#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አንድ
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
ይህቺን ፀሀፊ ልጅ ወዶታል…እሷ እራሷ የመጀመሪያ ደንበኛው ከመሆኗም በላይ ሌላ ደንበኛ አገኝታለታለች፡፡ስልኩን አወጣና ደወለ……አስቴር ጋር…
‹‹እሺ ወንድሜ ደህና ነህ?››
‹‹አለሁልሽ…የላክሻት ልጅ መታለች ልልሽ ነው፡፡››
‹‹እንዴት ነው …ተስማማችሁ?››
‹‹አዎ ጎበዝ ልጅ ትመስላለች››
‹‹ጎበዝ?››
‹‹አዎ ምነው?››
‹‹አይ በአንድ ቀን እንዴት ጎበዝ መሆኗን አወቅክ ?ብዬ ገርሞኝ ነዋ››
‹‹ማለቴ እንዲሁ ሳያት ተግባቢና ቀልጣፍ ነገር ነች ልልሽ ነው››
‹‹ወንድሜ ፍቅር እንዳይዝህና እንዳትጎዳብኝ…ልጅቷ ፍቀረኛ አላት››
‹‹አይዞሽ አታስቢ አውቃለው፣በዛ ላይ እኔ ማፈቀሪያ ጭንቅላቴ የተበላሸብኝ ሰው ነኝ….››
‹‹ምኑ ነው ምታውቀው?››
‹‹እንዳላት ነዋ››
‹‹ከምኔው?››
‹‹ውይ ኪያ ደግሞ ….በቃ ቻው ማታ ቤት እንገናኝ››
‹‹እሺ ቻው ወንድሜ››በተንከትካች ሳቅ አጅባ ስልኩን ዘጋችው፡፡
////
ወላጇቾ ብቻ ሳይሆኑ ያደገችበትና የእድሜዋን ግማሽ የኖረችበት እቤቷም ጭምር ናፈቃት‹‹ ቤት ማለት..ግን ምን ማለት ነው?ስትል እራሷን ጠየቀችና መልሱን ከአእምሮዋ ውስጥ በርብራ ለማግኘት አይኖቾን ጨፍና ማሰላሰል ጀመረች
‹‹አዎ እቤት ከድንጋይ ወይም ከእንጨት የሚታነፅ የሰው ልጅ መጠለያ ነው።ያንን ህንፃ ከመጠለያነት ወደ ቤትነት የሚቀይረው ግን የታነፀበት ማቴሪያል ጥራትና ውበት አይደለም...ውስጡ ያሉት ዘመናዊ የቤት እቃዎች እና ውድነትም አይደለም። ህንፃው ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች እርስ በርስ ያላቸው ግንኙነትና የፍቅር ትስስር መጠን ነው ህንፃውን እቤት የሚያደርገው።ለዚህ ነው ከኖርኩበት የተንጣለለ ቪላ ይልቅ አሁን እየኖርኩበት ያለሁት ባለ ሁለት ክፍል ጎስቋላ ቤት የተሻለ የሚሞቀውና የሚደምቀው
››መልሱን ለራሷ ሰጠች፡፡ ቀኑን እንዲሁ በሀሳብና በትካዜ ጊዜውን ብታሳልፍም ሲመሽ ግን ሁሉ ነገር የተለየ ሆነ፡፡
ማታ የቤተሰቡ አባል ጠቅላላ ተሰብስበው በሞቅ ደስታ ከወትሮ በተለየ ድግስ መሰል እራት ቀርቦ በመጎራረስ ከበሉና ቡናም ተጠጥቶ ከተነሳ በኃላ በፀሎት ሽንት ቤት ለመሄድ እንድምትፈልግ ለለሊሴ ነገረቻት…ያሰበችው እሷ ደግፋ እንድትወስዳት ነበር…በተቀራራቢ እድሜ ስለሚገኙ እቤት ውስጥ ካሉ ሰዎች ሁሉ እሷን ማዘዝ ወይም ትብብር መጠየቅ ቀላል ይላታል፡ ….ለሊሴ ግን እንዳሰበችው አላደረገችም….
‹‹ወንድሜ በፀሎትን ሽንት ቤት ትወስዳታላህ?››ብላ ስትጠይቀው ክው ነበር ያለችው….እሱ አንደበት አውጥቶ ፍቃደኝነቱን ሳይናገር በቀጥታ ከተቀመጠበት ተፈናጥሮ ተነሳና ወደእሷ በመሄድ ልክ ትናንት ለሊት እንዳደረገው ከስር ሰቅስቆ ልክ እንደህፃን ልጅ አቀፋት….እንዲህ አይነት ሁኔታ በህይወቷ ገጥሞት ስለማያውቅ መደንገጥ ብቻ ሳይሆን እፍረትም ተሰማት…‹‹.ወላጆቹ እንዲህ ሲያቅፈኝ ምን ይላሉ ?››የሚለው ሀሳብ አእምሮዋ ተሰነቀረና ያንን ለማጣራት እይታዋን በቤቱ ዙሪያ ስትሽከረከር ሁሉም በራሳቸው ጫወታ ተመስጠው እርስ በርስ እያወሩ እየተሳሳቁ ነው……አንከብክቦ እንዳቀፋት ይዟት ወጣ
..ቀጥታ ሽንት ቤት ወሰዳና ወደውስጥ አስገብቶ አቆማት…ልክ እንደሌሊቱ ውሀ በሀይላንድ ከቧንቧው ቀድቶ አመጣላትና የሽንት ቤቱን መጋረጃ ወደታች መልሶ ‹‹ስትጨርሺ ጥሪኝ
››ብሎ ከአካባቢው ዞር አለ፡፡
የሽንት ቤት ጣጣዋን ከጨረሰች በኋላ ቀጥታ ወደቤት አይደለም ይዞት የገባው፡፡ልክ እንደለሊቱ ወንበር አመቻችቶ ስለነበር ተሸክሞ ወስዶ አስቀመጣት….‹‹ቀኑን ሙሉ ተኝተሸ ስለዋልሽ አሁን ትንሽ ንፍስ ይንካሽ››
‹‹አዎ ትክክል ነህ፣በዛ ላይ ጨረቃዋም ናፍቃኝ ነበር፡፡››
እሱም ለራሱ መቀመጫ አምቻችቶ ከፊት ለፊቷ እየተቀመጠ‹‹ከጨራቃዋ ጋር ወዳጅ ናችሁ እንዴ?››ሲል ጠየቃት፡፡
‹‹አዎ ለዛውም የእድሜ ልክ››
‹‹ያን ያህል ብቸኛ ነሽ ማለት ነው?››
‹‹እንዴት ከጨረቃ ጋር ለመወዳጀጀት ብቸኛ መሆን የግድ ነው እንዴ?››
‹‹አይ የግድ ባይሆንም ከልምዴ ስነሳ ብዙውን ጊዜ ከጨረቃዋ ጋር ለረጅም ጊዜ የማውጋት ልምድ ያላችው እንቅልፍ አልባ ብቸኛ ሰዎች ናቸው……በተለይ በፍቅር የተሰበሩ››
‹‹እንዴ በፍቅር የተሰበሩ ነው ያልከው..አይ እንደዛ እንኳን አይደለም…..ባይሆን እንዳልከው ከቤተሰብ ጋር በተያያዘ በሚፈጠር ብቸኝነት ብንለው የተሻለ ነው..የፍቅር ጉዳይማ ቢሆን በምን እድሌ..ፍቅር እኮ በጣም ምርጥ ነገር ነው፡፡››
‹‹ትክክል ነሽ… ፍቅር በጣም ወሳኝ ስሜት ነው….አንድ ሰው ሩሚን ‹‹ፍቅር ምንድነው?››ብሎ ጠየቀ።ሩሚም ..‹‹ፍቅር ምን እንደሆነ ትክክለኛ ትርጉሙን ልታውቅ የምትችለው ውስጡ መጥፋት ስትችል ነው።›› ብሎ መለሰለት…..፡፡
‹‹አዎ ትክክለኛ አባባል ይመስለኛል….ፍቅር የምትተነትነውና የምታወራው ነገር አይደለም፣ፍቅር ኖረህ የምታጣጥመው የተቀደሰ ስሜት ነው….በፍቅር መጥፋት ጥሩ አባባል ነው››
‹‹አይ ጥሩ…ለማንኛውም ለደቂቃም ቢሆን እስቲ ከጨረቃዋ ጋር ብቻችሁን ልተዋችሁ…. መጣሁ›› ብሎ ተነስቶ ወደቤት ገባ..እሷ አይኖቾን ወደላይ አንጋጠጠች…ሰማዩ ጥርት ብሎ ይታያል ፡፡ጨረቃዋ ሙሉ ክብ ሆና ደፍናለች..ዙሪያዋን የተበተኑና ከዋክብቶች ብልጭ ድርግም እያሉ ይታያሉ…አናትና አባቷ ትዝ አሏት..ይሄኔ የእሷን መጥፋት ምክንያት በማድረግ የመጨረሻውን ጥል እየተጣሉና የመጨረሻ የተባለውን አንጀት በጣሽ ስድብ
እየተደሰዳደብ እንደሆነ በምናቧ አሰበችና ሙሉ ሰውነቷ ሽምቅቅ አለባት..ሰውነቷ ሲሸማቀቅ ደግሞ የእግሯ ሆነ የፊቷ ጥዝጣዜ ህመም ተቀሰቀሰባት….
ድንገት የሰማችው ድምፅ ነው ከሀሳቧ ያባነናት…..ያልገመተችውን ነገር ነው እያየች ያለችው..ፊራኦል ፊት ለፊቷ ቅድም የነበረበት ቦታ ቁጭ ብሎ ክራር እየከረከረ የሙሀመድ አህመድን የትዝታ ሙዚቃ ያንቆረቁራል….ፍዝዝ ብላ በፍፁም ተመስጦ ታዳምጠው ጀመር፡፡
ስንቱን አስታወስኩት…ስንቱን አስብኩት ልቤን በትዝታ ወዲያ እየላኩት
አንዴ በመከራ …አንዴ በደስታዬ ስንቱን ያሳየኛል ..ይሄ ትዝታዬ
በድምፁ ድንዝዝ ብላ ጠፋች………… የትናንቱ ፍቅር ….ጣሙ ቁም ነገሩ ምነው ያስተዋሉት ያዩት በነገሩ
ሁሉም እንደገና ኑሮን ቢያሰላስል አይገኝም ጊዜ ያኔን የሚመስል፡፡
ዘፈኑን ሲጨርስ‹‹አንተ..አንድ ሺ አመት በዚህ ምድር ላይ ኖረህ ከዛሬ 500 ዓመት በፊት ያለውን ጊዜ ናፍቀህ የምትተክዝ እድሜ ጠገብ አዛውንት ነው የምትመስለው፡፡››የሚል አስተያየት ሰጠችው፡፡
‹‹ያን ያህል?››
‹‹አዎ …ድምፅህ በጣም ግሩም ነው….ሙዚቃ ትሰራለህ እንዴ?››
‹‹አይ ያን ያህል እንኳን ሰራለሁ ማለት አልችልም …በፊት በፊት ቀበሌ ኪነት ከጓደኞቼ ጋር እሞክር ነበር አሁን ከህይወት ሩጫ ጋር አብሮ አልሄድ አለኝና ተውኩት፣እንዲህ አንደዛሬው ጨረቃዋ ሙሉ ስትሆን እንዲህ እቀመጥና ለእሷ አዜምለታለው፡፡››
‹‹እንዴ..ለእኔ የዘፈንክልኝ መስሎኝ ውስጤ በደስታ ተፍነክንኮ ነበር ..ለካ ለጨረቃዋ የተዘፈነውን ዘፈን ነው ሳይፈቀድልኝ የሰማሁት…..››
‹‹አይ እንደዛ አንኳን ለማለት አልችልም…የዛሬው ዘፈን ቀጥታ ላንቺ ነው..ምስጋናና ይቅርታ ለመጠየቅ፡ ብዬ ነው የዘፈንኩት፡፡››
‹‹አልገባኝም..ይቅርታውስ ለምን ?ምስጋናውስ?፡፡››
‹‹ይቅርታው ገና ስትመጪ ጀምሮ በሙሉ ልቤ ስላልተቀበልኩሽና ለእኔም ሆነ ለቤተሰቦቼ እንደሸክም ስለቆጠርኩሽ…ምስጋናው ዛሬ እናቴንም ሆና መላ ቤተሰብን አንበሽብሸሽ በማስደሰትሽ…..››

👍79❤18😱1
#የጣት_ቁስል
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ
"አንች ጠጭ ጠጭ ምንም አይልሽም ብለሽኝ አሁን እኮ አዞረኝ" አለች፡፡ ለጓደኛዋ መቅደስ፡፡
"አንዱን ቢራ ጨረሽው እንዴ? ትገርሚያለሽ እንደለስላሳ ነው ስልሽ እንደለስላሳ ጨለጥሽው፡፡ በይ አሁን ቀስ ብለሽ አንድ ድገሚና ከዚያ በኋላ ይበቃሻል፡፡ ለነገሩ ቢራ አንድ ስለማይጠጣ ነው እንጅ በአንድ ቢበቃሽ ጥሩ ነበር፡፡
"አሁን አመመኝ እያልኩሽ ድገሚና ጠጭ ትይኛለሽ ? ብላ ብትኮሳተርም መድገሟ አልቀረም ሁለተኛ ቢራዋን አስከፈተች፡፡
በስካር መንፈስ ምሽቱ ወደ ቀን ተቀይሮበታል፡፡ አይመሽም እንዴ? ሆቴሉ አይዘጋም? ይላል ፤ ተመስን በውስጡ ፡፡
"ከአሁን በፊት ከሴት ጋር ተኝተህ ታውቃለህ"? እንዴ አለው ያሬድ፡፡
"ከሴት ጋር መተኛት አይደለም ለመተኛትም አውርቼ አላውቅም፡፡ ዛሬ ግን ብተኛ ምን እሆናለሁ፡፡
"እና የትኛዋ ትሻልሃለች"?፡፡
"የሽሃረግ ትሻለኛለች ፤ እሽ ካለች፡፡
"እሽ ፤ እንጠይቃታለን ግን እንደ ገጠር ሴት ዝም ብለው እሽ አይሉም፡፡ ገንዘብ ይጠይቃሉ፡፡
"ለብር ችግር የለም፡፡ ብቻ እሽ አሰኝልኝ ፡፡
ያሬድ መቅደስን ለብቻዋ ጠርቶ ለማነጋገር ፈልጓል፡፡ ከመቀመጫው ተነሳ፡፡ መቅደስን ጠራት፡፡ ከሰው ጋር እንዴ? ብሎ ጠየቃት፡፡
"እኔ ከሰው ጋር ነኝ፡፡ የሽሃረግ ደግሞ እንደዚ አይነት ስራ ሰርታ ስለማታቅ አትወጣም አለችው፡፡
ደግሞ የከተማ ሴት እንደ ገጠር ነው እንዴ? በገንዘብ እሽ አትልም? ፡፡
"እሱማ ልክ ነህ ፤ እሷ ግን ስለማትሰራ ነው፡፡
ጓደኛየ ከአሁን በፊት ከሴት ጋር ተኝቶ አያውቅም፡፡ ዛሬ ምን እንደነካው እንጃ በየሽሃረግ አብዷል አላት፡፡
ብቻ ከእሷ ለመስማት እሽ ካለች እጠይቃታለሁ፡፡ ብላ ልጠይቃት እየፈራች ቢሆንም ተጠጋቻት፡፡ የሽሃረግ የጠጣችው የሐረር ቢራ አስክሯታል፡፡ ወደ ኋላ ያሰረችውን ሐር የሚመስለውን ፀጉሯን ለቃዋለች፡፡
ታዲያ አይኗን ሸፍኖት ትንሽ ትንሽ ነበር ፊቷ የሚታየው፡፡
መቅደስ የጠጣችው ቢራ እሷንም ሞቅ አድርጓት ስለነበር የሽሃረግን ሳትፈራ ስሟን አቆላምጣ የሺዬ ያሰውዬ ፎንቅቄያለሁ እያለ ነው አለቻት፡፡
"የቱ ነው"? አለች፡፡ ፀጉሯን ከፊቷ ላይ ገለጥ እያደረገች፡፡
ቢራ ከጋበዙሽ አንደኛው ፡፡ ያ የፂሙ አሪዝ የሚያምረው ሰውዬ፡፡ ደግሞ ሴት የሚባል አውጥቶ አያውቅም፡፡ ቢራ እራሱ የተማከራችሁ ይመስል እንደ አንችው ዛሬ ነው ፤ የጀመረው አለቻት፡፡
"አንች በምን አወቅሽ ዛሬ ቢራ መጀመሩን ?፡፡
አብሮት ያለው ጓደኛው ነው የነገረኝ፡፡
"እኔ እንደዚህ አይነት ስራ እንደማልሰራ እያወቅሽ ፤ ለምን ትጠይቂኛለሽ"? አለች፡፡ ውስጧ ፍራት ፍራት እየተሰማት፡፡
እሱንማ አውቃለሁ፡፡ ግን አንች እስከመቼ ድረስ ነው? ወንድ የማትፈልጊው ፤ የጠየቀሽን ሁሉ አልፈልግም እያልሽ፡፡ ላይፍሽን በአሁን ሰዓት ካልተጠቀምሽበት መቼ ልትጠቀሚበት ነው?፡፡ ደግሞ ጊዜሽ ካለፈ ወዲያ ማንም ሊጠይቅሽ አይደለም ዞር ብሎ የሚያይሽ አታገኝም፡፡ ይልቁንም ዛሬ እትዬም ስለሌለች አብረሽው እደሪ አለቻት፡፡
እሳትን በእሳት እንደ ሚባለው ሴትን በሴት አሳምኖ በቁጥጥር ስር ማድረግ በሴቶች የተለመደ መሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡
ጊዜሽ ካለፈ ዞር ብሎ የሚያይሽ አታገኝም፡፡ ያለቻት ህሊናዋን በመርፌ የተወጋች ያህል ተሰማት፡፡ በትካዜ ተዋጠች፡፡ መጀመሪያም ልቧን በአይን አፋርነቱና በጉንጩ ላይ መስመር ሰርቶ በወረደው አሪዛም ፂሙ አሸፍቶ የወሰደባት ተመስገን እንኳን ለሴት ልጅ ለወንድ ልጅ ያማልል ነበር፡፡
"እትየ ስትመጣ ካልነገርሽብኝ እኔም ወድጀዋለሁ"፡፡ አለቻት የልብ ትርታዋ ከመጠን አልፎ ቁና ቁና እያስተነፈሳት፡፡
አልነግርብሽም፡፡ ደግሞ እኔ የምናግረው ጣቱን የሚጠባ ህፃን አደረግሽኝ እንዴ ብላት "በይ አሁን
ሰውም ስለሌለ እንዘጋጋና እኔም ሰው እየጠበቀኝ ነው እንተኛ አለቻት፡፡
"እምቢ ሳትል አትቀርም አለ ፤ ያሬድ፡፡
የከተማ ሴት ገንዘብ ነው የሚፈልጉት አላልከኝም" እንዴ አለ ፤ ተመስገን፡፡
የዚች የተለየ ነው እባክህ ብሎ ሌላም ደግሞ ሳይናገር መቅደስ ጠጡና ተነሱ ልንዘጋ ነው አለች፡፡
ተመስገን መሸ እንዴ? አለ፡፡
አልታወቀህም እንዴ? ከመምሸቱም ሊነጋ ተቃርቧል፡፡ እንዴውም የእኛ ብቻ ነው፡፡
ያልተዘጋው እንጅ የሁሉም ሆቴሎች ተዘግተዋል አለች ፤ መቅደስ፡፡
"እሽ ፤ እንነሳለን ግን የሽሃረግ ምን አለችሽ"? አለ
መቅደስ በስንት ልመና እሽ አስብያታለሁ፡፡ አሁንም እየፈራች ስለሆነ እናንተ ተነሱና አልጋ ቤት ጠብቁኝ፡፡ እኔ ይዣት እመጣለሁ አለች፡፡
ተንገዳገደ፡፡ ደግፎት ወደ መኝታ ቤት ገቡ፡፡
መቅደስ ሆቴሉን ዘጋግታ ከጨረሰች በኋላ፤ የሽሃረግን የሆቴሉ ዘበኛ እንዳያያት ወደ ሽንት ቤት የሚሄዱ አስመስላ ወደ እነ ያሬድ አልጋ ቤት አስገባቻት፡፡ ያሬድ ለሚተኛበት ሌላ አልጋ ከፍታለት አብሯት ወደ ሚያድረው ሰው ጋር ተመለሰች ፡፡
ለተመስገን ችግር የሚያጋጥምህ ከሆነ እዚህኛው አልጋ ቤት ነው የምተኛው፡፡ ነገ በጥዋት ወደ አቶ ላንቻ ቤት እንሄዳለን ብሎት ሁለተኛ ወደ ያዘው አልጋ ሄዶ ተኛ፡፡
የመኝታው በር ተዘጋ፡፡ ልብሳቸውን አወላለቁ፡፡ ከአሁን በፊት እንደሚተዋወቁ ፍቅረኛ ተቃቀፉ፡፡ ታምሪያለሽ ፤ አንተም ታምራለህ፡፡ ብቻ የሚል ቃል ተነጋግረው በለበሱት ብርድልብስ ውስጥ ከንፈር ለከንፈር ተፈላልገው ተገናኙ፡፡
የሁለቱም የሰውነት ሙቀት ጨመረ፡፡ ሳይታወቃቸው የተመስገን እግሮች በየሻረግ እግሮች ውስጥ ተጠላለፉ፡፡ በስካር መንፈስ ጉዳያቸውን ከፈፀሙ በኋላ ሁለቱም እራሳቸውን ሳቱ፡፡ መተቃቀፉና መሳሳሙ ቀረ፡፡ ድጋሜም አልተገናኙም፡፡ የለሊቱ ጨለማ ለቆ የቀኑ ብርሃን ተተካ፡፡
ያሬድ እሱም በስካር መንፈስ የመኝታ በሩን ከፍቶ እንደ ገባ ጫማውን እንኳን አላወለቀም፡፡ የወደቀበትን አያውቀም፡፡ ስካርና እንቅልፉን አሳልፎ ከተኛበት መኝታ ላይ ባነነ፡፡ ጫማውን ሳያወልቅ በመተኛቱ ተገረመ፡፡እንደዚህ እራሴን እስከምስት ድረስ ሰክሬ ኖሯል፡፡ ወይ ነዶ የሰውዬው ልጅ እያለ ተነሳ፡፡ በሩን ከፈተ፡፡ ሌሊቱ ነግቶ ቀን ቀን እየሸተተ ነው፡፡
የስካር ፊቱን ታጠበ፡፡ ልቡ አቶ ላንቻ ጋር ለመሄድ ተቻኩሏል፡፡ የአልጋው በር አልተዘጋም፡፡ ገርበብ ብሏል፡፡ ሳይዘጉት ይሆን እንዴ? የተኙት እያለ ገርበብ ያለውን በር ከፈት አድርጎ ገባ፡፡
የሽሃረግ ከተኛችበት ስትነሳ ከማታውቀው ሰው ጋር ተኝታ የንፅህና ክብሯን በመስጠቷ የሞት ያህል ተሰምቷታል፡፡ በሁለት እጆቿ እራሷን ደግፋ ከአንገቷ ወደ መሬት አቀርቅራ ከመኝታው ላይ ተቀምጣለች፡፡ የተፈጠረውንና ያደረገችውን ሁሉ ለማስታወስ እየሞከረች ከህሊናዋ ጋር እየተሟገተች ሳለ ያሬድ በር ከፍቶ ገባ፡፡ ካቀረቀረችበት ቀና አለች፡፡ ከያሬድ ጋር አይን ለአይን ተጋጩ፡፡ ያሬድ ሰውነቱ ተንቀጠቀጠ፡፡ ድንጋጤ ተሰማው፡፡
የሽሃረግን ደጋግሞ አትኩሮ ተመለከታት፡፡ ማታ በዲም ላይትና በፌር ቅባት ህንዳዊ መስላ የታየችው የፊት ላይ ቅባት ተወግዶ የኢትዮጵያዊነት ደም ግባቷ ተመልሷል፡፡ የጠይም ለግላጋ ቆንጆ መሆኗን በደንብ ይታያል፡፡ የሚያውቃት የሚያውቃት መሰለው፡፡
ተመስገን የት እንደ ሄደ እንኳን አልጠየቃትም፡፡ ወደ ተቀመጠችበት መኝታ ተጠጋ፡፡
ምነው? የማውቅሽ መሰለኝ፡፡ ግን ስምሽ ትክክለኛ የሽሃረግ ነው? አላት፡፡
የሽሃረግ ጭንቅላቷን በመጥረቢያ እንደተመታች ያህል ባለችበት ክው ብላ ቀረች፡፡ ያሬድን አፍጣ ፣ ደግማ ፣ ደጋግማ አየችው፡፡
"የየየየየየየየየየየየየ..ታ...ውቀኛለህ"? አለች፡፡ አፏ እየተንተባተበ፡፡

👍69❤3
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
=====================
ሁሴን ወደዩኒቨርሲቲው ከተመለሰ ከአስራ አምስት ቀን በኋላ…
አላዛር እንደተለመደው ስራ ውሎ ቤት እንደገባ በራፉ ከልክ በላይ ተቆረቆረ..በድንጋጤ ሄደና ከፈተው፡፡ሰሎሜ ነች..፡፡አይኖቾ በለቅሶ ብዛት ደም ለብሰዋል፡፡በዛ ላይ አባብጣለች፡፡ወደውስጥ ጎትቶ አስገባትና በራፉን መልሶ ዘግቶ ‹‹ምን ሆንሽ?››ሲል ጠያቃት..ልትመልስለት ሞከረች ግን ሳግ እየተናነቃት ማውራት አልቻለችም፡፡ተንደርድራ ሄዳ ሶፋው ላይ ወጥታ እጥፍጥፍ ብላ ተኛች፡፡ለምን እንደዚህ እንደሆነች በደንብ ያውቃል፡፡ቢሆንም አሳዘነችው፡፡ቢቻለው ይሄንን ጉዳይ እሷን ቅንጣትም ሳያሳዝን በፀጥታ ማጠናቀቅ ነበር ምኞቱ…ግን እንደዛ ማድረግ አይችልም‹‹ካለመስዋዕትነት የሚገኝ ውጤት የለም››ብሎ በማሰብ እራሱን ለማፅናናት ሞከረ፡፡በጣም አሳዘነችው፡፡በዝግታ ሄዶ ፈራ ተባ እያለ ስሯ ተቀመጠ፡፡
‹‹ሶል ምን ሆንሽ?››
‹‹ያ ደደብ..ቺት ሲያደርግብኝ ነበር ለካ፡፡››
‹‹እንዴ ማን?›
‹‹እስራኤል ነዋ.. ሌላ ማን ይሆናል?››
‹‹እንዴ ገና ከመጀመሪያችሁ..አረ የተሳሳተ ወሬ ደርሶሽ እንዳይሆን?››ከመጋረጃ ጀርባ ያለውን እውነተኛ ሙሉ ታሪኩን ቢያውቅም በማስመሰሉ ቀጠለበት፡፡
‹‹ኸረ ባክህ…››አለችና ከተጋደመችበት ተስፈንጥራ ተነስታ ከጃኬቷ ኪስ ውስጥ ፎቶዎችን አወጣችና ጠረጴዛው ላይ ዘረገፈችለት፡፡
ልክ ፎቶውን ለመጀመሪያ ጊዜ እንዳየው በማስመሰል በመደነቅና በመገረም እያቀያየረ ይመለከታቸው ጀመር፡፡
‹‹ልጅም አለው ማለት ነው?›
‹‹አይገርምም..ምን አይነት ጅል ኖሪያለው?››
‹‹እንዴ አንቺ እንዴት ልታውቂ ትችያለሽ?››
‹‹አይደል …ልስልስ ብሎሰ ሲቅለሰለስ እኮ መላአክ ነው የሚመስለው፡፡.
ፎቶውን እንዴት እንዳገኘችው በደንብ እያወቀ‹‹ለመሆኑ ይሄን መረጃ እንዴት አገኘሽው?››ሲል ጠየቃት፡፡
..ካፌ አስተናጋጅነት ስራ ጀምሬለሁ አላልኩህም…ሽፍቴን ጨርሼ ወደቤት ለመምጣት ታክሲ እየጠበቅኩ ሳለሁ ነው የሆነ ህፃን ልጅ የሰጠኝ…የሆነች ሴት ነች የላከችልሽ››ነው ያለኝ…በወቅቱ ግራ ተጋብቼ ስለነበር ከዛ በላይ ማጣራት አልቻልኩም፡፡››
‹‹እራሷ ሚስቱ ትሆናለች፡፡››
‹‹አዎ መሰለኝ ከፎቶው ጋር አብሮት የሆነ ማስታወሻ ነበረበት
..‹እባክሽ የልጄ አባት ባሌን ተይልኝ……ትዳራችንን አትበጥብጪ› ይላል››
‹‹ይገርማል…ታዲያ እሱን አላናገርሽውም?››
‹‹ምን አባቱና ነው የማናግረው…..ወዲያውኑ ነው ስልኩን ብላክ ሊስት ውስጥ የጨመርኩት ፣ ብቻ እግዜር ነው የተፋኝ፡፡››
‹‹እንዴት ማለት?››
‹‹ምን እንዴት አለው..?አንድ ተጨማሪ ወር ቆይተን ቢሆን ኖሮ ሌላ ነገር ውስጥ ልንገባ እንችል ነበር››
‹‹ሌላ ነገር ማለት?››
‹‹አንተ ደግሞ በረዶ ነጭ ነው ካለሉህ አይገባህም….››አለችው በብስጭት፡፡
በረጅሙ ተነፈሰ….‹‹አለመነካካታችሁም አንድ ነገር ነው…አይዞሽ ቀስ እያልሽ ትረሺዋለሽ››ሲል ሊያፅናናት ሞከረ፡፡
‹‹አይ አካላችን አለመነካካቱን አትይ …ልባችን ተነካክቶ ነበር..በተለይ ልቤ ልቡ ላይ ተለጥፎ ነበር….ልብን ከተለጠፈበት መንጭቀህ ስታላቅቀው ደግሞ ተቦጭቆ የሚቀር ነገር አለ..የሚቆስልና የሚቆጠቁጥ…ያማል…..››
ጭንቅላቷን እያሻሸ‹‹አይዞሽ…!!.››አላት፡፡
‹‹አላዛር››ስትል ድንገት ጠራችው፡፡
‹‹ወዬ ሰሎሜ››
‹‹ቆይ እኔ አስጠላለሁ እንዴ?››
‹‹ምን አይነት ጥያቄ ነው?››
‹‹ጓደኛዬ ከሆንክ በታማኝነት መልስልኝ..እኔ አስጠላለሁ ወይ?››
‹‹አንቺ ማለት ድቅድቅና ጭለማ በሆነ አለም ውስጥ ቦግ ብለሽ በድምቀት የምታበሪ ጨረቃ ነሽ…አንቺ ውብ ካልሆንሽ..ውብ ሚባል ነገር ጭራሽ በዚህ አለም የለም ማለት ነው››አላት ከአንጀቱ፡
‹‹አንተ ደግሞ ከፊክሽን ያነበብከውን ውብ የፍቅር ውዳሴ አሰማኝ አላልኩህም እኮ….ንፅህ ስሜትህን ነው የጠየቅኩህ››
‹‹እኔም የነገርኩሽ ስለአንቺ የሚሰማኝን ነው..ፊክሽን ማንበብ እንደማልወድ ደግሞ ታውቂያለሽ፡፡››
‹‹ታዲያ እንደምትለው ከሆነ ..ለምን ፍቅርን በተመለከተ ስኬታማ መሆን አቃተኝ..?››
‹‹አንቺ ብቻ እኮ አይደለሽም ..እኛም ጓደኞችሽ እስከአሁን ይሄነው የሚባል የፍቅር ታሪክ የለንም፡፡ያ ማለት ወደፊት አይኖረንም ማለት አይደለም….ከፊታችን ገና ብዙ ብሩህ እድሎችና ተስፋዎች እንዳሉን አምናለው፡፡ደግሞ እንዳትረሺ ውቧች ሁሉ ሁሌ በፍቅር ውጤታማ መሆን አለባቸው የሚል ህግ የለም ፡፡ .››
‹‹ይሁን እስኪ እንደአፍህ ያድርግልን…..ምን አልባት ሁለችንም ጓደኛሞች ልጆች ሆነን ጀምሮ ተንኮል ስንሰራ ስላደግን የሆነ ሰው ‹ፍቅር በልባችሁ አይደር…ካደረም አይሰንብት› ብሎ እረግሞን ይሆናል….›› ብላ ከተቀመጠችበት ተነሳችና ቆመች፡፡
‹‹ምነው ልትሄጄ ነው እንዴ?››
‹‹እና ልደር?››
‹‹ምን ችግር አለው…?
‹‹በል ይሄን ያህል ካለቃቀስኩብህ ይበቃኛል ..አመሰግናለው..ትንሽ ቀለል ብሎኛል››
‹‹በይ እሺ ደህና እደሪ››አለና በራፉ ድረስ ሸኛት፡፡በራፉን እንደከፈተ ቆሞ በራፏን ከፍታ እስክትገባ ተመለከታት…ከዛ በእፎይታ እና በእርካታ በራፉን ዘጋና ወደመኝታው አመራ፡፡
////
አላዛር እና ሰሎሜ ለሁሴን ምርቃት ለመሄድ እየተዘጋጁ ባሉበት ወቅት ያልገመቱት አስደንጋጭ እና ያልተጠበቀ ግን ደግሞ አስደሳች ተብሎ ሊታሰብ የሚችል ዜና ደረሳቸው፡፡
መጀመሪያ ለአላዛር ነው መልእክት የተላከለት፡፡
ሰሎሜ እና አላዛር ወንድሜ እኔን ለማስመረቅ ወደእኔ ለመምጣት ምታደርጉትን ዝግጅት አቁሙ..አስፈላጊ አይደለም፡፡ልትልክልኝ ያሰብከውን ገንዘብም አትላክልኝ …እስከዛሬ ከበቂ በላይ ረድተኸኛል…አመሰግናለሁ፡፡ለምን እንደዛ እንዳልኩህ ዝርዝር ምክንያቱን ሰሞኑን ኢሜል አደርግልሀለው፡፡››ይላል፡፡
ገና ሰሞኑን ጠብቆ ኢሜል እስኪልክለት መጠበቅ አልችልም.፡፡ለምን እንደዛ እንዳላቸው ለማወቅ..ስልክ ደወለለት …አይነሳም፡፡ደጋግሞ መከረ…፡፡በማግስቱ እንደውም ጭሩሱን ስልኩ አይሰራም ፡፡ጥሪ አይቀበልም ይላል፡፡
ለሰሎሜም ሁኔታውን ነግሯት አብረው መጨነቅ ጀመሩ፡፡
እሷም ከእሱ በላይ ተጨንቃ
‹‹ታዲያ ምን ይሻላል ትላለህ?››ስትል ጠየቀችው ፡፡
‹‹እኔ እንጃ …ምን አልባት እኛን ማስቸገር ከብዷት እንዳይሆን››
‹‹ይመስለኛል…ማለቴ አንተን ማስቸገር ከብዶት ነው የሚሆነው››ስትል በሀሳቡ ተስማማች፡፡
‹‹ምን ማለት ነው..?ጓደኛቹ አይደለን እንዴ..?በእንደዚህ አይነት ጊዜ ከጎኑ ካልሆን ጥቅማችን ምኑ ላይ ነው፡፡››ተበሳጨ፡፡
‹‹ያው ሁሉም ጓደኛ እኮ አንተ እንደምታደርገው አያደርግም››
‹‹እንዴት? ››
‹‹እኛ እርስ በርስ ጓደኛሞች ብቻ አይደለንም የእድሜ ልክ ትስስር ያለን ወንድምአማቾች ነን››
‹‹ይሄ ገለፃ አሌክስንም ያጠቃልላል?››ሲል መልሶ ሌላ ጥያቄ ጠየቃት፡፡
ፊቷ ቅይርይር አለ…አሌክስ የሚባለውን ስም መስማት የማትፈልገው ስም ከሆነ ከራርሟል ፡፡መኮሰታተሯን አይቶ‹‹እሺ አትበሳጪ..እንዳልሺው ሊሆን ይችላል፡፡አሁን ዋናው ነገር ምን እናድርግ የሚለው ነው?›› ሲል ምክረ ሀሳቧን ጠየቀ፡፡
‹‹እኔም ግራ ገባኝ እኮ…፡፡›
‹‹ዝም ብለን ወደ ጎንደር እንሂድ እባክሽ››ሲል ቅፅበታዊ ውሳኔውን ነገራት፡፡
‹‹መቼ….?››
‹‹በቃ ነገ እንዘገጃጅና ተነገ ወዲያ እንሂድ፡፡››
‹‹ግን አውቀሀል… ለምርቃቱ ገና አስር ቀን ይቀረዋል…ደርሰን እንመለሳለን ወይስ እንዴት እናደርጋለን?››

👍50❤4
#አላገባህም
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
/////
ሚካኤል ከኦሮሚያ ማረሚያ ቤቶች ከፍተኛ ኃላፊ ጋር ሚስጥራዊ ስብስባ እያደረገ ነው፡፡እኚን ባለስልጣን ለማግኘትና ለማናገር በጣም ብዙ ውጣ ውረድ አሳልፏል …በጣም ብዙ ገንዘብም ከስክሷል፡፡
‹‹እሺ አቶ ሚካኤል እንዳገኝህ ያሳመነን ወዳጄ ትልቅ ባለውለታዬ ነው ..ምን እንዳደርግልህ ነው የምትፈልገው?፡፡››ሲል ቦርጫቸውን እሻሹ ጠየቁት፡፡
‹‹ያው ጫፉን ያውቁታል ስለአባቴ ጉዳይ ነው››
‹‹እሱን ሰምቼለው…አባትህ የሞት ፍርድ የተፈረደበት ሰው ነው፡፡ምን እንድረዳህ እንደፈለክም ያልገባኝ ለዛ ነው፡፡ታውቃለህ የሞት ፍርድ የተፈረደበት ፍርደኛ ቀጥታ ፋይሉ የሀገሪቱ ፕሬዘዳንት ጋር ነው ሚላከው..እሳቸው ሲፈርሙበት የሞት ቅጣቱ ተፈጻሚ ይሆናል…እስከዛው በእስር ይቆያል…ማንም ሰው ምንም ማድረግ አይችልም፡፡››
‹‹አውቃለው…..የእኔ ፍላጎት የሞት ፍርድ ተፈፃሚ እስኪሆንበት ያለው የማረሚያ ቤቱ አያያዝ እንዲሻሻልለት ለመጠየቅ ነው፡፡››
‹‹አዎ አንተን ለማግኘት ከመምጣቴ በፊት ስለአባትህ አጠቃላይ ሁኔታ በመጠኑ ለማጣራት ሞክሬ ነበር፡፡አሁን የታሰረው ጥብቅ በሆነ ጥበቃ ለብቻው መሆኑን ገልፀውልኛል፡፡››አሉን ፊትለፊታቸው የተቀመጠውን የውስኪ ብርጭቆ አንስተው ተጎነጩና መልሰው አስቀመጡት፡፡
ሚካኤልም ‹‹አዎ ያስጨነቀኝ እኮ ያ ነው፡፡››ሲል መለሰላቸው፡፡
‹‹ያ ለምን እንደሆነ መቼስ ታውቃለህ፡፡አባትህ ከሌሎች በእስር ቤት ካሉ ታራሚሆች ጋር በማሰር ከማረሚያ ቤቱ ለማምለጥ ሞክሮ አንድ የፖሊስ አባልና ሁለት እስረኛ ሞተዋል፡፡የዛ ኦፕሬሽን ዋናው ማስተር ማይንድ እና መሪ ደግሞ አባትህ ነበር…ያ ውሳኔ የተወሰነበት ከዛ ክስተት በኋላ ነው፡፡ለፖሊስ መገደል ምክንያት መሆን ምን ያህል ከባድ እንደሆነ መገመት አይከብድህም››
‹‹አዎ አውቃለው…ግን እኮ በጣም ተቀጣ..እዛ ጨለማ ክፍል በሰንሰለት ተጠፍሮ መኖር ከጀመረ ስድስት ወር አለፈው፡፡እሺ ብቻውን ይታሰር….ቢያንስ ከጨለማ ክፍል የሚወጣበትና ከሰንሰለት እስርም የሚገላገልበት እድል ቢኖር፡፡ዋናው ከሰው እንዳይቀላቀልና ተመሳሳይ አይነት የማምለጥ ሙከራ እንዳይሞክር አይደል››ሲል በንግግሩ ቃናም በአይኖቹም ተማፀናቸው፡፡
‹‹ይመስለኛል ..ያም ብቻ አይደለም..በእሱ ምክንያት የሞተው ፖሊስ በወህኒ ቤት ውስጥ በፖሊስችም ሆነ በእስረኞች በጣም ተወዳጅ ስለነበረ….በጓደኞቹ ዘንድ ከፍተኛ ብስጭት ፈጥሯል….እና አንድም በጣም እንዲቀጣ ይፈልጋሉ በሌላ ጎኑም በተግባሩ በተበሳጩ ሰዎች ጥቃት እንዳይደርስበትም ስጋት ስላለ መጠበቅ ይፈልጋሉ፡፡››
‹‹‹አውቃለሁ…ያ ጉዳይ በመፈፀሙ እኔም ከፍተኛ ልብ ስብራት ደርሶብኛል ፣ የሞች ፖሊስ ቤተሰቦች አግኝቼ ለማነጋገር ሞክሬለው፡፡ባለቤቱንና አንድ ልጁን ወዲው ነበር ያገኘዋቸው….እና ምንም እንኳን እሱን መልሼ ላመጣላቸው ባልችልም በኑሮ ግን እንዳይቸገሩ የተቻለኝን እያደረኩ ነው፡፡ለሚስቱ ስራ እንድታገኝ አድርጌለው….የልጁንም ትምህርት ቤት ክፍያ እና አንዳንድ ወጪዎች እየከፈልኩ ነው….ምንም ሆነ ምንም ወደፊትም ያንን ማድረጌን አላቋርጥም፣እባኮት እርሶ በተቻሎት መጠን ይርዱኝ…ምንም አይነት ቤተሰብ እንዳይጠይቀውም ስለተከለከለ እኔ እንኳን ካየሁት ስድስት ወር አልፎኛል…››
‹‹በእውነት እያደረከው ስላለ ነገር ምስጋና ይገባሀል..ትልቅ ሰው ነህ!!እንግዲህ እንዲህ እናድርግ….አንድ አስር ቀን ስጠኝ እና ሁኔታውን በተሻለ ሁኔታ ላጥና..ከዛ ሌሎች ጓደኞቼንም ቢሆን አስቸግሬ ማድረግ የምችለውን ነገር ላስብበትና መልሰን እናውራበት››
‹‹በእውነት በጣም ነው የማመሰግነው…..ምን አልባት ጓደኞቾትን ሲያስቸግሩ የሚያስፈልግ ነገር ካለ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ አሟላለሁ…፡፡››ሲል ቃል ገባ፡፡
‹‹ችግር የለም… የሚስፈልግ ነገር ካለ አሳውቅሀለው….እነደነገርኩህ አንተን እንድረዳህ የጠየቀኝ ሰው በጣም ወዳጄና ባለውለታዬ ነው…..እና በእኔ አቅም ማድረግ የምችለውን ነገር ሁሉ እንደማደርግና የአባትህን በእስር ቤት ውስጥ ያለውን አያያዝ ለማሻሻል ጥረት እንደማደረግ ልገልጽልህ አፈልጋለው…በተለይ አባትህን የመጠየቅ መብትህን መልሰህ እንድታገኝ ማድረግ ምችል ይመስለኛል፡፡››
‹‹አመሰግናለው..ስልኮትን በጉጉት ጠብቃለው፡፡›› በዛው ተለያዩ
////
ፀአዳ በአራተኛው ቀን ስሜቷን አብርዳ….መረበሿን አረጋግታ ልጇን ይዛ መጣች፡፡ከዶዶላ ተመልሳ አዳማ እስክትገባ ስልኳን አልከፈተችም ነበር፡፡ቤቷ ደርሳ አረፍ እንዳለች ከፈተችና ለአዲስ አለም ደወለችላት፡፡
አዲስአለም ከሰላምታ ሳይሆን ከስድብ ነው የጀመረችው‹‹አንቺ ቅሌታም…..ጤነኛ ነሽ ግን?››
‹‹ቀስ …ይሄ ሁሉ ቁጣ ናፍቆት ነው ወይስ ሌላ ምክያት አለው?፡፡››
በስድቧ ገፋችበት ‹‹ወሬኛ ነሽ እሺ…..ለመሆኑ አሁን የት ነሽ?››
‹‹ቤቴ ነኛ››
‹‹ማለት እዚህ አዳማ?››
‹‹አዎ..ምነው ሌላ ቦታ ቤት አለኝ እንዴ?››
‹‹እኔ ምን አውቅልሻለው….ግን ሳስበው በቅርብ አዲስአበባ ላይ ቤት የሚኖርሽ ይመስለኛል….በቃ ጠብቂኝ አሁኑኑ መጣሁ…፡፡››
‹‹ኸረ እኔ ራሴ መጣለሁ…፡፡››
‹‹መጣው እኮ አልኩሽ፡፡››ስልኩን ጠረቀመችባት፡፡
‹‹ዛሬ ልትደበድበኝ ሁሉ ትችላለች››ስትል አሰበችና ከተቀመጠችበት ተነስታ ቤቱን ማስተካከል ጀመረች ..ተዘግቶ ስለከረመ እምክ እምክ ይላል…መስኮቱን ከፋፈተች…ሰንደል ለኮሶችና በየኮርነሩ ላይ ሰካካች… ቡና ለማፍላት ሲኔ ደረደረች፣ከሰል በማቀጣጠል ላይ እያለች አዲስ አለም መጣች፡፡
ጠየቀቻት ካሰበችው ጊዜ በጣም ፈጥና በመምጠቷ ተገርማ‹‹እንዴ ..!!ስትደውይልኝ መንገድ ላይ ነበርሽ እንዴ?››ስትል ….፡፡
ልትስማት ስትጠጋት ወደኃ ሸሸቻትና ገፍትራት ወደቤት ገባች….ፀአዳማ እያቀጣጠለች የነበረውን ከሰል ትታ ከኃላ ተከተለቻት፡፡
‹‹ምስር የታለች?››
‹‹ጎረቤት ልትጫወት ሄዳለች››
‹‹ቆይ አንቺ ግን ያምሻል..?እንዴት አንድ ነር ሳትነግሪኝ ብን ብለሽ ትሔጃለሽ…እሺ መሄዱንስ ሂጂ እንዴትሰ ስልክሽን ትዘጊያለሽ?››
‹‹ስልኬ እኮ ተበላቶብኝ ነው››
‹‹አረ ባክሽ..አሁን እኔን የምትሸውጂኝ ይመስልሻል?››
‹‹‹እሺ በቃ ማንንም ለማውራት ጥሩ ሁኔታ ላይ አልነበርኩም…በፀጥታ ማሰብ ነበር የፈለኩት..በዛ ላይ አንቺ የሰርግና የመልስ ግርግር ላይ ስለሆንሽ ልረብሽሽ አልፈለኩም››
‹‹ወይ ረበሺኝ እኮ..እኔን ብቻ ሳይሆን ባሌንም ጭምር ነው በደንብ የረበሺን፡፡››
‹‹እንግዲህ አዝናለው…..በጣም ይቅርታ›
‹‹ደግሞ ሰውዬሽ..አብዶልሻል….››
‹‹የቱ ሰውዬ?››ግራ በመጋባት ጠየቀች፡፡
‹‹ስንት ሰውዬ ነው ያለሽ…?ዘሚካኤል ነዋ..ከደበቅሺበት ውለጂያት ብሎ ሊያንቀኝ››
‹‹እንዴ ደወለልሽ እንዴ?››
ምን ይደውልልኛል…በዛን ቀን ልክ ያንቺ መልእክት ደርሶኝ እሱን ከሚካኤል ጋር አንብበን እየተገረምን ሳለ ቤት ድረስ መኪናውን እያከነፈ መጣና ሰፈሩን በመኪናው ክላክስ አደበላለቀው…ምን ሆኖ ነው ብዬ ስወጣ መኪና ውስጥ አስገባኝና ከሰፈር ይዞኝ ሄደ….››ብላ የዛን ቀን የሆነውን በዝርዝር ተረከችላት፡፡›
ፀአዳ በሰማችው ነገር በጣም ተገረመች‹‹ፈፅሞ እንደዛ ያደርጋል ብዬ አልጠበቅኩም ነበር…ግፋ ቢል ደውሎ የሆነ ነገር ይልሻል ብዬ ነው ያሰብኩት፡፡››
‹‹ትቀልጂያለሽ እንዴ..?ልጁ እኮ ጨርቁን ጥሎልሻል››
‹‹ማለት?››
‹‹አፍቅሯሻል እያልኩሽ ነው››
‹‹እኔ ፍቅር አልፈልግም››
‹‹እና ወሲብ ነው ምትፈልጊው?

👍71❤19
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ…
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
___
///
‹‹ነይ የኔ ማር፣ ዝም በይ፣ ላደርቅልሽ እፈልጋለሁ።››ራሄል ትሁትን ከመታጠቢያ ገንዳው ውስጥ አውጥታ በፎጣው ጠቀለለቻት።
ወደ ምትሄድበት የስብሰባ ቦታ ፀጋን መውሰድ እንዳለባት ወስናለች፡፡ ህጻኗን ዛሬ ከሰአት በኋላ ለረጅም ሰዓት እንቅልፍ እንድትተኛ አድርጋ ስለነበር ማታ ከሶስት ሰዓት በፊት እንደማትተኛ ታውቃለች። ልብስ ልታለብሳት እየተዘጋጀች ሳለ ሕፃኗ ከንፈሯ ላይ በጥፊ መታቻት። ትልቅ ሰው በጥፊ ያጠናገራት ነው የመሰላት‹‹አንቺ ትንሽ ድርዬ›› ብላ አጉተመተመች፡፡ ‹‹ምን ፈልገሽ ነው የምትደባደቢው?›› ጠየቀቻት፡፡
በዛው ቅፅበት የበሩ ደወል ጮኸ። ለመክፈት ፊቷን ስታዞር የራሄል እግር ይዛ ታገለቻት ሳትወድ በግዷ ጎንበስ ብላ አቀፈቻት፡፡ አሁንም በፎጣው ተጠቅልላለች። ራሄል በረዥሙ ኮሪዶር ላይ ወርዳ የራሷን ክፍል አልፋ ወደ መግቢያ በር ቀረበች። መጥሪያው ከእንደገና ጮኸ…
‹‹መጣሁ፣ መጣሁ››ስትል ራሄል አጉተመተመች፣ አሁንም በደረጃው ላይ ነች።ከታች ስትደርስ የእብነበረድ ወለሉ ቅዝቃዜ በባዶ እግሯ ዘልቆ ተሰማት ፡፡በሩን በዝግታ ከፈተችው።ዶ/ር ኤልያስ ነበረ፡፡
ወደ ውስጥ ስትጋብዘው ተንደርድራ ጉንጩ ላይ ተጣብቃ ልትስመው ፈልጋ ነበር…እንደምንም እራሷን ተቆጣጠረች፡፡
እሱ የፀጋ ሐኪም ብቻ ነው። እሱ የእህቷን ደህንነትን ሊቆጣጠር እናሊከታተል ብቻ ነው ወደቤታቸው የሚመላለሰው ። በማለት እራሷን ለማረጋጋት ጣረች፡፡ የዔሊ ሞቃታማ ሰማያዊ አይኖች ቀና ብላ ስትመለከት፣ውስጧ ተናወጠባት፡፡
‹‹ኤሊ ውሰደኝ…››ትሁት ጮኸች፣
ራሄል እህቷን ችላ ብላ ከኤልያስ ጋር ማውራቷን ቀጠለች፡፡‹‹አንዲት ብዙ ገንዘብ ለፋውንዴሽናችን የምትለግስ ሴት ማግኘት አለብኝ እና ምርጫ ስለሌለኝ ፀጋን ይዣት ልሄድ ነበር ያሰብኩት…ምን ትላለህ?››
‹‹ማታስቸግርሽ ከሆነ ምንም ችግር የለውም….››አላት
‹‹ እሱ የእኔም ስጋት ነው….ድፍረት ካልሆነብኝ ልትረዳኝ ትችላለህ?››
‹‹ለምን አይሆንም?እዚህ ሆኜ እንድጠብቅልሽ ነው የምትፈልጊው?››
‹‹ኮስተር አለችበት‹‹እሱም ይቻላል..ግን አብረኸን ብትሄድና እዛ ሴትዬዋ ጋር በምነጋርበት ሰዓት አንተ ፀጋን ታጫውትልኛለህ ብዬነበር ያሰብኩት…እኔም እንዲህ ሆና ይሆን ከሚል ስጋት ተገላግዬ በተረጋጋ መንፈስ ከሴትዬዋ ጋራ አወራለው››አለችው፡፡
ሳቀባት…….
በሳቁ ግራ ተጋባች‹‹ምነው ያልሆነ ነገር ተናገርኩ እንዴ?››
‹‹አይ…አሁን ኦርጂናል እናት እየሆንሽ እንደሆነ ስለታዘብኩ ነው…እዚህ ለእኔ እንኳን ቢሆን አምነሽ ጥለሻት ልትሄጂ አልፈቀድሽም…በእውነት ደስ ብሎኛል…አብሬችሁ እሄዳለው››
‹‹እሺ ይህችን ልጅ ላልብሳት እና እኔም ለብሼ መጣን ….አስር ደቂቃ ታገሰን››
‹‹ችግር የለም..ሂዱ›› ፈቀደላቸው…ሄለን ፀጋን እንዳቀፈች ወደመኝታ ቤት አመራች፡፡ፀጋን ካለበሰች በኃላ የራሷን ልብስ ቀየረችና መስታወት ፊት ስትቆም ቅድም ፀጋ የመታቻት ከንፈሯ ቀልቶ እና አብጦ ተመለከተች….፡፡
ወደፀጋ ዞራ ልንቦጯን ዘርግታ እያሳየቻት ‹‹ውይ አንቺ ልጅ ….እይው እስኪ ያደረግሺኝን››
ፀጋ እየተመለከተቻት ሳቀችባት፡፡ራሄል ከፍሬጅ ውስጥ በረዶ አወጣችና ያዘችበት፡፡ከዛ ቀይ ሊፒስቲክ አወጣችና በስሱ በመቀባት የቀላውን ከንፈሯን ከሌላው ክፍል ጋር አመሳሰለችው፡፡
ከዛ ዝግጅቷን እንዳጠናቀቀች ከተረዳች በኃላ ቦርሳዋን ይዛ በአንድ እጆ የፀጋን እጅ ጨብጣ ወደሳሎን ሄደች፡፡ተያይዘው ከቤት ወጡ፡፡
ራሄል ከንፈሯን አስጨነቀች፣ ጸጋና መሀከላቸው አድርገው ወደ ራሄል መኪና ሲያቀኑ ልክ በቅርብ የተጋቡ ባልና ሚስቶች ይመስሉ ነበር፡፡ፀጋን ከኋላ በስርዓቱ ቀበቶዋን አሰሩላትና እነሱ ገቢና ጎን ለጎን ተቀመጡ..መኪናውን የምታሽከረክረው ራሄል ነበረች፡፡
ለተወሰነ ደቂቃ በዝምታ ነበር የተጓዙት ያሉት፡፡በፋውንዴሽኑ ውስጥ ስላሏት ችግሮች ለአንድ ሰው መንገር ፈልጋ ነበር። የሮቤል ሚስጥራዊነት አሳስቧታል።ትናንት ማታ አነጋግራዋለች። ለምን ጥሪዋን እንዳልመለሰላት ስትጠይቀው ሞባይሉን ቤቱ ረስቶ እንደነበር ነው የነገራት።በበጎ አድራጎት ድርጅት ውስጥ ያገኘኛቸውን መረጃዋች በማጠናከር ላይ ተጠምዷ ስለነበር ጊዜ አልነበረውም .. እሱ የሚፈልገው አንድ ነገር እንዳለ በግልፅ ነግሯታል….እሷም ልታምነው ፈለገች ነገር ግን አልቻለችም እና ዛሬ ከሰአት በኋላ በፋውንዴሽን ከኮምፒውተሯ ጋር ስትገናኝ፣ ሌላ ሰው የቢሮውን ኮምፒውተር ላይ እንደገባ አስተዋለች። መረጃዋን የሚበረብር ማን እንደሆነ ግራ ተጋብታለች፡፡
የአእምሮዋን ፍጭት ያነበበ ይመስል‹‹የምታናግሪው ሰው አለ?›› ስል ጠየቃት። ራሄል ወደ
‹‹ስለዚህ ነገር በተለምዶ ከአባቴ ጋር ነበር የምንነጋገረው፣ ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ እንደምታውቀው በእናቴ ጉዳይ በጣም የተጠመደ ነው እና እሱን ማስቸገር አልፈልግም።››
‹‹የፋውንዴሽኑ ቦርድ እንዴት ነው? አይረዳዱሽም እንዴ?››
ራሄል አንገቷን በአሉታ ነቀነቀች። ‹‹አይ አሁን ያጋጠመን … ውስጣዊ ችግር ነው እነሱን ወደዚህ ጎትቼ ማስገባት አልፈልግም….እኔ በራሴ በምችለውን መንገድ መፍትሄ መፈለግ አለብኝ››
‹‹ሁሉንም ነገር በራስሽ ብቻ ማድረግ የለብሽም››ኤሊ ተቃወማት ።በዚህ ጊዜ የሚሄዱበት ቦታ ደርሰው መኪናዋን እያቆመች ነበር፡፡
ትንሽ ሳቅ ብላ‹‹በቅርብ ጊዜ ሁሉንም ነገር በራሴ የማደርገው ይመስላል››ስትል ቦርሳዋን አንጠልጥላ ከመኪናዋ ወረደች፡፡ራሄል ከመኪናው ጎን በመጣችበት ጊዜ ኤሊያስ ፀጋን ከታሰረችበት ቀበቶ እየፈታት ነበር። የዳይፐር ቦርሳውን ለራሔል ሰጣት እና በሩን ዘጋው። ራሄል ወደ ወ.ሮ ላምሮት መግቢያ ደረጃ ሲወጡ‹‹ልክ እንደ ትንሽ ቤተሰብ እንመስላለን››ስትል አሰበች።
መግቢያ በራፉ ላይ ደረሱና ደወሉን ተጫኑት፡፡ ‹‹ማግባት ምን አይነት ጣዕም ሊኖረው ይችላል?››እራሷን ጠየቀች፡፡ ጋብቻ ከኪሩቤል በኃላ ያልተጠቀመችበት ቃል ነበር።የስሙ ትዝታ የደስታ ስሜት እንዲሰማት አደረጋት፣ ከዚያም የታማኝነት መጉደል ውስጧን ሲያንቀጠቅጣት ተሰማት። እንዲህ ያሉ የቀን ህልሞችን እንድታልም ስውር ኃይል የነበረው ኪሩቤል ብቻ ነበረች። ከዚህ በፊት ወይም በኋላ ማንም ሌላ ሰው ያንን ስሜት ሊቀሰቅስባት አልቻለም ።
ራሄል ድጋሚ ደወሉን ልትደውል ስትል በሩ በራሱ ተከፈተ። ራሄል ወደ አንድ ትልቅ አዳራሽ መሳይ ሳሎን ውስጥ ገባች ወዲያው ጥርት ያለ ሰማያዊ ቀሚስ የለበሰች ሴት ተቀበለቻት።
‹‹ወ/ሮ ላምሮት ከኋላ ባለው አትክልት ስፍራ እየጠበቀችሽ ነው።››በማለት ዘወር ብላ ወደ ሌላ በር መራቻቸው፡፡ ወደ ዔሊ ተጠግታ በሹክሹክታ ‹‹ፀጋ ከስርህ እንድትርቅ አትፍቀድላት። ››ስትል ተናገረች፡፡ፈገግ አለላት….በፊት ፀጋን በተመለከተ እንዲህ አድርጊላት… ይሄንን ተጠንቀቂላት… እያለ የሚያጨናንቃት እሱ ነበር..አሁን ግን ይሄው በተቃራኒው ለእሱ መመሪያ እየሰጠችው ነው፡፡እያሳየች ባለችው ለውጥ በውስጡ እርካታ ተሰማው፡፡
ወ.ሮዋ ከተቀመጠችበት መድረክ መሳይ ውብ ቦታ ባሻገር በሁለት በኩል በጡብ ግድግዳ የተከበበ አበባ ሞልቶ ነበር። ወ.ሮ ላምሮት በትልቅ ዣንጥላ በተከለለ የመስታወት ጠረጴዛ ጎን ከተቀመጠችበት ልዩ ወንበር ተነስታ ‹‹ ጤና ይስጥልኝ ራሄል …በድጋሚ እንኳን ደህና መጣሽ ›› አለቻት ፡፡

❤60👍3😱2👏1
#ቋጠሮ_ሲፈታ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
፡
፡
///
ፀሀፊዋ አለምን አቁማ ወደዳኛው ቢሮ ተራማዳ በራፉን በጥንቃቄ አንኳኳች እና ወደውስጥ ገባች…ብዙ ሳተቆይ ተመልሳ ወጣችና ወደአለም ቀርባ …በአጭሩ
‹‹ሊያይሽ ተስማምቷል ››አለቻት፡፡
"አመሰግናለሁ።" አለችና እሷን አልፋ ወደ ክፍሉ ገባች።
"ወ.ሮ አለም …በዚህ ጊዜ ስለምንድነው የምታናግሪኝ?" ዳኛ ዋልልኝ ኮቱን ከመስቀያው ላይ እየጎተተ ነበር የሚያናግራት። "ያለ ቀጠሮ ሰው ቢሮ የመግባት መጥፎ ልማድ ያለሽ ይመስላል። እንደምታየው እኔ ልወጣ ነው። ልጄ ስርጉት ያለ እኔ እራት መብላት አትወድም እና እሷን ማስጠበቅ ለእኔ አሳፋሪ ነው።"
"ሁለታችሁንም ይቅርታ እጠይቃለሁ ክቡር ዳኛ… ለፀሀፊዎ እንደነገርኩት ጉዳዬ በጣም አስቸኳይ ስለሆነብኝ ነው ።"
"እሺ…ልስማው?"
"መቀመጥ እንችላለን?"
" ቆሜ መስማት እችላለሁ …ምን ልትነግሪኝ ፈልገሽ ነው?"
"የእናቴ አስከሬን ተቆፍሮ እንዲወጣ እና ዳግም የፎረንስክ ምርመራ እንዲደረግበት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲሰጡልኝ እፈልጋለሁ."
ዳኛው ቀስ ብሎ ወንበሩ ላይ ተቀመጠ። አለም ግልፅ የሆነ ጭንቀት ተመለከተችበት።
"ይቅርታ፣ ምን አልሺኝ?፧"
"ክቡር ዳኛ ያልኩትን እንደሰሙኝ አምናለሁ፣ ግን ጥያቄዬን መድገም አስፈላጊ ከሆነ፣ አደርገዋለሁ።"
ዳኛው እጁን አወዛወዘ። "አይ. ቸሩ ጌታ አይሆንም. አንድ ጊዜ መስማት በቂ ነው…ለምን እንዲህ አይነት አስቀያሚ ነገር ማድረግ ፈለግሽ?"
"የመፈለግ ጉዳይ ሳይሆን ግድ ሆኖብኝ ነው, በጣም አስፈላጊ ነው ብዬ ባላምን ኖሮ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አልጠይቅም ነበር."
"አስቲ ተቀመጪና… ምክንያቶችሽን አስረጂኝ።››
"እናቴ ላይ ወንጀል ተፈጽሟል ፣ነገር ግን ትክክለኛው ፍርድ ተገኝቷል ብዬ አላምንም ።"
"እንደዛ ማድረግ አትችዬም " ብሎ ጮኸ።
"አልሰማሽም።ከአመታት በኃላ ድንገት ከመሀከላችን ተገኘሽ፣ ወዲያው መሠረተ ቢስ ውንጀላ ይዘሽ ትረብሺኝ ያዝሽ፣ ለበቀል ቆርጠሻል።"
"ይህ እውነት አይደለም" ስትል ለመከላከል ሞከረች ፡፡ " ለመሆኑ ሀለቃሽ ግርማ ስለዚህ ጉዳይ ምን ይላል?"
"አሱ ለጊዜው የለም ..ለጥቂት ቀናት እረፍት ወሰዶ ወደ አዲስአበባ የሄደ ይመስኛል።›› ዳኛው ተናደደ።
" ለማንኛውም ጥያቄሽ … ጥሩ ሀሳብ አይመስለኝም››
" ክቡር ዳኛ ማስረጃ እንድፈልግ ይፈቅዱልኛል?"
"ምንም ማስረጃ አታገኚም" ሲል አፅንዖት ተናገረ፡፡
"ከእናቴ አስከሬን የተወሰነ መነሻ ሚሆነን መረጃ ልናገኝ እንችላለን."
" የተገደለችውና ሬሳዋ የተገኘው እኮ ከዛሬ ከሃያ አምስት ዓመታት በፊት ነበር ።"
"በዚያን ጊዜ ለሬሳ ምርመራ ለማድረግ ቴክኖሎጂዎች አልነበሩም… ..በአሁኑ ጊዜ ግን ነገሮች የተለዩ ናቸው፡፡እኔ በግሌ ጎበዝ የተባለ የፎረንሲክ ስፔሻሊስት አውቃለሁ።አሁን ለሚከሰቱ የወንጀል ድርጊቶች በተደጋጋሚ ጊዜ ከእሱ ጋር የመስራት እድል ነበረኝ …እሱና ጎደኞቹ በጣም ውጤታማ ናቸው ..በዛን ወቅት ባለው ቴክኖሎጂ ሊገኝ ያልቻለ የሆነ ነገር ሊያገኝልን እንደሚችል ዋስትና እሰጥዎታለሁ።››
"ጥያቄሽን እንደጥያቄ እወስደዋለሁ።››
"መልሱ ለዛሬ ማታ ቢደርስልኝ ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው ።"
" ይቅርታ ወ/ሪት አለም ማድረግ የምችለው በአንድ ጀምበር አስብበት እና በጠዋት መልሱን እሰጥሻለው።እስከዛው ሀሳብሽን ለውጠሽ ጥያቄውን እንደምትሰርዢ ተስፋ አደርጋለሁ።"
"አላደርገውም።››
ዳኛው ከተቀመጠበት ተነሳ። "ደክሞኛል፣ በዛ ላይ ርቦኛል፣ እናም በዚህ የማይመች ቦታ ላይ ስላስቀመጥሺኝ ተበሳጫችቻለሁ።" የክስ አመልካች ጣት አነጣጥሮባት። "እኔ እንደህ አይነት የተጨመላለቀ ነገር አልወድም."አላት፡፡
" ይህ በጣም አስፈላጊ ባይሆን እኔም አላደርገውም ነበር."
"አስፈላጊ አይደለም."
"እኔ ደግሞ እንደሆነ አምናለሁ" ስትል በግትርነት መለሰች።
" አሁን፣ በቂ ጊዜዬን ወስደሻል። ይሄኔ ልጄ ስርጉት ተጨንቃለች።››
‹‹ ደህና ይሁኑ ብላ ።"ከክፍሉ ወጣች።
///
አለም ቀጥታ ወደመኪናዋ አመራችና ወደቤቷ ነው የነዳችው… መንገድ በትራፊክ ስለተጨናነቀ ወደቤቷ ለመመለስ ረጅም ጊዜ ነበር የወሰደባት፡፡
ክፍሏ ገብታ አልጋዋ ላይ ተዘርራ ትንሽ እረፍት ለመውሰድ ሞከረች…ከዛ ተነሳች….ማስታወሻዎቿን እንደገና ለመገምገም ሞከረች….ወዲያው ሰለቻት፡፡ ቴሌቪዥኑን ለመክፈት ወሰነች። ሪሞቷን አነሳችና ከፈተች፡፡ፊልም ላይ አደረገችውና ሰውነቷን ለመለቃለቅ ልብሷን አወላልቃ ወደሻወር ቤት ሄደችና መታጠብ ጀመረች……ታጥባ ከመጨረሷ በፊት አንድ ሰው በሯን ሲያንኳኳ ሰማች… እርጥብ ፀጉሯን በፎጣ ጠቅልላለች። ረጅምና ነጭ ካባዋን አደረገችና እና ወገቧ ላይ ያለውን መቀነት ለማሰር እያስተካከለች ወደሳሎን ሄደችና በበራፉ ቀዳዳ በማጮለቅ ማንነቱን ለማረጋገጥ ሞከረች፡፡
የሰንሰለት መቆለፊያው እስከሚፈቅደው ድረስ በሩን ከፈተችው "እንኳን ደህና መጣህ ኩማንደር ምነው በሰላም?"
ኮስተር ብሎ"በሩን ክፈቺ" አላት
"ለምን?"
" ካንቺ ጋር መነጋገር አለብኝ።"
"ስለ ምን?"
‹‹ወደ ውስጥ ካስገባሺኝ እነግርሻለሁ።
አለም አልተንቀሳቀሰችም."በሩን ልክፈት ወይስ ምን?"እለች ከራሷ ጋር ሙግት ገባች፡፡ግድግዳ ላይ የተንጠለጠለውን ሰዓት ተመለከተች….ለሶስት እሩብ ጉዳይ ይላል፡፡
"እዚያው ሆነህ ላናግርህ እችላለሁ።"
"በሩን ክፈቺ" ብሎ ጮኸ።
‹‹ሰውነቴን እየታጠብኩ ነበር."አለም ሰንሰለቱን አላቀቀችና በሩን ከፍታ ወደ ጎን ቆመች።
"አንድ ሰው እየጠበቅሽ ነበር?"
"አይደለም."
ኮፍያውን ከጭንቅላቱ አወለቀና ጠረጴዛው ላይ አስቀምጦ … ወደ ወንበር ሄዶ ተቀመጠ እና ወደ ቴሌቭዥን ስክሪን ተመለከተ፣ ልብስ ያልለበሱ ጥንዶች ተቆላልፈው ይሳሳማሉ ። ካሜራው የወንዱ ከንፈር ከሴቷ ጡት ጋር ሲጣበቅ እያሳየ ነው፡፡
"ስለአቋረጥኩሽ መናደድሽ አይገርምም።››አላት ሪሞቱን አነሳችና አጠፋችው "አያየሁት አልነበር."
"በራፍሽን ለሚያንኳኳ ሰው ሁል ጊዜ በርሽን ትከፍቺያለሽ?"
"በዚህ ከተማ ውስጥ ከፍተኛው የህግ አስከባሪ የፖሊስ መኮንን ነህ። አንተን ማመን ካልቻልኩ ማንን ማመን እችላለሁ?ይልቅ በዚህ ማታ ለምን መጣህ? እስከ ጠዋት ድረስ መጠበቅ አልቻልክም?"
"ዳኛ ዋልልኝ ደውሎልኝ ስለጠየቅሽው የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ነገረኝ.››
በንዴት ሲመታ የነበረው ልቧ በፍጥነት ቀዘቀዘ፣ "በዚህ ከተማ ውስጥ የግል የሚባል ነገር የለም ማለት ነው?"ብላ ጠየቀች፡፡
"ብዙ አይደለም"
"በከተማው ክልል ውስጥ ያለ ማንኛውም ሰው የእናንተ ቡድን ሳይፈቅድለት ማስነጠስ የሚችል አይመስለኝም።"
"እንደፈለግሽ ተርጉሚው …አንቺ ዙሪያችን እየተሸከረከርሽ ጉድጓዳችንን ስትቆፍሪ ምን እንድናደርግ ጠብቀሽ ነበር?"
"የእናቴን መቃብር እንዲከፈት ማድረግ ትክክለኛ የግድያዋን መንሴ ለማወቅ ወሳኝ እርምጃ ነው ብዬ ባላስብ ኖሮ የምረበሻት ይመስላችኋል?" ሞቅ ባለ ስሜት ጠየቀች ።
‹‹አንቺ ቋሚንም ሆን ሟችን ከመረበሽ ውጭ ምን ስራ አለሽ?››
"አምላኬ ሆይ ጥያቄውን ማቅረብ እንኳን ቀላል ብሎኝ ያደረኩት ይመስልሃል? እና ዳኛው ከ አንተ እና ከሰዎች ሁሉ ጋር መማከር ለምን አስፈለገው?"
‹‹ለምን ብለሽ ትጠይቂያለሽ እንዴ?… ተጠርጣሪ ስለሆንኩ ነዋ?"
"ዳኛው በዚህ ጉዳይ ከአንተ ጋር መወያየቱ ሞያዊ ሥነ ምግባር የጎደለው ሽማግሌ መሆኑን ነው የሚያሳየው "
"እኔ እኮ የከተማው ፖሊስ አዛዥ ነኝ፣ አስታውሺ?"

❤39👍4