አትሮኖስ
279K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
457 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ


#ክፍል_አስራ_ሶስት


#ድርሰተ_በዘሪሁን_ገመቹ
___
//

ዛሬ ጠዋት ሎዛን  ከስራ መባረሯን ለመናገር ፀጋን ይዛ  ወደ ፋውንዴሽን ቢሮ ሄዳ ነበር፡፡
የሎዛ ክህደት አሁንም እያመማት ነው፣እሷን በመገላገሏ ደስ ብትሰኝም ከእስከአሁኑ  በባሰ ሁኔታ፣ የስራ ጫናው ሊጠነክርባት እንደሚችል ተሰምቷታል።እሷ የምትፈልገውን ስራ በእቅዳቸው መሰረት እንዲከወንላት ከፈለገች  ሁለት ተጨማሪ ጥንድ እጆች፣ አይኖች እና ጆሮዎች ያስፈልጋታል።

ራሄል በቁጭት እና በንዴት ቢሮ ቁጭ ብላ ከሮቤል ጋር እያወራች ነው፡፡

‹‹ ሮቤል በሆነው ነገር በጣም አዝኛለው…የማፍያ ፀባይ ካላቸው የበጎ አድራጎት ድርጅተች ጋር ተመሳጥራ በእኔ ድርጅት ስም ልትዘረፍ ስትል ነው የያዝኳት››

‹‹አዎ..ከዚህ በፊት የምታደርጋቸው አንዳንድ ሁኔተዎች ሳላላማሩኝ ጥንቀቄ እንድታደርጊ ጠቆም አድርጌሽ ነበረ….ይመስለኛል እንደቁምነገር ወስደሸሽ አላዳመጥሽኝም››

‹‹አዎ ትክክል ነህ…በጣም እኮ ነበር የማምናት››

‹‹ለማንኛውም ከፍተኛ ኪሳራ ሳታስከትል በጊዜ ስለደረሽባት ጥሩ ነገር ነው….ለወደፊቱ ትምህርት ይሆንሻል››አላት፡፡

‹‹ አዎ ትክክል ነህ…ለማንኛውም አሁን ሌላ ጎበዝ እና ታማኝ ረዳት ማግኘት አለብኝ ፡፡››

‹‹ያንን ስራ በንዑስ ኮንትራት  ማሰራት የሚሻል  ይመስለኛል››የሚል ምክር ሰጣት፡፡

‹‹አይ ይህ በራሴ ማድረግ አለብኝ።ብቻ በፋውንዴሽኑ ላይ ሌላ ጉዳት እንዳላደረሰች ተስፋ አደርጋለሁ።››

የቢሮውን ስራ ለሮቤል በአደራ ሰጥታ ፀጋን ይዛ ከቢሮ ወጣችና  ወደሆስፒታል ነው የሄደችው፡፡ፀጋ ታማ ሳይሆን መደበኛ ክትትል የምታደርግባትን ቀን ስለሆነ  ነበር ወደ ሆስፒታል የወሰደቻት..ከዛ በኋላ ነው ወደቤታቸው የተመለሱት፡፡

ራሄል በምትወደው ሶፋ ላይ ተቀምጣ  ትራስ በመደግፋ ወረቀቶች እያገላበጠች ሳለ ስልኳ ጠራ..አነሳችና አየችው፡፡አባቷ ናቸው፡፡በጭኗ ላይ ያሉትን ወረቀቶች ማገለባበጧን ሳታቆም  አባቷን ማውራት ጀመረች፡፡

‹‹አባዬ እንዴት ነህ..እማዬስ?››

‹‹እናትሽ በጣም ቆራጥ ነች እና ዶክተሮቹ በጤናዋ መሻሻል  በጣም ተደስተዋል.››አላት አባቷ፡፡

‹‹ደስ ብሎኛል አባዬ..እኛጋም ነገሮች ጥሩ ናቸው….ስራዬንም ወደቤት አዘዋውሬ አንተ ቢሮ ስሰራ ነው ምውለው››

‹‹አንዳንድ ስራዎችሽን አሁን ለቀጠርሻቸው ረዳቶችሽ መስጠት አልቻልሽም?››ሲሉ ጠየቋት፡፡
ስለ ሎዛ እስካሁን አልነገረቻቸውም። አሁን በትከሻቸው ላይ ምንም ተጨማሪ ሸክም ልትጭንባቸው አልፈለገችም።

‹‹አባዬ ስራውን ለሌሎች ለማከፋል እየሞከርኩ ነው..ቢሆንም ታውቃለህ አመታዊው የገቢ ማሰባሰቢያ በአላችን እየደረሰ ነው..በዚህ ጊዜ ስራ ይበዛብናል›› አለች.፡፡

‹‹በዛ ላይ እህትሽን መንከባከቡ በጣም ፈታኝ ስራ ነው››
‹‹ኖ…ኖ አባዬ….አሁን ከእህቴ ጋር በጣም እየተግባባን ስለሆነ ነገሮች የምታስበውን ያህል ከባድ አይደሉም…እናንተ ምንም አታስቡ››

‹‹ይሁን ልጄ…በጣም ነው የምኮራብሽ››

‹‹አመሰግናለው አባዬ…ለመሆኑ ዶክተሮቹ እናቴ ከሆስፒታል መች ትወጣለች ብለው ያስባሉ?››

‹‹ግምቱን አሻሽለዋል፤ከአሁን በኋላ ቢያንስ ሁለት ሳምንት ሳያቆዬት አይቀርም፡፡ ከፀጋ ጋር መነጋገር እችል ይሆን?››

‹‹ይቅርታ አባዬ አሁን ተኝታለች ››
.የእለቱ ተግባራቸውን ሁሉ አከናውነው  ወደ ቤት እስኪመጡ ድረስ የፀጋ ባህሪ  ከንጭንጭ የራቀና   በፈገግታ የተሞላ ሆኖ በመታየቱ አመስጋኝ ነበረች። ግን ወደቤት ከተመለሱ በኃላ መነጫነጭ ጀመረች ከዛ ሰውነቷን አጥባ እራቷን ካበላቻት  በኋላ አልጋ ላይ አስቀመጠቻት… ከዛ  ትንሿ ልጅ በሰከንዶች ውስጥ ተኛች። ይህም ራሄል ምስኪኗን ልጅ ከወዲህ ወዲያ እያሽከረከረች ስታንገላታት ስለዋለች  የጥፋተኝነት ስሜት እንዲሰማት አድርጎታል።..እና አሁን ልትቀሰቅሳትና የበለጠ ልታበሳጫት አልፈለገችም፡፡
አባቷን ለተጨማሪ ጥቂት ደቂቃዎች አወራቻቸው፣ አባቷን ስትናገር እንኳን ስራዋ እያንገበገበባት ነበር ..ትኩረቷን የሚከፋፍልባት ምንም ነገር ባይኖር ደስተኛ ነች  ።ወዲያው ሌላ ስልክ ተደወለላት.. ቃተተች እና ማን እንደሚደውል ሳታረጋግጥ አነሳችው..ቁጣ በሚመስል የድምፅ ቃና  ‹‹ራሄል ነኝ.››አለች

‹‹ሄይ ራሄል… እንዴት ነሽ?››ዔሊያስ ነበር…ፍስስ የሚለውን   ድምፁን ስትሰማ ብስጭቷን አቃለላት። ራሄል ዛሬ ወደቤት ከተመለሰች  በኋላ ዔሊን ለማየት ፈልጋ  ከአሁን አሁን በራፉን ያንኳኳል እያለች  በናፍቆት ስትጠብቅነበር፡፡

‹‹ስልክሽ ለረጅም ጊዜ ተይዞ ነበር››

‹‹ከአባቴ  ጋር እያወራው ነበር ››አለችው።

‹‹ነገሮች እዛ እንዴት እየሄዱ ነው…?ሄጄ ካየዋቸው እኮ ሳምንት ሊያልፈኝ ነው››

‹‹እናቴ ጥሩ እያገገመች ነው። ግን እስከሚቀጥሉት  ሁለት  ሳምንታት ወደ  ቤት እንደማትመጣ ነው የሰማሁት››

‹‹አይዞሽ…ዋናው የመዳን ሂደታችው እድገት እያሳየ መሄዱ ነው››

‹‹እሱስ እውነትህን ነው….ታዲያ አሁን  ምን እያደረክ ነው? ››ብላ ጠየቀችው

‹‹ምንም…ሶፋዬ ላይ ጋደም ብዬ ስለአንቺና ስለፀጋ እያሰብኩ ነበር››አላት፡፡

ደስ አላት‹‹እየፎገርክ ነው?››

‹‹አረ እውነቴን ነው…መቼስ ማል አትይኝም››

‹‹መምጣት ትፈልጋለህ?›› ቃላቶቹ ድንገት ነው ከአንደበቷ ያመለጧት….የአእምሯዋን ሳይሆን የልቧን  ምኞት ነው አንደበቷ ያሳበቀባት….

‹‹ከስራ ከወጣው በኋላ ከሶስት ጊዜ በላይ ልመጣ ተነስቼ ነበር ከዛ ‹‹አረ ኤልያስ እግርና አብዝተሀል…..ሰዎቹን እያጨናነቅካቸው እንዳይሆን ››ብዬ ራሴን በመገሰፅ ያቆምኩት፡፡

‹‹እባክህ ና:: እዚያ ባገኝህ ደስ ኀይለኛል።›› ድጋሚ አመለጣት…በራሷ ሽምቅቅ አለች፡፡

‹‹እንዲህ ከሆነ››አለ ዔሊ በፈገግታ ‹‹ መምጣት የምችል ይመስለኛል….››

‹‹ቆንጆ እራት ሰርቼ ጠብቅሀለው››

‹‹በጣም ደስ የሚል ነገር ነው..በዛውም የሞያ ብቃትሽ ይፈተሻል››

‹‹አንተ የእማዬ ልጅ እኮ ነኝ..በሞያዬማ ምንም ጥርጣሬ ሊገባህ አይገባም››

‹‹እኮ ላየው አይደል?››

‹‹አይ ዛሬ እንኳን አታየውም…ይሄንን ዙሪያዬን የተቆለለ ወረቀት ባለበት ጥዬ ኪችን አልገባም››

‹‹እና እራቱ  የለም እያልሺኝ ነው?››

‹‹እሱማ አለ ..ግን አለም ነች የምትሰራው››

‹‹ይሁን እሺ…..እስክንገናኝ ቻው››
‹‹ቻው››ስልኩን ዘጋች፡፡እንደገና ዘና ያለ ስሜት ተሰማት ፡፡

አለምን ተጣራችን እንግዳ ስለሚመጣ ቆንጆ እራት እንድታዘጋጅ አዘዘቻት እና ትኩረት ሰበሰበች እና ወደ ስራዋ ተመለሰች፡፡
///
ረዳቷ ሮቤል ወደእነ ራሄል ቤት መጥቶ አባቷ ቢሮ ውስጥ ተቀምጠው ስለፋውንዴሽኑ አመታዊ የገቢ ማሰባሰ
ቢያ ዝግጅት እየተወያዩ ነው፡፡
‹‹የትኛውን ስራ በማን እንደማሰራ እና …የተወሰኑ ስራዎችን ውክልና መስጠት ከየት እንደምጀምር አላውቅም።››ራሄል በንዴት ተነፈሰች።

‹‹ እኔም ስለእሱ እያሰብኩነበር…ሁሉንምነገር በራስሽ ለመስራት በመሞከር በራስሽ ላይ አላስፈላጊ ጫና ማሳደር የለብሽም…እኔ አለሁ››

‹‹እኔ ካንተ የበለጠ ጊዜ አለኝ ብዬ አስባለሁ… ።››

ሮቤል ንግግሯ አልተዋጠለትም፡፡ቢሆንም ብዕሩን በፋይሉ ላይ ሰክቶ እያዳመጣት ነው፡፡በሁሉም ነገር  ትዕግስት እያጣ እንደመጣ በሁኔታው መታዘብ ይቻላል፡፡

‹‹ራሄል እህትሽን በመንከባከብ እንደተጠመድሽ አውቃለሁ…የደከመሽ ትመስላያለሽ ።አሁን የሎዛን ስራ የሚሰራ ሌላ ሰው መፈለግ አለብሽ እና ጊዜ እንደሌለሽ አውቃለሁ። ››በማለት የሚያስበውን በግልፅ ነገራት፡፡
47🔥1😁1