#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)
፡
፡
#ክፍል_አስር
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ከዛ በኃላ ኑሀሚ በመገረም እንደተዋጠች ፊቷን አዙራ ወደወንድሟ ነበር የተመለሰችው፡፡ እንደደረሰች ጆንያውንና አሮጌ ብርድልብሱን ገለጠችና ወንድሟ እቅፍ ውስጥ ገባች፡፡
‹‹ምነው አኮረፍሽ?››
‹‹አረ ይህቺ ደነዝ ነች…ጭራሽ ታሾፋለች፡፡››
‹‹ይገልሻል አላልሻትም?››
‹‹አይገባትም አልኩህ እኮ …የጨለለች ሳትሆን አትቀርም ፡፡››
ወዲያው ንግግራቸውን ሳያገባድዱ ነበር የቾንቤ ድምፅ የተሰማው .. እያጓራና እየለፈለፈ ወደእነሱ እየቀረበ ነበር…‹‹ተሸፋፈኚ ..ተሸፋፈኚ….››ናኦል እህቱን አስጠነቀቀ፡፡ሁለቱም ተሸፋፈኑና አይኖቻቸውን በብርድልብሱ ቀዳዳ አጨንቁረው የሚሆነውን ለመመልከት ዝግጁ ሆኑ፡፡እንደጠበቁት ቾንቤ እየለፈለፈና እየፎከረ ቀጥታ ወደልጅቷ ነበር የሄደው፡፡ዘና ብላ ከተቀመጠችበት ነቅነቅ ሳትል እየጠበቀችው ነበር፡፡
‹‹ወንድሜ አለቀላት..ስታሳዝን››ኑሀሚ በቀጣይ የሚሆነውን እየገመተች ተሸማቀቀች፡፡
ቾንቤ ደረሰባትና ዘፍ ብሎ ስሯ ቁጭ አለ፡፡ያ ሁሉ ሲሆን ከልጅቷ ምንም አይነት እንቅስቃሴ እየታያቸው አልነበረም ፡፡
‹‹ምንም እየተንቀሳቀሰች እኮ አይደለም፡፡››
‹‹አዎ መሞት እንደምትፈልግ ነግራኛለች…እንዲገድላት ነው የምትፈልገው፡፡›› ከልጅቷ ጋር ባደረገችው ንግግር የገባት የመሰላትን ለወንድሟ አብራራችለት፡፡
ቾምቤ ሲያቅፋት ተመለከቱ…ወደኃላ ሊያስተኛት እየሞከረ ነበር፡፡ከዛ እጇን አዙራ ስታቅፈው አዩ…..‹‹እንዴ ልጅቷ እራሷ መከካት ፈልጋለች መሰለኝ?›› ናኦል ነበር ተናጋሪው፡፡
ቀስ ብላ ወደኃላ አስተኛችውና እሷ ተነስታ ቆመች፡፡ከዛ ልብሷን ረገፍ ረገፍ አደረገችና ስሯ የነበረውን አንድ ጥቁር ፔስታል ይዛ ሁለት ሜትር ያህል ከእሱ ራቅ አለችና ተቀመጠች..ቾምቤ እንደተዘረረ ነው..እየተንቀሳቀሰ አይደለም፡፡››
‹‹ወይኔ አይንቀሳቀስም እኮ፡፡››
‹‹ምን አደረገችው?››
‹‹እኔ እንጃ…ሁለቱም ከተሸፋፈኑበት ገልጠው ወጡ፡፡አስር ደቂቃ ያህል ጠበቁ….፡፡ምንም የተለየ ነገር እየታያቸው አልነበረም…፡፡እንደውም ልጅቷ ከፔስታሏ ውስጥ ሻርፕ ነገር አውጥታ ፊቷን ተሸፋፈነችና ሸርተት ብላ ግንቡን ተደግፋ እንደመተኛት አለች፡፡
‹‹እንዴ ገደላት ስንል ገደለችው እንዴ….?››እሱ የለበሰውን ከላዩ ገፎ ተነሳ
‹‹ወዴት ነው?››ኑሀሚ ጠየቀችው፡፡
‹‹ …ሄጄ ላጣራ?›››
‹‹ቆይ አብረን እንሂድ ፡፡››አለችና እሷም ተነሳች፡፡ፈራ ተባ እያሉ ተጠጉ፡፡ ደረሱ…. ቾምቤ እጥፍጥፍ ብሎ እንደተኛ ነበር፡፡
‹‹እ ጩጬዎቹ ምንነው?››
‹‹ደየመብሽ እንዴ?››ናኦል ፈራ ተባ እያለ ጠየቃት፡፡
‹‹ጎንበስ ብለህ እየው…..እኔ እንዲተኛ ብቻ ነው ያደረኩት፡፡ሞቶም ከሆነ የእኔ የእጅ የለበትም፡፡››
‹‹ካራቲስት ነገር ነሽ እንዴ..?እንዴት አድርገሽ ቆለፍሽው?››
ናኦል ጎንበስ አለና ትንፋሹን አዳመጠው፡፡እውነትም አልሞተም፡፡ ትንፋሹ በደንብ ይሰማል፡፡
‹‹አይ ሰላም ነው፡፡››
‹‹ኑ እስቲ ከጎኔ ተቀመጡ፡፡››
ሁለቱ ታዳጊዎች እርስበርስ ተያዩ፡፡ የዚህችን እንግዳ ሴት ግብዣ እንቀበል ወይስ ይቅርብን ሚለውን በአይን እየተነጋገሩ ይመስል ነበር፡፡ከዛ እንደተግባባ ሰው ወደእሷ ቀረቡና እሱ በቀኟ እሷ ደግሞ በግራዋ በኩል ተቀመጡ፡፡
‹‹እዚህ ቆያችሁ…ማለቴ በርንዳ ላይ?››ጠየቀቻቸው፡፡
‹‹አዎ አንድ አመት ሊሞላን ነው፡፡››
‹‹ታዲያ አይተናኮሏችሁም…በተለይ አንቺን፡፡››
‹‹አይ እንደመጣን ሰሞን ያስቸግሩን ነበር..ግን እዛ ፖሊስ ጣቢያ የሚሰራ ፓሊስ አባታችንን በደንብ ያውቀው ነበር..እና እዚህ ሰፈር ላሉት ጉልቤዎች በጠቅላላ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷቸዋል፡፡አንድ ሰው እኛን ቢያጠቃ ሁሉንም እንደሚያጠፋችው ስለነገራቸው አይነኩንም፡፡››በሰላም እየኖሩ ያሉበትን ምክንያት በግልፅ አብራሩላት፡፡
‹‹ለጊዜው ጥሩ ነው..ግን እዚህ ጎዳና ላይ እስከኖራችሁ ድረስ በሌላ ሰው ላይ ተማምናችሁ እስከመጨረሻው ከጥቃት ተጠብቃችሁ መኖር አትችሉም፡፡ያላችሁት ፖሊስ አዛዥ የመንግስት ቅጥረኛ ነው፡፡መንግስት ደግሞ ነገ ተነስቶ ሌላ ወረዳ ወይም ሌላ ከተማ ሊመድበው ይችላል፡፡የዛን ጊዜስ ምን ትሆናላችሁ?››በውድቅት ለሊት ቀን እንኳን ቢሆን መመለስ ሚከብድ ጥያቄ ነበር የጠየቀቻቸው፡፡፡
‹‹እውነትሽን ነው..ይሄ ጉዳይ ሁሌ ያስጨንቀኛል….ለእኔ ሳይሆን ለእህቴ?››የሚል መልስ እንደሰጣት ያስታውሳል፡፡
‹‹እንዴ እንዲህ እንደምታስብ እኮ አንድም ቀን ነግረኸኝ አታውቅም…?›› ኑሀሚ በጭለማው ውስጥ አፈጠጠችበት፡፡
‹‹እንዴት እንዲህ ብዬሽ እንድትፈሪ አደርጋለሁ?››
ልጅቷ ቦርሳዋን በረበረችና ትንሽ የመጠጥ ብልቃጥ በማውጣት ክዳኑን አሽከርክራ ከፈተችና ተጎነጨችለትና መልሳ በመክደን ከፊት ለፊቷ አስቀመጠች፡፡
‹‹የት ነበርሽ..?ማለቴ እዚህ ሰፈር እንዴት ልትመጪ ቻልሽ?››
‹‹እንዲሁ በዚህ ሳልፍ ሰፈሩ ደስ አለኝና እዚሁ አረፍ አልኩ፡፡››
‹‹እና ነገ ትሄጂያለሽ ማለት ነው?››
‹‹እኔ እንጃ… ሂጂ ሂጂ ካለኝ እሄዳለሁ፡፡››
ናኦል‹‹ብትቆይ ግን ደስ ይለኛል፡፡›› አላት፡፡እንደዛ ያላት ልጅቷ በእድሜ በጣም ታላቁ ብትሆንም ገና እንዳያት በጣም ስለወደዳት ነበር…የዛን ጊዜ ስለእሷ የተሰማው ስሜት ዛሬም ድረስ በልቡ ላይ ተቋጥሮ እንደቆረቆረው ነው፡፡
ዞር ብላ አየችውና እጆቾን ዘርግታ ፀጉሩን እያሻሸች‹‹ጎረምሳው…ተከየፍክብኝ እንዴ?››ነበር ያለችው፡፡
እንደማፈር አለና …አቀርቅሮ ዝም አላት፡፡በወቅቱ ብዙ ነገር ሊመልስላት ፈልጎ ነበር፡፡ግን ከንፈሮቹ ተነቃንቀው ቃላት ከአንደበቱ ማውጣት አልቻሉም፡፡
‹‹አይዞኝ ስቀልድ ነው፡፡ለማንኛውም አሁን ሂዱና ተኙ፡፡.ነገ እናወራለን፡፡››
‹‹እሺ›› አሉና ሁላቱም ከግራና ከቀኞ ተነስተው ባዶ መሬት ላይ ዘና ብሎ በመዘረጋጋት ተኝቶ እያንኳራፋ ያለውን ቾንቤን በጎሪጥ እያዩ በስሩ አልፈው ወደመኝታቸው ሄዱ፡፡ኑሀሚና ናኦል ጥዋት ተነስተው አካባቢውን ሲቃኙ የለሊቷ ልጅ ተነስታ ልክ እንደደላው የቤት ልጅ ስፖርት እየሰራች ነበር ያገኞት፡፡…ሳንቾ በአካባቢው የለም፡፡ሌሎች ጓደኞቻቸው የተወሰኑት ተኝታዋል…የተቀሩትም ወደሚሄድበት ሄደዋል፡፡ለብሳው ያደሩትን አሮጌ ብርድልብስ እና ጆንያ ከስር የሚያነጥፉትን ካርቶን ስብስበውና አጣጥፈው ወደጥግ በማድረግ ዘወትር እንደሚያደርጉት በላዩ ላይ ድንጋይ ጭኑበት እና ወደልጅቷ ሄዱ ፡፡
‹‹እ ጩጬዎች ..ተነሳችሁ፡፡››በሚል ጥያቄ ነበር የተቀበለቻቸው፡፡
‹‹አዎ…ቡሌ ፍለጋ ልንሄድ ነው… ትመጪያለሽ?››
‹‹አዎ…››አለችና እስፖርቷን አቋርጣ ..ፔስታሏን ያዘችና ተከተለቻቸው፡፡
‹‹እ የት ነው ምንበላው?
ሁለቱም አፍጥጠው አዮት‹‹እንዴ ገና ሆቴል ሄደን ተመላሽ ጠይቀን ነዋ››ኑሀሚ ነበረች በመኮሳተር የመለሰችላት፡፡
‹‹አይ ብር አለኝ ..ለምን ገዝተን አንበላም…፡፡››
ሁለቱም በደስታ ፈገግ አሉ…‹‹ስንት አለሽ..?››ናኦል ነበር ጠያቂው፡፡
‹‹ጅንስ ሱሪ ኪሷ ውስጥ እጇን ሰደደችና ሁለት መቶ ብር መዛ አወጣች…››
‹‹አይበቃም…››
‹‹አረ ይበቃል..ነይ ዝናሽ ጋር እንሂድ፡፡››
‹‹ዝናሽ ማነች…?››

👍68❤9👎1
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)
፡
፡
#ክፍል_አስር
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
ሀሳቧን ሳትጨርስ ፊራኦል ከውጭ ስልኩን እየጎረጎረ መጥቶ ፊት ለፊቷ ቁጭ አለ…ለረጅም ደቂቃዎች አላናገራትም …
‹‹ይሄን ያህል ምን ቢመስጥህ ነው?››
‹‹ባክሽ የድሮ መስሪያ ቤቴ..ማለቴ ቆርቆሮ ፋብሪካ ምናምን ብዬ አውርቼሽ ነበር አይደል?››
‹‹እ..ስለምትናፍቅህ ልጅ እያወራኸኝ ነው?››
‹‹አዎ ..ትክክክል?››
‹‹እና እሷ ምን ሆነች?››
‹‹እባክሽ ጠፋች…አንድ ብቸኛ ልጃቸው ጠፋችባቸው…ከዛሬ ነገ አገኛታለሁ ብዬ ስቃትት የእህቴንም ልብ ይዛ ጠፋች››
‹‹ጠፋች ማለት?››
‹‹እኔ እንጃ ..ዛሬ ሶስተኛ ቀኗ ነው…ማህበራዊ ሚዲያው ሁሉ ስለእሷ ነው የሚያወራው››
‹‹ስለጠፋች ብቻ?››
‹‹አዎ አባትዬው ያለችበትን ለጠቆመ 5 ሚሊዬን ብር በሽልማት መልክ እክፍላለሁ ብሎ ስላሳወጀ ምድረ ዱርዬ ጠቅላላ መንገድ ላይ ያገኞትን ወጣት ሴት ሁሉ እያስቆሙ ከእሷ ፎቶ ጋር ማስተያያት ጀመረዋል፡፡››
‹‹እየቀለድክ መሆን አለበት?››
‹‹እውነቴን ነው…አታይውም እንዴ..?››ብሎ ስልኩን አቀበላት… ማህበራዊ ሚዲያውን የተቆጣጠረውን ሁለት ሶስት ፎቶዋን አየች…ውስጧን በረዳት…ግማሽ ፊቷ በፋሻ የተሸፈነ ቢሆንም አስተውሎ ያያት ሰው ሊለያት ይችላል…ፊቷ የተቀመጠው ፊራኦል እስከአሁን እንዴት እንዳለያት ተደንቃለች፡፡
ስልኩን መለሰችለት‹‹ምን ሆና ይሆን …..?የሀብታም ልጅ ነገር ይሄኔ ቀብጣ ሊሆን ይችላል?››ስትል አፏ ላይ እንደመጠላት ተናገረች፡፡
‹‹አይ እንደዛ እንኳን ብሎ ድምዳሜ ላይ መድረስ አይቻልም…እሷ የሀብታም ልጅ ስለሆነች ነገሩ ጮኸ እንጂ በየቀኑ እኳ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች እዚህም እዛም ከያሉበት ተወስደው የሚጠለፉበት…በሰው ሚሊዬን ብር የሚጠየቅበት ሀገር ነው እኮ ያለነው….ስንቶች የተጠለፈባቸውን ልጃቸውን ወይም ባላቸውን ለማስመለስ ቤታቸውን ሸጠዋል…?ስንቶች የመኪናቸውን ሊቭሬ አስይዘው አራጣ ተበድረዋል….?.ንብረቱን አሟጦ ሸጦ ከከፈለስ በኋላ ስንቱ ሬሳ ተልኮለታለል…….እዚህ አገር በዚህ ጊዜ እየሆኑ ያሉትን ነገሮች እንኳን ለማውራት ለማሰብም ይከብዳ…እና ይህቺ ልጅ ምን እንደገጠማት ማንም የሚያውቅ የለም….፡፡››
‹‹እንዲህ አይነት ነገር መኖሩን አላውቅም››
‹‹እንዴ!! ሀገር ውስጥ እየኖርሽ አልነበረም እንዴ…..?ክፍለሀገር ያለች የእናቱን ሞት ሰምቶ ሄዶ መቅበር ያልቻለ ስንት አለ….?ዘመድ ከዘመድ ከተቆራረጠ እኮ ቆየ፣ስንቱ የትውልድ አካባቢውን ሄዶ ለማየት ልክ እንደአውሮፓና አሜሪካ እንደመሄድ ከባድና የማይቻል ሆኖበታል…እና የዚህች ልጅ ቤተሰብ ጭንቀታቸውን ተመልከቺ…ስንቱን ያስባሉ… እህቴ ብትሆንስ ብዬ ሳስብ ዝግንን ይለኛል…እንደውም በቀደም የሰማሁትን ታሪክ ላጫውትሽ…››
በጉጉት ትኩረቷን ወደእሱ አቅንታ‹‹እሺ እየሰማሁህ ነው..››አለች ፡፡
ከአስር ወራት በፊት አዳማ አካባቢ ካለ አንድ የጠበል ቦታ ታጣቂዎቹ ድንገት ይመጡና የተወሰኑ ሰዎች አፍነው ይወስዳሉ፡፡ከተወሰዱት ውስጥ አንዱ ከአርሲ አካባቢ ነው የመጣው…የተጠየቀውን ብር ወላጆቹ በቀላሉ ማሟላት አይችሉም ቢሆንም ተለምኖና ከየሰው ተለቃቅሞ ከተጠየቀው ሩቡን ያህል ብር ለታጣቂዎች ይላክና የልጁ መለቀቅ ይጠበቃል..ግን ከዛሬ ነገ ይመጣል ሲባል ወራቶች ያልፋሉ፣..እናት እንቅልፍ ታጣለች…ቀንና ለሊት ማልቀስ ይሆናል ስራዋ…ልጇ ይኑር ይሙት የምትጠይቀው ሰውና የምታጣራበት መንገድ አልነበራትም…በመጨረሻ ሰው መፍትሔ ያለውን ይነግሯታል…የሞተ ሰው ነፍስ ጠርተው የሚያናግሩ ሰዎች ጋር ይዘዋት ይሄዳሉ…እንደተባለውም የልጇ ነፍስ ሲጠራ ይመጣል..‹‹አዎ እማዬ እኔ ልጅሽ ከሞትኩ 6 ወር አልፎኛል….እርምሽን አውጪ ይላታል››እናትም ወደቤቷ ተመልሳ ድንኳን ጥላ የልጇን እርም ታወጣለች…ዘመድ አዝማድ ሁሉ ለቅሶ ደርሶ እርማቸውን ያወጣሉ..በጣም የሚገርመው ምፀት ደግሞ ምን መሰለሽ እሷን ለቅሶ ለመድረስ ከሚመጡት የቅርብ ዘመዶቾ ውስጥ ሶስቱ ዳግመኛ በታጣቂዎች ተጠልፈው አረፉት፡፡››
ንግግሩ ይበልጥ ሆድ እንዲብሳት አደረጋት..እንባዋን ሊዘረገፍ ሲተናነቃት ተሰማት..
እሱ ንግግሩን ቀጠለ…‹‹አባዬ ይሄንን ባይሰማ ደስ ይለኛል…ከሰማ በጣም ነው የሚያዝነው….እሷን ሰፈራቸው ድረስ እየሄደ ከመኪና ስትወርድና ከቤት ስትወጣ እንደሚያያት አውቃለው…ልጄን በውስጧ ይዛለች..እሷን ሳያት ልጄ በከፊልም ቢሆን በህይወት እንዳለች ይሰማኝና እፅናናለው ይላል…ይገርምሻል እኔ እራሱ እንዲዚህ እንዳስብ ተፃዕኖ ያደረገብኝ እሱ ነው››
‹‹ይገርማል ….ግን ጋሼ ምን በሩቅ አሳያቸው ማለቴ እቤት ገብተው ቢያዮት እኮ ሰዎቹ የሚቃወሙ አይመስለኝም፡››
አዎ እንዳልሽው አይቃሙም ይሆናል..ግን አባዬ እኛን ፊት ለፊታቸው ካዩ ይሳቀቃሉ…ልጅቷ ፊት ከቀረብን ማልቀሳችን አይቀርም.. እሷ ፊት ማልቀስ ማለት ደግሞ ልጅቷ ልክ በሌላ ሰው ህይወት እንደምትኖር እንድታስብ ማድረግና ልጅቷን መጉዳት ነው….ሁላችንም ከእሷም ሆነ ከቤተሰቡ በስህተት እንኳን መገናኘት የለብንም ብሎ ቁርጥ ያለ ትዕዛዝ ለሁሉም አስተላልፏል…እኔንም ከዛ ፋብሪካ ስራዬን ጥዬ እንድወጣ ያስገደደኝ በዛ ምክንያት ነው፡፡አሁን አሁን ግን ያንን የእሱን ትዕዛዝ ለመጠበቅ እየተቸገርኩ ባለሁበት ሰዓት ነው…ይሄው አንደምታይው ልጅቷ የጠፋችው…››
‹‹‹በቃ ደከመኝ መሰለኝ ትንሽ ልተኛ ››ብላ አልጋ ልብሱን ወደላይ ሳበችና ሙሉ በሙሉ ተሸፈነችና ..በፀጥታ እንባዋን ዘረገፈች…አባትና እናቷ አሳዘኗት….ቢሆንም ለአመታ ያበሳጮትን ብስጭት ልትረሳላቸው አልቻለችም….በውሳኔዋ ፀንታ እስከመጨረሻው መቆየት እንዳለባት ዳግመኛ ወሰነች፡፡‹‹አዎ አሁን እያዩት ያሉት ስቃይ ይገባቸዋል››በማለት በረጅሙ ተነፈሰች፡፡
////
ሰለሞን በሶስተኛው ቀን አርፍዶ ሶስት ሰዓት አካባቢ ወደቢሮ እየሄደ ሳለ ስልኩ ጠራ…የማያውቀው አዲስ ቁጥር ነው…አነሳው፡፡
‹‹ኪያ የፍቅርና የጋብቻ አማካሪ ነው፡፡››ድርጅቱን ኪያ ብሎ የሰየመው አስቴርን ለማስደሰት ስለፈለገ ነበር…አስቴር እናቷ ከመሞታቸው በፊት ‹‹ኪያ ›› እያሉ ነበር የሚጠሯት እሱም አልፎ አልፎ ይሄንን ስም ይጠቀማል…ድርጅት ለመመስረት ሲያስብ ግን ወዲያው በምናብ የመጣለት ስም ይህ ኪያ የሚለው ስም ነው፡፡እንደምንም ብሎ አግብቶ ከእሷ ጋር አንድ ቤት መኖር ሲጀምሩ ደግሞ ሙሉ በሙሉ በወጥነት ኪያ የሚለውን ስም ይጠቃማል..ሚስቱም ሆነ ድርጅቱ በአንድ ስም ይጠራሉ…ይህ ነው እቅዱ፡፡
ሴሎቹ ሁሉ ተነቃቁ…‹‹በስተመጨረሻ ተሳካ…በስተመጨረሻ የመጀመሪያ ደንበኛዬን አገኘሁ….‹‹ሰሎሞን ጀግና ነህ፣›››ብሎ ተደሰተና ድምፁን ጎርነንና ሻከር አድርጎ፡፡‹‹አዎ ትክክል ኖት..ምን ልታዘዝ?፡፡››ሲል መለሰ፡፡
‹‹እባኮት የቢሮዎትን ትክክለኛ አድርሻ ላስቸግሮት…?››
‹‹ሜክሲኮ ኬኬር ህንጻ 3ተኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102 ፡››
‹‹አመሰግናለው ..ከ15 ደቂቃ በኃላ ደርሳለሁ›› ስልኩ ተዘጋ፡፡
እሱ ደግሞ ቢሮ ለመደርረስ 5 ደቂቃ ብቻ ነው የሚቀረው..

👍81❤9
#የጣት_ቁስል
፡
፡
#ክፍል_አስር
፡
፡
#ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ
አንድ አይጠጣም
የወጣት ሰውነቱ ፣ ለግላጋ ቁመናው ፣ ተቀያይሯል፡፡ ከአሁን በፊት ያልነበረውን ፂም አውጥቷል፡፡ ታዲያ በጉንጮቹ ላይ ግራና ቀኝ የወረደው አሪዝ መሳይ ፂሙ ጳጳስ አስመስሎታል፡፡ እንኳን ለማያቀው ለሚያውቀውም ሰው ተመስገንን መለየት ያስቸግር ነበር፡፡
ምግብ አዝዘው እየበሉ ነው፡፡ መብላቱን ተወት አድርጎ በሆቴሉ ዲም ላይት ይገረማል፡፡
"ከተሜ ማለት እንደ ዚህ ነው እንዴ"? አለ ተመስን፡፡
የተለየ ነገር አየህ"? አለው ያሬድ፡፡
"እኛም አገር ነጫጭ ሰው አስተናጋጅ ሆኖ ሳይ ነው"፡፡
"ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ………...ትገርማለህ የአገርህን ሰው እንኳን መለየት አቃተህ፡፡ እነዚህ እኮ የእኛ አገር ሰዎች ናቸው፡፡ ቅባት ስለተቀባቡ ነው፡፡ ነጭ የመሰሉህ ብሎት ለምግብ ማወራረጃ ቢራ ለማዘዝ ከተቀመጠበት ወንበር ላይ አንገቱን ዞር አደረገ፡፡ ከአንድ መልከ መልካም ህንዳዊ ከምትመስል ቆንጆ ሴት ልጅ ጋር አይኖቹ ተጋጨ፡፡
"ማነሽ እህት ቢራ ታዘዥን" አላት፡፡
"እኔ እኮ ቢራ ጠጥቼ አላውቅም፡፡ ያሰክረኛል ፣ አልጠጣም፡፡ ለራስህ እዘዝ ፤ ለእኔ ጠጅ የለመድሁት ይሻለኛል፡፡ አለ ፤ ተመስገን፡፡
"አይ! ተመስገን ትገርማለህ ፤ እኔ እኮ ብዙ የምታቅ ትመስለኝ ነበር፡፡ ለካስ ምንም አታውቅም፡፡ ጠጅ እኮ እንደዚህ ያለ ሆቴል ውስጥ አይሸጥም፡፡ አለማወቅህ ነው እንጅ ከጠጁ ቢራው ነው የሚሻለው፡፡ ባይሆን አንድ ጠጥተህ ትተወዋለህ፡፡ ብሎት ቢራ እንዲጠጣ አሳመነው፡፡
"ምን አይነት ቢራ ልታዘዛችሁ አለች፡፡ የተጠራችው መልከ መልካም የህንድ ቆንጆ የምትመስል አስተናጋጅ፡፡
"በእናንተ አገር መጀመሪያ ሰላምታ አይፈቀድም እንዴ"? አላት ያሬድ፡፡
"ኧረ ! ይባላል፡፡ እሽ ይቅርታ ብላ የእጅ ሰላምታ ሰጠቻቸው፡፡ ለዛ ያለው ፈገግታዋ በታከለበት፡፡
"ስምሽ ማን ይባላል"? አላት ያሬድ፡፡ እጁን ከእጇ ሳያላቅቅ፡፡
"የሽሃረግ እባላለሁ" ፡፡
"እሽ አመሰግናለሁ ብሏት የራሱን ስም ሳይነግራት ሁለት ሐረር ቢራ አምጭልን አላት፡፡
የሽሃረግ አስተናጋጅ አይደለችም፡፡ አስተናጋጅዋ ወደ ሱቅ ወታለች፡፡ እስከ ምትመለስ ግን ወደ ሆቴሉ የሚገቡትን ተስተናጋጆች ታስተናግዳለች፡፡
ታዲያ የሆቴሉ አረንጓዴ ፣ ቢጫ ፣ ቀይና ሐምራዊ የተቀላቀለ በሚመስለው ዲም ላይት ውስጥ ሽር ሽር እያለች ስታስተናግድ አትኩሮ ለተመለከታት ፤ የቀሚስ አለባበሷ ፤ ኢትዮጵያዊነቷን ያለቀቀ ሆኖ በሰው እጅ የተሰራ ሳይሆን ከለግላጋ ሰውነቷ ጋር አምላክ አብሮ የፈጠረው ይመስል ነበር፡፡
ተመስገን የሽሃረግ እጁን ከጨበጠችው በኋላ፤ ከባንኮኒው ስትወጣና ስትገባ አብሯት በአይኖቹ ይመላለሳል፡፡
"ሊያመኝ ነው መሰለኝ"? ፡፡
"ጠጣበት ይለቅሃል፡፡ ዘና በል ደግሞ እንደ ልጅ አገረድ አትሽኮርመም"፡፡ "ምነው ደግሞ አይንህን በልጅቷ ላይ የምታንጃብበው"? አለው ያሬድ፡፡
"ኧረ ! አላንጃበብኩም፡፡ ግን ጓደኛዋ የወንድ ሱሪ ነው ያጠለቀችው፡፡ እሷ ደግሞ እንዴው ሳያት አለባበሷ አገረኛውን አለቀቀም፡፡ ታምራለች" ፡፡
"የቤት ልጅ ሆና ይሆናል፡፡ አለ ፤ ያሬድ፡፡
ያሬድ የአልባሳት ንግድ ከጀመረ ብቻ ሳይሆን በፊትም ከእናት አባቱ ቤት እያለ ስለከተማ ሴቶች አንዳንድ ነገሮችን ያውቃል፡፡ ለከተማ አዲስ አይደለም፡፡
ተመስገን አንድ ቢራ ያሰክረኛል ብሎ እየፈራ ቢጠጣውም አንድ ቢራ ግን አላሰከረውም፡፡ ለመድገም ፈልጓል፡፡
"ለካ ቢራ እንደዚህ ይጣፍጣል እንዴ"? አለ፡፡ ከጠርሙሱ ውስጥ የቀረውን እየጨለጠ፡፡
ቢራ እንግዴህ አንድ አይጠጣም፡፡ ከሰከርክም ከአሁን በኋላ ፤ ስለማንቀሳቀስ መቼም መኝታችን ድረስ ገብተን መተኛት አያቅተንም፡፡ ብሎት ቢራ ሊደግሙ የሽሃረግን ጠራት፡፡
የሽሃረግ ደግሞ አስተናጋጇን መቅደስን ጠርታ እዛጋ እየጠሩሽ ነው፡፡ ታዘዣቸው አለች፡፡
መቅደስ "ቢራ ይደገም"? አለች፡፡
ድገሚን ሳይላት "የሽሃረግ አታስተናግድም እንዴ"? አላት ያሬድ፡፡
"እሷ ብዙም አታስተናግድም፡፡ ሂሳብ ነው የምትቀበለው፡፡ የማስተናግደው እኔ ነኝ ፡፡
"እሽ ሁለት ሐረር ድገሚን" ፡፡
ተመስገን የጥላሁን ገሰሰ "ያቺ ቆንጆ ጥርሰ በረዶናት ፤ ውብ አይናማ ናት፡፡ የሚለውን ቀዝቀዝ ያለ ዜማ ልቡን ወሰድ አድርጎታል፡፡ አይኖቹን በየሽሃረግ ላይ ማንከራተቱን አላቋረጠም፡

"አሁን ከቅድሙ ድብርቱ ለቀቅ አላደረገህም ?
ካለቀቀህ ቢራውን ደጋግምበት፡፡ አልያም ሐገረኛ ሙዚቃ አስከፍተን እንጨፍራለን" አለ ፤ ያሬድ፡፡ የያዘውን ቢራ ጎንጨት እያደረገ፡፡ አንዳንድ ቢራ አልበቃቸውም፡፡ አራት አራቱን ቆነደዱት፡፡ ተመስገን ሞቅ እያለው መጣ፡፡
ያሬድ አገረኛ ሙዚቃ የለም እንዴ? አለ ፤ ለመቅደስ፡፡
"ልቀይርላችሁ"? ፡፡
"አዎ፤ በዚያውም ቢራ ይዘሽልን ነይ" ፡፡
አገረኛው ሙዚቃ ተከፈተ፡፡ ተነስተው ግን አልጨፈሩም፡፡ በተቀመጡበት አንገታቸውን ያወዛውዛሉ፡፡ የጠጣው ሐረር ቢራ መንፈሱን ሰረቅ አድርጎታል፡፡"ያች ኮረዳ ዝምብላ ታየኛለች" አለ ተመስገን፡፡ የራሱ አትኩሮ ማየት ሳይታወቀው፡፡
"የቷ ኮረዳ"? ፡፡
"ያቺ እዛ ውስጥ ተቀምጣ አንገቷን ብቻ የምትታየው፡፡ ስሟ ማን ነበር ያለችው"?
"የሽሃረግን ነው የምትለው"?፡፡
"አዎ፤ ትክክል ነህ፡፡ ቅድም እኮ ስትጠራት ሰምቼ አሁን አፌ ላይ ጠፍቶብኝ ነው፡፡
"የፈለግሃት ትመስላለህ፡፡ ለማንኛውም የሽሃረግን ለማግኘት መቅደስን መጥራት አለብን፡፡ በእጁ አጨብጭቦ መቅደስን ጠራት፡፡
"ልድገማችሁ" ብላ ጠየቀች መቅደስ፡፡ ቢራ ፈልገው መስሏት፡፡
"ቢራ እንኳን አልጨረስንም፡፡ ለየሽሃረግ አንድ ቢራ
ስጫት" አለ ፤ ያሬድ፡፡
ቢራ ጠጥታ አታውቅም፡፡ ለስላሳ ከሆነ ነው እንጅ ፡፡
"እሽ ፤ ስጫት" ፡:
መቅደስ የታዘዘችውን ለስላሳ ከፊሪጅ አውጥታ ሰጠቻት፡፡
ማነው ያዘዘሽ ; አለቻት የሽሃረግ?፡፡
"እዛጋ የተቀመጡት ሁለት ሰዎች ናቸው የጋበዙሽ፡፡ ብላ እነ ያሬድን በእጇ አመለከተቻት፡፡ ደግሞ ስምሽን ያውቁታል፡፡ ከአሁን በፊት ትተዋወቃላችሁ እንዴ?
"ኧረ ! ካለ ዛሬ አላየኋቸውም፡፡ ቅድም ነው ሱቅ ሄደሽ ሳስተናግዳቸው ስምሽ ማነው ሲሉኝ የነገርኳቸው" አለች፡፡ በዲም ላይቱ ፈገግታ ተመስገንን በስርቆት እየተመለከተች፡፡

👍47❤9
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች
፡
፡
#ክፍል_አስር
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================
አላዛር በግንባታ ሰሎሜ ደግሞ በአካውንቲንግ በሌቭል 3 ከተመረቁ ወራቷች ተቆጠሩ፡፡ ሰሎሜ ስራ ለመቀጠር መባከን ብትጀምርም አላዛር ግን ለመቀጠር ሙከራ አላደረገም፡፡ቀጥታ ስራውን ነው አስፋፍቶ የቀጠለበት፡፡
ከምረቃው ከሶስት ወር በኃላ ሰፈራቸው በኮሪደር ልማት ምክንያት እንደሚነሳ ተነገራቸው ፡፡በአንድ ወር ውስጥ ኮዬ ፈጬ ኮንደሚኒዬም ምትክ ቤት ተሰጣቸውና ወደእዛው እንዲዘዋወሩ ተደረገ፡፡ለሁለቱም ቤተሰቦች የተሰጣቸው ቤት አንድ ህንፃ ላይ ከመሆኑም በላይ አንድ ፍሎር ላይ ነው፡፡ሰሎሜና እናቷ ይሄ አጋጣሚ በመፈጠሩ ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ነው የተሰማቸው፡፡ የሚኖሩበት ቤት በየወሩ ኪራይ የሚከፈልበት የቀበሌ ቤት ቢሆንም ግን ደግሞ በተለይ ሰሎሜ እድሜ ልኳን የኖረችበት ሙሉ ትዝታዋ ያለበት.. የሳቀችበት.. ያለቀሰችበት የታመመችበት የዳነችበት የህይወቷን ጠቅላላ ታሪክ ተፅፎ የታተመበት ቤት በመሆኑ ስሜቷን ድፍርስርስ ነው ያደረገባት… ቢሆንም ግን አሁን በምትክ የተሰጣቸው ቤት የተሻለ ጥራት ያለው በመሆኑ እንደማካካሻ ቆጥራ በፀጋ ተቀበለችው፡፡
ለአላዛር ግን ልክ እንደሎተሪ ነው የቆጠረው፡፡ግድ ሆኖበት እንጂ ያንን ተወልዶ ያደገበትን ቤት አይወደውም..ከዛ ቤት ጋር በተያያዘ ካለው አስደሳች ትዝታ በእጥፍ ሀዘኑና ቁጭቱ ይበዛል፡፡በተለይ ቀጥታ አባቱን ስለሚያስታውሰው ሁሌ እንደቀፈፈውና የመቃብር ቤት አይነት ስሜት እንዲሰማው እንዳደረገው ነው፡፡እንደውም ከእዚህ ቤት ለመገላገል ሲል የራሱን የሆነ ቤት ለመግዛት የተለየ የባንክ ደብተር ከፍቶ ብር ማጠራቀም ከጀመረ አመት አልፏታል …፡፡ስለሆነም ዜናውን በደስታ ነው የተቀበለው፡፡ከዛ ቀጥታ ያደረገው የሱቅ ስራውን ላለማቋረጥ እዛው አካባቢ ሌላ ሱቅ በመከራየት እቃውን ወደእዛ ማዘዋወረና እቤቱን በደስታ አስረክቦ ወደኮዬ ፈጬ ጠቅልሎ ገባ፡፡በጣም አሪፉ አጋጣሚ ደግሞ በዛው ሰሞን በጣም የሚወዱት አያትዬው ህይወታቸው ስላለፉ ከበፊት ጀምሮ የልጅ ልጃቸውን ጥረቱና ትጋቱን ያዩ ስለነበረ ጠቀም ያለ የውርስ ገንዘብ ትተውለት ሞቱ ፡፡ከዛ ደረጃ 6 የኮንትራክተርነት ፍቃድ አወጣና የግንባታውን ዘርፍ ተቀላቀለ፡፡
///
ወደኮዬፌጬ ተዘዋውረው መኖር ከጀመሩ ከሁለት ወር በኃላ ነው፡፡
ስራ ውሎ ድክም ብሎት ወደ እቤት ገብቶ ሶፋው ላይ ጋደም እንዳለ በሩ ተቆረቆረ…በቅልጥፋና ሄዶ ከፈተው..እንደገመተው ሰሎሜ ነበረች፡፡
‹‹ግቢ›› አላትና በራፉን ክፍት ትቶላት ወደ ውስጥ ተመለሰና ሶፋው ላይ ተቀመጠ፡፡
በራፉን ዘጋችና ወደውስጥ ዘልቃ ዘላ ሶፋው ላይ በመውጣት ከጎኑ ተወሸቀች፡፡
ስሩ በመቀመጧ እና ሰውነቷ ከሰውነቱ በመነካካቱ በውስጡ እርካታ እየተሰማው በአንደበቱ ግን
‹‹ካልጠፋ ሶፋ ለምን ታጨናንቂኛለሽ?››አላት ፡፡
እንደማኩረፍ ብላ‹‹ጉረኛ ..አግኝተህ ነው?››አለችው ፡፡
‹‹አረ ባክሽ….?ለመሆኑ እንዲህ በተለየ ሁኔታ እየተፍለቀለቅሽ ያለሽው በምን ምክንያት ነው?››
‹‹ውይ በእቴቴ ሞት ያስታውቅብኛል እንዴ?››
‹‹በደንብ ነዋ…አንቺ እኮ ነሽ… ደስታሽም ሆነ ሀዘንሽ በግልፅ ነው ፊትሽ ላይ የሚፃፈው…ለመሆኑ ምን ተገኘ…?ብቻ ስራ አገኘሁ እንዳትይኝ?››
‹‹አንተ ደግሞ…እንዴት ብዬ ነው ስራ ማገኘው…ያው እዛው ካፌ እየሰራሁ ነው፡፡››
‹‹እና ምንድነው?››
‹‹ፍቅር ያዘኝ››
‹‹ምን?›› ብሎ በመደንገጥ ከጉልበቱ ላይ አሽቀንጥሮ አስነሳትና እግሮቹን ከሶፋው አውርዶ ቁጭ ብሎ አፈጠጠባት፡፡
አደነጋገጡ አስደነገጣት‹‹እንዴ ምን ያልኩህ መስሎህ ነው….?ፍቅር ያዘኝ እኮ ነው ያልኩህ››
‹‹ሰማሁሽ እኮ!!››
‹‹አይ አልሰማኸኝም.ኤሌክትሪክ ያዘኝ እንዳልኩህ እኮ ነው አደነጋገጥህ?››
‹‹እንዴ ምን ነካሽ? ኤሌክትሪክ ቢይዝሽ ይሻላል …አሁን ኤሌክትሪክ ቢይዝሽ ቆጣሪው አውቶማቲክ ስለሆነ ቶሎ ያጠፋል… ለጊዜው ተንዘርዝረሽ ወዲያው ታገግሚያለሽ…ፍቅር ግን ለዛውም በዚህ እድሜሽ!!››
‹‹በዚህ እድሜሽ….!ምን ለማለት ነው?››
‹‹ምን አስቸኮለሽ ለማለት ነዋ››
‹‹ሰውዬ..ስንት አመቴ ነው ታውቃለህ?››
‹‹እኔ እንጃ …ሀያ መሰለኝ››
‹‹አይደለም ሀያ ሶስት….ከእናንተ ጓደኛ ተብዬዎች ጋር ስንዘላዘል ተላልፎብኛል…››
‹‹እሺ ለመሆኑ አውቀዋለሁ….ማነው?››
‹‹ታውቀዋለህ….እስራኤል ነው››
‹‹እስራኤል …እስራኤል?››
‹‹ኮሌጅ እያለን አስተማሪያችን የነበረ፡፡››
‹‹እ እሱ ነው››አለ ቀዝቀዝ ብሎ ፡፡ተማሪ እያሉም አይኑን ይጥልባት እንደነበረ ታዝቧል…አሁን ኮሌጁን ሙሉ በሙሉ ለቀው ከተለዩ በኃላ በየት ዞረው እንደተገናኙ ምንም ሊገባው አልቻለም…፡፡
‹‹እና ምን ትላለህ?››
‹‹ምንም…በዚህ ዘመን አስተማሪ ማግባት ግን ጥሩ ነው?››አላት፡፡ይህን ያላት አስቦበት ሳይሆን ድንገት የሆነ ነገር ብሎ ጉዳዩን መቃወም ስላለበት ነው አፉ ላይ የመጣለትን የተናገረው፡፡
‹‹ምን ለማለት ነው ..?አስተማሪ ሰው አይደለም እንዴ…?.ደግሞ አፈቀርኩት አልኩህ እንጂ ላገባው ነው አልኩህ እንዴ?፡፡››
‹‹ያው ነው..ዛሬ ካፈቀርሺው ነገ ላግባው ማለትሽ ይቀራል?››
‹‹እና ብልስ ምን ችግር አለው?››
‹‹አይ ምንም ችግር የለውም..ከነጭ ድህነት ወደ ጥቁር ድህነት መሸጋገር ነው የሚሆንብሽ ብዬ ነው፡፡››
‹‹ብሽቅ የሆንክ ነገር ነህ፡፡ሰው ሁሉ አንደአንተ ብራም መሆን አለበት…?ፍቅር ደግሞ በገንዘብ አይገዛም››
‹‹ባክሽ እሱ ጊዜ ያለፈበት የድሮ አባባል ነው..በዚህ ዘመን ፍቅር ድብን አድርጎ በገንዘብ ይገዛል..እናም ደግሞ ድህነት የነበረን ፍቅር አባሮ ከልብ ያስወጣል፡››
‹‹እሱ ያንተ እምነት ነው..ለማንኛውም አፍቅሬዋለው.. ስላፈቀርኩትም በጣም ተደስቼለሁ..ደግሞ እኮ አንተም በእኔ መደሰት በጣም የምትደሰት መስሎኝ ነበር ዜናውን ላበስርህ እየበረርኩ የመጣሁት፡፡››አለችው በቅሬታ፡፡
..አፍቅሬዋለሁ እያለች ስታወራ ፊቷ ላይ ያለው ብርሀን ልዩ ነው፡፡‹‹ምን አለ እኔን አፍቅረሽ አብረን እንዲህ በደስታ ብናብረቀርቅ››ሲል በውስጡ አጉረመረመ፡፡እና እንደምንም እራሱን አረጋጋና ለእሷ ንግግር መልስ ይሰጥ ጀመረ‹‹ደስታሽ እንደሚያስደስተኝ አንቺም ታውቂያለሽ…ግን ደግሞ ለአንቺ የምመኝልሽ ዘላቂ ደስታ ነው…ዛሬ ለሳቅሽ ምክንያት የሆነ ነገር ነገ ሀዘን ላይ እንዲጥልሽ ለአልፈልግም….ለዛ ነው ሁሉን ነገር በጥንቀቃቄ እና በእርጋታ እንድትይዥው የምፈልገው፡፡››
እሷም ለስለስ አለችና ‹‹ለእኔ አስበህ እንደሆነ እኮ አውቃለው…ግን አታስብ እጠነቀቃለሁ…በል አሁን ቤት ስራ አለብኝ..እቴቴ ሳትጠራኝ ልሂድ››አለችና ከተቀመጠችበት ተነስታ ጉንጩን ስማ ወደውጭ መራመድ ጀመረች…፡፡
አይኖቹ አብረዋት ተንከራተቱ….፡፡በሰማው መርዶ የዛለ ሰውነቱን እንደምንም ጎትቶ ከተቀመጠበት ተነሳና በራፉን ከውስጥ ቀርቅሮ ወደቦታው ተመለሰ፡፡30 ለሚሆኑ ደቂቃዎች በድንዛዜ አሰበ….ከዛ የሆነ ነገር አድርጎ ይሄንን ጉዳይ ማኮላሸት እንዳለበት ድምዳሜ ላይ ደረሰና .ስልኩን አነሳ፡፡ አንዳንድ ጉዳዬችን የሚያስፈፅምለት ልጅ ጋር ደወለ ስልኩ ተነሳ‹‹‹እንዴት ነህ…ከመሸ ደወልኩ ይቅርታ››
‹‹ሰላም ነኝ አላዛር ….ችግር የለውም….ምን ልታዘዝ?››
‹‹ለአንተ የሚሆን አንድ ስራ ነበረኝ፡፡››
‹‹ምንድነው?››

👍52❤11👎1
#አላገባህም
፡
፡
#ክፍል_አስር
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
///
ፀደይ በንጋትገና ወፎች መንጫጫት ሲጀምሩ አንድም ኮሽታ ሳታሰማ በፀጥታ ከስሩ ሾልካ ወጣች፡፡ ሰውነቷ ደንጋይ ሲፈልጥ እንዳደረ ሰው ውልቅልቅ ብሏል።ክፍሉ በወሲብ ጠረን ታውዷል…ትናንት ማታ ወደ አንበሳው ጉድጓድ ውስጥ ሰተት ብላ ነበር በፍቃዷ የገባችው..እሱም ቆረጣጥሞ እና ቀረጣጥፎ በልቷታል፤ግን ደግሞ አድቅቋ አላጠፋትም….የማታው ታሪክ ወሲብ ብቻ ነበር - ደስ የሚል ጣፋጭ ወሲብ ። ሌሊቱን ሙሉ እንደዛ እራሷን ስታ እቅፉ ውስጥ ማሳለፍ አልነበረባትም። ለመራቅ የወሰነችው ይህ አይነት ቅርርብ ነበር።አንዳቸው ለሌላቸው ምንም ቃል አልገቡም፣ ። ስሟን እንኳን የማስታወስ እድሉ እስከ መቼ እንደሚቆይ እርግጠኛ አይደለችም? ‹ደግሞም አንድ ሰው ብዙ ልምምድ ካላደረገ በቀር እንዲህ ዓይነት ፍቅር መጠለፍ ውስጥ አይገባም› ስትል አሰበች።ከአልጋዋ ሾልካ ወጣች።ወለሉ መሀከል በባዶ እግሯ ምንጣፍ ላይ እርቃኗን ቆመች… .. አልጋው ላይ ተዘርሮ የሰላም እንቅልፍ የተኛውን ዘሚካኤልን አየችው፡፡ሰውነቷን ሙቀት ተሰማት፡፡አሁንም ቀስቅሳው ሰውነቷን ከሰውነቱ አጣብቃ ሌላ የሚያስጨነቅና የሚያቃት ወሲብ ብትሰራ ደስ ይላት ነበር…አዎ ቢያንስ አንድ የመጨረሻ የስሜት ጡዘትና ፍንዳታ የማስተናገድ እንጥፍጣፊ ጉልበትና ፍላጎት አታጣም፡፡ግን ራሷን ማቀብ አለባት.‹.በጣም ጣፋጭና የሚጥም ነገርን ከመጠን በላይ መጠቀም ለተውከት ይዳርጋል….፡፡›አለችና ቀጥታ ወደሻወር ሄደች ..ሙሉ እርቃን ሰውነቷን በሙሉ መስታወት ውስጥ ስታይ መደመም ውስጥ ገባች‹‹ፀዲ ግን የእውነት አንቺ ነሽ?››እራሷን በገረሜታ ጠየቀች….፡፡ትናንሽ ጡቷቾ ያለመደባቸውን ከመጠን በላይ ስለተጠቡና ስለታሹ ፍም መስለዋል፡፡ ከንፈሯም እንደዛው ሊፒስቲክ የተቀባች ይመስል ቀልተዋልም..በተወሰነ መጠንም የተንሻፈፈ እብጠት አብጠዋል፡፡ ሰውነቷ ላይ አልፎ አልፎ የተቧጨረ እና የቀላ ምልክት ይታያል.. ትናንት ወዲያ ለሰርጉ ዝግጅት ብላ ያን ሁሉ ብር ከስክሳ ለሳዕታት መከራ አይታ የተሰራችው ፀጉሯ አሁን እንዳይሆኑ ሆኖ እብዶች የጨፈሩበት የገለባ ክምር መስሏል፡፡
…እውነትም እንዳለው የሰውነቷ ቅርፃ በጣም ያምራል….እንደዚህ እርቃን ሰውነቷን ሙሉ መስታወት ፊት ቆማ አይታው አታውቅም…እና ብርቅ ሆኗባት ከፊትም ከኋላም እየተዟዟረች ተመለከተችው….በራሷ ተሰምቷት የማያውቀው በራስ የመታማመን ስሜት ተሰማት፡፡ ከስሞና ተኖ ነበር ብላ የምታስበው ሴትነቷ ከተበታተነበት እየተሰባሰበ በመገጣጣም ላይ ያለች መሰላት፡፡ሽንቷን ሸናችና ፊቷን ተጣጥባ ..ተመልሳ ወደክፍሉ ተመለሰች..ቀሚሷን አንስታ ለበሰች፡፡ ፊት ለፊት ባገኘችው የደረሰኝ ብጫቂ ወረቀት ላይ ማስታወሻ ፅፋላት…ቀስ ብላ ክፍሉን ለቃ ወጣች…፡፡በተቻለ መጠን በፍጥነት ከእሱ ለመራቅ ጓጓች።
ዛሬ አዲስአለም እና ሚካኤል የአዲስ አለም ቤተሰበች ጋር መልስ ተጠርተዋል..እና እዛ መልስ ላይ አብራቸው መሄድ ነበረባት…አሁን ባለችበት ሁኔታ ግን ያንን ማድረግ አትችልም፡፡ቀጥታ ወደቤቷ ሄዳ በራፏን ስትከፍት ገና ከጥዋቱ አንድ ሰዓት ከሩብ ነበር፡፡ ቤቷን ከፍታ ገባችና ቀጥታ ወደ ሻወር ቤት ነው የገባችው ..ቀጥታ የለበሰችውን ቀሚስ አውልቃ ጥላ ሰውነቷን ታጠበችና ቀጥታ ወደመኝታ ቤቷ ሄዳ የተለመደ አይነት አለባበሰዋን ጅንስ ሱሪ ከቲሸርት እና ከስኒከር ጫማ ጋር ለበሰችና የተወሰኑ ቅያሪ ልብሶችን በቦርሳዋ ከታ መልሳ ቤቱን ዘግታ ወጣች…፡፡ቀጥታ ወደ መነኸሪያ ነው የሄደችው፡፡አሁን ይሄን ከተማ ለቃ መሄድና እናቷን ጉያዋ ውስጥ ሆና የልጇን ጭንቅላት በማሻሸት በዚህ ሳምንት በተለይ ዛሬ ለሊት በህይወተዋ የገጠማትን ታአምራዊ ክስተት በስክነት ማሰብና ማጣጣም ትፈልጋለች፡፡ወደ ዶዶላ የሚወስዳት ባስ ውሰስጥ ገብታ ከተቀመጠች በኋላ ስልኳን አወጣችና ለአዲስ አለም መልዕክት ለመላክ መፃፍ ጀመረች፡፡
አዲስ አዝናለው…ጥሩ ስሜት እየተሰማኝ ስላልሆነ ወደእማዬ ጋር ሄጇለው…ከሶስት ቀን በኋላ ተመልሼ መጣለሁ….መልሱ ጋር አብሬችሁ ስላልሄድኩ ይቅርታ….ጥሩ ስሜት እየተሰማኝ ስላልሆን ብኖርም ሙዳችሁን ነው የማበላሸው…
በጣም ወድሻለው…ሚኪን ይቅርታ ጠይቂልኝ፡፡
ፅፋ ጨረሰችና ላከችው…ወዲያው ስልኳን ጠረቀመችው…ማንም ደውሎ እንዲጨቀጭቃት አትፈልግም፡፡አሁን አዲስአለም ደውላ..‹‹ምን ሆነሽ ነው..?አዳርሽ እንዴት ነበር?››ብትላት ምን ብላ ትመልስላታለች…አይ አሁን እንደዛ አይነት መዳረቅ ውስጥ መግባት አቅሙ የላትም…ደስታና ትካዜ..እርካታና ቁዘማ ብቻ ፅንፍ የያዙ ድብልቅልቅ ስሜቷች ናቸው እየተሰማት ያለው፡፡፡ የተሳፈረችበት ባስ ልክ እሷ የነበረችበትን ስሜት የተረዳ ይመስል የሚኪያን ዘፍን ከፈተና በከፍተኛ ድምፅ በተነው፡፡
መስሎኝ ነበር ድሮ፤ ፍቅር ገራገር/2/
አፌን ፈታው ገና… ስላንተ ስናገር
ምን ቀረህ ልበልህ ፤ፀጉሬንም ቆጥረሀል/2/
ታሪኬን ገልብጠህ …እንደአዲስ ፈጥረሀል
ይሄ ዘፈን በዚህ ልክ ገብቷት አያውቅም ነበር…አብራ ማንጎራር ጀመረች…
///
ዘሚካኤል ከመኝታው ከተነሳና ጥላው እንደሄደች ካወቀ በኃላ ልብሱን ለባብሶ ቀጥታ መኪናውን እያሽከረከረ ወደወንድሙ ቤት ነው የሄደው፡፡
መኪና ውስጥ ሆኖ የመኪናውን ክላክስ ከመጠና በላይ ሲያንባርቅው የነአዲስአለም ሰራተኛ መጥታ የውጩና በራፍ ከፈተችና ..‹‹ምንድነው..ማንን ፈልገው ነው?››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹አዲስአለምን ጥሪልኝ››
‹‹መኝታ ክፍል ውስጥ ነች ..አልተነሱም፡፡››
የትዕዛዝ ቃና ባለው ጠበቅ ያለ ቃል ‹‹አንኳኪና ቀስቅሻት››አላት፡፡
ልጅቷ እንደማቅማማት አለች‹‹ዘሚካኤል ይፈልግሻል በያት፡፡››
ዘሚካኤል የሚለውን ስም በመስማቷ በድንገት እንድትደነግጥ አደረጋት…ይሄ ስም ተደጋግሞ በቤቱ ውስጥ ሲጠራ ሰምታለች፡፡‹‹እሺ ይጠብቁኝ ››አለችና በራፉን ክፍት ጥላ ወደውስጥ ተመልሳ ሮጠች፡፡፡
ከደቂቃዎች በኃላ ሚካኤልና አዲስ አለም ከነቢጃማቸው ከኋላና ፊት ተከትለው መጡበት፡፡
ሚካኤል በራፉ ላይ ተገትሮ ሲቀር አዲስ አለም ወደዘሚካኤል ግዙፍ መኪና ተራመደች፡፡
ከድንጋጤና ግራ ከመጋባት ውስጥ ሳትወጣ‹‹ደህና አደርክ..?ምነው ..?ለምን ወደቤት አትገባም?፡፡››
‹‹አይ አልገባም..አንዴ ላናግርሽ ሰለፈለኩ ነው፡፡››
‹‹እሺ አናግረኝ…
‹‹መኪና ውስጥ ግቢያ››
‹‹ዞራ መኪና ውስጥ ስትገባ..ወንድሙን ዞር ብሎ ሳያየው መኪናውን አንቀሳቀሰና ወደፊት ነዳ‹‹እንዴ ምን እየሰራ ነው?››አዲስ አለም ጠየቀችው፡፡
‹‹ምነው ፈራሽ እንዴ?››
‹‹ምንድነው የምፈራው ..አለባባሴን አታይም እንዴ …?በቢጃማ እኳ ነኝ››
‹‹ብዙም አንርቅም….መልሼ አመጣሻለው..››አለና አንድ ኪሎ ሜትር ከሰፈሯ ከራቀ በኃላ መኪናዋን ከአስፓልቱ አውጥቶ ዳር አቆመና ሞተሩን አጥፈ፡፡
‹‹ምን ሆነሀል ?ምን ተፈጠረ?››
‹‹ጓደኛሽ?››
‹‹ማ ፀዲ››
‹‹አዎ…››
‹‹ጥሩ …..እኔም ስለእሷ ልጠይቅህ እፈልግ ነበር..፡፡ምን አደረካት…?እሷ ለእኛ ጓደኛችን ብቻ ሳትሆን ለሁለታችንም እንደእህታችን ነች..እንዴት ታስቀይማታለህ?››
‹‹ምነው? አስቀየመኝ አለቺሽ እንዴ?››
‹‹አረ በፍፅም የት አግኝቼያት..?ግን ድንገት ብን ብላ ከተማውን ለቃ ከሄደች የሆነ ነገር ሆናለች ማለት ነው››
‹‹ወደየት ነው ከተማውን ለቃ ሄደችው?፡፡››
‹‹ወደእናቷ ጋር፡››
‹‹በይ እንቺ ደውይላት››
‹‹ሞክሬ ነበር ስልኳ አይሰራም፡፡››
‹‹እና መሄዷን በምን አወቅሽ ››

👍71❤7🥰1
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ…
፡
፡
#ክፍል_አስር
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
///
ከሰዓት በኋላ ራሄል የፀጋን ጋሪ መኪናው ውስጥ አስገባች ። የዳይፐር ቦርሳውን ያዘች፣ሁሉንም ነገር እንዳላት ለማረጋገጥ ቦርሳውን ሁለቴ ፈትሸች፣ከዛ መኪናዋን ከወላጆቾ ጊቢ አንቀሳቀሰችና ነዳችው፡፡
ወደእንጦጦ ፓርኩ ነው የነዳችው፡፡ይህ ሀሳብ ድንገት ነው የመጣባት፡፡ እንደደረሰች መኪናዋን ፓርክ አደረገችና ..የጸጋን ጋሪ አወረደች…እሷን አነሳችና ጋሪው ላይ አስቀመጠቻት….አነስተኛ ሻንጣ አነሳችና በጀርባዋ አዘለች፡፡ከዛ ጋሪውን እየነዳች ወደፊት ቀጠለች… ስትራመድ የፓርኩ ፀጥታ፣የፀሀይ የሳሳ ሙቀት እና እርጥበት አዘል ንፋስ እና የዛፉ ቅጠሎች ሹክሹክታ በፅሞና እያዳመጠች ነው ።በርቀት ልጆችን ሲስቁ እና ሲሯሯጡ ይታያል። በቡድን የሚዝናኑ ሰዎች….ሳይክል የሚያበሩ ወጣቶች..ብዙ ብዙ ነገር እያየች ፀጋን ወደ ዳገቱ እየገፋች ወደፊ ቀጠለች ፡፡
‹‹ሄሎ፣ ሄሎ›› ፀጋን አላፊ አግዳሚው ሰላምታ እየሰጦት ያልፉ ጀመር...ራሄል መንገዱን በመከተል ደስተኛ ሆና በአእምሮዋ ብዙ ነገር እያሰላሰለች ቀጥላለች.. ዛሬ ጠዋት ከኬሩቤል ሞት በፊትም በውስጦ የነበሩትን አስደሳች የበረከት ስሜቶችን ቀስቅሶባታል ።
የሚገርመው፣ ቤተክርስቲያን ሆና የእግዚአብሔር ቃል ሲነገር መስማት፣ መዝሙር ሲዘመር አብራ መዘመር መቼም አደርገዋለው ብላ የምታስበው ጉዳይ አልነበረም ፡፡ ምናልባት ለእግዚአብሔር ሁለተኛ እድል ልትሰጥ ትፈልግ ይሆናል።
ራሄል ዳገቱን ጨርሳ ቁልቁለት እየወረደች ሳለ ድንገት ሳታስበው የፀጋ ጋሪ ከእጇ አሟልጮ አመለጣት …ጋሪው እህቷን ይዞ በራሱ ወደታች ተንደረደረ….ራሄል በድንጋጤ በድን ሆና ጮኸች… ጥቂት ሜትሮች ርቀት ላይ ባለው ሳሩ ውስጥ ምንም ጉዳት ሳይደርስባት ወደቀች ..ወደእሷ ስትንደረደር ቀድሟት አንድ ሰው ፀጋ ጋር ደርሶ ጋሪውና አቃንቶ አነሳና እሷን ከጋሪው አንስቶ አቀፋት…..‹‹ወይኔ በጌታ!!!›› አለች ራሄል…..ያስገረማት ፀጋ ሳትጎዳ መትረፏ ብቻ ሳይሆን ከሷ ቀድሞ የደረሰላት ደ/ር ኤልያስ ሆኖ መገኘቱ ነው፡፡‹‹ይሄ ሰውዬ ይከታተለኛል ማለት ነው…?እንደዛ ካልሆነማ እንደጠባቂ መልአክ በየሄድኩበት ሁሉ በድንገት አላገኘውም ነበር››ስትል አሰበች
በፈገግታ እንደተዋጠ‹‹አይዞሽ ..ምንም አልሆነችም››ሲል ሊያበረታታት ሞከረ፡፡
‹‹ቆይ እዚህ እንገናኝ ብዬ መልእክት ልኬልህ ነበር እንዴ ?።››ስትል ጠየቀችው
‹‹አዎ እንደዛ መሰለኝ..ምነው ስላገኘሺኝ ደበረሽ እንዴ?››
‹‹ለምን ይደብረኛል….ገርሞኝ እንጂ››
‹‹ላስገርምሽ ስለቻልኩ ደስ ብሎኛል››
ፀጋ እጆቿን እያጨበጨበች።‹‹ቤተክርስቲያን ሂድን››አለችው ፡፡
‹‹ቤተክርስቲያን?››ምን ለማለት እንደፈለገች አልገባውም፡፡
‹‹ወላጆቼ ሁል ጊዜ እሁድ እሁድ ቤተክርስቲያን ይዘዋት ይሄዱ ስለነበር ቅር እንዳይላት ብዬ ጥዋት ይዣት ሄድኩ…እሱን ልትነግርህ ፈልጋ ነው››ሥትል አብራራችለት ፡፡
‹‹እና እንዴት ነበር?››
‹‹በእውነቱ በጣም ጥሩ ነው.››
‹‹እሺ ..ወደሆነ ካፌ ሄደን አረፍ እንበል?የሆነ ነገር ልጋብዛችሁ?››አላት፡፡
‹‹አይ…. ለእኔ እና ለፀጋ መክሰስ አዘጋጅቼ ነበር… ቡና, ወተት እና ኩኪስ አለን.. ካፌ ከተማም ሰልችቶናል…የሆነ ለመብላት ጥሩና ጸጥ ያለ ምቹ ቦታ ፈልጌ ነበር.››
‹‹ከዚህ የአስር ደቂቃ የእግር መንገድ በአንዳንድ በዛፎች የተከበበ ወንበርና ጠረጴዛ ያለበት ቦታ አለ። ለፀጋም ቅርብ የሆነ የመጫወቻ ሜዳ አለ። ከፈለግሽ ላሳይሽ እችላለሁ።››
ራሄል የጠቀሰውን ቦታ ማግኘት ያን ያህል ከባድ እንደማይሆንባት ታውቃለች።አረ እንደውም የሚለው ቦታ በትክክል ትዝ ብሏታል፡፡ግን አብሯቸው እንዲሆን ፍላጎቷ ነው፡፡
‹‹ካላስቸገርንህ ደስ ይለኛል››አለችው፡፡
ችግር የለውም..ጥቂት ደቂቃ ስጡኝ ጓደኞቼን ተሰናብቼ ልምጣ አለና ወደኋላ ሄዶ አብረውት ከነበሩት ሶስት ጓደኞቹ ጋር በመሳሳቅ ጥቂት ቃላትን ከተለዋወጠ በኃላ ተመልሶ መጣና የፀጋን ጋሪ እየገፋ ወደተባለው ቦታ እየመራ ይወስዳቸው ጀመር፡፡
በአሁኑ ጊዜ ስለ ምንም ጥልቅ ነገር ማሰብ አልቻለም,ከእርሷ ጋር አብሮ ሄደ, ከዚህች ሴት አጠገብ ሲሆን ለራሱ ሐቀኛ እንዳይሆን ታደርገዋለች፡፡ብዙውን ጊዜ ከሴቶች ጋር መነጋገር ይከብደዋል ፣ ከፊቱ ላሉት የተወሰኑ አመታት ከሴት ራሱን ለማራቅ በተለይ ቆሚ የሆነ ግንኙነት ላለመመስረት ቁርጥ ያለ ውሰኔ ወስኖ ነበር።ለምን አሁን ራሄልን እንደሚያሳድዳት እርግጠኛ አይደለም። እሷ በተለምዶ የሚማረክባት አይነት ሴት አልነበረችም። ከመጀመርያው አንስቶ ለእሷ አሉታዊ አመለካከት ቢኖርም ፣ እሷ የሚያስደንቅ ጥንካሬ ባለቤት ሆና በሀሳቡ ውስጥ ተሰንቅራ መቆየት ችላለች ።
‹‹ስራ እንዴትነው..ማለቴ ፋውንዴሽኑ?››ሲል ጠየቃት
‹‹ጥሩ ነው…ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጥሬ ገንዘብ ፍሰት ላይ ችግር አጋጥሞናል.››
‹‹ ፋውንዴሽኑ ጥሩ ለጋሾች እንዳለው ከወላጆችሽ ተረድቼ ነበር እኮ።››
‹‹በአብዛኛዎቹ ጉዳዮች አዎ ትክክል ነው፣ ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ብዙ አዳዲስ በጎ አድራጎት ድርጅቶችን ገንዘብ እየጠየቁን ነው። እነዚህ ሁሉ መመርመር አለባቸው፣ ይህም ደግሞ ገንዘባቸውን ምን ላይ እንደዋለ ለማረጋገጥ ለሚፈልጉ ደንበኞችም የምናደርገው ነው። አጋጣሚ ሆኖ ደግሞ በሆነ እንግዳ ምክንያት ላለፉት ጥቂት ወራት የተወሰኑ ለጋሾችን አጥተናል።››ንግግሯን አቁማ የይቅርታ ፈገግታ ፈገግ አለችለት ።
‹‹ይቅርታ ስለ ፋውንዴሽኑ ሳወራ መጮህ እጀምራለሁ:››
‹‹አረ ችግር የለውም..አልጮኸሽም..ደግሞ ማወቅ ያለብሽ አንቺን ማዳመጥ ሁልጊዜ አስደሳች ነው።አንድ ሰው ስለ ሚወደው ነገር ሲናገር ሁል ጊዜ በጣም ስሜታዊ መሆኑ የሚጠበቅ ነው።››ሲላት ሳቀች።
‹‹ጓደኞቼ ከስራዬ ጋር እንደተጋባው አድርገው ያወራሉ። ፋውንዴሽኑ ለእኔ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ አይረዱም። እዚያ መስራቴ ለእኔ ረድቶኛል ከጥልቅ ሀዘኔም እንዳገግም ያገዘኝ ስራዬ ነው ።››ቀና ብላ ተመለከተችው፣ ዓይኖቿ በብርታት እያበሩ ለሥራው ያላትን ቁርጠኝነት አጥርቶ ያሳይ ነበር።
የተባለበት ቦታ ደርሰው ቆሙ፡፡
‹‹በቂ ቡና እና ተጨማሪ ስኒ አለኝ። ከእኛ ጋር ትቆያለህ አይደል?›› ስትል ጠየቀችው… ።ለአፍታ እርግጠኛ ያልሆነች የትምህርት ቤት ልጅ ትመስላለች። ይህም ለዔሊ ግብዣዋን እንዲቀበል በቂ ማበረታቻ ሰጥቶታል።ራሄል ፌርሙሱን እና ኩባያዎቹን ስታወጣ ትሁት ከእሱ አፈንግጣ ወደ መጫወቻ ሜዳ ሄደች።
ተመቻችተው ተቀመጡና ጫወታ ጀመሩ
‹‹ ለምን ሆስፒታሎችን ትጠያለሽ?››ሲል ያልጠበቀችውን ጥያቄ ጠየቃት፡፡
ራሄል ራሷን ነቀነቀች፣ ለአፍታ ያህል መልስ እንደማትሰጠው አሰበ። በኋላ ግን ጉልበቷን ወደ አገጯ ሳብ አድርጋ እጆቿን አነባብራ ማውራት ጀመረች።‹‹ከስምንት አመት በፊት በሆስፒታል ውስጥ ለአንድ ወር ከግማሽ አሳልፌያለሁ….ኪሩቤልን እግዚአብሔር እንዳገባው የፈቀደልኝ የልቤ ሰው መስሎኝ ነበር…አደጋው በደረሰበት ጊዜ እንደሚድን በማመን አልጋ አጠገብ ተቀምጬ ነበር። ለስድስት ሳምንታት ያህል እግዚያብሄር እንዲያድልንኝ ያለማቆረጥ ጸለይኩ። የሆስፒታል የመተንፈሻ መሳሪያ ድምፅ እንዴት እንደሆነ ጠንቅቄ ያወቅኩት በዛን ጊዜ ነው፣ የልብ መቆጣጠሪያውንም እንደዛው። ጸሎቴ ግን ለውጥ አላመጣም…››ድምጿ በመጨረሻው ቃል ላይ ደምቆ ተሰማ፣ እና ዔሊ ታሪኩ ወዴት እንደሚሄድ ተረዳ። በእሷ ላይ ያለውን

❤73👍5👏1
#ቋጠሮ_ሲፈታ
፡
፡
#ክፍል_አስር
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
///
አለም በረጅሙ ተነፈሰችና "እናቴ እዚህ አካበቢ ነው የተገደለችው አይደል?"
"ትክክል እዚህ ነው የሞተችው" ብሎ በቁጣ መለሰላ፡፡
"የት? የትኛው ጋጣ አካባቢ?"
ዝም አላት…
‹‹ኩማንደር ሬሳዋን የት እንዳገኘህ አሳየኝ” ስትል ተማፀነችው፡፡
በረድፍ ካሉት የፈረስ ጋጣዎች ሁለተኛ ጋጣ ላይ ወሰዳትና። "እዚህ ነው የሞተችው"ብሎ ነገራት፡፡
አለም ሙሉ በሙሉ ደንዝዛ ቆመች፣ ከዚያም ወደ ገመዶ እስክትቀርብ ድረስ በዝግታ ወደፊት ሄደች። ወደ ጋጣው ዞረች። በውስጡ ምንም ፈረስ ሆነ ድርቆሽ አልነበረም, ወለል የተሸፈነው በጎማ ብቻ ነው. በሩ ተወግዷል ..ክፍት ነበር"ያ አደጋ ከተፈጠረ ጀምሮ በዚህ ጋጣ ውስጥ ፈረስ ገብቶበት አያውቅም?።"ስትል ጠየቀችው፡፡
በንቀት፣ "ጋሽ ፍሰሀ ስሜታዊ ስለሆነ ይሄን ውሳኔ ወስኗል›› አላት።
አለም በደም የተጨማለቀ አስከሬን በጋጣው ውስጥ እንደተጋደመ በምናቧ አሰበችና ..ተንቀጠቀጠች፡፡ ጠያቂ አይኖቿን ወደ ገመዶ አነሳች።ቆዳው በጉንጩ አጥንቶቹ ላይ በደንብ የተለጠጠ ይመስላል፣ ፡፡
ወንጀሉን የተፈጸመበትን ቦታ መጎብኘት ያሰበችውን ያህል ቀላል አልነበረም።"ስለ ጉዳዩ በዝርዝር ንገረኝ እባክህ?››አለችው፡፡
እያመነታ፣
“በጎኗ ተኝታ ነበር፣ ጭንቅላቷ በዚያ ጥግ ላይ ነበር፣ እግሮቿ እዚህ ነበሩ” እያለ በዝርዝር አስረዳት፡፡ባደረገው ቦቲ ጫፍ አንድ ቦታ እየነካ፡፡" በደም ተሸፍና ነበር፤ፀጉሯ በደም ተነክሮ ነበር… በሁሉም ቦታ ላይ ደም ነበር."
"ስንት ሰአት ነበር?" ብላ ጠየቀች።
" ሳገኛት?"
‹‹አዎ››
"ንጋት ላይ ነበረ. 12 ሰዓት ከሰላሳ አካባቢ."
"በዚያ ቀን አንተ እዚህ ምን ታደርግ ነበር?"
"ብዙውን ጊዜ ወደቢሮ ከመሄዴ በፊት ወደእዚህ መጥቼ ፈረሶቼን አይቼና ምግብ እንደተሰጣቸው አረጋግጬ ነበር የምሄደው››
"ሌሊቱን ሙሉ ቤትህ ነበርክ ?"
"ተጨማሪ መልስ ከፈለግሽ ፣ ጉዳዩን ለፍርድ ቤት በኩል አቅርቢው።" "እንደዛ አቅጃለሁ."
ወደ ኃላዋ ዞረችና ወደፊት ተንቀሳቀሰች…ከኃላ ተጠጋት፣ ክንዷን ይዞ ወደ እሱ አስጠጋት። ከባድ እና ጠንካራ ወንድ ነው። "ወ.ሪት አለም" በብስጭት እና ትዕግስት በማጣት አጉረመረመ
"ብልህ ነሽ… ይህን ጉዳይ ተይው። ካላደረግሽው ግን አንድ አካል ሊጎዳ ይችላል።"
"ማለት?"
ሰውነቱን ወደ እሷ ይበልጥ አቀረበ።‹‹ ሴትን የመግደል አቅም ነበረው?›› ስትል እራሷን ጠየቀች…በአጠቃላይ ለሴቶች ዝቅተኛ አመለካከት ያለው ይመስላል፤ነገር ግን እንደ ጁኒየር ሁሉ እሱም ሰሎሜን ይወዳት ነበር. እሷም በአንድ ወቅት እሱን ማግባት ትፈልግ ነበር። ምናልባት ገመዶን ጨምሮ ሁሉም ሰው ሰሎሜ ጎበና የተባለ ሌላ ሰው አግብታ እሷን እስክትፀንስ ድረስ እንደሚጋቡ ያስብ ይሆናል።አለም ገመዶ በማንኛውም ሁኔታ ሰሎሜን ሊገድላት እንደሚችል ማመን አልፈለገችም፤ነገር ግን እሱ ጨካኝ፣ ትዕቢተኛ፣እንደሆነም መካድም አልቻለችም ። ገዳይ ግን?አይመስልም። ወይም እሷ ሁልጊዜም ለፈርጣማ ሰውነትና ጥቋቁር ሰርሳሪ አይኖቹ ላላቸው ወንዶች ደካማ ስሜት ስላላት ይሆናል።
‹‹እናቴን ማን እንደገደላት እና ለምን እንደገደላት እስካውቅ ድረስ ይህን ምርመራ የማቋረጥ ሀሳብ የለኝም። የእናቴን ገዳይ ለማወቅ ህይወቴን በሙሉ ጠብቄአለሁ። አሁን እዚህ ደርሼ ተስፋ አልቆርጥም"
አለም ከጋጣው በወጣችበት ደቂቃ ኩማንደሩ የእርግማን መአቱን አዥጎደጎደ ።ከቀናት በፊት በአቶ ፍሰሀ ከስራው የተባረረው ሙስጠፋ በአቅራቢያው በሚገኝ ጋጣ ውስጥ ተደብቆ የሚያወሩትን ሁሉ ሰምቷቸው ነበር። በቦታው የተገኘው በአጋጣሚ እንጂ ንግግራቸውን ለማዳመጥ አስቦ አልነበረም። ብቸኝነት ስለተሰማውና ግራ ስለተጋባ ነበር በጨለማ ውስጥ ጭብጥብጥ ብሎ ሲተክዝ የነበረው… ከስራ ስላባረረው የቀድሞ አሠሪው እያሰላሰለ እንዴት ቂሙን እንደሚወጣ ማሰብ ብቻ ነበር የሚፈልገው። አሁን ግን በአጋጣሚ ያላሰበውን የኩማንደሩን እና የአለምን ውይይት ቃል በቃል ሰምቷል፡፡ እና የሰማው ነገር ደግሞ ለእሱ ልክ ከሰማይ እንደወረደ መና ነው የቆጠረው ፣ እሷ በደንብ የሚያውቃት የሰሎሜ ሴት ልጅ መሆኗን አውቋል፣ እዚህ የተገኘችው የእናቷን ግድያ ለመመርመር እንደሆነ በመስማቱ ተደንቋል። አቶ ፍሰሀ ላይ በቀሉን ለመወጣት ወርቃማ እድል እንዳገኘ ተሰምቷታል እና ያ የማይረባ ልጁንም ደህና አድርጎ ያጠፋዋል። ወደ ሠላሳ ዓመታት ጉልበቱን አንጠፍጥፎ አገልግሎት ነበር።ደህና፣ በመጨረሻ እድል ለሙስጠፋ ፈገግ እንዳለችለት ገባው ፡፡እሱ በትክክል ካርዶቹን መጫወት ከቻለ በመጨረሻ የተወሰነ ገንዘብ ሊያገኝ እንደሚችል አሰበ፡፡ የአሁኑ አዲሷ ሚስቱ ገንዘብ ስለሌለው እያመነጫጨቀችው ነው…እንደውም ከቤቷ ገፍትራ ወደበረንዳ ልትጥለው ቋፍ ላይ እንደሆነች ተረድቷል….ታዲያ በዚህ ሚስጥር የሆነ ገንዘብ ማግኘት ከቻለ ሀሳቧን እንደሚያስቀይራት እርግጠኛ ነው፡፡
ኩማንደሩ ስራውን ጨርሶ ጋጣውን ለቆ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ በትዕግሥት ማጣት ባለበት ተወሽቆ ነበር ያሳለፈው።ሙስጠፋ ትኩስ ገለባ ውስጥ የተጠቀጠቀበት ጋጥ ከመውጣቱ በፊት በአካባቢው ሌላ ሰው እንደሌለ ለማረጋገጥ ብዙ ጊዜ ጠብቋል።ከዛ ቀጥታ በጥላ ከተሸፈነው ኮሪደር ወርዶ አካባቢውን ለቆ ወደከተማ ሔደና ሁለት መለኪያ አረቄ ጠጥቶ ራሱን ካበረታታ በኃላ ስልኳን ለማግኘት ምን ማድረግ እንዳለበት ማሰብ ጀመረ….ግን በከተማ ውስጥ እሷን የሚያውቁ ሰዎች በቁጥር ስለነበሩ ቀላል ስራ አልነበረም….እንምንም በሁለተኛው ቀን ማግኘት ቻለና በኤርገንዶ ስልኩ ደወለላት…፡፡ ከአምስት ጥሪ በኃላ ስልኩ ተነሳ፡፡
"ወ.ሪት አለም ነሽ?"
"አዎ ማን ልበል?"
"ማወቅ አያስፈልገሽም ..እኔ አውቅሻለሁ እና ያ በቂ ነው።"
ግራ መበጋባት‹‹አልገባኝም ?" አለችው፡፡
"ስለ እናትሽ ግድያ ሁሉንም አውቃለሁ።"
ሙስጠፋ በድንገት ዝምታ ውስጥ በመግባቷ እየተደሰተ ..እስክታገግም ጠበቃት፡፡ ለእሷ ሚያደነዝ አይነት ድብዳ ዜና ነው የሆነባት፡፡
‹‹እየሰማሁ ነው።››አለችው፡፡
‹‹አሁን ማውራት አልችልም.፡፡"
‹‹ለምን አይሆንም?"
‹‹ስለማልችል ነው ..ጉዳዩ አደገኛ መሆኑን የምታውቂ መሰለኝ።››
በስልክ ከእሷ ጋር ለመግባት አደገኛ እንደሆነ አስቦል… አንድ ሰው ሰምቷት ለአቶ ፍሰሀ ወይም ለኩማንደሩ ሹክ ሊላቸው ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋት አለው፡፡
‹‹መልሼ እደውልልሻለሁ።"አላት፡፡
‹‹ግን "
‹‹መልሼ እደውልልሻለሁ አልኩሽ እኮ…ስልኬን ጠብቂ…ደህና ሁኚ።››
ሙስጠፋ እሷ በምትገደልበት ጊዜ በቦታው ነበር.. እርሱ ጣልቃ ሳይገባ በተደበቀበት ሆኖ ሲመለከት ነበር ።ያንን ምሽት እንደ ትላንትናው የሆነውን ሁሉ ያስታወሰ። ይህን ሁሉ ጊዜ በሚስጥር ነበር ያያዘው። አሁን ግን የሚያወራበት ጊዜ መድረሱን አውቋል ። እናም ስለ ጉዳዩ ሁሉ ለዐቃቤት ሕጓ ለመናገር እስከ ሞት ድረስ ክፍያ ሊያስከፍለው እንደሚችል ያምናል…ግን ደግሞ ጥሩ ገንዘብም ሊያገኝበት የሚችልበት እድልም ሰፊ ነው፡።
/////

❤44👍5