከተማዋ በበጥባጭ ጎረምሶች ተረብሻ ያንን ማረጋጋት ሲጠበቅብኝ እኔ አንቺን በየመቃብር ቤቱ እከታተልሻል። ለማንኛውም እንዴት እዚህ ደረስሽ?"
" እየነዳሁ።"
በንዴት በጠረጴዛው ላይ የተበተኑትን ፋይሎች አያመለከተ"ይህ ሁሉ ምንድን ነው?"ሲል ጠየቃት፡፡
" መዛግብት ነዋ…..እናቴ ስትቀበር ለአገልግሎት የተከፈሉ ካርኒዎች እና መሰል መረጃዎች ሊኖሩ ስለሚችሉ ያንን እያዩልኝ ነው፣ ፡፡
"አስገድደሽው ነው?::"
‹‹እኔ እንደዚህ ያለ ነገር አላደረኩም..እንዴት ነው ምታስበኝ…?ደፍሬ አባቶቼን የማስገድድ ይመስልሀል?."
" ታዲያ የፍተሻ ማዘዣ ፍቃደሽን አልጠየቁሽም?"
ካህኑ‹‹ልጆቼ ይቅርታ እስኪ እናንተ አውሩ እኔ መጣሁ››ብለው ከመቀመጫቸው ተነሱና ክፍሉን ለቀውላቸው ወጡ … ገመዶ ወደሷ ቀረበና በንዴት ክንዷን ጨምድዷ ያዘ፡፡
‹‹ምን እያደረክ ነው?››
‹‹ቄሱን የሆነ ነገር ብዬ ከማስቀየሜ በፊት ቀጥ ብለሽ ቦታውን ለቀሽ ውጪ››
‹‹ለምንድነው እንደዛ የምታደርገው?››
‹‹ነገርኩሽ እኮ..አሁን ተከትለሺኝ ትሄጂያለሽ ወይስ…የማደርገውን ቆመሽ ትመለከቻለሽ?››
ትኩር ብላ አየችው … ፊቱ እንደ ተራራ ሰንሰለታማና ወጣ ገባ ነው፣በአጭሩ ቋጥኝ ይመስላል፣ ነገር ግን እስካሁን ካጋጠሟት በጣም ማራኪ ወንዶች ውስጥ አንዱ ነው።አብረው በሚሆኑበት ጊዜ ሁሉ፣ ስለ እሱ፣ ስለ ሰውነቱ ታስባለች፡፡ የእሷ ለእሱ ያላት መስህብ ሥነ ምግባር የጎደለው እና ከዛም አልፎ እንዝላልነት እንደሆነ ታውቃለች። መጀመሪያ የእናቷ ፍቅረኛ ነበረ።ያንን በደንብ ታውቃለች ..ሆኖም ብዙ ጊዜ እሱን ለመንካት ትፈልግ ነበር። ትናንት ማታ በምታለቅስበት ጊዜ እንዲያባብላት ትፈልግ ነበር። ወደመኝታ ቤቷ ተከትሏት እንዲገባም ፈልጋ ነበር…ደግነቱ እሱ በተሻለ ብቃት እራሱን የመቆጣጠር ችሎታ ነበረው እና ምንም ሳያደርግ ትቷት ሄደ።
‹‹የሰሎሜ ሬሳ እንደተቃጠለ ነግሬሻለሁ።››
"አንተ እና ዳኛው ጭንቅላታችሁን አንድ ላይ አድርጋችሁ እያሻጠራችሁ መሆኑን ማወቄ የተመቸኝ ይመስልሀል?።››
"ነገሮችን መገመት ያስደስትሻል?."
"ጁኒየር እናቴ ሬሳ መቃጠሏን ለምን አልነገረኝም?እንደተቀበረች ነበር የነገረኝ ››
‹‹እኔ እየዋሸሁሽ ይምስልሻል….?ለምን ብዬ?" " አስከሬኑ እንዳይወጣ ስለምትፈልግ ነዋ።"
"ሬሳው እንዳይወጣ ለምንድነው የምፈልገው? በእኔ ላይ ምን ለውጥ ያመጣል?"
ፍርጥም ብላ "የእድሜ ልክ እስራት" በማለት መለሰችለት፡፡ "የፎረንሲክ ሪፖርቱ አንተን ነፍሰ ገዳይ መሆንህን የሚያመለክት ፍንጭ ከሰጠን ወደወህኒ መወርወርህ የማይቀር ነው።››
" “አህ...” አለ..ደም ስሯቹ ሲግተረተር እየታዘበች ነው፡፡ "አንቺ ጠበቃ አይደለሽም, ጠንቋይ አዳኝ ነሽ."
"ወንጀል ባይኖር ኖሮ ያ እውነት ሊሆን ይችላል….ግን አንድ ሰው ወደዚያ በረት ውስጥ ገብቶ እናቴን ወግቶ ገድሏታል..እና እስከአሁን ለጥፋቱ የሚመጥን ቅጣት አላገኘም።››
"በእስክሪፕት ደረጃ ትክክል ነሽ" አለ እየተሳለቀ።
"ጋሽ ፍሰሀ ፣ ጁኒየር ወይስ እኔ የቀዶ ጥገና መሳሪያ ይዘን እናትሽን እንደወጋናት ነው ግምትሽ? ለምን በባዶ እጃችን አንገቷን አንቀን አንገድላትም??"
"ሁላችሁም ጎበዝ ስለሆናችሁ።ከመካከላችሁ ወንጀሉን የፈፀመው ሰው እንደዛ ያደረገው ወንጀሉን የአእምሮ ሚዛናዊ የተዛባ ሰው ያደረገው እንዲመስል ፈልጎ ነው።››
‹‹አመንሽም አላመንሽም …እኔ አላደረግኩም
"በብስጭት መለሰላት፡፡
"ታዲያ ማን እንዳደረገው ማወቅ አትፈልግም? ወይስ ነፍሰ ገዳዩ የምትወደው ሌላ ሰው እንዳይሆን ትፈራለህ ?"ስትል ሞጋች ጥያቄ ጠየቀችው፡፡
‹‹አይ ማወቅ አልፈልግም" ሲል በአጽንኦት መለሰላት፡፡
"እኔ ግን ገዳዩን እስካገኝ ድረስ ምርመራዬን አላቋርጥም..››
ሊመልስላት አፉን ሲከፍት አንድ ግራ እግራቸው ሸንከል የሚል አዛውንት አንድ ያረጀች መዝገብ ይዘው ወደውስጥ ሲገቡ ሲመለከት አፉን መልሶ ከደነ፡፡

❤43👍1